ሰው ሲደክመው እና ሲርበው ምን ይመስላል? ይህንን ለማወቅ ወደዚች መንደር በመግባት ላይ ያለውን መንገደኛ ማየት ብቻ ይበቃል፡፡ ዓይኖቹ ከፊቱ ላይ ጠፍተው የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡ አፍንጫ እንዳለው ለማወቅ መዳሰስ የግድ ያስፈልጋል፡፡ መታወቂያ ቢኖረው ኖሮ አሁን የእርሱ ሊሆን አይችልም ነበር፡፡ የገዛ ልብሱ ስለከበደው አውልቆ እየጎተተው ይጓዛል፡፡ ሁለት ነገሮች ብቻ በትከሻው አሉ፡፡ ካናቴራው እና በስልቻ የያዛት ድስት፡፡
ረሃብ ምን ያህል ጊዜ ይሰጣል? ነበር ያለው ጸጋየ ገብረ መድኅን፡፡ ይህንን ሰው ቢያይ ደግሞ ውኃ ጥም ምን ያህል ጊዜ ይሰጣል? የሚል ድንቅ ግጥም ይጽፍ ነበር፡፡ ያ በበላዔ ሰብእ ታሪክ ጥርኝ ውኃ ሲያገኝ ውኃው በእጆቹ ንቃቃት ላይ የቀረውን ሰው ታስታውሱታላችሁ?
አይደርሱ የለም ደረሰ፡፡ መጀመርያ ከድካሙ ለመላቀቅ በመንደሩ መካከል ከበቀለ ዋርካ ሥር ጋደም አለ፡፡ ከጎኑ የዱባ ዛፍ ቢኖር ኖሮ
አንደ የባላገር ሰው ከገበያ ውሎ
ሲመለስ ቢደክመው በፀሐይ ቃጠሎ
ካንድ የሾላ ዛፍ ሥር ሄዶ ተጠግቶ
እያሉ ከበደ ሚካኤል የጻፉለት የባላገር ሰው ዛሬም ከዋርካው ሥር አልተነሣም እንዴ ያሰኛችኋል፡፡
ሆድ ባዶ ከሆነ ዕንቅልፍም ባዶ ይሆናል መሰል፡፡ የድካሙን ያህል ሊተኛ አልቻለም፡፡ ተነሣ፡፡ ተነሣና ወደ መንደርዋ ቤቶች ተጠጋ፡፡ የሚያሳዝን ፊቱን እያሳየ፣ የደከመ እጁን እያርገበገበ፣ በሰለለ ድምፁ ቁራሽ ለመነ፡፡
የሚሰጠው ግን አላገኘም ነበር፡፡ ቤቶቹን ሁሉ አዳረሰና ተመልሶ ዋርካው ሥር ተጋደመ፡፡
ያለው ሁለት ነገር ብቻ ነው፡፡ ነፍስ እና ብረት ድስት፡፡
ከተሠወሩበት እንደ ገጠር መብራት ብልጭ ባሉት ዓይኖቹ አንዳች ነገር አዩ፡፡ የሚወርድ የምንጭ ውኃ፡፡ እየተጎተተ ሄዶ በብረት ድስቱ ቀድቶ መጣ፡፡ አንድ ያልደረሰበት የርሱ ቢጤ መንገደኛ አንዳች ነገር ጥዶበት የነበረ ምድጃ አጠገቡ አለ፡፡ እንጨቶቹን ቆስቆስ አደረገና የብረት ድስቱን ውኃ ጣደው፡፡
እናም በሚፍለቀለቀው ውኃ መዝናናት ጀመረ፡፡ ምን ያድርግበት? አንዱን ድንጋይ አነሣና ብረት ድስቱ ውስጥ ጨመረው፡፡ድንጋዩ፣ ውኃ እና ብረት ድስቱ እየተጋጩ በሚፈጥሩት ዜማ ረሃቡን ለመርሳት አሰበ፡፡
እርሱ ድስት ድስቱን አይቶ ድንገት ቀና ሲል አንድ ሰው የሚያደርገውን በአግራሞት እያየው ነበር፡፡
«ምን እየሠራህ ነው ጃል» አለው ሰውዬው፡፡
«የድንጋይ ሾርባ እየሠራሁ ነው» አለው መንገደኛው በማሾፍ፡፡
«የድንጋይ ሾርባ!» ሰውዬው ተገረመ፡፡
«አዎ ከድንጋይኮ ምርጥ ሾርባ ይሠራል፡፡ በተለይማ ድንች ቢገባበት ኖሮ» አለው መንደኛው፡፡
«ርግጠኛ ነህ»» ሰውዬው የሚሆነውን ለማወቅ ጓጉቷል፡፡
«መቶ በመቶ» መንገደኛው መለሰ፡፡
«ቆይ እኔ ድንች አመጣለሁ» አለና መንገደኛው ተጓዘ፡፡
የርሱ እግር እንደለቀቀ መንገደኛው ዓይኑን ጨፈነ፡፡ ምንም ያህል ሳይቆይ ግን «ጌታው» የሚል ድምፅ ቀሰቀሰው፡፡
«እርስዎም እንግዳ ነዎት፤ የሚሠሩትም እንግዳ ነገር ነው» አለ የቆመው ሰው፡፡
«እንዴት ማለት» ጠየቀ መንገደኛው፡፡
«ድንጋይ ውኃ ውስጥ ጨምረው ምን ሊሠሩ ነው»
«ሾርባ ነዋ»
«የምን ሾርባ»
«የድንጋይ ሾርባ»
«የድንጋይ ሾርባ ደግሞ ከምን ከምን ነው የሚሠራው»
«ከድንጋይ፣ ከሥጋ፣ ከድንች፣ ከካሮት፣ ከጨው፣ ከሽንኩርት፣ ከዘይት እና ከሩዝ»
«አሁን የማየው ድንጋዩን ብቻኮ ነው»
«ሌላው ነገርማ የለኝም፤ ቢኖረኝ ኖሮ ያዩት ነበር»
«ይህንን እንግዳ ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ፤ እኔ ካሮት እና ጨው ላመጣልዎት እችላለሁ» አለ ሰውዬው፡፡
«መልካም፣ እኔ ደግሞ አዲስ ሞያ ላሳይዎት እችላለሁ»
ሁለተኛው መንደርተኛ በጥድፊያ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
የርሱን መጓዝ ተከትሎ ሌላም መንደርተኛ መጣ፡፡ ያም ዘይት፣ ሥጋ እና የማቅረቢያ ሰሐን ሊያመጣ ተጓዘ፡፡ ሌላው ደግሞ ዳቦ ሊያመጣ መንደር ገባ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያሉ ሰባት ሰዎች ለሾርባ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ አመጡ፡፡
መንገደኛውም በሚያውቀው ሞያ እያዋሐደ ሾርባውን መሥራት ጀመረ፡፡ «አሁን ድንጋዩ አያስፈልግም» አለና አወጣው፡፡
ሾርባው ሲደርስ በየሰሐኑ አቀረበላቸው፡፡ ማንኪያውንም ጨምረው ሊውጡት ነበር፡፡
ይህንን ያዩ ሌሎች መንደርተኞች የድንጋይ ሾርባ እንዲሠራላቸው ጠየቁት እርሱም ሠራ፡፡ ለሌሎች መንደሮች ሁሉ ዜናው ተዳረሰ፡፡ እናም መንገዱን ትቶ ሾርባ እየሠራ ይሸጥ ጀመር፡፡
እዚህ መንደር ዋርካው ሥር ምግብ ቤት የከፈተው ሰውዬ እይውላችሁ እንዲህ አድርጎ ነው ምግብ ቤት ከፍቶ ሀብታም የሆነው፡፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ ጋዜጠኞች መጥተው ጠየቁት፡፡
«ድንጋዩ ለሾርባው ምኑ ነው?» አሉት፡፡
እርሱም «ምኑም አይደለም» አለና መለሰላቸው፡፡ ደነገጡ፡፡
«ታድያ ለምን ትጨምርበታለህ?»
«ታሪኩ ረዥም ነው» አለና በዚያች በተራበ ሰዓት ያደረገውን ነገራቸው፡፡
«እና ያኔም ድንጋዩ ምንም አልነበረም ማለት ነው?» አሉት፡፡
«አሁን ታሪኩን ትቼ የተማርኩትን ልንገራችሁ፡፡ እኔ መንገደኛ ሆኜ ወደዚች መንደር ስመጣ፡፡ ያጣሁ የነጣሁ ድኻ የሆንኩ መስሎኝ ነበር፡፡ ምንም ነገር የሌለኝ መስሎኝ ነበር፡፡ ስሕተቴ ከዚህ ይጀምራል፡፡ ምንም ነገር የሌለው ሰው የለም፡፡ ያለውን የማያውቅ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት የማያውቅ ሰው ግን ሞልቷል፡፡
«ችግሩ የሚጀመረው ከአቆጣጠራችን ነው፡፡ እኛ ቁጥር መቁጠር የምንጀምረው ከሌለን ነገር ነው፡፡ ተስፋ የምንቆርጠውም ከሌለን ነገር ስለምንጀምር ነው፡፡ ወዳጄ ሁይ ካለህ ነገር ተነሣ፡፡ ምን አለህ? ጉልበት፣ ዕውቀት፣ ጤና፣ መልካም ትዳር፣ ጥሩ ልጆች፣ ደስተኛ ቤተሰብ፣ እምነት፣ ነገር የማቅለል ችሎታ፣ ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ትምህርት፣ ልምድ፣ ገንዘብ፣ ጊዜ? ምን አለህ? ካለህ ነገር ጀምር፡፡ ተአምር የማይሠራበት ነገር በዓለም ላይ የለም፡፡
«እኔ በዚያ ጊዜ ውኃ፣ ድስት እና ድንጋይ ነበረኝ፡፡ የድንጋይ ሾርባ ለመሥራት ባልነሣ ኖሮ ማን ዘወር ብሎ ያየኝ ነበር፡፡ ድንቹ፣ ካሮቱ፣ ጨው፣ ዘይቱ፣ ሩዙ፣ ዳቦው፣ ሁሉንም ያመጣቸው ድንጋዩ ነው፡፡ ያ ድንጋይ እዚያ ቦታ ላይ ስንት ዘመን ኖሯል፡፡ ስንት ሰው ተደባድቦበታል፣ ስንት ሰው ተቀምጦበታል፣ ስንቱን ሰው እንቅፋት ሆኖ መትቶታል፡፡ ስንቱ ሰውስ ተጫውቶበታል፡፡
«እኔ ግን ሾርባ ሠራሁበት፡፡ ወዳጄ አንተም አጠገብህ ባለው በቀላሉ ልታገኘው በምትችለው ነገር፣ እግዜር በነጻ ባደለህ ነገር በርሱ ሾርባ ለመሥራት ተነሣ፡፡ የሌለህን ሥጋ፣ ድንች፣ ካሮት፣ ሩዝ፣ እያሰብክ ለምን ትናደዳለህ፣ ለምንስ ታዝናለህ፣ ለምንስ ተስፋ ትቆርጣለህ፣ ለምንስ ራስህን ድኻ ታደርጋለህ?
«ሀብታም ነህ ወዳጄ፣ ሀብታም ነህ፡፡እግዜር የሰጠህን ስላላወቅከው እንጂ ካለህ ከጀመርክ ሀብታም ነህ፡፡ ከሌለህ ከጀመርክ ያለህን ታጣለህ፡፡ ካለህ ከጀመርክ ግን የሌለህንም ታመጣዋለህ፡፡ ድንጋይ ሾርባ አይሆንም፡፡ ካሰብክበት ግን ድንጋይ ሾርባ ያመጣል፡፡
«በልመና የምታገኘው የበታችነትን ብቻ ነው፡፡የምትለምን ከሆነ ተለማኞቹ ይንቁሃል፡፡ ተወው አትለምን፡፡ አንተ ራስህ ባለህ ነገር ጀምር፡፡ ያን ጊዜ የምትለምናቸው በተራቸው አንተን ይለምናሉ፡፡
«ባዶ እጅህን አትቁም፡፡ ሰዎች የሚለግሱህ አንተ ዘንድ አንዳች ነገር መኖሩን ካወቁ ብቻ ነው፡፡ አንተ ደግሞ ያ ነገር አለህ፡፡ ጥያቄው አንድ ብቻ ነው፡፡ ያለህን ነገር ታውቀዋለህን? ይህንን ከመለስክ የድንጋይ ሾርባ መሥራት ትችላለህ፡፡»
ይህንን ሲጨርስ ጋዜጠኞቹ ጋዜጠኛ መሆናቸውን ረስተው እንደ ተመልካች አጨበጨቡ፡፡ በቀጣዩ ቀን ጋዜጦቹ ሁሉ ተመሳሳይ ርእስ ነበር ይዘው የወጡት፡፡
«የድንጋይ ሾርባ» የሚል፡፡
“የድንጋይ ሾርባ“ ብለህ መጣህልኝ። የምትገርም ምክር ናት። ልቅም ያለች ምክር። አንባቢን ወዲያውኑ ወደ ውስጡ ዘልቆ ራሱን እንዲጠይቅ፤ያለውን እንዲፈትሽ፤ ንቆ የተወውን እንዲያነሳ የምታደርግ ምክር። እንዲህ ነው እንጂ ተሰፋ ሰጪ ወንድም። እግዚአብሔር አብዝቶ አትረፍርፎ ይስጥህ። ረጅም ጢና እና እድሜ ይስጥህ። ስንቱ በዚች ምክር ሊቀየር እንደሚችል ሳነብ ውስጤ በሐሴት ተሞላች። እኔው ከእራሴ ጋር እየተመካከርኩ ነው። የረሳዃቸውን። “የቆጡን አውርድ ብላ .....“ የተባለው የደረሰብኝ ይመስለኛል። እናም የአይምሮ ጓዳየን እየፈተሽኩ ነው። እንዲህ እንዳስብ ስላደረግኸኝ አምላክ ውለታውን ይክፈልህ።
ReplyDeleteወንድምህ
Inspiring.KHY Memihir.
ReplyDelete«ባዶ እጅህን አትቁም፡፡ ሰዎች የሚለግሱህ አንተ ዘንድ አንዳች ነገር መኖሩን ካወቁ ብቻ ነው፡፡ አንተ ደግሞ ያ ነገር አለህ፡፡ ጥያቄው አንድ ብቻ ነው፡፡ ያለህን ነገር ታውቀዋለህን? ይህንን ከመለስክ የድንጋይ ሾርባ መሥራት ትችላለህ፡፡»
ReplyDelete02/02/2012 @ 11:02AM
Dani esti bertalin. I always read your belog and feel we have a hope for change but nothing due to woyyane and abune paulos.
ReplyDeleteyedenedene libachinin Egziabher yikfetlin. Mekarina astemari wendim ayasatan. God Bless you!!
ReplyDeleteErut kalchalk teramed esunam kaqatehe tenfuaqeqi gen befitsum endatikom.
ReplyDeleteYetegegnew sayhon yetataw new yemifelegew yibalal. Mehon yalebet gin yetataw sayhon yetegegnew new leka asfelagiw. Dinq eyita Dani.
ReplyDeletegreat dani! keep it up!
ReplyDelete«እኔ በዚያ ጊዜ ውኃ፣ ድስት እና ድንጋይ ነበረኝ፡፡ የድንጋይ ሾርባ ለመሥራት ባልነሣ ኖሮ ማን ዘወር ብሎ ያየኝ ነበር፡፡ ድንቹ፣ ካሮቱ፣ ጨው፣ ዘይቱ፣ ሩዙ፣ ዳቦው፣ ሁሉንም ያመጣቸው ድንጋዩ ነው፡፡ ያ ድንጋይ እዚያ ቦታ ላይ ስንት ዘመን ኖሯል፡፡ ስንት ሰው ተደባድቦበታል፣ ስንት ሰው ተቀምጦበታል፣ ስንቱን ሰው እንቅፋት ሆኖ መትቶታል፡፡ ስንቱ ሰውስ ተጫውቶበታል፡፡
ReplyDelete«እኔ ግን ሾርባ ሠራሁበት፡.......«የድንጋይ ሾርባ»
Daniel,
ReplyDeleteWow, you taught us again with your nice intervention.
I would like to quote you:
«ችግሩ የሚጀመረው ከአቆጣጠራችን ነው፡፡ እኛ ቁጥር መቁጠር የምንጀምረው ከሌለን ነገር ነው፡፡ ተስፋ የምንቆርጠውም ከሌለን ነገር ስለምንጀምር ነው፡፡ ወዳጄ ሁይ ካለህ ነገር ተነሣ፡፡ ምን አለህ? ጉልበት፣ ዕውቀት፣ ጤና፣ መልካም ትዳር፣ ጥሩ ልጆች፣ ደስተኛ ቤተሰብ፣ እምነት፣ ነገር የማቅለል ችሎታ፣ ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ትምህርት፣ ልምድ፣ ገንዘብ፣ ጊዜ? ምን አለህ? ካለህ ነገር ጀምር፡፡ ተአምር የማይሠራበት ነገር በዓለም ላይ የለም፡፡
Actually, life is full of challenge. To cope up with the challenge one should have a wisdom. Wisdom comes from knowledge of self. The technique to success is to find and be yourself. Knowing yourself is the beginning of all wisdom.
Like Tzu Sun stated that "If you know the enemy and know yourself, you need not fear a hundred battles."
To sum up, I want to say that, " Knowing others is intelligence; knowing yourself is true wisdom. Mastering others is strength, mastering yourself is true power."
እግዜር የሰጠህን ስላላወቅከው እንጂ ካለህ ከጀመርክ ሀብታም ነህ፡፡ what an amazing advise i like that. keep up on giving us your priceless advises brother
ReplyDelete«ባዶ እጅህን አትቁም፡፡ ሰዎች የሚለግሱህ አንተ ዘንድ አንዳች ነገር መኖሩን ካወቁ ብቻ ነው፡፡ አንተ ደግሞ ያ ነገር አለህ፡፡ ጥያቄው አንድ ብቻ ነው፡፡ ያለህን ነገር ታውቀዋለህን? ይህንን ከመለስክ የድንጋይ ሾርባ መሥራት ትችላለህ፡፡»
ReplyDeleteእንደ መከርከን መካር አያሳጣህ፡፡ እግዜር ዕድሜና ጤና ይስጥህ፡፡
ReplyDeleteእርግጠኛ ነኝ ይህ ምክር በዳኒ ብዕር ሁኖ ከእግዚአብሄር የተጻፈልኝ መልእክት ነው፡፡500 % እኔ እና እኔን ይመለከታል፡፡
ReplyDeleteአቤቱ ባንተ እጅ ያለውን ቁለፍ ማየት ተስኖኝ በተዘጋው ልቤ ውስጥ ያኖርክልኝን ህያው ስጦታ እጠቀምበት ዘንድ በአስተዋዮችና በመካሪ ዎዳጆችህ የተባ ብዕር ሁነህ “ሳሙኤል ተነስ! “ ስትል የቀሰቀስከኝ ያባቶቸ አምላክ ሥላሴ ሆይ……አዎ ባሪያህ የተናገርከውን ሰምቻለሁ!!!!
አምላኬ ሆይ አቤቱ ህዝብህን ትመክርባቸው ዘንድ ማስተዋልን የሞላህባቸውና ድንጋይ መቀቀል ያስተማሩንን ጠቢባን በመንገድህ እና በቤትህ ህያው አርጋቸው አሜን!
ሳሚ ዘሰመራ
Dani, egziabher yirdah bertalin.
ReplyDeleteTebarek.
ReplyDeleteAmeseginalehu Dani! Astemirognal.
ReplyDeleteእንደ መከርከን መካር አያሳጣህ፡፡ እግዜር ዕድሜና ጤና ይስጥህ፡፡
ReplyDeleteEgziabeher aberzto yestelem wondem Danel
ReplyDeleteTnx dani! Egziabher yistilen!
ReplyDelete'...ሰዎች የሚለግሱህ አንተ ዘንድ አንዳች ነገር መኖሩን ካወቁ ብቻ ነው::
ReplyDeletethat is true
Egzier yibarkih!!!!!
ReplyDeleteWondim Daniel, egiziabehare yebeletewun yegiletileh! legnam yeminastewulibet libona yesten. Amen!!!!!!
ReplyDeletebetam yamiral
ReplyDeleteDiakon Adinakih negn and i am reading your article always ,Begugit newu yemitebikew hulem
thanks ,long live to you
መልካም ትምህርት ነው፡፡ ብዙ ግዜ ስለ ብልጽግና ማስተማር አልተለመደም፡፡ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ማስተማር ግን ግድ ነው፡፡ መጽሐፉም የሚለው ታማኝ መጋቢ ባለጸጋው በሐብቱ ላይ የሚሾመው ማን ነው እንጂ ለምን ባለጸጋ ሆንክ የሚል የለም፡፡
ReplyDeleteAs always Inspiring!Egziabher Yibarkh!
ReplyDeleteWOW!!! D/N Dan!! it it is all about me thanks My God bless your hard work
ReplyDeleteችግሩ የሚጀመረው ከአቆጣጠራችን ነው፡፡ የሌለንን ከመፈለግ ይልቅ ላለን ትኩረት እንስጥ ታላቅ ምክር ነው ፡፡ የሌለንን በመፈለጋችን ከገነት ተባረናልና፡፡
ReplyDelete«ችግሩ የሚጀመረው ከአቆጣጠራችን ነው፡፡ እኛ ቁጥር መቁጠር የምንጀምረው ከሌለን ነገር ነው፡፡ ተስፋ የምንቆርጠውም ከሌለን ነገር ስለምንጀምር ነው፡፡ ወዳጄ ሁይ ካለህ ነገር ተነሣ፡፡ ምን አለህ? ጉልበት፣ ዕውቀት፣ ጤና፣ መልካም ትዳር፣ ጥሩ ልጆች፣ ደስተኛ ቤተሰብ፣ እምነት፣ ነገር የማቅለል ችሎታ፣ ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ትምህርት፣ ልምድ፣ ገንዘብ፣ ጊዜ? ምን አለህ? ካለህ ነገር ጀምር፡፡ ተአምር የማይሠራበት ነገር በዓለም ላይ የለም፡፡ Mamush,MN
ReplyDeleteI take Stone Soap 'Yedingay Shorba' In china.
ReplyDeleteIt may be the reason for them to be strong
Thank you Dani
Dani,it is a promising advice.i loved it. it should be tried by every individual.it is a current affair in Ethiopia which hunger and poverty is intensified now.so economically and politically every body should start trying the ''dingai shorba''experience.
ReplyDeletefrom aa
tabarake dane
ReplyDeleteegziabher betibeb yigeletsal...eniho beanitelay adrom yinageral...masitewalihin yibarikew!
ReplyDeletestay blessed
እግዚአብሔር ይባርክህ!!!!!
ReplyDelete