ሰውዬው እቤቱ ሲገባ ባለቤቱ ያቀረበችለት ምግብ ምንም ሊጥመው አልቻለም፡፡ አንዳች ነገር ጎድሎታል፡፡ አሰበ አሰበና አገኘው፡፡ ቅቤ የለውም፡፡
«ምነው?» አለ፡፡
«ቅቤ አልቋል» ተባለ፡፡
የተዘረጋውን ማዕድ ትቶ ወጣና ወደ ጎረቤቱ ገባ፡፡
«አያ እገሌ ዛሬ ምን አግር ጣለህ» አለና ጎረቤቱ አባ ወራ ተቀበለው፡፡
«ባክህ አንዳች የሚበላ ነገር ካለ ብዬ ነው» አለ እንዳኮረፈ መሆኑን በሚያሳብቅ ድምፅ፡፡
«ውይ በሞትኩት» አለችና የጎረቤቱ ሚስት እንጀራውን በመሶብ ሞልታ ፊቱ ላይ አቀረበችለት፡፡ የምግብ አምሮቱ ተነቃነቀ፡፡
ወጡን በእንጀራ ሲያጠቅሰው ግን ያ መጣሁ መጣሁ ያለው አምሮት እልም ድርግም አለ፡፡ እዚህም ያለው ወጥ አንዳች ነገር ጎድሎታል፡፡
«ቤት ያፈራውን ብላ እንጂ ጨው አለቀ ብላ ብዙም አላደረገችበት፡፡ ለረሃብ ይሆንሃል ብላ» አለው አባ ወራው፡፡
አልቻለም፡፡ ነካክቶ ተወውና ተሰናብቶ ወጣ፡፡
ወደ ሦስተኛው ጎረቤቱ አመራ፡፡ የሦስተኛው ጎረቤት አባ ወራ ከጎጆው ውጭ መደብ ላይ ተቀምጦ አንዳች ነገር ይበላል፡፡
«አይዋ እገሌ እስቲ ጠጋ በል፡፡ እግርህ ርጥብ ነው» አለና አጎዛውን አስተካከለለት፡፡ ተቀመጠ፡፡ የጎረቤቱ ሴት ልጅ የጣት ውኃ ይዛ መጣች፡፡ ታጠበ እና ቀረበ፡፡
ጎረቤቱ እንጀራ በአዋዜ ነው የሚበላው፡፡
«እቴዋ ገበያ ሄዳ ወጥም አለተሠራ፤ ብላ ምንም አይልህም» አለው እንጀራውን ወደፊቱ እያደረገ፡፡ ጥቂት ቀማመሰና ተሰናብቶ ወጣ፡፡
«እንዴው የሚጣፍጥ ምግብ በሠፈሩ ሊጠፋ ነው» እያለ ወደ አራተኛው ጎረቤቱ ቤት አመራ፡፡ ማዕድ ቀርቦ ቤተሰቡ እየተመገበ ነው፡፡
«ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ መልሰኝ ማለት ይሄኔ ነው» አለችና እማወራዋ ተቀበለችው፡፡ አባወራውም ወንበር ለቀቀለት፡፡ እጁን ታጥቦ ቀረበ፡፡
«በርበሬ ስላላስፈጨን አልጫ ነው፡፡ ግን ይጣፍጣል ብላ» አለው አባወራው፡፡ በይሉኝታ ተመቻችቶ ቀረበ፡፡ እርሱ እቴ በርበሬ ለሌለው ወጥ መች ወስፋቱ ይከፈትለታል፡፡ ለምላሱ ሳይሆን ለሆዱ ቀመሰ፡፡ ጥቂት ተጫወተና ወጥቶ ወደ አምስተኛ ጎረቤቱ አመራ፡፡
አቦል ቡና ላይ ነበር የደረሰው፡፡ እማወራዋ ወደ ጓዳ ገብታ እንጀራውን አጠፈችና ፊቱ ላይ ዘረጋችው፡፡ ወጡ በሰታቴ ቀረበ፡፡ በምላሱ አጣጣመና ቅር አለው፡፡ አባወራው ገባውና «ምን እዚህ ቤትኮ ሽንኩርት የገባበት ወጥ ከተሠራ ቆየ፤ እኔም ይህንኑ ነው የበላሁት» አለው፡፡ እንዴው ለላንቲካው ጎራረሰ፡፡ እስከ ሁለተኛው ቡናውን ጠጣና ወጣ፡፡
እንዲህ እያለ መንደሩን ሁሉ ዞረው፡፡ አንዱ ቤት እንጀራው ይጠቁራል፤ አንዱ ቤት እንጀራው ይደርቃል፣ አንዱ ቤት ወጡ ያርራል፣ አንዱ ቤት ወጡ ይጎረናል፡፡ አንዱ ቤት ቅመም አይኖረውም፣ ሌላው ቤት በሚገባ አይበስልም፡፡ የተሟላ ማዕድ አላገኘም፡፡
መጨረሻ ላይ በጣም ወደሚቀርበው ጎረቤተሩም ወዳጁም ወደ ሆነ ሰው ቤት ገባ፡፡
«እኔ እዚህ ቤት የመጣሁት የሚጣፍጥ ነገር ፈልጌ ነው» አለ ዘና ብሎ፡፡
«ይጣፍጥ አይጣፍጥ እንጃ፤ የሚበላ ግን አይጠፋም» አለችና እማወራዋ አቀረበችለት፡፡ ምን የመሰለ ጥብስ፡፡ ምን ዋጋ አለው ታድያ ያለ መጥበሻ ቅጠል ነው የተጠበሰው፡፡ አዘነ፡፡ መርገምት ያለበትም መሰለው፡፡
ጠጋ አለ ወደ ወዳጁ፡፡ «አንተዋ፤ እኔ ከቤት የቀረበልኝን ጥዬ የወጣሁት የተሻለ አገኛለሁ ብዬ ነበር፡፡ ሁሉም ቤት ቀመስኩ፡፡ ሁሉም ቤት ጎደሎ አለ፡፡ ጨው ያለው ሽንኩርት፣ ሽንኩርት ያለው ጨው፣ ዘይት ያለው፣ ቅመም፣ ቅመም ያለው ዘይት፣ በርበሬ ያው ቅቤ፣ ቅቤ ያለው በርበሬ፣ እንጀራው ሲያምር ወጡ፣ ወጡ ሲያምር እንጀራው፣ አንዳች ነገር ይጎድላል፡፡
«እንዴው የተሟላ ነገር የት ነው የሚገኘው?» አለና አዋየው፡፡
«የትም» አለው ወዳጁ፡፡
«እንዴት እንዴት?»
«ሁላችንም ጎደሏችንን እናሟላለን እንጂ ሙሉ የት ይገኛል፡፡ ሁሉም ቤት ጎደሎ አለ፡፡ ልዩነቱ የጎደሎው ዓይነት ነው፡፡ አንተ ቤት የጠፋው እኔ ቤት፣ እኔም ቤት የጠፋው አንተ ቤት ይገኛል፡፡ ያ ማለት ግን ሙሉ ነው ማለት አይደለም፡፡
«ሰው ሁሉ ትዳሩን የሚያማርረው ይህንን ባለማወቁ ነው፡፡ እርሱ ቤት የጎደለውን እዚያኛው ቤት ሲያየው ያኛው ቤት የተሟላ ይመስለዋል፡፡ እዚያም ቤት እሳት አለ አሉ አለቃ ገብረ ሐና፡፡
«ታድያ ምን ያዋጣናል»
«የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡ ምሉዕ የሆነች ሚስት፣ ምሉዕ የሆነ ባል፣ ምሉዕ የሆነ ትዳር የት ይገኛል፡፡ ሁሉ እየተሟላ ይሄዳል እንጂ፡፡ ትዳር ማለት በጎደለው ነገር መጨቃጨቅ፣ መነዛነዝ፣ መጣላት እና መኳረፍ፣ መለያየት እና መፋታት አይደለም፡፡ ትዳር ማለት የሚጎድለውን እየሞሉ መቀጠል ማለት ነው፡፡ ሙሉ ባል ወይንም ሙሉ ሚስት የሉም፡፡ ሊሟሉ የሚችሉ ባል እና ሚስት ግን አሉ፡፡
«ቆይ ግን ሁላችንም እዚያ ማዶ ያለው ነገር የሚያምረን ለምንድን ነው?»
«እዚያ ማዶ ስናይ ጎደሎው ስለማይታየን ነዋ፤ የሚታየን ከኛ የሌለው እዚያ መኖሩን ነው፡፡ እስቲ እይ አንዳንድ ሰዎች ሌሎች ባለ ትዳሮች ቤት ደርሰው ሲመጡ የራሳቸውን ያማርራሉ፡፡ እነዚያ የተሻሉ መስለው ይሰማቸዋል፡፡ ባልም ሚስቱን ሚስትም ባልዋን እንደዚያኛው ቤት እንዲሆኑ ይመኛሉ፤ ይመክራሉ፡፡ እነዚያኞቹንም ብትሰማ ቸውኮ በነዚህኞቹ የሚቀኑ ናቸው፡፡ ወዳጄ ሁሉም የየራሱን ጎደሎ እያሰበ ያማርራል እንጂ ለመሙላት አያስብም፡፡
«ለመሆኑ አንተ ለምን ነበር ምግቡን ጥለህ የወጣኸው?»
«ቅቤ የለውማ»
«ቀላሉ መንገድኮ ቅቤ ገዝቶ የራስህን ወጥ ሙሉ ማድረግ ነበር፡፡ አንተ ግን ቅቤ ያለው ስትፈልግ ጨው የለለው መጣብህ፣ ጨው ያለው ስትፈልግ፣ ሽንኩርት ያነሰው መጣ፣ ሽንኩርት ያለው ስትፈልግ በርበሬ የሌለው መጣ፤ እንዲህ እንዲህ እያልክ ስትዞር ትኖራለህ እንጂ ያልጎደለው ወጥ የት ይገኛል፡፡
«ተመለስ ወዳጄ፣ ቅቤውን ግዛና ግባ፡፡ ያኔ የራስህ ጎደሎ ይሞላልሃል፡፡»
ጎረቤቱ ቀና ሲል፡፡ እንግዳው ሰውዬ ለቅቤ መግዣ የሚበቃ ገንዘብ መያዙን ለማረጋገጥ ብሩን እየቆጠረ ነበረ፡፡
Yerasin godolo sayawiku yesewin memelket tiru endalehone teredahu egiziabher yistih Dani
ReplyDelete"«ታድያ ምን ያዋጣናል»
ReplyDelete«የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡ ምሉዕ የሆነች ሚስት፣ ምሉዕ የሆነ ባል፣ ምሉዕ የሆነ ትዳር የት ይገኛል፡፡ ሁሉ እየተሟላ ይሄዳል እንጂ፡፡ ትዳር ማለት በጎደለው ነገር መጨቃጨቅ፣ መነዛነዝ፣ መጣላት እና መኳረፍ፣ መለያየት እና መፋታት አይደለም፡፡ ትዳር ማለት የሚጎድለውን እየሞሉ መቀጠል ማለት ነው፡፡ ሙሉ ባል ወይንም ሙሉ ሚስት የሉም፡፡ ሊሟሉ የሚችሉ ባል እና ሚስት ግን አሉ፡፡
«ቆይ ግን ሁላችንም እዚያ ማዶ ያለው ነገር የሚያምረን ለምንድን ነው?»"
Dn. Daniel kale hiwot yasemalin. Grum timhirt new. Egziabiher Yaqoyilin, Be-edime betsega Yitebiklin.
በእውነት ጥሩ ትምህርት ነው ዲያቆን እግዚአብሔር ይስጥልን::
ReplyDeleteegezeabeher yestelen.
ReplyDeleteegezeabeher yestelen teru meker new
denke new!!!«የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡ ምሉዕ የሆነች ሚስት፣ ምሉዕ የሆነ ባል፣ ምሉዕ የሆነ ትዳር የት ይገኛል፡፡ ሁሉ እየተሟላ ይሄዳል እንጂ፡፡ ትዳር ማለት በጎደለው ነገር መጨቃጨቅ፣ መነዛነዝ፣ መጣላት እና መኳረፍ፣ መለያየት እና መፋታት አይደለም፡፡ ትዳር ማለት የሚጎድለውን እየሞሉ መቀጠል ማለት ነው፡፡ ሙሉ ባል ወይንም ሙሉ ሚስት የሉም፡፡ ሊሟሉ የሚችሉ ባል እና ሚስት ግን አሉ፡፡
ReplyDeleteIt is very Nice Daniyewaye!!
ReplyDeleteእነዚያኞቹንም ብትሰማቸውኮ በነዚህኞቹ የሚቀኑ ናቸው፡፡
WoW, It is really touched, For the long time I felt this thing when I am looking my grilfriend. Eventually, in such kind of thought I couldn´t find my... specially in this month my big ambicious is becoming surrender himself to accept the reality. You wrote at this time and I took this as a conicidence.
ReplyDeleteየሃሳብን ጎዶሎ የምትሞላ ሸጋ ጽሁፍ! መምህር ዳኒ ህዝቡን ይመክርበት ዘንድ ስላሴ ብእርህን በመንፈሱ ቀለም ይሙላልህ!!!! ያምራል!!!!!!!
ReplyDeletegood expression you man
DeleteYigiremale betam tiru tsehufe nawu melkam
ReplyDeletedani silasitemakigne amasigenehalewu
Dani betam yamral kezihm yebelete endittsif Egziabher aeemrohin ena edmehin yibark.
ReplyDeleteGreat article Dani.
ReplyDeleteተመለስ ወዳጄ፣ ቅቤውን ግዛና ግባ፡፡ ያኔ የራስህ ጎደሎ ይሞላልሃል፡፡»
ReplyDeleteጎረቤቱ ቀና ሲል፡፡ እንግዳው ሰውዬ ለቅቤ መግዣ የሚበቃ ገንዘብ መያዙን ለማረጋገጥ ብሩን እየቆጠረ ነበረ፡፡Thanks Dane
Solomon Dejene
የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡
ReplyDelete«ሰው ሁሉ ትዳሩን የሚያማርረው ይህንን ባለማወቁ ነው፡፡ እርሱ ቤት የጎደለውን እዚያኛው ቤት ሲያየው ያኛው ቤት የተሟላ ይመስለዋል፡፡ እዚያም ቤት እሳት አለ አሉ አለቃ ገብረ ሐና፡፡
ReplyDeleteGood perception Dani.
One of your best pieces.Thanks Dani. KHY.
ReplyDeleteDn, Dani betam astemarInew Egziabher tibebun yadilih...
ReplyDeleteVery Nice Article! Keep on writing! Endante ayinet tsehafiwoch bibezu eko tiliku ye ethiopia chigir yifetal biye aminalehu i.e nikate hilinaw yedabare hibireteseb lemegenibat we need many Daniels. God Bless Ethiopia!
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteIt is a very nice intervention. There is no complete in human life. Everything has its own gap. The wise solution is attempting to fill the gap we have.
«ሁላችንም ጎደሏችንን እናሟላለን እንጂ ሙሉ የት ይገኛል፡፡ ሁሉም ቤት ጎደሎ አለ፡፡ ልዩነቱ የጎደሎው ዓይነት ነው፡፡ አንተ ቤት የጠፋው እኔ ቤት፣ እኔም ቤት የጠፋው አንተ ቤት ይገኛል፡፡ ያ ማለት ግን ሙሉ ነው ማለት አይደለም፡፡
«ሰው ሁሉ ትዳሩን የሚያማርረው ይህንን ባለማወቁ ነው፡፡ እርሱ ቤት የጎደለውን እዚያኛው ቤት ሲያየው ያኛው ቤት የተሟላ ይመስለዋል፡፡ እዚያም ቤት እሳት አለ አሉ አለቃ ገብረ ሐና፡፡
«ታድያ ምን ያዋጣናል»
«የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡ ምሉዕ የሆነች ሚስት፣ ምሉዕ የሆነ ባል፣ ምሉዕ የሆነ ትዳር የት ይገኛል፡፡ ሁሉ እየተሟላ ይሄዳል እንጂ፡፡ ትዳር ማለት በጎደለው ነገር መጨቃጨቅ፣ መነዛነዝ፣ መጣላት እና መኳረፍ፣ መለያየት እና መፋታት አይደለም፡፡ ትዳር ማለት የሚጎድለውን እየሞሉ መቀጠል ማለት ነው፡፡ ሙሉ ባል ወይንም ሙሉ ሚስት የሉም፡፡ ሊሟሉ የሚችሉ ባል እና ሚስት ግን አሉ፡፡
«ቆይ ግን ሁላችንም እዚያ ማዶ ያለው ነገር የሚያምረን ለምንድን ነው?»
«እዚያ ማዶ ስናይ ጎደሎው ስለማይታየን ነዋ፤ የሚታየን ከኛ የሌለው እዚያ መኖሩን ነው፡፡ እስቲ እይ አንዳንድ ሰዎች ሌሎች ባለ ትዳሮች ቤት ደርሰው ሲመጡ የራሳቸውን ያማርራሉ፡፡ እነዚያ የተሻሉ መስለው ይሰማቸዋል፡፡ ባልም ሚስቱን ሚስትም ባልዋን እንደዚያኛው ቤት እንዲሆኑ ይመኛሉ፤ ይመክራሉ፡፡ እነዚያኞቹንም ብትሰማ ቸውኮ በነዚህኞቹ የሚቀኑ ናቸው፡፡ ወዳጄ ሁሉም የየራሱን ጎደሎ እያሰበ ያማርራል እንጂ ለመሙላት አያስብም፡፡
good lesson! It is time to focus on what we have than what we are missing. we have 90% full but we look the 10% missing.
ReplyDeleteGod Bless You
D.Dani min endemilh alwkm yante tsihufwoch yehiwoten menged eyasitekakelugn new kelb amesegnhalehu. Hiwot bado honabignalech biye asbalehu bizu godolo neger endalegn yisemagnal gin silalegn silehonelign neger alasbm yante tsihufoachin saneb bizu neger yigeletilignal desitam yisemagnal. Medihanalem abzto yibarkh edme ena tena yisth.
ReplyDeleteIt is amazing article and it conveys a great message.
ReplyDeleteDani,thank u so much for your wonderful article
ቆይ ግን ሁላችንም እዚያ ማዶ ያለው ነገር የሚያምረን ለምንድን ነው?»
ReplyDelete«እዚያ ማዶ ስናይ ጎደሎው ስለማይታየን ነዋ፤ የሚታየን ከኛ የሌለው እዚያ መኖሩን ነው፡፡ እስቲ እይ አንዳንድ ሰዎች ሌሎች ባለ ትዳሮች ቤት ደርሰው ሲመጡ የራሳቸውን ያማርራሉ፡፡ እነዚያ የተሻሉ መስለው ይሰማቸዋል፡፡ ባልም ሚስቱን ሚስትም ባልዋን እንደዚያኛው ቤት እንዲሆኑ ይመኛሉ፤ ይመክራሉ፡፡ እነዚያኞቹንም ብትሰማ ቸውኮ በነዚህኞቹ የሚቀኑ ናቸው፡፡ ወዳጄ ሁሉም የየራሱን ጎደሎ እያሰበ ያማርራል እንጂ ለመሙላት አያስብም፡፡
dani tiru newu siletidar ymetesatawu aseteyayet betam dessi ylali
ReplyDelete"ሁሉም ቤት ጎደሎ አለ፡፡ልዩነቱ የጎደሎው ዓይነት ነው፡፡......የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡
ReplyDeleteasdenaki mekere new dani egziabeher tsegawen yebelete yabzaleh
የኔን ጸባይ ነው የነገርከኝ ምግብ ካልጣፈጠኝ ይሉኝታ ይዞኝ እንኳን መብላት እቸገራለሁ ከባለቤቴ ጋር ሁሌ ጭቅጭቅ በዚህ ነው፡፡ ሚስቶችም ለመስማት ለማስተካከል ይቸገራሉ የድሮ ሰዎች ምናልባት ጥሩ መድኃኒት ነበራቸው ተጨማሪ ሚስት ያገቡ ነበር በፉክክር እንዲንከባከቧቸው ምን ይመስልሃል ለሐዲስ ኪዳን የሚሆን ዘዴ ካለህ ጠቁመኝ
ReplyDeletepolygamy ! Wrong idea!
Deletethank you ; Eyemegebiken newu, betam begugt newu yemitebikewu yanten tsuhuf
ReplyDeletekale hiwut yasemalin
የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡
ReplyDeleteThank you Dani Betam des yelal
ReplyDeleteDani,
ReplyDeleteI appreciate the article. However, I believe that the final solution is highly simplified. In real life you cannot easily buy what you lack (the butter in this case) and make things complete. I understand that you should exert the maximum possible effort to make things complete by your own. Equivalently, we are also expected to learn to live only with what we posses at a point of time.
thank you my brother yes
Delete«ለመሆኑ አንተ ለምን ነበር ምግቡን ጥለህ የወጣኸው?»
ReplyDelete«ቅቤ የለውማ»
«ቀላሉ መንገድኮ ቅቤ ገዝቶ የራስህን ወጥ ሙሉ ማድረግ ነበር፡
Mamush,MN
It is interesting and has preaching power. Let God bless you Daniel.
ReplyDelete"ሁሉም ቤት ጎደሎ አለ፡ ልዩነቱ የጎደሎው ዓይነት ነው፡፡"
ReplyDeleteበአዲስ ኪዳን ሌላ ዘዴ ካለህ ላልከው
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል ሰፋ ያለ ምላሽ ሊሰጥበት ይችላል
ለአዲስ ኪዳን የሚሆነው ዘዴማ ሌላ የጣፈጠ ወጥ የምትሰራ ሚስት ማግባት አይደለም፡፡ ይህ እንኳን በአዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳንም ህገ ወጥ ነበርና ነብየ እግዚአብሔር ሙሴም የፈቀደላቸው ትክክል ስለሆነ ሳይሆን ስለልቦናቸው ጥንካሬ ብቻ ነበር፡፡ ለአዲስ ኪዳን የሚሆነው መፍትሔ ስለክርስቶስ ሁሉን መተው ነው፡፡ የፀኑትን ማሰብ ነው፡፡
ምግቡ አልጣፍጥ ያለህ ስላንተ ሲል የመረረ ሐሞት የተጎነጨውን የባህሪ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ስላላሰብክ ነው፡፡ በእውነት የክርስቶስን ነገረ መስቀል የሚያስብ እንኳን አልጣፈጠኝም ብሎ ሊማረር በጠቅላላው ምግብም ሊያቆም ይችላል፡፡ አባቶቻችን ለምንድነው ሬት ሲበሉ የማይሰቀቁት? አርብ አርብ ኮሶ የሚጠጡም አባቶች አሉ የሚገርመው ግን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ስለሆኑ አይመራቸውም፡፡
የጣመ የላመ መልመድ ደግሞ እንደ ባለታሪኩ ቀላዋጭ ብቻ ሳይሆን ሁል ጊዜም ተማራሪ ያደርጋል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም ይህንኑ ነው የሚመክረን፡፡
እስኪ ደግሞ ‹‹አሁንስ ሁል ጊዜ ሽሮ›› ብለው ትዳራቸውን ትተው ልጆቻቸውን በትነው በየስጋ ቤቱና በየድራፍት ቤቱ የሚጋፉትን እናስባቸው፡፡ እንዴት ምስኪኖች ናቸው?
እስኪ አንተስ አልጣፈጠኝም የምትለውን ምግብ አስበው፡፡ አልጣፍጥ አለኝ የምትለው እኮ ሆቴል ውስጥ ወይም ለተለየ ድግስ ከሚሰራው ምግብ ጋር እያወዳደርከው ይሆናል፡፡ የዚህ ምድር ክብር እኮ ሃላፊ ነው፡፡ ምናልባትም ሚስቶቻችንን እስከመፍታት የሚያደርሰን ጣፋጭ ምግብ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ ምንነት እንደሚለወጥ ማሰብ ጠቃሚነት ያለው ይመስለኛል፡፡ ይህን ጊዜ ጣፋጭ ብናገኝ እንበላለን ባናገኝ ደግሞ ያገኘነውን ተመስገን ብለን ጣፍጦን እንመገባለን፡፡
በጣም በጣም ደግሞ ምግቡን የሚያጣፍጠው በቤት ውስጥ ያለው ፍቅር ነው፡፡
በጣም ብዙ ዓይነት ምግቦች ቀርበው የማእድ ፀሎት ሳይሆን ጭቅጭቅና ንትርክ የሚቀድምባቸው ስንት ማዕዶች አሉ? ስለዚህ ምግቡን የሚያጣፍጠውም የማያጣፍጠውም የኛው ሕይወት ነው፡፡
ለማንኛውም ‹‹ ተግባራዊ ክርስትና ›› የምትለውን የዲ/ን ሄኖክን አዲስ መፅሐፍ እንድታነብ ጋብዤሃለሁ፡፡ ህዋሳቶቻችንን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብን ብዙ ግንዛቤ ታገኝበታለህ፡፡
ዓለምንና በዓለም ውስጥ ያሉትን የምንንቅበትን ጸጋ ያድለን አሜን፡፡
This is the second time that a blog platform on the subject of marriage was placed for discussion on Daniel's blog(unless I over sighted some.
DeleteI see so many people would like to express their views, ideas/thoughts and perception.
Dikon Daniel, I strongly suggest that you open a forum on christian marriage, way of living life under this divine union.
It may be a challenging task but in my view you are much better positioned to bring professional and expertise on board who could assist in creating an appropriate platform.
PLease so many family are breaking because of a wrong societal teachings/practice in marriage and lack of proper advice and guidance in solving problems in the union.
Antes bitil.
ReplyDeletethe article you raised is so nice and it should be raised in these days, really the answers of'Addis kidan' really perfect
ReplyDelete"...አንተዋ፤ እኔ ከቤት የቀረበልኝን ጥዬ የወጣሁት የተሻለ አገኛለሁ ብዬ ነበር፡፡ ሁሉም ቤት ቀመስኩ፡፡ ሁሉም ቤት ጎደሎ አለ፡፡ ..." ጥሩ አባባል ነው! እስቲ ለሁላችንም ማስተዋሉን አድሎ ወደ ቀናው መንገድ ይመልሰን::
ReplyDeleteIt is good advise for those who are married.It is also so good for those who do not married b/c it is warning what is life after married.
ReplyDeleteany way keep it up
የኔ አስተያየት ከየትኛውም ፅሁፍ ጋር የሚገናኝ አይደለም፣ ግን ምናልባት ካነበባችሁት እና ካሻሻላችሁት ብዬ ነው ያልሆነ ቦታ ገብቼ እንደዚህ ባልዘባረኩ ነበር.....1ኛ Should have contact tab 2ኛ፣ ስለፈለኩት ነገር አስተያየት ለመስጠት የሚያስችል comment box ቢኖር በመጨረሻ ይህን ሁሉ ያልኩበት ምክንያት (ማህበሩ ለራሱ ጥቅም ባንተ ፈቃድ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ ትምህርቶችህን እንደሚሸጡ አውቃለሁ ገዝቻለሁም)ስብከትህን ለራስህ ብር ማከማቻ ሌሎች እንደሚያደርጉት በሲዲ እና በቪሲዲ አለመቸብቸብህ ሲያስመሰግንህ ስብከትህን በቪሲዲ ወይ በኦዲዮ እዚሁ ብሎግህ ላይ የምናገኝበትን ሁኔታ ብታመቻችልኝ እና ቃለእግዜሩን ብሰማ የነፍሴ ደስታ ወሰን ባልነበራት ነበር....እባክህ...እባክ...እባክህ....አነጋገር አልችልበት ይሆናል ለዚህም ይቅርታ፡፡ ምላሽ‹ህን›ችሁን እና የአስተያየቱን ለውጥ በታላቅ ጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ liyuhosi@gmail.com
ReplyDeleteI found it as very much helpful in ones life. THank You!
ReplyDeleteGerum Timhirt new!! sew hulu yehen berda noro andun tito lela balfelge neber. Egeziabhar edemawen ketina gar yesetilne!!
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል፡ ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ ቁርስ በላሁና ወደ University of Southern California ቤተ መጻህፍት አመራሁ፡፡ ከመቀመጤ ይችን ምክር/ቁም ነገር አገኘሁ፡፡እግዚአብሔር ባንድም በሌላም መንገድ ይመክራል፤ ያስተምራል፡፡ “እኔ ራሴ የሆንኩትን ማን ሹክ አለው?” ብየ ራሴን ጠየኩ፤ ታላቅ ምክር አገኘሁበት፡፡ ረጅም የአገልግሎት ዘመን ልዑል እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡
ReplyDelete«የሚያዋጣንማ የየራሳችንን ጎደሎ ማሟላት ነው፡፡ ምሉዕ የሆነች ሚስት፣ ምሉዕ የሆነ ባል፣ ምሉዕ የሆነ ትዳር የት ይገኛል፡፡ ሁሉ እየተሟላ ይሄዳል እንጂ፡፡ ትዳር ማለት በጎደለው ነገር መጨቃጨቅ፣ መነዛነዝ፣ መጣላት እና መኳረፍ፣ መለያየት እና መፋታት አይደለም፡፡ ትዳር ማለት የሚጎድለውን እየሞሉ መቀጠል ማለት ነው፡፡ ሙሉ ባል ወይንም ሙሉ ሚስት የሉም፡፡ ሊሟሉ የሚችሉ ባል እና ሚስት ግን አሉ፡፡
ReplyDeleteKale Hiwot Yesemalin.
Endezih bastemarken kutr legna ena yelelochinim hiwot mekariwoch lemehon tru timihrt eyesetehen silehone yihinim asibibet.
TESFAHUN, PHOENIX, AZ
ምነው መምህር ጠፉ፡፡ ሙሉ ወጥ የሚገኝበትን እያፈላለጉ ይሆንን ?
ReplyDeleteብዙዎቹን ወግ ቀመስ ቁም ነገራም ጽሁፎችህን ወድጃቸዋለሁ። ችሎታህ በሂደት እየጎመራና የጽሁፍን ደርዝ እየያዘ ሲመጣ ይታያል። ባንዴ የሚሞላ ብቃት አለመኖሩን ስናውቅ ወደዚያ እንደሚሄዱ የሚያመላክቱ ንባቦችህን አለማክበር በእውነቱ ጥፋት ይሆንብናል። በርታ! ከዚያ ባሻገር በሌላኛው ደርዝ መምህርና ዲያቆን፣ ተመራማሪ የሚሉ ስላቅ መሰል ተጸውዖዎችን አስቀድመህ ስናይ በእውነት «ላም ባልዋለበት»እንደሚሆን ያንተንም ኅሊና እልም-ድርግም አድርገህ ካልዘጋኸው ታውቀዋለህ። እኛም ለነዚያ ተጸውዖ ሚዛን የሆነውን መለኪያ ስንገመግም ደፋርነትህን ለራስ ክብር ስትል ያለይሉኝታ መጠቀምህ ይገርመናል። እነዚህን ተጸውዖዎች መጠቀም አይቻልም ማለት ሳይሆን ለእያንዱንዱ መለኪያ (ስታንዳርድ) ስላለው ማለቴ ነው። በዚህ ላይ ቢሆንልህ ጥሩ፣ ካልሆነልህ የጽድቁን ተወውና እንደአንድ ቁም ነገራም ጸሐፊ ጥሩ ይሉኝታን ገንዘብ አድርገህ ቀጥል በመለኪያ ስፈር፣ እንድንሰፍርህም እድል ስጠኝ!
ReplyDeleteደግሞም እንደኔ ዓይን ጥሩ ወጋዊ የቁም ነገር ጸሀፊ ነህ እንጂ የወንጌል ሰባኪ አይደለህም። ትምህርቶችህ ለጭብጨባና ለሙገሳ የጅምላ ድጋፍ ይበቁ እንደሆን የምስራቹን መልእክት የሚገልጹ አይደሉም። አንዳንዶቹን ትምህርቶችህን ሰምቼ « ወኢይኵኑ እምውስቴትክሙ ብዙኃነ መምህራነ። አኀዊነ ተአምሩ ከመ እንተ ተዐቢ ደይነ ንነሥእ» ያለውን ቃል ሰምቶ አያውቅም እንዴ? የሚያስብሉ ናቸው። ለማንኛውም ሰው ሳይልህ ምን ጊዜም አውቀዋለሁ ከምትለው እውነት ሳይሆን ከሚታወቀው እውነት ጋር ታርቀህ ጽሁፍህን ቀጥል!! እግዚአብሔር ይርዳህ!!!!
You are pessimist and simply jealous. Our brother is sharpened in many ways - a writer on social issues, a preacher and a researcher in Ethiopian issues (including the church)....
DeleteDiakon Daniel, God bless you. You are the true son of our beloved Church. And a hard worker citizen. You are contributing your part to this country and our beloved church. Keep it up.
ለእኔ ግን፣ በተለይ ከዛሬ ዘመን ሰው ከሚጠብቀው አንፃር ስመለከት፣ ያለካቸው ስሞች ለዳንኤል ብያንስበት እንጂ አይበዛትም፡፡ እስቲ አንተ (እኛ) ምን ሰራህ (ሰራን)?...ስለዚህ ዳኒ ያለህ ይበቀሃል… በዚሁ ቀጥል… ለዚሁ ታመን፡፡ እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡
Deleteበርግጥ አንድ ጸሐፊ ሁልጊዜ ጥሩ ጥሩ አስተያየቶች እየተሰጡት ቢሄድ ለእድገቱ ማነቆ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ነገር ግን ለእድገቱ የሚጠቅሙትን እየመረጠ መውሰድ ግድ ይለዋል፡፡ ከላይ አስተያየቱን የሰጠው ግለሰብ አስተያየቱ እንደአስተያየት ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ቢያንስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የሚጽፋቸውን ጽሑፎች እያነበበ ቁም ነገር እየቀሰመበት ነው፡፡ “የምስራቹን አልተናገረም” ለሚለው ንግግርህ እንኳን የራሴን ተቃውሞ እነግርሃለሁ፡፡
Delete“ወኢይኵኑ እምውስቴትክሙ ብዙኃነ መምህራነ። አኀዊነ ተአምሩ ከመ እንተ ተዐቢ ደይነ ንነሥእ»
ሐዋርያው ይሔን መለዕክት ያስተላለፈበት የራሱ ምክንያት አለው፡፡ እኔ ከምገልጸው እርስዎ ያንብቡት ወይም ምድራዊ ያልሆነ ሰማያዊ ማዕረጉን ስልጣነ ክህነቱን አልቀበልም ያልከው ነገር ግን እንዳንተ ትርጉሙን እና ምስጢሩን በትክክል በማታውቀው ግእዝ ቋንቋ ስለጻፍክ እና ስለተናገርክ ብቻ (ይሔ ማለት ግን ግእዝ ስለመቻልህ ወይም የቤተክርስቲያን ሰው ስለመሆንህ እርግጠኛ አይደለሁም) ገንዘብ ናላህን እያዞረው የቤተክርስቲያን ዕድገት ዐይንህን እያቀላው የምትተቸው ዲቁናውን ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ ስራ ላይ ያዋለ ወንጌልን በተግባርና በሚጣፍጥ ማሕበራዊ ሕይወት ትንታኔ ዘወትር በየጊዜያቱና በየቀኑ እገለጸ አንተንም ጨምሮ እየመከረ እየገሰጸ የሚያስተምርህን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይንገርህ፡፡
እንዳንተ ዓይነት ብዙ መምህር ቢኖሩ መራራ ስር ያበቅላሉና ብዙዎች መምህር አይሁኑ ተብሏል፡፡ መራራ ፍሬም ታፈራላችሁና፡፡ ለማንኛውም ዐይንህን ግለጥ፣ ሰው ገንዘብን ብቻ ካለመ ከክርስቶስ በብዙ ርቀት ይሸሻልና መጠንቀቁ ይሻላል፡፡ አጽራር ከሆንክ ደግሞ እንኳንስ አንተን ደካማውን፣ የገሃነም ደጆች አይችሏትምና ለብቻህ መሞትን ምረጥ፡፡
“ወንጌልን እንደገና ደግመህ ደጋግመህ አንብበው….፡፡ የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት አውቀዋለሁ ማለትን ልመድ”
በርግጥ አንድ ጸሐፊ ሁልጊዜ ጥሩ ጥሩ አስተያየቶች እየተሰጡት ቢሄድ ለእድገቱ ማነቆ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ነገር ግን ለእድገቱ የሚጠቅሙትን እየመረጠ መውሰድ ግድ ይለዋል፡፡ ከላይ አስተያየቱን የሰጠው ግለሰብ አስተያየቱ እንደአስተያየት ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ቢያንስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የሚጽፋቸውን ጽሑፎች እያነበበ ቁም ነገር እየቀሰመበት ነው፡፡ “የምስራቹን አልተናገረም” ለሚለው ንግግርህ እንኳን የራሴን ተቃውሞ እነግርሃለሁ፡፡
Delete“ወኢይኵኑ እምውስቴትክሙ ብዙኃነ መምህራነ። አኀዊነ ተአምሩ ከመ እንተ ተዐቢ ደይነ ንነሥእ»
ሐዋርያው ይሔን መለዕክት ያስተላለፈበት የራሱ ምክንያት አለው፡፡ እኔ ከምገልጸው እርስዎ ያንብቡት ወይም ምድራዊ ያልሆነ ሰማያዊ ማዕረጉን ስልጣነ ክህነቱን አልቀበልም ያልከው ነገር ግን እንዳንተ ትርጉሙን እና ምስጢሩን በትክክል በማታውቀው ግእዝ ቋንቋ ስለጻፍክ እና ስለተናገርክ ብቻ (ይሔ ማለት ግን ግእዝ ስለመቻልህ ወይም የቤተክርስቲያን ሰው ስለመሆንህ እርግጠኛ አይደለሁም) ገንዘብ ናላህን እያዞረው የቤተክርስቲያን ዕድገት ዐይንህን እያቀላው የምትተቸው ዲቁናውን ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ ስራ ላይ ያዋለ ወንጌልን በተግባርና በሚጣፍጥ ማሕበራዊ ሕይወት ትንታኔ ዘወትር በየጊዜያቱና በየቀኑ እገለጸ አንተንም ጨምሮ እየመከረ እየገሰጸ የሚያስተምርህን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይንገርህ፡፡
እንዳንተ ዓይነት ብዙ መምህር ቢኖሩ መራራ ስር ያበቅላሉና ብዙዎች መምህር አይሁኑ ተብሏል፡፡ መራራ ፍሬም ታፈራላችሁና፡፡ ለማንኛውም ዐይንህን ግለጥ፣ ሰው ገንዘብን ብቻ ካለመ ከክርስቶስ በብዙ ርቀት ይሸሻልና መጠንቀቁ ይሻላል፡፡ አጽራር ከሆንክ ደግሞ እንኳንስ አንተን ደካማውን፣ የገሃነም ደጆች አይችሏትምና ለብቻህ መሞትን ምረጥ፡፡
“ወንጌልን እንደገና ደግመህ ደጋግመህ አንብበው….፡፡ የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት አውቀዋለሁ ማለትን ልመድ”
ቃለ ህይወት ያሰማልን::
ReplyDeleteሰው ሁሉ ትዳሩን የሚያማርረው ይህንን ባለማወቁ ነው፡፡ እርሱ ቤት የጎደለውን እዚያኛው ቤት ሲያየው ያኛው ቤት የተሟላ ይመስለዋል::
ReplyDeletethat is TRUE
አይን መግለጫ ነው የሆነኝ በእዉነት ዲያቆን
ReplyDeleteሙሉ ባል ወይንም ሙሉ ሚስት የሉም፡፡ ሊሟሉ የሚችሉ ባል እና ሚስት ግን አሉ፡፡
ReplyDeleteEzami beti esati ale ewineti New
ReplyDeleteYene ekele beti fikiri wezete eyetebale yerasuni michoti sayawikew bekagni Yale's sinitu yihoni beti yikuterew beteley bezihi Yemeni