Monday, January 2, 2012

ኀዘን እና ደስታ

(click here for pdf)
በየሀገሩ እየዞረች ከልዩ ልዩ ሕዝቦች ጋር መገናኘት የምትወድ አንዲት ፓይለት ነበረች፡፡ በዓለም ላይ ያልዞረችበት ሀገር አልነበረም፡፡

አንድ ቀን ፓይለቷ በሰሐራ በረሃ ላይ ስትበርር የአውሮፕላኑ ሞተር ተበላሸባት እና በፓራሹት ወደ መሬት ወረደች፡፡ የወረደችበትን ቦታ አታውቀውም፡፡ ግን ጭው ያለ በረሃ ነበር፡፡ የት እንዳለች እና ወደ የት መጓዝ እንደምትችል አታውቅም፡፡ በአካባቢዋ ያለው መንደር በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሚገኝም ምንም መረጃ የላትም፡፡

ለብዙ ሰዓታት ካሰበች በኋላ ያላት አማራጭ በአንዱ አቅጣጫ መጓዝ እንደሆነ አመነች፡፡ እናም የምት ችለውን ዕቃ ተሸክማ ጉዞዋን ጀመረች፡፡ በዚያ በረሃ ከሚያጋጥማት የአሸዋ አውሎ ነፋስ ጋር እየታ ገለች፣ በአሸዋው ተራራ ላይ እየወደቀች እና እየተነሣች፣ ከሚያጋጥሟት አራዊት ጋር እየተጋደለች ወደፊት መጓዟን ቀጠለች፡፡

መንገዱ በሁለት ምክንያት አድካሚ እና አሰልቺ ሆነባት፡፡ በአንድ በኩል ወደየት እንደ ምትሄድ በርግ ጠኛነት ባለማወቋ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መቼ እንደምትድረስ ለመገመት ባለመቻሏ፡፡ በአንድ ነገር ግን ርግጠኛ ነበረች፡፡ በመንገዷ ከሚያጋጥሟት ፈተናዎች ይልቅ መንፈሷ ጠንካራ መሆኑን፡፡ ባለ ማቋረጥ ከተጓዘች አንዳች ጠቃሚ ቦታ ላይ እንደምትደርስ፡፡ እናም መጓዝ ቀጠለች፡፡

ይደክማታል ትወድቃለች፡፡ ዐቅም ሰብስባ ትነሣለች፡፡ ተስፋ አትቆርጥም ትጓዛለች፡፡
ተሸንፋ አንድ ቦታ በመቀመጥ ሞትን መጠበቅ ትችላለች፡፡ እርሱ ግን አማራጭ የማይሰጥ ሞት ነው፡፡ ሽንፈት ማለት ሞትን ያለ ምርጫ መቀበል ነው፡፡ እየታገሉ መሞት ሞትን በራሱ ጊዜ ብቻ እንዲመጣ ማስገደድ ነው፡፡ ሳይታገሉ መሞት ግን ሞትን ብቸኛ ምርጫ አድርጎ መጋበዝ ነው፡፡

መታገል ሁለት ዕድሎች አሉት፡፡ ማሸነፍ ወይንም መሸነፍ፡፡ አለመታገል ግን ምርጫው አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም መሸነፍ፡፡

እያለቀ ከሚሄደው ስንቋ በቀር ምንም ዓይነት ምግብ በአካባቢው አልነበረም፡፡ የውኃ ጥሙ ከባድ ነው፡፡ ያላትን እየቆጠበች መጓዝ ነበረባት፡፡ ሌሊት እና ቀን ቢፈራረቅም እንኳን እርሷ ማቋረጥ የለባትም፡፡ መጓዝ ብቻ፡፡

አንድ ቀን እጅግ ደክሟት አሸዋው ላይ ተኝታ እያለ አንድ ፍጡር ታያት፡፡ ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ዓይነት ፍጡር፡፡ እንዲህም አላት «እኔ አንዳች ነገር ልነግርሽ ነው የመጣሁት፡፡ ተስፋ አትቁረጭ፣ ትካዜ ውስጥም አትግቢ፣ እጅሽንም አትስጭ፣ እኔ የምልሽን በትክክል ሰምተሽ ተግባራዊ አድርጊው፤ መንገድሽ ረዥም እና አስቸጋሪ ነው፣ መጨረሻው ግን ጣፋጭ ይሆንልሻል፡፡ ጠዋት ከዚህ አሸዋ የምትችይውን ያህል አፍሰሽ ያዥ፣ ከዚያም መንገድሽን ቀጥይ፡፡ በመጨረሻም ደስተኛም ኀዘንተኛም ትሆኛለሽ፣  ያኔ አንዳች ምዕራፍ ላይ መድረስሽን ታረጋግጫለሽ» አላት፡፡

ነቃች፡፡ ሕልም ብቻ አልነበረም፡፡ ያንን ፍጡር በርግጠኛነት አይታዋለች፡፡ ከነበረችበት ተነሥታ የምትች ለውን ያህል አሸዋ ዘግና መንገድዋን ቀጠለች፡፡ ሌት እና ቀን ባለ ማቋረጥ ቀጠለች፡፡ እየወደቀች እየተነሣች ተጓዘች፡፡ አንደኛው ቀን ለሌላው ቀን ተስፋ እየወለደ ተጓዘች፡፡ በመጨረሻም አንድ ጉብታ ላይ ደረሰች፡፡ ወደ ታች ስታይ የሰዎች መንደር ታያት፡፡ ያን ጊዜ በደስታ ብዛት ዝላ ወደቀች፡፡

እንግዳ ነገር በጉብታው ላይ ያዩት መንደርተኞቹ እየተሯሯጡ ወደ ጉብታው መጡ፡፡ አንሥተውም ወደ መንደራቸው ወሰዷት፡፡ ምግብ እና ውኃ ሰጧት፡፡ ለረዥም ሰዓታትም ተኛች፡፡ በፍጻሜውም ነቃች፡፡

የተጓዘችበትን መንገድ አሰበቺው፡፡ ውጣ ውረዱን አስታወሰቺው፤ ፍርሃት እና ድፍረቷን ገመገመቺው፡፡ በመጨረሻ ሰው ያለበት፣ ነፍሷ ሊተርፍ የሚችልበት ቦታ በመድረስዋ እጅግ ተደሰተች፡፡ በሕይወቷ ካጣጣመቻቸው ደስታዎች ሁሉ የሚበልጠውን ደስታ ተደሰተቺው፡፡ እጥረት ከሌለ ርካታ አይኖርም፡፡ ርሃብ ከሌለ ምግብ አይጣፍጥም፡፡ድካም ከሌለ ደስታ የለም፡፡ «እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ» እንዲል፡፡

እንደ ገና ደግሞ አንድ ነገር ትዝ አላት፡፡ ያ ሌሊት የታያት ፍጡር የነገራት ነገር፡፡ ወደ ኪሷ እጇን ከተተቺው፡፡ ያንን አሸዋ ዘግና አወጣችው፡፡ ስታየው አሸዋ አልነበረም፡፡ የአልማዝ እንክብሎች ናቸው፡፡ በደስታ እንደገና ወደ ኪሷ ገብታ የያዘቺውን ሁሉ ዘረገፈቺው፡፡ የአልማዝ እንከብሎች፡፡

ደስታም ኀዘንም አንድ ላይ መጡ፡፡ ሕይወቷ በመትረፉ ከዚያም በላይ አንድ እፍኝ አልማዞች በማግኘቷ ተደሰተች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ አልማዞችን ለመያዝ ባለመቻሏ አዘነች፡፡ ኀዘን እና ደስታ በአንድ ላይ፡፡

ያ ፍጡር እንዳላት ፍጻሜዋ ኀዘን እና ደስታ በአንድ ላይ ሆኑ፡፡ ምናለ እንዲህ ባደርግ ኖሮ፡፡ በሁሉም ኪሶቼ ብይዝ ኖሮ፡፡ ምግቡን አውጥቼ አሸዋ ብሞላው ኖሮ፡፡ በጃኬቴ ቋጥሬ ብይዘው ኖሮ፡፡ ኖሮ፣ ኖሮ፣ ኖሮ፡፡

እንደ ገና ደግሞ ደስታ፣ ይህን እና ያንን እንኳን አደረግኩ፣ እንኳንም ተስፋ አልቆረጥኩ፣ እንኳንም አልተሸነፍኩ፣ እንኳንም ባለማቋረጥ ተጓዝኩ፣ እንኳንም ያንን ፍጡር ሰማሁት፣ እንኳንም አሸዋውን ዘገንኩ፡፡ (“the parable of the pebbles” ከሚለው የጥንት ታሪክ የተወሰደ)

አንድ ሰው በሕይወቱ መጨረሻ ሲደርስ ኀዘን ብቻ የሚሰማው ከሆነ ምንም ባለ መሥራቱ ይፀፀታል ማለት ነው፡፡ ትርጉም ያለው አንዳች ነገር ሳይሠራ፣ ኅሊናውን የሚያረካው አንዳች ነገር ሳይፈጽም ነው እዚያ የደረሰው ማለት ነው፡፡ እድሜው በርሱ ላይ ሠራ እንጂ እርሱ በእድሜው አልሠራበትም ማለት ነው፡፡ ሠርቶ ሳይሆን በልቶ ነው ያረጀው ማለት ነው፡፡

አንድ ሰው በመጨረሻ ደስታ ብቻ የሚሰማውም ከሆነ ያ የጤና አይደለም፡፡ ራሱን አያውቀውም ማለት ነው፡፡ ሰዎች የሠሩትን ሁሉ እንደ ራሱ ሥራ አድርጎ ይቆጥራል ማለት ነው፡፡ ሥራውን ለመገምገም የሚያስችል ብቃት የለውም ማለት ነው፡፡

የሚታገል ሰው፣ የሚሠራ ሰው፣ ጀግና ሰው በመጨረሻ ሁለቱም ነገሮች ናቸው የሚገጥሙት፡፡ ደስታ እና ኀዘን በአንድ ላይ፡፡ እንኳንም ሠራሁት፣ እንኳንም ታገልኩት፣ እንኳንም ወሰንኩት፣ እንኳንም እምቢ አልኩት፣ እንኳንም እሺ አልኩት፤ እያለ የሚደሰትባቸው ነገሮች አሉት፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሚፀፀትበትም ነገር አለው፡፡ ምነው እንዲህ ባደርገው ኖሮ፣ ይህንን ባላደርገው ኖሮ፣ ይህንን ባልወስን ኖሮ፣ በእገሌ ላይ እንዲህ ባላደረግ ኖሮ፣ እንዲህ ባደርግ ኖሮ፣ ይህንን ብወስድ ኖሮ፣ ይህንን ባልወሰድ ኖሮ እያለ የሚፀፀትባቸው፡፡

ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው የሠራሁት ሁሉ፣ የታገልኩት ሁሉ፣ ያደረግኩት ሁሉ፣ ትክክል ነበረ ብሎ አይሟገትም፡፡ በዚያ ወቅት ትክክል መስሎት ቢሠራው እንኳን፣ አማራጭ አጥቶ ቢሠራው እንኳን፣ ሕግን እና ደንብ፣ ሥልጣን እና አሠራር አስገድደውት ቢሠራው እንኳን፣ አምኖበት ቢሠራው እንኳን፣ ሁሉም ነገር ግን ትክክል ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ እየቆየ ሲያየው የሚገለጥለት፣ እየበሰለ ሲረዳው የሚፀፀትበት፣ እየሰነበተ ሲያስተውለው ድክመት የሚያገኝበት፣ ውሎ አድሮ ሲገመግመው ባይሆን ኖሮ የሚልበት ነገርም ይኖረዋል፡፡

ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ መከራ ያዩት ቴዎድሮስ ነገሩ ሁሉ ተበላሽቶባቸው መቅደላ ብቻ ስትቀራቸው የተናገሩትን ጸጋዬ ገብረ መድኅን በምናብ ተረድቷቸው

ከዛሬ ላይ ቁጭ ብዬ የትናንቱ ሲታወሰኝ

ከሠራሁት ነገር ይልቅ ያልሠራሁት ነው የሚቆጨኝ

ነበር ያሉት፡፡

ምንም ዓይነት ትክክል ነገር የማይሠራም ሆነ ምንም ዓይነት ስሕተት የማይሠራ ሰው የለም፡፡ ሥርዓቶች፣ ፖሊሲዎች፣ ዐዋጆችም ሆኑ አሠራሮች የሰዎች ውጤቶች ናቸውና እንከን አልባ ሊሆኑም ሆነ ጥቅም አልባ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ባይሆን የትኛው ያመዝናል? ነው ጥያቄው፡፡

ፍጻሜው ኀዘንና ደስታ መሆኑ የጤነኛነት እንጂ የስሕተት መለኪያው አይደለም፡፡ እነዚህ ነገሮቼን ዛሬ ሳስባቸው ማድረግ አልነበረብኝም ብሎ መናገር ለጠላት ከመሸነፍ ለምን ይቆጠራል? ጠላትንኮ ትክክል በመሆን ብቻ ሳይሆን ስሕተትን በማመንም ማሸነፍ ይቻላል፡፡ እነዚህን ነገሮች ማድረጌ ትክክል ነበረ ብሎ መመስከርም ከትዕቢት የሚቆጠር አይደለም፡፡ ሰው ያመነበትን ሊሟገትለት ስለሚገባ እንጂ፡፡ ችግሩ የሚከሰተው ምንም ችግር ያልፈጠሩ እና ችግር ብቻ የፈጠሩ ሰዎች ከኖሩን ነው፡፡

የደቡብ አፍሪካው የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ «ለነጻነት የተደረገ ረዥሙ ጉዞ» በሚለው መጽሐፋቸው ላይ «ላለመሳሳት ብዙ ጥረት አድርጌያለሁ፣ ነገር ግን በመንገዴ ላይ ብዙ ስሕተቶችን ሠርቻለሁ፡፡ ያም ቢሆን በጉዞዬ አንድ ምሥጢር ተገልጦልኛል፡፡ አንድን ተራራ ከወጣን በኋላ የምናገኘው ነገር ልንወጣቸው የሚገቡን አያሌ ተራራዎች መኖራቸውን ነው» ብለው ነበር፡፡

እናም እስኪ እንገምግመው፡፡ ባለ ትዳሮች፣ ጓደኛሞች፣ ባለ ሽርኮች፣ ማኅበርተኞች፣ ጎረቤታሞች፣ አብሮ አደጎች እስኪ ጉዟችንን እንደ ማንዴላ እንገምግመው፡፡ የግምገማችን ውጤት ኀዘን እና ደስታ ነውን?የመጀመርያዎቹን ተራሮች ወጥተናቸዋል፡፡ ማንዴላ እንዳሉትም አያሌ ተራሮች ከፊታችን አሉ፡፡ የዚህኛውን ተራራ ጉዞ ካልመረመርነው በቀጣዮቹ ተራሮችም ከዚህ የባሱ ስሕተቶች መሥራታችን አይቀርም፡፡

ሀገር የመራን፣ ሕዝብ የመራን፣ ፓርቲ የመራን፣ የታገልን፣ ያታገልን መሪዎች፡፡ የዕውቀት መሪዎች ሆነን ለሕዝብ ዕውቀት ስናቀብል የኖርን ምሁራን፣ ሊቃውንት፡፡ ሕዝብን በእምነት ጎዳና እየመራን ያለን የሃይማኖት መሪዎች፣ ተቋማት፣ ማኅበራት፣ ድርጅቶች፣ ሚዲያዎች፡፡ እስኪ ረዥሙን ጉዞ እንየው፡፡ ኀዘን እና ደስታ ካመነጨልን ጤነኞች ነን፡፡ ታግለን ይሆናል፣ ተጉዘን ይሆናል፣ አያሌ ፈተናዎችን አልፈን ይሆናል፣ ብዙ አስተዋጽዖ አበርክተን ይሆናል፣ የማይተካ ሚና ኖሮን ይሆናል፡፡ ይህ ሁሉ ሲደመደም ግን የሚያስደስተንም የሚቆጨንም ነገር ሊኖር ይገባል፡፡
አቡዳቢ

35 comments:

 1. Yatekaberk dani slaewnat betam amasegenalhu amlak abezezto tibaben yesteh banazhi hulate hasaboche west eyalhu naw yanten weg yanababekut bezu astemwerognale.

  ReplyDelete
 2. Yatekaberk dani slaewnat betam amasegenalhu fetary abezezto tibaben yesteh banazhi hulate hasaboche west eyalhu naw yanten weg yanababekut bezu astemwerognale.

  ReplyDelete
 3. Yatekaberk dani slaewnat betam amasegenalhu amlak abezezto tibaben yesteh banazhi hulate hasaboche west eyalhu naw yanten weg yanababekut bezu astemwerognale.

  ReplyDelete
 4. ከአቀረብከው ሐሳብ ጋር አይገናኛም ነገር ግን አንድ ጥያቄ አለኝ ለአንተ መልሱን እፈልጋለሁ፡፡
  ጥያቄው በአንድ ወቅት ፀጉር ቤት ሂጀ ነበር የሴቶች ማለት በወቅቱ ልጅቷ ፀጉሬን እያጠበችሀን ነበር
  የሆነ ጉረምሳ በሩ ላይ ቆሞ ወደ እቤት ለመግባት ስለፈለጉ እኔን ፀጉሬን የምታጥበኝ ልጂ ወንድ አይገባም
  አለችሁና ቁሞ ነይ አነጋግሪኝ ሲላት ዝም አለችው አብረዋት የሚሠሩት ልጆች በነገሩ ተገርመው ምንድን ነው ብለው ጠይቅኳት ጠየቋት እሷም የእሱ ጓደኛ ነው አለቻቸው እና እኔም ነገሩ ስለገባን ለምን በሰላም አትፈቸውም ስላት እምቢ አለ ሂወቴን ማበላሸት አልፈልግም አለ ወይ በደንብ አይዘኝ ወይ አይለቀኝ ስትል ይቅርታ አድርጊልኝ እና አንድ ነገር ልጠይቅሽ ስላት እሺ አለችን ባለቤትሽ ዲያቆን ነው ወይ ብዩ ጠየቅኳት አይ መሪ ጌታ ነው አለቺኝ ይህማ ለአንቺም ጥሩ አይደለም ስጋ ወደሙ ተቀብለሽ ከባለቤትሽ ጋር መለያየት አትቺይም አልኳት
  እሷም እኔ የ18 ዓመት ልጂ እያለሁ ቤተሰቦቸ ናቸው ያገቡ እንጂ እኔ ፈቅጄ አይደለም አለችን፡፡ በጣም አዘንኩ አሁን አንተን የምጠይቅህ ጥያቄ
  1. ያለፈላጐቷ ቤተሰብ በመጣባት ጣጣ ምን መድረግ አለባት
  2. ከሰወየው ጋር ብትለያያ መሪ ጌትነቱ ይቀርበታል ወይ
  3. ከቀረበት እሱ መሪ ጌትነቱ ይቀርበታል ተብሎ እድሜ ልኳን ከእሱጋር መኖር አለባት ወይ

  ReplyDelete
 5. ዲያቆን ዳንኤል ምስጋናዬ ይድረስህ !!!

  እጥረት ከሌለ ርካታ አይኖርም፡፡ ርሃብ ከሌለ ምግብ አይጣፍጥም፡፡ድካም ከሌለ ደስታ የለም፡፡ «እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ» እንዲል፡፡


  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ፡፡

  ReplyDelete
 6. Dear Daniel,

  What a fascinating view is this?

  I was totally hopeless when I lost my father by death. I assume my self in the ocean without any sort of direction indicator or a compass.

  As an alternative I came to Addis Ababa to join my uncle family with the hope that I could find something to live after I completed my high school.

  My hope was to assist my mother and sisters. I was try my best by engaging myself in different jobs as a plumber, clerk and a mail boy at the Ministry of Construction.

  I tried my best to cope up the unfavorable world. In the mean time, I decide to be join the armed force which was an easy entry point and had a risk of life.

  Fortunately, I joined the Ethiopian Police College. When I joined it; my mother was so sad because I am the only son to her and she thought that I was deciding to die sooner or later. I told her death could come at any time and at any point and advised her no need to worry about it.

  I graduated successfully and assigned as an instructor in the Police College. Two years later I joined Addis Ababa University the evening program. I brought two of my sisters to live with me and life is started like this way.

  Four years later after my graduation I went to Germany to made a senior study in policing. I stayed their for 11 months and got back to Ethiopia. I continued my study at Addis Ababa University and after two years I got another chance to Join FBI National Academy at Quantico, Virginia in USA. Then I graduated and returned back home. After a while, I graduated from Addis Ababa University and has got my BA in PSIR.

  My struggle is continued, I got married and has a baby boy. Still my mind was not satisfied and instigate me to make the post graduate study. I Joined again the Addis Ababa University the field of International Relation(IR) and has got my MA on IR. Life is continued.

  During my post graduate study a friend of mine informed me to apply for the job with Intergovernmental Organizations. I applied for it and has got a very good job which i was not dreamed before. Now I am working with this regional organization and even assume a very senior position.

  When I red your article it touches my heart and mind and attempt to write to you briefly. Of course, when I pass all the obstacles and challenges that I faced I made many mistakes, which regrets me.

  One thing that I want to share with you is that, there is a light at the end of the tunnel. We must remain strong when we face any sort of challenge. At the end of the day we will harvest what we have sow. Hope is not the conviction that something will turn out well but the certainty that something makes sense regardless how it turns out. May God Bless Ethiopia.
  Hargiesa, Somaliland.

  ReplyDelete
 7. BEAKSUM BENGUS KALEB YMERET WUST MENGED LAY YETENEGEREW "YEZEGENEM AZENE YALZEGENEM AZENE" YEMILEWUN BELELA TARIK AYENEW!! MECHEM BEKRSTINA GUZO LAY ENDEMAYSERA BZU SEBAKYAN YAWERALU... YIHN KANEBEBU MIN ENDEMILU ALAKIM!

  ReplyDelete
 8. undo yelem enge undoma binore.........

  ReplyDelete
 9. dn.Daniel it is a great article.God bless you.tefera (nv)

  ReplyDelete
 10. እግዚአብሄር ይስጥልን ዳቆን ዳንኤል። በርታ ጠንክር እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 11. Dn daniel thank you.

  ReplyDelete
 12. ዳኒ፡ሁል፡ጊዜ፡የምትፀፋቸውን፡አነባቸዋለሁ፡ብዙ፡ነገር፡ያስተምሩኛል፡እግዚአብሔር፡የበለጠ፡ምስጢሩን፡ይግለፀልህ

  ReplyDelete
 13. Dea Daniel Kibret

  Quale Hiywoy yasemalin , Betena, Betsega, beselam yetebkihe, Dingle Timrah, Titebkihe

  Cher Yaseman

  ReplyDelete
 14. ቀደምት በአገራችን ብዙ አሉ ግን እኔ ከአለቃ ገብር ሃና ልጀምርና እንደነ ገ/ህይወት ባይከዳኝ & አደፍርስ & ብላታ ህሩይ ገ/ስላሴ& አባመላ&አዲስ አለማይሁ& በዓሉ ግርማ….. በየክፍለ ዘመንናቱ ቀድመው የሚያስቡ ሲሆኑ እንደ ጥላሁን ገሰሰ ተፈቃሪ እኛም በዘመናችን እግዚአብሄር አላሳጣንም ይኸው እንደ ዳኒ ያለ ሰጥቶናል፡፡ በጣም ክበን ከመስመር እንዳይ ወጣ@ ኮርኩመንም ወደ ታች እሳናስቀረው ተገቢውን አስተያየት እየሰጠን እንድንማማር ጌታ ይርዳን እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete
 15. Dear Dn. Dani, God bless you, I learn many valuable things from this article.

  ReplyDelete
 16. Min endemilh alwkm Dn.Danh betam amesegnalehu. Egizyabiher yibarkh!

  ReplyDelete
 17. ዳኔ
  ደስ የሚል እይታ ነው ...

  Hope is not the conviction that something will turn out well but the certainty that something makes sense regardless how it turns out.

  great story and saying ......
  Thanks Abebe M.

  ReplyDelete
 18. It is a beautiful idea!
  Thank u so much!

  ReplyDelete
 19. Ye hiwot migib yemagegnibat blog. Egziabher yabertah Diakon Daniel.

  ReplyDelete
 20. Kalehiwot.yasemaln

  ReplyDelete
 21. Dear daniel, this is a very good article which encompases a lot of issues and definetly will teach something to the reader. Whenever I read your blog, I always think that if most people in Ethiopia could get acces to your writtings, this would really help in transforming the misrable condition of our people and country. So it would be wise of you if you try your best in publishing these articles in local papers and you can also advertise your blog. I know for sure that you have been trying in every means you could to reach to the people and I appreciate that very much......peace

  ReplyDelete
 22. Dani I always regret/sad/encourage by your blog but I dont know when I do something good for my country and religion that makes me satisfied enough.
  I dont want depend on and give reasons cos reasons by itself used to far away the problems from you and even never helped humanbeings(Adam).
  Tes, PHX, AZ

  ReplyDelete
 23. ዳ/ዲኒ ግሩም የንስር እይታ ምለት እንዴሕ ነው ...አንድ ለመንገድ ልበልሀ «Happiness and sorrw come to pass alternatively one life.>> የእግዚአብሕር ቃል ስለ ዛሬ በሚገባ ኑሩ የነገን አታስቡ....ያለው ስለትናትናው ከመቆዘም ዛሬ ምን ስርተን እንለፍ ነው ጥያቂው ? ተራራውም ይሕ ነው።

  ReplyDelete
 24. This article teaches me that we have to be persistant in the decision we make in life.
  Berta.

  ktilq misgana gar

  ReplyDelete
 25. it is wonderfull God bless u...

  ReplyDelete
 26. Dear deakon Daneil,your articles always make sense and it tauches every walk of life.may God beless you.

  ReplyDelete
 27. Dani it is so sweet. Betam yeteleye ginzabe yemagegnibet blog binor yante newe. God Bless u. Bereket

  ReplyDelete
 28. it is great. happy Christmas!!!

  ReplyDelete
 29. Great one.Thanks. Melkam Beal lantena lemelawu betesebih.

  ReplyDelete
 30. kale hiwot yasemalin dn daniel. how is አቡዳቢ?..........ታግለን ይሆናል፣ ተጉዘን ይሆናል፣ አያሌ ፈተናዎችን አልፈን ይሆናል፣ ብዙ አስተዋጽዖ አበርክተን ይሆናል፣ የማይተካ ሚና ኖሮን ይሆናል፡፡ ይህ ሁሉ ሲደመደም ግን የሚያስደስተንም የሚቆጨንም ነገር ሊኖር ይገባል፡፡yes yes yes this what I gain from this interesting article.

  ReplyDelete
 31. ዳኒ የጥያቂና መልስ ዓምድ ለምን እንዲኖርህ አትሞክርም?የግዚ እጥረት መኖሩን እንዳለ ሆኖ ማለቴ ነው:: በርታ እግዚአብሔር ይርዳህ::

  ReplyDelete
 32. Dear Dn Dani everything what you write is nice and important but we have many question to be answered by u or other readers pls try to have one article for question and answer specially question related to spiritual marriage,I hope u will consider it.

  ReplyDelete
 33. Waw semonun esky alubuwalita yikiribignina ketibebi gari tezamije ewiketi ligebiy alkuti lerase endalikutim kezihu susi kemiyasizew getsihi lay hone wiloye enami mini aliku meselehi Ethiopian sasibi hule yemiyasifeligati erasun sayihon esuwani wedo endihi endante behulum akitacha sefa adirigo yemiyayi new biye asebiku lenegeru sefa arigo emiyaisibi sew behulum akitacha byinori mani yitelali
  Enatimi, lijuea ehitimi wendimuwa,misitim balebetuwa melikami byihonilati ejguni timeritalechi
  Balehibeti ahunim egizabiheri tibebun yabizalihi zendi tselote New
  Bewineti yeminirew sew hageri bemehonuna tinishi gitim bite silemichachir yemitsifi ayimiro anibaby mehoni Silalebeti ehuni erasen andi hagere wisiti Yale betemetsehafiti layi yalehu New tenderloin
  Z

  ReplyDelete
 34. It is fantastic! Keep it up DAN.

  ReplyDelete