click here for pdf
ትናንትና በአንድ የኤፍ ኤም ራድዮ የሚተላለፍ ፕሮግራም ታክሲ ውስጥ ሆኜ እየሰማሁ ነበር፡፡ «ጋዜጠኛው» ቀብሩ በትናንትናው ዕለት ስለተፈጸመ አርቲስት ተናገረና «rest in peace ብለናል» አለ፡፡ የአፍ ወለምታ ወይንም ልማድ ነው ብዬ ዝም አልኩ፡፡ አሁንም ስለ ሌላ ስለ ዐረፈ ሰው ተናገረና ያንኑ ደገመው፡፡ ይኼኔ ደነገጥኩ፡፡ ይኼ የኤፍ ኤም ሬዲዮ በአማርኛ ቋንቋ ለሕዝበ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ፕሮግራም ነው፡፡ አሁን «ነፍስ ይማር» የሚለው የአማርኛ ቃል የሚጠፋው ጋዜጠኛ እንዴት ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጉዳዮች ሊያነሣ የሚችለው? ወይስ
የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አናግሪያቸው
እንደሚለው የሠርግ ዘፈን እንግሊዝኛ ማወቅ የዕውቀት መለኪያ ነው? ለነገሩ እርሱ ምን ያድርግ «ቢሾፍቱ አውቶቡስ? ብሎ መጻፍ ሲቻል «ቢሾፍቱ ባስ» ብሎ ጽፎ በከተማዋ ውስጥ በኩራት በሚዞርባት ሀገር፣ «ልዩ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ስፔሻል ክትፎ» «ተራ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ኖርማል ክትፎ» ተብሎ የጉራጌ ክትፎ እንግሊዛዊ በሚሆንባት ሀገር «ነፍስ ይማር»ን አለማወቅ ነውር ላይሆን ይችላል፡፡
ይህንን እያሰላሰልኩ እነዚያኞቸ$ «good bye have a nice weekend´ ብለው ተሰናበቱንና ሌሎች ደግሞ መጡ፡፡ ስለ ውጭ ሀገር ዘፋኞች፣ የፊልም ተዋንያን፣ ፊልሞች እና ዘፈኖች እንደሚያወሩን፣ ስለ አንዳንዶቹም ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጡን ነገሩንና ለመሸጋገርያ ብለው የእንግሊዝኛ ዘፈን ጋበዙን፡፡
ይኼኔ ነው ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች የማን ናቸው? እያልኩ መጠየቅ የጀመርኩት፡፡ አንድ ዓይን ያላት በዐፈር አትጫወትም ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ ጥርስ የላት በዘነዘና ትነቀስ አማራት ብሎም ይጨምርበታል፡፡ ለራሳችን ኤፍ ኤም ሬዲዮ እና ስኳር እያጠረን ተቸግረናል፡፡ ከነዚሁም ቆርሰን ለፈረንጆቹ ከሰጠናቸው ምን ሊተርፈን ነው? ወይስ እነርሱ ለኛ ብድር እኛ ለእነርሱ ሬዲዮ ልንሰጣቸው ተስማምተናል፡፡
እስኪ በሞቴ ክፈቱ እና ስሙ፡፡ አሜሪካኖች ወይንም እንግሊዞች የሚያከብሩት በዓል ካለ ኤፍ ኤሙ በሙሉ የሚያወራው ስለ አከባበሩ ነው፡፡ የአድዋ በዓል ዕለት ብትሰሙ ግን የጣልያንኛ ዘፈን ተለቀቆ ታገኛላችሁ፡፡ ስለ ድል በዓል ምንም የማይል ሬዲዮ ስለ አሜሪካኖቹ የምስጋና ቀን እስኪበቃን ይነግረናል፡፡
እገሊት የተባለችው የአሜሪካ ዘፋኝ የምትበላው ባናና ነው፣ የምትጠጣው አፕል፣ ልብሷ ሚኒ ነው፣ ጫማዋ ቲዌንቲ ናይን ቁጥር፣ ቤቷ ማንሐተን ነው፣ አቧቷ ጄምስ እናቷ አና ትባላለች፡፡ ባለፈው ሰኞ ስፒች አደረገችና ኤ ሎት ኦፍ ፒኦፕል አደነቋት፡፡
አሁን ይኼ የአማርኛ ነው ወይስ የእንግሊዝኛ ፕሮግራም? ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚወራ ጠፋ? ጉዳይ ጠፋ?
ለመሆኑ ለምን ይሆን ኤፍ ኤሞቻችን ዲያስጶራ የሆኑት? ስገምተው አንድ አራት ምክንያቶች አያጣቸውም፡፡
የመጀመርያው ሀገርን የማወቅ ችግር ነው፡፡ የሀገሪቱን ባህል፣ እምነት፣ ቋንቋ እና ሃሳብ የማወቅ ችግር፡፡ እንጅ ነፍስ ይማር ጠፍቶት «ሬስት ኢን ፒስ» ማለት ከየት ይመጣል» በመገናኛ ብዙኃን የሚነገር ነገር ከልጅ እስከ ዐዋቂው የሚሰማው በመሆኑ የሀገርን ወግ፣ ባሕል እና ደረጃ መጠበቅ አለበት፡፡ አንዳንዴኮ ጠዋት የሚተላለፍ ፕሮግራም ላይ እንደምን ዋላችሁ» የሚል ሰላምታ ትሰማላችሁ፡፡ እንዴት ነው አንድ ሰው በእንደምን ዋላችሁ? በእንደምን አረፈዳችሁ?፣ በእንደምን አመሻችሁ? እና በእንደምን አደራችሁ መካከል ያለውን ልዩነት ሳያውቅ ጋዜጠኛ ለመሆን የቻለው? መቼም ይህቺ ሀገር መቀባት እንጂ መማር የማይጠቅምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ያለመዘጋጀት ነው፡፡ በባህላችን እነኳንስ ሰው ፊት ለሚቀርብ ነገር ለቤተሰብ ለሚቀርብም ነገር መጨነቅ መጠበብ ልማዳችን ነበር፡፡ በሃይማኖት ትምህርታችን እንኳን አዳምን ፈጣሪ ለምን ዓርብ ቀን ፈጠረው? ሲባል ሰማይን ከነግሡ ምድርን ከነ ግሣግሡ አዘጋጅቶ አስውቦ ሊያመጣው ስለወደደ ብለው ሊቆቻችን ይነግሩናል፡፡
አንዳንድ ጋዜጠኞቻችን ግን ስለ ፕሮግራማቸው ማሰብ የሚጀምሩት ማይክራፎኑን ሲይዙ ነው መሰል፡፡ አንድ ታላቅ ሰው አንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ቀርቦ የተናገረውን እዚህ ላይ ባነሣው እንዴት ጥሩ ነው፡፡ «እኔ የሚናገረውን የሚያውቅ ወይንም የሚያውቀውን ብቻ የሚናገር ሰው እወዳለሁ» ነበር ያለው፡፡ በዚህ ዘመን ሰዎችን እያባለገ ያለ አንድ ነገር አለ፡፡ ኢንተርኔት የሚባልÝÝ ዩ ትዩብ የሚባል «መጋኛ» አለ ክበበው ገዳ፡፡ ስለ አንድ ነገር በቀላሉ ለማግኘት ካሰብክ መጽሐፍ ሳታገላብጥ፣ ሊቃውንት ሳትጠይቅ፣ መስክ ሳትወርድ፣ የዓይን ምስክር ሳትሻ፣ ማሰብ ማሰላሰል ሳያስፈልግህ ጉግልን መጎርጎር ነው፡፡
በአብዛኛው ደግሞ የሀገራችን ጉዳይ በጉግል አይጎረጎርም፡፡ መረጃዎች ሁሉ ያሉት መስኩ ላይ ነው፡፡ መውጣት መውረድ፣ መሄድ መምጣት፣ መልፋት መድከም ይጠይቃሉ፡፡ መረጃው ያለው በጥሬው ነው፡፡ አዘጋጅቶ፣ አብስሎ፣ አጣፍጦ የሚያቀርበው ጋዜጠኛ ይጠይቃል፡፡ ይህ ደግሞ የበሰለ ቀርቦለት፣ የተጠመቀ ተቀድቶለት እየበላ ላደገ የኔ ብጤ ከባድ ነው፡፡ እናም ሳይወድ በግድ ወደ ኢንተርኔት ገብቶ ማን እንዳበሰለው የማይታወቅ መረጃ ጎልጉሎ ያጎርሰናል፡፡
ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ስለ ውጭ ሀገር ሰዎች እና ስለ ውጭ ሀገር ጉዳዮች ማውራት እና መዘገብ እንደ ነጻ መሬት ስለሚቆጠርም ነው፡፡ የውጭ ሀገር ሰዎች እና ጉዳዮች ነገር ከማን ኛውም ዓይነት የፖለቲካ አመለካከት ተጽዕኖ ነጻ ናቸው፡፡ እገሌን ደገፍክ ወይንም እገሌን ተቃወምክ አያሰኝም፡፡ አንዳንዴም እዚህ ሀገር የመንግሥት ያህል ዐቅም ያላቸው ቱባ ግለሰቦችም አሉ፡፡ እነዚህ ቱባ ግለሰቦች አስቀየመን ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ልክ ሊያስገቡ ይችላሉ ተብለው ይታማሉ፡፡
እናም ጎመን በጤና ለመብላት ሲባል ማንም የማይከራከርባቸውን የውጭ ሀገር ሰዎች እና ጉዳዮች ማቅረብ ለጋዜጠኞች ነጻ ቀጣና በመሆናቸው ሁሉም ወደ እነርሱ ሳይዘምት አይቀርም፡፡
አራተኛው ደግሞ በእንግሊዝኛ የማሰብ ችግር ነው፡፡ አንዳንድ ጋዜጠኞች በእንግሊዝኛ እያሰቡ ነው በአማርኛ መናገር የሚፈልጉት፡፡ በተለይም ይህ ችግር በስፖርት ጋዜጠኞች ይብሳል፡፡ ፍቅሩ ኪዳኔ የፒያሳ ልጅ በተሰኘው መጽሐፉ እነ ይድነቃቸው ተሰማ እግር ኳስን በኢትዮጵያ ሲያስፋፉ እና ሕጉን ሲያመጡ የአማርኛ ትርጉም ለማግኘት ይደክሙት የነበረውን ድካም ነግሮናል፡፡ እግር ኳስን በአማርኛ ለማቅረብ፡፡
ይህንን ያልሰሙ አንዳንድ ጋዜጠኞቻችን ግን ደብል ኳስ፣ ፓስ አደረገ፣ ሚድ ፊልድ ላይ የሚጫወተው፣ በራይት ዊንግ ያለው፣ ኮምፕሌት ፓስ ነው፣ ኳስ ኮንትሮል ማድረግ፣ የሚሉት ቃላት ሁሉ ሀገርኛ ትርጉም ጠፍቶላቸው ነው? አንዳንዴማ ምክንያቱም ማለት ተረስቶ «ቢኮዝ» የሚባልበትም ጊዜ አለ፡፡
እና ወዳጆቼ ዕጣ ፈንታችን ምን ሊሆን ነው፡፡ ኤፍ ኤሞቻችን በአብዛኛው ዳያስጶራ እየሆኑኮ ነው፡፡ ምሁሮቻችንን አጣን፣ ወጣቶቻችንን አጣን፣ ቅርሶቻችንን አጣን፡፡ ምነው በዚህ ቢበቃን፡፡ ደግሞ ኤፍ ኤሞቻችንን እንጣ እንዴ፡፡
እባካችሁ ኤፍ ኤሞቻችንን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የቀማችሁን ሰዎች ስለማርያም ብላችሁ መልሱልን፡፡ የሀገሬን ጉዳይ፣ የሀገሬን ሃሳብ፣ የሀገሬን ሰዎች፣ የሀገሬን ታሪክ፣ የሀገሬን ታዋቂ ሰዎች፣ የሀገሬን ዜማ፣ የሀገሬን መረጃ ልስማበት፡፡ እባካችሁ ኤፍ ኤሞቻችንን መልሱልን፡፡
ኢትዮጵያዊ ሊነገረው እንጂ ሊነገርለት አይችልም ያላችሁ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊሰማ እንጂ ሊሰማ( ሰ ይጠብቃል) አይገባም ብሎ የፈረደ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊታሰብለት እንጂ ሊያስብ አይችልም ያለ ማነው?
ኒውዮርክ ጎዳና ላይ መኪኖች ተጋጭተው መንገድ መዘጋቱ ምን ይፈይድልናል? እዚህ ሃያ ሁለት ተጨናንቆላችሁ የለም እንዴ? እገሊት የተባለቺው ዘፋኝ ሆሊውድ ውስጥ በሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ገብታ የአንድ ሺ ዶላር ራት በላች ብሎ ማውራት ድኻውን ከማስጎምጀት ያለፈ ጥቅሙ ምንድን ነው? እገሊት ከእገሌ ጋር በፍቅር ወደቀች፣ እነ እገሌ ሊጋቡ ነው፣ እገሊት ርጉዝ መሆንዋ ታወቀ፣ እገሌ ደግሞ አንድ ልጅ ከአፍሪካ በማደጎ ሊወስድ ነው እያሉ አዲስ አበባ ተቀምጦ እንግሊዝ እና ካሊፎርንያ ላይ መፎነን ምን የሚሉት አባዜ ነው፡፡
ኧረ ስለፈጠራችሁ ኤፍ ኤሞቻችንን መልሱልን፡፡ ያለበለዚያማ እዚህ ሀገር FM የሚለው ምሕፃረ ቃል ትርጉሙ foreign media ሊሆን እኮ ነው፡፡
እስኪ አንድ አቦ ሰጠኝ ግጥም ልስጥና የሀገሬ አዝማሪ ይቀበለኝ
ኤፍ ኤሜን ያያችሁ
አላየንም
ጋዜጠኞች እባካችሁ
አላየንም፡፡ አላየንም፡፡
© ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።
you r so write
ReplyDeleteኢትዮጵያዊ ሊነገረው እንጂ ሊነገርለት አይችልም ያላችሁ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊሰማ እንጂ ሊሰማ( ሰ ይጠብቃል) አይገባም ብሎ የፈረደ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊታሰብለት እንጂ ሊያስብ አይችልም ያለ ማነው?
ኤፍ ኤሞቻችን በአብዛኛው ዳያስጶራ እየሆኑኮ ነው፡፡
ReplyDeleteDERTOGADA BEWOXA MAGISTE EHETE TSHAFIW GAR(YISMAEKE)DEWLA DANIEL KIBRET NEH ALECH AYDELEWUM.AYE ENDIH AYNET NEGER LITSIF YEMICHIL ESU NEW BEYE NEW ALECHEW.YISMIAKEM BIZU DANIEL KIBRETOCH ENDALU ATRISH ALAT.GIN,GIN GIN BIZU DANIEL KIBRETOCH YELUM WUSHET NEW.
Dani you always see things quiet different ...!!! Thank you very much brother ! min tadergewaleh ahun ahun gazetegna lemohon mesfertu " limatawi " mehon bicha new alebelezia lehager dehninet sigat tihonaleh....
ReplyDeleteHATE FM ....., FULL OF YOUNG ,NON PROFFESIONAL,....ESTI YITAYIH AND BOTA LAY " WEDE HULET YEMITEGU FOKOCH YEMILU GAZETEGNOCH!
ohhh erererere dani chefechefklegn. good observation and critic.
ReplyDeleteያለበለዚያማ እዚህ ሀገር FM የሚለው ምሕፃረ ቃል ትርጉሙ foreign media ሊሆን እኮ ነው፡፡
ReplyDeleteመልካም እና አንድ እርምጃ ወደፊት ሊባል የሚገባው ስራ!
ReplyDeleteመቸም አንድ ሰው አስቦ አንድ በሬ ስቦ አይሆንም እንደሚባለው ባይሆንብኝ ዳኒ በነካ እጅህ በጻፈ ብዕርህ ለምን ስራዎችህ አንድ እርምጃ የሚሻገሩበትን መንገድ አትዘረጋም?አንድ መምህሬ ሲያስተምር እንዲህ ይል ነበር፡፡ከምድር ወገብ በታች ያሉ አገራት ብዙ ጊዜ ትኩረት የሚያደርጉት አንድ የተከሰትን ችግር ለመቅረፍ ስራ የሚሰሩት ችግሩ ላይ ነው፡፡ግን መሆን ያለበት የችግሩ መንስኤን ለይቶ ከዚያ ላይ ቢሰራ ነው ውጤታማ ሊያደርግ የሚችለው ይል ነበር፡፡እናም እንደተባለው አንተ ችግሩን ነገርከን፤እኛም አለ ብለን በሚያምር የጽሁፍ ጋጋታ ከቢሮው እስከ ሰፈሩ ምሳሌ እየሰጠን ብናልፍ ጠቀሜታው ቢበዛ ሊሆን የሚችለው ስለ ችግሩ እውቀት ብቻ ነው፡፡
ዳኒ ዘወትር የምታነሳቸው ጉዳዮች ይበል የሚያሰኙ ሲሆኑ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ቢባሉ ደግሞ ለእኛ አይደለም ለሌሎችም በጠቀሙ ነበር፡፡ ለምሳሌ ስለ ግብረ-ሰዶም አንድ ነገር አልከን፡፡ከሚዲያም እንደዚሁ ሰማንው፡፡እናም ዜና ሆኖ ቀረ፡፡ከዜና በኋላ ምን ተሰራ፤ምን ምን ነገሮች ያስፈልጉናል ይህን መሰል ጸያፍ ድርጊት ለማስወገድ---?የሚሉ ነገሮችን በማንሳት ውይይት እንዲደረግበት መንገዱ አልተመቻቸም፡፡እናም ዳኒ በጡመራ መድረክህ የውይይት አርዕስትን እያነሳህ ከፊሉ አስተያየት የሚሰጥበት፤ሌላው ጥናት የሚያደርግበት፤ሌላው ደግሞ ከስህተቱ የሚመለስበት ዘዴ ይፈጠር፡፡ብዙ ጊዜ ስለ አንድ ነገር ለማጥናት ሰዎች ሲነሱ ችግር ተደርጎ የሚወሰደው የመረጃ እጥረት ነው፡፡እናም አንተ የምታነሳቸው ምርጥ ማህበራዊ፤ሐይማኖታዊ፤ፖለቲካዊ(?)፤ኢኮኖሚያዊ--- አርዕስት በውይይት መልኩ ቢቀርቡ ሰው የሚሰጠውን መረጃ ተንተርሶ ለችግሮቹ መፍቻ ቁልፍ የሚሆን ጥናት ማጥናት ይቻላል፡፡
ጌታ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ!
ውብሸት ከባህር ዳር!
እባካችሁ ኤፍ ኤሞቻችንን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የቀማችሁን ሰዎች ስለማርያም ብላችሁ መልሱልን፡፡ የሀገሬን ጉዳይ፣ የሀገሬን ሃሳብ፣ የሀገሬን ሰዎች፣ የሀገሬን ታሪክ፣ የሀገሬን ታዋቂ ሰዎች፣ የሀገሬን ዜማ፣ የሀገሬን መረጃ ልስማበት፡፡ እባካችሁ ኤፍ ኤሞቻችንን መልሱልን!! መልሱልን!! መልሱልን!! መልሱልን!!
ReplyDeleteFirst of all its name is F.M. which is not Amharic.There fore,it becomes diaspora.We start from its name.Hasn't it Amharic translation for F.M.?Let us start from its name which leads them to be diaspora
ReplyDelete1. መቼም ይህቺ ሀገር መቀባት እንጂ መማር የማይጠቅምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡
ReplyDelete2. አዘጋጅቶ፣ አብስሎ፣ አጣፍጦ የሚያቀርበው ጋዜጠኛ ይጠይቃል፡፡ ይህ ደግሞ የበሰለ ቀርቦለት፣ የተጠመቀ ተቀድቶለት እየበላ ላደገ የኔ ብጤ ከባድ ነው፡፡
3. እገሊት የተባለቺው ዘፋኝ ሆሊውድ ውስጥ በሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ገብታ የአንድ ሺ ዶላር ራት በላች ብሎ ማውራት ድኻውን ከማስጎምጀት ያለፈ ጥቅሙ ምንድን ነው?
Wow! What a wonderful article. God may bless you Dani
ዲ/ዳንኤል እግዚአብሄር ይስጥልን ወደ እንግሊዙ ከተሰደዱት ወገኖች አንዱ ነኝ
ReplyDeleteወገን ምን ነካው?እኟም እንኳ በተሰደድንበት ቋንቋ እንዳይጠፉም አማርኟውን ከእንግሊዙ አፍ እንዳይቀላቅሉ ከልጀቻችን ጋር እንታገላለን ሀገር ቤት ደሞ ኤፍ ኤሞቻችን
የተገላቢጦሽ ካረጉት አማርኛ ሊያስተምር ወደጐንደር የሄደው የ እንትን ሀገር ሰው የተተረተበት እንዳይገጥማቸው። ታዲያ ይህን ስል እዚህ እኟም በተሰደድንበት አብዛኟው ወላጅ ለልጁ የራሱን ቋንቋ ከማስተማር ይልቅ በልጁ ቋንቋ ሲማርበት እየታየ ነው። ወይ ትክክለኛውን እንግሊዝኛ አላወራን ወይ የራሳችንን አልተናገርን፡ እኔንም አንዳንዴ ሰረቅ ያረገኛልና ነው እኛ እያልኩ የምለው እውነቱን ለመናገር በዚህ ጽሁፍ ብዙ ተምሬበታለው እግዚአብሄር ፀጋውን ያብዛልህ።
Thanks , Dani!
ReplyDeleteBut I don't think that you don't understand the purpose of establishing FM in Ethiopia today.It is one of the strategy in eradicating all what we have.
Dani betam des yemil ewnetegna neger new yethafkew melsunim eko thifehewal mereja betikikil yemiset yelem weyim yemigegnebet neger yelem beza lay 1 negerin weyim siran ketekawemk tekawami kedegefk degafi yemitibalibet hager lay endat sile hager yemiyawera yigegnal gin yihn yahlm mehadachew yanadidal. Melkam neger endigetmen metheley new Dani enamesegnalen.
ReplyDeleteወንድም ዳንኤል ፈጣሪ አብዝቶ ይስጥልኝ። ይህ ዛሬ የምትጽፈው የዛሬዋ ኢትዮጵያ አሳዛኝ ገጽታ ብቻ ሳይሆን ፣ ወደጠቆምኸው የመፍትሄ ሃሳብ አድራሽም ትልቅ ህልም ነው። መገናኛ ብዙሃንን እንዲህ እንዳንተ በሌላ መገናኛ ብዙሃን መተቸቱ ህዝብን ለማነጽ እንደሚጠቅም አሌ ባይባልም ፤ እንደመጣጥፍህ ሁሉ ፣ አንተም ባለህ ህዝባዊ ተቀባይነት ስም … እነዚህን “ጋዜጠኛ ” ተብየወች በግልህ ጊዜ ወስደህ በቡና እያዋዛህ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ለማነጽ ሞክር። ስህተቱን ከምንጩ ለማድረቅ።
ReplyDeleteሌላው ለማረሚያ ያህል ፣ “አራተኛው ደግሞ በእንግሊዝኛ የማሰብ ችግር ነው፡፡” ላልኸው ፣ የሰው ልጅ የሚያስበው በመጀመሪያው ቋንቋ እንደሆነ ነው ሳይንስ የሚያምን። ስለዚህ ፣ ሰዎች ከአማርኛ አድማጫቾቻቸው ጋር በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለመግባባት የሚጥሩት በእንግሊዝኛ አስበው ሳይሆን ፣ በአማርኛ አስበው አማርኛውን ወደ እንግሊዝኛ ተርጉመው ነው። የጭንቅላታችንን የማሰብ ፍጥነት መቸም ለአንተ መንገር አያምርብኝም። ለዚህ እሳቤየ ቀጥተኛ አጋዥ ሃሳቤ የአንተው መጣጥፍ ነው። ሰዎች “ስፔሻል ክትፎ” ብለው ለመጻፍ ያሰቡትን ፤ ስህተታቸው ሲገባቸውም መስረዝም በቻሉ ነበር። ግን መቸ አደረጉት?! ዛሬ ዛሬ የሚወጡት ተንቀሳቃሽ-ምስሎችስ ስያሚያቸው የእንግሊዝኛ አይደለ?! በመጨረሻም ፣ እንዴው የራስህ የሆነ የሬዲዮ ፕሮግራም ቢኖርህ ምናለበት? ወጭህን እንደሆነ እንድዚህ በአክብሮት የምንከታተልህ መሸፈን አያቅተን?
ሰላም
ከፍያለው
ዳኒ ዛሬ አለብላቢቶቹን ነካሀቸው.............. ልታስለበልበን ነው በቃ.....
ReplyDeleteI am from country side, I came to Addis Ababa four months before to upgrade my education, here in Addis there are many things which may be new for those who are from the states, for me too.But I was highly surprised by Addis Ababa youngsters language usage, especially, the females .with out exageration more than 50% of their amharic language is tied by English words.with my short time stay what I do understand is they believe as if it is the measure of smartness and modernization.Although I am not linguistic professional most of their words are not appropriate to express their idea.....In case if you were no hearing the following words I dont know, but I personally heard the following words thousand times a day:my God, I swear,what,shit, .....My point is we had better develop our language, proud on ourselves, we have plenty of words to express our ideas, Even bible is translated in to amharic, we are still colonized by the western, you may look at china's who are running in the best track using their own culture and language, ur good personality should be evalluated based on your fear to God, ........Dani thanks a lot for the Issue you raised....by the way I follow most of our FM radios but most of the reporters flen is more of to english rather than their mother tounge language.....thanks God bless Ethiopia
ReplyDeleteWow. This is so funny but so true!Ebziabhere ke'sega fetena Ke'mekera nefese yetebekieh. Amen
ReplyDelete ረቂቅ ምልከታ ዉብ አቀራረብ!
ReplyDeleteስለዚህ ጉዳይ ምን ይባላሉ ሀጌሬቱረን እያጠፉና ባህላችንን እየበረዙ ሰለመሆኑ ምን ያጠራጥራል ሰዉን እኮ እንድህ እነደኛ አውሩ ማለት ነዉ ማለቴ ለዛዉም በሬደዮችን ባይሆን የኛ ይበቃ አልነበር እንዴ ፈረንጅ አነከዋን አማርኛ ልማር ቢል እኮ ይስቅበናል ምክንያቱም ከገራመይሌችን እንጀሊዘኛ ሊያሰተምረን ይችላል! ምን አለበት ስራን ሀገረን ሀላፌናትን መያችንን ኢትዮጽያዊነታችንን ብናከብር ህዝባችንን በናከብር ከምንም ነገረ በላየ ደሞ ይትም የማይገኛዉን ማንነታችንን ባንበርዘዉ መጥፎ ልማድ እኮ ነዉ ዳኒ እሬዴዮ ላየ አሎጣም እንጄ ስንቶቻችንስ ልምዶብናል የሬድዮ ገን ይደብራል!
ReplyDeleteberavo
ReplyDeleteayee dani endiyaw dekem bileh new enji, aradenet,zemenawinet englizegna betenagere kehone koye eko. emaye ena abayes be ene mommy eyeteteku aydel. aye alemetadel.alemawek endehone biyawku teru neber.
ReplyDeleteእኔ የሚናገረውን የሚያውቅ ወይንም የሚያውቀውን ብቻ የሚናገር ሰው እወዳለሁ»
ReplyDeleteWEY DANY YE MIGEREEM TEZEBT NEW FM MENORU MELKAM HONO SALE NE GERE GEEN MESTEKAKEL YALEBET NEGER BEZU NEGER ALE I HOPE TIKOMAW YEDERSACHEWAL !!!
ReplyDeleteD MARYLAND
Thanks for raising the issue. I am also worried-where are we heading? are we ashamed of our language? In Addis, have u observed sign boards of shops,cafes, resturants, bldgs,schools etc., written in English? I always wonder why it is not written both in Amharic and Eng. if not only in Amharic. Who are our audiences/viewers? who is going to respect our language and pass to the next generation, if not us?! Please say sthg on this too.
ReplyDeleteEGZABHAR ybarkehe Dany ewnetken eko naw
ReplyDeleteእኔ እንደሚመስለኝ ይህ ሁሉ የሚያሳየው
ReplyDelete1)ጋዜጤኞቹና የሚዲያዎቹ ሃላፊዎች ለኣድማጮቻቸው አክብሮት እንደሌላቸው ነው
2)የትምህርት ሥርዓታችን ያልተጠናና በየመስኩ ብቁ ባለሙያ ለማፍራት የማይበቃ መሆኑ (በጋዜጠኝነት ብቻ የሚታይ ችግር አይደለም)
3)የትውልዱን በራሱ ባህልና ቋንቋ ያለመተማመን እና ተስፋ መቁረጥ
እስቲ አንተም ለሙያው ዕድገት የበኩልህን አስተዋጽኦ ለማድረግ ሞክር:: ለምሳሌ የራስህን ዝግጅቶች በማቅረብ ወይም የሥልጠና ተቋም በመመሥረት ሊሆን ይችላል::በርታ
እስቲ አንተም ለሙያው ዕድገት የበኩልህን አስተዋጽኦ ለማድረግ ሞክር:: ለምሳሌ የራስህን ዝግጅቶች በማቅረብ ወይም የሥልጠና ተቋም በመመሥረት ሊሆን ይችላል::በርታ
Deleteመቼም ይህቺ ሀገር መቀባት እንጂ መማር የማይጠቅምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡
ReplyDeleteውድ ዳኒ አሪፍ ምልከታ ነው።
ReplyDeleteዳኒ "ኢትዮጵያዊ ሊነገረው እንጂ ሊነገርለት አይችልም ያላችሁ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊሰማ እንጂ ሊሰማ( ሰ ይጠብቃል) አይገባም ብሎ የፈረደ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊታሰብለት እንጂ ሊያስብ አይችልም ያለ ማነው?" የሚለውን አንቀጽ ሳነብ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ምልከታዎችህ 'እኛ ኢትዮጵያውያን ስንባል...?'የሚል ቅሬታ አዘል መልእክት ይዘው ነበር የሚደርሱኝ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡
ReplyDeleteአክባሪ እህትህ፡፡
ይህን ጉዳይ ሁሉም ሊያጤነው ይገባል ጥሩ የሆነ ጽሁፍ ነው የምታቀርበው በርታ
ReplyDeleteSelam Dn Daniel,
ReplyDeletepls check the pdf format again. We can't access it from any computer.
Thank you and keep it up!
ማለፊያ..ስለ FM(frequency modulation)በዲን. ዳንኤልኛ ስለ Foreign Media የተነገረ ለጋዜጠኞች ቢሆንም ፍጻሜው ግን ለእያንዳንዳችን ነው።ጋዜጠኞች ማንን ይመስላሉ ቢባል እኛኑ ።ነጋዴ ገበያ ተኮር ነው... ሸቀጦችንም በሸማቹ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ እንደሚያቀርብ ጋዜጠኛውም የትውልዱን የቋንቋ ዘዬ ተከትሎ ቢፈስ ላያስደምም ይችላል።በርግጥ "መገናኛ ብዙሃን የማኅበረሰቡን እሴት ባሕል ቋንቋ የመጠበቅ የማሳወቅ የመሪነት ሚናውን ሊጫወትና አገራችን በራሷ ፍልስፍናና ቋንቋ ማደግ እንደምትችል መንገር እንዳለባቸው አምናለሁ... ያምናሉ እናምናለን...ለተግባራዊነቱ ወኔ ባይኖረንም።ይህን ሚና ካልተጫወቱ ለማዝናናቱና ለማፈረንጅማ ለቅኝ መገዛቱም የሚሉ አሉ በቅርቡ ደሞ ለግብረ ሰዶማዊነት(ይቅርታ ካጸነፍኩት) እነ 'አይፓድ' እነ 'ኢንተርኔት' እነ 'ዲሴቲቪ' እነ 'አምሽር'(አግዙኝ በትርጉም) መች ጠፉ ብዬ አጠናክረዋለሁ ።አገር በቀል ቋንቋን ዕውቀት ከአዲስ ነገር ነበር የምናገኘው የዛሬን አያድርገውና ሌላው ሸገርም እንዲሁ በአገርኛው ልሳን የአገርኛውን ጥበብ ዜማ ፍልስፍና ለመያዝና ለማስያዝ ይታትራል ማኅበረ ቅዱሳንም አገር በቀል ትውልድ ለመፍጠር ያደረገው ጥረት በከፊል የተሳካለት ይመስላል።ዲ.ን ዳንኤል እንደምትለን ሌሎቹ ምንአልባት አዲሱ ትውልድ ጠፋቶ ስላለ ጠፍተው አገኙት እንጂ የወሰዱብን አልመሰለኝም ።ያኛው ትውልድ አማርኛ ያወራ ነበር?የኔ ትውልድ ዝንቅ፣ ጅ/ዥንጉርጉር አዲሱ አማርኛ ጠፍቶ አንግሊዝኛ እንደሚያቀላጥፍ ነቢይነት አያሻውም በአገር ቤት ያሉ መዋዕለ ሕጻናትን ማየት በቂ ነው።የግእዝ መምህራችን መምህር ደሴ "ፊደል ስንቀንስ አብረን ቃላቱን ከዚያ ጽንሰሐሳብን ወይም እውቀቱን እናጠፋዋለን" ብሎ ከስድስት ኪሎ መካነ አይምሮ በ"ባለ አእምሮ" የተነሳውን ተግዳሮት አስመልክቶ የነገረንን አልረሳውም። ቋንቋውን እጥፍተን በአፍርንጅ የምንኮላተፈውን ኢትዮጵያውያን አገራችንን ለመውደዳችን መገለጫው ምንድነው? ተብለን ልንሞገት ይገባልና.. ዲ.ን በርታልን... ውቀሰን ይገባናል።ትችቱንም ወደነዋል።ብትሳለቅብንም ሊሰማን አይገባም ባይ ነኝ።በየጥጋ ጥጉ ግን ለመታረም እንዘጋጅ አንተንም ጨምሮ መርሐ ግብርን ፕሮግራም ላልከን። እንደመከራከሪያ እንግሊዝኛውን የማይገልጽ አማርኛ ነው ያለን ብለን ልናመካኝ እንችላለን። ከምንጩ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራ ለውጥ ይመጣል።ከችግሩ ወደመፍትሔው እንዙር። ግእዝ!!! ግእዝ!!! ግእዝ!!!። እሱ ሲመለስ የተወሰደው ይመለሳል የጠፋው ይገኛል የራቀው ይቀርባል። እንደበገናው ለማስነሳት ግእዙን በሁሉም ዘንድ ተደማጭ ተነባቢ ተነሽ ለማድረግ ለዓይኖቻችን መኝታ ለሽፋሽፍቶቼም እንቅልፍ ባንሰጥ እያልኩ ለእይታህ ያለኝን አድናቆትና ፍቅር ከሩቅ ምሥራቅ አቀርባለሁ(አድናቂህ ነኝ ከ...) እንዲሉ አዲሳባ።
ReplyDeletegera yegebaw tewelede . . .
ReplyDeleteD DaneilThank you berta Abune Abirham -Abune Fanueil bemalet medegefikin & mekawemkin titeh ahun melkam neger ametsah lehager tasbaleh lechurch tasbaleh lesew tasbalehimelkam sew neh bet papas ke papas tileyayalehi zereginet yimeslal Abune Abirhamn degifeh Abune Fanueiln tekawimeh tayitehal Huletunim tekebel wided emen astewl hulum yalfal yetemarik awaki sew neh bizu mastewal aleh yetesasatikew bezi bicha neber
ReplyDeleteይቅርታ ልጨምር ግእዝ በመስመር ላይን የወጠነ ወዳጅህ እንደሆነ ንገርልን ዘወጠንከ ፈጽም በልልን የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም ምነው ምነው እዘንባለሁ ብለህ ደመናውን አሳይተህ ጠፋህ ለማሳው አይገድህም ወይ በለው ቁልጭ ቁልጭ እያልን እንጠብቃለን ይላሉ በልና ንገረው ከባህር ማዶ በዝርው ላለነው ቋንቋ በመጎልጉል አይታሰስ ሆነብነ... መጦመሪያ ካለ በዚያ አስተምሩን እንጂ ይላሉ በልልን አደራህን።ጎሽ ...የው ደሞ
ReplyDeleteDani tigermalhi melkam eyeta new!
ReplyDeleteHey Dani, I agree on some of your points and i respectfully disagree on the others.
ReplyDeleteEven though i did not attend journalism class, I think each radio program has it's own targeted audience and from pure economic point of view there can be FM program which targets the younger part of the population and can use languages and programs which are attractive to its audience. I have a message for those of you who wrote as if speaking in amhaengl( Amharic with some English)is a sin, I bet all of you guys speak like the guys in the FM radio, but in our country it is easy to say than do.
Dn. Daniel, let God gives you health, wisdom....
ReplyDeleteDn.Daniel, it is not only our FM's who became Diaspora but also our brothers and sisters. They know neither about Ethiopia nor the westerns. Some times i ask my self are these guys Ethiopian's or..../ I thought behizib kotera tekotrewal/? Guys, if you are Ethiopian, whether you like it or not what you can be is Ethiopian/ Actually it is to be more than blessed/, what you doing other than this is pretending. I see a lot of Ethiopians here in US and in some places in Ethiopia, they are neither Africa American nor Ethiopian....'Rasachewin yatu'..'Egizihabiher rasachewin endiwiku yirdachew'. A lot has to be done to make our brothers and sisters to make them them selves/ rasachew indihonu/. It has to be started from academic education to different medias..... We are loosing our identity, great loss. what i personally believe is, Growth and development comes from individuals who knows them selves and got love for each other and for their country. A guy who knows about Adwa.....doesn't want to be others.' Endet mesirat biyakiten, ayatocahin yeteserawim mawirat yakitenal....?'Surprising negative growth for my mother land, those who did good things/our grand grand fathers/, those who only tell history very well/ majority our fathers/, those nether do nor tell history/ majority of this generation, it is really shame. let the Almighty God make us to tell and make good history for Ethiopia.
God bless the world and God bless Ethiopia!
Hailemariam, Chicago
…ቆርሰን ለፈረንጆቹ ከሰጠናቸው ምን ሊተርፈን ነው?
ReplyDeleteAM bicham aydelem: ETV, balesiltanochachin,…… Yihenin program yetignawus ferenj yisemawuna bileh new…..ayifech ayikola neger eko new!
ለምን ይሆን ኤፍ ኤሞቻችን ዲያስጶራ የሆኑት?
Ye diaspora megenagna bizuhanoch (DW, VOA….) betam yishalalu……endewum Dani enezih megenagnawoch yager betochun kale meteyik siyadergu kalat lemarem sitagelu yistewalal
5. Dani, ene amstegna lichemribet……midiawun ena siltanun yetekotaterut “ye arada” weyim “yechat” sefer tikit lijoch silehonum new. Yemigermew, enesu endih yemifolilut ena yenesun fulela yemiyadamitut tikit sewoch programu yeteseraw bemaygebachewuna bemayimeleketachew gibir kefay enat ena abatochachin mehonu new.
ዲያቆን ፅሁፍህ ወቅታዊና በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ኤፍኤሞቻችን የዘፈንና የስፖርት ወሬ ብቻ ማስተላለፊያ ከሆኑ ቆዩኮ ግን ግን እኔ የምለው ተቆጣጣሪ የላቸውም እንዴ ? ነው ወይስ ስለ መንግስትና ስለ ፖለቲካ ሲናገሩ ነው ዘራፍ የሚባለው፡፡አረ ተው ጎበዝ ትውልድ ይዳን በኛ ይብቃ መጪውን ትውልድ እንኳን ሀገር ተረካቢ እናድርገው፡፡ ስለ ጋዜጠኞቻችን ዕውቀት እኔም ትንሽ ልበል፡፡ ቀኑ የመስቀል በዓል ማግስት ነው ማታ 3 ሰዓት ከ20 አካባቢ የትላንትናው በዓል ምን ይመስላል እያሉ ሁለት ሴት ጋዜጠኞች ሲያወሩ አንዷ ማመን የሚከብድ ነገር ስትናገር ሰማዋት ምን አለች መሰላቹ ከፊቷ ሰፊው የመስቀል አደባባይ የበዓል ቦታ ይታያል እርሳም ሰፊውን ቦታ እያመለከተች አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ካህናት እዚህ ቦታ ላይ ወረብ ያቀርባሉ እስከዚያ ግን እዚያ ጋር እየተለማመዱ ነው አለች በጣቷ ወደ ሌላ ቦታ እያመለከተች፡፡በመጀመሪያ ጆሬየን ተጠራጠርኩት የሰማውት ነገር ዱብ ዕዳ በመሆኑ ከዚያ ወደ ቀልቤ ስመለስ ኢቲቪ ለኛ ለኢትዮጵያውያን እንደዚ ያለ አሳፋሪ ነገር ” እስከዚያ ግን እዚያ ጋር እየተለማመዱ ነው” የሚለውን ነገረን በኢቲቪ ተስፋ መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ተሸማቀቁ ታዲያ እነዚህ ጋዜጠኞች ናቸው መልዕክት ለትውልድ የሚያስተላልፉት ድንቄም ጋዜጠኛ ድንቄም ዕውቀት እቴ ሲሆን ሲሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ የአቋቋም ትምህርት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ መጠየቅ እንጂ አባቶቻችንን ” እስከዚያ ግን እዚያ ጋር እየተለማመዱ ነው” አይባሉም ስንት ተፈትነው ነጥረው የወጡ ናቸውና፡፡ በመጨረሻ ማለት የምፈልገው ኤፍኤሞቻችንን ብቻ ሳይሆን ማሠራጫ ጣቢያዎቻችንን በሙሉ መልሱልን ውድ የሆነ ባህላችንን፣ ሀይማኖታችንን፣ ማንነታችንን እንድናስተላልፍበት፡፡ ዲያቆን በርታ ሰላመ እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን፡፡
ReplyDeleteኤፍ ኤሜን ያያችሁ
ReplyDeleteአላየንም
ጋዜጠኞች እባካችሁ
አላየንም፡፡ አላየንም፡
Good comment, they need to read it.
እረ ይሄ ብቻ አይደለም የመስቀል በዓላችንም የጉራጌ በዓል ነው የሚመስለው፡፡ የጉራጌ የመስቀል በዓል አከባበር መልካም የሆነ እና የእነሱ የአከባበር መገለጫ እንጅ፣ የኦርቶዶክስ ሐይማኖትን የመስቀል በዓል እምነትም፣ ታሪክም አይገልጽም፡፡ ‹‹ እባካችሁ ኢቲቭ ›› ባህልንና ሀይማኖትን ለዩ፡፡
ReplyDeleteማሂ
We should be ourselves.
ReplyDelete“የብቃት፤በራስ የመተማመን፡አርቆየማስተዋል፤የብስለት” ማጣት ይሄ ሁሉ የFM ጋዜጠኞች ችግር ነው
ReplyDeleteእግዚአሔር ይስጥልኝ!
ReplyDeleteለነገሩማ መንግሥትስ ራሱ መች ስለባህልና ስለሕዝብ ማንነት (identity) ይገደዋል? የአዲስ ዓመት በዓላችን አከባበር ለየትኛው እንግሊዝኛ ተናጋሪ ነው ሲተረጎም የነበረው? ... ተዘርዝሮ አያልቅም።
እግዚአብሔር ይሁነን!
“ኤፍ ኤሜን ያያችሁ
ReplyDeleteአላየንም
ጋዜጠኞች እባካችሁ
አላየንም፡፡ አላየንም፡”
አላየንምማ ሊሉ አይችሉም፡፡ የእኛ ጆሮ መቀለጃ ነው እንዴ? አይታችኋል መልሱ መልሱ !!!!!!!!!
Really interesting!!!!!
ReplyDeleteThis is what I ask myself and I ashamed of. It is not the way to reflect our civilization by ignoring our identity. Some ignorant peoples acting like something.....but it is not the way, first you must have to respect yourself and then try to know the truth. Other ways those people will goes to the garbage. Let me give you one evidence what I have seen around megenagna, Addis, the gay around 55 year old waiting one oldish white ledy and she arrived,
whether she arrive on time or not nobody knows but he said that " this is the behavior of ferenge". You see, he was not speaking English perfectly but he lied-down himself easily.
ተባረክ። ጥሩ ታዝበሀል። እንደው የእኛ ነገር ጠራዝ ነጠቅ እየሆነ ተችገርን እንጂ። በነገራችን ላይ "ቢሾፍቱ አውቶቡስ" ቢባልም ያው የእኛ አይሆን። ምክንያቱም "አውቶ" በጀርመን አፍ "መኪና" ማለት ሲሆን "ቡስ" ደግሞ "ባስ" መሆኑ ነው። ስለዚህ ተስማምተን ዳቦ ቆርሰን "ለአውቶቡስ" ስም ማውጣት ይኖርብናል። አይመስልህም? እስኪ ምን እንበለው? ኧረ ለመሆኑ "መኪናስ" የአማራ አፍ ነው?
ReplyDeleteቸር ይቆየን
Dear Daniel,
ReplyDeleteOur languages had its own historical heritage, which we don't keep it up. Actually, we are in a hurry to loose our self, identity and image in all terms. Except few, I can say all mix English when they are talking. For that matter currently the bench mark to be consider as a modern one resemble talking by putting some English words as if our languages can not express our idea. If you said to someone welcome he/she will respond to you well stay. This is Amharic English at all. Some of us think in Amharic and speak in English that is the way to down. Your intervention capture our weakness that caution to be careful.
this is a generation created by the countrie's leaders.the leaders are very happy with it.this is the so called identity crisis.
ReplyDelete"ኢትዮጵያዊ ሊነገረው እንጂ ሊነገርለት አይችልም ያላችሁ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊሰማ እንጂ ሊሰማ( ሰ ይጠብቃል) አይገባም ብሎ የፈረደ ማነው? ኢትዮጵያዊ ሊታሰብለት እንጂ ሊያስብ አይችልም ያለ ማነው?"
ReplyDeleteWhat about those who change their sex organs?Who
ReplyDeleteAbort the womb?Who use pills?Who use Serigery to change their Physical gift?etc...
What about Implantation of defected organ with another new given from some body?
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteየኛ ኤፍ ኤሞች ከቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ መማር ይገባቸዋል እላለሁ፡፡ እንኳን እነሱ ኢንተርቪ ያደረጉት ሰው እንኳን የእንግሊዝኛ ቃል ሲያስገባ ይተረጉሙለታል ወይም ያርሙታል፡፡ ምክንያቱም የአማርኛ ጣቢያ በመሆኑ፡፡
በተረፈ የሬዲዮ ጣቢያዎቻችን የውጩን ኢንፎርሜሽን ፈጽሞ አይዘግቡ አይደለም ሃሳቡ ግን ጥቅሙ ይመዘን፡፡ የአንድ ዘፋኝ የጫማ ቁጥር ወይም የልብስ ምርጫ ብዙ ሰዓት መያዙ በጣም ያሳዝናል፡፡
አንድ የእንግሊዝን፣ የስፔንን፣ የጣሊያን እግር ኳስ ተጫዋቾችን ሙሉ ስም ከነትውልድ ቦታቸውና ከነክለባቸው ልቅም አርጎ የሚያውቅ ወንድም ጋር ተገናኘንና በአጋጣሚ ስለጀግናው አብዲሳጋ ተነሳ እንኳን ታሪኩን አብዲሳጋ የሚባል ሰው እንኳን አለማወቁን ገለጸልኛ፡፡ ታዲያ ይህንን ምን ትለዋለህ?
እግር ኳስ መዝናኛ ነው ሰው እንደ ምርጫውና እንደ ዝንባሌው ሊዝናናበት ይገባል፡፡ ግን ከልክ አልፎ ስራ ሊያስፈታና ጊዜ ሊገድል ግን አይገባውም ፡፡ ስለጫወታው፣ ስለተጫዋቾቹ፣ ስለዳኞቹ፣ ስለአሰልጣኞች፣ ወይም ስለተመልካች ይዘገብ ምክንያቱም ልምድ ለመለዋወጥ ስለሚጠቅም ግን ስለአንድ ተጫዋች ለዚያውም የማናውቀው የአጎት ልጅ ወይም ፍቅረኛ በሚዲያ ሽፋን መስጠት ስራ እንደመፍታት ነው፡፡
አሁን አሁንማ ሰንበት ት/ቤቶቻችን ራሱ ጫዋታ ባለበት ቀን እየተዘጉ ነው፡፡ ጻድቁ ተክለሃይማኖት የት ተወለዱ ስትለው አይኑ የሚፈጠው ሰንበት ተማሪ የነሮኒንና የነድሮግባን እድሜና ታሪክ ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ልጆቻቸውን ብዛት ከነጫማ ቁጥራቸው ሁሉ ሊነግርህ ይችላል፡፡ ታዲያ ይህ ትልቅ ወረርሺኝ አይመስላችሁም?
አደራችሁን ኳስ ማየት ሃጢያት ነው እያልኩ አይደለም ግን የጉባኤ፣ የፀሎት፣ የንባብ፣ የጥናት፣ በተለይም ወላጅ ለቤቱና ለልጆቹ መስጠት የሚገባውን ሰዓት የሚሻማ ከሆነ ግን ከዚህ የበለጠ ምን አይነት መሸነፍ ሊኖር ነው? የትኛው መስመር ላይ እንደቆምን ራሳችንን መመርመር አለብን፡፡
አንድ ፕሮግራም ሲካሄድ አስተማሪ፣ አመራማሪ፣ አዝናኝ፣ አወያይ፣ መልእክት ወይም ማስታወቂያ አስተላላፊ መሆን አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን የ90 ደቂቃ ቆይታ ላይ ከምንም የማይመደቡ ወሬዎች ይደመጣሉ፡፡
ለማንኛውም የኛ ጋዜጠኞች የሚያነቡት አይመስለኝም እንጂ በበጎ አስተያየት ተመልክተው ለሚዲያ ሽፋናቸው ትኩረት ቢሰጡት መልካም ነው፡፡
Gosh dani, saladenkh malef alfelgm. Gudayu bexam angebgabi new, awon idget yale bahl, tarik ina tiwfit ale bye alamnm. Igna degmo yerasachinin kalxebekn lela man aleln? Yhen tshufihn yayehut zare memhrachn bewereket atimo liyaweyayen sisexen new. Ayeh bzu danieloch kegonh alu. Berta, berta.
ReplyDeleteአይ ዳኒ ጥሩ ዕይታ ነው
ReplyDeleteበጣም የሚገርም ነገር ልጨምርልህ
የእንግሊዘኛ ፊልም በአማርኛ ርዕስ ተጽፎ አንብበክ ታውቃለህ? ወይንስ የህንድ ፊልም ርዕስ በቻይና ቋንቋ ተጽፎ አይተህ ታውቀለህ? ይህን የምታየው የራሷ ቋንቋ የራሷ ፊደል ባላት ሃገር በኢትዮጵያ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ ልጥቀስልህ
ኮመን ኮርስ
ዌይተሩ
ቴክኢት ኢዚ
ሲቲ ቦይዝ
የሚገርም እኮ ነው
ምን አይነት የስነ ጽሁፍ ባለሞያዎች እንዳሉንና ምንም ያህል ለቋንቋቸው ለባህላቸው እና ለማንነታቸው ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች እንዳሉን እየታዘብን ነው አቤት በስንቱ ነው ችግር ያለብን ጉድ እኮ ነው ኢትዮጵያ ማንነቷን አታ ቀፎዋን እንድትቀር ነው የሚፈለገው ይሄ ደግሞ በራሳችን ሰዎች እየተሰራ ነው ምን እናድርግ ተው የሚል በሌለበት ሃገር ምን ማድረግ ይቻላል፡፡
enem silefilm riesoch tinish lichemirilih
Deleteloundary boy
shefu
surprise
.
.
.
.
/
tekekele
ReplyDeleteኒውዮርክ ጎዳና ላይ መኪኖች ተጋጭተው መንገድ መዘጋቱ ምን ይፈይድልናል? እዚህ ሃያ ሁለት ተጨናንቆላችሁ የለም እንዴ? እገሊት የተባለቺው ዘፋኝ ሆሊውድ ውስጥ በሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ገብታ የአንድ ሺ ዶላር ራት በላች ብሎ ማውራት ድኻውን ከማስጎምጀት ያለፈ ጥቅሙ ምንድን ነው? እገሊት ከእገሌ ጋር በፍቅር ወደቀች፣ እነ እገሌ ሊጋቡ ነው፣ እገሊት ርጉዝ መሆንዋ ታወቀ፣ እገሌ ደግሞ አንድ ልጅ ከአፍሪካ በማደጎ ሊወስድ ነው እያሉ አዲስ አበባ ተቀምጦ እንግሊዝ እና ካሊፎርንያ ላይ መፎነን ምን የሚሉት አባዜ ነው፡፡
ReplyDelete(etiopical link) yemibalew wuy wuy
መሐመድ ሰልማን እውቀት አጠር ጋዜጠኞች ብሎ የለጠፈባቸው ታርጋ ሳያንስ አንተ ደሞ ተጨማሪ ሆነህ አብጠለጠልካቸውሳ፡፡ እነሱ ምን ያድርጉ ብለህ ነው፡፡ ነጻ መሬትና ነጻ ቀጠና ላይ ነብሳቸውን በጨርቃቸው ቋጥረው በሰላም ለመኖር ከመታኮሻው መስመር መራቅ የግድ ሆኖባቸው ነው፡፡ የኛ ነጻ ቀጣና የት ይሆን፡፡
ReplyDeleteGOD BLESS YOU DANI
ReplyDeleteHi D/n Dani
ReplyDeleteይህን ጉዳይ ሁሉም ሊያጤነው ይገባል ጥሩ የሆነ ጽሁፍ ነው የምታቀርበው በርታ
GOOD BLESS YOU
Hailemeskel Z Maputo
you are amezing dany
ReplyDelete«ጋዜጠኛው» ቀብሩ በትናንትናው ዕለት ስለተፈጸመ አርቲስት ተናገረና «rest in peace ብለናል» አለ፡፡ የአፍ ወለምታ ወይንም ልማድ ነው ብዬ ዝም አልኩ፡፡ አሁንም ስለ ሌላ ስለ ዐረፈ ሰው ተናገረና ያንኑ ደገመው፡፡ ይኼኔ ደነገጥኩ፡፡ ይኼ የኤፍ ኤም ሬዲዮ በአማርኛ ቋንቋ ለሕዝበ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ፕሮግራም ነው፡፡ አሁን «ነፍስ ይማር» የሚለው የአማርኛ ቃል የሚጠፋው ጋዜጠኛ እንዴት ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጉዳዮች ሊያነሣ የሚችለው? ወይስ
ReplyDeleteYe Ethiopia Amlak Yakoyeh!
ReplyDeleteWhat I absolutely shared!!!!!!!!!
ReplyDeletedawit
FM ko lekek yemibalbet enji be wegina besirat sewn yemiyachenanik adelem. wedaje ketegbabah min yasfeligal?wededinim telanim demo engilizigna alemakef kuanka new. etyopiachininim chemiro malete new. Ena eneamarigna weym motoch atachenanikun abo! lekek bilen ennurbet. sew huluko amarigna atigni mehon yelebetim. endemikelew yawra. wanaw semiw gebtotal wey new gudayu. egngn...gn atibelu abo.
ReplyDeleteለቀቅ አድርጉን በፈለገው እናውራ ያልከው ሰው እኔ አፈርኩብህ። ማንነትህ የጠፋብህ ሰው ስለሆንክ እንኳን ላገር ለራስህም ግራ እንደገባህ ትኖራለህ።
ReplyDeleteእኛ ሀገር እኮ እንግሊዝኛ የእውቀት መለኪያ ሆኖ ተቸገርን.አማርኛችንን ማን ያክብረው.ጥሩ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ጎበዝ ተደርጎ እየታሰበ ነው.በዚህ አጋጣሚ ትምህርት ቤቶቻችንንስ ማን አያቸው?
ReplyDeleteAbet complex! yecomplex tig! Gitim argo yeewket melekia newna. Malete yeenglizigna kuanka ewket.Amargnam eko yeewket melekia new.
ReplyDeleteKeethiopia weta bitl yane kuankua(englizigna) ewket mehonu ygebahal ajire. Bezi agatami ene majere englizigna minore amarigna newna huletunum sinekakubign alwedim.wanaw ajenda lay binatekur yshalal lije.
A good point on the issue of mixing up languages but asociating what Ethiopia is and what it's got with christianity and the amharic language is a bit narrow, just my opinion.
ReplyDeleteአግባብ ያለው እይታ ነው፡፡ ነብስ ይማርና አፄ መለስ ይቅርታ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊም እኮ “ምነው በንግግሮ መሃል እንግሊዘኛ ይቀላቅላሉ” ተብለው፡ “የምሁር መገለጫው ነው ብለው” ነበር ይባላል፡፡
ReplyDeleteDani yalew eko englizgna ayneger sayhon programu be amargna hono eyale englizgnawn min ametaw new. programu englizegna kehone be englizgna, amargna kehone bamaregna, oromgna kehone be oromgna mehon alebet. benegerachin lay enezih englizgna yemiterzut ye englizgna adnaqiwoch enji awaqiwoch aydelum.lenegeru kign gizat teyzen bihon noro tiru neber yemilu sewoch bebezubet ager yihie lenie minm aygermegnm. Enam dani betam tiru new qetlbet mannetun yemaywq yeminagerwn ayawqm.Amesegnalehu!
ReplyDelete