በኦሮምኛ አንድ ድንቅ ተረት አለ፡፡ በአንድ የኦሮሞ መንደር ውስጥ ሮቤል መገራ የሚባሉ ጥበበኛ ሽማግሌ ነበሩ፡፡ አንድ ቀን የሁለት ጎረቤታሞች ንብረት የሆኑ ሁለት ውሾች ሲጣሉ ያያሉ፡፡ እኒህ ጥበበኛ ሽማግሌም «እነዚህን ውሾች እንገላግላቸው፤ ያለበለዚያ ችግራቸው ለሁላችንም ይተርፋል¿ በዓለም ላይ ችግር የሚነሣው ከአጥንት በላይ ማሰብ በማይችሉ ውሾች የተነሣ ነው» ይላሉ፡፡ በአካባቢው የነበሩ ሽማግሌዎች እና መንገደኞችም በሽማግሌው አባባል ተገርመው «ሁለት ውሾች ተጣልተው ምን ሊያመጡ ነው» እያሉ ሳቁባቸው፡፡
በዚህ መካከል ከሁለቱ ጎረቤታሞች መካከል አንድ ልጅ ወጣና የውሾቹን ጠብ ተመለከተ፡፡ የእርሱ ውሻ የተበደለ ስለመሰለው ፍልጥ አምጥቶ ያኛውን ውሻ ደበደበው፡፡ ወዲያውም ከሌላኛው ቤት ሌላ ልጅ ወጣና ያኛውን ውሻ መደብደብ ጀመረ፡፡ ነገሩ ወደ ሁለቱ ልጆች ተዛመተና በውሾቹ ምትክ ልጆቹ ይደባደቡ ጀመር፡፡ ሽማግሌውም «እባካችሁ እነዚህን ልጆች አስታርቁ» አሉ፡፡ በሥፍራው የነበሩትም «ተዋቸው ይዋጣላቸው» ብለው እንደ ቀልድ አለፉት፡፡
ልጆቹ እየተደባደቡ እያሉ የአንዱ እናት ብቅ አለች፡፡ ወዲያውም ያኛውን ልጅ በፍልጥ ታንቆራጥጠው ጀመር፡፡ የልጇን ጩኸት የሰማቺው ሌላዋ እናትም መጣች፡፡ የልጆቹ ጠብ ቀረና ድበድቡ በሁለቱ እናቶች መካከል ሆነ፡፡ ሮቤል መገራም «እባካችሁ ይህ ጠብ ተዛምቶ ሁላችንንም ከማካተቱ በፊት ገላግለን እናስማማቸው» አሉ፡፡ ተመልካቾቹ ግን የሁለቱን ጠብ እንደ ነጻ ትግል እያዩ ይዝናኑ ነበር፡፡ አንዳንድ ሽማግሌዎችም «ሁለት ሴቶች ተጣልተው የት ይደርሳሉ» እያሉ ንቀው ተውት፡፡
በግርግሩ የከበቡትን ሰዎች እየጣሰ አንድ ሰው ወደ መካከል ገባ፡፡ ያንደኛዋ ባል ነበር፡፡ እንዴት ሚስቴን ትመቻታለሽ ብሎ ያቺኛይቱን ሴት መደብደብ ያዘ፡፡ ይኼኔ ነገሩን የሰማው ሌላኛው ባልም ሲሮጥ መጥቶ ድብድቡን ተቀላቀለ፡፡ ሮቤል መገራ አሁንም «እባካችሁ ገላግሏቸው፤ ይህ ጠብ ለሀገር ይተርፋል» ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሰሚ ግን አላገኙም፡፡
ሁሉም የራሱን ልጅ፣ ሚስት እና ቤት ብቻ ይጠበቅ ነበር፡፡ ወንዶቹም ልጆቻቸው እና ሚስቶቻቸው እንዳይገቡ ይቆጡ ነበር፡፡
የሁለቱ ባሎች ጠብ ተባባሰ፡፡ ሕዝቡም ከብቦ ያይ ጀመር፡፡
በዚህ መካከል የሰውዬው ወገኖች ነን ያሉ ያንደኛዋን ባል መደብደብ ያዙ፡፡ ተመልካች ሆነው ከቆሙት መካከል የዛኛው ወገን ነን የሚሉ ደግሞ ያኛውን ይዘው ይደበድቡ ጀመር፡፡ እንዳጋጣሚ የሁለቱ ሰዎች ጎሳች የተለያዩ ስለነበሩ ጠቡ ወደ ጎሳ አደገ፡፡ ዱላ እና እጅ ብቻም ሳይሆን የጦር መሣርያም ተጨመረበት፡፡ ቤት ንብረት መዝረፍ፣ ማቃጠል እና መግደል እየተባባሰ መጣ፡፡ መንደሩም የጦርነት አውድማ ሆነ፡፡ ከሁለቱም ወገን ስምንት ስምንት ሰዎች ሞቱ፡፡
በስንት መከራ ጠቡ ቆመ፡፡ ሮቤል መገራም አዘኑ፡፡ «ውሾቹ ሲጣሉ ብናስቆማቸው ኖሮ ጎሳዎቹ አይጣሉም ነበር» አሉ፡፡
ሽማግሌዎቹ ጉማ ተቀመጡ፡፡
በባህሉ መሠረት ለእያንዳንዱ ለሞተው ነፍስ ከሌላው ወገን ሰው ይገደላል ወይንም መቶ መቶ ከብት ይሰጣል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ከሁለቱም ወገን ስምንት ስምንት መቶ ከብት ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ በሞቱት ምትክ ከሌላው ወገን ሰው ይገደልም ከተባለ በተጨማሪ አስራ ስድስት ሰዎች ሊገደሉ ነው፡፡ የሟቾቹም ቁጥር ወደ ሠላሳ ሁለት ከፍ ሊል ነው፡፡ ይህ ነገር ሽማግሌዎቹን አስጨነቀ፡፡
ይኼኔ ሮቤል መገራ ተነሡ፡፡ «ቅድሞ እኔን ሰምታችሁኝ ቢሆን ኖሮ መልካም ነበር፡፡ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን እንጂ ስለ ሌሎች ግድ ስለሌለን ዕዳው በመጨረሻ እኛው ላይ መጣ፡፡ ውሾቹን ተው ማለት አቅቶን እዚህ ደረጃ ደረስን፡፡ ምን ጊዜም ጦርነቶች የሚነሡት ውሾቹን ተው የሚል እየጠፋ ነው፡፡ ጎረቤት እና ጎረቤት፣ ጎሳ እና ጎሳ፣ ንጉሥ እና ንጉሥ፣ ሀገር እና ሀገር፣ እስላም እና ክርስቲያን፣ መንደር እና መንደር፣ የሚጣላው ውሾቹን ተው የሚል እየጠፋ ነው፡፡ የጦርነት መነሻ ውሾች ናቸው፡፡ ውሾቹ በአጥንት የጀመሩት ጠብ ሕይወት አስከፈለን፡፡ እነዚህ ውሾችኮ ከአጥንት በላይ አርቀው ማሰብ የማይችሉ ውሾች ናቸው፡፡ ዓላማቸው አጥንት መጋጥ ብቻ ነው፡፡ አገር ቢጠፋ፣ ሕይወት ቢጠፋ፣ ንብረት ቢጠፋ እነርሱ ምን ጨነቃቸው፡፡ እንዴት ከአጥንት በላይ ማሰብ የማይችሉ ውሾች ይህንን ሁሉ ዋጋ ያስከፍሉናል?
«እነዚያን ውሾች ለያዩዋቸው ስላችሁ ሁላችሁም የእናንተ ውሾች አለመሆናቸውን ብቻ ነበር የምታዩት፡፡ ሌሎች ተበጥብጠው እኛ እንዴት ሰላም እንሆናለን? ሌሎች እየተዋጉ እንዴት እኛ በደኅና እናድራለን? ሌሎች ተርበው እንዴት እኛ እንጠግባለን? የማይሆን ነገር ነው፡፡
በሉ አሁንም ሌላ ሕይወት ማጣት የለብንም፣ ከብቶቻችንንም ማጣት የለብንም፤ ከሁለቱም ወገን የየአንገ ታችሁን የብር ማተብ አምጡ፤ ያንንም ሰብስባችሁ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፣ ሁሉም ጦሱን ይውሰድ፤ እናንተ ግን ይቅር ተባባሉ» ብለው አስታረቋቸው ይባላል፡፡
ውሾቹን «ተው» ካላልናቸው የመጨረሻውን ውጤት ማንም ሊገምተው አይችልም፡፡ ሂትለር እና ሞሶሎኒ የሚባሉ ውሾች ሲነሡ ማንም «ተው» ማለት አቅቶት ዓለምን በእሳት ለበለቧት፡፡ በወቅቱ አይሁድ እየተሰቃዩ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች እየተናገሩ ምዕራባውያን ግን ዓይናችንን ግንባር ያድርገው ብለው በበርሊን ኦሎምፒክ ሂትለርን ሲያመሰግኑ ሰነበቱ፡፡ እንዲህ በመጨረሻ ጦሱ ለእነርሱም ሊተርፍ፡፡
ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በዓለም ማኅበር ተገኝተው ውሾቹን «ተው» በሏቸው ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡ ብዙዎች ራሳቸው እንደ ውሻ በመጮኽ የንጉሠ ነገሥቱን ንግግር ለመበጥበጥ ሞከሩ እንጂ አልሰ ሟቸውም ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን የውሾቹ ጠብ ወደ ዓለም ጦርነት ተቀየረ፡፡ ዛሬ ዓለም በኢራን የኑክሌር መሣርያ እንዲጨነቅ ያደረገቺው ራሷ አሜሪካ ናት፡፡ ኢራኖች ኒኩልየር የሚባል መኖሩን ባላወቁበት ዘመን የግድ ኒኩልየር ካልኖራችሁ ብላ በራቸውን አንኳኩታ ስትሄድ ዓለም በዝምታ ነበር ያያት፡፡ ያኔ ውሾቹን «ተው» የሚላቸው ቢኖር እንዲህ እሥራኤል እና አሜሪካ በጭንቀት ውለው አያድሩም ነበር፡፡
አሜሪካ ሶቪየት ኅብረትን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ቢን ላድንን ስታሠማራ ተይ የሚላት ባለመኖሩ ራስዋ ያመጣችው መከራ ለእርሷም ለዓለምም ተረፈ፡፡ ያሳደግኩት ውሻ ነከሰኝ፣ የቀለብኩት ፈረስ ጣለኝ እንደሚባለው ሆነ፡፡
ሩዋንዳ ላይ ሬዲዮ ከፍተው ጎሳ ከጎሳ የሚያጣላ ፕሮግራም የሚያራምዱትን፣ ግደሉ ጨፍጭፉ እያሉ የሚያቅራሩትን ውሾች በወቅቱ ፈረንሳዮች በዝምታ ነበር ያዩዋቸው፡፡ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ሲጀመር የተባ በሩት መንግሥታት ድርጀትን ጨምሮ ብዙዎች አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ ሆኑ፡፡ ውሾቹን ተው የሚል ጠፍቶ ውሾቹ ያመጡት ጣጣ ምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካን የሚያቃጥል እሳት ወለደ፡፡
ለዚህ ነው ከአጥንት በላይ ማሰብ የማይችሉትን ውሾች በጊዜ «ተው» ማለት የሚያስፈልገው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ እዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ቤተ እምነት ተቃጠለ ሲባል በዝምታ እየታየ ነው፡፡ ይህ እኩይ ተግባር ማንኛውንም የእምነት ማኅበረሰብ የሚወክል ነው ተብሎ ፈጽሞ አይታመንም፡፡ ነገር ግን ሙስሊ ሞችም ሆኑ ክርስቲያኖች ይህንን እሳት የሚለኩሱትን ውሾች «ተው» ልንላቸው ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ፍጻሜው ለሁላችንም ይደርስና ከባድ ዋጋ ይጠይቀን ይሆናል፡፡ እነዚህ ውሾች ከዕለት አጥንት አርቀው ማሰብ አይችሉም፡፡ ለጊዜው ከሌላው ጋር ተሻምተው አንድ አጥንት ማግኘታቸውን ብቻ ነው የሚያውቁት፡፡
እዚህ ዓይን ማጥፋት፣ እዚያ አሲድ መድፋት፣ እዚያ ሕፃን መድፈር፣ እዚህ ግብረ ሰዶም፣ እዚያ አካል ማጉደል፣ እዚህ በፈላ ውኃ መንከር ሚዲያዎቹ ይጮኻሉ፣ በሹክሹክታ ይነገራል፣ አንድ ሰሞን ጉድ ይባላል፡፡ ውሾቹን ተው የሚላቸው ግን እየጠፋ ነው፡፡ እነዚህን ሕፃናትን የሚደፍሩትን፣ የእኅቶቻችንን አካል የሚያጎድሉትን፣ በአውሬነት መንፈስ አረመኔ ተግባር የሚፈጽሙትን ውሾች ተው የሚል አልተገ ኘም፡፡ ምናልባት ሁላችንም የምንነቃው የሁላችን በር ሲንኳኳ፣ የሁላችንም ልጆች ሲነኩ፣ የሁላችንም አካል ሲጎድል፣ የሁላችንም አኅቶች ሲደፈሩ ነው ማለት ነው፡፡ ኧረ ውሾቹን ተው እንበላቸው፡፡
ገንዘብ ከማግኘት ባለፈ ማሰብ የማይችሉ፣ የሀገር ክብር፣ የዜጎች መበት፣ የሰው ልጅ ሰብአዊነት የማይገዳቸው ላኪዎች አቀባዮች እና ተቀባዮች ከየገጠሩ ምንም የማያውቁ ኢትዮጵያውያንን እየመለመሉ፣ ሕጋዊ በሚመስል ሕገ ወጥነት ወደ ዓረቡ ዓለም ሲያሻግሩ ዝም እየተባሉ ነው፡፡ ውሾቹ አጥንታቸውን ብቻ እንደሚያዩት እነርሱም ገንዘባቸውን ብቻ ነው የሚያዩት፡፡ የሚላከው ሰው የት ይውደቅ የት፣ ምን ይግጠመው ምን፣ እንዴት ይሁን እንዴትም አያገባቸውም፡፡ ወገን ግን እየተሰቃየ ነው፡፡
የሰው ኃይል ወደ ዓረብ ሀገር መላክ በኛ አልተጀመረም፡፡ ሕንዶች፣ ፊሊፒኖች፣ ፓኪስታኖች፣ ባንግላዴሾች፣ ሱዳኖች፣ ግብጾች ይጎርፋሉ፡፡ የኛ ሰውን ያህል ግን መከራ የበዛበት የለም፡፡ ለምን? ውሾቹን ተው የሚል በመጥፋቱ፡፡ የናንተ ጦስ ለሀገር እና ለወገን ይተርፋል ብሎ የሚቆጣ በመጥፋቱ፣ መሥመር የሚያስይዘ በመጥፋቱ፡፡ ዛሬ ዛሬ አንዳንድ ሀገሮች አበሻ አታምጡበን፣ ቪዛ አንሰጥም፣ አንቀበልም እስከማለት የደረሱት ኃላፊነት የማይሰማቸው እንደ ውሾች አጥንታቸውን ብቻ የሚያስቡ ሰዎች በሚፈጽሙት ሕገ ወጥነት ምክንያት ነው፡፡
አንዱ እምነት በሌላው ላይ፣ አንዱ ብሔር በሌላው ላይ፣ አንዱ ፓርቲ በሌላው ላይ ቂም እንዲቋጥር፣ እንዲያዝን፣ የጥላቻ ስሜት እንዲያዳብር፣ የሚያደርጉ ትምህርቶች፣ ጽሑፎች፣ ንግግሮች፣ ዘፈኖች፣ አሠራ ሮች፣ በዝምታ እየታዩ ነው፡፡ እነዚህን ከጊዜያዊ ሥልጣን፣ ሹመት፣ ገንዘብ፣ ግብዣ፣ ጭብጨባ ባለፈ ማሰብ የማይችሉ ውሾችን ተው ማለት ይገባል፡፡ አንዳንዶቻችን የኛ በመሆናቸው፣ ሌሎቻችን የተነኩት ከኛ ውጭ ያሉት በመሆናቸው ዝም እያልናቸው ነው፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ቤታችን የተሠራው በመስተዋት መሆኑን አንዘንጋ፡፡ ውሾቹን ተው ካላልናቸው እነርሱ እንደ ዋዛ መወራወር የጀመሩት ድንጋይ በመጨረሻ የሁላችንንም ቤት ሊፈረካክሰው ይችላል፡፡
እናም ውሾቹን «ተው» በሏቸው
ከአቡዳቢ
ኢትዮጵያ ውስጥ እዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ቤተ እምነት ተቃጠለ ሲባል በዝምታ እየታየ ነው፡፡ ይህ እኩይ ተግባር ማንኛውንም የእምነት ማኅበረሰብ የሚወክል ነው ተብሎ ፈጽሞ አይታመንም፡፡ ነገር ግን ሙስሊ ሞችም ሆኑ ክርስቲያኖች ይህንን እሳት የሚለኩሱትን ውሾች «ተው» ልንላቸው ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ፍጻሜው ለሁላችንም ይደርስና ከባድ ዋጋ ይጠይቀን ይሆናል፡፡ እነዚህ ውሾች ከዕለት አጥንት አርቀው ማሰብ አይችሉም፡፡ ለጊዜው ከሌላው ጋር ተሻምተው አንድ አጥንት ማግኘታቸውን ብቻ ነው የሚያውቁት፡
ReplyDeleteኢትዮጵያ ውስጥ እዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ቤተ እምነት ተቃጠለ ሲባል በዝምታ እየታየ ነው፡፡ ይህ እኩይ ተግባር ማንኛውንም የእምነት ማኅበረሰብ የሚወክል ነው ተብሎ ፈጽሞ አይታመንም፡፡ ነገር ግን ሙስሊ ሞችም ሆኑ ክርስቲያኖች ይህንን እሳት የሚለኩሱትን ውሾች «ተው» ልንላቸው ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ፍጻሜው ለሁላችንም ይደርስና ከባድ ዋጋ ይጠይቀን ይሆናል፡፡ እነዚህ ውሾች ከዕለት አጥንት አርቀው ማሰብ አይችሉም፡፡ ለጊዜው ከሌላው ጋር ተሻምተው አንድ አጥንት ማግኘታቸውን ብቻ ነው የሚያውቁት፡
Deleteኢትዮጵያ ውስጥ እዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ቤተ እምነት ተቃጠለ ሲባል በዝምታ እየታየ ነው፡፡ ይህ እኩይ ተግባር ማንኛውንም የእምነት ማኅበረሰብ የሚወክል ነው ተብሎ ፈጽሞ አይታመንም፡፡
ReplyDeleteis 2012 year of.... Signs & symptoms are agraveting in this world & country
Habtamu
Z Awassa
bereket tesfayonas A.A
ReplyDeleteWow dani this article should be in every wall of ethiopia. Forsure i will post it.
ጊዜያዊ ተድላ ደስታንና ዝናን ለማግኘት በአገራችንንና በሀይማኖታችን ላይ እየተሰራ ያለው ነገር በጣም ይሳዝናል፡፡ ይህም መቅሰፍትንና ጥፋትን እንጂ መልካም ነገርን አያመጣም፡፡ ለዚህም ተው የሚልና የሚያስተባብር ነው የጠፋው አምላክም ትንቢቱ እስኪፈፀም ነው ሁሉን በዝምታ የሚያሳልፈው፡፡ ቀን በጨመረ ቁጥር ለህልውናችን አስጊ የሆኑ ድርጊቶች እየተፈፀሙ እንደ ጥሩ እድገትና ህዝቡ የተስማማበት ለማስመሰል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ከአሁን አሁን ምን ይፈፀም ይሆን እያልን መሳቀቅና መስጋት ከጀመርን ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ አምላክ በቃ ብሎ የሚበጀውን እንዲሰጠን የዘወትር ፀሎታችን ነው፡፡
ReplyDeleteyes you are right we have to block those human with dog characters...
ReplyDeleteby the way who let the dogs out!!!
formerly we were looking and grow in a society who has due respect for others though they had been wrong or that deviate from the accepted truth. we can take as the best example the family of muslims Prophet Mohamed.
at least this history is one example which tells us about the former Ethiopians that they were living without cooperating with dogs. today there is loos of humanity respect not only social, poletycal, family respect... if a person who is at least normal in such area is found in many places we would be sure he/she has a potential to be normal on his/her religion too... really we lost in our mind, experience, life style such bad habits of leting the dogs out as they are... yesterday one one old man from hosana having a habit of taking a holy communion in recent days corecting his former life ... said in our culture we say hold your dogs and behaviour in your house so that we will not be in trouble ... it meens if not the result is what we are experiencing today which is the product of such dog like character... I am amazed sometimes on my and other different religious people devotion for there religion but if you are able to see even their family you will be surprised that it is empty. this can be observed in any religion. as yeneta Eshetu said even if our religious difference widens our gap but kality prison unites us because we are teft being under the cover of religion...
i am trying to see such faulty in my self thinking i was also the one with such dog like character... so we have to start from our own selfs... and as daniel said we yes we all based on our potential and status have to block and not cooperate with dogs in what ever cover they are found...
tx
ዳኔ ...
ReplyDeleteእግዚአብሄር እውቀትን ያብዛልህ ...
እናም ውሾቹን «ተው» በሏቸው
ReplyDeleteትክክል ሃሳብ ነዉ ያነሳኸዉ ሀኃሳብ የሚደገፍ ነዉ።
ReplyDeleteHi dani, you have said good, in every corner of the country if we say ውሾቹን «ተው» at early stage, really there will not be an abusing of the money of the church(eotc)specially the development committee of the church building in some areas(example st.Gebriel church of the dire dawa).
ReplyDeleteGood article!
ReplyDeleteThere is also a"fire" in that house, and lets stop dogs.
ReplyDeleteእነሆ የዛሬው ምሣዬ ብዙ ቫይታሚኖች ነበሩት
ReplyDeleteጣእሙንማ አትጠይቁኝ እጅ ያስቆረጥማል!
አያያያ ያቺ ምሣ ይህን ትመስላለች፦
የሰው ገበያ ላይ ልገበይ ወጥቼ
ዙሬ ተመለስኩኝ ልብ ያልው አጥቼ
እናም እደገና ሀሳቤን ቀይሬ
ልብ የሚሆነውን ማስተዋል ልገዛ
ወጣሁ እንደገና ፈላጊው ሳይበዛ
ልብ ያለው አገኝ ይሆን???
-//-
"ኢትዮጵያ ውስጥ እዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ቤተ እምነት ተቃጠለ ሲባል በዝምታ እየታየ ነው፡፡ ይህ እኩይ ተግባር ማንኛውንም የእምነት ማኅበረሰብ የሚወክል ነው ተብሎ ፈጽሞ አይታመንም፡፡ ነገር ግን ሙስሊ ሞችም ሆኑ ክርስቲያኖች ይህንን እሳት የሚለኩሱትን ውሾች «ተው» ልንላቸው ይገባል"
የጎረቤት እሳት እኛም ቤት ይመጣል ብሎ ካለማሰብ የመነጨ ድቅድቅ ጨለማ ወጥተን በቀና ልብ የምናስብበት ጌዜ መሆኑን ልብ ይላል !!!! እየመጣ ያለው አደጋ የሁላችንንም ህልውና የሚፈታተን መሆኑን ተመልክተን ገና ከአሁኑ እሳት ማጥፋቱ ላይ ልንረባረብ ይገባናል !!!
ReplyDeletenice as usual. kaleheyewete yasemalene.
ReplyDeleteThank you. <> ymile akale yesetene.....
H from Addis
እውነት ነው! ውሾቹን ዛሬ ተው ካላልናቸው “ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆመው ለማውረድ ይቸግራል” እንደሚሉት አበው ነገ ሊነሳ የሚችለውን እሳት ማጥፋቱ ክባድሊሆን ይችላል፡፡ በተረፈ እግዚአብሔር ተባብረን ለመጠቀም ያብቃን…አዱዱ ነኝ
ReplyDeleteአንዱ እምነት በሌላው ላይ፣ አንዱ ብሔር በሌላው ላይ፣ አንዱ ፓርቲ በሌላው ላይ ቂም እንዲቋጥር፣
ReplyDeleteእንዲያዝን፣ የጥላቻ ስሜት እንዲያዳብር፣ የሚያደርጉ ትምህርቶች፣ ጽሑፎች፣ ንግግሮች፣ ዘፈኖች፣ አሠራ
ሮች፣ በዝምታ እየታዩ ነው፡፡ እነዚህን ከጊዜያዊ ሥልጣን፣ ሹመት፣ ገንዘብ፣ ግብዣ፣ ጭብጨባ ባለፈ
ማሰብ የማይችሉ ውሾችን ተው ማለት ይገባል፡፡
you run forward ,we need more man like you
you have potential thank you
Thank you sir! But today no one think to end the dog's fight which provokes too much costly devastation on this country.it has already need cost but still not late.please let us stand up together and stop the mad dogs.
ReplyDeleteRobel Megera could have played active role in stopping the fight between the dogs rather than finally acting as protagonist field player in the negotiation
ReplyDeleteዳኒ እኔ የዚህ ሁሉ መንሥኤው “ድንቁርና” ይመስለኛል (ይህን ቃል በመጠቀሜ ይቅርታ!)፡፡ ኢትዮጵያችን ውስጥ ድንቁርና እግሯን ዘርግታ ተቀምጣለች፡፡ ከኬጂ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተመችቷታል፡፡ በስማ በለው መጓዝን እንጂ ራስን ችሎ ማሰብን የሚፈቅዱ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ጥቂት ይመስለኛል፡፡ ራሳቸውን ችለው የሚያስቡ ነቂስ አሳቢዎቻችንን ከመከተል ይልቅ መግደል (ወይ በጥይት ወይ በሐሜት ወይ በሽሙጥ) ልምዳችን ነው፡፡ ከመንጋው ተለይተው የሚያስቡ ሰዎችን እንደጠላቶቻችን ማሰባችን “መንጋው ለዘለዓለም ትክክል ነው! መንጋው ለዘለዓለም ይኑር!” የሚል የኑሮ መፈክራችን ለድንቁርና ትራስ አቀብሏት እነሆ ላያችን ላይ ተጋድማ እየነዳችን ትገኛለች፡፡
ReplyDeleteሀይማኖት ማለት ጮኽ ብሎ የተናገረውን መስማት ከሆነም ከረምረም ሳይል አልቀረም፡፡
የምናምነውን የምናምነው የሆኑ ጥሩ ድምጥ ያላቸው ሰዎች ደመቅ አድርገው ስለነገሩን ከሆነ ደግሞ የምናምነው የተሰበከውን እውነት ሳይሆን የሰዎቹን ድምጸት ይሆናል፡፡ ስለሆነም እነዚህ በገንዘባቸው ብዛት ወይም በአቆላማጮቻቸው ብዛት ራሳቸውን የፈጣሪ እንደራሴ ያደረጉ ሰዎችን ሳናውቀው ማምለክ እንጀምራለን፡፡ ሰዎቹንም ፍጹማንና የፈጣሪ አማካሪዎች አድርገን እናስቀምጣቸዋለን፡፡ ከዚያ በኋላማ በቃ! ብዙ ኢትዮጵያውያን ቤተክርስቲያን የምንሔደው፣ የጁምዓ ሶላት የምንሰግደው፣ ቡርቃ የምናጠልቀው በእውነቱ ሃይማኖቱ ይዘዝ አይዘዝ አውቀን ሳይሆን የሆኑ ያመንናቸው ሰዎች እንደዚያ እንደሚደረግ ስለነገሩን ወይም እነርሱ ሲያደርጉ ስላየን ከእነርሱ ተከታዮች ላለመገንጠል ይመስለኛል፡፡ የሚገርመው ግን አፋችንን ሞልተን የምናመልከው ፈጣሪን እንደሆነ እንመሰክራለን፡፡
ፈጣሪህ የፈጠረውን ወንድምህን እያሳዘንህ ፈጣሪን አገለግላለሁ የምትል አንተ በእውነት የፈጣሪ ተቃራኒ ነህ ፈጣሪህ ወድዶ ፈቅዶ የፈጠረውንና የሚያኖረውን ወንድምህን መኖር አይገባውም ብለሃልና፡፡ ፈጣሪህ እርሱን ደስ እንዲለው፣ እንዲመቸው ብሎ ዝናብ አዝንቦ፣ ፀሐይ አውጥቶ የሚያገለግለውን ወንድምህን ደስታውን ልትነጥቀው ትሮጣለህና ሐዘን ይገባሃል፡፡
እስኪ ከመንጋው አንድ ጊዜ ነጠል ብለህ አስብ፡፡ ለፈጣሪህ መሥዋዕት የምታቀርበው የወንድምህን እንባ ነውን? በእንባ ጎርፍ የተደረመሱ ከተሞች እንጂ የጸደቀ ችግኝ በዓለም ታሪክ ተሰምቶም አይታወቅ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድም ሆኑ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥክር እንጂ ጠበቃ አይፈልጉም፡፡ ኢስላም ማለት ሰላም ከሆነ ሰላምነቱን ሰላማዊ በመሆንና ለወንድምህ ፍቅርን በመስጠት ካላሳየኸው አንተ የኢስላም ጠላት ነህ፡፡ የነቢዩ ሙሐመድም ተቃራኒ ሆነህ ቆመሃል፡፡ ክርስትና ማለት ራስን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አሳልፎ በመስጠት ለዓለም መሞት እንደሆነ ካመንህስ ስለምን ወንድምህን ለሐዘን አሳልፈህ ትሰጣለህ? ከመንጋው ነጠል በልና ባለጭፍራዎቹ የሚከትቧቸውን ሳይሆን በእውነት የሃይማኖቶቹ ምንጭ የሆኑ መጻሕፍትን መርምር፡፡ ሰዎች ስላደረጉት ብቻ ምንም ነገር አታድርግ፡፡ ራስህን ቻል! ስትሞት ፈጣሪ ዘንድ የምትቀርበው ብቻህን መሆኑንም አትዘንጋ!
Mehari yante Mizanawi new ahunim bekisu shigut kemishekem Papasena begunchu sidibin kacheke diakon endisewuren enitseliy.
DeleteDiaqonma Wshanm betselot ner neber yemiyastagis abtie endenegeregn.
atent sibal zer,gosa maletem yihonal
ReplyDeleteDani weladite amilak tsegawin tabizalih.
ReplyDeleteAmazing! Thank You! Good point like always
ReplyDeleteDeacon Daniel,
ReplyDeleteGood article!
Though many people agree you are walking a fine line, and I agree you should, you know from your heart deep down who started all these and is the root cause for all evils you mentioned. How long would it take for us to come forth and focus? I am just wondering!
You have said well and right.We all should have to say Stop for those who only looking dumn bone!!!I love my relegion and country..pls pls bone seeker get out of from our society
ReplyDeleteጆሮ ያለው መንግስትና የሃይማኖት መሪ ካለ ይስማ!
ReplyDeleteኢትዮጵያ ውስጥ እዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ቤተ እምነት ተቃጠለ ሲባል በዝምታ እየታየ ነው፡፡ ይህ እኩይ ተግባር ማንኛውንም የእምነት ማኅበረሰብ የሚወክል ነው ተብሎ ፈጽሞ አይታመንም፡፡ ነገር ግን ሙስሊ ሞችም ሆኑ ክርስቲያኖች ይህንን እሳት የሚለኩሱትን ውሾች «ተው» ልንላቸው ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ፍጻሜው ለሁላችንም ይደርስና ከባድ ዋጋ ይጠይቀን ይሆናል፡፡ እነዚህ ውሾች ከዕለት አጥንት አርቀው ማሰብ አይችሉም፡፡ ለጊዜው ከሌላው ጋር ተሻምተው አንድ አጥንት ማግኘታቸውን ብቻ ነው የሚያውቁት፡፡
ReplyDeleteEgziabher yestelene, gene weshochne tewe lemalete mene enaderege? memeria yemisetene ena yemiyastebabrene yeleme, selezihe anbebene tiru newe kemalete yezelele neger meserate selalechalene azenalehu.
ReplyDeleteእንደ ሮቤል መገራ አይነት አስታራቂና አስተዋይ አባት ከሃይማኖት አባቶች ወገንም ሆነ ከሃገር መሪዎች ወገን ጠፋ በሃገር ውስጥም በውጭም ያሉ አባት ነን ባዮች ውሾቹን ተው ማለት ሲገባቸው ዝም አሉ ስለዚህ ውሾቹን ተው ማለት ያለብን እኛ ከታች የምንገኝ የሕብረተሰብ ክፍሎች ነን ውሾቹን ተው ብለናቸው ካልሰሙ ግን ችግሩ ሳያድግ በፊት ተገቢውን እርምጃ መውሰድ የግድ ይላል ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን በርታ አንተን የወለደ ማሕጸን የተባረከ ይሁን አሜን
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteYour article advised to consider things wisely. Simple things like the fight of two dogs costs the life of peoples.Just, to strengthen your argument I would like to share how World War I started.
The causes of World War I, which began in central Europe in July 1914, included many intertwined factors, such as the conflicts and hostility of the four decades leading up to the war. Militarism, alliances, imperialism, and nationalism played major roles in the conflict as well. However, the immediate origins of the war lay in the decisions taken by statesmen and generals during the July Crisis of 1914, casus belli for which was the assassination of Archduke Franz Ferdinand of Austria and his wife by Gavrilo Princip, an irredentist Serb.
The crisis came after a long and difficult series of diplomatic clashes between the Great Powers (Italy, France, Germany, the British Empire, Austria-Hungarian Empire and Russia) over European and colonial issues in the decade before 1914 that had left tensions high. In turn these diplomatic clashes can be traced to changes in the balance of power in Europe since 1867.The more immediate cause for the war was tensions over territory in the Balkans. Austria-Hungary competed with Serbia and Russia for territory and influence in the region and they pulled the rest of the Great Powers into the conflict through their various alliances and treaties.
To sum up, we should handle carefully things which resembles not important. One can not see a smoke without fire.
እኛም ከውሻቹ አንሻልም ሁሌ ስለአጥንት ብቻ ማሰብ፡፡
ReplyDeleteMamush,MN
It is good article. We need to think in advance because everything we let to happen ignorantly will be a problem back to us!! There are many things we need to deal and tackle rather than fighting against each other!! let us work against poverty, famine and change our image. we can do that; we can fix our endless problems.
ReplyDeleteከሰማይ ዋጋህን አያስቀርብህ ብል ይሻለኛል።Golden idea but freeeeeeeeee.ውለታህን አበዛህብኝ...ሐሳብህን በመጋራት እመልሰው ይሆን?
ReplyDeleteGOOD INGENERAL,BUT I AGREE BY HALF THE IDEA
ReplyDeleteGood article.
ReplyDeletehulachnem ymimlktn krasache jamro katente blay mmlekt alben Egziabher yestelene,
ReplyDeleteዳ/ዳኒ በሚያደስት አጻጻፍ የልቤን አስቀመትከው ሁላችንም ማለት ያለብን «ውሾችን ተው ማለት ያስፈልጋል »አበው እንደሚሉት «ሳይቃተል በቅተል»ማለት ነው ፣ ይሕ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርሻ ነው!!
ReplyDeleteዲ.ዳንኤል መልእክቱ ጥሩ ቢሆንም በአርአያ ስላሴ የተፈጠረውን የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ ውሻ ከማለት ይልቅ ጠባዩን 'የውሻ ጠባይ'ብሎ መግለጽ የበለጠ ሊያስተምር ይችላል ብዬ አስባለሁ፤ ተሳሳትኩ?????????????
ReplyDeleteዳንኤል ጥሩ ተመልክተሃል
ReplyDeleteግን እኮ ፡ ተፈጥሮ ራሷ እንዲህ ናት ። አንዱ ለመኖር ሌላውን መብላት አለበት ። ችግሩ የተፈጠረው ፤ የሚበላውንና የማይበላውን ከመለየቱ ላይ ይመስላል ።
እግዚአብሔር አዳምን “ሁሉን ብላ” ብሎት አንዷን ብቻ ለይቶ “ይህችን ግን እንዳትበላ በበላህበተ ቀን ትሞታለህ” አለው ፡ ኢሱ ግን የጠላት ምክር እውነት መስሎት ቅጠሏን ቀጠፋትና ተቀጠፈ ።
አሁንም እኛ ብዙ የሚበላ ነገር እያለ ፡ እርስ በርስ እየተበላላን እየተላለቅን እንገኛለን ። ክርስቲያንም ይሁን ሙስሊም ፤ ተቃዋሚም ይሁን ደጋፊ ፡ ምንም ዓይነት ፡ ዘር ፣ የቆዳ ቀለም ፡ አመለካከት ፣ እምነት ፣ ርዕየተ ዓለም… ወዘተ ይኑረው ፡ ሰው ግን ምንጊዜም ሰው ነው ። ስለዚህ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ማየት ተገቢ ነው ። ይህ ካልሆነ ግን ፡ መተላለቃችን መቸም አያባራም ።
i can't know to thank enough!!, you print my dream to say!! thank you for all.
ReplyDeleteተው የሚል በጠፋበትና ሁሉም ተው የሚባል በሆነበት ዘመን ላይ ይሆን ያለነው?
ReplyDeleteጨውና ቅባት የበዛበት ምግብ ደም ፍላት ላለባቸው ሰዎች አይስማማም፡፡ የዛሬው ቫይታሚን ሳይሆን እንደኔ እንደኔ ጨውና ቅባት ጠቃ ብሎታል ዳኒ እንዴት ነው? ግን አታስዋሸኝ ወድጄዋለሁ፡፡
ReplyDeleteአሁንም እኛ ብዙ የሚበላ ነገር እያለ ፡ እርስ በርስ እየተበላላን እየተላለቅን እንገኛለን ። ክርስቲያንም ይሁን ሙስሊም ፤ ተቃዋሚም ይሁን ደጋፊ ፡ ምንም ዓይነት ፡ ዘር ፣ የቆዳ ቀለም ፡ አመለካከት ፣ እምነት ፣ ርዕየተ ዓለም… ወዘተ ይኑረው ፡ ሰው ግን ምንጊዜም ሰው ነው ። ስለዚህ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ማየት ተገቢ ነው ። ይህ ካልሆነ ግን ፡ መተላለቃችን መቸም አያባራም ።
ReplyDeleteዲያቆን በእዉነት ጥሩ ብለሃል:: በጊዜ በቃ ሊሏቸዉ ይገባል:: ምንም እንኳን ከብዙ ጥፋት በኋላ ቢሆንም::
ReplyDeleteበዓለም ላይ ችግር የሚነሣው ከአጥንት በላይ ማሰብ በማይችሉ ውሾች የተነሣ ነው»
ReplyDeleteምስጋናዬ ይድረስህ !!!
Dear Dn. Daniel selam leante yihun
ReplyDeleteበዓለም ላይ ችግር የሚነሣው ከአጥንት በላይ ማሰብ በማይችሉ ውሾች የተነሣ ነው»
ውሾቹን «ተው» በሏቸው
Amlake Kidusan kekifu yitebikih
ዳኒ አንተ ያልከዉ ሁሉ ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ባለዉ ሁኔታ ዉሾችም ዉሾችን ተዉ የሚሉትም ያዉ ዉሾች ስለሆኑ ለዉሾች ልብ ስጥልን ብለን እግዜሩን መለመኑ ሳይሻል አይቀርም፡፡
ReplyDeleteቃለ ሒወት ያሰማልን
ዛሬ ዝም ካልን ምንም ጥርጥር የለዉም ነገም ይደግሙታል የህግ ያለህ!!!!
ReplyDeletegeta yetemesegene yihun!! tiru meliket new ''libona yisten'' "b fekir Yeminashenif yaderegen"
ReplyDeleteI like it very much
ReplyDeletethanks Dani
yedingil mariam lij eyesus kiristos hulgize keante gar yihun! tsegana bereketu ayleyih!!
ReplyDeleteoh what amarvelous article.may GOD keep u insafe dn Dani....asteway lebonan yadelen.amen
ReplyDeleteHow???
ReplyDeleteለዳንኤል ጽሁፍ የዶክተር በድሉ “ጠያቂ” ምላሽ ተገቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ! ስለሆነም ግራ ቀኝ ለማመዛዘን ያመች ዘንድ እንሆ ለጥፌዋለሁ።
ReplyDelete----------------------------------------------------------
ከበድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)
ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩኹ!! (ይድረስ ለወዳጄ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)
.
‹‹ውሾቹን ተዉ በሏቸው›› የሚለውን ጽሁፍህን አነበብኩት፡፡
እኔ እንዲህ እላለሁ፤ ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!! አንድም ከመጣብን አደጋ ይጠብቁናል፤ አልያም ይቀሰቅሱናል፤ ያነቁናል፡፡ ጯሂ ውሻ የሌለበው ነው በአልፎ ሂያጁ ሁሉ ቅጥሩ የሚደፈር!!
.
ወንድሜ ዳንኤል ክብረት፣ የውሾቹን ተረት አነበብኩ፡፡ ተረቱን ብወደውም፣ የአጠቃቀምህን አግባብነት ሳላጠይቅ አላለፍኩም፡፡ መቼም ነገርን በምሳሌ ማቅረብ ያለውን ጥቅም ለንዳተ አይነቱ ታታሪ ጸሀፊ አይነግሩም፡፡ በዚህ ምሳሌህ ግን አብይና መንታ ስህተት ሰርተሀል፤ የመጀመሪያው ስህተት በአለም ላይ የተነሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን (ከአለም ጦርነት፣ የቤተእምነት ጥቃት፣ የጎሳ ግጭት፣ የሴት መደፈር፣ የአካል ጉዳት. . . ወዘተ.) በአጥንት ላይ በሚጯጯሁ ውሾች መስለህ ማቅረብህ ነው፡፡ ሁለተኛው ስህተት ደግሞ ሁለቱንም ውሾች፣ ‹‹ዝም በሉ፣ ጩኸት አይሰማ›› ማለትህ ነው፡፡ ነጥቦቼን ላብራራ፡፡
.
መቼም አንድ ምሳሌ የምንጠቀመው ከምንገልጠው ሀሳብ ጋር ተዋድዶ፣ ጭብጣችንን እንዲያጸናልን፣ እንዲተረጉምልን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የአለማችን ችግሮች፣ ከጦርነት እስከ ቡድናዊና ግለሰባዊ መብት መደፈር ያሉ እኩይ ተግባራት ሁሉ፣ የሚነሱት ‹‹በአጥንት ላይ በሚራኮቱ ስግብግብ ውሾች›› የተነሳ አድርጎ ማቅረብ፣ ለህጻናት ግርድፍ ግብረገብ ለማስትማር ካልሆነ በቀር፣ መጠየቅንና መመርመርን ከህይወት ውጣ ውረድ ለተማረ የሙሉ ሰው ህሊና በጣም ይጎረብጣል፡፡
.
መቼም የውሾቹን ጩኸት ማንጸሪያና መተርጎሚያ አድርገኸዋልና የማነሳቸውን ሙግቶች ለምን አነሳህ አትለኝም፡፡ አየህ፣ እኛ ሰዎች ችግራችን ሁሉ የ‹‹አጥንት››፣ ጩኸታችን ሁሉ በ‹‹አጥንት›› ላይ ብቻ አይደለም፡፡ የአለም ጦርነት የተነሳው የሚግጡት አጥንት ባጡ ውሾች ሳይሆን፣ ከግቢያቸው ሾልከው፣ የጌቶቻቸው ከብቶች የሚውሉበትን መስክ አቋርጠው፣ አድማስን ተሻግረው፣ በበቀለው ቁጥቋጦ ላይ ሁሉ እግራቸውን አንስተው መሽናት፣ ጠረናቸውን መተው በተመኙ ውሾች የተነሳ ነው፡፡ የቡድናዊና ግለሰባዊ መብቶች መደፈርም ከ‹‹አጥንት›› የዘለለ መግፍኤ አለው፡፡ ሌላው ቀርቶ በእህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መንስኤ እንዴት ከ‹‹አጥንት›› ጋር እንደምታገናኘው አይገባኝም፡፡ እንዲህ አይነቱ የሌሎችን መብት መድፈር መንስኤው ሆዳምነት (በአንተ አገላለጽ ‹‹አጥንት››) ሳይሆን፣ የህሊናዊ ልእልና ልሽቀት ወይም መንፈሳዊ ረሀብ መሆኑን፣ ለንዳንተ አይነት ከእድሜው እኩሌታ በላይ ሀይማኖታዊ ስነምግባርን ሲሰብክ ለኖረ ዲያቆንም ቢሆን፣ ማስታወስ እንደሚያስፈልግ ልብ ያልኩት ጽሁፍህን ሳነብ ነው፡፡
.
ወንድሜ ዳንኤል፣ ሌላው ያቀረብከውን ምሳሌ ለሰዋዊው ማህበረሰብ ማንጸሪያና መተርጎሚያ እንዳይሆን የሚያደርገው፣ ሁለቱም ውሾት፣ ‹‹ዝም ይበሉ›› የሚለው አንድምታ ነው፡፡ እንዴት ነው ማህበረሰብ ያለተቃውሞ፣ ዝም ብሎ፣ ሁሉን ይሁን ብሎ የሚኖረው? ይህ ሊሆን የሚችለው የአንባገነንነት ጉልበት በበረታበትና ማህበረሰቡም ሁሉን ችሎ፣ ከእንሰሳ በታች ራሱን ጥሎ የሚኖር ከሆነ ነው (ከእንሰሳ በታች ማለቴ፣ እንሰሳትም ምንም እንኳ ባያስቡም፣ ደመነፍሳዊ ጠቅታቸው ጥቃትን እንዲቃወሙ ያደርጋቸዋልና ነው፤ ‹‹ጎሽ ለልጅዋ ስትል ተወጋች›› እንዲሉ)፡፡ እንኳን ማህበረሰብ፣ ቤተሰብም የሚኖረው በተቃርኖ ነው፡፡ እስቲ ቤትህን ፈትሽ! ልጆችህ በቀንም ባይሆን በሳምንት ስንት ጊዜ ይጋጫሉ? አንተና ባለቤትህስ በአመት ስንት ጊዜ ባትጣሉ ተኳረፋላችሁ? ልጆችህ ሲጋጩ ዝም በሉ ነው የምታላቸው? ባለቤትህ ስታኮርፍስ አርፈሽ ተቀመጪ ነው የምትላት? እርግጠኛ ነኝ አይደለም፡፡ ልጆችህ ሲጋጩ በምን እንዳልተስማሙ ትጠይቃቸዋለህ፤ አጥፊውን ለይተህ ትገስጻለህ፤ አንዱ የሌላውን ንብረት ወስዶ እንደሁ ታስመልስለታህ፡፡ እንግዲህ ይህንን የአስተዳደር ዘይቤ ወደ ማህበረሰብ ስታመጣው ደግሞ፣ ጉዳዩ የውሾች የአጥንት ላይ ጩኸትና፣ ዝም በሉ ባያ አዛዥ ማግኘት ብቻ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ማህበረሰቡ በሁለቱ ውሾች ከተገለጸ፣ ዝም በሉ ባዩ ሽማግሌ በማን ይወከላል? በመንግስት? በሀይማኖት ተቋማት? በማን? እና ወንድሜ ዳንኤል ዝምታ አደንቋሪ ነው፡፡ ጩኸት ሁሉ የነውጥ፣ የማፍረስ ምልክት አይደለም፤ ዝምታም እንዲሁ የመስማማት፣ የሰላም ምልክት ብቻ አይደለም፡፡ ዝምታ አምባገነንነትንም ያሰፍናል፡፡ .
እና እኔ እንዲህ እላለሁ! ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!! አንድም ከመጣብን አደጋ ይጠብቁናል፤ አልያም ይቀሰቅሱናል፤ ያነቁናል፡፡ ጯሂ ውሻ የሌለው ነው በአልፎ ሂያጁ ሁሉ ቅጥሩ የሚደፈር፡፡ ውሾቹን ስለምን አሳደግናቸው? ስለጩኸታቸው፣ ስለጥበቃቸው አይደለምን? ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ! በረታችንን ከከበቡት ጅቦች፣ ያረባነውንና ያሰባነውን ይጠብቁልናል፤ እልፍኛችንን ከቀማኛ ሌቦች እንድንጠብቅ ያነቁናል፡፡ ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!! ጯሂ ውሻ አጥቶ ነው ስንቱ በረት ሙሉ ከብቱ የተነዳ፤ ስንቱ የእልፍኙ በር በወሮበላ እየተበረገደ፣ ለዘመናት የቋጠረው ጥሪት እየተዘረፈ ከንቱ ሆኖ…ድሀ ሆኖ…የቀረ፡፡ . . . ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!!. . . ይልቅ ጯሂ፣ ቀስቃሽ. . .አንቂ . . እንዳናጣ ውሾቹን እንጠብቃቸው፡፡
ይህንን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ የዶ.ር በድሉ ዋቅጅራ "ውሾችን ተዋቸው ይጩኹ" የሚለው ለዲ.ን ዳንኤል ክብረት "ውሾችን ተው በሏቸው" ለሚለው ጽሁፍ የተሰጠ መልስ ነው። ይህንን ስጽፍ ለሁለቶች ግለሰቦች ያለኝ ከፍተኛ ቦታ እንደተጠበቀ ሁኖ ነው።
ReplyDelete1. የዶ.ር በድሉ ጽሁፍ ርዕስ በራሱ የዲ.ን ዳንኤልን ጽሁፍ እንዳልተረዳው ወይም በተንሸዋረረ መልኩ እንደተገነዘበው ያሳያል። ዳንኤል ያለ "ውሾችን ተው በሏቸው" ነው። ውሾች ሲጣሉ ዝም አትበሏቸው፤ ገላግሏቸው...ነው እንጂ ውሾች አይጩሁ አላለም። ይህን በኋላ ላይ እመለስበታለው።
የዶክተር በድሉ ስህተት የመነጨው ሀሳቡን በሙሉ ምሳሌው ላይ ማድረጉ ነው። የዲ.ን ዳንኤል ሀሳብ ደግሞ ትኩረቱ በተረት ተመስርቶ የተገለጸው ሀሳብ ላይ ነው።
ዶ.ር በድሉ የዳንኤልን ጽሁፍ ለመተቸት መሰረት ያደረጋቸውን መከራከሪያ ነጥቦች ላይ ሀሳቤን ልስጥ። ሁለት ትችቶችን አንስቷል። የመጀመሪያው "በአለም ላይ የተነሱ ግጭቶችን በአጥንት ላይ በሚጯጯሁ ውሾች መስለህ ማቅረብህ" ስህተት ነው ይላል ዲ.ን ዳንኤልን። ለዚህም አበባሉ መደገፊያ የሚመስሉ ግን ያልሆኑ 2 ነጥቦችን አንስቷል።
ሀ. " ከጦርነት እስከ ግለሰባዊ መደፈር ያሉ እኩይ ተግባራት ሁሉ የሚነሱት 'በአጥንት ላይ በሚራኮቱ ስግብግብ ውሾች' የተነሳ አድርጎ ማቅረብ ለህጻናት ግርድፍ ግብረ ገብነት ማስተማር ነው" ይላል ዶ.ር በድሉ። ይህ ሃሳብ ስህተቱ የዳንኤልን ሀሳብ ቀጥታ እንደወረደ መውሰዱ ላይ ነው። ዳንኤል ውሻወችን የተጠቀመው እኮ እንደምሳሌ ነው። ሁሉም የአለም ችግር ከውሻ ከሚባሉት እንስሳ ጸብ ይጀምራል አላለም። ነገር ግን በውሻነት በተመሰሉ ግለሰቦች ይጀምራል ነው ያለ። ለዛም እኮ ነው እነ ሞሶለኒና ሂትለርን፣ የሀገራት መሪዎችን፣ የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎችን፣ ግለሰቦችን ...እንደምሳሌ ያጣቀሰው። ስለዚህ ዶ.ር በድሉ ዲ.ን ዳንኤል እያለ ያለው የአለም ሆነ የአካባቢያችን ችግሮች በውሻ በተመሰሉት ግለሰቦች ይነሳል ነው እንጅ ውሻ የሚባለው እንስሳ የሁሉም ጽብና ችግር መንስኤ ነው እያለ አይደለም። እዚህ ጋ ዲ.ን ዳንኤል ግብረ ገብነትን የሚሰብክ ወይም የሚያወርድ ነገርም አልተናገረም።
ለ. የመጀመሪያውን ሀሳቡን ለማጠናከር ዶ.ር በድሉ የተጠቀመበት ምርኩዝ ደግሞ እንዲህ ይላል። "...የሌሎችን መብት መድፈር መግፍኤው ...የህሌና ልዕልና ልሽቀት ወይም መንፈሳዊ ርሀብ ነው" ይላል። እዚጋም ዶ.ር በድሉ ከዲ.ን ዳንኤል የተለየ ሀሳብ ያመጣህ የመሰለህ "አጥንት" የሚለውን ቃል እንደ ወረደ "አጥንት" ብለህ መውሰድህ ነው። አጥንትን እንደሚበላ ነገር መቁጠርህ ነው። እንደ ዲ.ን ዳንኤል አገላለጽ "አጥንት" ማለት በውሻ የተመሰሉት አካላት የሚፈልጉት ነገር፣ የራሳቸው ማድረግ የሚቋምጡለት ነገር፣ የሌላን ሰው ጥቅም ጎድተው ለግላቸው ብቻ ማድረግ የሚፈልጉት ነገር፣ ስለሌሎች እንዳያስቡና ስግብግብ ሊያደርጋቸው የሚችል ነገር በመላ ነው። ስለዚህ ዶ.ር በድሉ "አጥንት" የሚለው ቃል አንተ ያልካቸውን የህሌና ልዕልና ልህሽቀት ና መንፈሳዊ ርሀብን የሚያመላክቱ ነገሮችን ስለሆነ ከዲ.ን ዳንኤል የተለየ ነገር አምጥተህ ለሙግትህ ምርኩዝ አላደረክህም።
2.ዶ.ር በድሉ የዳንኤልን ጽሁፍ ለመተቸት የተጠቀመበት ሁለተኛው መከራከሪያ ሃሳብ ዲ.ን ዳንኤል ክብረት "ውሾች ዝም በሉ፤ ጩኸታቹህ አይሰማ" ማለት አልነበረበትም የሚለው ነው። ከላይ መግቢያየ አካባቢ እንደገለጽኩት ዲ.ን ዳንኤል ክብረት ውሾችን ተው በሏቸው እንጂ ዝም በሉ በሏቸው ወይም አትጩሁ በሏቸው አላለም። ዲ.ን ክብረት እያለ ያለው "ውሾች ሲጣሉ ገላግሏቸው...ጸቡ ይብረድ...ይህ ጸብ ከፍ እያለ ሲሄድ ሌላ መዘዝ ያመጣል" እንጂ ውሾች አይጩሁ...ባለቤታቸውን ከሌባና ባላንጣ አይጠብቁ አላለም። ዶ.ር በድሉ ትኩረቱን ምሳሌው ላይ ብቻ ማድረጉን ማሳያ ሊሆነን የሚችለው መደድደሚያውም ነው። "እና እኔ እንዲህ እላለው..ውሾችን ተዋቸው ይጩኹ፤ አንድም ከመጣብን አደጋ ይጠብቁናል፤ አለያም ይቀሰቅሱናል፣ ያነቁናል......ይልቅ ጯሂ ቀስቃሽ ...አንቂ እንዳናጣ ውሾችን እንጠብቃቸው።" ይላል። ዶ.ር ሀሳቡን በሙሉ "ውሻ" ን እና "አጥንትን" ቀጥታ literally ወስዶ የትችቱ ማጠንጠኛ ተረቱ ላይ ብቻ ማድረጉ ሲሆን ዲ.ን ዳንኤል ክብረት ግን ተረቱን እንደመነሻ ወስዶ በ"አጥንት"ና በ"ውሻ" የተመሰሉ ብዙ ጉዳዮችን ዳስሷል። ትኩረቱም እኒህ ጉዳዮች ላይ ነው።
ዶ.ር በድሉ " እንዴት ነው ማህበረሰብ ያለተቃውሞ ፣ ዝም ብሎ፣ ሁሉን ይሁን ብሎ የሚኖረው?" ብሎ ይጠይቃል። የሚገርመው ግን ዲ.ን ዳንኤል ያለው የሚጣሉትን...የሚስገበገቡትን...ከራሳቸው አላማና ጥቅም ውጭ የማይታያቸውን ግለሰቦች ሲጣሉ ዝም አትበሏቸው...እዳቸው ነገ ለናንተም ለአለምም ይተርፋል አለ እንጂ ማህበረሰብ ያለ ሙግት ይኑር...ዝም ይበል የሚል መልዕክት አላስተላለፈም።
ይችን እንድጽፍ ያነሳሳኝ ያለወትሮው ዶ.ር በድሉ ዋቅጅራ ትንሽ ወረድ ያለች ጽሁፍ የጻፈ ስለመሰለኝ ነው።
ለማነጻጸሪያ ይሆን ዘንድ የሁለቶችንም ግለሰቦች ጽሁፍ ገጼ ላይ ለጥፌያቸዋለው።
By:- Dr.Bedilu Wakjira
ReplyDeleteውሾቹን ተዉዋቸው ይጩኹ!! (ይድረስ ለወዳጄ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)
.
‹‹ውሾቹን ተዉ በሏቸው›› የሚለውን ጽሁፍህን አነበብኩት፡፡
እኔ እንዲህ እላለሁ፤ ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!! አንድም ከመጣብን አደጋ ይጠብቁናል፤ አልያም ይቀሰቅሱናል፤ ያነቁናል፡፡ ጯሂ ውሻ የሌለበው ነው በአልፎ ሂያጁ ሁሉ ቅጥሩ የሚደፈር!!
.
ወንድሜ ዳንኤል ክብረት፣ የውሾቹን ተረት አነበብኩ፡፡ ተረቱን ብወደውም፣ የአጠቃቀምህን አግባብነት ሳላጠይቅ አላለፍኩም፡፡ መቼም ነገርን በምሳሌ ማቅረብ ያለውን ጥቅም ለንዳተ አይነቱ ታታሪ ጸሀፊ አይነግሩም፡፡ በዚህ ምሳሌህ ግን አብይና መንታ ስህተት ሰርተሀል፤ የመጀመሪያው ስህተት በአለም ላይ የተነሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን (ከአለም ጦርነት፣ የቤተእምነት ጥቃት፣ የጎሳ ግጭት፣ የሴት መደፈር፣ የአካል ጉዳት. . . ወዘተ.) በአጥንት ላይ በሚጯጯሁ ውሾች መስለህ ማቅረብህ ነው፡፡ ሁለተኛው ስህተት ደግሞ ሁለቱንም ውሾች፣ ‹‹ዝም በሉ፣ ጩኸት አይሰማ›› ማለትህ ነው፡፡ ነጥቦቼን ላብራራ፡፡
.
መቼም አንድ ምሳሌ የምንጠቀመው ከምንገልጠው ሀሳብ ጋር ተዋድዶ፣ ጭብጣችንን እንዲያጸናልን፣ እንዲተረጉምልን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የአለማችን ችግሮች፣ ከጦርነት እስከ ቡድናዊና ግለሰባዊ መብት መደፈር ያሉ እኩይ ተግባራት ሁሉ፣ የሚነሱት ‹‹በአጥንት ላይ በሚራኮቱ ስግብግብ ውሾች›› የተነሳ አድርጎ ማቅረብ፣ ለህጻናት ግርድፍ ግብረገብ ለማስትማር ካልሆነ በቀር፣ መጠየቅንና መመርመርን ከህይወት ውጣ ውረድ ለተማረ የሙሉ ሰው ህሊና በጣም ይጎረብጣል፡፡
.
መቼም የውሾቹን ጩኸት ማንጸሪያና መተርጎሚያ አድርገኸዋልና የማነሳቸውን ሙግቶች ለምን አነሳህ አትለኝም፡፡ አየህ፣ እኛ ሰዎች ችግራችን ሁሉ የ‹‹አጥንት››፣ ጩኸታችን ሁሉ በ‹‹አጥንት›› ላይ ብቻ አይደለም፡፡ የአለም ጦርነት የተነሳው የሚግጡት አጥንት ባጡ ውሾች ሳይሆን፣ ከግቢያቸው ሾልከው፣ የጌቶቻቸው ከብቶች የሚውሉበትን መስክ አቋርጠው፣ አድማስን ተሻግረው፣ በበቀለው ቁጥቋጦ ላይ ሁሉ እግራቸውን አንስተው መሽናት፣ ጠረናቸውን መተው በተመኙ ውሾች የተነሳ ነው፡፡ የቡድናዊና ግለሰባዊ መብቶች መደፈርም ከ‹‹አጥንት›› የዘለለ መግፍኤ አለው፡፡ ሌላው ቀርቶ በእህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መንስኤ እንዴት ከ‹‹አጥንት›› ጋር እንደምታገናኘው አይገባኝም፡፡ እንዲህ አይነቱ የሌሎችን መብት መድፈር መንስኤው ሆዳምነት (በአንተ አገላለጽ ‹‹አጥንት››) ሳይሆን፣ የህሊናዊ ልእልና ልሽቀት ወይም መንፈሳዊ ረሀብ መሆኑን፣ ለንዳንተ አይነት ከእድሜው እኩሌታ በላይ ሀይማኖታዊ ስነምግባርን ሲሰብክ ለኖረ ዲያቆንም ቢሆን፣ ማስታወስ እንደሚያስፈልግ ልብ ያልኩት ጽሁፍህን ሳነብ ነው፡፡
.
ወንድሜ ዳንኤል፣ ሌላው ያቀረብከውን ምሳሌ ለሰዋዊው ማህበረሰብ ማንጸሪያና መተርጎሚያ እንዳይሆን የሚያደርገው፣ ሁለቱም ውሾት፣ ‹‹ዝም ይበሉ›› የሚለው አንድምታ ነው፡፡ እንዴት ነው ማህበረሰብ ያለተቃውሞ፣ ዝም ብሎ፣ ሁሉን ይሁን ብሎ የሚኖረው? ይህ ሊሆን የሚችለው የአንባገነንነት ጉልበት በበረታበትና ማህበረሰቡም ሁሉን ችሎ፣ ከእንሰሳ በታች ራሱን ጥሎ የሚኖር ከሆነ ነው (ከእንሰሳ በታች ማለቴ፣ እንሰሳትም ምንም እንኳ ባያስቡም፣ ደመነፍሳዊ ጠቅታቸው ጥቃትን እንዲቃወሙ ያደርጋቸዋልና ነው፤ ‹‹ጎሽ ለልጅዋ ስትል ተወጋች›› እንዲሉ)፡፡ እንኳን ማህበረሰብ፣ ቤተሰብም የሚኖረው በተቃርኖ ነው፡፡ እስቲ ቤትህን ፈትሽ! ልጆችህ በቀንም ባይሆን በሳምንት ስንት ጊዜ ይጋጫሉ? አንተና ባለቤትህስ በአመት ስንት ጊዜ ባትጣሉ ተኳረፋላችሁ? ልጆችህ ሲጋጩ ዝም በሉ ነው የምታላቸው? ባለቤትህ ስታኮርፍስ አርፈሽ ተቀመጪ ነው የምትላት? እርግጠኛ ነኝ አይደለም፡፡ ልጆችህ ሲጋጩ በምን እንዳልተስማሙ ትጠይቃቸዋለህ፤ አጥፊውን ለይተህ ትገስጻለህ፤ አንዱ የሌላውን ንብረት ወስዶ እንደሁ ታስመልስለታህ፡፡ እንግዲህ ይህንን የአስተዳደር ዘይቤ ወደ ማህበረሰብ ስታመጣው ደግሞ፣ ጉዳዩ የውሾች የአጥንት ላይ ጩኸትና፣ ዝም በሉ ባያ አዛዥ ማግኘት ብቻ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ማህበረሰቡ በሁለቱ ውሾች ከተገለጸ፣ ዝም በሉ ባዩ ሽማግሌ በማን ይወከላል? በመንግስት? በሀይማኖት ተቋማት? በማን? እና ወንድሜ ዳንኤል ዝምታ አደንቋሪ ነው፡፡ ጩኸት ሁሉ የነውጥ፣ የማፍረስ ምልክት አይደለም፤ ዝምታም እንዲሁ የመስማማት፣ የሰላም ምልክት ብቻ አይደለም፡፡ ዝምታ አምባገነንነትንም ያሰፍናል፡፡ .
እና እኔ እንዲህ እላለሁ! ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!! አንድም ከመጣብን አደጋ ይጠብቁናል፤ አልያም ይቀሰቅሱናል፤ ያነቁናል፡፡ ጯሂ ውሻ የሌለው ነው በአልፎ ሂያጁ ሁሉ ቅጥሩ የሚደፈር፡፡ ውሾቹን ስለምን አሳደግናቸው? ስለጩኸታቸው፣ ስለጥበቃቸው አይደለምን? ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ! በረታችንን ከከበቡት ጅቦች፣ ያረባነውንና ያሰባነውን ይጠብቁልናል፤ እልፍኛችንን ከቀማኛ ሌቦች እንድንጠብቅ ያነቁናል፡፡ ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!! ጯሂ ውሻ አጥቶ ነው ስንቱ በረት ሙሉ ከብቱ የተነዳ፤ ስንቱ የእልፍኙ በር በወሮበላ እየተበረገደ፣ ለዘመናት የቋጠረው ጥሪት እየተዘረፈ ከንቱ ሆኖ…ድሀ ሆኖ…የቀረ፡፡ . . . ውሾቹን ተዉዋቸው ይጩሁ!!. . . ይልቅ ጯሂ፣ ቀስቃሽ. . .አንቂ . . እንዳናጣ ውሾቹን እንጠብቃቸው፡፡
እናም ውሾቹን «ተው» በሏቸው
ReplyDeleteእናም ውሾቹን «ተው» በሏቸው
ReplyDeleteDn Daneal the Illusionist one! you are one of these have to undertake that happening in Ethiopia. Because you lead all the peppoples to be racial through your soothing spiritual mingled words specially Amhara. You preached us to hate the government on the name of spiritual. We deceived and did your wish. I able to recognize your hidden agenda when you are master of ceremony with Dr Abiy. Why Dn? You know what the church reward to Dr Abiy. Why you said nothing about that? But I know what you had to write if the former government is this. Wake up! meditate what is going on and what you are doing. Please write something about the current government to the confused Ethiopians. You have to atone us now telling the main conspiracy of Dr Abiy. You know that what he is dealing about Ethiopia with the foreign governments. Is he selling the whole country!? Please what ever a guilty you were we Ethiopians need your help now. There are many peoples who follow you. We are ready to hear you earnestly write about what is going on Ethiopia. Don't be racism it is the right time to save writing the truth.
ReplyDeletePlease I have a dream to the church that one day reveals, I will help you then. I know I have no power now to do anything with out daring to insult you the elite one.
As you have the ability to write like this good article you have more information who the actor to condemned is. There is time to preach, but not now. Tell us who the dogs are. You are seeding hate in every heart to hate what he/she guess as dog. Write explicitly in concise way. Dr Abiy "yeken jboch" you else "wshoch" I don't know what kind of game and motto is this!
ReplyDeleteanyways the AlmightyGod may bless you!