እጅግ ሞቃት የሆነ የበጋ ጊዜ ነበር፡፡ በአካባቢው ኃይለኛ ዝናብ አንዳንድ ጊዜም ነጎድጓድ እና መብረቅ እየቀላቀለ ይጥላል፡፡ ፀሐይ ብቻዋን ስትወጣ የአካባቢው ሰዎች ከየቤታቸው ይወጡና ለመንደርዋ ውበት ወደ ሰጣት የባሕሩ$ ዳርቻ ያመራሉ፡፡ ለአመል የምትሆን ብጢሌ ጨርቅ ገላቸው ላይ ጣል ያደርጉና አሸዋው ላይ ተዘርግተው የባሕሩን ነፋስ እና የፀሐይዋን ሙቀት ይኮመኩማሉ፡፡
ዛሬ ግን እንዲህ ማድረግ አልተቻለም፡፡ ዝናቡ ሌሊት ነው የጀመረው፡፡ አብረውት ነጎድጓድ እና መብረቅ ያጅቡታል፡፡ ጋብ አለ ሲባል ደግሞ ውሽንፍር ይነሣል፡፡ ባሕሩም በውሽንፍሩ ቀስቃሽነት ከሥሩ እየተነሣ ዳንግላስ ወደ የብሱ ይጋልባል፡፡ ከዚያም አረፋ ደፍቆ ለምድሪቱም የአክብሮት ስግደት ሰግዶ ይመለሳል፡፡
ከእኩለ ቀን በኋላ ዝናብ እና መብረቁ ቆመ፡፡ ነፋሱ ግን ባሕሩን ማሰገዱን አልተወም፡፡ አካባቢው በቅዝቃዜ ተሞልቶ መንደርተኞቹ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ከመውጣት ይልቅ እሳት እያነደዱ በየቤታቸው እንዲቀመጡ አደረጋቸው፡፡
አንዲት በዐሥርዮሽ ውስጥ ያለች ልጃገረድ ግን ጥቁር ካፖርቷን ለበሳ፣ ቦት ጫማዋንም ተጫምታ፣ ከነፋሱ ጋር እየታገለች ወደ ባሕሩ ዳርቻ ስትሄድ ታየች፡፡ ጃኬቷን አስወልቆ ለመውሰድ ከሚታገለው የባሕሩ ነፋስ ጋር በሁለት እጆቿ የጃኬቷን ጫፍ እና ጫፍ በመያዝ እየተፎካከረች በጽናት ወደ ባሕሩ ዳር ታመራ ነበር፡፡ አልፎ አልፎ ነፋሱ በፀሐይዋ ሲሸነፍ ቀና ብላ የምስጋና ያህል እያየቻት ባሕሩ ዳር ዘለቀች፡፡
በባሕሩ ዳርቻ ስትጓዝ አካባቢው በቀያይ ነገሮች ተሞልቶ አየች፡፡ በነፋሱ የተገፋው ባሕር እንድ ጋላቢ እየሰገረ መጥቶ የብሱ ላይ ሰግዶ ሲመለስ እንድ ግብር ኮከብማ ዐሦችን እየተፋ መሬት ላይ ጥሏቸው ይሸሽ ነበር፡፡ ከሌሊት ጀምሮ እዚያ ዳርቻ የተተፉት ዐሦች አልፎ አልፎ በሚመጣው የባሕሩ ውኃ ነፍስ እየዘሩ ለመኖር ሲታገሉ ቆዩ፡፡ አሁን ግን ዝናቡም አቆመ፡፡ ነፋሱም ጋብ እያለ ነው፡፡ የባሕሩ ውኃም ወደ ዳርቻው መገንፈሉን ትቷል፡፡ ፀሐይዋ ደግሞ እየጋለች በመውጣት ላይ ናት፡፡ እናም ዐሦቹ ከመኖር ወደ አለመኖር ሊሰናበቱ ነው፡፡
ያቺ ለግላጋ ልጃገረድ ይህንን ነበር ያየቺው፡፡ አሁን እዚህ አካባቢ ትልልቅ ሰዎች ቢኖሩ ኖሮ፣ ስለ ዓሣ የሚያውቁ ሰዎች ቢኖሩ ኖሮ፣ ልምድ ያላቸው ሰዎች ቢኖሩ ኖሮ፣ የባሕሩ አጽጂዎች ቢኖሩ ኖሮ እያለች አንዳች ተአምር ጠበቀች፡፡ ዓሣዎቹን ማዳን የሚችል ዐቅም ያለው ፈለገች፡፡ ግን ከእርሷ ሌላ በአካባቢው ለጊዜው ማንም አልነበረም፡፡
ድንገት አንዳች ነገር መጣላት እና ጎንበስ አለች፡፡ ከዚህ በፊት በሕይወት ያለ ኮከብማ ዐሣ በእጇ ነክታ አታውቅም፡፡ አንዱን ኮከብማ ዐሣ አንሥታ ወርውራ ወደ ባሕሩ መለሰቺው፡፡ ባሕሩ ላይ ሲደርስ ዋኝቶ ሲሰምጥ አየቺው፡፡ እናም ያደረገቺው ነገር ትክክል መሆኑን አረጋገጠች፡፡ ቀጠለቺና ሌላውን፣ ሌላውን፣ ሌላውን፣ ሌላውን፣ ጎንበስ ቀና፣ ጎንበስ ቀና፣ ጎንበስ ቀና እያለች ዐሣዎቹን ወደ ባሕራቸው መመለስ ቀጠለች፡፡ እየደከማት፤ ጫን ጫንም እየተነፈሰች ቀጠለች፡፡
እርሷ ጎንበስ ቀና እያለች ኮከብማ ዐሦችን ወደ ባሕሩ ስትመልስ በአጠገቧ የነፋሱን እና የዝናቡን መቆም ተከትሎ የመጣ አንድ ሰው ገርሞት እየተመለከታት መሆኑን አላወቀቺም ነበር፡፡ ሌላም ሰው ተከተለው፣ ሌላም መጣ፣ ሌላም፣ ሌላም፣ ሌላም፡፡ አያሌ ሰዎች ተሰብስበው ለግላጋዋ ልጃገረድ የምታደርገውን ይመለከቷት ነበር፡፡ እርሷን ለማገዝ የፈለገ አንድም ሰው አልነበረም፡፡ እርስ በርሳቸው እየተያዩ የምትሠ ራውን ብቻ ይመለከቱ ነበር፡፡
በዚህ መካከል አንዱ «ይቺ ልጅ ዕብድ መሆን አለባት» አለ፡፡
«ምን ጥርጠር አለው» አለ ደግሞ ሌላው
«ዕብድ ባትሆንማ በዚህ ብርድ በሺ የሚቆጠሩ ዐሣዎችን እያነሣች ትወረውር ነበር» ሌላው አጽንዖት ሰጠ፡፡
«አሁን እርሷኮ አዲስ ነገር ያየች መስሏት ነው፡፡ በየበጋው ኮከብማ ዓሣዎችን ባሕሩ እያመጣ መዘርገፉ የተለመደ ነው፡፡ በያመቱ ስንት እና ስንት ይሞታሉ፡፡ የተለመደ ነው፡፡» ሌላው ታሪክ ጨመረበት፡፡
«ደግሞስ ቢሆን»አለ ሌላው «እነዚህን በሺዎች የሚቆጠሩ ኮከብማ ዐሣዎች ለቅማ እንዴት ትጨርሳለች፡፡ ለቅማ ከመጨረሷ በፊት እርሷ ደክሟት ትዘረጋለች፡፡»
«አሁን እርሷ ዐሥር ዐሣዎችን አዳነች አላዳነች ምን ለውጥ ይመጣል?» ሌላው ጠየቀ፡፡
«መንደርተኞቹ ወሬ እየተቀባበሉ ዳርቻውን ሞሉት፡፡ ልጂቱን የሚረዳት አልነበረም፡፡ አያሌ ትቺቶች እና ስድቦች ግን ይወርዱባት ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ክብ እየሠሩ ይወራረዱ ነበር፡፡ አንዳንዶቹም ስለ ኮከብማ ዐሣ የተማሩትን እየተነተኑ ነበር፡፡ ሌሎቹም በሌሎች አካባቢዎች በኮከብማ ዐሦች ላይ ስለደረሱ ጉዳቶች የሰሙትን በመግለጥ ላይ ነበሩ፡፡
ልክ በዚህ ሰዓት በአካባቢው ሰዎች ዘንድ እንደ ጥበበኛ እና ዐዋቂ የሚታይ አንድ ሰው መጣ፡፡ እጆቹን ደረቱ ላይ አጣጥፎ ያቺ ለግላጋ ወጣት ስታደርገው የነበረውን ሁሉ በዐጽንዖት ተመለከተ፡፡ ከዚያም ወደ ልጂቱ በቀስታ አመራና «ትንሿ ልጅ» ሲል ጠራት፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ ቀና ብላ አካባቢዋን አየቺው፡፡ ዳርቻውን መንደርተኞቹ ሞልተውታል፡፡ ትቺቱን እና ስድቡን፣ ሃሳቡን እና አስተያየቱን ሰማቺው፡፡ ሰውዬውም ወደ እርሷ ደረሰ፡፡
«ልጄ በሺዎች የሚቆጠሩ ኮከብማ ዐሣዎች በባሕሩ ውኃ ታጥበው በዳርቻው ላይ ተዘርግተው እያየሽ እንዴት ለውጥ የማያመጣ ሥራ ትሠሪያለሽ?» ሲል ጠየቃት፡፡ የከበቧት ሁሉ አንገታቸውን በስምምነት ነቀነቁ፡
«ምናለ አጉል ድካምሸን ትተሽ እንደ ጓደኞችሽ ብትጫወቺ» አለና መከራት፡፡
ሞቋታል፣ ደክሟታል፣ እናም ዕንባ ዕንባ አላት፡፡ ያንን ሰው ትኩር ብላ አየቺው፤ ከዚያም የከበቧትን ሁሉ ተመለከተቻቸው፡፡ ድንገት ሁሉም አንድ ጊዜ እንደ ብራቅ ሳቁባት፡፡
«አሁን አንቺ ምን ለውጥ አመጣለሁ ብለሽ ነው?» አላት ዐዋቂው ሰው፡፡
ሁሉም ጸጥ ብለው ምላሿን መጠባበቅ ያዙ፡፡
ምናልባት እርሱ እውነት ይሆን ይሆን? ምናልባትም እነዚህ ሰዎች እውነታቸውን ይሆን? ይህንን ያህል ሰዓት መድከሜ ምንም ለውጥ አያመጣ ይሆን? ከእኔ በፊት እንደዚህ ደክመው ሰዎች ምንም ለውጥ አላመጡ ይሆን? ሰዎች የሳቁት እነዚያ ለውጥ ሳያመጡ እኔ እንዴት ለውጥ ላመጣ እችላለሁ ብለው ይሆን? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ያልገባቸውን እንዴት እኔ ብቻ ይገባኛል? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ያልተቀበሉት ነገርስ እንዴት ትክክል ይሆናል? ይህ ዐዋቂ ሰው ነው፡፡ መንደርተኞቹም ምክር የሚጠይቁት እርሱን ነው፡፡ ይህ ዐዋቂ ሰው ከእኔ የተሻለ ያውቃል፡፡ ታድያ እንዴት ከእርሱ እበልጣለሁ ብዬ እቀጥላለሁ? ታሰላስል ጀመር፡፡
ቀና ብላ አየች፡፡ ኮከብማ ዐሣዎች ገና ዳርቻውን እንደሞሉት ናቸው፡፡ ደክሟታል፡፡ ርቧታል፡፡ ክንዶቿ ዝለዋል፡፡ ምን ያህል ሰዓት ሊወስድባት እንደሚችል ስታስበው ደከማት፡፡ እናም በእጇ ይዛው የነበረውን ኮከብማ ዓሣ ጣለቺውና ከአሸዋው አካባቢ መውጣት ጀመረች፡፡
«ትክክል» አለ ዐዋቂው፡፡ «ሂጅና ተጫወቺ፡፡ ለውጥ ላታመጭ ያውም ባንቺ ዕውቀት እና ዐቅም መልፋት የለብሺም» አላት እየተከተለ፡፡
ስትሠራ ያላጨበጨቡላት የአካባቢው ሰዎች ርግፍ አድርጋ ትታ ተሸንፋ ስትወጣ አጨበጨቡላት፡፡
ይሄኔ መንገዷን ገታ አድርጋ ቆመች፡፡ «ተሸነፍኩ ማለት ነው?» ብላ አሰበቺ፡፡ «እኔ የምችለውን አደርጋለሁ፡፡ የምችለውን የማድረግ እንጂ የሚያስፈልገውን የማድረግ ግዴታ የለብኝም» አለቺ፡፡ ይሄኔ የዛለው ክንዷ ሲበረታ፣ የተጫናት ድካም እንደ ቅርፊት ሲቀረፋ፣ የሞተው ሞራል እንደ አልዓዛር ሲነሣ ተሰማት፡፡
ከዚያም ወደ ኋላዋ ተመለሰቺና አንደኛውን ኮከብማ ዐሣ አነሣቺው፡፡ መንደርተኞቹም ገርሟቸው ያይዋት ነበር፡፡ አንሥታም አልቀረች ወረወረቺው፡፡ በባሕሩ ውኃ ላይ ዋኝቶ ሲጓዝ «ይኼው ቢያንስ ለዚህ ዓሣ ለውጥ አመጣሁ» ብላ ጮኸች፡፡ ያኔ አንድ በርሷው እድሜ ያለ ወጣት ከከበቡት ሰዎች መካከል ወጥቶ አንድ ኮከብማ ዓሣ አነሣ፣ ወረወረ፡፡ ዓሣው ባሕሩ ውስጥ ዲንቁል ብሎ ሲገባ «እኔም ለዚህ ዓሣ ለውጥ አመጣሁ» ብሎ ጮኸ፡፡
ሌላም ሰው መጣና እርሱም ወረወረ፡፡ የዓሣውን ወደ ሕይወት መመለስ ሲመለከትም «ይኼው እኔም ለውጥ አመጣሁ» አለ፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ወደ ታች ወረዱና መወርወር ጀመሩ፡፡ እነርሱም «እኔም ለውጥ አመጣሁ» እያሉ ይጮኹ ነበረ፡፡
ይመለከቷት የነበሩት ሁሉ ወደ እርሷ እየመጡ ዓሣዎቹን በመወርወር «እኔም ለውጥ አመጣሁ» እያሉ ይጮኹ ነበር፡፡
የአካባቢው መልክ ተቀየረ፡፡ የሚታየው ጎንበስ ቀና እያሉ ኮከብማ ዐሣዎችን ወደ ባሕሩ የሚመልሱ ሰዎች ነበሩ፡፡ የሚሰማውም «እኔም ለውጥ አመጣሁ» የሚሉ ድምፆች ነበሩ፡፡
አንድ ሰዓት አልፈጀም፡፡ ዐሣዎቹ ሁሉ ወደ ባሕራቸው ተመለሱ፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም ተሰበሰቡና
«በአንድ ላይ ሁላችንም ለውጥ አመጣን» ሲሉ በደስታ ጮኹ፡፡
ከብዙ ዘመናት በኋላ በተመሳሳይ እድሜ ላይ ያለች ከሌላ ቦታ የመጣች ልጃገረድ በበጋው የዝናብ ወቅት ወደ ባሕሩ ወጥታ ነበር፡፡ በባሕሩ ዳርቻ አሸዋ ላይ አያሌ ኮከብማ ዐሣዎች ወጥተው አየች፡፡ የሚገርመው ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዓሣዎቹን ወደ ባሕሩ በመመለስ ተግባር ተጠምደው ነበር፡፡
እጅግ ገርሟት በአካባቢው የነበሩትን አንድ አዛውንት «እንዴት እነዚህ ሁሉ ሰዎች በዚህ ሥራ ላይ ተጠመዱ? ማንስ አሠማራቸው?» ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
አዛውንቱም «ከብዙ ዘመናት በፊት በዚህ ወቅት አንዲት ልጃገረድ ወደ ባሕሩ መጥታ ዐሣዎቸን አየቻቸው፡፡ እርሷም ቆማ ከመመልከት ይልቅ የምትችለውን ማድረግ ፈለገቺና እያነሣች ወደ ባሕሩ መለሰቻቸው፡፡ እኛ በመጀመርያ ተቸናት፣ ወቀስናት፣ ሳቅንባት፣ ቀለድንባት፣ አንጓጠጥናት፣ ምንም አታመጣም ብለንም አጣጣልናት፡፡ በኋላ ግን በሥራዋ አሳመነቺን፡፡ መጀመርያ አንድ ልጅ ተከተላት በኋላም ብዙዎች ተከተሏት፡፡ ያም ባህል ሆኖ በየዓመቱ ሁላቺንም እየወጣን «እኔም ለውጥ አመጣለሁ» እያልን ዓሣዎቹን ወደ ባሕሩ እንመልሳለን፡፡ በዚያ ጊዜ ልጅ ሆኖ እርሷን የተከተላትም የመጀመርያ ሰው ዛሬ ሽማግሌ ሆኖ ላንቺ ታሪኩን እየነገረሽ ነው» አሏት፡፡
"the star thrower( Loren c. eiseley, 2004)" k¸lW m{/F t²Mì yttr¯mÝÝ
Thanks God you well come back Dani
ReplyDeleteenenka holachenem madreg yemenchelewen enaderg.
ReplyDeleteDani enamesegnhalen Ewunet new gin eko akaten, gulbetachin tebrekereke yabatochachi lijoch aydelenm, hulachinme dikala honen keyet endetdekeln enkuan yemanawuk, abat alba dikaloch
Deleteawen negeru tejemere yetegber gizew awen new belu hulachenm yeminchelewen lemadreg enenesa
ReplyDeleteAnd lomi leand sew shekmu leamsa sew getu!
ReplyDeleteGOBEZ ENREDADA BENATACHIHU....THANK YOU DANI
ReplyDelete“ድልድይ ገንቢዎች” ያልካቸው ሰዎች ሊሄዱበት የሚገባው መንገድ ይመስለኛል
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteActually, change means that what was before wasn't perfect and yet people want things better. Because things are the way they are, things will not stay they are. For that matter, change is not an easy task, it is rather a hard work. Any change, even a change for the better, is always accompanied by drawbacks and discomforts.
All changes, even the most longed for, have their melancholy; for what we leave behind us is part of ourselves; we must die to one life before we can enter another. I would like to emphasized that everyone thinks changing the world, but no one thinks of changing himself.
One must pray like:" God grant me the serenity to accept the things I can not change, the courage to change the things I can, and the wisdom to know the difference."
Mark Twain stated that, " a round man can not be expected to fit in a square hole right away. He must have time to modify his shape. He further acclaimed that, " a person who won't read has no advantage over one who can't read."
ወዳጆቼ: ሆይ: እንኳን: ለበዓለ: ጥምቀቱ: በሰላም: አደረችሣሁ::እግዚአብሄር: ኢትዮዽያችንን: ይጠብቅ:ይባርክ::
thank you Dani.
ReplyDeleteWelcome back Dani!!!!
ReplyDeleteDn. Daniel
ReplyDeleteWhat happened to the visitation of holly places? One time you started going to holly places like Malta, and Egypt and write about it. Sometimes with pictures, and videos. But lately, you just write things like this which we really can get from any libraries and read it for ourselves. Please return to the old you. This is not you at all. Be like an Ethiopian Orthodox Tewahedo Deacon. I'm not saying you are doing anything bad, but I just missid your old teachings. Atlanta.
"እኔም ለውጥ አመጣለሁ"
ReplyDelete"ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረቻት"እንዲሉ ታናሽዋ ብላቴና ለአዋቂዎቹ አሳወቀቻቸው!
"ለላም ቀንዷ አይከብዳትም" አለች ሴትዮዋ እውነቷን እኮ ነው፤
"እኔም ለውጥ አመጣለሁ" ብለን ለሃገር እድገት ብንነሳ የራሳችን ሸክም አይከብደንም።
"ምክርስ ከድሃ ነበርሽ ማን ቢሰማሽ" ትላለች እናቴ!
የፀጋ ስጦታህ ይብዛ ወንድም አለም!!!
"እኔም ለውጥ አመጣለሁ"
ReplyDelete"ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረቻት"እንዲሉ ታናሽዋ ብላቴና ለአዋቂዎቹ አሳወቀቻቸው!
"ለላም ቀንዷ አይከብዳትም" አለች ሴትዮዋ እውነቷን እኮ ነው፤
"እኔም ለውጥ አመጣለሁ" ብለን ለሃገር እድገት ብንነሳ የራሳችን ሸክም አይከብደንም።
ምክርስ ከድሃ ነበርሽ ማን ቢሰማሽ ትላለች እናቴ!
የፀጋ ስጦታህ ይብዛ ወንድም አለም!!!
ልብ የሚሞላ ጽሁፍ!!
ReplyDelete«እኔ የምችለውን አደርጋለሁ፡፡ የምችለውን የማድረግ እንጂ የሚያስፈልገውን የማድረግ ግዴታ የለብኝም» አለቺ፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ
በጣም ይገማል «ለአንድ ሺ ኪሎሜትር ለመጎዝ መነሻው አንድ እርምጃ ነው» ያሉት ቻይናውያን እኛስ............?
ReplyDeleteGood job!!!
ReplyDeleteልብ ያለው ልብ ይበል ከዚህ በላይ ምንም ሊባል አይቻልም
ReplyDeleteስሚ ልቦናን ይስጠን እባኲችሁ የእግዚዓብሄር ቤተሰቦች
እናስተውል፡፡
Like the people in the story most of us are doubtful that a little things we could do if it makes any difference. I think that is definitely our short coming, and I think most of all it is just the reflection of our luck of faith. However, with Our Holy Mother help I hope we will have a wisdom to believe and start walking a little step and leave the rest to almighty God. Dear Dn. Daniel thank you so much for posting this wonderful article. I always love the way you get your point across.
ReplyDeleteGod bless you !
ውብ ነው!የፅሁፎችህ መልዕክቶች በብዛት የሰብዕና መሰረት ቁፋሮ ላይ ያተኮሩ ናቸውና
ReplyDeleteይብለ ያስብላል: ሆኖም እኔ የጫማ ቁጥር ስጠየቅ...ስለታረደው በሬ መናገር አይሆንልኝም:'.ያለውን የብዕር ሰው ምልከታ' ከዘመነኛው'ትውልድ ጋር ብትመዝነው
መልካም ነው: ብዕርህ አትንጠፍ ብራናው አይጎርብጥ በርታ: ዳን.ዳንኤል::ምኞቴ
ብዙነህ@ፍሎሪዳ ጫካ
ዲ.ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ መሆን እንዲህ ነው በማህበራዊ ሳይንሱ ዘርፍ ሙያዊ ግዴታህን እየተወጣህ እንደሆነ ሁሉ በክህነቱም ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋቱን ቸል አለማለትህ ሊያስመሰግንህ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ ለኛም ከበረከቱ ይክፈለን!!
ReplyDeleteTo the person from Atlanta,
ReplyDeleteI think you are living in a better condition that you did not have time to see and know what is going on in Ethiopia. By the way, if the case is so, I am really sorry for you, and I will tell you that you are so selfish that you only care about your comfort while many Ethiopians are desperately struggling for some little hope, just hope for living. Ethiopia needs more people like Dn.Daniel to show us the way out from the darkness, to give us hope that we can contribute to the change Ethiopia strives to achieve. Plz ... we have enough obstacles in our way, don't be a plus. Dn.Daniel move on, go on, pretty soon you will see Ethiopia changing.
Thank you .
God Bless Ethiopia
I love it. very Nice.
ReplyDeleteIf everyone of us have willingness to do sth. relevant, we all can do bring change.
ReplyDeleteTHANK YOU DANI. THE ALMIGHTY BLESS YOU FOR YOUR RELEVANT MESSAGES.
Dani i like you writing such kind of articles too .it is a guiding one but we all are sleeping may GOD the allmighty give peace & wealth to ethiopian poors .Ethiopians are not lazy people by the way but this tyrant melese zenawi & his followers are dumping us to absolute poverty.how could the poor bring change ???he is dying by the government bullet if try to strugle for change.any how if melese & his followrs have access to read this site this message will guide them.for we poors, we can cry to GOD and only GOD!!!!
ReplyDeleteTHANK YOU DANI .
ReplyDeleteGOD BLESS ETHIOPIA AND ETHIOPIAN!!
thank you, May God be with you ALWAYS!!
ReplyDeleteበእዉነት ለዉጥ አመጣለሁ፡፡ ሀሳቤን ወደ ተግባር ሥቀይር፣ ተመልካች ሳልሆን የቅን አሳቢዎችና የፋና ወጊዎች ተባባሪ ስሆን፣ ባለራእይ ሆኜ አሁኑኑ ስጀምር . . እኔም ለዉጥ አመጣለሁ !
ReplyDeleteከባዱ ነገር "እኔም ለውጥ አመጣለሁ" ብሎ ማሰቡ ነው። ከዚያ በኃላማ......
ReplyDeletedase yelale
ReplyDeletelawete
ReplyDelete«እኔ የምችለውን አደርጋለሁ፡፡ የምችለውን የማድረግ እንጂ የሚያስፈልገውን የማድረግ ግዴታ የለብኝም»
DeleteWow Dn.Daniel it is a very wonderful article.And also a good lesson for me. Thank you.
ReplyDeleteሁልጊዜ ከእኛ የሚጠበቅብንን እናድርግ ተከታየ አናጣም ብናጣም እኛ የድርሻችንን አድርገናልና ህሌናችን ንጹህ ነው
ReplyDelete