Thursday, January 5, 2012

«ድንጋይ ፈላጮች»

click here for pdf 
አንድ ጥበብ አሳሽ ጥበብን ፍለጋ በየሀገሩ ይዞር ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ አንድ መንደር ሲደርስ ሰዎች ድንጋይ ሲፈልጡ ተመለከተ፡፡ ቀና ብሎ ቢያይ በአካባቢው ምንም የሚገነባ ነገር የለም፡፡
 
ወደ አንዱ ድንጋይ ፈላጭ ተጠግቶ «እባክህ ወዳጄ እኔ ለአካባቢው አዲስ በመሆኔ አንድ ነገር ልጠይቅህ ፈለግኩ፣ ለመሆኑ ምን እያደረጋችሁ ነው?»አለው፡፡ ያም ድንጋይ ፈላጭ «ወንድሜ የማደርገው ነገርኮ ግልጽ ነው፤ አንተም ታየዋለህ፤ ድንጋይ እየፈለጥኩ ነዋ»አለው፡፡ ያ ጥበብ አሳሽ ከዚያ እልፍ አለ፡፡ ወደ ሁለተኛውም ሰው ቀረበ፡፡ «ወዳጄ ለሀገሩ እንግዳ ለሰው ባዳ ነኝ፡፡ እባከህ ምን እየሠራችሁ እንደሆነ ንገረኝ?»አለው፡፡ ያም ድንጋይ ፈላጭ «ወዳጄ እኔ የዕለት እንጀራዬን ለማግኘት እየደከምኩ ነው፡፡ ይኼው ነው» ሲል መለሰለት፡፡

ጥበብ አሳሹ አንገቱን ነቅንቆ ወደ ሦስተኛው ፈላጭ ሄደ፡፡ እዚያም ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፈላጩ ቀና አለ፡፡ መፍለጫውንም ተደግፎ ቆመ፡፡ ከዚያም «እይውልህ ወዳጄ እኔ ካቴድራል እየሠራሁ ነው» አለው፡፡ ያን ጊዜም «አሁን መልሱን አገኘሁት» ብሎ ሄደ ይባላል፡፡

ዓለምን የሚለውጡት እነማን ናቸው? ችግርን የሚያሸንፉት እነማን ናቸው? ሀገርን የሚያሳድጉት እነማን ናቸው? ታላቅ ሥራ የሚሠሩት እነማን ናቸው?ድንጋይ ሲፈልጡ ካቴድራል እየገነቡ መሆኑን የሚያስቡ አይደሉምን?መሥመር ሲሠሩ ሥዕሉ የሚታያቸው አይደሉምን?ሊጡን ሲያቦኩ ዳቦው፣ ሽንኩርቱን ሲልጡ ወጡ፣ ፊደል ሲጥሉ መጽሐፉ፣ በሬ ሲጠምዱ ብልጽግናው፣ ግሬደሩን ሲጨብጡ ጎዳናው የሚታያቸው አይደሉምን?

ሦስቱም ሰዎች በተመሳሳይ ሥራ ላይ ተጠመደዋል፤ ሦስቱም ሰዎች ድካማቸው ተመጣጣኝ ነው፤ ሦስቱም ሰዎች የሚከፈላቸው አንድ ዓይነት ክፍያ ነው፤ ሦስቱም ሰዎች የያዙት መፍለጫ አንድ ዓይነት ነው፡፡ ሦስቱም ሰዎች በቀን የሚሠሩት እኩል ይሆን ይሆናል፡፡ ሦስቱን የለያቸው ግባቸው ነው፣ ርእየታቸው ነው፣ ሥዕላቸው ነው፡፡ አንዱ እጆቹ የሚሠሩትን እንጂ ሥራው የሚያመጣውን ውጤት አያውቅም፡፡ አንዱ ሥራው የሚያስገኝለትን ዕለታዊ ገቢ እንጂ ሥራው የሚፈጥረውን ትልቁን ሥዕል አያውቀውም፡፡ አንዱ ግን የሚያመጣውን ለውጥ እያሰበ ለትልቁ ሥዕል ነበር የሚሠራው፡፡

ለውጥ የሚመጣውኮ በዘመናዊ መሣርያ በመሥራት፣ በቂ በጀት በመመደብ፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል በመቅጠር፣ የቢሮ ወንበር እና ጠረጲዛ በማሣመር፣ አይደለም፡፡ እነዚህ ሁሉ አጋዦች እንጂ አንቀሳቃሾች አይደሉም፡፡ ለውጥ የሚመጣው ለምንድን ነው የምሠራው? ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ በመመለስ ነው፡፡

ምንም እንኳን በድካም፣ በክፍያ እና በመሣርያ አንድ ቢሆኑም በርካታ ግን ይለያያሉ፡፡ በርካታ ብቻ ሳይሆን በጥራትም ይለያያሉ፡፡ እነዚያ የዕለቱን ብቻ እያሰቡ ይሠራሉ፡፡ ይኼ ግን ትልቁን ሥዕል እያሰበ ለትልቁ ሥዕል የሚሆን ነገር ይሠራል፡፡ እነርሱ ለዕለት እንጀራ የሚሆን ምን ያህል ድንጋይ ፈለጥን?ብለው ይጠየቃሉ፡፡ እርሱ ግን ለካቴድራሉ የሚሆን ምን ያህል ድንጋይ አዘጋጀሁ? ብሎ ይጠይቃል፡፡ ለእነዚያ የዕለቱ ድንጋይ ተፈልጦ ሲያልቅ ሥራቸውን ይጨርሳሉ፡፡ እርሱ ግን ካቴድራሉ እስኪጠናቀቅ ሥራው አያልቅም፡፡

በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየንግዱ ሥፍራ፣ በየግል ደርጅቱ፣ በየትምህርት ቤቱ፣ በየማኅበራቱ፣ በየፓርቲዎቹ፣ በየርዳታ ደርጅቶቹ፣ በየሕክምና ተቋማቱ፣ በየግል ኑሯችንም እነዚህ ሦስቱ ሰዎች አሉ፡፡

ሥራቸውን ለደመወዙ ብቻ የሚሠሩ አሉ፡፡ የሚማሩትም ሆነ የሚሠሩት ደመወዙን ብቻ አስበው ነው፡፡ የሥራ ዝርዝራቸውን፣ ቅጣት እና ሽልማታቸውን፣ ብቻ አይተው ነው፡፡ ሥራው ለሀገር እና ለወገን የሚያመጣውን ትልቅ ሥዕል አያስቡትም አያውቁትምም፡፡ እነዚህ ካቴድራል ገንቢዎች አይደሉም፡፡ ድንጋይ ፈላጮች ብቻ ናቸው፡፡ የክፍል ተማሪዎቹን ሲያስተምር አስተምሮ እንጀራ ለመብላት ሲል ብቻ የሚያስተምር መምህር የዘወትር ጭንቀቱ የደመወዝ ቀን መቼ ነው? የሚለው ጥያቄ ብቻ ነው፡፡

እርሱ አስተማሪ አይደለም ተናጋሪ ብቻ ነው፡፡ ለልጆቹ የታዘዘውን ይነግራቸዋል፡፡ አላስተማረም እንዳይባል፣ ሥራውንም እንዳያጣ፣ ግዴታውም ስለሆነ፣ ቅጣትም ስለሚመጣበት ብቻ ይነግራቸዋል እንጂ አያስተምራቸውም፡፡ ለምን ያስተምራቸዋል? እርሱኮ ትልቁ ሥዕል የለውም፡፡ አስተማሪ ብቻ እንጂ አገር ቀያሪ፣ ለውጥ አምጭ፣ ካቴድራል ገንቢ አድርጎ ራሱን አያየውም፡፡ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ በዚያች ክፍል ተማሪዎች እንደሚወሰን አያስብም፡፡

በየቢሮው ድንጋይ ፈላጮችን ታውቋቸዋላችሁኮ፡፡ እነርሱ የተሰጠቻቸውን ሥራ ከመሥራት ያለፈ ምንም የሚያውቁት ነገር የላቸውም፡፡ ጸሐፊዋ ትጽፋለች፣ መዝገብ ቤቱ ዶክመንት ያስቀምጣል፣ ባለ ማኅተሙ ማኅተም ይረግጣል፣ ገንዘብ ቤቷ ገንዘብ ታወጣለች ታስገባለች፣ ኃላፊው ይፈርማል፣ ጥበቃው ይፈትሻል፣ ተላላኪው ይወጣል ይወርዳል፣ ሾፌሩ ይሄዳል ይመጣል፣ የመስክ ሠራተኛው ተራራ ይወጣል ይወርዳል፤ የሚሰበሰበው ይሰበሰባል፣ የሚበተነው ይበተናል፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ድንጋይ መፍለጣቸውን እንጂ ለምን እንደሚፈልጡ አያውቁትም፡፡ አገር እያሳደጉ መሆኑን፣ ለውጥ እያመጡ መሆኑን፣ ታሪክ እየሠሩ መሆኑን፣ አይረዱትም፡፡

እናም ለእነርሱ ኮምፒውተር አይሠራም ብሎ መቀመጥ አሳማኝ ምክንያት ነው፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ኮምፒውተር አይሠራም፤ አይሠራም፡፡ ኮምፒውተሩ ሲሠራ የሚያመጡትን ለውጥ ስለማያውቁት ኮምፒውተሩ ሲቆምም የሚያስከትለውን ችግር አይረዱትም፡፡ እነርሱ ድንጋይ ፈላጮች እንጂ ካቴድራል ገንቢዎች አይደሉም፡፡ እነርሱ ሀገሪቱ ስላላደገችበት ምክንያት ተጠያቂ ነን ብለው አያስቡም፡፡ እነርሱ ያ ደብዳቤ ለምን ወጭ እንዳልተደረገ ብቻ ነው የሚጠየቁት፡፡ ለርሱ ደግሞ በቂ መልስ አላቸው፡፡ ኮምፒውተሩ አይሠራም፡፡

እኔን አይመለከትም፡፡ የተቀመጥኩት ይህንን ልሠራ አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ እኔ አልጠየቅም፡፡ የሚሉ አባባሎች ሁሉ የድንጋይ ፈላጮች መልሶች ናቸው፡፡ ድንጋይ ፈላጮች እነርሱ ምን እየሠሩ እንደሆነ እንጂ በአካባቢያቸው ምን እየተሠራ እንደሆነ አያውቁም፡፡ አንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ እንኳን ሆነው ከእነርሱ ጎን ያለው ክፍል ምን እንደሚሠራ አይረዱም፡፡ ለመረዳትም አይፈልጉም፡፡ ይህ ሥራቸው አይደለማ፡፡

በየቢሮው ግድግዳ ላይ አንድ የሚገርም ማስታወቂያ ታያላችሁ፡፡ «ከቢሮ ስትወጡ መብራት ማጠፋትዎን ይመልከቱ» ይላል፡፡ ይህንን ማስታወቂያ የሚለጥፉት የመረራቸው የአስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍሎች ናቸው፡፡ በየቢሮው ያሉት ወገኖች ይህንን ለማሰብ ማስታወቂያ ያስፈለጋቸው ለምንድን ነው? በቃ ለእነርሱ ሥራቸው አይደለማ፡፡ የመብራት መብራት እና መጥፋት ስለሚያስከትለው ሀገራዊ ወጭ እና ቁጠባ ማሰብ የለባቸውማ፡፡ እነርሱ ድንጋይ ፈላጮች እንጂ ካቴድራል ገንቢዎች አይደሉማ፡፡

ለመሆኑ ማንን እያከምን ነው? አንድ በሽተኛ ወይስ ሀገር እያከምን ነው? ሕይወት ስለ ማትረፍ እያሰብን ነው ወይስ የካርድ ገንዘብ ስለመሰብሰብ? በሽታን ለማጥፋት እየታገለን ነው ወይስ ከበሽተኞች ለማትረፍ? የሆስፒታሉን የጥራት ደረጃ የሚወስነው ይኼን ጥያቄ በትክክል መመለስ እና አለመመለስ እንጂ ከውጭ ሀገር የተገዛ መሣርያ መኖር፣ የታዋቂ ሐኪሞች መገኘት፣ የአልጋው እና የወንበሩ ጥራት፣ ወይንም የመደኃኒቶቹ ከጀርመን መምጣት አይደለም፡፡

እኛ አንዲት ጭብጥ ወረቀት ጨባብጠን መንገድ ላይ ስንጠል ምን እያሰብን ነው?በቃ አንዲት ጭብጥ መናኛ ወረቀት፡፡ እኔ አንዲት መናኛ ወረቀት ጣልኩና ምን ይመጣል፡፡ በቃ ጣልኩ፡፡ የጽዳት ሠራተኞቹ ያነሡታል፡፡ ድንጋይ ፈላጮች እንደዚህ ነው የሚያስቡት፡፡ አንድን ነገር ለእነርሱ የዕለት ጥያቄ መልስ ይሆን ዘንድ ማድረጋቸውን እንጂ ያ መልስ የሚያስከትለውን ውጤት አያስቡትም፡፡ ግን እስኪ ቆም ብለን እንደ ካቴድራል ገንቢ ደግሞ እናስብ፡፡

በዚያች ከተማ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች አሉ እንበል፡፡ ከሁለት ሚሊዮኖቹ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑት በየቀኑ እንዲህ እንደርስዎ ወረቀት ጨባብጠው ይጥላሉ አሉ፡፡ የአንዷ ወረቀት ክብደት አምስት ግራም ብቻ ነው እንበል፡፡ ይምቱት በአንድ ሚሊዮን፡፡ አምስት ሺ ኪሎ ቆሻሻ በየቀኑ ወደ ከተማዋ ይጨመራል ማለት ነው፡፡ ከከተማዋ ወጣ ብለው እንደ ሀገር ያስቡት፡፡ ቆሻሻው እርስዎን ከነ ቤተሰብዎ ሊውጥዎት ይችላል፡፡ ግን ደግሞ ጸዳ ያለ ውብ ከተማ በፊልም ወይንም በቴሌቭዥን ሲያዩ ይመኛሉ፡፡ ከተማዎ እንዲህ ባለ መሆንዋ ይቆጫሉ፡፡ ግንኮ ያቆሸሿት እርስዎ ጭምር ነዎት፡፡ እነዚያ የሚያዩዋቸው ከተሞች በካቴድራል ገንቢዎች ንጽሕናቸው የሚጠበቅላቸው ከተሞች ናቸው፡፡ እነዚያ ከተሞች ድንጋይ ፈላጮች ደስ እንዳላቸው ያገኙትን አይወረውሩባቸውም፡፡ ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው፡፡

ውኀው ከቧንቧው ላይ ጠብ ጠብ ጠብ ሲል እያዩት ነው አይደል፡፡ ዘጉት ወይስ አለፉት?ለምን ይዘጉታል፤ እርስዎ አይከፍሉበት፡፡ ደግሞ ሥራዎ አይደለም፡፡ ምን ጥልቅ አደረገዎት፡፡ በወሩ መጨረሻ ሂሳብ ሲቆነድደው ባለቤቱ ራሱ ያሠራው የለ፡፡ ይሄ ነው የድንጋይ ፈላጮች አስተሳሰብ፡፡ እያንዳንዷን ጠብታ ውኃ ከወንዝ ወይንም ከሐይቅ ለማምጣት፣ ለማጣራት፣ በቧንቧ ለማስተላለፍ ስንት ወጭ ወጥቷል? ይህ የወጣው ገንዘብ ደግሞ ከእኔ ኪስ የሚወጣ ግብር ነው፡፡ በእያንዳንዷ ጠብታ ውኃ የተነሣ ስንት የሀገር ገንዘብ ይባክናል? ይህቺን ውኃ እኔ ብዘጋት ስንት የሀገር ወጭ አተርፋለሁ? ብለው ካሰቡማ ካቴድራል ገንቢ ሊሆኑ ነው፡፡

ለውጥ ለለውጥ በቆረጡ፣ መለወጥ እንችላለን ብለውም በሚያስቡ፣ ከዕለት ጉዳይ አልፈው ታላቁን ሥዕል ለማየት በሚችሉ ሰዎች የምትመጣ ናት፡፡ በመሥራት ብቻ አትመጣም፡፡ በመፈክር አትመጣም፣ በሰልፍ አትመጣም፣ በስብሰባ ብቻ አትመጣም፡፡ ቃል በመግባት ብቻ አትመጣም፡፡ በውብ ፖሊሲዎች ብቻ አትመጣም፡፡ እርሱ የሚፈልጣት ድንጋይ ካቴድራሉን የምትገነባው እርሷ መሆንዋን ተረድቶ ለትልቁ ካቴድራል የሚሆን ውብ፣ ጠንካራ፣ አስተማማኝ፣ ተገቢ፣ ድንጋይ በሚያዘጋጅ ገንቢ ነው የምትመጣው፡፡ እንዲሁ በሚፈልጥ ብቻ አትመጣም፡፡ ለውጥ እጅ ላይ አይደለችም አእምሮ ውስጥ ናት፡፡

ታክሲ ነጅው፣ ወያላው፣ የአውቶቡስ ሾፌሩ፣ አስተናጋጁ፣ ጉልት ሻጯ፣ የሱቁ ባለ ቤት፣ ምግብ አብሳዩ፣ ሞግዚቷ፣ ፖሊሲ አውጭው፣ ዳኛው፣ ፖሊሱ፣ ዐቃቤ ሕጉ፣ ጠበቃው፣ የፓርላማ አባሉ፣ ካድሬው፣ የሂሳብ ባለሞያው፣ ኦዲተሩ፣ ወታደሩ፣ ጋዜጠኛው የየራሱን ሥራ ለትልቁ ሥዕል እያሰበ ሲሠራ ነው ለውጥ የሚመጣው፡፡ ሁላችንም በተመሳሳይ ደረጃ፣ ፍጥነት፣ ዐቅም፣ ችሎታ፣ ዕውቀት እና ሥልጣን አንድ ዓይነት ተግባር ልንከውን አንችልም፡፡ የተለያየ ፍላጎት፣ የተለያየ መንገድ፣ የተለያየ ርእዮት፣ የተለያየ ስትራቴጂ፣ የተለያየ ደረጃ ሊኖረን ይችላል፡፡ አንድ ነገር ላይ ግን መግባባት አለብን፡፡ የሁላችንም ጥረት ካቴድራሉን ለመገንባት መሆኑን፡፡

ካቴድራሉን ለመሥራት የብዙ ድንጋይ ፈላጮችን ላብ፣ ችሎታ እና ጊዜ ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ብዙ ትውልድ ይሳተፍበት ይሆናል፡፡ በአንድ ዕለት አያልቅ ይሆናል፡፡ ምናልባትም አንዳንዶቹ ካቴድራሉ ተገንብቶ ለማየት አይታደሉ ይሆናል፡፡ አንዳንዶቹም ከካቴድራሉ ጥቅም ላይቋደሱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ለካቴድራሉ ግንባታ አስተዋጽዖ ማድረግ አለብን፡፡ መኖር ማለት ከመኖር በላይ ለሆነ አንዳች ነገር አስተዋጽዖ ለማድረግ መቻል ነው፡፡ የመኖራቸውን ያህል የሚሠሩ እንስሳት ናቸው፡፡

ካቴድራሉ ያማረ የሚሆነው ድንጋዩን የሚያዘጋጀው፣ በሩን የሚሠራው፣ መስተዋት የሚቀርጸው፣ መብራት የሚተክለው፣ ወለል የሚያነጥፈው፣ ቀለም የሚቀባው፣ ግድግዳ የሚለስነው፣ ጣራ የሚመታው፣ ውስጡን የሚያሳምረው፣ ስለ ካቴድራሉ ውበት እያሰቡ እነርሱ የየራሳቸውን ድርሻ ወብ አድርገው ከሠሩት ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዱ ውብ አድርጎ ያልሠራውን፣ ድምሩ እንዴት ውብ ይሆናል?

ወዳጄ! ለውጥ፣ ዕድገት፣ ብልጽግና፣ የተሻለ አሠራር፣ የተሻለች ዓለም፣ ሥልጣኔ ከሌላ ቦታ ይመጣል ብለህ አትጠብቅ፡፡ ያለው በአንተ እጅ ነው፡፡ ለውጥ ከሩቅ አይጀመርም እዚሁ ካንተ ዘንድ ነው፡፡ ጀግኖች ሌሎች አይደሉም፤ አንተ ነህ፡፡ ቤትህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ትዳርህን የተሻለ ዓለም ማድረግ ትችላለህ፡፡ መሥሪያ ቤትህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ንግድህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ሆስፒታልህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ጉልትህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ የጫማ መስፊያ ቤትህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ አሠራርህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ትልቁን ሥዕል እያሰብክ ከሠራህ፡፡

የግድ የሀገሪቱ መመርያ እስኪለወጥ፣ ቢ ፒ አር እስኪሠራ፣ ሥልጠና እስኪሰጥህ፣ መመርያ እስኪወጣ፣ ቅጣት እስኪጣልበህ፣ ውድድር እስኪመጣ፣ ጓደኛህ እስኪበልጥህ፣ በስብሰባ እስኪነገርህ፣ አለቃህ እስኪስማማ፣ ውሳኔ እስኪወሰን፣ የሌላ ሀገር ልምድ እስኪቀሰም ለምን ትጠብቃለህ? «ልታየው የምትፈ ልገውን ለውጥ መጀመሪያ አንተው ራስህ ሁነው» ይልሃል ማኅተመ ጋንዲ፡፡

በአንዲት ጎጆ ውስጥ ዘመንዋን ሁሉ የኖረች አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ቀኑን ሙሉ በሥራ ስትደክም ውላ ማታ የምትጽናናው አጋፔ በምትባለው ወፏ ነበር፡፡ ይህንን ነገር ያወቁ ሁለት ጎረምሶች ተመካከሩና አንድ ቀን በሌለችበት ቤቷን ሠብረው ወፏን ወሰዱባት፡፡

ማታ ስትመጣ ቤቷ ተሰብሯል፡፡ ወፏም የለችም፡፡ ደንግጣ ፍለጋ ስትወጣ ሁለቱን ወጣቶች አገኘቻቸው፡፡ ወደ እርሷም ቀረቡና ሁለቱን እጆቻቸውን ጨብጠው፡፡ «እማማ ወፏ በእጃችን ውስጥ ናት፡፡ ግን አንድ ጥያቄ እንጠይቅዎትና መልሱን ከመለሱ እንሰጥዎታለን´ አሏት፡፡

«ምን?» አለቻቸው፡፡

«ወፏ አለች ወይስ ሞታለች?»

አሰበች፡፡ ሞታለች ብትላቸው መልሱን አላገኘሽም ብለው ይለቋታል፡፡ ከዚያም በኋላ አታገኛትም፡፡ አለች ብትላቸውም ተሳስተሻል ብለው በእጃቸው ጨፍልቀው ይገድሏታል፡፡

እናም በመጨረሻ እንዲህ አለቻቸው «መኖርዋም መሞቷም በእጃችሁ ውስጥ ነው»

ኢትዮጵያም እንዲህ ናት፡፡

አቡዳቢ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት

© ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔትላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።


44 comments:

 1. << ሁላችንም ለካቴድራሉ ግንባታ አስተዋጽዖ ማድረግ አለብን፡፡ መኖር ማለት ከመኖር በላይ ለሆነ አንዳች ነገር አስተዋጽዖ ለማድረግ መቻል ነው፡፡ የመኖራቸውን ያህል የሚሠሩ እንስሳት ናቸው፡፡>>

  ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን ፡፡

  ReplyDelete
 2. ዲያቆን ዳንኤል Melkam Yegena Beal Yihunilih.

  “Lezetewelde Emkidist Dingile Minteniblo Nastemasilo Lemedahinine...”

  ReplyDelete
 3. Dear Daniel,

  Thank you very much. Life without purpose is nothing.

  What are we living for? What does life mean? Is it perhaps a stage-play -- are we here to act our part for a few brief moments, only to disappear behind the stage forever? Or is life a trip that takes us somewhere, and if so, what is our final destination?

  Please think about this crucial issue and answer for yourself: What am I living for? What values do I embrace? What objectives am I attempting to reach?

  I believe that we were all sent here for a reason and that we all have significance in the world. I genuinely feel that we are all blessed with unique gifts. The expression of our gifts contributes to a cause greater than ourselves.

  Last year, I was running at full speed; chasing after my dream of money and ‘success’. However, I had forgotten why I was running. Luckily, I met my friend. My friend had achieved all the financial goals I was reaching for. He had financial independence, several successful businesses, homes in multiple countries, and the luxury to afford the finest things money could buy. Through hard work, persistence and sheer action; he had made it! But, my friend was not happy. He did not have the free time to enjoy his wealth. He wanted a family. He wanted peace. He wanted to live his life… but he was not able to. He had too many responsibilities, too much to lose, and too many things to protect. He had spent years building his castle, and now that it is complete, he is spending his time keeping it from eroding.

  Getting to know my friend was a life altering and eye opening experience. His words snapped me out of my state of ‘unconsciousness’. It became clear to me that, “I did not want to spend the next 10 years chasing after money, only to find that I’ll be back at the same place I am at today; emotionally, mentally, and spiritually”. My ‘chase’ came to a screeching halt, everything was put on hold, and I spent the next two months re-evaluating my life and purpose.

  These questions were running through my mind:

  What am I chasing after? Why am I chasing it? What is my purpose? Why was I put here?

  May God bless Ethiopia and I wish you all " መልካም: ገና"
  Addis Ababa, Ethiopia

  ReplyDelete
 4. መኖር ማለት ከመኖር በላይ ለሆነ አንዳች ነገር አስተዋጽዖ ለማድረግ መቻል ነው፡፡
  i was waiting your note---
  thank you Dn.Daniel

  ReplyDelete
 5. Best article!
  Keep on wrting such wonderfull articles though we are not going to practice it. But at least you will find some people who can practice it.

  M.M.G

  ReplyDelete
 6. ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

  የመጨረሻው ተረት የየኔታ አባባል ይመስለኛል፡፡ ምነው ለፈረንጅ ሰጠህብን ?

  ReplyDelete
 7. It is a good speculation. I personally agree with this idea.Thanks my brother.

  PJmuluken,Debermarkos University

  ReplyDelete
 8. ዳኔ ...

  አሁን የሚያሳስበኝ ምን ያክል ኢትዮጵያውያን ያንተን ጽሁፎች ያገኛሉ የሚለው ነው ? መንግስት የ እውንነት ለውጥን የሚፈልግ ቢሆን አንድ ነገር ያደርጋል ብየ አስባለሁ .... በአዲስ ዘመን ላይ እንቶ ፈንቶ ወሬ ከሚያራግብ ያንተን መልክቶች ያሰራጭበት ነበር :: ምን ያደርጋል ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው አካሎች ድንጋይ ፈላጮች ናቸው ....

  እግዚአብሄር ያበርታህ

  ReplyDelete
 9. Really Thank You! God Bless You! ዉለታህ በዛብን።እግዚአብሄር ፀጋዉን ያብዛልህ።

  ReplyDelete
 10. endet wub kalatoch nachew so inspirational thanks

  ReplyDelete
 11. Oh Dani thanks for your advise.

  ReplyDelete
 12. REALY TAHNK U DANI,BERTALN EDME KETENA GAR YSTLN.
  LET WE ETHIOPIAN SAY THIS PHRASE
  "ሥልጠና እስኪሰጥህ፣ መመርያ እስኪወጣ፣ ቅጣት እስኪጣልበህ፣ ውድድር እስኪመጣ፣ ጓደኛህ እስኪበልጥህ፣ በስብሰባ እስኪነገርህ፣ አለቃህ እስኪስማማ፣ ውሳኔ እስኪወሰን፣ የሌላ ሀገር ልምድ እስኪቀሰም ለምን ትጠብቃለህ?ልታየው የምትፈ ልገውን ለውጥ መጀመሪያ አንተው ራስህ ሁነው» "

  ReplyDelete
 13. Yetibeb balebet Lieul Egziabher Tibebu Ena Mastewaluun Lante yefekede leegnam yetibebu ena yemastewalu TSEGA yadilen!!! Amen!!!

  Ande Zenbel,Ande Gadem, Ande Dirik, Ande Bik yemilewun wutta wured yalteleyew Astesasebie Bante Menfesin Bemyiadissu, Bemiyalemelimu, Libe Mulunetin Bemiyalabissu, Be migestsu, Bicha ena key Mebrat Bemiyaberu Eyitawochih Mingigna ende migelegel bitak, Amlakihin minigna bawedeskew!!!

  Gebre Kirkos wendimih negne: Ebakih bestelotihm Assibegne, Anbabiwochihm chimir

  ReplyDelete
 14. Oh dani betam arif new. "yethiopia menorim memotuam be ijachin lay new silezih gib yinuren hulachinim."

  ReplyDelete
 15. Dear Dn Dani
  You wrote an amazing article.You have beutifully said what I have been thinking after looking a surprisingly clean eastern europe country.It was my first time to go out of Ethiopia and I really regret by what I was doing previously like throwing gum covers and mobile cards here and there; now I swear to carry out my duty to keep my country clean at least she won't be dirty because of me.
  Dear Dani thanks time and again.

  ReplyDelete
 16. ከልብ የፈለቀ ምስጋና ላንተ፤ ለኛም የሰማነውን በልቦናችን አሳድሮብን ፍሬ እንድናፈራ ይርዳን።አሜን!። እንዲህ እንዳንተ የሚያስተምሩን በመካከላችን ካሉልን ድንጋይ ስንፈልጥ ካቴድራሉን እያሰብን እንደሚሆን ተስፋም እናደርጋለን እናምናለንም ።እምነታችን አይደል ዓለምን የሚያሸንፈው።

  ReplyDelete
 17. Please Daniel put this article in pdf. Otherwise I cannot read it. Banebebut kenahu!!!

  ReplyDelete
 18. Daniel please put this article in pdf. otherwise I cannot read it.

  ReplyDelete
 19. It's been months since I stared visiting Deacon Daniel's blog.It's really amazing.I like your ideas Daniel.please keep the good job... you are building the Cathedral!

  I also appreciate the comments being posted.for example Mr. Abebe M. Beyene's comment is very fantastic.your friend's situation has snapped you out of your unconsciousness, and your idea has done the same for me.Thank you very much Mr. Abebe! For all this great ideas Deacon Daniel is the cause. Thanks a lot.

  As you gentle men put it vividly,all the problems in our country is just lack of vision. we are all fighting like cats and dogs for mere selfish interest.our politicians are unable to see beyond their nose, and so are we the supporters.yes! our main enemy is poverty. and this the result of ethnic fighting.even thought we are all back,we think we are different. then comes racism...a monster,our real enemy, that's the evilest of all.the second enemy is corruption... a pandemic disease. this generation should say no to these two demons.we should be ready to slay them...to cut them,to put off the flame, let's pull the weeds from to the root.

  ReplyDelete
 20. ጥሩ እይታ ነው፡፡ ስንቱ ነው በከተማችን ለውጦችን ከሌላ እየጠበቅን በየመስራቤቱ የሚገኝ ግንቦች በውንድሞችን ሽንት ሊፈርስ ነው እንዲሁም በከተማዋ ነዋሬ ከጉንፋን ጋር ተጋብቶ መኖር ከጀመርን ሰንበትን ምን ከመሰለ መኪና ወረዶ አፍንጫውን ሸፍኖ ግንቦ ላይ ሲሸና መች አፍሮ! ምክንያቱ ለውጥን ከሌላ ሰው ስለሚፈልግ አይደል? እናመሰግናለን ዳኒ እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete
 21. ህ! አንተ በርክትልን
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 22. We are all leaders of z country, Ethiopia. Z politicians are only part of z leadership who direct z direction and make z move organized and secure. Many thanks dani, keep on writing. Merry christmas.

  ReplyDelete
 23. +++

  Ene leyet yale Tiyake mesay hasab alegne.
  Ye Deacon Daniel website chemirro, Leloch bizzu Yeteleyayu sile kidist Betekirtiyanachin Tuwfit ena tarik endihum yeteleyayu gudayoch yeminsabachew websitoch Alu. Enezih websitoch BE EWNET siratte Betekristiyann ena Tiwfitwan tebikew Selemhedachew enam Masked silalebachew yemiyasassib yebelay Akal weyim yetderage mahber ale wey?

  Tiyakeye yezegeye alyam yekecheche kehone yikirtta, Binor gin destaye weder yelewum.

  Ahinim Gebre Kirkos negne.

  ReplyDelete
 24. Another wonderful article, dear Danny Geta ejige abezto yebarkeh!! this truly explains the current as well as the past working habits of our Ethiopians no wonder we still are immersed in poverty and starvation, we can not point our fingers on external factors unless we change our views and working habits, we must be able to see the big picture the ultimate result while doing our daily endeavors this also works for government and business agencies that are sucked in serving their narrowed self interest rather than a nation wide vision and goals ...again thank you so much Danny!

  ReplyDelete
 25. ወይ ጉድ እንደ ድንጋይ ጭንቅላታችንን የሚፈልጠን አግኝተን አንስተካከልም አንተ ለካቴድራሉ የሚሆን ድንጋይ መፍለጡን ከጥል

  ReplyDelete
 26. ለውጥ እጅ ላይ አይደለችም አእምሮ ውስጥ ናት፡፡
  ካቴድራሉን ለመሥራት የብዙ ድንጋይ ፈላጮችን ላብ፣ ችሎታ እና ጊዜ ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ብዙ ትውልድ ይሳተፍበት ይሆናል፡፡ በአንድ ዕለት አያልቅ ይሆናል፡፡ ምናልባትም አንዳንዶቹ ካቴድራሉ ተገንብቶ ለማየት አይታደሉ ይሆናል፡፡ አንዳንዶቹም ከካቴድራሉ ጥቅም ላይቋደሱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ለካቴድራሉ ግንባታ አስተዋጽዖ ማድረግ አለብን፡፡ መኖር ማለት ከመኖር በላይ ለሆነ አንዳች ነገር አስተዋጽዖ ለማድረግ መቻል ነው፡፡ የመኖራቸውን ያህል የሚሠሩ እንስሳት ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 27. ማሰብ መጠየቅ ለሆድ አለመገዛት እንደ ሶስተኛው ድንጋይ ፈላጭ አይነት መሆን ያስችላል

  ReplyDelete
 28. ለካቴድራሉ ግንባታ፡-ድንጋይ የማይፈልጡ ፈላጮች ከመሆን የሚፈለጡ ድጋዮች ለመሆን ያብቃን፡፡

  ReplyDelete
 29. Dani!! now you are coming with our life or work???????????????

  ReplyDelete
 30. this is good.but u r acting like civic teacher!.... pls tell us about religeous issues. there is a lot we expect from u

  ReplyDelete
 31. Great Perspective
  Abnet Agegnehu

  ReplyDelete
 32. የሚክትለውን ለለጥፍክው፡

  Anonymous said...

  this is good.but u r acting like civic teacher!.... pls tell us about religeous issues. there is a lot we expect from u

  በእውኑ የ ዲ. ዳንኤልን መንፈሳዊ ትምሕርቶች አዳምጠህ/ሽ ጨርስህ/ሽ ነው? ይህ የለጠፍክ/ሽው መልክቱ ግብቶህ/ሽ እንደሁ ያጠራጥራል።
  ጎበዝ በድንጋይ ፈላጭንት ችክ አንበል እንጂ። ብንችል ካቴድራሉን እንገንባ ባንችል ቢያንስ አንገነባም አንማርም አንሰራም (ገ፣ ሰ ይጥብቃሉ) አንበል።
  ብዙ እንጠብቃልን ላልከው/ሽው እስካሁን እንግዲህ ቀን 24 ሰአት ብቻ ነው ያለው እኔ እይገረመኝ ያለው መች ለእቅልፍ አረፍ አንደሚል ነው። ከየት እንድጻፈው ብንመልከት እንኩዋን ለአገልግሎት ከሔደበት መሆኑን እንረዳለን።

  ሙሉጌታ ሙላቱ
  ከ ቫንኩቨር ደሴት

  ReplyDelete
 33. greaat great hulum bisemaw tiru nebber

  ReplyDelete
 34. ዳኒ ነገሮችን የምታይበት መነጽር፣ የምታመሳስልበት ዘዴና የምታስተምርበት ስልት በጣም በጣም ያስደስተኛል፡፡ ይህ ደግሞ ለተወሰኑ ብቻ የተሰጠ ጸጋ ነው፡፡ ይህ ጽሑፍህ የጣመ፣ የላመ፣ ልዩና የአገራችን ሰዎች ሁሉ ሊያነቡት የሚገባ ነው፡፡ አያያዛችንን፣ አመለካከታችንንና ስሜታችንን እየመረመሩ ለደዌአችን ስም የሚሰጡልን፣ በሽታችንን የሚለዩልንና መዳኛ መድሃኒቱን የሚለግሱን እንዳንተ ያሉ ብዙ የማህበራዊ ጉዳይ ሀኪሞች ያስፈልጉናል፡፡ ለምን ቢባል በሽታችን በዝቷላ፡፡

  ይህ በጽሑፍህ ማብቂያ ጽሑፉ እገሌ በተባለ መጽሔት ስለወጣ በሌላ ሕትመት ማውጣት አይቻልም ምናምን እያልክ በቀይ ቀለም የምትጽፈው መልዕክት ግን ያናድደኛል፡፡ ሁሉም ሰው ሊያነበውና ሊማርበት የሚገባ ጽሑፍ ሆኖ እያለ ቢቻል ለእያንዳንዱ ዜጋ እንደ የዕለት ጸሎት መጽሐፍ ተባዝቶ መበተን ሲገባው የጋን መብራት እንዲሆን ማድረግ ምን ማለት እንደሆነ ፈጽሞ አይገባኝም፡፡ መልዕክቱ በሰዎች አመለካከት ለውጥ አምጥቶ ለሐገር የሚፈጥረውን ፋይዳ አስበህ የምታበረክታቸው እንጂ ለአንድ መጽሔት ፍጆታና ለክፍያ ብቻ ብለህ የምትጽፈው አይመስለኝም፡፡

  ReplyDelete
 35. የሚከተልውን ለለጠፉት :

  Anonymous said...

  ዳኒ ነገሮችን የምታይበት መነጽር፣ የምታመሳስልበት ዘዴና የምታስተምርበት ስልት በጣም በጣም ያስደስተኛል፡፡ ይህ ደግሞ ለተወሰኑ ብቻ የተሰጠ ጸጋ ነው፡፡ ይህ ጽሑፍህ የጣመ፣ የላመ፣ ልዩና የአገራችን ሰዎች ሁሉ ሊያነቡት የሚገባ ነው፡፡ አያያዛችንን፣ አመለካከታችንንና ስሜታችንን እየመረመሩ ለደዌአችን ስም የሚሰጡልን፣ በሽታችንን የሚለዩልንና መዳኛ መድሃኒቱን የሚለግሱን እንዳንተ ያሉ ብዙ የማህበራዊ ጉዳይ ሀኪሞች ያስፈልጉናል፡፡ ለምን ቢባል በሽታችን በዝቷላ፡፡
  ይህ በጽሑፍህ ማብቂያ ጽሑፉ እገሌ በተባለ መጽሔት ስለወጣ በሌላ ሕትመት ማውጣት አይቻልም ምናምን እያልክ በቀይ ቀለም የምትጽፈው መልዕክት ግን ያናድደኛል፡፡ ሁሉም ሰው ሊያነበውና ሊማርበት የሚገባ ጽሑፍ ሆኖ እያለ ቢቻል ለእያንዳንዱ ዜጋ እንደ የዕለት ጸሎት መጽሐፍ ተባዝቶ መበተን ሲገባው የጋን መብራት እንዲሆን ማድረግ ምን ማለት እንደሆነ ፈጽሞ አይገባኝም፡፡ መልዕክቱ በሰዎች አመለካከት ለውጥ አምጥቶ ለሐገር የሚፈጥረውን ፋይዳ አስበህ የምታበረክታቸው እንጂ ለአንድ መጽሔት ፍጆታና ለክፍያ ብቻ ብለህ የምትጽፈው አይመስለኝም፡፡
  January 11, 2012 1:16 PM

  በመጀመርያው አንቀጽ ብስማማም ብሁለትኛው ግን አልስማማም።ዳንኤል ይህን ማሳሰብያ(disclaimer) ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች መለጠፍ ይገባዋል፡
  1. አንቱ እንዳሉት ከመጽሔቱ ጋር በክፍያ ምክንያት በሚኖረው ስምምንትና ከሙያ ግዴታና ከሕግ አኩዋያ።
  2.ሌላ ግለስብ ጽሁፉን ወዶት በሌላ ህትመት ከነ እውነተኛ ደራሲው ስም ቢያትምው ተጠያቂነቱ የዳንኤል ስልሚሆን።
  ከላይ ያለውን አስተያየት የጻፉት በዚህ ድህረ ገጽ መግቢያ ላይ የተለጠፍውንና ከዳንኤል ፎቶ በላይ የተጻፈውን፤ የዚህን ብሎግ ስራ ማገዝ ከፈለጉ በዚህ ይጠቀሙ የሚለውን ማሳሰብያ አንብበውት ይሆን? አንብበውስ የሚችሉትን አድርገዋል? ካልቻሉ ቢያንስ ሁሉን ለሚችል አምላክ ዳንኤል በሚሰራው ሰራ እንዲረዳው አንዴ እንኩዋን ጸልየዋል?ይህን ካደረጉ መልካም። ቢሆንም ግን እኒህን ጽሁፎች በመካነ ድር በነጻ ስለምናገኛቸው ብቻ ዳንኤል ጊዜውን ገንዘቡን ያወጣባቸው የአዕምሮ ስራ ውጤቶች(intellectual properties) መሆናቸውን ለዚህም ተመጣጣኝ ክፍያ የመጠይቅ መብት እንዳለው ልንዘነጋ ግን አይገባም። እሱ ለሚገነባው ማህበራዊ እሴት መሰረት የተቻለንን ጡብ እንኩዋን በማቀበል እናግዝ አለበለዚያ ደግሞ ያነበብንውን እንኩዋን መረዳታችንን በተግባር እናሳይ።እንዲህ ካላይ እንደጻፉት ወዳጄ ግን እርስ በርሱ የሚጋጭ አስተያየት ከመስጠት እንቆጠብ።
  ሰላም!
  ሙሉጌታ ሙላቱ ነኝ
  ክቫንኩቭር ደሴት

  ReplyDelete
 36. አንድ ታላቅ ሰው እንዲህም ብለው ነበር.." የዘመናችን ረሀብ የሚበላ ብቻ ሳይሆን የሰው ችጋርና ረሃብ ነው:" በእውነት አድማጭ ካለው መልዕክትህ ጥሩ ነው::ብቻ ፍሬ ይስጥም አልይም ጫጭቶ ይቅር አንተ ደግ አደረግህ :እንዲህ እያዋዛህ ንገረን:ሰው ብንሆን ፍሬ ቢገኝብን:ግሩም ዳ.ዳንኤል ምኞቴ ብዙነህ@ፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete
 37. ዲ. ዳኔል ድንግል ከልጇ ጋር ትጠብቅህ!
  አንባቢዎች ሆይ!
  • አስተያየታችሁ ወይም ደግሞ መልክቶቻችሁ ሁሉ መልካም ናቸው፤ነገር ግን ከራሳችሁ የሚጠበቀውን ሃላፊነት ለራሳችሁም ሆነ ለሌሎች አንባቢዎች ቃል መግባቱንና መናገሩን ዘነጋችሁት፡፡ ይህም ማለት እኔ ስራየ ይህ ነው (የስራ ትንሽ የለውም)፣ ከዛሬ ጀምሮ ከእኔ ወይም በእኔ ሙያ የሚጠበቀውን ለማድረግ ቃል እገባለው ብሎ እራስን ከዉስጥ ማሳመንን፤

  • ለምሳሌ፡-
  o እኔ መምህር ነኝ፤መምህር ሁሉም እንደሚያውቀው የእዉቀት ምንጭ ወይም አባት ነው፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ተማሪዎቼን ሳስተምር ደመወዜን በማሰብ እና ማስተማር ስላለብኝ ብቻ ሳይሆን የዛሬ ተማሪዎቹ የወደፊት አገር ተረካቢዎች መሆናቸውን በማሰብ ተማሪዎቹ በእውቀት እነዲበለጽጉ፣በተግባር እንዲሰለጥኑ፣በስነ-ምግባር የታንጹ እንዲሆኑ፣እንዲሁም ከእኔ ሙያ የሚጠበቀውን በተቻለኝ አቅም ሁሉ ለእነርሱ ለማድረግ ቃል እገባለሁ፡፡

  ReplyDelete
 38. ለአስተያየት ሰጭዎች ከቫንኩቨር ምላሽ የሚጽፉ ሰው እባክዎ ብዕርዎን በለጋ ቅቤ አሸት አሸት ያድርጓት፣ ካልተደደብዎ ደግሞ ጠብ ቢያረጉባትም ሸጋ ነው፡፡ ከያ ወዲያ መልዕክትዎችዎን በትህትና አለዝባ ባታወጣልዎ ምን አለች ይበሉኝ፡፡ እንደ አዲስ ዘመን ጣፊዎች እንዳትደርቅብዎ፣ ደርቃም ሰው እንዳትወጋብዎ ብዬ ነው እንጂ ይሙቱ ለሌላ አይደለም፣

  ትዕግስት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውድ ትዕግስት
   ምን ላድርግ ብለው ነው። አንዳንዴ የተጻፈውን እንኩዋ መረዳታችንን የሚያጠያይቅ መልዕቶች ሳነብ ግልፍ ቢለኝ ነው።
   ስሜንም የምጽፈው እንደሌላው ስለምለው ነገር ምን ያመጣብኛል ብዬ ካለመስጋት ሳይሆን ስልምልው ነገር ሃላፊነት መውስዴ ነው።
   ያሉትን በሙሉ ልቤ ተቀብዬዋለሁ አመሰግናለሁ!!
   ሙሉጌታ

   Delete
 39. የግድ የሀገሪቱ መመርያ እስኪለወጥ፣ ቢ ፒ አር እስኪሠራ፣ ሥልጠና እስኪሰጥህ፣ መመርያ እስኪወጣ፣ ቅጣት እስኪጣልበህ፣ ውድድር እስኪመጣ፣ ጓደኛህ እስኪበልጥህ፣ በስብሰባ እስኪነገርህ፣ አለቃህ እስኪስማማ፣ ውሳኔ እስኪወሰን፣ የሌላ ሀገር ልምድ እስኪቀሰም ለምን ትጠብቃለህ? «ልታየው የምትፈ ልገውን ለውጥ መጀመሪያ አንተው ራስህ ሁነው» ይልሃል ማኅተመ ጋንዲ፡፡

  ReplyDelete
 40. Dakon Daniel astewlo lanebebew tiru timihirt new Egziabher yestehn tsega keminetik fetena ena seytan yadinih

  ReplyDelete
 41. Dakon Daneil yihin tsega yeseteh Egiziabher yimesgen.Yebeltewn tsega yabizalih Egiziabher tsega siset adera new aderhin lemeweta YeDingli milijawa yeEgiabher Chernet yirdah

  ReplyDelete
 42. The only thing people must do in their day to day activity is working for the CATHEDRAL even if we work for money,the money couldn't buy anything.......so we must work at our most good faith...GOD Bless U.

  ReplyDelete