Tuesday, December 20, 2011

የባላንጣዎች ደርግ


Doris Kearns Goodwin የጻፈቺውን Team of Rivals የሚለውን ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ሰሞኑን እያነበብኩት ነበር፡፡ መጽሐፉ ስለ ታላቁ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ስለ አብርሃም ሊንከን የተጻፈ ነው፡፡ በአሜሪካ ታሪክ እንደ አይከን ከሚታዩ መሪዎች አንዱ ነው አብርሃም ሊንከን፡፡
አብርሃም ሊንከን ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ሲወዳደር እጅግ የሚንቁት እና ብቃቱን የሚጠ ራጠሩት ተቀናቃኞች ገጥመውት ነበር፡፡ ከራሱ ከሪፐብሊካን ፓርቲም ሆነ ከዴሞክራቲክ ፓርቲ በሞያም፣ በልምድም፣ በታዋቂነትም እንልቃለን ብለው ከሚያስቡ ተቀናቃኞች ጋር ነበር የተፎካከረው፡፡
በወቅቱ የነበሩ ሚዲያዎች የአብርሃም ሊንከንን መመረጥ ዕድለኛ ስለሆነ ነው ነበር ያሉት፡፡ ምክንያቱም ተፎካካሪዎቹ ከእርሱ የተሻሉ ናቸው ተብለው ይታሰቡ ስለነበር ነው፡፡ አንድ በጥብቅና ሞያው እጅግም ያልታወቀ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አንድ ዙር ብቻ ያገለገለ፣ ለሁለት ጊዜያት ያህል ለሴናተርነት ተወዳድሮ ያልተሳካለት ሰው ፕሬዚዳንት ሲሆን ሚዲያዎች ምን ያድርጉ፡፡
 ሊንከን የተመረጠበት ዘመን በአሜሪካ ታሪክ እጅግ ወሳኝ ከተባሉት ዘመናት አንዱ ነው፡፡ በሰሜነኞቹ እና በደቡቦቹ መካከል ሀገሪቱን ለሁለት የሚከፍል መለያየት መጥቶ ነበር፡፡ በባርያ አሳዳሪዎች እና ባርነት ለአሜሪካ ርግማን ነው በሚሉት ተራማጆች መካከል የነበረው ክርክር እየተጧጧፈ መጥቶ ወደ ባላንጣነት እየተቀየረ ነበር፡፡
አብርሃም ሊንከን የፕሬዚዳንትነቱን ሥፍራ እንደ ያዘ ያደረገው ነገር ነበር መላውን አሜሪካ ያስገረመው፡፡ ካቢኔውን ያቋቋመው በእነዚያ ባላንጣዎቹ በነበሩት ተፎካካሪዎች ነበር፡፡ ዋና ዎቹ የሪፐብሊካን ተቀናቃኞች የነበሩትን የኒውዮርኩን ዊልያም ሴዋርድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኑ፣ ሪፐብሊካኑ የኦሐዮ ገዥ ሳልማን ቼዥ የገንዘብ ሚኒስትር ሆኑ፣ ሪፐብሊካኑ የሚዞሪ ግዛት ታዋቂ ፖለቲከኛ ኤድዋርድ ቤትስ ዋና ዐቃቤ ሕግ ሆነው ተሾሙ፡፡
ሌሎች ኃያላንን ደግሞ ከዴሞክራቲክ ፓርቲው አመጣ፡፡ እነዚህም ቢሆኑ የሊንከን የውስጠ ፓርቲ ተቀናቃኞች ነበሩ፡፡ ጌዲዮን ዌልስ የባሕር ኃይል ሚኒስትር ሆነ፤ ሞንት ጎመሪ ብሌይር ፖስት ማስተር ጄኔራል ተብለው ተሾሙ፡፡ ኤዲዊን ኤም ስታንተን የጦር ሚኒስትር ተደረጉ፡፡ ሁሉም ማለት ይቻላል በዕውቀትም ሆነ በልምድ ከአብርሃም ሊንከን እጅግ የተሻሉ ነበሩ፡፡ በወቅቱ ሹመቱን የሰሙ ሁሉ እነዚህ ስመ ገናና ሰዎች ፕሬዚዳንቱን ይውጡታል ብለው ፈርተውለት ነበር፡፡ ከዚያም በላይ እርስ በርሳቸውም ሆነ ከሊንከን ጋር የማይስማማ ሰዎች በአንድ ካቢኔ መገኘት ያንን ካቢኔ የባላንጣዎች ደርግ (ደርግ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ኮሚቴ ማለት ነው) አሰኘው፡፡
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደካማ እና ልምድ የሌለው፣ አሜሪካንንም ከችግር ሊያወጣ የማይችል እያሉ ይወቅሱት የነበረውን ሊንከንን ማመስገን እና ማድነቅ የጀመሩት ዋነኛ ባላንጣዎቹ ነበሩ፡፡ «ብቃት የሌለው አስተዳዳሪ» እያለ ይወቅሰው የነበረው ሪፐብሊካኑ ኤድዊን ስታንተን «ፍጹም ለመሆን የተቃረበ» ሲል ሊንከንን አደነቀው፡፡ ሴዋርድ አብርሃም ሊንከንን ከማድነቅ አልፎ የሊንከን የአስተዳደር ጉዳዮች አማካሪና የቀርብ ወዳጁ ሆነ፡፡
በመጀመርያዎቹ ጊዜያት ስለ ሊንከን ሲያስብ «አሜሪካ በአጋጣሚ ያገኘችው ደካማ መሪ» ይል የነበረው ኤድዊን ሳንተን የአሜሪካውን ጠቅላይ የጦር አዛዥ ሊንከንን አድናቂ ሆነ፡፡ እንዲያውም ሊንከን ከሞተ በኋላ ለብዙ ሳምንታት ዕንባውን መቆጣጠር እየተሳነው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ያለቀስ ነበር፡፡ ከሊንከን የተሻለ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኖ ለመመረጥ ባለመታከት ይለፋ የነበረው ኤቨን ቼዝ በመጨረሻ ላይ ሊንከን ከእርሱ እጅግ የሚበልጥ መሪ መሆኑን ራሱ መሰከረ፡፡
በዚህ ሁኔታ ነበር አብርሃም ሊንከን አሜሪካን ከእርስ በርስ ጦርነት እና ከባርነት መርገም ያወጣት፡፡ 1876 እኤአ ታዋቂው ተናጋሪ ፍሬዴሬክ ዳግላስ አፍሪካ አሜሪካውያን ለአብርሃም ሊንከን ያሠሩትን የመታሰቢያ ሐውልት ሲመርቅ «ማንኛውም ሰው ስለ አብርሃም ሊንከን እውነተኛ ነገር ሊናገር ይችል ይሆናል፤ አዲስ ነገር ግን መናገር አይችልም» በማለት እንደተናገረው አብርሃም ሊንከን ትውልደ ትውልድ አሜሪካውያን ሁሉ የሚያውቁት እና የሚያደንቁት፤ ታሪኩን እንደ ሕዝብ መዝሙር በቃላቸው የሚሸመድዱት፣ በየንግግራቸው የሚጠቅሱት እና የሚያሞግሱት መሪ ለመሆን ቻለ፡፡
የመጀመርያው አፍሪካ አሜሪካዊ ፕሬዚዳንት ሆኖ የተመረጠው ባራክ ኦባማ እንኳን የፕሬዚዳንትነቱን ቃለ መሐላ ሲፈጽም በዚሁ ተፈቃሪ ፕሬዚዳንት በአብርሃም ሊንከን መጽሐፍ ቅዱስ ነበር የማለው፡፡
አገር ከአጣብቂኝ ወጥታ አብዛኛውን ሕዝብ ወደሚያግባባ እና ወደሚያስተባብር ጎዳና እንድትሻገር፣ ክርክሩ ለጠብ እና ለመለያየት መሆኑ ቀርቶ እንደ ቢላዋ ስለት አንድ ነገር ለመቁረጥ እንዲውል ለማድረግ ከተፈለገ ሀገር በባላንጣዎች ደርግ መመራት አለባት፡፡
አንድ ዓይነት ከበሮ ሲመታላቸው ተመሳሳይ እስክስታ የሚወርዱ፣ ለምን? እንዴት? የት? ማን? ሌላስ? ብለው መጠየቅ የማይፈልጉ ሰዎች ተባብረው የሚመሩት ሀገርም ሆነ ተቋም እንደ ረግረግ ጭቃ ችግሩን እዚያው ላይ ሲወ ቅጥ ይኖራል እንጂ ከችግሩ መውጣት አይችልም፡፡
ብዙዎቻችን በሃሳብ እና በአመለካከት ከሚመስሉን፣ ሃሳባችንን ከሚደግፉ እና ያልነውን ሁሉ ይሁን ይደረግልን ብለው ከሚቀበሉ ሰዎች ጋር ለመሥራት ጁዎች እና ፈቃደኞች ነን፡፡ ከማይደግፉን እና ከሚቃወሙን፣ ከኛ የተለየ ሃሳብ ካላቸው እና ከማይስማሙን ሰዎች ጋር መሥራት ግን ይከብደናል፡፡
ሊንከን ይቃወሙት የነበሩትን ባላንጣዎቹን ወደ ካቢኔው ሲያመጣ ለተወሰነ ጊዜ ችግር እንደ ሚገጥመው አጥቶት አልነ በረም፡፡ ግን በራሱ የሚተማመን ሰው ነበረ፡፡ እነዚያ ባላንጣዎቹ መቃወም ብቻ ሳይሆን በዕውቀት እና በልምድ ከእርሱ የተሻሉ መሆናቸውን እያወቀ ነው ያመጣቸው፡፡ በራሱ ይተማመን ስለነበር ግን ስማቸው ከእኔ በላይ ይገናል፣ እኔን ይረቱኛል፣ ይንቁኝ ይሆናል፣ የሚሉ ስሜቶች አልነበሩትም፡፡ የእነርሱን ብርታት የሚያውቀውን ያህል የራሱ በርታት ያውቀዋል፡፡
ጀግና መሪ ማለት ከእርሱ ከሚበልጡም ሆነ ከእርሱ ከሚያንሱ፣ ብሎም ከእርሱ ከሚስተካከሉ ሰዎች ጋር መሥራት የሚችል መሪ ነው፡፡ ጀግና መሪ ማለት እንዳልከው ይሁንልን ከሚሉት ሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ያልከውን አልተቀበ ልነውም፣ እኛ ደግሞ በዚህ እና በዚያ መንገድ አይተነዋል ከሚሉት ተቀናቃኞቹ ጋር መሥራት የሚችል ነው፡፡
ሊንከን እነዚህን ሰዎች ወደ ካቢኔው ሲያመጣ የሰዎችን ተቃውሞ አይደለም ያየው፡፡ እነዚህ ሰዎች ልዩ ልዩ አሜሪካ ውያንን ይወክላሉ፡፡ የእነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የብዙዎቹም አፎች ናቸው፡፡ ይህ የእነርሱ ሃሳብ ያዋጣል ብለው የሚያስቡ አያሌ አሜሪካውያን ነበሩ፡፡ ስለዚሀም ለእነዚህ ሃሳቦች ዕድል መስጠት ፈለገ፡፡ እነዚህ ሃሳቦች ብቻቸውን ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ፤ ከሌሎች ሃሳቦች እና አመለካከቶች ጋር ሲፋለሙ እና ሲዋሸዱ ለሁሉም አሜሪካዊ የሚጠቅም የተሻለ ሃሳብ ይፈልቃል፡፡ ስለዚህም የወዳጅ የቀናቃኞች ካቢኔ አቋቋመ፡፡
ለሀገር የማይጠቅም ሃሳብ የለም፡፡ ግን ብቻውን ለሀገር የሚጠቅምም ሃሳብ የለም፡፡ ማንኛውም ሃሳብ የሰዎች ሃሳብ ነው፡፡ የሰዎች ሃሳብ ደግሞ ውሱንነት አለበት፡፡ በዚህ ዓለም አንድ እና ብቸኛ መፍትሔ የለም፡፡ ከሌሎች የተሻለ መፍትሔ ግን ሊኖር ይችላል፡፡ መፍትሔ ከሌሎች የተሻለ ነው ማለት ግን ብቻውን ፍጹም ነው ማለት አይደለም፡፡ የሕክምና ሰዎች የተሻለ መድኃኒት የሚሉት የተሻለ የማዳን ያለውን እና አነስተኛ ተጎንዮች ጉዳት የሚያመ ጣውን ነው፡፡ ምንም የጎንዮች ችግር የማያመጣም ሆነ መቶ በመቶ ፍቱን የሆነ መድኃኒት ግን የለም፡፡
ከታችኛው ጀምሮ እስከ ላይኛው የመንግሥት መዋቅራዊ አካል፤ መንግሥታዊ ባልሆኑ ሌሎች ተቋማት እና ማኅበራት ውስጥም ቢሆን አለቆች እና መሪዎች በዙርያቸው ሊሰበስቧቸው የሚያስፈልጓቸው ሲጠሯቸው አቤት፣ ሲልኳቸው ወዴት የሚሉትን ብቻ ከሆነ ራሳቸውን በራሳቸው ለመግደል ተዘጋጅተዋል ማለት ነው፡፡ የሚቃወሙን፣ የሚሞግቱን፣ ስሕተታችንን የሚያሳዩን፣ የተሻ ሃሳብ የሚያመጡልን፣ እኛንም ጭምር የሚያስንቁን ሰዎችም በዙርያችን ያስፈልጋሉ፡፡
አንድ ካቢኔ፣ ምክር ቤት፣ ቡድን፣ ኮሚቴ፣ ማኅበር፣ ተቋም፣ ቦርድ፣ ኅብረት፣ ወዘተ ሲቋቋም የተለያዩ ሃሳቦች እና አመለካከቶች ውክልና ያላቸው፣ ክርከሩን እና ውይይቱን የሚያሞቁ፣ የተለየ መንገድ የሚያዩ፣ በድፍረት ሊገዳደሩ የሚችሉ፣ ግን በመጨረሻ ለአንድ ዓላማ የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
ሰው ሲፈጠር መጀመርያ የተቋቋመው ተቋም ቤተሰብ ነው፡፡ የመጀመርያው ቤተሰብ የተመሠረተው በአዳም እና በሔዋን መካከል ነው፡፡ የእነዚህን የሁለቱን አፈጣጠር፣ ሥነ ልቡና፣ ፍላጎት፣ ዐቅም፣ ጠባይ፣ ከተመለከትን አብረው መኖር አይገባቸውም ነበር፡፡ ነገር ግን የተፈጠሩት አብረው እንዲኖሩ ነው፡፡
ብቻም አልነበረም፡፡ የሀገራችን ሊቃውንት ስለ ሰው ተፈጥሮ ሲያብራሩ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ተፈጠረ ይላሉ፡፡ አራቱም እርስ በርሳቸው የሚቀዋወሙ ናቸው፡፡ እሳት እና ውኃ፣ አፈር እና ነፋስ፡፡ እሳትን ነፋስ ያቀጣጥለዋል፣ እሳትን ውኃ ያሞቀዋል፣ እሳትን ውኃ ያጠፋዋል፣ አፈርን ውኃ ይወስደዋል፣ አፈርን ነፋስ ያጉዘዋል፣ ነፋስን የአፈር አቀማመጥ (የመልከዐ ምድር ሁኔታ) ይገታዋል፡፡ ሁለቱ ረቂቅ ናቸው፤ ነፋስ እና እሳት፡፡ ሁለቱ ግዙፍ ናቸው፣ አፈር እና ውኃ፡፡ አንዱ ቋሚ ነው፣ አፈር፣ አንዱ ረቂቅ ቋሚ ነው፣ እሳት፤ አንዱ ፈሳሽ ሯጭ ነው፣ ውኃ፣ አንዱ ፈጣን ሯጭ ነው፣ ነፋስ፡፡
ሁለቱ ቀሊል ናቸው፣ እሳት እና ነፋስ፡፡ ሁለቱ ከቢድ ናቸው፣ አፈር እና ውኃ፡፡ ሁለቱ ቀሊል ሆነው ወደላይ ሲንጠለጠሉ፣ ሁለቱ ከቢድ ሆነው ወደታች ይመዝናሉ፡፡ ሁለቱ ከቢድ ሆነው ወደታች ስበው እንጦሮጦስ እንዳይከቱ፣ ሁለቱ ቀሊል ሆነው ወደ ላይ ይስባሉ፡፡
 እንዲህ እንዲህ እያልን ስናይ ሰው ራሱ «የባላንጣዎች ደርግ» ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
የባላንጣዎች ደርግ የሚያስፈልጋቸው የመግባቢያ ሰነድ ነው፡፡ ይህቺ ሀገር ምን እንድትሆን እንፈልጋለን? የት እንድ ትደርስ እንፈልጋለን? ዓላማችን ምንድን ነው? ግባችን የት ነው? እዚህ ላይ ከተስማማን መንገድ ልዩ ልዩ ነው፡፡ ሃሳብ ልዩ ልዩ ነው፤ መፍትሔ ልዩ ልዩ ነው፣ አማራጭ ልዩ ልዩ ነው፡፡ ሞያ ልዩ ልዩ ነው፣ ችሎታም ልዩ ልዩ ነው፣ ስልትም ልዩ ልዩ ነው፡፡
እንደ ሊንከን ዓይነት በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ከሚበልጧቸው እና ከሚቀናቀኗቸውም ጋር ለመሥራት ዐቅሙ ያላቸው፤ የራሳቸውን ክብር ሳይሆን የሀገርን ጥቅም የሚያዩ ሰዎች እንደ ጅራታም ኮከብ ከዘመናት አንዴ ብቅ ሲሉ ነው የሚታዩት፡፡ ብዙ ጊዜ የሚገኙት እንደ እኒህ ቀጣሪ ዓይነት ናቸው፡፡
ሰውዬው ለኩባንያቸው የሂሳብ ባለሞያ መቅጠር ፈልገው ማስታወቂያ አወጡ፡፡ በማስታወቂያው መሠረትም አራት ሰዎች ለቀለ መጠይቅ ቀረቡ፡፡ ጠያቂው ሰውዬው ነበሩ፡፡ የመጀመርያው ተወዳዳሪ ገባ፡፡ «ቀላል ጥያቄ ነው የምጠይቅህ» አሉት ሰውዬው፡፡
«ሁለት እና ሁለት ስንት ነው»
ተወዳዳሪው ገርሞት እየሳቀ «አራት» አላቸው፡፡
«አላለፍክም» ብለው አሰናበቱት፡፡
ሁለተኛው ገባ፡፡ የመጀመርያው የሆነውን ነግሮት ነበር፡፡
«ሁለት እና ሁለት ንት ነውአሉት
 «ሦስት» አላቸው፡፡
«አላለክም» ብለው ይሄንንም አሰናበቱት፡፡
ሦስተኛው ገባ
«ሁለት እና ሁለት ስንት ነው ትላለህአሉት ቀጣሪው
«አምስት» አላቸው፡፡
«አልመለስከውም» እርሱም ተሰናበተ፡፡
በመጨረሻ አራተኛው ገባ፡፡
«ሁለት እና ሁለት ስንት ነው ተመሳሳይ ነበር ጥያቄው፡፡
«እርስዎ ስንት ቢሆን ይፈልጋሉ´ አላቸው፡፡ ተደንቀው ዓይን ዓይኑን አዩትና «የምፈልገው እንዳንተ ዓይነት ባለሞያ ነው» ብለው ቀጠሩት ይባላል፡፡

50 comments:

 1. ጥሩ እይታ ነው!

  ReplyDelete
 2. Dani

  I love this article. Write more in this kind of issues, who knows Melese may also read it and turn his heart. You know small drop of water can break stone. By the way I love working with challenging people, I am doing that. I am more productive.

  ReplyDelete
 3. እውነት ለመናገር ይሔ የጽንፈኝነት ባህል ካልተለወጠ በስተቀር ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ያለ መሪ በቅርብ ርቀት ይመጣል ብሎ መጠበቅ በጣም ከባድ ይመስለኛል- በተለይ ሀገር በመምራት ደረጃ፡፡ ምክንያቱም የባህል ጠበብት እንደሚሉት ባህል የአእምሮ ሶፍትዌር ነው፡፡ ይህ የአእምሯችን ሶፍት ዌር የሆነው ባህላችን ደግሞ በጥሞና ስናጤነው አስደንጋጭ ጽንፈኝነትን በይምሰል ትሕትናና መልመጥመጥ ሸፍኖ ይዞ የሚገኝ ይመስላል፡፡ አብዛኞቻችን በአካባቢያችን ያሉትን ሰዎች በሁለት መንገድ ብቻ የምንመለከት ሆነን እንስተዋላለን፡፡ ነገሮች ወይ ጥቁር ናቸው አልያም ነጭ ናቸው፡፡ እኛን ያልሆነ ሁሉ ደግሞ ጠላታችን ነው፡፡ “ጠርጥር ከገንፎም ይገኛል ስንጥር፡፡ ያመኑት ፈረስ ጣለ በደንደስ፡፡ ከራስ በላይ ነፋስ፡፡” ወዘተ. የሚሉት የቋንቋችን ድቃቂዎችም ሆኑ የአነዋወር ዘይቤዎቻችን አለመተማመናችንንና እጅግ የጸነነ ራስ ወዳድነታችንን ሳይጠቁሙ አይቀሩም፡፡ (ለምሳሌ፡- ቤት ለመሥራት አጥሩ ላይ የምናፈሰውን ገንዘብ አስቡ፡፡ የአንዳንድ ቤት አጥር ዋጋ ከቤቱ ሳይበልጥ እንደማይቀር በቀላሉ መገመት ይቻላል፡፡ ሌላ ምሳሌ ደግሞ፡- በዓመት በዓል ጊዜ ለልጆቻቸው ልብሶችን የሚሸምቱ ወላጆችን አድምጡልኝማ- “ልጆቼ ከጎረቤት እንዳያንሱ” ሲሉ ትሰሟቸዋላችሁ፡፡ ታዲያ ይህን እየሰማ ያደገ ልጅ በአካባቢው ያሉትን ሰዎች ሁሉ እንደ ጥብቅ ተፎካካሪዎቹ ቢመለከትና ተፎካካሪዎቹን ለማደባየት መወሰድ እንዳለበት ያመነውን እርምጃ ሁሉ ቢወስድ ምን ይገርማል?)
  ይልቁንስ የሚገርመው ነገር “ሃይማኖተኛ ሕዝብ ነን፡፡” እያልን ራሳችንን የምንሸነግልበት የማንቆለጳጰሻ ዐረፍተ ነገራችንን ሁሌም በአጽንዖት ለመናገር ጥቡዐን መሆናችን ነው፡፡ ለድፍረቴ ይቅርታ ይደረግልኝና አንዳንዴ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አማናዊ ክርስቲያኖች ይልቅ የተገነቡት አብያተ ክርስቲያን በቁጥር እንደሚበልጡ አስባለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የኢስላም (ኢስላም ማለት ራስን ለአምላክ መስጠት ማለት እንደሆነ ሊቃውንቱ ያስተምራሉ፡፡) ተከታዮች ይልቅም የመስጊዶቹ ቁጥር ሳይልቅ እንደማይቀር እጠረጥራለሁ፡፡ ለምን? ብላችሁ ብትጠይቁኝ መልሴ “አካባቢያችሁን ተመልከቱና ከራሱ ጋርም ሆነ ከሌሎች ጋር በሰላም የሚኖር ሰው ፈልጉ፡፡” የሚል ይሆናል፡፡ እኔ የአእምሮ ሰላም የሌለውና ለሌሎችም የአእምሮ ሰላም የማይሰጥ ሰው የሃይማኖት ድርጅት አባል እንጂ “መንፈሳዊ ሰው” ብዬ ለመጥራት እቸገራለሁ፡፡

  አንዳንድ ያልተረጋገጡ የውስጥ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ “ከእኛ ጋር ያልሆነ ሁሉ ከአሸባሪዎች ጋር ነው፡፡” የሚለውን ዐረፍተነገር በቀጥታ ከ9/11 ጥቃት በኋላ የተናገረው ከኢትዮጵያ ተልኮለት ነው ይባላል፡፡

  ReplyDelete
 4. hay dani,thank u!!! ሰው ራሱ «የባላንጣዎች ደርግ» ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. dani, please let us know what is going on in silte zone, where St. Arsema Church is burnt. What is been done so far to solve the problem? How is the reaction of our fathers on the situation????
  Please please give us some info
  Thanks

  ReplyDelete
 6. Dear Daniel,

  What a nice insight is this? One thing the we should consider is that, if we have a yes man surrounding us, we are starting the way step down. There is Amahric saying that entails two is better than one. This means idea must be differ each other, the sum of this difference will brought a synergistic end.
  ለሀገር የማይጠቅም ሃሳብ የለም፡፡ ግን ብቻውን ለሀገር የሚጠቅምም ሃሳብ የለም፡፡ ማንኛውም ሃሳብ የሰዎች ሃሳብ ነው፡፡ የሰዎች ሃሳብ ደግሞ ውሱንነት አለበት፡፡ በዚህ ዓለም አንድ እና ብቸኛ መፍትሔ የለም፡፡ ከሌሎች የተሻለ መፍትሔ ግን ሊኖር ይችላል፡፡ ያ መፍትሔ ከሌሎች የተሻለ ነው ማለት ግን ብቻውን ፍጹም ነው ማለት አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 7. Dear Dani,

  What wonderful Opinion !! I love it.I wish to my country to get a leader us Abrham linken.

  Be blessed.

  Feker-Alem
  From Joburg

  ReplyDelete
 8. ቡና የለም እንጅ ቡናማ ቢኖር ውይ ሀገር ወይ ህገር..... ብለው እንደዘፈኑት ነው ነገሩ ዳኒ!እንዲህማ የኛወቹ ሰዎች ስልጣናቸውን ቢያካፍሉ ጥሩ ነበር!ህገራችን ውስጥ ስልጣን ለመያዝ ደም ተፋሶ መሆን አለበት ከተባለ እኮ ብዙ ቆየ!እንጅማ ዶ/ር ብርሃኑ የኢኮኖሚ ሚንስተር፣ፕ/ር መራራ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር፣ፕ/ር ጴጥሮስ የግብርና ሚንስተር፣ወ/ሪት ብርቱካን ፍትህ ሚንስተር፣ አቶ ሌንጮ ለታ መከላከያ ሚንስተር.....ሆነው ሀገርን ቢያገለግሉ መልካም ነበር። እስኪ ይህን ሆኖ እንድናየው የደነደነውን የፈረኦንን ልብ "እለቃለሁ" ያስባለው የሰራዊት ጌታ ቅዱስ እ/ር ይርዳን! እ/ር ሀገራችን በቃሽ ይበላት! ምነው እመብርሀን አዛኝቱ ኢትጵያዮን ጨከንሽባት እስከመቸ መቀነትሽን ታጠብቂባት..አቡነ ጴጥሮስ በዚያች ጭንቅ ሰዕት አሉ ብሎ ሎሬት ጸጋዬ እንደተቀኘው። እ/ር ሆይ! የቃልኪዳንህ ጠባቂዎች እኛ ልጆችህ በፖለቲከኞች አለመግባባት ስንቱ መከራና ስደት እንደደረሰብን እስኪ ተመልከት!ቀንበራችን እንዴት እንደጠበቀብን እስኪ እይልን!"ከአሁን በኋላ ዛሬ የምታዩትን የችግር ደርግ ለዘለዓለሙ አታዩትም" እንሆ ብለን! አሜን!

  ReplyDelete
 9. very interesting idea that we ethiopians have to develop where ever we are...actually the closing story that you brought from the company owner so that he will be able to fined a person who works what he is going to tell him only is not much stated and connected with the idea that you brought... what ever the case what we majority of ethiopians lost as i understand is also to work and accept others who can challenge us...
  in my case i am not much happy to work with others though i know there potential is better than me... so i tried in my little power to develop such important quality or habit... to continue and develop such an important character that we have to have the story that you brought can support much for me too... tank you daniel it is wonderful to read such things... our country, chourch, organizations, buziness and poletics do not only belonged to a certanin group...and at the same time we have to be much strong on keeping our own personal self confidence while letting others to work with us even if we know they do have better potential in some area. Yes abrham linkon can be good example who practice it without fearing others potential... we are not absolute in any conditions but we will be better to become near to the reality if we develop working together without ignoring the so called people whom we considr them as "weeks"…
  a priest of our church who is living in europ and studyng in one of catholic university have experience to teach others I mean his class meet students and instructors who appreaciat a student who come up with new idea thay they never heard before…many may have some loose of information and may not know completely what we have as much as we know... so that he told us for what you know you are a teacher even if you are a student and for what you don't know you are a student even if you have got a chance to be a proffessor... i agree and i appreaciate if we all readers of this blog develop such habits even in our comments before we start to comment on the issues we don't agree we can build others. Don’t you agree???...
  we are created beings by God haveing equall access and right for this world so if we dream to have better world that have a better church of Creator and social life… we have to know and let others practice the valuable thing that they can contribute for our strugle of keeping the world and us safe in general us God command Keep and cultivate the world and ...
  thanks again daieil

  ReplyDelete
 10. Very nice daniel. Thank u and one who commented about our culture. I always hope that we shall over come our worst social crisis when we openly discuss our defects in public from z bottom of our hearts.

  ReplyDelete
 11. ዮናስ ዘለንደንDecember 20, 2011 at 9:38 PM

  በላነው ጠጣነው ከእንጀራው ከወጡ
  እግዚአብሔር ይስዝልኝ ከመሶብ አይጡ!

  እኔስ የበላሁትን እናገራለሁ የት ሀገር ይሆን በነጻ ምግብ የሚበላው?
  እኔስ የበላሁትን እናገራለሁ ሰማያዊ ምግብ በነጻ ነውና
  እኔስ የበላሁትን እናገራለሁ፦

  ሁለቱ ቀሊል ሆነው ወደላይ ሲንጠለጠሉ፣ ሁለቱ ከቢድ ሆነው ወደታች ይመዝናሉ፡፡ ሁለቱ ከቢድ ሆነው ወደታች ስበው እንጦሮጦስ እንዳይከቱ፣ ሁለቱ ቀሊል ሆነው ወደ ላይ ይስባሉ፡፡

  ReplyDelete
 12. Thank you Dn. Dani.
  It is good look. This is what st. Paul said in his epistle to the Corinthians. Different parts of the body function one body in different ways. The eye, the ear, the hands, the feet, all have different functions. But they never conflict with each other, instead they cooprate. In the same way each nation and nationalities, parties, organozations, communities, though they have different ways of understanding outlooks and objectives, if we accept, hear, and tolerate with them we will build our country. It is known that no body is full, and he /she has to take what he/she lucks from the others and then he/she will become full.Though our leaders tell us that their agenda is the perfect and last option, one party or ethnic group, or leader never presents such a perfect development program. Instead of this let us think and work according o our saying; "Dir biyabir anbesa yasir".

  ReplyDelete
 13. እንደ ሊንከን ዓይነት በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ከሚበልጧቸው እና ከሚቀናቀኗቸውም ጋር ለመሥራት ዐቅሙ ያላቸው፤ የራሳቸውን ክብር ሳይሆን የሀገርን ጥቅም የሚያዩ ሰዎች እንደ ጅራታም ኮከብ ከዘመናት አንዴ ብቅ ሲሉ ነው የሚታዩት፡፡

  Mamush,MN

  ReplyDelete
 14. ዲሞክራሲ,ፍትህ,ፍቅር,አንድነት,ብልጽግና, አኩልነት,....These are our common need. Let us focus on these & other common things
  God Bless Ethiopia!
  Dani Ewedihalehu...God Bless You!

  ReplyDelete
 15. ገር ከአጣብቂኝ ወጥታ አብዛኛውን ሕዝብ ወደሚያግባባ እና ወደሚያስተባብር ጎዳና እንድትሻገር፣ ክርክሩ ለጠብ እና ለመለያየት መሆኑ ቀርቶ እንደ ቢላዋ ስለት ተፋጭቶ አንድ ነገር ለመቁረጥ እንዲውል ለማድረግ ከተፈለገ ሀገር በባላንጣዎች ደርግ መመራት አለባት፡፡
  Mamush

  ReplyDelete
 16. ዲያቆን ያነሳህው ጉዳይ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በእጅጉ የሚሄድ ነው፡፡ሀገራችን መቼ ይሆን እንደ አብርሀም ሊንከን ያለ መሪ የምታገኘው? ስለ እውነት መርተውን ስለ እውነት የሚያልፉ ፣ ቂምና ጥላቻን አስወግደው ፍቅርን የሚሰብኩ፣ መቻቻልን በህይወት ተሞክራቸው የሚያሳዩን----- እንጃብቻ ብዙ ነገሮችን ስናያቸው በሀገራችን ችግሮች በዝተው ይታዩኛል ፖለቲከኞች አይቻቻሉ ፣የሀይማኖት አባቶች አይቻቻሉ፣ ታላቅ እና ታናሽ አይቻቻሉ፣ ቤተሰብ አይቻቻል፣ ከብዙ ባህላችን ውስጥ መቻቻል ከጠፋች ሰነበተች አምላክ ልቡና ያድለንና፡፡ ከምንም በላይ ግን እኔ ብቻ አውቃለሁ አውቅላችኃለሁ ከሚል እንደ ዘመኑ ካለ መሪ ይሰውረን፡፡እኔ ይህን ቁጣ እንጂ እውቀት አልለውም፡፡ ድሮስ መሪ ከእግዚአብሄር ሲቀባ እንጂ በሀይል እና ተፅዕኖ ሲሆን ውጤት አያመጣም፡፡ ሰላመ እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 17. It is a nice idea. However, this has to be started from yourself, buddy. You don't like people who comment challenging ideas on your blog. If you really believe in this very true truth, you shouldn't censor anyone's opinion before you post them on here so that all can contribute something different.
  I am just saying!

  ReplyDelete
 18. እግዜር ይስጥልን ዳኒ ስለ አብርሃም ሊንከንስ ይሄን ያህል አወቅን ስለኛዎቹ መሪዎችስ ተስማምተን እገሌ ይሄን መልካም አድርጎ አለፈ የምንልበት ዘመን መች ይሆን

  ReplyDelete
 19. good man with good idea

  ReplyDelete
 20. Your wish is good.It is very difficult to apply the principle here in Ethiopia where a mono party is a decision maker. The future of our country is gloomy!!

  ReplyDelete
 21. እኔ ምለው ለምንድነው መሪዎቻችን እንደዚህ የምትጫወቱብን ? ከአብረሀም ሊንከን ትንሽ ተማሩ እንጂ ፍትህን፣ መልካም አስተዳደርን( እናንተ ምትሏት የፌኳን አይደለም) ተቻችሎ አገር ማቅናትን፣ ለትውልድ ታሪክ ማስተላለፍን------- አረ ስንቱ ይዘረዘራል--ብቻ እናንተ ቅን --ቅን---ቅኖች ሁኑ እንጂ ሌላው ሁሉ እንደ አብረሀም ሊንከን በአስተዋይነት እና ‘በኮንፊደንስ’ ትወጡት ነበር፡፡ለመሪዎቻችን ልብ ይስጥልን እኛንም ከእንቅልፋችን ያንቃን፡፡

  ReplyDelete
 22. ዘ ሐመረ ኖህDecember 21, 2011 at 3:03 PM

  ዳኒ ይሄ እንኳን ቤተ መንግስት ቤተክህነትም አይገኝ እንኳን የፖለቲካ መሪዎች ጋር ይቅርና የሃይማኖት መሪዎች ጋር አይገኝም የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ያንተ ጽሑፍ ብቻ በቂ ነበር በርታ ዳኒ እግዚአብሔር ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 23. i have read the same story written by u.but am glad u write this one because this is based on a true story of a leader of a successful nation.now i would like to point out the only and major difference between the committee of Lincoln and the committee that could exist in Ethiopia.that is Lincoln and the people around him agree on one important thing,that is the constitution of USA is undisputed word of the nation written by the so called founding fathers.here in Ethiopia every new comer or the one who wants to be come as new dreams to be the founding father of a nation there is no common ground to play.
  My hope is the idea of opposing should come from with in the one in power,so that we can see Jefferson and Hamilton,individuals who has a common ground but different strategy.in other words eprdf needs to be split in to two.or the opposition parties needs to accept the founding fatherhood which seems to exist.

  ReplyDelete
 24. ዲያቆን ዳንኤል ግሩም አርዕስት፤ ድንቅ ቁምነገር ያዘለ ጉዳይ አቀረብክልን እ/ር ይመስገን በአንተ አንደበት አድሮ በጎ አስተሳሰብ አነበብን አሁንም በየትኛውም ደረጃ ላሉ መሪዎቻችን ይህ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲሰርፅባቸው ልቡና ይስጣቸው
  ይጋርዱ አማረ
  Dec.31/2011

  ReplyDelete
 25. ሰላም ዳኒ ጥሩ ብለሃል በዚህ አጋጣሚ አስተያየት መስጠት የምፈልገው አስተያየት የምትሰጡት ላይ ነው፡፡ ዳንኤል የተናገረውን ቃል ደግማችሁ ትጽፎታላች በጣም ያናድዳል ትርጉሙ ምን እንደሆነ አልገባኝም ስንት ነገር መፃፍ ሲገባ ያንኑ ቃል መድገም ምን ማለት ነው፡፡ ስላል ገባኝ ነው አስረዱኝ

  ReplyDelete
 26. የአልባኒያን ኮሚኒዝም ያለቀቃቸው መሪዎቻችን በዴሞክራሲ ስም የነ ሰሜን ኮሪያ አይነት ከአምልኮ ያልተናነሰ ቀንበር ከጫኑብን ውለው ሰንብተዋል፡፡ እነሱ የሚታያቸው ቀን ከሌት በዛ መከረኛ ቴሌቪዝናቸው ጠመንጃ አዝሎ የሚሮጥ ጦረኛ /ከተገባው/ እያሳዩን ያፈሰሱትን ደም የተቀበሉትን መስዋዕትነት እየተረኩልን ミነገር ግን የገደሉት ወገናቸው እንደነበረ እንኳ ትዝ የማይላቸው እነርሱ ብቻ ጀግኖች፡፡ እነሱ ብቻ ለሃገር አሳቢዎች፡፡ ለየት ያለ አስተሳሰብ ያለው ከተገኘ ፀረ ምናምን የሚል ቅጥያ እያበጁ የሚለጥፉ፡፡ 20 ዓመታትን ሙሉ ያለፈ ታሪክ እያነሱ መነዝነዝ የማይታክታቸው፡፡ ደርግ እነዲህ አድርጎ ንጉሱ ወድያ ሄደው… ለሀገሪቱ እነሱ ብቻ የተፈጠሩላት የመሰላቸው የወንበር ጥም ያልቆረጠላቸው ሆዳሞች፡፡ ከተቻለ ዳኒ ካለም ፈልግና የ አብርሃም ሊንከንን ጠበል አስመጥተህ በካህን ብታስረጭልን ይለቁን ይሆናል አለዚያማ Demo-communism’ን create ያደርጉልንና እናርፈዋለን ፡፡ ሲሞቱ በኮሪያንኛ እናለቅስላችው ይሆናል … ዳኒ ረጅም እድሜ ላንተ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 27. በአሜሪካ ታሪክ እንደ "አይከን" ከሚታዩ መሪዎች አንዱ ነው አብርሃም ሊንከን፡፡

  ምነው አንተም ጉራማይሌው አማረህ እንዴ

  ReplyDelete
 28. ዳኒ ያነሳኻው ሃሳብ በጣም ትልቅ ነው ፡፡ በእውነት ጸጋውን ያብዛልህ፡፡ እኔ ሁሌ የሚገርመኝ አኛ ሃገር ውስጥ ከመለስኣ አስተሳሰብ ውጪ ማሰብም ሆነ ሃሳብን ማራምድ ከወንጀልም በላይ ኃጥያት ነው ካንድ ግለሰብ አስተሳሰብ የወጣውን ሲፈልግ አሸበሪ፤ ኪራይ ሰብሳቢ፤ የአመለካከት ችግር እያሉ የተለያዩ አሰተሳስቦች ተነስተውና ዳብረው ለሀብረተሰባችን አና ለሃገር ጠቃሚ ነገር እንዳይሰራ ሆነኮ በተለይ የአመለካከት ችግር የሚባለው አኔ ትርጉሙ አልገባኝም የግድ አንድ አይነት አስተሳስብ ካልተያዘ የአመለካከት ችግር ነው ብቻ እግዚሐብሔር ይህችን ምስኪን ሃገር ይጠብቃት እንጂ እኔ ይቅርታ ይደረግልኝና አፍሪካ አንደ አብርሃም ሊንከን አይነት መሪ መጠበቅ ይከብደኛል፡፡

  ReplyDelete
 29. I wants to tell you guys stand up together unite her in localy letus dosomething together for ethiopia ethiopia ertirian eko end hager yemikebl tiwlid eyemetanew yetinantun abronet tarik silatefut ....bewkete

  ReplyDelete
 30. ዮናስ ዘለንደንDecember 21, 2011 at 11:27 PM

  This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 31. Dani thanks a lot with all your doings

  ReplyDelete
 32. Dani it was nice view

  ReplyDelete
 33. Dani,

  Thanks Dani for your well articulated piece.
  Just as a minor correction,Abrham Lincon was from Republican party.He was not democrat by the time when he run for the president.

  Addis

  ReplyDelete
 34. እኔም የ melaን ሃሳብ እጋራለሁ፡፡ ነገር መደጋገም በጣም ያስጠላል፡፡ አንድ ጊዜ የተጻፈውን ሃሳብ መስጫው ላይም ያንኑ መድገም ምን ለማለት ተፈልጐ ነው? በበኩሌ በጣም አሰልቺ እና ትርጉም አልባ ነው፡፡ ጊዜ እና ቦታን በአግባቡ እንጠቀም እንጅ ጐበዝ !!!!

  ReplyDelete
 35. ዳኒ እናመሰግናለን፡፡ በዚህ ድንቅ ጽሑፍህ ካሳየኸን ከአብርሃም ሊንከን የአመራር ስልት ጋር የዛሬው የኛ ሁኔታ ሲነጻጸር መቶ በመቶ ተቃራኒ መሆኑ ቁልጭ ብሎ ነው የታየኝ፡፡ በሕዝቡ ላይ የሚካሄደው የስነልቡና ውጊያ አደለም በተግባር ለመቃወም ስለተቃውሞ ለማሰብ ራሱ እንዲፈራና እንዲሳቀቅ የሚያደርግ ነው፡፡ በሌሎች የሚደርስ ቅጣትና እስራት፣ በየመድረኩ ከየመሪዎቹ የሚሰነዘሩ ሃይለቃላት፣ የባለስልጣናት መግለጫዎች፣ የሚዲያዎች የዘመቻ ዜናዎች ፕሮግራሞችና ጥናታዊ ፊልሞች ሁሉ ትውልዱን የራሱ ሃሳብ የለሌለው፣ እንደ ፓሮት ያሉትን የሚደግም፣ የጋቱትን የሚያቀረሽ ሙትና ተቀባይ ብቻ እያደረገው ነው፡፡

  ReplyDelete
 36. በጽሑፉ ውስጥ ያሉ አባባሎችን መድገም ምን ያስፈልጋል ለሚሉ እኔ ምላሽ አለኝ፡፡ የምመልሰው እንደራሴ ስሜትና አመለካከት መሆኑ በቅድሚያ ይታወቅልኝ፡፡ የዳኒ ጽሑፎች በባህሪያቸው ሰርስረው የሚገቡ፣ አንጀት የሚያርሱ፣ በልብ ውስጥ ሲጉላላ የነበረ ሃሳብን ወርቅ አድርገው የሚገልጹ፣ ንባቡ ካለቀ ከረጅም ጊዜ ቦሃላ እንኳን በሃሳብ እንደዘፈን አዝማች ተቀርጸው የሚቀሩ አባባሎችና አረፍተ ነገሮችን የያዘ ነው፡፡ አስተያየት ሰጭዎች ሌላ ነገር ከመዘብዘብ የተሻለ አንጀታቸውን ራስ ያደረገውን ዐረፍተ ነገር መጻፍ ስሜታቸውን በትክክልና በአጭሩ የሚገልጽላቸው ስለሚመስላቸው የሚጠቀሙበት ይመስለኛል፡፡ እኔ ሲመስለኝ ምክንያቱ ይኸው ነው ክፋቱም አልታየኝም፡፡

  ReplyDelete
 37. Dn. daneil beewnet yasdesetegne tsihuf neew . engdi yebelete lemesrat yabkah

  ReplyDelete
 38. Thank you for letting me know what "Derge" is ....Commitee..i have been hearing this word for the last 22 years.....

  ReplyDelete
 39. It is good, but what is with the employer...is right?
  I don,t understand the last part.

  ReplyDelete
 40. Dani I wish you write about current event of Ethiopia and the destitute people of the country.
  Abraham Lincoln was indeed a great man for all humanity. He stood firm for the cause that was impossible to call at his time. Whereas here in our country, people eat from the garbage cane, drink the most contaminated water by the Alamudin mess, and live under bridge, and still the affluent intellectual and the so-called down to earth religious convict write polemic just like you’re doing.
  You could also write about St. Abune Petros, and St. Abune Michael, how they lost their dearest life for the people, the country, and belief.
  As far as I am concerned you and the organization you belong stood with the killers of this country. You still be friend with those murderers, and criminals. Never wrote a piece on current condition of the country, and the poor people of ours. You still believe Paulos is the patriarch of our church etc.
  I wish leave this kind of write-ups for the historians of the other nation and focus on your conviction. You know what you wrote last summer? “በታሪክ ላይ መተኛት” who you were trying to make happy if not these ethno-fascist woyane? You even not regret after pointed out by others in different forums and circles. I just like to say good to be a good writer, but that would be in words if it is not serving the good cause.

  ReplyDelete
 41. As a matter of fact when we see human nature its relay very difficult to determine the physiological and cosmological beahivours,but the point is ,its really good to be easy going for other with-in a certain limits....even Jesus said for us dont seek other faults,just seek peace and do a fruitful did....

  ReplyDelete
 42. Dn.. daniel kalehiwot yasemalin yageleglot zemenhinen yibarkilin.

  wow I have never ever heared such wonderful views in my life keep it up. god bless you...
  ጀግና መሪ ማለት ከእርሱ ከሚበልጡም ሆነ ከእርሱ ከሚያንሱ፣ ብሎም ከእርሱ ከሚስተካከሉ ሰዎች ጋር መሥራት የሚችል መሪ ነው፡፡ ጀግና መሪ ማለት እንዳልከው ይሁንልን ከሚሉት ሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ያልከውን አልተቀበ ልነውም፣ እኛ ደግሞ በዚህ እና በዚያ መንገድ አይተነዋል ከሚሉት ተቀናቃኞቹ ጋር መሥራት የሚችል ነው፡፡

  ReplyDelete
 43. berta Danie ende ayinetu sidetegn anbibo yemilewutew yelem yaw ken eskiyalf ende feres sichan menor new 4 kilo akababi silemiyanebut EGZABHER libachewun arariros fidachin endiyabeka etseliyalehu

  ReplyDelete
 44. ሳሚ (ወ/ሚካኤል)January 3, 2012 at 6:58 PM

  ህህህህህህ....ዎይ ዳኒ መድሃኒት ሆንክብኝ እኮ.እያቃጠለ ከትኩሳት የሚያድን መድኃኒተ ጽሁፍ፡፡በይበልጥ 97 ከ100 አባላቱ የአንድ ፓርቲ ሰዎች በሆኑበት ፓርላማ ለሚተዳደር ኢትዮጲያዊ ኡኡ የሚያስብል ጽሁፍ ነው፡፡ዕግዚአብሄር ሙሴን ወደ ፈርኦን እየላከው ሳለ ነገር ግን ፈርኦን ሙሴን እንዳይሰማው እግዚአብሄር የፈርኦንን ልብ ያደነድን ነበር፡፡ይህም የጌታ ኀይል ለትውልድ ሁሉ እንዲነገር የኃይሉን ተአምራት እያበዛ ነበርና ነው፡፡ዳኒ የዚህ ትውልድ ሙሴ ነህና ፈርኦን ባይሰማህም እንኩዋን ዝም ብለህ ጩህ...አዶናይ ቀን አለውና ባንተ ምልከታ ውስጥ ሁነን እንጠብቀዋለን፡፡ ዐምላከ ተ/ሀይማኖት ይጠብቅህ!!!!ሣሚ (ወ/ሚካኤል ከሰመራ!)

  ReplyDelete
 45. ዳኒ እናመሰግናለን,«ፍጹም ለመሆን የተቃረበ»............ላንተ ልጠቀመው"«ፍጹም ለመሆን የተቃረብክ»"

  ReplyDelete
 46. ወይ ዳኒ ውስጤን በብሶት ሞላው ፍትህ በማጣትብሶት፣ በመልካም አስተዳደር እጦትብሶት፣ የወስጥን ሰሜት ለመተንፈስ አለመቻል ብሶት፣ አረ ስንቱን መፈትሄ የሌለው መብሰልሰል ለማንኛውም በጽሁፍህ ቀጥልበት፡፡ ምን አልባት አንድ ቀን የጨለመው ቀን በብርሃን ይሞላ ይሆናል !ምን አልባት

  ReplyDelete