(click here for pdf) በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ የቅዱስ እንድርያስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ የሆኑት ቄስ እንድርያስ ቶምሶን በ2011 «Christianity in the UAE´ የተሰኘ ምርጥ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡
መጽሐፉ የዛሬዋን የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን ጨምሮ በመላው የዐረቡ ዓለም ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ክርስትና ይተርካል፡፡ በመካከሉ ክርስትና እንዴት ሊጠፋ እንደቻለ በቁፋሮ የተገኙ የአርኬዎሎጂ መረጃዎችን እያጣቀሰ መልስ ለመስጠት ይሞክራል፡፡ ከዚያም ዛሬ በዓረብ ኤምሬት ያለውን የክርስቲያን ሙስሊም ግንኙነት ይተነትናል፡፡
እንድርያስ ቶምሰን መጽሐፉን ሲያጠናቅቁ እንዲህ ብለው ይጮኻሉ «Where are the bridge - builders?»
እስኪ እኔም ጩኸታቸውን ልቀማቸውና በሀገሬ እንደ እርሳቸው «ድልድይ ሠሪው ሆይ የት ነው ያለኸው?» ብዬ ልጩኽ፡፡
በጎሳ እና በጎሳ፣ በእምነት እና በእምነት፣ በባህል እና በባህል፣ በፓርቲ እና በፓርቲ፣ በአመለካከት እና በአመለካከት መካከል ኢትዮጵያ ውስጥ አያሌ አጥሮች ተገንብተዋል፡፡ እነዚህ አጥሮች ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ የመጠበቂያ እና የመከለያ አጥሮች፡፡ አንድ ህልው የሆነ ነገር ራሱን መጠበቁ ተፈጥሯዊም፣ ሕጋዊም፣ ተገቢም ነው፡፡ መኖር አለበትና፡፡ አንድ ሰው ለራሱ ቤት ሠራ ማለት ሌላው ቤት አይኑረው ማለቱ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ለራሱ ተመገበ ማለት ሌላው ይራብ ማለቱ አይደለም፡፡ አንድ ሰው የራሱን ሀብት እና ንብረት ተቆጣጥሮ በሚገባ ያዘ ማለት የሌላውን ሀብት ዘረፈ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ሰው የራሱን ጤና ጠበቀ ማለት ሌላው እንዲታመም አደረገ ማለት አይደለም፡፡ ራስን እና የራስ ማንነት ለመጠበቅ እስከዋሉ ድረስ የመጠበቂያ አጥሮች አስፈላጊ ናቸው፡፡
ችግር የሚከሰተው ለመጠበቂያነት የተሠሩ አጥሮች ወደ መከለያነት ከተሸጋገሩ ወይንም ከመጠበቂያ አጥሮች በተጨማሪ የመከለያ አጥሮች መሠራት ከጀመሩ ነው፡፡ ያለሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ የምኖረው እኔ ብቻ ነኝ፤ ስለ ሌላው አያገባኝም፤ ስለሌላው አላውቅም፤ ያኛው አይመለከተኝም፤ ያ የራሱ ጉዳይ ነው፤ እዚያ ማዶ ጠላቴ አለ፤ በሚሉ ጡቦች ነው የመከለያ አጥር የሚሠራው፡፡
በአንዳንድ የሀገራችን መንደሮች ሰዎች ግቢያቸውን ያጸዳሉ፡፡ መልካም፡፡ ነገር ግን ቆሻሻውን ከግቢያቸው ያወጡና መንደር ውስጥ በሚገኝ ባዶ ቦታ ይጥላሉ፡፡ ሁሉም የመንደሩ ነዋሪ ግቢውን አጽድቶ መንደሩ ግን ቆሻሻ ይሆናል፡፡ ከዚያ የቆሻሻ ክምር የምትነሣው ዝንብ ተመልሳ በእርሱ ቤት ላለመግባቷ ማንም ዋስትና የለውም፡፡
በዚያ ቆሻሻ ክምር አጠገብ ሁላችንም እናልፋለን፤ ወደ ሁላችንም ቤት የሚመጡ እንግዶች ያልፋሉ፤ ከዚያም በላይ ደግሞ የሁላችንም ልጆች በዚያው ይጫወታሉ፡፡ የመንደርዋ ሰዎች አጥር የመከለያ አጥር ነው ማለት ነው፡፡ ከግቢያቸው ውጭ ስለሚደረገው ነገር ምንም ላለማየት የከለሉት አጥር፡፡ የኔ ግቢ መጽዳቱ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ የጎረቤቴ ግቢ ካልጸዳ ግን ዋጋ የለውም፡፡ የእኔ ቤት ሰላም ወሳኝ ነው፡፡ ጎረቤቴ ሰላም ከሌለው ግን መበጥበጤ አይቀርም፡፡ የእኔ ልጆች ጨዋ መሆናቸው የሚያስመሰግን ነው፡፡ የጎረቤቴ ልጆች ዱርዬዎች ከሆኑ ግን በሽታው ላለመዛመቱ ዋስትና የለንም፡፡ በናይጄርያ ያሉ የኢግቦ ጎሳዎች «ልጅን ለማሳደግ የመንደሩ ሰው ሁሉ ያስፈልጋል» የሚል አባባል አላቸው፡፡
እናም እኔን እና ጎረቤቴን አጥር ብቻ ሊያገናኘን፣ ካርታ ብቻ ሊያቀራርበን፣ ሰላምታ ብቻ ሊያዛምደን፣ ቡና ብቻ ሊያወዳጀን፣ ልቅሶ ብቻ ሊያፋቅረን፣ ሠርግ ብቻ ሊያጎራርሰን፣ ኡኡታ ብቻ ሊያጠራራን አይችልም፡፡ የኛን ግቢ ከጎረቤታችን ግቢ የሚያገናኝ ድልድይም ያስፈልገናል፡፡
የደቡብ አፍሪካ ዙሉዎች ዘመናትን ያስቆጠረ አንድ ጠንካራ እምነት አላቸው፡፡ በአጭሩ ሲጠሩት «ኦቡንቱ» ይሉታል፡፡ ሲተነተን ደግሞ «ኡሙንቱ፣ ኙሙንቱ፣ ኛማንቱ» ይላል፡፡ «እኔ ሰው የሆነኩት በሌላው ምክንያት ነው፤ የኔ ሰውነት ካንተ ጋር የተቆራኘ ነው» እንደማለት ነው፡፡ በኦቡንቱ እምነት «አንድ ሰው ሌሎች እየተሰቃዩ እርሱ ሊደሰት፣ የሌሎች መብት ተገፎ የርሱ ሊከበር፣ ሌሎች ደኽይተው እርሱ ሊበለጽግ፣ ሌሎች እየተዋጉ እርሱ በሰላም ሊኖር አይችልም» ይላል፡፡ በሌላው ላይ የሚደርሰው ሁሉ ያገባኛል ብሎ ማሰብ ነው ኦቡንቱ፡፡ «ነጻነት የሚሰፍነው ሁላችንም ነጻ ስንሆን ነው» ይላሉ፡፡
አሁን ሀገር «ኦቡንቱ» የሚሉ ድልድይ ሠሪዎችን ትጣራለች፡፡ ከጎሳ፣ ከመንደር፣ ከክልል፣ ከእምነት፣ የመከለያ አጥር ባሻገር ችግሮችን ማየት የሚችሉ፡፡ ይህቺ ባቄላ ስታድግ ምን እንደምትሆን አሻግረው ማየት የሚችሉ ድልድይ ሠሪዎች፡፡
ድልድይ ሠሪዎች የየራሳቸውን ባህል፣ እምነት፣ ታሪክ፣ አካባቢ፣ ቋንቋ፣ አመለካከት፣ ርእዮተ ዓለም በሚገባ የሚያውቁ የጠነቀቁም ናቸው፡፡ በያዙት ነገር የማይታሙ፣ የራሳቸውን የሚወድዱ እና የሚያከብሩ ናቸው፡፡ ግን ከዚህ ያለፈም ኅሊና አላቸው፡፡ ሌላውንም ይወድዳሉ፣ ያከብራሉ፣ ይረዳሉ፣ ይገነዘባሉ፣ ለሌላውም በጎ ያስባሉ፣ በጎ ይሠራሉ፣ የሌላውም መብት እንዲከበር ይጥራሉ፡፡ ሌላውም ያስፈልገኛል ይላሉ፡፡
ድልድይ ሠሪዎች ፍላጎታቸውን ሳይሆን እውነታውን ይገነዘባሉ፡፡ በጋራ መገናዘብ (mutual understanding) እና በጋራ መከባበር (mutual respect) ያምናሉ፡፡ አንዱ አንዱን ዐውቆት፣ ተረድቶት፣ ፍላጎቱን እና ማንነቱን ተገንዝቦ፣ የሚወድደውን እና የሚጠላውን ዐውቆ በመኖር ያምናሉ፡፡ «አንድን ሰው ባስራብከው ቁጥር አንተን እንዲበላህ እያስተማረከው ነው» የሚለውን ይረዳሉ፡፡
በመናነናቅ፣ በማንቋሸሽ እና በመሰዳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም፡፡ አንድ ሰው ወይንም አካል ለመከበር የእኔ ዓይነት መሆን አይጠበቅበትም፡፡ ማክበር መቀበል አይደለም፡፡ የሌላውን ርእዮተ ዓለም ማክበር የሌላውን ርእዮተ ዓለም ትክክል ነው ብሎ መቀበል፣ የሌላውን እምነት ማክበር የሌላውን እምነት ትክክል ነው ብሎ መቀበል አይደለም፡፡ የሌላውን ማክበርም የራስን ከመናቅ የሚመጣም አይደለም፡፡
ማክበር ሰላማዊነትን መግለጥ ነው፡፡ ማክበር ለመከበር ነው፡፡ ማክበር ተግባቦትን ለመፍጠር ነው፡፡ የበላይ እና የበታች፣ አጥፊ እና ጠፊ፣ ሆኖ መግባባት አይቻልም፡፡ መግባባት የሚቻለው መከባበር እና እኩልነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡
ታሪካዊ እና ወቅታዊ እውነታዎች አሉ፡ እነዚህ እውነታዎች ለተለያዩ አካላት ልዩ ልዩ ጠቀሜታዎችን በጊዜያቸው ሰጥተው ይሆናል፡፡ ለምሳሌ በታሪካዊ ምክንያት የተነሣ ኤምሬት ውስጥ ብዙ መስጊዶች አሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ አማርኛ በኢትዮጵያ በብዙ ቦታዎች የመነገር ዕድል አግኝቷል፤ በአሜሪካ የሚኖሩ አፍሪካ አሜሪካውያን ቋንቋቸው ጠፍቷል፡፡ በላቲን አሜሪካ ነባሩ ቋንቋ ጠፍቶ ወይንም ደክሞ ስፓኒሽ የበላይነት ይዟል፡፡
እነዚህ ታሪካዊ እውነታዎች ናቸው፡፡ ሆነዋል፡፡ መከባበር እና መገናዘብ ማለት እነዚህን እውነታዎች ወደ ኋላ ሄዶ መቀየር ማለት አይደለም፡፡ ወደፊት ተጉዞ የተሻ ለማድረግ መሞከር እንጂ፡፡ በኤምሬትስ ክርስቲያኖች መብት አገኙ ለመባል የመስጊዶችን ያህል ቤተ ክርስቲያኖች መሠራት አያስፈልጋቸውም፡፡ ለክርስቲያኖች የሚበቃ ቤተ ክርስቲያን እንጂ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር ልክ መስጊዶች ሲሠሩ አይደለም የሙስሊሞች መብት የሚከበረው፡፡ ለሙስሊሞች በቂ የሆኑ የአምልኮ ቦታዎች ሲኖሩ እንጂ፡፡ ኦሮምኛ ሲያድግ እንጂ አማርኛ ዕድገቱ ሲገታ አይደለም መገናዘብ እና መከባበር የሚቻለው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ለመገናዘብ እና ለመከባበር ከትናንቱ ይልቅ የነገውን ማየት የተሻለ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በሀገራችን ትልቁ ክርክር የሚደረገው በትናንት ላይ ነው፡፡ ከትናንት ይልቅ ግን ነገ ያግባባናል፡፡ ትናንትን መቀየር ከባድ ነው፡፡ ነገ ግን በእጃችን ነው፡፡ አሁን ያለው ዓለም ለነገሮች የሚሰጠን ምርጫ ሁለት ነው፡፡ ወይ ሁላችን የሚበቃንን ያህል እንጠቀማለን፣ ያለበለዚያ ማናችንም አንጠቀምም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሊጠቀሙባት የሚችሉባት ዓለም እያለፈች ነው፡፡ ሰላም ከጦርነት አለመኖር የምትገኝ አይደለችም፤ ከጋራ ተጠቃሚነት እንጂ፡፡ ሁላችንም እኩል ላንጠቀም እንችል ይሆናል፡፡ ሁላችንም የሚበቃንን ያህል መጠቀም ግን አለብን፡፡
ለዚህ ነው ከአጥር ሠሪዎች ይልቅ ዛሬ ድልድይ ሠሪዎች የሚያስፈልጉን፡፡ ሕዝብ እና ሕዝብ፣ ጎሳ እና ጎሳ፣ አማኞች እና አማኞች፣ ፓርቲዎች እና ፓርቲዎች በየአጥራቸው ተከልለው አንዱ ሌላውን እያጮለቀ እያየ ተቀምጧል፡፡ አጥሮቹ የጠላትነት መንፈስን አዳብረዋል፡፡ አጥሮቹ የተከላካይነትን ስሜት አምጥተዋል፡፡ ሁሉም እየተጠቃሁ ነው ብሎ እንዲያስብ አድርገዋል፡፡ አጋጣሚውም ሲገኝ አጥር ተሻግሮ ትንኮሳ ለመፈጸም እና መልሶ አጥር ውስጥ ገብቶ ለመሸሸግ አመቺ ሆነዋል፡፡
እነዚህ አጥሮች ሰዎች በግላቸው ድካማቸውም ሆነ ብረታታቸው እንዳይታይ አድር ገዋል፡፡ «አማራ እንዲህ አደረገ፣ ኦሮሞ እንዲህ አደረገ፣ ትግሬ እንዲህ አደረገ፣ ወላይታ እንዲህ አደረገ፣ እስላም እንዲህ አደረገ፣ ክርስቲያን አንዲህ አደረገ፣ ገዥው ፓርቲ እንዲህ አደረገ፣ ተቃዋሚ እንዲህ አደረገ» እየተባለ በአጥሮቹ ውስጥ ስላሉት ሁሉ ነው የሚነገረው፣ የሚከሰሰው፣ የሚወቀሰው፡፡ አጥሮቹ መደበቂያ ሆነዋል፡፡
እነዚህ አጥሮችን የሚያገናኙ ድልድዮች ያስፈልጋሉ፡፡ እንድንነጋገር፣ እንድንከራከር፣ የጋራ ጉዳይ እንድ ንፈልግ፣ በሚያግባባን ተግባብተን የሚያለያየንን አክብረን እንድንኖር የሚያደርጉ የመገናኛ ድልድዮች ያስፈልጉናል፡፡ ከዚህኛው አጥር አልፈው በዚያኛው አጥር ውስጥ ባሉ ወገኖችም ጭምር የሚከበሩ፣ የሚታፈሩ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ እነርሱ ናቸው ድልድይ መሥራት የሚችሉት፡፡
እዚያ ማዶ ጢስ ይጤሳል
አጋፋሪ ይደግሳል
ያችን ድግስ ውጬ ውጬ
ከድንክ አልጋ ተገልብጬ
የምትለው የልጆች ዜማ እንዴት ውብ ናት፡፡ ጢሱ እዚያ ማዶ ነው፡፡ የጠላት ጢስ አይደለም፤ የጠላት ከተማ ተቃጥሎ አይደለም፤ ደግ አደረጋቸው አላሉም፤ ድግስ ነው፡፡ ድግሱ ጠላት ሞቶ ለተዝካር አይደለም፡፡ አጋፋሪ ናቸው የደገሱት፡፡ እናም እዚያ ማዶ የተደገሰው ድግስ የኔም ነው ብለው ያስቡና ያቺን ድግስ አልጋ ላይ እስክገለበጥ ድረስ እውጣለሁ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ጠላትነት የለም፤ እነርሱ ድልድይ ሠርተው ነበር፤ ግን ማን አፈረሰው?
እናም ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፡፡
ትውልድን ከትውልድ አገናኙ፤
ጎሳን ከጎሳ አቀራርቡ፣
አማኝን ከአማኝ አስተዋውቁ፣
ተባልተን እንዳናልቅ፣ ቂም እና ጥላቻ ብቻ ለትውልድ እንዳይተርፍ፣ አንዱ ስለ ሌላው ክፉውን ብቻ እንዳያውቅ፣ እዚያ ማዶም ዘመድ አለኝ የሚል እንዲኖር፣ «አጋፋሪ ይደግሳል» እንዲል፤ እዚያ ማዶ ሆኖ ስለ እነዚህ የሚሟገት፣ እዚህ ማዶም ሆኖ ስለ እነዚያ የሚቆረቆር እንዲኖር
ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፤
ይህቺ ሀገር የሁላችንም መሆን አቅቷት የማናችንም ሳትሆን እንዳትቀር፤ እኛ እና እነርሱ፣ ይህ እና ያ፣ እዚህ እና እዚያ፣ በሚለው አጥር መካከል «እኛ ሁላችንም» የሚል ድልድይ ትገነቡ ዘንድ፣
ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፡፡
እንደ ነዌ እና ዓልአዛር አንዱ በገነት ሌላው በሲዖል ሆነን «ከኛ ወደ እናንተ፣ ከእናንተም ወደ እኛ የሚወስድ መንገድ የለም» እያልን ነውና
ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፣
ሁላችንም ተያይዘን ወደ ገነት እንገባ ዘንድ ድልድዩን ገንቡ፡፡
በየቢሮው፣ በየሠፈሩ፣ በየሻሂ ቤቱ፣ በየታክሲው፣ በየመገናኛ ብዙኃኑ፣ በየስብሰባው፣ በየዕድሩ የመከለያ አጥር የሠራ ሰው ስታዩ የዘጋውን በር አስከፍታችሁ ድልድይ ሥሩለት፡፡ ዝም አትበሉት፡፡ ምሽግ ይዞ ፈርቶም አስፈርቶም እንዲኖር አትተውት፡፡ ሌላም መኖሩን ያይ ዘንድ የመሻገርያ ድልድይ ሥሩለት፡፡
ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፡
አቡዳቢ
እስከ ዛሬ ድረስ በሀገራችን ትልቁ ክርክር የሚደረገው በትናንት ላይ ነው፡፡ ከትናንት ይልቅ ግን ነገ ያግባባናል፡፡ ትናንትን መቀየር ከባድ ነው፡፡ ነገ ግን በእጃችን ነው፡ ይህቺ ሀገር የሁላችንም መሆን አቅቷት የማናችንም ሳትሆን እንዳትቀር፤ እኛ እና እነርሱ፣ ይህ እና ያ፣ እዚህ እና እዚያ፣ በሚለው አጥር መካከል «እኛ ሁላችንም» የሚል ድልድይ ትገነቡ ዘንድ፣
ReplyDeleteድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፡፡
ዮናስ አበበ
Egziabher Yebarkehe tekekeleya terinew
ReplyDeleteWonderful Article.
ReplyDeletethinking tomorrow is the only way for our peace,prosperity, and integration.we can learn from the past but we cannot change the past b/ we cant live in it,but we can change today and tomorrow b/c we are living in it.God bless You
This is a very good view and touchy presentation. God Bless you and God Bless Ethiopia!
ReplyDeleteEthiopia le Zelalem Tinur!
it is real message of the time. God bless you.
ReplyDeleteby the way, do we have Ibo or Igbo in Nigeria?
Thank you.
Thanks Dn. Daniel, What a pretty nice article.....
ReplyDeleteYesterday is passed, today is ready cash, and tomorrow is promissory. Lets use today's and think for tomorrow. Forgot yesterday learn from the mistakes of past. Stay blessed Dani!!!
Yes of course, it is clear that thinking tomorrow is better than killing time on the past. But the past is still important to shape the future in right way. The problem, however, comes when asking who has gone beyond talk?
ReplyDeleteእንዲህም እየተነገረ ይህች አገር ድልድይ ገንቢወችን ካላገኘች .... ???....
ReplyDeleteዳኒ አንተስ የዚግነት ግዴታህን እየተወጣህ ነው ... ሌሎቻችንስ ?
እግዚአብሄር ያበርታህ ..
እስከ ዛሬ
ReplyDeleteድረስ በ ገራችን ትልቁ ክርክር የሚደረገው በትናንት ላይ ነው፡፡ ከትናንት ይልቅ ግን ነገ ያግባባናል፡፡
ትናንትን መቀየር ከባድ ነው፡፡ ነገ ግን በእጃችን ነው፡፡
Thank you,This blog is my school
ReplyDeleteሰላም ደኒ እንደምን ከረምክ አስተያየት ከመስጠት ብጠፋም ከማንበብ ግን አልጠፋሁም ደኒ ምንእንደምል አላውቅም የምታነሳቸው ነጥቦች ወይም ሀሳቦች ሁሌይገርሙኛል ምክንያቱም ከትውልዱ አንድወደፊት የቀደምክ ይመስለኛል አለበለዚያማ መጣጥፎችህ እንዲህ ሁሌየልባችንን ቁስላችችንን ትኩሳታችችንን ህመማችችንን እንዲሁም ግርምታችችንን እየቆሰቆሱ ሁላችንንም ዳኒ ምንአለ እያልን ብሎግህን በቀን ሁለቴ እንድንጎበኝ ባልሆን ነበር ለማንኛውም ከማያልቅ ተሰጥኦው ያካፈለህ አምላካችን የተመሰገነይሁን ላንተም ረጅም እድሜ ከማስተወልጋር ለኛም ያነበብነውን (የተማርነውን ) በስራ ለመተርጎምና እያዳንዳችንም በግልና በጋራ ያጠርነው የመጠበቂያ አጥራችን እንዳለሆኖ የመገናኛ ድልድይ ለመስራት የበቃን ያድርገንና ሀገራችንን ከክፉ ለመጠበቅ የበቃን ያድርገን አሜን ::
ReplyDeleteplease let us do our better to make our country peace full, other-ways the response of the victimed people is may be the cause more damage,Dn.Dani you are one of responsible persons,to stop our tear seeing burn of our holly mekides,silence is not indicate...
ReplyDeleteየዛሬው የቤተሰብ ራት ሞቅ ደመቅ ብሏል።
ReplyDeleteሰብሰብ ብለን እየተዝናን ይህን ተመገብን
ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፡
ትናንትን መቀየር ከባድ ነው፡፡ ነገ ግን በእጃችን ነው፡፡ ለዚህ ነው ከአጥር ሠሪዎች ይልቅ ዛሬ ድልድይ ሠሪዎች የሚያስፈልጉን፡፡ «ኦቡንቱ» ብለናል።
አቤቱ አምላካችን ሆይ!ድልድዩን ይሰሩ ዘንድ አማላጆቻችንን ወዳጆችህን ቅዱሳንን ላክልን፡፡
ReplyDeleteአቤቱ አምላካችን ሆይ! ድልድዩን ይሰሩ ዘንድ ወዳጆችህን ቅዱሳንን ላክልን፡፡
ReplyDeleteGod bless u. this is what ethiopia need today
ReplyDeleteአመቱ የሰላም የፍቅር የጢና ዓመት ያድርግልን::ግሩም ጽሑፍ ነው:: ላንተ ዘላቂ እውቀት ለኛ የሚሰማ ጆሮ ጊታ ይስጠን:: በርታ::
ReplyDeleteነገሩ ሁሉ ግሩም ነው ዳኒ፣ አንድ ኦሮሚያ ክልል ውሥጥ የተዋቀረ ፓርቲ ምን ብሎ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄደ መሰላችሁ፤
ReplyDeleteእኛ ብንመረጥ፤ ኦሮምኛ ቐንቐን የሀገሪቱ የስራ ቐንቐ እናደርጋለን፤ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያሉ ነገር ግን የአማርኛ ስም ያላቸውን ቦታወች ኦሮምኛ እናደርጋለን፤ የኦሮሞን ህዝብ ነጣነት እናስከብራለን፤ ወዘተ. ተመልከቱ እስኪ ይህን ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ምርጫ ነው ወይስ የሀገር ምርጫ ነው የሚወዳደረው?/ እውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው የቦታ ስም ለውጥ ነው ወይስ ዕድገት? እውን የኢትዮጵያ ህዝብ የፈለገው ኦሮምኛ ቐንቐ የሀገሪቱ የስራ ቐንቐ መሆኑን ነው ወይስ ልማትን ነው የናፈቀው? ዕውን ኢትዮጵያ አላድግ ያለቸው አዳማ ናዝሪት ስለተባለች ነው? እኛ እኮ የማንኛውምቐንቐ ይሁን፤ እድገት ነው የፈለግነው፤ ልማት ነው የናፈቅነው፤ መብት ጥሰት ነው እኮ የመረረን፡፡ አስቡት ይህ የፖለቲካ ፓርቲ ማን ነው ሊመርጠው የሚችለው? በእሡ እይታ የኦሮሚያ ህዝብ ሊል ይችላል፡፡ የኦሮሚያ ህዝብ ኢትዮጵያዊ አደለም እንዴ? የኦሮሚያ ህዝብ የሚፈልገው ዕድገት ነው ወይስ የቦታ ስም ለውጥ?
ዶ/ር መራራ ጉዲና፡ በባለፈው ስለ አባይ መገደብ አስመልክቶ ቃለመጠይቅ ተደርጎላቸው ነበር፤ ከሰማችሁ፡፡ መልሳቸውም የሚከተለው ነበር፡-
ጋዜጠኛ፡- ዶ/ር መራራ፤ አባይ በመገደቡ ምን ተሠማዎት፤ህዝቡ ትልቅ ዕንቅስቃሴ እያደረገ ነው?
ዶ/ር መራራ፡- ሚን ኢነሱ እኮ የኢህአዴግ ተከታዮች ናቸው፡፡
ጋዜጠኛ፡- ምን ለማለት ፈልገው ነው; ግልጥ ያርጉት እስቲ?
ዶ/ር፡- የአባይን ነገር ለአባይ ልጆች ብቲሰጭ አይሻልም፡፡
ጋዜጠኛ፡- የአባይ ነገር እኔን አይመለከተኝም እያሉ ነው?
ዶ/ር፡- ተይ እባክሽ ከዘመዶቸ ጋር ታጣይኛለሽ
ተመልከቱ እስኪ፤ የዶ/ሩ ንግግር ምንን ያመለክታል? የእሳቸው እይታ ከምን አቅጣጫ ነው? አስቡት እስኪ እድሉ ቢያጋጥመን አገር እንመራለን ተምረናል ብቁ ነን ብለው ከሚያስቡ ተቃዎሚዎች የአባይ ድልድይ መገደብ ለኛ አያስፈልግም ማለት ምን ይሉታል? እስኪ ከኛ ባለፈ እናስብ አንድ የሚያደርገን (shared vision) ይኑረን አሰኪ፣ ናሳ የጠፈር ምርምር ውስጥ ያለች ፅዳት በማፅዳት ላይ ሳለች ምን እያረግሽ ነው ተብላ ለተጠየቀችው ጥያቄ ወደ ጨረቃ ሰው ላመጥቅ ነው ነበር ያለችው የ አርባ ቀን እድሌ ማፅዳት ነው እያፀዳሁ ነው አላለችም እሶ ያንን ቦታ ስታፀዳውና ወደ ጨረቃ የሚወረወረው ሰው ሲገባ ከፅዳት ጀምሮ ያለው አካባቢያዊ ሰላም ተልእኮው ላይ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠንቅቃ ታውቃለች:: ዳኒ አንተ ከመጮህ አልቦዘንክም; ቻይናዎች እንድ የሚሉት አባባል አላቸው "ልጂ ካልተማረና የሚገባው ቦታ ካልደረሰ የሚወቅሰው አባቱን ነው" አንተ የነገው ትውልድ ከሚጠይቀው ጥያቄ ለመዳን ቃጭሉን እያቃጨልክ ሀዝበኒን ለማንቃት ደክመሀልና እግዚአብሄር ይባርክህ::ይህን ፅሁፍ ያነበባችሁ የመንግስት አካላት ተቃዋሚዎች የሐይምኖት አባቶች እና ሌሎችም ካላችሁ እባካችሁ አስተውሉ :መቸም አንዴውኑ ማስተወል ተስኖችሆል!!!
ሰላም ዳኒ ጥሩ እይታነው ይህ አጥር መፍረስ አለበት መንፈሳዊ ሰባክያንም ስብከት ማለት የሌላውን እምነት መንቀፈና ማቃለል ሳይሆን ምህመኑን የሚያንጽ ትምህርት ላይ ቢያተኩሩ መልካም ነው፡፡የሌላውን እምነት ማክበር የሌላውን እምነት ትክክል ነው ብሎ መቀበል አይደለም እኔ ብርሃንን ከተሰበኩኝ ብርሃኔ በሰው ፊት ይበራል፡፡ ያትክክል ያልሆነ እምነት የያዘው ሰውም የእኔን ብርሃን አይቶ ይመጣል፡፡ ነገር ግን እኔ ጨለማ ሆኜ እንዴት ጨለማን እከሳለሁ መጀመሪያ ብርሃን መሆን ያስፈልጋል፡፡
ReplyDeleteእንደዚህ አይነት መልካም አስተሳሰብ ቢኖረንማ የት በደረስን ነበር፡፡ በነበር ሆነ እንጅ፤ነገር ግን አሁንም ይቻላል ትልቅ ለመሆን በሰውነት በብልጽግና ...ወዘተ፡፡ ግን ምን አገባህ ትባላለህ ትኮረኮምም አለህ፤ በማህበረሰባችንም አይ እሱ…. የሚል ቅጽል ስም የሰጥሀል… ወዘተ፡፡ ስለዚህ ነገ የእኛ ናት መልካሙን እንያዝ ፤እንስራ ስንል ክፉውን የሚጋፈጥ ወኔ ይኖረን ይሆን? ዲንፕል
ReplyDelete«አንድን ሰው ባስራብከው ቁጥር አንተን እንዲበላህ እያስተማረከው ነው» የሚለውን ይረዳሉ፡፡
ReplyDeleteበመናነናቅ፣ በማንቋሸሽ እና በመሰዳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም፡፡ አንድ ሰው ወይንም አካል ለመከበር የእኔ ዓይነት መሆን አይጠበቅበትም፡፡ ማክበር መቀበል አይደለም፡፡ የሌላውን ርእዮተ ዓለም ማክበር የሌላውን ርእዮተ ዓለም ትክክል ነው ብሎ መቀበል፣ የሌላውን እምነት ማክበር የሌላውን እምነት ትክክል ነው ብሎ መቀበል አይደለም፡፡ የሌላውን ማክበርም የራስን ከመናቅ የሚመጣም አይደለም፡፡
ማክበር ሰላማዊነትን መግለጥ ነው፡፡ ማክበር ለመከበር ነው፡፡ ማክበር ተግባቦትን ለመፍጠር ነው፡፡ የበላይ እና የበታች፣ አጥፊ እና ጠፊ፣ ሆኖ መግባባት አይቻልም፡፡ መግባባት የሚቻለው መከባበር እና እኩልነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡
' አቤቱ አምላካችን ሆይ! ድልድዩን ይሰሩ ዘንድ ወዳጆችህን ቅዱሳንን ላክልን፡፡ '
Mamush,MN
It's really impressive,
ReplyDeleteEvery body practicing it, we don't have to point our finger to others, each of us responsible for the consequence b/c we are practicing discrimination, violence, prejudice, dislike and injustice,,, based on race( tigre, oromo,amhara,,,,). To overcome these problems everybody should look for him/hersef rather to point on others.
kezare jemiro hulum atirun yaferis dildunim yisira::"atirunim inafersalen dildunim ingenebalen yesemayim amilak yakenawinilinal"yihun yideregilin
ReplyDeleteD/n Dani tebarek ejig tirue hasab new yaneshaw betam des yemil geletsa. Medihanealm begown endnasb yirdan melkam yehonewn ednsera yagzen lantem yeblete mastewal yisth. Yanten tsihuf manbeb bemechale edlegna negn. Regim edme ena tena yisth. Betam amesegnalhu kelb!
ReplyDeleteእስከ ዛሬ
ReplyDeleteድረስ በ ገራችን ትልቁ ክርክር የሚደረገው በትናንት ላይ ነው፡፡ ከትናንት ይልቅ ግን ነገ ያግባባናል፡፡
ትናንትን መቀየር ከባድ ነው፡፡ ነገ ግን በእጃችን ነው፡፡
i liked it.... but one more thing to add....last time the narration on ALEKA GEBREHANA" on FM 97.1.... I T WAS VERY NICE BUT I DON'T KNOW WHY U WARE A LITTLE RUSHING.IT COULD BE BECAUSE OF THE GIVEN TIME, U HAD S.THING TO DO OR MAY BE OUT OF U'R CONSCIOUS MIND.....BUT GENERALLY IT WAS VERY NICE!!!
ReplyDeleteBINI ZEGETESEMANI
ዳኒ ሁሌም ሃሳቦችህ ጥሩ ናቸው:: እኛ ግን ልባችን ደነደነ:: እንስማማ: ሃሳብ ለሃሳብ እንለዋወጥ: የጋራ ስብሰባም ይኑረን: ወይም ያጠፋው ከጥፋቱ ይመለስ ለማለትም ድፍረቱን አጣን:: ብንደፍርም አሸባሪ እንባላለን:: ግራ ገባን:: እግዚአብሔርም ዝም ብሎናል:: ለማንኛውም አንተ መጩህሕን አታቁዋርጥ:: እኔም ይህን ሼር ማድረግ እፈልጋለሁ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ስለሚጠቁም..
ReplyDeletehttp://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=qT6sdABiCzk
Ubuntu = humanity to others = I am what I am because of who we all are
ReplyDeleteThank you Daniel, what a blessing!
ReplyDeleteዳንኤል
ReplyDeleteCan I ask you something?
ለመሆኑ ይህን ድልድይ ከየት አገኘኸው ባክህ ?
ትልቁን የድልድይ ግንባታ ስራ የተያያዝከው አንተ በመሆንህ በርታ አምላክ ይደግፍህ።ሌሎቻችን ብንችል ዳንኤል ለሚያደርገው የድልድይ ስራ እንተባበር ባንችል ሰራ አናደናቅፍ። ይህን ማልቴ ብዚሁ ጡመራ ላይ በሚገለጹ አንዳንድ አስትያየቶች የሚይሳዝኑና አንዳንዴም እሰራልሁ ብሎ ለተነሳ ተስፋ የሚይስቆርጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስልተመለከትኩ ነው።
ReplyDeleteእኔም በስንት መከራ በአማርኛ መጻፍ በመቻሌ በጣም ትደሰቻለሁ።
ሙሉጌታ ሙላቱ
ከ ቫንኩቨር ድሴት
በሌላ በኩል ደግሞ ለመገናዘብ እና ለመከባበር ከትናንቱ ይልቅ የነገውን ማየት የተሻለ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በሀገራችን ትልቁ ክርክር የሚደረገው በትናንት ላይ ነው፡፡ ከትናንት ይልቅ ግን ነገ ያግባባናል፡፡ ትናንትን መቀየር ከባድ ነው፡፡ ነገ ግን በእጃችን ነው፡፡ አሁን ያለው ዓለም ለነገሮች የሚሰጠን ምርጫ ሁለት ነው፡፡ ወይ ሁላችን የሚበቃንን ያህል እንጠቀማለን፣ ያለበለዚያ ማናችንም አንጠቀምም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሊጠቀሙባት የሚችሉባት ዓለም እያለፈች ነው፡፡ ሰላም ከጦርነት አለመኖር የምትገኝ አይደለችም፤ ከጋራ ተጠቃሚነት እንጂ፡፡ ሁላችንም እኩል ላንጠቀም እንችል ይሆናል፡፡ ሁላችንም የሚበቃንን ያህል መጠቀም ግን አለብን፡፡
ReplyDeletethis bad government have to do better thing onwards and let not give chance to them for giving their bad politics to us.
thank you brother
Dear Daniel,
ReplyDeleteI am writing you from Hargessa, Somaliland. What I strongly underscored that mutual understanding and respect are highly required. Don't expect to be respected by others unless and otherwise you respect others.
It was said that love your neighbor and hate your enemy. But God tell you, love your enemies and pray for those who persecute you, that you may be children of your Father in heaven. He causes his sun to rise on the evil and the good, and sends rain on the righteous and the unrighteous. If you love those who love you, what reward will you get? Are not even the tax collectors doing that? And if you greet only your own people, what are you doing more than others? Do not even pagans do that? Be perfect, therefore, as your heavenly Father is perfect.
I like your expression that is posted below:
ተባልተን እንዳናልቅ፣ ቂም እና ጥላቻ ብቻ ለትውልድ እንዳይተርፍ፣ አንዱ ስለ ሌላው ክፉውን ብቻ እንዳያውቅ፣ እዚያ ማዶም ዘመድ አለኝ የሚል እንዲኖር፣ «አጋፋሪ ይደግሳል» እንዲል፤ እዚያ ማዶ ሆኖ ስለ እነዚህ የሚሟገት፣ እዚህ ማዶም ሆኖ ስለ እነዚያ የሚቆረቆር እንዲኖር
ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፤ ይህቺ ሀገር የሁላችንም መሆን አቅቷት የማናችንም ሳትሆን እንዳትቀር፤ እኛ እና እነርሱ፣ ይህ እና ያ፣ እዚህ እና እዚያ፣ በሚለው አጥር መካከል «እኛ ሁላችንም» የሚል ድልድይ ትገነቡ ዘንድ፣ ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፡፡ እንደ ነዌ እና ዓልአዛር አንዱ በገነት ሌላው በሲዖል ሆነን «ከኛ ወደ እናንተ፣ ከእናንተም ወደ እኛ የሚወስድ መንገድ የለም» እያልን ነውና: ድልድይ ገንቢዎች ሆይ ኑ፣
ሁላችንም ተያይዘን ወደ ገነት እንገባ ዘንድ ድልድዩን ገንቡ፡፡
በየቢሮው፣ በየሠፈሩ፣ በየሻሂ ቤቱ፣ በየታክሲው፣ በየመገናኛ ብዙኃኑ፣ በየስብሰባው፣ በየዕድሩ የመከለያ አጥር የሠራ ሰው ስታዩ የዘጋውን በር አስከፍታችሁ ድልድይ ሥሩለት፡፡ ዝም አትበሉት፡፡ ምሽግ ይዞ ፈርቶም አስፈርቶም እንዲኖር አትተውት፡፡ ሌላም መኖሩን ያይ ዘንድ የመሻገርያ ድልድይ ሥሩለት፡፡
We need bridge builders who will help us to cross to the more respectful and much understandable world. Let we throw down " Us versus them" mind setup. May God bless Ethiopia.
miliyon sebsibe to adama university :- bewnet daniel betam tiru eyeta new adama university wist ante sigat yasaderebih yerasn bicha yemaseb neger tekesto neber negerum yebher tile neber. Behahun sehat yihe yebher tile beye universitiw eyetesfafa yemigegn sihon slezihe neger ande litlen yigebal enena guadegnochem beuniversitiw yalew neger sigat wist keton A.A new yalenew. egzihabher yirdah.
ReplyDeleteketlant yelike nege yagebabanal. what a fantastic expression it is!
ReplyDeleteዳ/ዳኒ በጣም ሁልግዜ የሚገርመኝ ድልድይ ሰሪዎች ኑ የዛሬዎን ኢትዮጵያን ገንቡ በለን እንድንጠራ ማድረግሕን ወድጀዋለሁ፤ ሆኖም እያንዳንዱ በመጀመርያ የልቦና አጥር መሰባበር አለበት እራሱን ከእራሱ ጋር አናቦ ካስታረቀ ቦኃላ የእራሱን ድልድይ መገንባት ይጀምራል ፈረሳይኞች እንደሚሉት «እያንዳንዱ የእራሱን ቤት ስያፅዳ አገር ትፀዳለች » ነው የሚሉት እና ጎበዝ ምን እንጠብቃለን ምስራቅ አውሮፓ ሩማንያ አገር የለሽ እንደሚባሉት «ሲጎነሪ»ከመባል ለመዳን ዛሬን መኖር ስንችል በትናንትናዎች በኖሩት ስንቆዝም ዛሬ መኖሬችን አልፎ ለነገ ስንደረደር የዛሬ ድልድዩን መገባታችንን አልፎብ እንዳንቀር ቆመን የምናስብበት ሰአት አሁን ነው !!!
ReplyDeleteHello dear dani. Ur effort is one of z bridge building process in Ethiopia -im always optimistic -it is possible!. As one said above me, at least we must not discourage ur selfless efforts in a very anti-unity,anti-nationalist and ignorant political sphere in z ruling and opposition parties and z public at large. Anyway they r ur targets too. Wish u all z best.
ReplyDelete"«አማራ እንዲህ አደረገ፣ ኦሮሞ እንዲህ አደረገ፣ ትግሬ እንዲህ አደረገ፣ ወላይታ እንዲህ አደረገ፣ እስላም እንዲህ አደረገ፣ ክርስቲያን አንዲህ አደረገ፣ ገዥው ፓርቲ እንዲህ አደረገ፣ ተቃዋሚ እንዲህ አደረገ»" i quoted this to our Politicians, medias
ReplyDeleteand governmental leaders, i hate the way to present the past history of Ethiopian people.after all they are trying to keep us on revenge up on each others! in other hand i Sense they are the one to be bridge builders for goodness!! thank you d/n daniel!!!
ebakachihu ategebachin yalutin hulgizee sile tilant bicha yemiyawerutn "egelee yetebale biher siletebedele zare kalibedele weyim kalitegenetele selam yelem " yemilutin hulachinim dilidiy enihunachew.
ReplyDeleteDani ene yetechelegnin etiralehu, mechem ategebe lalut dilidy kehonku yegid media ayasifeligegnim.
Rejim edime yistilign
Tesfahun PHX, AZ
ጢሱ እዚያ ማዶ ነው፡፡ የጠላት ጢስ አይደለም፤ የጠላት ከተማ ተቃጥሎ አይደለም፤ ደግ አደረጋቸው አላሉም፤ ድግስ ነው፡፡ ድግሱ ጠላት ሞቶ ለተዝካር አይደለም፡፡ አጋፋሪ ናቸው የደገሱት፡፡ እናም እዚያ ማዶ የተደገሰው ድግስ የኔም ነው ብለው ያስቡና ያቺን ድግስ አልጋ ላይ እስክገለበጥ ድረስ እውጣለሁ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ጠላትነት የለም፤ እነርሱ ድልድይ ሠርተው ነበር፤ ግን ማን አፈረሰው?
ReplyDeleteEre bakachu blogkillers asteyayet sechiwechi... dont make copy and paste of Dani's Work!!! Beenante asteyayet Mikinyat yihin blog metew alebigni endie? Dani ecko endi yale neger mekiret endalebet new eyetare yalew enante gin esu yetsafewun Copy and paste tadergalachu!!!! asteyayet kelelachu "amesginalehu" bilachu metsaf bicha yibekal alebelezia gin ....plz
ReplyDeleteዳኒየ...ይመስለኛል ድልድይ እንገነባ ዘንድ ድልድይ በሆነው ጽሁፍህ ላይ እየተንሸራሸርን ያለነው ባንተ ግቢ ውስጥ የምንኖረው ሰዎች ብቻ ነን ብየ አስባለሁ፡፡ብዙ ኢትዮጵያውያን በመከለያ አጥሮቻቸው ተደበቀው የነደፍከውን የድልድይ ፕላን እንዳያዩ በሚያስችል ፍራቻና ጥላቻ ውስጥ ያሉ ይመስለኛል፡፡ሥለዚህ መምህር ዳኒ ..ባንድ እጅ አይጨበጨብምና እኛ ብቻ ድልድዩን መስራት ብንጀምር ምናልባችም **ድልድይ ሰርተው ሊዘርፉን መጡ** ተብለን በሌሎች አጥር ነዋሪዎች ልንከሰስ እንችላለን፡፡ስለሆነ ዲ/ዳኒ ከያንዳንዱ አጥር ነዎሪ ስለኢትዮጵያ በጎ የሚተልሙት ጋር ተባብረህ አንድ **ብሎገ-ድልድይ** ብትገነቡ እና በሁሉም አጥር ስላለው ሀገራዊ አስተሳሰብ ብንወያይ መልካም ነው፡፡ለኛም ከሌሎች አጥር ነዋሪዎች ዘንድ ልናከብራቸው የሚገቡ ሰዎችን ብታስተዋውቀንና ያንተን ብሎግ እንደ ድልድይ ተጠቅመው በኛ አጥር ውስጥ መከባበርን እንዲሰብኩ እድል ብትስጣቸው እና አንተም እንዲህ አይነቶቹ ሀገራዊ ሃሳቦችህን በሌሎች ግቢ ጦማሪዎች ገጽ ላይ በማስነበብ ላንዲት ኢትዮጵያ እውን መሆን ርምጃ ብትጀምሩ ደስ ይላል!!!!
ReplyDeleteሌላው ዳኒየ....የጻፍከውን ሁሉ መረዳት የማይቻልበት ሁኔታ እና የማንችል ስዎችም ስላለን በጽሁፍህ ላይ ለተሰጡት አስተያየቶች መልስ እና ትርጉዋሜ በመቸር ካለመረዳት የተነሳ ባንተ እና በሃሳብህ ላይ የሚዘላብዱ ያጥርህ ውስጥ ነዋሪዎችን ቁጥር መቀነስ ይኖርብሃል!፡፡በዚህ በኩል የወዳጃችንን የኤፍሬም እሸቴን ዘዬ ብትከተል እመክርሀለሁ፡፡ እኔም ላነሰሁት ሃሳብም መልስ በመስጠት ያልኩህን ትጀምራለህ ብየ እመኛለሁ፡፡
በተረፈ ግን ላንተ ማስተዋልን ለኛም አንተን የሰጠን ሥሉስ ቅዱስ (ስላሴ) ይባረክ!!!
ሳሚ(ወ/ሚካኤል) ከሰመራ
First I would like to thank the writer for his eagle eyes observation and sharing his worries to the public. As to my observation it is the current leaders who want to exaggerate the past and used it as escape goat to build fences among the people to hide their evil deeds.The Ethiopian people showed its interest during the election process of 2005. The people tried to dismantle the fancies and came out to unite.Building bride will be easy among Ethiopians if there is media to speak to them freely. As know, there is total crack down on free presses and we are forced to listen to propaganda dispatched from one source calling for the construction of fences than bridge. I fear we are on the wrong track. But, as the historian said "Ethiopian is a country of miracle". Who knows what God will do?
ReplyDeleteDani, Do you know that u are one of them, the bridge builders that we have long waited to come? I love u Bro, every time I read u, I feel refreshed.
ReplyDeleteP.S. I'm a Muslim.
dilidiy genbiwoch hoyiii nu....
ReplyDeletedilidiy genbiwoch hoyii nu....
በ እውነት እኔ የ ሃገር መሪ ብሆን ምን እንደማደርግ ታውቃላችሁ ?
ReplyDeleteልክ እንደዚህ አይነት ጠንካራ ይዘትና ትስስር የሚፈጥሩ ጽሁፎችን የሚጽፉ ሰዎችን በ TV እና ሬድዮ ፕሮግራሞች ሰፊ ሽፋን ተሰጥቷቸው ህዝቡን እንዲሰብኩትና ከክፉ መንፈስ እንዲወጣ, መልካም ነገር እንዲያስብ እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
አሁንም አልረፈደም ፡፡ ተገንብቶ የነበረውን ድልድይ በዘመናዊ ጥበብ አሻሽለን እንገንባ፡፡
ReplyDeleteአቤት አለመታደል ይህ ጽሁፍ ከተለጠፈ ሁለት ዓመት አለፈው ነገር ግን ትውልዱ በመለያየትና በመጠላላት አንዱ አንዱን ጥሎ በማለፍ እሽቅድድም ላይ ይገኛል፡፡እግዚኣብሄር ማስተዋሉን ያድለን ይበልጥ በሰው አገር ያለን ኢትዮጽያውያን ።ወንድማችን ዲያቆን ቃለህይወት ያሰማልን ለኛም ማስተዋልን ያድለን።
ReplyDeleteዲ/ን ምነው ሙሴህ ድልድሉን መስራት አቃተወ እነዴ? ወደፊት እንይ እንዳትለኝ! ምክንያቱም ያለፈው ሥራ ውጤት ነው እየደረሰብን ያለ። በጣም ታዘብኩህ ይህ ስብከትህ አሁኑ ላለው ሁኔታ ወሳኝ ቢሆንም ግን ይህ ይሆን ዘንድ ጸሎትህ እንደነበር የቀድመው ጽሑፎችህ ተመልሰህ መመልከት ትችላለህ።
ReplyDelete