Tuesday, January 31, 2012

ለምሥራቅ ኢትዮጵያ ወገኖቼ ሁሉ


                           

click here for pdf 
                                 ራእየ ዮሐንስ፡- የዓለም መጨረሻ
የተሰኘው መጽሐፍ  
         ቅዳሜ የካቲት 3 ቀን 2004 ዓም  
         በድሬዳዋ ከተማ 
         ትሪያንግል ሆቴል አዳራሽ
         ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 1130 ይመረቃል፡፡

በዚሁ መርሐ ግብር ላይ 

  • በልዩ ልዩ መምህራን እና ሊቃውንት ስለ ራእየ ዮሐንስ ማብራርያ ይቀርባል
  • ስለ መጽሐፉ ዳሰሳ ይቀርባል
  • ስለ ዮሐንስ ራእይ እና ስለ ፍጽሞ ደሴት ፊልም ይቀርባል
  • በተሳታፊዎች ውይይት ይደረጋል
 1.     በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ከአስበ ተፈሪ እስከ ጅጅጋ ያሉ ወገኖች ሁሉ ተጋብዘዋል፡፡
2.     መርሐ ግብሩ በድሬዳዋ የተደረገውም ለምሥራቅ ኢትዮጵያ ነዋሪዎች እድል ለመስጠት ሲባል ነው፡፡
3.     የመግቢያ ካርዱን ከቅዳሜ ጥር 26 ቀን 2004 ዓም በስልክ ቁጥር 0923169899 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

በአንድ የዘመዴ ቤት

አንድ ዘመዴ ቤት ሄጄ ነው፡፡ እናቱ «እስኪ ያንን ነገር ለዳንኤል አሳየው» አለቺው ልጇን፡፡ ልጇ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ ደብተሩን ይዞት መጣ፡፡ ትናንት ሠርቶ ዛሬ ባሳረመው የአማርኛ የቤት ሥራ ሁለት ኤክስ አግኝቷል፡፡ ልጁ ግን ለምን ኤክስ ሊሆን እንደቻለ ሊገባው አልቻለም፡፡ እናቱን ደጋግሞ ጠየቃት፡፡ እርሷም ግልጽ አልሆነላትም፡፡
የተሰጠው ጥያቄ አዛምድ ነው፡፡ እዚያ መካከል «እንደ ወትሮው» የሚል ሐረግ «» ሥር ይገኛል፡፡ «» ሥር ደግሞ «እንደ ሁልጊዜው» የሚል ምርጫ አለ፡፡ ልጁ የመጀመርያውን ኤክስ ያገኘው እነዚህን በማዛመዱ ነበር፡፡ ከዚያው በታች «» ሥር ላለው «መሞከር» ለሚለው ቃል «መጣር» የሚል ተዛማጅ «» ሥር ተቀምጧል፡፡ የሚል ሌላ አዛምድ አለ፡፡

Monday, January 23, 2012

ሰብአ ሰገል


(click here for pdf) በየዓመቱ የልደት በዓል በመጣ ቁጥር ከሚነሡ ሰዎች መካከል ናቸው፡ ሰብአ ሰገል፡፡ ማናቸው? ከየት መጡ? ሀገራቸው የት ነው? ስንት ናቸው? ለምን ዕጣን፣ ከርቤ እና ወርቅ አመጡ? የሚሉት ጉዳዮችም አብረው ይነሣሉ፡፡
ስለ ሰብአ ሰገል የመጀመርያውን መረጃ የሰጠን ቅዱስ ማቴዎስ ነው፡፡ ማቴዎስ በወንጌሉ በምእራፍ ሁለት ላይ የጥበብ ሰዎች መሆናቸውን፣ የመጡት ከምሥራቅ መሆኑን፣ የተመሩት በኮከብ መሆኑን፣ የመጡበት ዘመን ንጉሥ ሄሮድስ ይሁዳን ሲገዛ መሆኑን፣ ሕፃኑ በተወለደ ጊዜ መድረሳቸውን፣ ዕጣን፣ ከርቤ እና ወርቅ በእጅ መንሻነት መስጠታቸውን፣ በኋላም ደስ ብሏቸው በሌላ መንገድ ወደመጡበት መመለሳቸውን ይነግረናል፡፡

Wednesday, January 18, 2012

እኔም ለውጥ አመጣለሁ


እጅግ ሞቃት የሆነ የበጋ ጊዜ ነበር፡፡ በአካባቢው ኃይለኛ ዝናብ አንዳንድ ጊዜም ነጎድጓድ እና መብረቅ እየቀላቀለ ይጥላል፡፡ ፀሐይ ብቻዋን ስትወጣ የአካባቢው ሰዎች ከየቤታቸው ይወጡና ለመንደርዋ ውበት ወደ ሰጣት የባሕሩ$ ዳርቻ ያመራሉ፡፡ ለአመል የምትሆን ብጢሌ ጨርቅ ገላቸው ላይ ጣል ያደርጉና አሸዋው ላይ ተዘርግተው የባሕሩን ነፋስ እና የፀሐይዋን ሙቀት ይኮመኩማሉ፡፡
ዛሬ ግን እንዲህ ማድረግ አልተቻለም፡፡ ዝናቡ ሌሊት ነው የጀመረው፡፡ አብረውት ነጎድጓድ እና መብረቅ ያጅቡታል፡፡ ጋብ አለ ሲባል ደግሞ ውሽንፍር ይነሣል፡፡ ባሕሩም በውሽንፍሩ ቀስቃሽነት ከሥሩ እየተነሣ ዳንግላስ ወደ የብሱ ይጋልባል፡፡ ከዚያም አረፋ ደፍቆ ለምድሪቱም የአክብሮት ስግደት ሰግዶ ይመለሳል፡፡

Tuesday, January 10, 2012

እስከ ሰባት ትውልድ


በበዙ የሀገራችን ጥንታውያን መጻሕፍት እና ትውፊቶች ዘንድ ሰባት ትውልድ የሚለው ብሂል የተለመደ ነው፡፡ «እስከ ሰባት ትውልድ እምርልሃለሁ» የሚለው ቃል በየገድላቱ ይገኛል፡፡ እስከ ሰባት ትውልድ አለመጋባት በአያሌ ማኅበረሰቦቻችን ትውፊታዊም ሃይማታዊም ሕግ ነው፡፡
ከቀደምት የአሜሪካ ሕዝቦች አንዱ የሆኑት የኢሮቆዩስ ሕዝቦች በዚህ የሰባት ትውልድ አስተሳሰብ ያምኑ ነበር፡፡ እነዚህ በዛሬዋ ኒውዮርክ እና አካባቢዋ የነበሩ ጎሳዎች ተባብረው የኢሮቆዩስ ፌዴሬሽን የሚባል አስተዳደር መሥርተው ነበር፡፡ የራሳቸውም ሕገ መንግሥት ነበራቸው፡፡ አሜሪካኖቹ የፌዴራሊዝምን ጽንሰ ሃሳብ የወሰዱት ከእነዚህ ማኅበረሰቦች ነው ብለው የሚከራከሩም አሉ፡፡

Thursday, January 5, 2012

«ድንጋይ ፈላጮች»

click here for pdf 
አንድ ጥበብ አሳሽ ጥበብን ፍለጋ በየሀገሩ ይዞር ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ አንድ መንደር ሲደርስ ሰዎች ድንጋይ ሲፈልጡ ተመለከተ፡፡ ቀና ብሎ ቢያይ በአካባቢው ምንም የሚገነባ ነገር የለም፡፡
 
ወደ አንዱ ድንጋይ ፈላጭ ተጠግቶ «እባክህ ወዳጄ እኔ ለአካባቢው አዲስ በመሆኔ አንድ ነገር ልጠይቅህ ፈለግኩ፣ ለመሆኑ ምን እያደረጋችሁ ነው?»አለው፡፡ ያም ድንጋይ ፈላጭ «ወንድሜ የማደርገው ነገርኮ ግልጽ ነው፤ አንተም ታየዋለህ፤ ድንጋይ እየፈለጥኩ ነዋ»አለው፡፡ ያ ጥበብ አሳሽ ከዚያ እልፍ አለ፡፡ ወደ ሁለተኛውም ሰው ቀረበ፡፡ «ወዳጄ ለሀገሩ እንግዳ ለሰው ባዳ ነኝ፡፡ እባከህ ምን እየሠራችሁ እንደሆነ ንገረኝ?»አለው፡፡ ያም ድንጋይ ፈላጭ «ወዳጄ እኔ የዕለት እንጀራዬን ለማግኘት እየደከምኩ ነው፡፡ ይኼው ነው» ሲል መለሰለት፡፡

Monday, January 2, 2012

ኀዘን እና ደስታ

(click here for pdf)
በየሀገሩ እየዞረች ከልዩ ልዩ ሕዝቦች ጋር መገናኘት የምትወድ አንዲት ፓይለት ነበረች፡፡ በዓለም ላይ ያልዞረችበት ሀገር አልነበረም፡፡

አንድ ቀን ፓይለቷ በሰሐራ በረሃ ላይ ስትበርር የአውሮፕላኑ ሞተር ተበላሸባት እና በፓራሹት ወደ መሬት ወረደች፡፡ የወረደችበትን ቦታ አታውቀውም፡፡ ግን ጭው ያለ በረሃ ነበር፡፡ የት እንዳለች እና ወደ የት መጓዝ እንደምትችል አታውቅም፡፡ በአካባቢዋ ያለው መንደር በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሚገኝም ምንም መረጃ የላትም፡፡

ለብዙ ሰዓታት ካሰበች በኋላ ያላት አማራጭ በአንዱ አቅጣጫ መጓዝ እንደሆነ አመነች፡፡ እናም የምት ችለውን ዕቃ ተሸክማ ጉዞዋን ጀመረች፡፡ በዚያ በረሃ ከሚያጋጥማት የአሸዋ አውሎ ነፋስ ጋር እየታ ገለች፣ በአሸዋው ተራራ ላይ እየወደቀች እና እየተነሣች፣ ከሚያጋጥሟት አራዊት ጋር እየተጋደለች ወደፊት መጓዟን ቀጠለች፡፡

መንገዱ በሁለት ምክንያት አድካሚ እና አሰልቺ ሆነባት፡፡ በአንድ በኩል ወደየት እንደ ምትሄድ በርግ ጠኛነት ባለማወቋ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መቼ እንደምትድረስ ለመገመት ባለመቻሏ፡፡ በአንድ ነገር ግን ርግጠኛ ነበረች፡፡ በመንገዷ ከሚያጋጥሟት ፈተናዎች ይልቅ መንፈሷ ጠንካራ መሆኑን፡፡ ባለ ማቋረጥ ከተጓዘች አንዳች ጠቃሚ ቦታ ላይ እንደምትደርስ፡፡ እናም መጓዝ ቀጠለች፡፡

ይደክማታል ትወድቃለች፡፡ ዐቅም ሰብስባ ትነሣለች፡፡ ተስፋ አትቆርጥም ትጓዛለች፡፡