Tuesday, January 31, 2012

በአንድ የዘመዴ ቤት

አንድ ዘመዴ ቤት ሄጄ ነው፡፡ እናቱ «እስኪ ያንን ነገር ለዳንኤል አሳየው» አለቺው ልጇን፡፡ ልጇ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ ደብተሩን ይዞት መጣ፡፡ ትናንት ሠርቶ ዛሬ ባሳረመው የአማርኛ የቤት ሥራ ሁለት ኤክስ አግኝቷል፡፡ ልጁ ግን ለምን ኤክስ ሊሆን እንደቻለ ሊገባው አልቻለም፡፡ እናቱን ደጋግሞ ጠየቃት፡፡ እርሷም ግልጽ አልሆነላትም፡፡
የተሰጠው ጥያቄ አዛምድ ነው፡፡ እዚያ መካከል «እንደ ወትሮው» የሚል ሐረግ «» ሥር ይገኛል፡፡ «» ሥር ደግሞ «እንደ ሁልጊዜው» የሚል ምርጫ አለ፡፡ ልጁ የመጀመርያውን ኤክስ ያገኘው እነዚህን በማዛመዱ ነበር፡፡ ከዚያው በታች «» ሥር ላለው «መሞከር» ለሚለው ቃል «መጣር» የሚል ተዛማጅ «» ሥር ተቀምጧል፡፡ የሚል ሌላ አዛምድ አለ፡፡
ልጁ ከተሰጡት መልሶች ተቀራራቢ የሆነውን መልሷል፡፡ መምህሩ ግን አላረመለትም፡፡ እኔንም ጥያቄ ፈጠረብኝ፡፡ ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ ትክክለኛው መልስ ምን እንደሆነ አለመጻፉ ነው፡፡ ልጁን «መልሱ ምንድን ነው አላችሁ?» ብዬ ጠየቅኩት፡፡ «ኤክስ አደረገኝ እንጂ መልሱን አልጻፈልኝም» አለኝ፡፡ መምህሩ ደብተራቸውን ወስዶ ኖሯል ያረመው፡፡
«እስኪ መጽሐፉን አምጣ» አልኩና ጥያቄዎቹን መመልከት ጀመርኩ፡፡ አሁን ነገሩ ግልጽ ሆነልኝ፡፡ ልጁ «» እና «» ሲገለብጥ አቀያይሯቸዋል፡፡ መምህሩም የአዛምዱን መልሶች ያረመው ፊደላቱን እያየ እንጂ መልሱን እያየ አይደለም፡፡ ይህ ግን በልጁ ላይ ሁለት ነገር ፈጠረበት፡፡ አንደኛ ለምን ኤክስ እንዳገኘ ሊገባው አልቻለም? ሁለተኛ ደግሞ የእነዚህን ሐረጋት ትርጉም ሊያውቅ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም እርሱ ትርጉም ነው ብሎ የሰጠው መልስ ስሕተት ነው ተብሏል፡፡ ትክክለኛው ደግሞ አልተነገረውም፡፡
እኔ እዚህ ላይ ነበር ማሰብ የጀመርኩት፡፡ አሁን ይሄ ልጅ የሚጠበቅበት ምንድን ነው? የቃላቱን ትርጉም ማወቅ ነው? ወይስ በትክክል መገልበጥ? ለልጁ ሁለቱም ጥቅም አላቸው፡፡ የቃላቱን ትርጉም ማወቅ ዕውቀቱን፣ በትክክል መገልበጥ ደግሞ ክሂሎቱን ይጨምርለታል፡፡ ይህ የሚሆነው ግን መምህሩ ለልጁ ሁለቱንም ካስረዳው ብቻ ነው፡፡
የአዛምድ መልሶችን «እናሸንፋለን፣ ኢትዮጵያ ትቅደም፣ ሶሻሊዝም ይለምልም» እያለ ያመጣ የነበረው መምህሬ ትዝ አለኝ፡፡ ያንን ያደረገው አንድም ለማረም እንዲቀለው፣ አንድም ለዘመኑ ብሎ ይመስለኛል፡፡
እኔ መምህሩን ብሆን ኖሮ የመልስ ፊደል ብቻ እያየሁ አላርምም ነበር፡፡ ከመቶ በላይ ተማሪዎች በአንድ ክፍል በሚማሩበት ቦታ እና ዘመን ይህ ቢደረግ ለይቅርታ ልብ በኖረን ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ከሠላሳ በላይ ተማሪዎች በአንድ ክፍል ባልተቀመጡበት የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡ መምህሩ የተማሪዎቹን ደብተር ወስዶ ማረሙ የሚመሰገን ነው፡፡ ግን ቤቱ ከወሰደው ላይቀር ተረጋግቶ ቢያር ምላቸው ምን ነበረበት?
አንዳንዴኮ ልጆች ያልታሰበ መልስ ያመጣሉ፡፡ ከተለመደው ሁኔታም ሊያፈነግጡ ይችላሉÝÝ ይህንን ማየት የሚቻለው ልጆቹን በቅርበት በመከታተል እና ለእያንዳንዱ ተግባራቸው ትኩረት በመስጠት ነው፡፡ አያሌ የዓለም ሳይንቲስቶች ከትምህርት ቤት እየተባረሩ የወጡት መምህሮቻቸው ከተለመደው መንገድ ወጣ ብለው የተማሪዎቹን ችሎታ፣ ፍላጎት እና መንገድ ለማየት ባለመቻላቸው እና ባለ መፈለጋቸው ነበር፡፡
በተአምረ ኢየሱስ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስን የዕብራይስጥ ፊደል ሊያስተምረው የወሰደው መምህር የገጠ መውም ይሄው ነበር፡፡ «አሌፍ በል» አለው፡፡ «አሌፍ» አለ፡፡ «ቤት በል» አለው፡፡ ዝም አለ፡፡ መምህሩ ተናድዶ ይቆጣ ጀመረ፡፡ ያን ጊዜ ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ «መጀመርያ የአሌፍን ትርጉም ንገረኝና ቤት እላለሁ» ብሎ መለሰለት፡፡ መምህሩ ግን ከተለመደው መንገድ መውጣቱ ስላስደነገጠው ለእናቱ ወስዶ ሰጣት፡፡
አንድ መምህር የነገሩኝን እዚህ ላይ ባነሳው መልካም ሳይሆን አይቀርም፡፡ እርሳቸው የአማርኛ መምህር ናቸው፡፡ የአማርኛ አባባሎችን አስተምረው ለተማሪዎቻቸው ጥያቄ ሰጧቸው፡፡ ከጥያቄው በአንዱ «የነ ቶሎ ቶሎ ቤት» የሚለውን አባባል ጀምረውን ተውት፤ ተማሪዎቹ እንዲያሟሉት፡፡ አንዲት ልጅ ታድያ የተለየ ነገር ይዛ መጣች፡፡ «የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ሲሚንቶው አይደርቅም» ይላል መልሷ፡፡ «ገርሞኝ ለብዙ ደቂቃ አየሁት» አሉ መምህሩ፡፡ «እውነቷን እኮ ነው አልኩ፡፡ ትናንት ቤት በሣር በሚሠራበት ዘመን ግድግዳው ሰንበሌጥ የሚለው ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬ ቤት በብሎኬት በሚሠራበት ዘመን ግን ይህ ሊሠራ አይችልም፡፡ በዚህ ዘመን ችኩል ቤት ሠሪ ሲሚንቶው ሳይደርቅ ቀለም ሊቀባ ነው የሚችለው ብዬ አሰብኩ፡፡ እናም ዝም ብዬ ተውኩትና ልጂቷን ጠየቅኳት፡፡ እኔ ያሰብኩትን ነበር የነገረችኝ፡፡ እንዲህ በማሰቧ ገርሞኝ አስጨብጭቤ አረምኩላት» ብለውኛል፡፡
መምህር እንዲህ ነው፡፡ መምህር እና ሰይጣንኮ ምንም ሁለቱም ቢፈትኑ ሁለቱ ግን አንድ አይደሉም፡፡ ሰይጣን ለመጣል ይፈትናል፣ መምህር ለማሳለፍ፤ ሰይጣን ያላስተማረውን ይፈትናል፣ መምህር ያስተማ ረውን፡፡ ሰይጣን መውጫውን ደፍኖ ይፈትናል፣ መምህር እያሳየ፤ ሰይጣን ተስፋ ለማስቆረጥ ይፈትናል፣ መምህር ተስፋ ለመስጠት፤ ሰይጣን ለማሳሳት ይፈትናል፣ መምህር ለማረም፤ ሰይጣን ለማደንቆር ይፈትናል፣ መምህር ለማሳወቅ፤ ሰይጣን ለማጣመም ይፈትናል፣ መምህር ለማቃናት፡፡
ልጁኮ ከመጽሐፉ ሲገለብጥ መሳቱን እኔ እስክነግረው ድረስ አልገባውም ነበር፡፡ ታድያ ምኑን ተማረው፡፡ ወይ መምህሩ ተሳስቷል ብሎ መምህሩን ይንቃል፤ ያለበለዚያም ደግሞ እራሱን ስሕተተኛ አድርጎ የተጣመመ ዕውቀት ይገበያል፡፡ ለቃላቱ እርሱ የሰጣቸው ፍቺዎች ስሕተት ናቸው ብሎ እንዲደመድም አድርጎታልና፡፡
ጥያቄ እና ፈተና ዋና ዓላማቸው መስተማር እና መመዘን ነው፡፡ ሰው ከስሕተቱ እንዲማር፡፡ የዕውቀት ደረጃውንም እንዲያውቅ፡፡ የሚሆነው ግን ጥያቄዎቹ ግልጽ፣ ዕውቀትን ለመመዘን የሚያስችሉ እና በተማሪው ዐቅም የቀረቡ ከሆኑ ብቻ ነው፡፡
ትዝ ይለኛል ዐሥረኛ ክፍል እያለሁ የእንግሊዝኛ መምህራችን «say true or false´ የሚል ከሃምሳ የሚታረም ዐሥር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና አመጣ፡፡ ደግሞ ጥያቄው እንዴት ቀላል መሰላችሁ፡፡ ሁላችንም ዐሥር ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ጨርሰን መለስን፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በቀጣዩ ቀን ክፍሉ በድንጋጤ ነበር የተናጋው፡፡ ሁላችንም ዜሮ ማግኘታችን ተነገረን፡፡ የቁጣ እና የድንጋሬ ማዕበል ክፍሉን መታው፡፡ እንዴት? አልን ሁላችንም፡፡
መምህሩም አብራሩልን፡፡ «እኔ «say true or false» አልኩ እንጂ «write true or false» አላልኩም አሉን፡፡ «እና ምን ማድረግ ነበረብን?» አልናቸው፡፡ «ተናገሩ ነው የተባላችሁትና በቃላችሁ «true» «false» ማለት ነበረባችሁ ብለውን ዐረፉት፡፡ ፈተናው የተሰረዘው እስከ ዳይሬክተሩ ቢሮ በደረሰ ክርክር ነበር፡፡
ዋናው የትምህርት ዓላማው በተማሪዎቹ ዘንድ የጠባይ ለውጥ ማምጣት እንጂ የፈተና ቴክኒክ እና ታክቲክ እንዲያውቁ ማድረግ አይደለም፡፡ የኛ መምህር «write» እና «say» በሚሉ ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት እንድንረዳው ፈልገው ከሆነ አንድ ወይንም ሁለት ጥያቄዎችን በዚያ መልኩ ማቅረብ ይበቃቸው ነበር፡፡
ተማሪ ስሕተቱን የማረሚያ ዕድል ሊያገኝ ይገባዋል፡፡ ስሕተት መጥፊያ ሳይሆን መማርያ እንዲሆን፡፡ የራሱን ስሕተት ማረም እንዲለምድ፡፡ ወድቆ መነሣት እንደሚቻል እንዲገነዘብ፡፡ መውደቅ መጥፊያ እየሆነ ብዙ ወዳጆቻችን በአንዲት ቀን ፈተና የሕይወታቸው መሥመር ወደማይፈልጉት ተቀይሮባቸዋል፡፡ ከአንዲት ቀን ፈተና መውደቅ ከሕይወት ጉዞ መውደቅ እየተደረገ በመወሰዱም አያሌ ዜጎቻችን ትምህርት አይሆነኝም እንዲሉ አድርገናቸዋል፡፡
ሰው ከወደቀ በኋላ ሌላ ተመሳሳይ ፈተና የማያዘጋጅ ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን ሌላ የመውደቂያ ፈተና ነው የሚያዘጋጀው፡፡ ዓላማው ፈትኖ መጣል ነውና፡፡ መምህር ግን ከዚህ እጅግ በብዙ፣ እጅግ በሚሊዮን መለየት አለበት፡፡ ዓላማው ፈትኖ ማሳለፍ በመሆኑ፡፡ አንድ ተማሪ በአንድ ፈተና ሕይወቱ የሚፈተንበት ዘመን ሊያበቃ ይገባል፡፡ ዛሬ የተሳሳተውን ነገ የሚያርምበት ዕድል ማግኘት አለበት፡፡ እንዲያውም መምህሩ ከመፈተኑ በፊት ተማሪዎቹ እንዲጨብጡት የሚፈልገውን ዕውቀት ወይንም ክሂሎት መያዛቸውን በተለያዩ መመዘኛዎች እያገላበጠ ተማሪዎቹን መለካት አለበት፡፡ ፈተና ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡
በአንዳንድ ሀገሮች እንዲያውም የጥያቄ ባንክ የሚባል ነገር አለ፡፡ በአንድ የትምህርት ዓይነት እንዲጨበጡ የሚፈለጉ ነገሮችን አሟልተው የያዙ በተለያየ ዓይነት እና ቅርጽ የወጡ ጥያቄዎች ያሉበት ባንክ ነው፡፡ ተማሪዎቹ በዚያ ባንክ ያሉ ጥያቄዎችን በሙሉ ለመሥራት ከቻሉ ፈተናው አይከብዳቸውም፡፡ ምክንያቱም ራሳቸውን ፈትነው መጥተዋልና፡፡ የዚህ ምክንያቱ ፈተናን ለማቅለል አይደለም፡፡ ተማሪዎቹ በፈተናው ሰዓት ከዕውቀት እና ከክሂሎት ጋር እንጂ ከፈተና አወጣጥ ታክቲክ ጋር ሲሟገቱ እንዳይውሉ ለማድረግ እንጂ፡፡
አንዳንዴኮ ከጥያቄዎች እና ከፈተናዎች የምንማረው የሽወዳ ጥበቦችን እንጂ ክሂሎት እና ዕውቀትን አይደለም፡፡ አንዳንድ ጥያቄ አውጭዎችም እንዴት ተማሪዎችን ልሸውዳቸው እችላለሁ? ይላሉ እንጂ እንዴት ዕውቀታቸውን ልመዝነው እችላለሁ? አይሉም፡፡ እንዲያውም እንደ አስማተኛ ፊልም ሸዋጅ ፈተና የሚያወጡ መምህራን በአንዳንድ ቦታዎች እንደ ታላቅነት መለኪያ ተወስዶ ሲሞገሱበት ይሰማል፡፡ ሲከበ ሩበትም ይታያል፡፡
በትምህርት መቀለድ ለተማሪዎች የአራዳነት መለኪያ እንዳልሆነ ሁሉ ተማሪ መጣልም ለመምህራን የታላቅነት ማሳያ አይደለም፡፡ ቦንብ ማፈንዳት የሚጎዳውን ያህል ቦንብ ቦንብ ጥያቄዎችን ማውጣትም የተማሪን ሕይወት ይጎዳል፡፡
እዚያ ቤት ቁጭ ብዬ ነበር ይህንን ሁሉ የማስበው፡፡ ሌሴቶ ያኘሁት አንድ ወዳጄ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያስተምር በነበረበት ጊዜ ለተማሪዎቹ የሚያደርገውን እና ሌሴቶ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርገውን እያነፃፀረ «ግፍ ሳንሠራ አልቀረንም» ይል ነበር፡፡ እዚያ ከአንድ ፈተና በፊት ሦስት ተመሳይ ፈተናዎችን አውጥቶ የተማሪዎችን ብቃት መለካት ነበረበት፡፡ ከዚያም አብዛኞቹ የተሳሳቱባቸውን መርጦ እንደገና ማስተማር፣ በተለየ መንገድም ትምህርቱን ማቅረብ ነበረበት፡፡ ወደ ፈተና የሚገባው ቢያንስ ሰማንያ አምስት በመቶው ተማሪዎች ያወጣቸውን ሁሉንም ጥያቄዎች ሲመልሷቸው ነው፡፡
«እንዲህ ብናደርግ ኖሮ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ስንቱን ለክብር እናበቃው ነበር» እያለ ይቆጫል ሁልጊዜ፡፡ እዚያ በዘመዴ ልጅ ላይ እንደተደረገው በተማሪዎቹ የጥያቄ ደብተር ላይ ኤክስ ማድረግ ብቻ አይበቃም፡፡ ለምን ኤክስ እንደሆነ ማብራራት እና ተማሪው ያንኑ ዓይነት ጥያቄ በሌላ መንገድ ተጠይቆ ስሕተቱን እንዲያስተካክል ማድረግም ይፈለጋል፡፡ ያኔ ነው ታድያ መምህሩ በስተ መጨረሻ «ለወይኔ ያላደረግኩለት ነገር ግን ላደርግለት የሚገባ ምን ነገር አለ?» ብሎ መናገር የሚችለው፡፡

© ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔትላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

32 comments:

 1. D.daniel it is true !

  ReplyDelete
 2. IT IS GOOD DANI ,AMLAK EJIHN YABERTA!!

  ReplyDelete
 3. Dear Daniel,

  The concept of examination in our circumstance is totally different from the other parts of the world. Most of the time the definition of teaching is not available in our dictionary.

  At one point of time, I had a chance to join the FBI National Academy in Quantico, Virginia.

  When I studied there at the beginning of every session the professor will give you 400 questions and list of references.

  Basically, to get the answer of those questions you must read more than twenty books. At the end of the semester you will have an examination of 100 questions out of 400 question which you have it when the school was commenced. You should score 98 out of 100 to score A+.

  By this technique, they trained us to read more and to remain confident.

  Look, the purpose of examination in this context is to make you aware of the subject matter.

  So far, examination must focus on testing the student knowledge and skill. I totally in disagreement to the curve system of measurement. I rather suggest that We must scale up the continuous evaluation system.

  ReplyDelete
 4. Great stuff Daniel. I was also a teacher at some point. The way I was dealing with students was not good. Specially after having experience from the rest of the world. I know and I agree that there should be a boarder within student-teacher r/nship, but we should not make them afraid of us. I have learned my lesson and have already promised to treat students fairly.

  School is the way to build knowledge in every aspect not to just test them and make them fail. Teachers can we just focus mainly on the way of delivering the concepts of the subjects.

  keep it up my brother.

  ReplyDelete
 5. Dear Daniel kibret
  It is excellent view, God bless you.

  «ግፍ ሳንሠራ አልቀረንም» ይል ነበር፡፡ እዚያ ከአንድ ፈተና በፊት ሦስትተመሳይ ፈተናዎችን አውጥቶ የተማሪዎችን ብቃት መለካት ነበረበት፡፡ ከዚያም አብዛኞቹየተሳሳቱባቸውን መርጦ እንደገና ማስተማር፣ በተለየ መንገድም ትምህርቱን ማቅረብ ነበረበት፡፡ ወደፈተና የሚገባው ቢያንስ ሰማንያ አምስት በመቶው ተማሪዎች ያወጣቸውን ሁሉንም ጥያቄዎችሲመልሷቸው ነው፡፡
  «እንዲህ ብናደርግ ኖሮ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ስንቱን ለክብር እናበቃው ነበር» እያለ ይቆጫልሁልጊዜ፡፡

  ReplyDelete
 6. ዲ/ን ዳንኤል ዛሬም እንዴትናንቱ አድስ ነገር ይዘህ ብቅ በማለትህ ይበል ብያለሁ፡፡ ምልክቶች/ሲምፕተም/ ላይ ሳይሆን ምክንያቶች ላይ በማተኮር ጽሁፍህን ቀጥልበት፡፡ምክንያቱም የችግር ምንጮችን ካወቅን ለችግሮቹ የሚሰጠው መፍትሄ ዘላቂነት አለውና ነው መምህር፡፡
  WUBSHET,Gojjam!

  ReplyDelete
 7. Agenagn, Thanks dani አንዳንዴኮ ከጥያቄዎች እና ከፈተናዎች የምንማረው የሽወዳ ጥበቦችን እንጂ ክሂሎት እና ዕውቀትን አይደለም፡፡ አንዳንድ ጥያቄ አውጭዎችም እንዴት ተማሪዎችን ልሸውዳቸው እችላለሁ? ይላሉ እንጂ እንዴት ዕውቀታቸውን ልመዝነው እችላለሁ? አይሉም፡፡ እንዲያውም እንደ አስማተኛ ፊልም ሸዋጅ ፈተና የሚያወጡ መምህራን በአንዳንድ ቦታዎች እንደ ታላቅነት መለኪያ ተወስዶ ሲሞገሱበት ይሰማል፡፡ ሲከበ ሩበትም ይታያል፡፡

  ReplyDelete
 8. ጥሩ ምልከታ ነው! ነገር ግን ከሆነ አይቀር ከተማሪዎቻችን እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጎን ያለውን ችግር አካተህ ብታወጣው ከዚህም የተሻለ ይሆን ነበር፡፡

  ReplyDelete
 9. samuel Abera, from AAUJanuary 31, 2012 at 4:48 PM

  dani I really appreciate your variety of touchings, Ethiopian teachers need to learn from your lesotho's friend, ........thanks

  ReplyDelete
 10. Dn Daniel,
  so nice story.

  As a teacher i lernt so many things from this article.

  ReplyDelete
 11. "....መምህር እና ሰይጣንኮ ምንም ሁለቱም ቢፈትኑ ሁለቱ ግን አንድ አይደሉም፡፡ ሰይጣን ለመጣል ይፈትናል፣ መምህር ለማሳለፍ፤ ሰይጣን ያላስተማረውን ይፈትናል፣ መምህር ያስተማ ረውን፡፡ ሰይጣን መውጫውን ደፍኖ ይፈትናል፣ መምህር እያሳየ፤ ሰይጣን ተስፋ ለማስቆረጥ ይፈትናል፣ መምህር ተስፋ ለመስጠት፤ ሰይጣን ለማሳሳት ይፈትናል፣ መምህር ለማረም፤ ሰይጣን ለማደንቆር ይፈትናል፣ መምህር ለማሳወቅ፤ ሰይጣን ለማጣመም ይፈትናል፣ መምህር ለማቃናት፡፡" በጣም ደስ ይላ ዳንኤል

  ReplyDelete
 12. It is a good observation. That is why most people think that exams are tough in Ethiopia. This is just because teachers design exams to trick students instead of measuring their knowledge. In my experience exams are tougher here in Europe than Ethiopia. But the difference is, here they test the knowledge of students with carefully designed exams.

  ReplyDelete
 13. © ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

  "ያወጣኹት ነው" የሚለው "የወጣ ነው" በሚል ቢተካ የበለጠ ክርስቲያናዊ ትህትና ያሳያል::

  እግዚያብሔር ይስጥልን

  ReplyDelete
 14. ዲያቆን ዳንኤል እስከዛሬ የዘራኸውን የእውቀት ዘር በጣም አደንቃለሁኝ፡፡ብዙዎቹንም በቀልድና በተረት በምሳሌ እያደረግህ ነው ያስተላለፍከው፡፡ይህም የሰውን ልጅ ውስብስብ አስቸጋሪ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ ነገር ነው፡፡በተለይም እኛ ኢትዮጵያውያን አንድ ጥፋትና ስህተት ፊት ለፊት ሲነገር ስለማንወድና ትንሽ የህፃንነት አይነት ባህሪ ስለሚያጠቃን ትችቶችን እያዋዙ መናገር ግድ የሚል ነው፡፡ ነገር ግን ፈረንጆች እንደሚሉት Assertiveness የሚባለው ነገር እንደ አንድ ሙሉ ስብእና ያለው ሰው ከውስጣችን ሊኖር ግድ ይላል፡፡ይህ Assertiveness የሚባለው ነገር ከጎደለን ደግሞ ከውስጣችን አንድ ወሳኝ የሆነ ነገር ጎድሎናል እንዲሁም አንድ የሆነ የስነ-ልቦና ችግር ውስጥ ነን ማለት ነው፡፡ስልጣን ላይ ያሉት አገዛዞች በተለይም ደርግና ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የስነ-ልቦና ችግር አስከትለውበታል፡፡ይህም ለስልጣናቸው መደላድል ሲሉ የውስጡን የሚሰማውን ስሜቱንና አመለካከቱን እንደ ልብ እንዳይገልፅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቱን እረግጥውት ነበር፡፡ያሁኑ ይባስ እንዲሉ ወያኔ ደግሞ ከደርግ በባሰ ከአፈናው በበለጠ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የብሄራዊ ስሜት ከማጣት ጋር ጭምር የስነ-ልቦና ወከባና አፈና ውስጥ ነው የከተቱት፡፡ስለዚህም ዛሬ ኢትዮጵያውያን Assertiveness የሚባለው ወሳኝ ነገር እጎደለን ነው የመጣው፡፡ይህንን ያልኩበት ዋና ምክንያትም እውነቱን አፍረጥርጠን ለመናገርና አካፋን አካፋ ለማለት ግልፅነትና ድፍረት ማለትም ፈረኝጆች እንደሚሉት Assertiveness አጥተናል ለማለት ነው፡፡አንድ ሰው ይህ ወሳኝ ነገር ማለትም Assertiveness ከጎደለው ደግሞ ሙሉ ስብእና ያለው ሰው ነው ለማለት ይከብዳል፡፡በአንድ ሀገር ውስጥ መሃይምም ቢሆን በታማኝነት የፖለቲካውን ስርዓት እስከደገፈና እስካገለገለ ድረስ ስልጣንና ሃላፊነት እንሰጣለን የሚል አመራር ባለበት ሀገር ውስጥና አንደዚህ አይነት አመራርም አንድን ሀገር ከ20 ዓመታት በላይ ሲገዛ ምን አይነት አጠቃላይ ብሄራዊ ስር የሰደደና የተስፋፋ ምስቅልቅልና ችግር እንደሚፈጠር ለመገመት ብዙም አይከብድም፡፡አዎ አቶ መለስ ናቸው አንድ ወቅት ላይ የኢህአዴግን ፖለቲካ በታማኝነት እስከደገፈና እስካገለገለ ድረስ ስልጣንና ሃላፊነት እንሰጣለን ያሉት፡፡ስለዚህም ዋናው የፖለቲካ ታማኝነት እንጂ እውቀትና ትምህርት በዚህ ስርዓት ብዙም ዋጋ ያለው ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡አቶ መለስ ይህንንም ብለው አላበቁም ከ1997 ምርጫ በኋላ ፓርቲያቸው ኢህአዴግ በእውቀትና በችሎታ ላይ በመመርኮዝ ሳይሆን በጥቅማጥቅምና በፖለቲካ ታማኝነት በመመርኮዝ ወደ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ የፓርቲ አባላትን አፍርቻለሁ አሉን፡፡አዎ ዛሬ የከፍተኛ ትምህርት እድል ለማግኘት አይደለም ማንኛውንም ጥቃቅን ስልጠናና ጥቅማጥቅም ለማግኘት ቢያንስ አገዛዙን የማይቃወም ሰው መሆን አለበት፡፡ላለፉት 20 ዓመታት ሀገሪቱ ስነ-ምግባር ያለውና በእውቀትና በትምህርት የሰለጠነ የሰው ሃይልና ዜጋ የሚፈራባት ሳይንስና ቴክኒሎጂ የሚስፋፋባትና እውነተኛ ስልጣኔና እድገት የሚካሄድባት ሳትሆን በነፃ-ገበያ ሽፋን አብዛኛውን የማፍያ ስራ የሆነ ተራ የውንብድና ቢዝነስ የሚሰራባትና እርካሽ ሸቀጥ ማራገፊያ ሀገር ለመሆን በቅታለች፡፡ዛሬ የሰለጠነው ዓለም የደረሰበት ያለው ደረጃ የደረሰው በዋናነት ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለመመስረትና ለማስፋፋት የሚያስችል እውቀትና ችሎታ ሊያዳብር የሚያስችል የሰው ሃይል ለመፍጠር በመቻሉ እንጂ በተራ የማፍያና የወንብድና የመርካቶ ወይንም ሌላ አይነት ተራ የቢዝነስ ስራ አይደለም፡፡ሌሎች ችግሮች እንዳሉ ሆነው የትምህርት ስርዓቱ ባብዛኛው እንደዚህ አይነት ደረጃ ባለ አሳፋሪና አሳዛኝ ደረጃ እንዲወደቅ የሆነውም በዋናነት ከስርዓቱ ተፈጥሯዊ ዝቅጠት የተነሳ ነው፡፡ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን በነፃ-ገበያ ሽፋን ባብዛኛው ለተራ ማፍያ የሆነ የውንብድና ባህሪ ያለው የቢዝነስ መስሪያነት ብቻ ነው እየተገለገለባት ነው ያለው፡፡ከአምሰት ዲግሪ አንድ ግሮሰሪ እየተባለ በሚቀለድበት ሀገር ውስጥ ይህ አይነት አጠቃላይ የሆነ ጥልቀትና ስፋት ያለው ማህበረሰባዊ የትውልድ ዝቅጠትና በተከታይም ያለ የስነ-ልቦና የማህበራዊ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስና ምስቅልቅል ቢፈጠር ምን ይደንቃል፡፡አቶ መለስና ወያኔ ላለፉት 20 ዓመታት እየፈጠሩና እያፈሩ ያሉት ምን አይነት ትውልድ ነው እረ?ምሁራኖቻችን ትምህርት እያስተማሩ ትውልድ እየቀረፁ ያሉት ከሆዳቸው ለሆዳቸው ነው ወይንስ ከልባቸውና ከአእምሯቸው ነው?አቶ መለስና ወያኔ እኮ ትምህርትን እየተጠቀሙበት ያለው ሀገርንና ትውልድን ለራሳቸው የስልጣን ህልውና ሲሉ ለመቆጣጠሪያነትና ለፖለቲካ መሳሪያነት እንጂ እውቀትን ጥበብንና ስልጣኔን ለትውልድና ለሀገር ለማስተላለፊያነት አይደለም፡፡ስለዚህም ምሁሩ ዛሬ የተኮላሸና ስለሀገሩና ትውልዱ ደንታ የሌለው እንዲሆን ነው እየተደረገ ያለው፡፡አቶ መለስና ወያኔ እንደ ጦርነት ስልታቸው በቆረጣና በከፋፍለህ ግዛው በሂደት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ የእያንዳንዳችንን የኑሮ ህልውናችንን መሰረት እያናጉትና እያጠፉት ስለሆነ ሁሉም በደመ-ነፍስ የራሱን በህይወት የመኖር ህልውና ለማስጠበቅ ሲል በተናጠል በየፊናው የሚባዝን የሚንቀዠቀዥና የሚቅበዘበዝ እየሆነ ነው ያለው፡፡በጋራ በአንድነት መንፈስ ስለ ጋራ ሀገራዊ መፃኢ እድልና አጀንዳ በጋራ ማውራት እንደ ህልም ወይንም እንደ ተረት ተረት እየተቆጠረ ነው፡፡የትምህርት ስርዓቱም የዚህ ውጤት ስለሆነ ብዙም የሚገርም ነገር አይሆንም ማለት ነው፡፡ብቻ ሀገርና ትውልድ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ እንደ ቀልድ እየጠፋ እንደሆነ መረዳት ግድ የሚለን ይመስለኛል፡፡ስለዚህም ሁል ጊዜ በተረት ተረት ብቻ ዙሪያ ጥምጥም ከምንዞር ይህንን ነባራዊ ግልፅ እውነታ ለመናገር ቢያንስ የተወሰነው Assertiveness ይኑረን፡፡
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. you thank you, please write more idea for the future, this is the truth. I am the teacher in one of University in Ethiopia the condition is like what you are saying, if you are loyal for Government what ever your grade and knowledge you can be Teacher and the Economic system at all in the country is unfair and never happen before in the country it is based on Blood and politics.
   sorry for this in the Country
   bye

   Delete
 15. እዚያ ከአንድ ፈተና በፊት ሦስትተመሳይ ፈተናዎችን አውጥቶ የተማሪዎችን ብቃት መለካት ነበረበት፡፡ ከዚያም አብዛኞቹየተሳሳቱባቸውን መርጦ እንደገና ማስተማር፣ በተለየ መንገድም ትምህርቱን ማቅረብ ነበረበት፡፡ ወደፈተና የሚገባው ቢያንስ ሰማንያ አምስት በመቶው ተማሪዎች ያወጣቸውን ሁሉንም ጥያቄዎችሲመልሷቸው ነው፡፡

  እኔ እንደማስታውሰው 1986 ዓ.ም በዳግማዊ ምኒልክ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ትምህርት ያስተምሩ የነበሩት በቅጽል ስማቸው ማስተር የሚባሉ መምህር ይህንን ተግባራዊ ያደርጉ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 16. ስንት ያገሬ ሰዎች ናቸው የትምህርት ጥማት እያለባቸው ወደ ከፍተኛ ተቋም እንዳይገቡ በ COC እገዳ የተጣለባቸው ማንም የሌላ አገር ዜጋ እየመጣ እየተማረ በአገራችን የመማር እድሉን ተነፍጎ COC አላለፋችሁም በማለት የብር መሰብሰቢያ ከሆነ ከርሞአል፡፡ እናመሰግላናለን ዳኒ

  ReplyDelete
 17. አንዳንዴኮ ከጥያቄዎች እና ከፈተናዎች የምንማረው የሽወዳ ጥበቦችን እንጂ ክሂሎት እና ዕውቀትን አይደለም፡፡ አንዳንድ ጥያቄ አውጭዎችም እንዴት ተማሪዎችን ልሸውዳቸው እችላለሁ? ይላሉ እንጂ እንዴት ዕውቀታቸውን ልመዝነው እችላለሁ? አይሉም፡፡ እንዲያውም እንደ አስማተኛ ፊልም ሸዋጅ ፈተና የሚያወጡ መምህራን በአንዳንድ ቦታዎች እንደ ታላቅነት መለኪያ ተወስዶ ሲሞገሱበት ይሰማል፡፡ ሲከበ ሩበትም ይታያል፡፡

  that is good idea daniel, God bless you.

  ReplyDelete
 18. ማራናታ ሃሳብህ ጥሩ ነው፡፡ አንተ ለማለት የፈለከው ክርስቲያን ማንኛውንም ስራ ሰርቶ ይህንን አደረኩ ማለት አይገባውም ነው ፡፡ አንድም የሚያወጡት ሌሎች ወይም ጋዜጠኞቹ ስለሆኑ እንዴት ‹‹ያወጣሁት ›› ትላላህ ነው፡፡

  ከአማርኛ አንፃር ስናየው እኔነትን የሚገልፅ ይመስላል ፡፡ በሃይማኖት ስንመለከተው ግን እንኳን ‹‹የዳንኤል እይታ›› መፅሐፍ ቅዱስም ምስጢርን እንጂ ዘይቤን አይጠነቅቅም፡፡ እራሱ ዳንኤል አቅሙ ኖሮት መፅሔቱን ቢያሳትም እንኳን ከራሱ የሆነ ነገር የለም፡፡ ውዳሴ ከንቱን ደግሞ ከልብ ነው መቃወም፡፡

  ReplyDelete
 19. Dear Dn. Daniel,
  This is very exciting view. And should be practiced in our educational system.
  While I was a student, all my teachers (Elementary to University) tried to taught me the techniques and tactics of passing exams apart from the actual knowledge and skill that is expected from that level. Fortunately, I joined back the University to be a teacher. So, now who was my model to be good teacher? I followed their method of teaching and evaluation to examine my students. I did the same with them. Hence, who is responsible for this, myself,or my teachers? I don't blame all my teachers, because though small in number, I had some teachers who examined us what they taught. But most of the teachers in all levels have been examining like this; they taught " Abebe ate powder" the exam says "from where this powder came?".
  Also now I have a chance to look the external world teaching system. This is quite different from us/ Ethiopian. I promised for myself to do accordingly up on my return.

  "Lets stand for our educational policy and system"

  ReplyDelete
 20. most of we Ethiopians rejoice by peoples failure that is why our teachers passes sleepless nights how to make tough exams to abuse their students.Long live Dani you are the one who is on the position to change our attitude.

  ReplyDelete
 21. የመምህርን ነገር ካነሳነው ብዙ ነገር ማለት ይቻላል፡፡ በእኛ አገር bridge occupation ነው የሚባለው እኔ ኬሚስትሪ መምህር ነበርኩ ሁኔታው ስለላማረኝ ፊልዴን ቀይሬ በመምህርነት ሠርቼ በማገኘው ደመወዝ ኮምፒውተር ሳይንስ ተማርኩ፡፡ 30 ዓመት ሰራን የሚሉትን ሳያቸው ምንም ምንም በመምህርነት እንድትቆይ የሚያደርግህ ነገር የላቸውም ፡፡ አንዳንዴ ሳስበው መምህር መሆን ያለበት ዐለም በቃኝ ያለ መሆን አለበት ሲጀምርም መምህራን እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ነበሩ፡፡ መምህርነት ከደሞዝ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከጥልቅ ፍላጎት ጋር የተገናኘ መሆን አለበት፡፡

  ReplyDelete
 22. ግርማ
  መምህር እና ሰይጣንኮ ምንም ሁለቱም ቢፈትኑ ሁለቱ ግን አንድ አይደሉም፡፡ .

  በዚህ ዙሪያ ስንት ማለት በተቻለ፡፡ ይነስም ይብዛ ብዙዎች ተጎድተናል፡፡ አሁንም እየተጎዱ ያሉ ብዙዎች ናቸዉ፡፡ በዚህ ምክንያት ተማሪዉና ቤተሰቡ፣ ወገንና ሀገር ሁሉም ሰለባዎች ሆነዋል፤ ይሆናሉም፡፡
  ፀጋዉን ያብዛልህ…!

  ReplyDelete
 23. I have the filling to be a teacher and did it but it is like being a slave.Specially when you teach at private school you have to full fill different things which is beyond your capacity.Then, no quality work is done.Everything will be a fake.Bro I like very much what you have posted , keep it up and God bless your keyboard.
  Thank you!!!

  ReplyDelete
 24. Dear Dn Danny
  Very nice observation. In fact it is being practiced in the TVET Program recently. You should make continuous assessment for more than 50% before final exam and if the student fails finally, there will be a remedial test of two chances before passing judgment- competent or not competent.

  ReplyDelete
 25. ሰላም ዳኒ:
  የሀገራችንን የመንጃ ፈቃድ ፈታኞች አስታወስከኝ አውቶብስ ማቆሚያ ላይ አቁም ይሉህና ወድቀሃል ይሉሃል መንጃ ፈቃድ ላለመስጠት የሚፈትኑ ይመስለኛል እያደናገሩኝ ስንት ጊዜ ጥለውኛል ለካስ የእጅ መንሻ ማቅረብ ነበረብኝ የሀገራችንን መንጃ ፈቃድ ፈታኞች አሰራርን በይበልጥ ያዘንኩበት በውጬ ሀገር ፈታኞች የተፈተንኩ ጊዜ ነው እግዚኦኦኦኦኦኦኦኦ አልኩኝ.....

  ReplyDelete
 26. «እንዲህ ብናደርግ ኖሮ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ስንቱን ለክብር እናበቃው ነበር» እያለ ይቆጫል ሁልጊዜ፡፡
  good sight but now a day even life for teachers is difficult and inputs for education is not satisfactory in such condition to think good teacher is difficult so the government should see and support life of teachers.
  thank you brother

  ReplyDelete
 27. ይህ አስተማሪ እና ሌሎችም መምህራን እራሳችውን በዚህ አርቲክል መነር ቢያዩት እና እራሳቸውን ቢጠይቁ እኔ አስተማሪ ነኝ ወይስ ስይጣን?ብለው::

  Mamush,MN

  ReplyDelete
 28. ስንት ያገሬ ሰዎች ናቸው የትምህርት ጥማት እያለባቸው ወደ ከፍተኛ ተቋም እንዳይገቡ በ COC እገዳ የተጣለባቸው ማንም የሌላ አገር ዜጋ እየመጣ እየተማረ በአገራችን የመማር እድሉን ተነፍጎ COC አላለፋችሁም በማለት የብር መሰብሰቢያ ከሆነ ከርሞአል፡፡ እናመሰግላናለን ዳኒ

  ReplyDelete
 29. It's true i have got somthing thanks!

  ReplyDelete
 30. Dear Daniel
  Our experience of yesterday regarding education is a hope for tomorrow.But,today we must work hard and challenge ourselves to move from one step to another.I think the purpose of education as Malcom Forbes said is"to replace an empty mind with an open one."
  This initial view of Daniel will serve us as stepping stone for the multiple challenges ahead of us.If corrupt politics plays a major role in rewarding printout Diplomas for those who can hardly read and write,then the problem is much more deeper than we think.I feel sorry for those intellectuals who are forced to join ethnic political parties in order to attain their higher education or work in collages and universities.
  I hope this forum will invite scholars of different walks of life from abroad and within Ethiopia.
  Best regards
  Woldemariam

  ReplyDelete
 31. just yo are definitely write.I am from bdu here in our university there are more complicated techniques of cheating students mark through down loaded questions & answers from abroad.GOD BLESS NOW ALL OF US.d/n melaku

  ReplyDelete