Tuesday, December 6, 2011

የሕይወት ታሪኬለቤተ መጻሕፍ
አዘጋጅ( ፊታውራሪ አመዴ ለማ (መጋቢት 1913 ( 2001 ዓም)
ኅትመት( 2003 ዓም
ዋጋ( 60 ብር
ፊታውራሪ አመዴ ለማ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የንግድ እንቅስቃሴ፣ ፖለቲካዊ ጉዞ፣ የሕግ አወጣጥ፣ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ሽምግልና እና ቅርስ ላይ የራሳቸውን አሻራ መተው የቻሉ ሰው ናቸው፡፡
 በጥንቱ የወሎ ጠቅላይ ግዛት በወረሂመኑ አውራጃ በአሊ ቤት ወረዳ መጋቢት 30 ቀን 1913 የተወለዱት ፊታውራሪ አመዴ 88 ዓመት ጉዟቸው የኢትዮጵያን ዘመናዊ ታሪክ ያስቃኙናል፡፡ ስለ ባህላችን፣ ታሪካችን፣ ሃይማኖታችን እና ኢኮኖሚያችን፣ ብሎም ስለ ዘመናዊው የፖለቲካ ጉዟችን የሚነግሩን የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡
ፊታውራሪ አመዴ ሁለገብ ሰው በመሆናቸው የክርስትናን ባህል ከክርስቲያኖቹ በላይ ሲተርኩት እናያለን፡፡ በተለይም ደግሞ በአካባቢያቸው የነበሩ ዛሬ ግን በመጥፋት ላይ የሚገኙትን ባህላዊ ጨዋታዎች ሲተርኩ እኛንም የጨዋታው አካል አድርገው ነው፡፡ በዚያ ዘመን የነበረውን የንግድ አሠራር፣ የሂሳብ አያያዝ፣ የብድር መንገድ፣ የመጀመርያዎቹ ኩባንያዎች እና አክስዮኖች እንዴት እንደተቋቋሙ ይተርኩልናል፡፡
የኢትዮጵያውያን የኀዘን ልብስ ጥቁር የሆነው ከጣልያን ወረራ በኋላ ነው ብለው ይከራከራከሉ ፊታውራሪ፡፡ ለዚህም ባህላዊ ማስረጃ አምጥተው ባህላቸን ምን እንደነበር ይነግሩናል፡፡ አንብቡት፡፡
በጣልያን ዘመን የነበረውን አስጨናቂ ሁኔታ በልጅ አእምሯቸው የታዘቡትን ሲነግሩን እየተሰቀቅን እንድናነብ ያደርጉናል፡፡ የዚያን ዘመን የፓርላማ እንዴት ይሠራ እንደነበር ከራሳቸው ከንጉሡ ጋር ያደርጉት የነበረውን ክርክር፣ ከውጭ ይመጣ በነበረው ብድር ላይ ከንጉሡ ጋር በመለያየታቸው ፓርላማው እንዴት ውድቅ አድርጎባቸው እንደነበር ይነግሩናል፡፡
ፊታውራሪ አመዴ ሴተኛ አዳሪነት በመተዳደርያነት እንዴት በጣልያን ጊዜ እንደ ተጀመረ ራሳቸው ያትን ይነግሩናል፡፡ ጣልያን ካምፕ ሠርቶ ለወታደሮቹ የሚሆኑ ወጣት ሴቶችን በሴተኛ አዳሪነት እንዴት ያሠማራ እንደ ነበር ነግረውናል፡፡ እንዲያውም የሴቶቹ ፎቶ በር ላይ ተለጥፎ እንዴት ይመረጡ እንደ ነበር ያዩትን ይመሰክራሉ፡፡
ንጉሥ ኃይለ ሥላሴን እና የወሎን ሕዝብ ምን እንዳቀያየማቸው፣ በዚህም ምክንያት አልጋ ወራሹ በሕዝቡ ላይ ይፈጽሙት ስለነበረው በደል፣ ያም በጊዜው ባለ መስተካከሉ በማይጨው ጦርነት የተከሰተውን አሳዛኝ ነገር ፊታውራሪ እንደ ፊልም ያቀርቡታል፡፡
በእንግሊዝ ስላደረጉት ታሪካዊ ጉብኝ በዚያውም እንዴት ከደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴ ጋር እንደ ተገናኙ ይነግሩናል፡፡ ለሀገራቸው ቅን አሳቢ የነበሩት ፊታውራሪ አመዴ ደጃዝማች ዘውዴ ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ከላይ እስከ ታች የደከሙትን ድካም ያወጉናል፡፡
ፊታውራሪ አመዴ የአኩስም ሐውልት እንዲመለስ ከአርባ ዓመታት በላይ ያደረጉትን ተጋድሎም ተርከውታል፡፡ የታሠሩትን የቅንጅት መሪዎች ለማስፈታት እንዴት እንደ ታገሉ ይተርኩትና የተፈቱት የቅንጅት መሪዎች ያስፈቱን ፈረንጆች ናቸው በማለታቸው ማዘናቸውንም ነግረውናል፡፡ አያይዘውም «የፈረንጅ አስታራቂ እና የእህል አረቂ እራስ ከማዞር በስተቀር ዋጋ የለውም» ብለው ይመክራሉ፡፡
ፊታውራሪ አመዴ በገንዘብ እጥረት የተቸገሩ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን ችግር ለመፍታት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር አስፍረውልናል፡፡ በእርሳቸው ቅስቀሳ ቤተ ክርስቲያኑን ከመዘጋት እንዴት እንደታደጉት ሲነግሩን ምናለ የርሳቸውን ዓይነት ሺዎች ቢፈጠሩ እንላለን፡፡
በመጨረሻም በየመንግሥታቱ የመንግሥታቱን ፖሊሲዎች በመተቸት ያደረጓቸውን ንግግሮች አስቀምጠዋቸዋል፡፡
መጽሐፉን ፊታውራሪ ቢጽፉትም የታተመው ካረፉ በኋላ ነውና የአሟሟታቸውን ሁኔታ፣ የቀብራቸውንም ሥነ ሥርዓት ቤተሰቦቻቸው ቢያካትቱልን መልካም ነበር፡፡ የፊታውራሪ አሟሟት እና አቀባበር ለክብራቸው የማይመጥን እንደነበረ የታወቀ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለታላላቅ ሰዎቿ ያላትን ክብር የሚያሳይም ነው፡፡
መጽሐፉን ሳነብ አንዳንድ ጊዜ እያዘንኩ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብቻዬን እንደ ዕብድ እየሳቅኩ ነበር፡፡ በተለይም ለፓርላማ ሲወዳደሩ ያደረጉትን ክርክር በሳቅ ነው የጨረስኩት፡፡
በሉ እናንተም መጽሐፉን ግዙና እዘኑ፣ ሳቁም፡፡
መልካም ንባብ፡፡

15 comments:

 1. ከየት ልግዛው?
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 2. «የፈረንጅ አስታራቂ እና የእህል አረቂ እራስ ከማዞር በስተቀር ዋጋ የለውም»

  ReplyDelete
 3. edit this
  ለቤተ መጻሕፍዎት

  ReplyDelete
 4. ታላላቅ ሰዎች ዛሬ ባይከበሩም የሚከበሩበት ጊዜ ይመጣልና ዝም ብሎ መልካም ሥራ መሥራት ነው፡፡መልካም ሥራቸውን ዐቃቤ መልአክ በሕይወት መዝገብ ይመዘግበዋል ለክብራቸው መገለጫ በወርቅማ ቀለም፡፡

  ReplyDelete
 5. Dear Daniel, I must read this book.

  ReplyDelete
 6. ምነው ጃል !

  ከየት ልግዛውማ አይባልም፡፡ ከመሸጫ መደብር ነዋ፡፡

  ReplyDelete
 7. To the children of Amedie Lema
  Do u want profit from the history of your father? If u loves your father and to propagate your father's name through The Ethiopian's mind,why don't u sell by 10 birr only? you should cover the cost of the book.

  ReplyDelete
 8. Thank you Daniel: This was a man who did a lot for Ethiopia. The goverment and the media should had done better on his death how they broadcasted.

  ReplyDelete
 9. Fit. Amedie Lema,IS a national, hero and a,true icon of ethiopian nationalism and statesmanship ,he was a relentless advocate,to the interest of a greater ethiopia and its people,he was a seasoned,poletician and blessed with wisdom which enabled him to speake his mind through three generations of ethiopian government with out retribution and fear of reprisal ,which is a manifestation to his true nationalism and deep knowledge of the ethiopian affairs.it is a great read for any body who wants to know the historical journey of Ethiopia past present,and may be a glimse of future if the status qou contineus.the title of the book is rather misleading as much of it is about his views on national issues.we all owe gratitude to this great national hero.GOD BLESS HIS SOUL!
  ABRAHAM

  ReplyDelete
 10. he was very giving.he did alot for ethopia.he was the best grandpa a girl or boy could ever have.i will FOREVER remeber him. he was very much a hero. i love him
  love his grandaughter
  gunfo

  ReplyDelete
 11. I wish one of his children, specially the one who lives in Atlanta lives his life half of his father's legacy. He is a waste and an embaressment to his family. I don't want to name his name, he is well known with his out of hand ways of talking to people he encounter with.
  I agree Fitawrare Amade is a well deserved hero of our country. May god bless his soul.

  ReplyDelete
 12. የሰው ታሪክ.እንጂ የሆድ ታሪክ ያልነበራቸው:
  እውነተኛ መፅሀፍ ናቸውና ጥሩ አድርገህ ከተብከው ዳ.ዳንኤል መልካም ምልከታ:
  ከማን(man) እንማራለን…..?
  አውቀው ይሆን…ሳይገባቸው፤
  ይህን ማለታቸው…፤
  ማን ማለት…. ሰው ማለት ከሆነ፤
  ቃል በቃል ሲፈታ፤
  የማይገባኝ ነገር “ሰው እኮ…!”…
  የሚለው የምፀት ጨዋታ፤……ምኞቴ.ብዙነህ.@ ፍሎሪዳ.ጫካ…

  ReplyDelete
 13. Well ali beti abeyi beti brings some memory of where I born one of my anti was used it for greeting like this
  Ali betim abeyi betim amani New
  I really thank you for your great sharing dear Daniel

  ReplyDelete