Thursday, December 22, 2011

መንፈሳዊነት ጠገግ ወይስ ሕይወት?

click here for pdf 
በዓለም ላይ በሃይማኖት መንገድ አያሌ የጽድቅ ሥራዎች ተሠርተዋል፤ በተቃራኒውም በሃይማ ሽፋን አያሌ ግፎች ተሠርተዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን የሕይወት መንገዳቸው ሳይሆን የሕይወት ጠገጋቸው በማድረጋቸው ምክንያት፡፡ የእምነቱን ሕግ እና ሥርዓት ለማክበር ሳይሆን በእምነቱ ስም ሊገኙ የሚችሉ ጥቅሞችን ለማነፍነፍ በመጠጋ ታቸው የተነሣ፡፡ ለፖለቲካ፣ ለኢኮኖሚ እና ለሥልጣን ዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሲሉ ሃይማኖትን ተጠግተው ለሃይማኖታቸው ሳይሆን በሃይማኖታቸው ይጠቀማሉ፡፡
ይህ ሲሆን ደግሞ ሃይማኖት ዓላማውን ይስታል፡፡ የሃይማኖት ዋናው ዓላማ በሃይማኖት መመርያ መሠረት ለሰማያዊ ዋጋ የሚያበቃ መልካም ነገርን በምድር ላይ መፈጸም ነው፡፡ ሃይማኖት የፈጣሪን መንግሥት ይሰብካል፣ ፖለቲካ ደግሞ ምድራዊ መንግሥት፣ ሃይማኖት ሰማያዊ ትርፍን ይሰብካል፣ ንግድ ደግሞ ምድራዊ ትርፍ፣ ሃይማኖት ሰማያዊ ሹመትን ይሻል፣ ሥልጣን ደግሞ ምድራዊ፡፡
ሃይማኖት ምድራዊ ሕይወታችንን ሲቃኘው ኑሯችን መንፈሳዊም ሥጋዊም ጤናው የተጠበቀ ይሆናል፡፡ ንግድ፣ ፖለቲካ፣ ዘር እና ሥልጣን ሃይማኖትን ሲቃኘው ግን ሃይማኖት ከሰማያዊው ግቡ ጋር ይቆራረጣል፡፡
በተለይም ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በልዩ ልዩ እምነት የሚያምኑ ዜጎች በአንድ ላይ ተግባብተው እና ተገናዝበው በሚኖሩባት ሀገር ሃይማኖት ሰማያዊውን ዓላማ ለቅቆ ምድራዊ መሆን ከጀመረ የፍቅር እና የአንድነት ማሠርያነቱ ላልቶ የጠብ እና የጦርነት መንሥኤ ሊሆን ይችላል፡፡
ሃይማኖት መሥመሩን ለቅቆ ከማዋሐጃነት ወደ መከፋፈያ መሣርያነት የሚያመራው የሕዝቦች ግንኙነት ሃይማኖትን ብቻ መሠረት እያደረገ መጓዝ ሲጀምር ነው፡፡ በሕዝብ ግንኙነቶች ውስጥ ሃይማኖትን ብቻ መሠረት የሚያደርጉ ግንኙነቶች አሉ፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ተዛምዶ የማያበላሹ እና በየእምነት መጻሕፍቱም የተደነገጉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የጋብቻ ግንኙነቶች አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር የሃይማኖት ቤተሰብነትን መሠረት ያደርጋሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሃይማኖትን የግድ መሠረት ማድረግ የሌለባቸው ማኅበራዊ ግንኙነቶችም አሉ፡፡ የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የአካባቢ፣ የርዳታ፣ ወዘተ ዓይነት ግንኙነቶች፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች ተመሳሳይ አለመካከቶችን፣ ውሎችን፣ የሀገር ሕጎችን እና ሰብአዊነቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡
አንድ ከርስቲያን የምነግደው ከክርስቲያኑ ጋር ብቻ ነው ካለ፣ አንድ ሙስሊምም በዚሁ መንገድ ከተጓዘ፣ በአንድ አካባቢ ለመሥፈር ወይንም መኖርያን ለመሥራት አካባቢው የክርስቲያን ወይንም የሙስሊም ተብሎ ከተከፈለ፣ በአንድ መሥሪያ ቤት ለመቀጠር የኃላፊዎቹን ወይንም የባለቤቶቹን እምነት ማመን ዋና መመዘኛ ከሆነ፣ ርዳታ ለማግኘት የረጅዎቹን እምነት መቀበል አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ከተደረገ ሀገር እንደ ሀገር መኖር ይከብዳታል፡፡
እንዲህ እንደኛ ልዩ ልዩ እምነቶችን የሚከተሉ ሕዝቦች ያሉባት ሀገር ሕዝቦቿ በሰላም እና በጤና መኖር እንዲችሉ ሦስት ነገሮች ያስፈልጓታል፡፡ መተዋወቅ፣ መገናዘብ እና ከድምሩ በላይ ማሰብ፡፡
ለመሆኑ ከእኔ የተለየ እምነት ያለው ወገኔ ምንድን ነው የሚያምነው? ለምን? ከኔ ልዩነቱ እና አንድነቱ ምንድን ነው? የሚጠላው እና የሚወድደው ምንድን ነው? እኔ እና እርሱ ሳንጋጭም ሳንዋዋጥም እንዴት ተግባብተን ልንኖር እንችላለን? በሚሉት ጉዳዮች ላይ አንዱ ስለ ሌላው ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረጉን ነው መተዋወቅ የምንለው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ስለሌሎች የሰማናቸው እና ያወቅን የመሰሉን ነገሮች የተዛቡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በጠላትነት የምንተያየውም በተነገሩን የተዛቡ መረጃዎች ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ የማያምኑትን እንደሚያምኑ፣ የማይቀበሉትን እንደሚቀበሉ፣ የማይደግፉትንም እንደ ሚደግፉ እያደረግን የሰማናቸው እና ያነበብናቸው ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ምናልባትም አንዳችን ስለሌላችን ባለማወቃችን የተነሣ የሌሎችን መብቶች ልንደፈጥጥም እንችላለን፡፡ በቃላት አጠቃቀማችንም እንስታለን፡፡
መተዋወቅ እነዚህን ሁሉ ነው የሚፈታው፡፡ ብዙ ጊዜ መተዋወቅን ከመሳሳብ እና እምነትን ከመለወጥ አንፃር ስለምናስበው መገፋፋት በመካከል ይሰፍናል፡፡ ሰው ሌላውን ማወቅ ያለበት እምነቱን እና አመለካከቱን ለመለወጥ ብቻ አይደለም፡፡ የራስን አመለካከት መለወጥ እና ስለሌላው ያለንን አመለካከት መለወጥ ይለያያሉ፡፡
መገናዘብ የምንለው ምናልባትም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ይገኝ የነበረ አሁን ግን እየተዳከመ የሄደ በጎ ጠባይ ይመስለኛል፡፡ አንድን እምነት ዐውቆ፣ ያንን አማኝ ላለማስቆጣት እና ማኅበራዊ ግንኙነትን ላለማበላሸት ተጠንቅቆ፣ ነገር ግን መተጋገዝ እና አብሮ መኖር ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ቤተ ክርስቲያን ለሚሠሩ ክርስቲያን ወገኖቻቸው ርዳታ ሲሰጡ እስልምና አይጠቅምም ብለው የራሳቸውን ትተው፣ ወይንም ክርስትና ከኛ ይሻላል ብለው በክርስትና አምነው አይደለም፡፡ ለክርስቲያን ወገኖቻችን ቤተ ክርስቲያን ሊኖራቸው ይገባል ብለው እንጂ፡፡ ክርስቲያኖችም እንዲሁ፡፡ መገናዘብ ማለት ይሄ ነው፡፡
በማኅበራዊ ግንኙነቶቻችን ውስጥ ይህንኑ ነው የምናየው፡፡ በሙስሊሞች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ክርስቲያኖች በቤታቸው ሲገኙ ሙስሊም ወገኖቻቸው ለምግባቸው ተጠንቅቀው ነው፡፡ ይገናዘባሉና፡፡ ለእነርሱ ተብሎ የተዘጋጀውን የሚያቀርቡት የክርስቲያኖቹን ፍላጎት ተገንዝበው ነው፡፡
ሦስተኛው ከድምሩ በላይ ማሰብ መቻል ነው፡፡ ከእኛ ከአማኞቹ በላይ የሆነች ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች፡፡ ሁላችንም እንደልባችን ልንሆን የምንችለው ይህቺ ሀገር እንደ ሀገር ስትኖር ነው፡፡ እናም ይህቺን ሀገር እንደ ሀገር ለማኖር ስንል የምንከፍለው ሰማዕትነትም አለ፡፡ እኛ የየራሳችንን እምነት ብቻ እየተመለከትን በምናደርገው ሥጋዊ ፉክክር ይህቺ ሀገር እንዳትጎዳ የመጠንቀቅ ግዴታም አለብን፡፡ ስለ ክርስትና ቅርሶች፣ ስለ እስልምናም ታሪካዊ ቦታዎች ስናስብ ስለ ኢትዮጵያ ሀብቶች ማሰብ አለብን፡፡ ከወዲህ ማዶ እኛ ድንበሩን በገፋነው መጠን ከወዲያ ማዶም የሚገፋ መኖሩን መርሳት የለብንም፡፡
አለቃ ገብረ ሐና ቤት ወይዘሮ ማዘንጊያ በሌሉበት አንዲት ሴት የስድስት ወር ልጇን ይዛ ትመጣለች፡፡ የመጣችበት ምክንያት አልታወቀም፡፡ በድንገት ወይዘሮ ማዘንጊያ ሲገቡ ሴቲቱ ደንግጣ የራሷን ልጅ ትታ የማዘንጊያን ልጅ ይዛ ትሮጣለች፡፡ ማዘንጊያ አለቃ የባለጉ መስሏቸው ተናደዱ፡፡ ወዲያው ልጁን አነሡና እሳት ውስጥ ሊጨምሩት ወደ ምድጃው ሲሄዱ አለቃ «ተይ ማዘንጊያ እዚያም ቤት እሳት አለ» አሏቸው ይባላል፡፡
እዚህ ቤት አንዳች ነገር ሲደረግ እዚያም ቤት ሊደረግ እንደሚችል ማሰብ ነው፡፡ እዚህ አካባቢ ለምናቃጥላት ቤተ ክርስቲያን ወይንም መስጊድ በሌላ አካባቢ ዋጋውን ልንከፍልበት እንችል ይሆናል፡፡ እዚህ ሙስሊሞች አንሰው ክርስቲያኖች ስለበዙ የምንጨቁን ከሆነ እዚያ ክርስቲያኖች አንሰው ሙስሊሞች በሚበዙበት ቦታ ደግሞ ተመሳሳዩ እንዲፈጸም እያሳሰብን ነው ማለት ነው፡፡ አለቃ እንዳሉት እዚያም ቤት እሳት አለና፡፡
አሁን አሁን በዚህች ሀገር ከሚያሳስቡኝ ነገሮች አንዱ በሃይማኖት ንጣሌ የማሰብ አመለካከት ነው፡፡ በሃይማኖት ንጣሌ የማሰብ አመለካከት ማንኛውንም ነገር በሃይማኖት መነጽር ብቻ የማየት አስተሳሰብ ነው፡፡ አክስዮን ለመመሥረት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ገንዘብ በባንክ ለማስቀመጥ ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ አንድ አካባቢ ለመኖር ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ አንድን ነገር በጅምላ ወይንም በርካሽ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ርዳታ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ሥራ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት መጠየቅ እየተጀመረ ነው፡፡
ፈጣሪያቸውን አምነው፣ እርሱ የፈቀደውን አድርገው የርሱን መንግሥት ለመውረስ የተሰባሰቡ ወገኖች ዓላማቸውን ቀይረው የአማኙን ስብስብ እንደ አማራጭ ገበያ፣ እንደ ደንበኛ ማፍሪያ፣ እንደ ገንዘብ መሰብሰቢያ፣ ለሥልጣን እንደ መሸጋገርያ፣ የድምጽ ማግኛ፣ የርዳታ እህል መለመኛ ካደረጉት በዚህች ሀገር ንጥያ እየተባባሰ ነው ማለት ነው፡፡
በተለይም ቢቻል ከአባቶቻችን የተሻለ እንሠራለን፣ ባይቻልም አባቶቻችንን እናበረታለን ብለው የሚሰባሰቡ ወጣት መንፈሳውያን ለጽድቅ የተሰባሰቡባቸውን ማኅበራት ወደ ንግድ «ኢምፓየር» የሚቀይሯቸው ከሆነ፣ በመንፈሳዊ ዓላማ እና በሰማያዊ ግብ ያሰባሰቧቸውን አባላት ከሰማይ አውርደው በአክስዮን እና በካፒታል መዋጮ የሚያሰባስቧቸው ከሆነ፤ መንፈሳዊነቱ ሕይወት ሳይሆን ጠገግ ሆኗል ማለት ነው፡፡
በመንፈሳውያን መካከል ሊኖር የሚገባው ግንኙነት መንፈሳዊነትን ብቻ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡ የሚሠሯቸውም ሥራዎች ዓላማቸው ጽድቅ መሆን አለባቸው፡፡ መንፈሳውያን በምድር ላይ በሥጋ ሊጠቀሙ ሳይሆን ሊጠቅሙ ነው የሚመጡት፡፡ መንፈሳውያን በሃይማኖት የሚሰባሰቡት መክሊታቸውን ሊያተርፉ እንጂ አክስዮናቸውን ሊያተርፉ አይደለም፡፡
እስካሁን ድረስ በእምነት ስም የተነሡ ግጭቶች ራሳቸው እምነቶቹ የፈጠሯቸው አይደሉም፡፡ እምነቶቹን ለግላዊ ጥቅማቸው ማዋል የሚፈልጉ አካላት የፈጠሯቸው እንጂ፡፡ እነዚህ ሰዎች የመጀመርያቸው ሥራ ደግሞ በእምነቶቹ ሰማያዊ ዓላማ ላይ ምድራዊ ዓላማ መጨመር ነው፡፡ የግጭቱ መነሻም ይኼው ምድራዊ ዓላማ ይሆናል፡፡
እነዚህ እየታዩ ያለ ክስተቶች እኛው ኢትዮጵያውያን ማረም አለብን፡፡ አሁን የሚያስፈልገን የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት፣ የእስልምና፣ የይሆባ፣ ባንክ አይደለም፡፡ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የኢትዮጵያ ባንክ ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን በሃይማኖት ስም የተመሠረተው የማኅበረ እገሌ ወይንም እገሌ የአክስዮን ማኅበር አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ የአክስዮን ማኅበር ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን የሙስሊም ወይንም የክርስቲያን ሆስፒታል አይደለም፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ነው፡፡
አሁን የሚያስፈልገን የሙስሊም ወይንም የክርስቲያን የርዳታ ድርጅት አይደለም፡፡ የተቀበለውን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ የሚያውል የርዳታ ድርጅት ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን የክርስቲያኖች ወይንም የሙስሊሞች ሠፈር አይደለም፡፡ ተስማሚ የመኖርያ ሠፈር ነው፡፡
ይህ ጉዞ ኢትዮጵያውያንን ተነጣጥለን ብቻ የምናስብ፣ በአንድ ሀገር ከመኖራችን በቀር የመግባቢያ ሰነድ የሌለን ያደርገናል፡፡ ምናልባትም በንግድ እና በገንዘብ ምክንያት የሚመጡ ግጭቶችም ወደ እምነቶች ውስጥ ገብተው እንዲያተራምሱ ዕድል ይከፍታል፡፡ እናም ሃይማኖትን ለጽድቅ እና ለድኅነት እንጂ ለንግድ «ኢምፓየር» መገንቢያነት አንጠቀምበት፡፡
© ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔትላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

57 comments:

 1. Beautiful article Dn/Daniel
  I never seen even my e-mail often like your website every time:. new idea, basic things and seasonal.
  long live with health we wish for you.

  ReplyDelete
 2. Kale-Hiwot yasemalin, erejim yeAgelgilot zemenin yistilin.

  ReplyDelete
 3. ክርስቲያን ነኝ። ግን እዉነተኛ ሙስሊም እህቶቼንና ወንዲሞቼን አወዳቸዋለሁ።ቤተ-ክርስቲያን የሚያቃቲሉትን ግን እዉነተኛ የሆኑ ሙስሊሞችም ይናደዱባቸዋል። አገራቺን የጋራቺን ናት። በጋራ፡በፍቅር፡በአንዲነት፡በሰላም እንኑርባት።
  እግዚኣብሄር ሐገራችንን እና ህዝባችንን ይባርክ። አሜን!

  ReplyDelete
 4. እስካሁን ድረስ በእምነት ስም የተነሡ ግጭቶች ራሳቸው እምነቶቹ የፈጠሯቸው አይደሉም፡፡ እምነቶቹን ለግላዊ ጥቅማቸው ማዋል የሚፈልጉ አካላት የፈጠሯቸው እንጂ፡፡ እነዚህ ሰዎች የመጀመርያቸው ሥራ ደግሞ በእምነቶቹ ሰማያዊ ዓላማ ላይ ምድራዊ ዓላማ መጨመር ነው፡፡ የግጭቱ መነሻም ይኼው ምድራዊ ዓላማ ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 5. It is good to keep the name Ethiopia if we realy concider about it interesting and inportant may God bless

  ReplyDelete
 6. Oh May z Almighty protect z land from crisis. I think there are evil patriots who preach devil's dreams. This in fact should worry all of us and z govt. EPRDF's policy was to bring a diverse nation but resulted in rival group on z verge of sweeping EPRDF itself. What a curse. Anyway lets all be alert and protect our peace and stability. Dani and all readers lets remain positive until z last minute. Is z prophecy to happen???

  ReplyDelete
 7. “We had better dispense with the personification of evil, because it leads, all too easily, to the most dangerous kind of war: religious war.” Konrad Lorenz

  Thanks Danni.

  ReplyDelete
 8. yesterday with one of my friend i was able to meet one American family. The grand paretns and there grandson have been there. through them we were able to see why they came to Ethiopia... it was not only to see the christian heritage of our country though they never hide there filling on what they have been looking for the first time... yes they were also amazed to see a unique country where the great muslim prophit sent his familly and followers on earth... they were tring there best to get the best out of such wonderful history of Ethiopian christian and muslims where they are able to see a familly even with both religions... but they were not lucky as they told us. it is because both christians and muslims of this century are tring to rewrite the sweet story of the country and of the religions without any addition... why don't you respect what your religious grand parents left even if it might be wrong and tring to be best and do your best in your time??? was there strong question...if you go to rome, Jerusalem, meka and medina or saudi, turky, egypt, tunisia you will have a chance to learn and see a very shamefull and worset dids that they had been doing and practicing...no one among them can be free from such faulty activity... but if you come to Ethiopia more than any time this generation is distorting the image and the real beuty of the country... yes i perfectly agree with such important ideas... the former religious groups in ethiopia were tring there best for there own religion and to keep the country safe... but today it is becoming difficult to find such people... from any religious group of the country... rather we are facing different agendas from the religious groups and looking very dangerous activities from the "spiritual" people... it can call and develop war, financial strength, poletics, ignorance, illitracy not development as a whole...
  thank you Daniel for posting the very important message for which most of us are not able to find easily the hard copy of the magazine...

  ReplyDelete
 9. ይህቺ ፅሑፍ ውስጠ ወይራ ትመስለኛለች፡ አክስዮን አክስዮን የሚል ቃል ተደጋገመባት፡፡

  ReplyDelete
 10. our deep urge for development needs our unity.all we sud be asked to work in ol our regions is citizenship.not where we r from.z former governor shwinzinger was austian until he was 21.but he manages to be a governor in USA.i am born in addisababa. can i be a president of a region? I do not think so

  ReplyDelete
 11. ዲ/ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልን ይህ ክፉ አባዜ ሃገር ውስጥ ያለውን
  ብቻ አደለም በውጭ ያለነውንም ተፀናውቶናል ልብ ያለው ልብ ይበል።

  ReplyDelete
 12. አዎ ዳኒ ትክክል ብለሃል የሚያስፈልገን ኢትዮፕያን ትልቅ የሚያደርግ እንጂ የሃይማኖት ስብስብ የጎሳ ድርጅት አይደለም እግዚብሄር ያስበን

  ReplyDelete
 13. Dear Daniel,

  I personally believe on the notion of "unity in diversity" . For me, religion could not be the reason to commit violent action. Of course, it could be the force multiplier, to use it. This is because it is the simplest entry point to instigate sympathizers.

  Thus, your perspective inculcate in our mind the principles of patience, tolerance, and respect for others. I like you intervention which I refer from your article that entails:

  "እስካሁን ድረስ በእምነት ስም የተነሡ ግጭቶች ራሳቸው እምነቶቹ የፈጠሯቸው አይደሉም፡፡ እምነቶቹን ለግላዊ ጥቅማቸው ማዋል የሚፈልጉ አካላት የፈጠሯቸው እንጂ፡፡"

  Both AL Qaeda, Lord Resistance Army, Irish Revolutionary Army, the Red Brigade, or Badder Meinhof has no ground to refer religion as a source of their violent activities. No single reason to dehumanize others and attack indiscriminately. I totally disagree on the acclamation of " If you are not with us, you are against us" mentality. What I provoke is that universal justice and love prevails others not to do evils. Let us change "Them Versus Us" mind setup. May God Bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 14. ዳኒ ይህን ጽሁፍህን ከማንበቤ በፊት ቤተክርስቲያናቸውን ሙስሊሞች አቃጥለውባቸው የሚያለቅሱ ክርስቲያኖችን የሚያሳይ ቪዲዮ እያየሁ አብሬያቸው እያለቀስኩ ነበር፡፡ አንተ የጻፍከውንም እያለቀስኩ ጨረስኩት፡፡ ግን ወዴት እየሄድን ነው? ኢህአዴግ እግዚአብሔር ይይልህ!! ከፋፍለህ ከፋፍለህ ለዚህ አበቃህን፡፡ እንኳን ደስ አለህ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why do you refer to EPRDF, you have divided yourself before EPRDF

   Delete
 15. AGENAGN from ECSUN አሁን የሚያስፈልገን የሙስሊም ወይንም የክርስቲያን የርዳታ ድርጅት አይደለም፡፡ የተቀበለውን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ የሚያውል የርዳታ ድርጅት ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን የክርስቲያኖች ወይንም የሙስሊሞች ሠፈር አይደለም፡፡ ተስማሚ የመኖርያ ሠፈር ነው፡፡

  ReplyDelete
 16. It is really good. However, don't forget that differences will be there always. As for me, it is not the 'empire' that create the problem. But the idea behind it. For example establishing muslim or christean company may not have a problem. Prohibiting muslim or christean cusomers not to buy ther products and refusing to buy from others domain is very dangerous. Intellectual maturity
  may resolve this problem. We should 'think globally and act locally'.

  ReplyDelete
 17. ዲያቆን ያነሳህው ጉዳይ ከወቅታዊነቱ ባሻገር አሳሳቢም ነው፡፡የዛሬን አያድርገውና ኢትዮጵያውን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች አፈር ፈጭተው አብረው በልተው አብረው ጠጥተው አንድ ላይ አድገው ነበር የአንድ እናት ጡት ለሁለት ጠብተው፡፡እኔ እንደሚመስለኝ ወጣቱ ክርስቲንም ሙስሊምም ጋር ችግር አለ፡፡ሁለቱም ነገሮችን ከሀይማኖት አንጻር ብቻ ነው የሚመለከቱት የድሮ አብሮነታቸውን እረስተው፡፡ከዚህ ጋር ፍፁም የሚቃረን ባለፈው ሐይቅ ቅዱስ ከእስጢፋኖስ ገዳም ሄጄ ያጋጠመኝን ልንገራችሁ የሚወስደኝ ባለ ጋሪ ነው ያጫወተኝ ከቅዱስ ከእስጢፋኖስ ገዳም ባሻገር የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ነበረች በጣም ጉስቁልቁል ብላ የተጎዳች፤ እናም እዚያ ያሉ አገልጋይ ስባተ እግዚአብሄሩን ለማድረስ የገንዘብም የቁሳቁስም ችግር ስላጋጠማቸው ፅላቷን ይዤ ከቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም እሄዳለሁ ሲሉ የአካባቢው ሙስሊም ምን አለ መሰላችሁ ሁሉንም አስፈላጊ ነገር እኛ እናሟላለን ታቦቷ ከዚህ አትነቃነቅም አለላቹሀ እናም ሁሉም በሙስሊሞቹ ተማልቶ ስባተ እግዚአብሄሩ ቀጠለ፡፡የዛሬ ክርስቲያንና ሙስሊም መጣቶች ከዚህ ብዙ መማር አለብን ማለትም አብሮነታችንን እና ቀደም የነበረ መተሳሰባችንን፡፡ደሴም ላይ በቅርቡ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ ሙስሊሞች ቤተክርስቲያን በመገኘት የደስታ ተካፋይ ነበሩ አለኝ፡፡የተቀረው የሀገራችን ክፍልም ከደሴና ከአካባቢው ብዙ መማር አለብን እነዚህ አካባቢዎች ለክርስቲያንና ሙስሊም ወገኖች ተከባብሮና ተፋቅሮ የመኖር ምሳሌ ናቸውና፡፡ዲያቅን ሰላመ እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን ፡፡

  ReplyDelete
 18. kalehiwot yasemlin DANI

  ReplyDelete
 19. Dani Mechem yene Comment atawetawim

  Yehaymanotu gichit eko share memesrtu adelm miknyatuu... Eyawekew lmn wed gon endmigefaw eko new yemigermineg... Weyane edimewn lemarazem yemitekmbt zed new... beft bezr ahun degm behymanot... ebakih ketsfak ewnet tsaf kaltsefk bek zim bel..

  ReplyDelete
 20. wow Dani thank you for such a great and timely idea; you know this time even people select a shop from where they are to buy their mobile card as per their religious affliction, to me this is shame as we are all brothers and sisters working for the same country and common goal.

  ReplyDelete
 21. በመንፈሳውያን መካከል ሊኖር የሚገባው ግንኙነት መንፈሳዊነትን ብቻ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡ የሚሠሯቸውም ሥራዎች ዓላማቸው ጽድቅ መሆን አለባቸው፡፡ መንፈሳውያን በምድር ላይ በሥጋ ሊጠቀሙ ሳይሆን ሊጠቅሙ ነው የሚመጡት፡፡ መንፈሳውያን በሃይማኖት የሚሰባሰቡት መክሊታቸውን ሊያተርፉ እንጂ አክስዮናቸውን ሊያተርፉ አይደለም፡፡

  የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው። ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል። መዝሙር 19 9-10

  ReplyDelete
 22. Thank u for sharing this article but u make it more soft. Have u ever seen or heard that any burnt mosque in recent times? No. This problem is happening only on Christians and their church. And I think it is time now to get together and show our strength. We dont afford any church to burn any more. Does the Muslim community condemn the burning of St. Arsema church? No. Does our fathers condemn and react over the situation? No.
  I think we have to make some stiff measures now.

  ReplyDelete
 23. very nice idia thank you dani

  ReplyDelete
 24. ሃይማኖት በባሕሪው ያዋጋል፡፡ ሃይማኖቱ አዲስ ከሆነ ውጊያው የቃላት ውጊያ ነው፡፡ ሃይማኖት ሲያድግ እና ሲደረጅ፤ ውጊያውን በቃልም በጦርም ያደርጋል፡፡ ይህ የሃይማኖት ኢቮሉሽን ነው፡፡ መፍትሔው Strong Secular State መመስረት፤ ከተመሰረተም ማጠናከር ነው፡፡ መፍትሔው ለሃይማኖተኞች ባይጥምም፤ ሴኩላር ‹አማኞችን› ቢያበዛብንም፤ በከንቱ ከመተላለቅ ግን ይሻላል ባይ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 25. Thank you Daniel!
  I appreciate all of your ideas.
  I would like to tel you sometihng I read in history.

  Many years ago, European countries especially in central and north sides did exactly the same way to prevent people to good idea. During the time, people who were members of Catholic and new revolution (protestant) denominations were fighting everywhere, in the work places, in the bus stops (fermata), in the living areas and over of public centers. Then after, governments of European countries followed that way you mentioned in several aspects, shuch as, they created committees between two churches, manipulated people through Medea to become calm, and made together discuses panels between priests and parish councils. Those ideas kept people together and people had preceded their common land before personal things. So, we should separate between private and social(common)things. If we become more selfish in private matters, we togetherlose everything we have.

  ReplyDelete
 26. yeminanebewin endintegebrew yirdan. kale hiwot yasemah.

  ReplyDelete
 27. አሁን የሚያስፈልገን የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት፣ የእስልምና፣ የይሆባ፣ ባንክ አይደለም፡፡ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የኢትዮጵያ ባንክ ነው፡፡
  ተመቸነኝ ዳኒ ተባረክ

  ReplyDelete
 28. HI Danie well done
  here is some one say
  do you agree?
  AT least 2/3 of our miseries spring from human stupidity,human malice,those great motivators,justifies of malice and stupidity idealism,dogmatism,proselytizing,zeal on behave of religious or political ideas
  Aldous Huxley

  ReplyDelete
 29. ፈጣሪያቸውን አምነው፣ እርሱ የፈቀደውን አድርገው የርሱን መንግሥት ለመውረስ የተሰባሰቡ ወገኖች ዓላማቸውን ቀይረው የአማኙን ስብስብ እንደ አማራጭ ገበያ፣ እንደ ደንበኛ ማፍሪያ፣ እንደ ገንዘብ መሰብሰቢያ፣ ለሥልጣን እንደ መሸጋገርያ፣ የድምጽ ማግኛ፣ የርዳታ እህል መለመኛ ካደረጉት በዚህች ሀገር ንጥያ እየተባባሰ ነው ማለት ነው፡፡ትክክል ብለሀል፡፡ እሚሰማህ ካገኘህ፡፡
  እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡

  ReplyDelete
 30. Dani, this is a great idea that we Ethiopians take it as a great asset. The number of religion is not more than that of our ethnics. If we can tolerate and live peacefully united with our differences in race, we also can do the same with religion.

  I think we all have to be wolloye. If you go to wollo area, you will see how people cooperate and respect each other to live together besides their differences in religion and ethnic.

  Wollo has almost all religions and has also a lot of ethnics in the region: Amhara, Tigre, Oromo, Afar, Argoba, Lasta agew, if not more. However, they are relatively peaceful and united.

  I saw how Muslims set fire on a church in Silte gurage area. No one can eliminate a religion or an ethnic group by burning their house or killing a certain people in that specific group rather it will make the situation worse. That, I think, is an awareness problem. People, especially leaders in that area, have to equipped with basic general knowledge so that they can see and evaluate things from different perspectives.

  I also read a news that stated that 42 Christians were arrested and detained in Saudi because they tried to practice their faith in their own house. That is sick, we don't have to allow this to happen in our country. At the same time the Ethiopian embassy has to interfere in this case for the release of our citizens.

  Let's think positive and respect others opinion regardless of our differences in religion, gender, race, color, level of education, and others that might be causes for differences. If we practice doing this, we can change everything.

  God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 31. God Bless you Dani, you are right!!

  ReplyDelete
 32. ይህ ፅሑፍ እጅግ ወቅታዊ በመሆኑ ሳላመሰግን አላልፍም ፤ምክንያቱም በስልጤ ሀ/ስብከት ስልጢ ከተማ የጋሮሬ ቅ/አርሴማ ቤ/ክርስቲያን በአክራሪ ሙስሊሞች መፍረሱና ከዚያም መቃጠሉ የሰማንበት ወቅት ነውና፡፡
  ‹‹እዚህ ቤት አንዳች ነገር ሲደረግ እዚያም ቤት ሊደረግ እንደሚችል ማሰብ ነው፡፡ እዚህ አካባቢ ለምናቃጥላት ቤተ ክርስቲያን ወይንም መስጊድ በሌላ አካባቢ ዋጋውን ልንከፍልበት እንችል ይሆናል፡፡ እዚህ ሙስሊሞች አንሰው ክርስቲያኖች ስለበዙ የምንጨቁን ከሆነ እዚያ ክርስቲያኖች አንሰው ሙስሊሞች በሚበዙበት ቦታ ደግሞ ተመሳሳዩ እንዲፈጸም እያሳሰብን ነው ማለት ነው፡፡ አለቃ እንዳሉት እዚያም ቤት እሳት አለና፡፡››
  በሌላ መልኩ ስልጤ የእስላም እንጂ የክርስቲያን አይደለችም ማለታቸው ከምን የመጣ ነው
  እዚያም ቤት እሳት እንዳለ ረስተውት ይሆን ለነገሩ ምንጭ አሳይቶ ነዳጅ አለን ፤ኢትዮጵያ
  ኖረው አረብ ነን………ከሚሉ ምን ይጠበቃል…..

  ReplyDelete
 33. Ayyy Dani wedet eyehedk new?

  ReplyDelete
 34. ኦ ነገር ሁሉ በጣም የከበደ ይመስለኛል እግዚአብሔር አስተዋይ ልቦናን ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 35. እግዚአብሔር ይስጥልን ዳኒ! ትልቅ እና ብዙ ሊጻፍበት እና ልንወያይበት የሚገባ አጀንዳ ነው ያነሳሀው።ማኅበር እና አክስዮን የሚለውን ነጥብ መግባቱን መልዕክቱን አደበዘዘብኝ። ለብቻ ብታየው ይሻል ነበር።

  ReplyDelete
 36. "ሃይማኖት በባሕሪው ያዋጋል፡፡" በሚለው አስተያየት አልስማማም፤አማኞች በባህሪያቸው ደካሞች ናቸው ቢባል ግን ያስኬዳል፡፡

  ዳኒ እግዚአብሕር ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 37. I was born and raised in Ethiopia although am not Ethiopian, I share the language the culture and above all the Orthodox religion, I left Ethiopia when I was only teenager, Last year I come back to Addis Abeba and and had a chance to visit the country from "Zalanbesa" to "Moyale" ...while very satisfied by my fellow christian youth awareness on their religion...I was back very worried noticing the untold religious tension getting root in Ethiopia. Here in Europe my neighborhood is dominated by Muslims and when I entered their shop they nag me by asking if I am a Muslim. Because they think, that makes the bond strong if I was so. But I would never never want to see Ethiopia ( even though am not its citizen) to be in a position where people have twisted mind indulged in religious fanaticism.
  God Bless Ethiopia .

  ReplyDelete
 38. ይህቺ ፅሑፍ ውስጠ ወይራ ትመስለኛለች፡ አክስዮን አክስዮን የሚል ቃል ተደጋገመባት፡፡

  ReplyDelete
 39. ዳንኤል እግዚአብሕር ይስጥልን፡፡
  «ተይ ማዘንጊያ እዚያም ቤት እሳት አለ» ትልቅ ምሳሌ ነው

  ReplyDelete
 40. Dear Daniel,

  I am once again back to comment on your blog. Prior to getting on to the theme, I really would like as usual to appreciate your wonderful contribution to letting the citizen know about what is/are going on in their beloved motherland as regards spirituality, social affairs of life, the politics and economic activities.

  But your bizarre approach in recent articles has been urging me to pay more attention to what you wanna say or convey under cover (in beautiful story telling articles).

  Your professional quality is unquestionably perfect. You are so smart that you can let us have a big volume book from a rubbish phrase; that is wonderful and great!!

  But if a man of such great caliber and full of grace; how come he stick himself to what it to be called as "yemogn zefen hulgize abebaye hoy" in the sense that you have been firing you machine gun to your firstborn.

  A commentator boldly but in one line put forward your foolishness or shall I say malicious approach?
  ይህቺ ፅሑፍ ውስጠ ወይራ ትመስለኛለች፡ አክስዮን አክስዮን የሚል ቃል ተደጋገመባት፡፡

  I feel like you are telling story of the under establishment ''Noah Bank" which is believed to be orchestrated mainly by MK. This is not a rocket science to guess about your agenda. Although the article does have long paragraphs the theme of it is አክስዮን.

  I strongly support not only your idea but boldly in practice to get rid such a weed off before letting it to have ground deep-rooted.

  Your article is not organized in a way that can inspire citizens to say no to ethnio-centric and ritualistic approach to the economy.

  Let me remind of you where and how the big mess started small in the last decade. It starts with Awash Int'l Bank S.C which I had worked for sometime, tagged as of Oromifas, then comes Abyssinia tagged as of Neftegna Amhara, and then comes Wogagen tagged and still is rich source of funds for EPRDF led economic empires (Guna, Ambasel, and the like). I can list more others like NiB as for Guraghe, Anbesa as for Tigray.

  But the following are convincing evidences of the late 2000's. Hawassa Bank, Zemzem Bank, Enat Bank, Debub Global Bank. These are banks come into the economic lifeline either as ethnocentric, or religion based, or gender based or zonal based.

  When The PM was asked about banks of those nature and their potential danger, He lamented we would like to advise and suggest that these approach is not just and could have bad impact in the long run. He continued that if they stick to their philosophy we can't do anything as it is constitutional right.

  MK is not exceptional in the manner that it comes out from the footsteps of its predecessors. The country is scrambled into fierce battlefield on account of ethnocentric federalism that really helps the cults (arrogant and greedy leaders emanated from different parts of the country) to have economic dominion one over there others.

  THIS IS THE TRUTH BEHIND አክስዮን!!! THIS IS THE REAL NATURE IN THE RACE TO አክስዮን. Whom you may blame now? Do you still rigidly blame the EFFECT forgetting about the CAUSE?

  If you are really good enough to be the FALCON like the one appeared in you blog, let you wisely and in good respect put your sharp critic unto The Government and PM Meles Zenawi who willingly and knowingly admit theses Tsunami to happen now but to dismantle Ethiopia in the near future.

  Please STOP attacking your first bone. Please STOP writing for the innocents for they have no better access to information or they may not be interested in politics. Please fight to weed out ethnocentric business empires and approaches.

  Many Thanks to Daniel

  May God Bless Ethiopia Amen
  y

  ReplyDelete
 41. ሰላም ዳኒ የዛሬው ጽሁፍህ በጣም አስደሳች ነው፡፡ በሃይማኖትሽፋን የሚደረጉ ነገሮች በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ በተለይ አሁን አሁን በእኛ በኦርቶዶክስያዊያን ዳይቆን ነን ባዮች የሚፈጸሙ ድርጊቶች እውነት እግዚአብሔር እንዲህ ይዘበትበታል ያሰኛል፡፡ ብዙ ያጋጠሙኝ ነገሮች ስላለነው ካጋጠመኝ ችግር አንዱ የእግዚአብሔርን ቃል በደንብ ያውቃል ሰባኪም ነው፡፡ ለጓደኝነት እንደሚፈልገኝ ነገረኝ እሺ ብዬ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀጣጥረን ተለያየን በቀጠሮው ሰዓት እሱም እኔም መጣሁኝ አብረን ፀሎት አድርገን መነጋገር ስንጀምር ግን ይህሰው ሰይጣን ነው ወይስ በሰው የተገለጠ ሰይጣን እስክል ድረስ የሚያወራው ነገር በጣም የሚገርም ነው፡፡ ከጳጳሱ እስከ ታች ድረስ ሁሉንም ያውቃል፡፡ ውጭም ለመሄድ ከፈለግሽ በጣም ቀላል እንደሆነና ለስብከት ወደ ውጭ አገር አሜሪካ፣ካናዳ፣ጀርመን...ወዘተ እንደሚመላለስ ነገረኝ በዚህ አጋጣሚ ታዲያ ብዙ ሴቶችን ሚስት አድርጉ እንደሚወስድና እያንዳዳቸው 90,000.00 ብር እደከፍሉትና ቢዝነስ እንደሚሰራ ነገረኝ አሁን ግን ዕድሜዬ እየሄደ ስለሆነ ትክክለኛ ሚስት አግብቼ ለመሄድ የምፈልገው አለኝ፡፡ እኔ ግን ይሄ ነገር ለእኔ አዲስ ነገርና በጣም ትክክል እንዳልሆነ ነገርኩት፡፡ በጣም ነው የሳቀብኝ፡፡ በመጨረሻ ግን ትንሽም አልቆየም ወድያው አልጋ እንድንይዝ ሲጠይቀኝ በጣም አናደደኝ ለምን ትናደጂያለሽ እግዚአብሔር እኮ ፍቅር ነው እኛ ስለተዋደድን እግዚአብሔር አይፈርድብንም አለኝ ምንም አልተናገርኩትም ተነስቼ ወደቤቴ ሄድኩኝ ከዚያ ወዲህ ሲደውልልኝ ምልስ አልሰጠውም ነበር አሁን አቆሞል ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ነገሮች ያጋጥመኛል ለምን እንደሆነ አይገባኝም እና ዳኒ ያነሳኸው ዕርስ በጣም ትምህርት ሰጭ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ልብ ይስጠው፡፡

  ReplyDelete
 42. Ze-Nazareth (የናዝሬቱ )December 24, 2011 at 3:04 PM

  ዲያቆን ዳንኤል ጽሑፍህ የተደበላለቀ ስሜት ነው የፈጠረብኝ፡፡ ትክክል የሆኑ እና ትክክል ያልሆኑ ሐሳቦችን ያየሁበት መሰለኝ፡፡ ምን አልባት ሙሉ በሙሉ ከግል ስሜት ፀድተህ የጻፍከው ከሆነ ግን አንዳንድ ነገሮችን ማለት ፈለግሁ፡፡
  የእምነት ተቋማት የኢኮኖሚ አቅማቸውን ከማጠናከር አንጻር አክሲዮን ቢኖራቸው እንደ እኔ ክፉ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ነገር ግን ክፋት የሚሆነው በሌሎች የእምነት ተቋማት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እና ጫና ለመፍጠር ታስቦ ከሆነ ግን ፍፁም ስፍተት ነው፡፡ አክስዮን የሚመሠርቱ አካላትም ትክክለኛ ዓላማቸውን ቆም ብለው ይመርምሩ ማለት እፈልጋለሁ፡፡
  ከዚያ ውጪ ግን አንዱ በዚህ በተሳሳተ መልኩ እየሔደ ተጽዕኖ ሲፈጥር ሌላው ራሱን በማጠናከር አዎንታዊ በሆነ መልኩ ተጽዕኖውን መከላከል የለበትም የሚል አቋም የለኝም፡፡
  እግዚአብሔር ይስጥልኝ
  ዲያቆን ዳንኤል ጽሑፍህ የተደበላለቀ ስሜት ነው የፈጠረብኝ፡፡ ትክክል የሆኑ እና ትክክል ያልሆኑ ሐሳቦችን ያየሁበት መሰለኝ፡፡ ምን አልባት ሙሉ በሙሉ ከግል ስሜት ፀድተህ የጻፍከው ከሆነ ግን አንዳንድ ነገሮችን ማለት ፈለግሁ፡፡
  የእምነት ተቋማት የኢኮኖሚ አቅማቸውን ከማጠናከር አንጻር አክሲዮን ቢኖራቸው እንደ እኔ ክፉ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ነገር ግን ክፋት የሚሆነው በሌሎች የእምነት ተቋማት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እና ጫና ለመፍጠር ታስቦ ከሆነ ግን ፍፁም ስፍተት ነው፡፡ አክስዮን የሚመሠርቶ አካላትም ትክክለኛ ዓላማቸውን ቆም ብለው ይመርምሩ ማለት እፈልጋለሁ፡፡
  ከዚያ ውጪ ግን አንዱ በዚህ በተሳሳተ መልኩ እየሔደ ተጽዕኖ ሲፈጥር ሌላው ግን ራሱን ማጠናከር አዎንታዊ በሆነ መልኩ ተጽዕኖውን መከላከል የለበትም የሚል አቋም የለኝም፡፡
  እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  ReplyDelete
 43. ዘ ሐመረ ኖህDecember 24, 2011 at 3:32 PM

  በቅርቡ ከዚህ በፊት በጅማና አካባቢው እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ክርስቲያኖች በገጀራና በሰየፍ በአክራሪ ሙስሊሞች ተጨፈጨፉ በእሳት ተቃጠሉ አሁን ደግሞ በስልጤ ቤተከርስቲያን አቃጠሉ ይህ በሚገባ የሚያመለክተው በሃገራችን ውስጥ አክራሪ እስልምና ሥር እየሰደደ መምጣቱን ነው ይህንን ኢሰብአዊ ድርጊት መንግስት ለስልጣኑ ሲል ዝም ብሎ አልፎታል የሞተውም ሆነ የተጎዳው ክርስቲያን በሰማእትነት አልፏል ከእንግዲህ ወዲህ ግን እዚያም ቤት እሳት መኖሩን ማስታወስ ወቅታዊ ማሳሰቢያ ነው ተዋህዶ የፍቅርና የሰማእትነት ሃየማኖት ነች ከትእግስት በላይ ሲሆን ግን ጥቃትን መከላከልን የተዋህዶ እምነት እንዳትመነምን መጠበቅን እናውቅበታለን በወንጌል ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ ተብሎ ተጽፏልና ኃይል የእግዚአብሔር ነው አግዚአብሔር ይስጥልን ዲ ን ዳኒ

  ReplyDelete
 44. DANI EGZIABHER ABZITO YIBARKIH, GIZEWUN YEWAJE MELIKT NEW BERTA.
  SAMUEL ZE GONDAR

  ReplyDelete
 45. It is good that you mention it. Where is the tolerance???

  No protection for them. They have always been against our church, since the time of Gragne Ahmed. I guess they have forgotten that they came to that land as a guest. As a Christian duty, we just allowed them to live and practice their belief. It is sad to see such a deprived, impenitent and violent society who do crimes under the religion umbrella.

  ReplyDelete
 46. ከላይ በ December 23, 2011 8:44 PM “But I would never never want to see Ethiopia ( even though am not its citizen) to be in a position where people have twisted mind indulged in religious fanaticism.” ብለው አስተያየት የሰጡትን ሰው

  ከልቤ “በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ባለመሆንዎት እንኳን ደስ ያለዎት!” ልላቸው እወድዳለሁ፡፡ አምላክ እጅግ ይወድዎታል፡፡ ብዙው ሰው እየተሰቃየ ያለው አንድም የመለወጥ አማራጭ በማጣቱ አንድም ኢትዮጵያዊነቱን መርሳት አቅቶት ነውና ፡፡

  ReplyDelete
 47. ልቦና ያለው ያስተውል ... ይህ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለት የተቀመጠ የመጀመሪያ መስፈርት ነው :: እራሰዎን ይፈትሹ

  ዳኒ እውቀትን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 48. wow Dn. Dani May God bless you!

  ReplyDelete
 49. Why don't you speak for the real cause ...

  ReplyDelete
 50. ዳኒ ይህን ጽሁፍህን ከማንበቤ በፊት ቤተክርስቲያናቸውን ሙስሊሞች አቃጥለውባቸው የሚያለቅሱ ክርስቲያኖችን የሚያሳይ ቪዲዮ እያየሁ አብሬያቸው እያለቀስኩ ነበር፡፡ አንተ የጻፍከውንም እያለቀስኩ ጨረስኩት፡፡ ግን ወዴት እየሄድን ነው? ኢህአዴግ እግዚአብሔር ይይልህ!! ከፋፍለህ ከፋፍለህ ለዚህ አበቃህን፡፡ እንኳን ደስ አለህ፡፡

  ReplyDelete
 51. YOU ARE REALLY BAD,FOOL AND JEALOUS.

  ReplyDelete
 52. እውነት ብለሀል ወንድሜ ግን ሲጀመር '"ሰው" በጨለማ እየሄደ በጅብ ያመካኛል.'እንዳይሆን
  ነገሩ ቆም ብሎ በጥቂቱ ኢትዮጵያዊውን ፊት አውራሪ አመዴን:እማሆይ ቴሬዛን: አርበኛውን ጋንዲን:.
  ብንናዳምጥ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉና..የፅሁፉ ሚዛን እነዚህን ቢሰፍር መልካም ነበር:..ውብ ነው ለዛ አለው ዳ.ዳንኤል:: ምኞቴ ብዙነህ@ ፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete
 53. አክስዮን ለመመሥረት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ገንዘብ በባንክ ለማስቀመጥ ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ አንድ አካባቢ ለመኖር ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ አንድን ነገር በጅምላ ወይንም በርካሽ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ርዳታ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ሥራ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት መጠየቅ እየተጀመረ ነው፡፡
  It is true. But @Y at Dec 24,8:43. Why do you misguide people to relate this with Noah Bank and MK and associate it with the Constitution and PM Meles. We are also members and it is his right to criticize. I don't think it you belong to the majority of MK. ዲያቆን ዳንኤልን ለማሳጣት ካልሆነ በቀር!(ሳ ይጠብቃል )
  Stop criticizing your own brother please.Stop and contribute your best to your own country and your Church.
  እግዚአብሔር ለሁላችንም ልብ ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 54. @ AnonymousDec 27, 2011 04:36 AM it seems that this article concerns you most. You are such a person (look what you said) who is living under the cover of spirituality.
  God Bless Ethiopia!

  ReplyDelete
 55. Your bold quote "Ezam Esat Ale" does not describe Christianity. The fire is only there . There is no fire to react against Muslims from Christians. I have never heard of any Christian who did wrong to mosques in reaction to what has been done on churches. That is wrong comparison.

  ReplyDelete