Saturday, December 3, 2011

ይህ ስም ክቡር ነው


ኢትዮጵያ የሚለው ስም ተራ ስም አይደለም፡፡ ብዙ ሚሊዮኖች እንዲሠው ያደረገ ስም ነው፡፡ አያሌዎች በስፖርት አደባባይ ካገኙት ድል በላይ ይህ ስም ሲጠራ አንብተዋል፡፡ ይህ ስም በቅዱስ መጽሐፍ ከአርባ አራት ጊዜ በላይ የተጠቀሰ ነው፡፡ ይህ ስም ሲጠራ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ደማቸው ይሞቃል፣ ስሜታቸው ይንራል፣ ነርቫቸውነም ይነዝራቸዋል፡፡
ይህ ስም ከረሃብ እና ከእርዛት፣ ከድህነት እና ከችግር ጋር ሲነሣ የማያመው ዜጋ የለም፡፡ በዚህ ስም ሲለመንበት የማይቆስል ዜጋ የለም፡፡ በአንፃሩ ይህ ስም በክብር ሲነሣ ልቡ የማይሞቅ ሞራሉም የማይ ነሣሣ ዜጋ የለም፡፡ ተድባበ ጥላሁን ስለ ካዛንችስ የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት በጻፈው መጽሐፉ ላይ አንድ ግሩም እውነታ ይነግረናል፡፡ አብዛኛው ወደ ሴተኛ አዳሪዎቹ ቤት የሚመጣው ሰው የሚቀንሰው መቼ ነው? ለሚለው የነገረን ነገር፡፡
 ኢትዮጵያ በሩጫ ስታሸንፍ፣ ወይንም ብሔራዊ ቡድኑ ሲያሸንፍ፣ ያለበለዚያም ሀገሪቱ በአንዳች ነገር አሸነፈች ሲባል ብዙዎቹ የሴተኛ አዳሪዎች ደንበኞች ወደቤታቸው መሄድን ይመርጣሉ ይለናል፡፡ ለምን? እንደ እኔ ግምት አንዳች የሞራል ልዕልና፣ አንዳች የስብራት መጠገን፣ አንዳች የምግባር ከበሬታ ይሰማቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህ ስም ከፍ ከፍ ሲል ብዙዎቹን ከድቀት እንደሚያነሣቸው ይነግረናል፡፡
ይህ ሰም ክቡር ስም ነው፡፡
ኢትዮጵያን የረሃብ ምሳሌ አድርጎ ካስቀመጠው መዝገበ ቃላት ይህንን ስም ለማስፋቅ በመላው ዓለም እንቅስቃሴ የጀመሩ ሀገር ወዳዶች አሉ፡፡ ይህ ስም ከዕድገት እና ከብልጽግና ጋር ብቻ፣ ከሰላም እና ከልዕልና ጋር ብቻ፣ ከሀብት እና ከፍቅር ጋር ብቻ እንዲነሣ በልማቱ ጎዳና ትግል የጀመሩ አሉ፡፡ ይህ ስም በመቻቻል እና በመፋቀር፣ ይቅር በመባባል እና በመግባባት ብቻ እንዲነሣ የሚደክሙ የሀገር ሽማ ግሌዎች አሉ፡፡ ይህ ስም ክቡር ስም ነውና፡፡
ይህ ስም ፈጽሞ ከግብረ ሰዶማዊነት ጋር ለነሣ አይገባም፡፡ ፈጽሞ፡፡ 97 በመቶ ኢትዮጵያውያን ከሚጸየፉት ተግባር ጋር ሊነሣ አይገባም፡፡ ፈጽሞ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስብሰባችንን በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ እያደረግን ነው አሉ፡፡ መገናኛ ብዙኃንም እያደረጉ ነው አሉላቸው፡፡ ይህ ለኛ ለኢትዮጵያውያን የአንገት መሰበር ነው፡፡ ለዚህ ስም ግብረ ሰዶም አይመጥነውም፡፡ ፈጽሞ፡፡
ከአድዋ ድል ጋራ፤ ከአኩስም አና ከላሊበላ፣ ከሐረር አና ከጎንደር ሥልጣኔ ጋር የተጠራ ስም ከዚህ አስነዋሪ ተግባር ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ፈጽሞ፡፡ ከያሬድ እና ከአባ ጊዮርጊስ፣ ከቴዎድሮስ አና ከምኒሊክ፣ ከኃይሌ እና ከቀነኒሳ፣ ከደራርቱ እና ከመሠረት ጋር የተነሣ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡
ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡ በመንፈስ ያልበለጸገ ሕዝብ በቁሳዊ ነገር ሊበለጽግ አይችልም፡፡ ቢበለጽግም ዘላቂ አይሆንለትም፡፡
መንግሥት እንደ መንግሥት ይህንን ተግባር መከልከል ነበረበት፡፡ ይህ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር አብሮ እንዳይነሣ መከልከል ነበረበት፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ መሰብሰብ ከጀመሩ፣ ነገ በአዲስ አበባ ይሰለፋሉ፣ ከነገ ወዲያ ደግሞ በአደባባይ ይፈጽሙታል፡፡
በአዲስ አበባ የልማት ጀግኖች ይሰብሰቡ፣ መሪዎች ይሰብሰቡ፣ አትሌቶች ይሰብሰቡ፣ አርቲስቶች ይሰብሰቡ፣ ደራስያን ይሰብሰቡ፣ የፖለቲካ መሪዎች ይሰብሰቡ፣ የባህል እና የእምነት መሪዎች ይሰብሰቡ፡፡ ባልገው ልጆቻችንን የሚያባልጉ፣ ያልበላንን የሚያክኩ፣ እየወጣነው ላለው ገደል ተጨማሪ ጉድጓድ የሚፈጥሩ ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው፡፡
ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡

99 comments:

 1. ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው፡፡

  ReplyDelete
 2. እና የእውነት ተሰበሰቡ ማለት ነው? መንግስትም ፈቀደ ማለት ነው? ታድያ ከዚህ በላይ ምን ሞት አለ??? ስለዚህ......

  ReplyDelete
 3. God be with you in all your way... you are doing what you can...it is right we have to corelate the name Etiopia with such issues only. the great history and practice of our for fahters is proving only this even today. we can see it alive...Yeneta Eshetu's interview with ADDIS GUDAY in today's issue is one proof that helps us to see where we are ... really very thanks daniel for you and all of them who are around...the picture of tomorrows Ethiopia is the result of todays elites of the church so we don't have to give it only for poleticians...

  ReplyDelete
 4. they have started long ago....todefame the country,to deny its history...to sell its land ...too late we are.....

  ReplyDelete
 5. ውድ ዲያቆን ዳንኤል!
  በበኩልህ ሀገራችን እና ወገችን ሃይማኖታችን እና የተቅደሰው ባህላችን ሳይበረዝ እና ሳይሸራረፍ ቅድስናውን እንደያዘ እንዲቀጥል ለማድረግ ለምትከፍለው የድካም ዋጋ እግዚአብሄር እጽፍ ድርብ አድርጎ መልካሙን እና ዘላለማዊውን ዋጋ ይስጥህ እላለሁ።
  ከዚህ ጽሑፍህ ጋር በተያያዘ የምጠይቅህ ነገር: በውኑ በሀገራችን በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚፀየፍ 97 በመቶ ብቻ ነው እንዴ? እንደኔ ግምት ከ99.9 በመቶው በላይ ግብረ ሰዶማዊነትን ይፀየፋል ባይ ነኝ። አንተ ይህን አኀዝ ከየት አግኝተህ ነው የወሰድኸው? መረጃውስ ቢኖር እንኳ ምን ያህል ሊታመንበት ይችላል?

  3ኛው ሐሳቤ:እስከ አሁን ሳውቅህ ለማንም አታዳላም አሁንም አዳላህ ለማለት ሳይሆን በተለይ ከአትሌቶቻችን እነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴን እነ ቀነኒሳን እነ ደራርቱን እነመሠረትን ስታነሳ ምነው እነ ጥሩነሽ ዲባባን እነ አበበ ቢቅላን እና ሌሎችንም ረሳኃቸው?
  አዳላህ እንዳትባል ያለኝን ሥጋት ለማካፈል ፈልጌ ነው።
  በተረፈ በዚሁ ቀጥል እላለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. lemin wanawen hasab bicha yizen aneguazem

   Delete
 6. የልማት ጀግኖች ይሰብሰቡ፣ መሪዎች ይሰብሰቡ፣ አትሌቶች ይሰብሰቡ፣ አርቲስቶች ይሰብሰቡ፣ ደራስያን ይሰብሰቡ፣ የፖለቲካ መሪዎች ይሰብሰቡ፣ የባህል እና የእምነት መሪዎች ይሰብሰቡ፡፡
  ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. Egziabher abezito yebarkhe dn DAni be ewenet yihen setsef anjethe kitel belo endehone yesemagnal miekneyatum ene sanebew betam weste nedede minew amelake esrael yihechen ager ETHIOPIYAN bemeleketat ebakachehu wegenoche eski ers be eresachen yiker tebabelen yihe yemetaben mekseft endiweged entseley yihe hulu yemetaw yemeslegnal yegna feker metfat new eski asbu bezhich hager sedomaweyanoch sesebesebubat neges yebeletew ayemetam belachehu tasebalachew wegen? Daniye ebakehe be wechem be hager westem yalu bemulu yihen neger endet mekawem endaleben aketacha weyem hasab betakerbelen Egziabher tenana edeme yesthe kemela beteseboche gar

  ReplyDelete
 8. ዳኒ በጣም በጣም በጣም ትክክል! ለመድገም አስቤ ባይሄንም በ ሰንድ ሀሰብ ልረደህ "ከአድዋ ድል ጋራ፤ ከአኩስም አና ከላሊበላ፣ ከሐረር አና ከጎንደር ሥልጣኔ ጋር የተጠራ ስም ከዚህ አስነዋሪ ተግባር ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ፈጽሞ፡፡ ከያሬድ እና ከአባ ጊዮርጊስ፣ ከቴዎድሮስ አና ከምኒሊክ፣ ከኃይሌ እና ከቀነኒሳ፣ ከደራርቱ እና ከመሠረት ጋር የተነሣ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡" በማስፋፋት!!!

  ReplyDelete
 9. yes indeed...i am againest to this evel action!God doesnt like this..we all must rem wt happened on ''sedom and gamora''we dont need to suffer anymore,lets keep a blessing for the next generation.we have suffered cos of famine,poverity and poletical problems. instade we need our country to be blessed,develeop,and change her image around the world.'' oh Jesus help us to fight againest this''

  ReplyDelete
 10. ኢትዮጵያውያን ስም ፈጽሞ ከግብረ ሰዶማዊነት ጋር ለነሣ አይገባም፡፡ ፈጽሞ፡፡

  ReplyDelete
 11. ሰዎች እንዴት አናስቁመው በሚለው ሀሳብ ላይ እንነጋገር

  ReplyDelete
 12. Let the Almighty God bless you and gives you the wisdom more! You speak out my 'internal shout'/Yewisten chuhet chohikilign/. Hope you have speak out on behave of most people. Let us pray!!!...This at least shows some what 'Ethiopia' deserves..it is more than what even we think and imagine...

  God bless the world and God bless Ethiopia!!!

  Thanks,

  Hailemariam

  ReplyDelete
 13. Ante ende Tarik balemuya tinageraleh egna eyanebebin zim enilalen. Ethiopia egnan aferach min waga alew Dani. Bahilachin tefa, kuratochachin afer lebesu, Eminetachin malagecha hone, yehager simetachin wuha tedefabet, wegenachin hager leqo besew hager bayitewar hone....lelochim....egna gin zimita meretin. Engdih min keren yihon???

  ReplyDelete
 14. Dn, Daniel, kale hiwot yasemalin.
  I completely agree with what you have written. But I have a question, when do we start doing somethig about it. Does the government read your blog? I doubt it. So let's gather together and do something about it to show this unEthiopian governmet that we the people own our country not few people in office. This government has lost respect for the Ethiopian people because he sees no retaliation about any wrong doing. The government thinks that the people of the country has no moral anymore. And it is a SHAME!!!! As a women, I think we all have no use anymore if we don't make this government respect us. Enough is enough. Disrespecting the church, the people, the country.... what else is left? Let's do something about it. Writing about it only isn't going to change anything. GOD HELP US

  ReplyDelete
 15. I wanted to comment about this denouncing in the very strongest terms and in detail.Yet, most of the time you don't post my comments.You are very shy when one mentions the name of TPLF and tagaye Paulos. Please librate yourself first from ... before you even try to share your ideas to others.Who do you think who is creating this mess? We should aim the right target and hit it so that all these unheard and unseen shame won't come again.Good bye.

  ReplyDelete
 16. ለዚህ ስም ግብረ ሰዶም አይመጥነውም፡፡ ፈጽሞ፡፡

  ከአድዋ ድል ጋራ፤ ከአኩስም አና ከላሊበላ፣ ከሐረር አና ከጎንደር ሥልጣኔ ጋር የተጠራ ስም ከዚህ አስነዋሪ ተግባር ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ፈጽሞ፡፡ ከያሬድ እና ከአባ ጊዮርጊስ፣ ከቴዎድሮስ አና ከምኒሊክ፣ ከኃይሌ እና ከቀነኒሳ፣ ከደራርቱ እና ከመሠረት ጋር የተነሣ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡

  ነበር እዳይባል እግዚአብሄር በቸርነቱ ይመልከተን !!!
  ሶፎኒያስ

  ReplyDelete
 17. God bless you Dn. Daniel. The most amazing thing for me is when the current Ethiopian government does something,the orthodox church doesn't complain regardless of evil situation specially the pope. We have in difficult situation.The government and the the pope have common sense organs. Common ears, eyes.....

  ReplyDelete
 18. እነሱ በሰሩት አፍረው ብቻቸውን እንዳይሆኑ እኛንም ሊያሳፍሩን ተነስተዋልና ጎበዝ አሁን ነው በጊዜ በራችንን መዝጋት እነዚህ የቀን ጅቦች ሊበሉን ተዘጋጅተዋል:: ለራሳቸውም ሊያቆሙት ፈልገው የባህል እሴቱ ስለሌላቸው ልጓሙ አጥሮባቸው እንጂ አምነውበት ላለመሆኑ ከብዙ ሁኔታዎች ለመረዳት ይቻላል::

  ReplyDelete
 19. "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!!

  ReplyDelete
 20. Egziabher yakbriln Dany.Emebetachin ye asrat hageruwan titebkilen.Bemiljawa titadegen!AMEN!

  ReplyDelete
 21. ወ/ሚካኤል(የሚካኤል ልጅ)December 4, 2011 at 10:10 AM

  .ይህ ጸሀፊ ክቡር ነው..ሰስለሀገረሩ ይተጋልና
  ይህ ጸሀፊ ደድነንቀቅ ነው...ትውልድን ይመክራልና
  ይህ ጸሀፊ ስስት ነው ...ተተኪ የለውምና
  ጸሎት ያስፈልገዋል...እንዳይዎድቅ ፍጡር ነውና እግዚአብሄር ይባርክ..የልቡን ሃሳብ ...ይስጥልን እድሜና ጤና
  አቤቱ ያባቶቻችንን ቃልኪዳን አስበህ ይህ ትውልድ ከሰዶም እሳት የሚያመልጥበትን ማስተዋልና እምነት ስጠው!ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መቅደስከ!!!
  ቃለ ህይዎት ያሰማልን መምህር!!!
  ሳሚ (ሰመራ)

  ReplyDelete
 22. 'መንግሥት እንደ መንግሥት ይህንን ተግባር መከልከል ነበረበት፡፡ ይህ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር አብሮ እንዳይነሣ መከልከል ነበረበት፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ መሰብሰብ ከጀመሩ፣ ነገ በአዲስ አበባ ይሰለፋሉ፣ ከነገ ወዲያ ደግሞ በአደባባይ ይፈጽሙታል፡፡'

  መንግስት ለስልጣን መራዘም ብሎ የስበረው የህዝቡ ልቦና ገና በዙ ያመጣብናል፡፡ ዝም ብቻ ትናንት ቤ/ትያን ስትሰደብ ዝም ዛሬ ሌላ ነገ ደግሞ ይቀጥላል 'ጥሬ ጭዋዎች' ሆነናል።
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 23. what is going on ? where are we heading ?what should we do ?.
  once a radio program was on the air based on this immoral act, a lots of heart breaking issues raised . every body was participating with phone calls .it goes for a couple of days or so and ...that is it ! done !.none of the concerned hierarchy came and say a word on it not a single one !. nothing has been done and no single step will be taken by the government in the future.
  it is obvious that, God,BIBLE,church,cultural value, frame work of a nation ,nationality, country... is a fairy tail for the ruling government all they think is about wealth and the so called democracy .wegenoche ! this issue is our home work it is we who should fight and do some thing about it . D,Dainel,it is a heart BREAKING news you told us ...it is !. EGZIABEHAIR TENEKAREWN LEHULACHEN YESTEN . H

  ReplyDelete
 24. ወንድሜ ተባረክ፡

  ልንቃወመው የሚገባ ክፉ አንዱ ግብረ ሰዶማውያን

  ReplyDelete
 25. በቃ ይህች አገር አሳቢና አስተዋይ መሪ አጣች ማለት ነው? ብቻ ፈጣሪ ፍርዱን ይስጥ::

  ReplyDelete
 26. በተቃውሞ የምንወጣበት ወይንም የምንፈራረምበት መድረክ እንዴት ይመቻች? ይህ የሃይማኖት ባቻ ሳይሆን የአገር ጉዳይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 27. God will pay their wages soon coz the wages of sin is death,not only to these vulgar people but also to Government of Ethiopia that allow them to go for to this step.
  Daniel....God bless u and we all Ethiopian will stand together up to death to vanish these devils from our land.

  ReplyDelete
 28. ኩራት እራት ነው የሚለው የገባኝ አሁን ነው፡፡

  ReplyDelete
 29. Have mercy on me, O God, according to your unfailing love; according to your great compassion blot out my transessions.
  Psalm 51:1

  ReplyDelete
 30. ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው" ሮሜ 1፥26-28
  ይህን ጉባኤ እንደተራ ነገር ብንቆጥረው፤ በሀገራችን ነውር የሚባል ነገር ላይኖር ነው፣ የከበረውና የተዋረደው ተቀላቅሎ በሚመጣው ትውልዳችን ትከሻ ላይ ሊወድቅ ነው፤ እንዲህ ዓይነቱ ጉባኤ መወገዝ አለበት!!!!

  ReplyDelete
 31. አህያውን ፈርቶ ዳውላውን
  እሳቱን ፈርቶ ጢሱን

  ዲያቆን ዳንኤል አስተያየቴን ለመለጠፍ እንደማትፈለግ ለመረዳት ችያለሁኝ፡፡አለመለጠፍ ለጊዜው ያልተረዳሁት ያንተ የውስጥ ችግር ነው፡፡እንደ ዜጋና እንደ ሰው ከውስጤ የሚሰማኝን ተናግሬ ባትለጥፈውም ግድ አይሰጠኝም፡፡እሳቱ ከሌለ ጢሱ አይታይም አዎ ልክ ነህ ይህንን ሁሉ ተቆጥሮ የማያልቅ የማህበራዊ ቀውስ ምስቅልቅሎች ጢሶች ያመጣብን ዋና እሳት ደግሞ ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ነው፡፡ኢትዮጵያውያን ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ካለባቸው ይህንን ዘረኛ ዘራፊና አረመኔ የወያኔ አገዛዝ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እንጂ 200 ግብረሰዶማውያን ኢትዮጵያው ውስጥ ተሰበሰቡ ብሎ መሆን የለበትም፡፡ዲያቆን ዳንኤል አንተ ይብልጡኑ የሃይማኖት ሰው ነህ ስለዚህም የዚህን አለም ውስብስብ የረቀቀና የተቀነባበረ የፖለቲካ ጨዋታ በደንብ ጥንቅቀህ ላታውቅ ብትችል ብዙም አይገርመኝም፡፡ዲያቆን ዳንኤል ዛሬ አለማችንና ህዝቦቿ በኦፊሴል ስብሰባና ውሳኔ እይደለም እየተመሩ እየለሙም ሆነ እየጠፉ ያሉት፡፡ጥቂት ልሂቃን ናቸው በዝግ ስብሰባና በስልክም ሆነ በሌላ መልክ ሎቢ እያደረጉ ከበስተጀርባ ሆነው ነገሮችን የሚያሽከረክሩት፡፡ስለዚህም ከእንደዚህ አይነት ስብሰባ በስተጀርባ ምን ምን ነገሮች እንደሚሰሩ መገመት ብዙ ከባድ ነገር አይደለም፡፡
  አሁንም ደግሜ እናገራለሁ ይህ ስብሰባ ከበሰተጀርባው የፖለቲካ ቁማርና ድራማ እንዳለበት መገመት ከባድ አይደለም፡፡አዎ ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን 200 የሚሆኑ ግብረሰዶማውያን ተሰበሰቡ ብለን ሰላማዊ ሰልፍ እንድንወጣ ከበስተጀርባ በረቀቀ መልክ የተቀነባበረ የፖለቲካ ቁማር ነው፡፡ከዚያም ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ “እንዴ ለካ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ” አለ ለማስባልና የፖለቲካ ትርፍ ለማስገኘት የታሰበች የፖለቲካ ቁማር ነች፡፡ዲያቆን ዳንኤል አለም አንተ እየተረተርክና እየተነተንክ እንዲያም ሲል በተረት ተረት በምታቀርባቸው አማላይ የቲዎሪ ስብስቦች ብቻ አይደለም እየተመራች ያለችው፡፡ስለዚህም አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እሳቱን ፈርቶ ጢሱን አይነት መቃወምና መታገል ከቻልንና ካለብን ይህንን አይነት ስር የሰደደና የተስፋፋ ማህበረሰባዊ ቀውስና ምስቅልቅል ያመጣብንን ስልጣን ላይ ያለውን አስከፊና አሳፋሪ የወያኔ አገዛዝ እንጂ ከየት እንደመጡ የማናውቃቸውን ግብረሰዶማውያንን መሰብሰብ አይደለም፡፡ደግሞስ ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ አስቀድሞ እስከፈቀደላቸው ድረስ ደግሞ የተራው ህዝብ መንጫጫት ምን ሊቀይር ነው፡፡ሀገሪቱ እኮ የአቶ መለስ የወያኔና የስብስቦቹ ብቻ ነች የእኛ አይደለችም እኛማ ሁለተኛ ዜጋ ነን፡፡ይህ አገዛዙ የገባበትን የራሱን የፖለቲካ ትኩሳትና ቀውስ በተዘዋዋሪ ለማብረጃነትና የህዝብንም አትኩሮት ከዋናው አንገብጋቢና ወቅታዊ የሆነ ሀገራዊ የፖለቲካ አጀንዳ ለመበታተንና ለማዘናጋት የጣቀደ የተለመደ የተበላበት የፖለቲካ ቁማር ነው፡፡
  ቂቂቂቂቂቂ……………………….. የፖለቲካ ቁማር!!!
  የፖለቲካ ቁማር!!!
  የፖለቲካ ቁማር!!!
  የፖለቲካ ቁማር!!!

  ReplyDelete
 32. መንግሥት እንደ መንግሥት ይህንን ተግባር መከልከል ነበረበት፡፡ ይህ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር አብሮ እንዳይነሣ መከልከል ነበረበት፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ መሰብሰብ ከጀመሩ፣ ነገ በአዲስ አበባ ይሰለፋሉ፣ ከነገ ወዲያ ደግሞ በአደባባይ ይፈጽሙታል፡፡

  ReplyDelete
 33. ይህ ጸሀፊ ክቡር ነው..ሰስለሀገረሩ ይተጋልና
  ይህ ጸሀፊ ደድነንቀቅ ነው...ትውልድን ይመክራልና
  ይህ ጸሀፊ ስስት ነው ...ተተኪ የለውምና
  ጸሎት ያስፈልገዋል...እንዳይዎድቅ ፍጡር ነውና እግዚአብሄር ይባርክ..የልቡን ሃሳብ ...ይስጥልን እድሜና ጤና
  አቤቱ ያባቶቻችንን ቃልኪዳን አስበህ ይህ ትውልድ ከሰዶም እሳት የሚያመልጥበትን ማስተዋልና እምነት ስጠው!ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መቅደስከ!!!

  ReplyDelete
 34. "ይህ ስም ፈጽሞ ከግብረ ሰዶማዊነት ጋር ለነሣ አይገባም፡፡ ፈጽሞ፡፡ 97 በመቶ ኢትዮጵያውያን ከሚጸየፉት ተግባር ጋር ሊነሣ አይገባም፡፡ ፈጽሞ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስብሰባችንን በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ እያደረግን ነው አሉ፡፡ መገናኛ ብዙኃንም እያደረጉ ነው አሉላቸው፡፡ ይህ ለኛ ለኢትዮጵያውያን የአንገት መሰበር ነው፡፡ ለዚህ ስም ግብረ ሰዶም አይመጥነውም፡፡ ፈጽሞ፡፡
  ከአድዋ ድል ጋራ፤ ከአኩስም አና ከላሊበላ፣ ከሐረር አና ከጎንደር ሥልጣኔ ጋር የተጠራ ስም ከዚህ አስነዋሪ ተግባር ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ፈጽሞ፡፡ ከያሬድ እና ከአባ ጊዮርጊስ፣ ከቴዎድሮስ አና ከምኒሊክ፣ ከኃይሌ እና ከቀነኒሳ፣ ከደራርቱ እና ከመሠረት ጋር የተነሣ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡"

  Very True. Dn. Dani, Egziabiher Yistilin.
  Antenis Egziabiher be-Egziabihernetu Yitebiqih.

  ReplyDelete
 35. "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!!

  ReplyDelete
 36. መሰብሰባቸው አይገርመኝም እኔ የምፈራው በህግ አንቀጹ ላይ አንዳይሰፍር ብቻ ነው፡፡የሃገሪቱ መሪ እንደሆነ ለአባይ ግድብ ማስፈጸሚያ ብር እንሰጠሃለን በህግ አንቀጹ ላይ ግን አስፍርልን ቢባል እሺ ከማለት አይቦዝንም ለዚህም ብልጣብልጥ ነን ብለው እንደ ምክንያት ያቀርቡታል ብዬ የማስበው ብሩን እንዲሰጡን በህግ እንዲጸድቅላቸው እናደርግና ግድቡ ሲያልቅ ደግሞ በህዝቡ ከፍተኛ ግፊት እና ጥያቄ መሰረት ከህጉ ዐንዲወጣ አድርገነዋል ከማለት ዐይቦዝኑም ፤አንደ አዲስ አበባ በከንቲባ አርከበ ዐቁባይ ገዜ ከኦሮሚያ ክልል ግዛት ተነስታ የነበረችና በሆላም አቶ አርከበ ዐቁባይ ሲወርዱ ደግሞ የተመለሰችበት አካሄድ አይነት፡፡ማስብ ያለብን ግን ህጉ ስራ ላይ ከዋለ በሆላ የሚፈጠረውን ችግር መቼም በምንም ነገር የማንመልሰው መሆኑ ነው፡፡ ሞኝ ብልጥ ሲሆን ማለት ነው ፡፡የፓለቲካ ቁማር ነው ያልከው አስተያት ሰጪ ግን ዐልገባህኝም፡፡

  ReplyDelete
 37. ደ/ን ዳንኤል በመጀመረያ ላመሰግንህ እወዳለሁ! በመቀጠል አብዘኞች ሰስተያያት ሰጭዎች ከስሁፈ ዎሰጥ አወጥተዉ ልክ እርሳቸው ያለሉት የመስል የደግምታል ሰተያያት ካለን እነደም ሀለትም መሰመረ ጽፈን ብናጋረዉ አንጂ ይሄ እከሌ አስተያያት አለሰጠም እነዳየባለበን ይመስል ቦታ ባናበካንሸሸበተረፈ ገን በዘ ሰለተባለላተ ስበሰሰባ ትላንና በ ራስ ሆቴል ስበሰባዉ ተጀምሮአል ከውብሰይት ላይ ለማገሸት እነደተምከረዉ ቅድመ ስብሰባዉ ምንም አይነት የግበረ-ስይጣን አጀንዳ እንላሄ ነዉ! ማን የወቃል ይዘሬ መሪወች ደም እየበለ እየጠጡ ህዘብ እየተጋፋ ስሄድ እንሱ ታግበዉ እያተመላላሱ በቻ ምኑ ቅጠ እሊናቸዉን ሸጠዉ የበሉ ሆ ኑ ! የሄኮ የሜያሳዬን ከጋዳፊ የተለዩ ያለመሆናቁንንና ነገ ለ ሌላም ነገር አሳልፈዉ ሌሰጠን ግድ እንደሌላቸዉ ነዉ! ወይ ጉድ! በፖለቴካቸዉ እትምጣባቸዉ እንጂ ገና መን አይተን በቍማችን ይሸጡናል--በእጃሁር እኮ አንም ተሸጠናል---የነ አጼ ቴዎደሮስ ሀግር እንዴህ መህንዋ እጀ እጅግ ያሳዝናል!

  ReplyDelete
 38. Dn. Daneil Kale hiwt yasemalen! talak sera new eyeseraih yalehew. God bless u , bless Ethiopia!!

  ReplyDelete
 39. "SEDOM GEMORA"

  I don't know what to say.I was shocked when I heard it.Is that necessary to let them to conduct this type of meeting with in our country?

  ReplyDelete
 40. በእግዚአብሄርም፣ በሰውም ዘንድ ነውር ነውና እንቃወማለን፡፡ አምላክ ከመአቱ ይጠብቀን!!

  ReplyDelete
 41. Dani yihe kebefitu atsatsafih leyet yalena tinish wered yale reasoning yalebet tsihuf newu !!! bezalay yanten hasab mikarenu asteyayetochn alayehum; yihem ine kezih betach yemagarawun comment post indemataregewu simetu adrobgnal bihonm ante kanebebkewu yibekagnal!!!

  First of all(just to make it clear) i believe in individual rights. No one should tell me what to do in my life as i don't want to order you in yours. And if u don't believe in individual right, stop reading my comment, you might find it offending to your thoughts.

  so if you believe in individual right, no one forced you to be Catholic, Orthodox, Muslim, atheist etc... no one forced you to follow EPRDF, CDU...., and similarly no one should force you to be homo, bi and hetero, as it is totally your right to exercise your choice and beliefs.

  I have not seen, read or heard any tangible argument from anti-homo individuals that is not associated with religion, culture or just plain hatred. The religion reasoning only works for believers, how about for Atheist's? what is your argument for some one who is not in the circle of believing in God?

  The culture reason only holds so long as the culture is stagnant. However, every culture in human history is evolving and changing through time. I don't think you still believe that women should not dress up shorts (which was literally our culture awhile back). It might not be our culture to support the idea of being homo or bi, but that argument could not hold long, it will eventually change. Some things which were considered as morally unethical just 10 years ago, are just normal those days.

  After all we have to understand that life is a matter of choice and doing your best to achieve those choices while respecting others' choices.

  But one thing that i would like to point out is that, if a homo person knock on my door and tried to persuade me in to his world (just like what the Jehovah witness individuals do), i wouldn't tolerate such action on my property and that would be enough for me to take some further measures. That's why i respect anyone's decision, so long as they respect mine.

  Last but not least, respect and argue against ideas, not against the person. "don't hate the player hate the game".

  ReplyDelete
 42. እኔ እኮ በጣም በጣም በጣም የሚገርመኝ እንሰብሰብ ማለታቸው ሳይሆን ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ለመቀነስ ነው የምንሰበሰበው ማለታቸው ነው፡፡ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በስብሰባ ሳይሆን ህገ እግዚአብሔርን በመጠበቅ ብቻ የሚጠፋ ነው፡፡ ሰዶምና ገሞራ የጠፉት በምን ይሆን?
  ለመሆኑ ስንት ወንድሞቻችን ናቸው በወንድ ተደፍረው የበሽታ ቁራኛ የሆኑት? ይህንን ደግሞ ፖሊስ ራሱ በማስረጃ የሚያውቀው ነው፡፡ የሚያስፈልገው በእንጭጩ መቅጨት ነው፡፡ በእርግጥ ለሃይማኖት ሰዎች ቀድሞ የተነገረ ትንቢት በመሆኑ አይደንቃቸውም፡፡ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ነገር እንደምንሰማም ቀድሞ የተፃፈ እውነታ ነው፡፡
  የኢትዮጵያን ጥፋት አታሳየን ውሰደን ብለው የተማፀኑ በበጎ አጠራር የተጠሩ እንዴት የታደሉ ናቸው፡፡

  ትግራይ ክፍለ ሃገር ውቅሮ ውስጥ ዲቦ ቅድስት ድንግል ማርያም የአንድነት ገዳም አለች፡፡ ከዚያ የመጡ አባቶች እንደነገሩኝ ሁልጊዜ በ9፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የበቁ ቅዱሳን ይሰበሰቡባታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የተሰዋውን መስዋዕት የተጸለየውን ጸሎት ያሳርጋሉ፡፡ ቦታዋም ምዕራገ ጸሎት፣ ምዕራፈ ቅዱሳን ተብላ ተጠርታለች፡፡
  እነዚህ ቅዱሳን በሚመላለሱባት በሚሰበሰቡባት አገር ስማቸውን ለመጥራት የሚያስጸይፉ ጉዶች ይሰብሰቡባት?
  ስንት እኛ የማናውቀው ምስጢር የሚከናወንባት አገር ናት ኢትዮጵያ፡፡ ስንት ስውራን፣ ስንት ነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ ላይ የደረሱ አባቶች ያሉባት፣ ስንት ሳር በቅሎባቸው ጤዛ ልሰው፣ ዳዋ ጥሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው ከፈጣሪ ጋር የሚገናኙባት አገር ናት ኢትዮጵያ፡፡
  በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን አድባራትና ገዳማት እስኪ እናስባቸው፡፡ በሁሉም ቤተክርስቲያናት ኪዳን ይደርሳል ፣እጣን ይታጠናል ፣ተአምረ ማርያም ይነበባል፡፡ በአብዛኞቹ ቅዳሴ ይቀደሳል ፣ማኅሌት ይቆማል፣ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ይደገማል፣ መልካ መልኩ ግብረህማማቱ ስንክሳሩ ይነበባል፡፡
  የካህናቱ፣ የመናንያኑ፣ የቅዱሳን አንስቱ ጸሎት የምእመናኑ የአባቶች የእናቶች እንባ ምኑ ይነገራል? በ7ቱ አጿማት አጋንንት ይቀጠቀጣሉ ፡፡ በስግደት፣ በፀበል፣ በምፅዋት፣ በትህትና፣ እንግዳ በመቀበል ፈፅሞ ዲያብሎስ ይባረራል በኢትዮጵያ ምድር፡፡
  ሌሎችም ሌሎችም፡፡
  ታዲያ ይህ የምንሰማው አያስለቅስም?

  አባቶቻችን ቅዱሳን እንደ ግያዝ አይነ ልቦናችን ይበራ ዘንድ የኢትዮጵያንም ክብር እንረዳ ዘንድ ጸልዩልን፡፡

  ከተቻለ የመጡትን ጉዶች የደብረሊባኖስን ወይ የሚጣቅ አማኑኤልን ጸበል እንዲጎበኙ ማድረግ ነው? ማን ያውቃል ለንስሃስ እንደሆን የተጠሩት?

  ReplyDelete
 43. Such thing is a shame for Ethiopia!It is not deserve not only for Ethiopia but also for the world!But such things are the sign of the last domes day.So please pray and apply our petition to God.

  The ruler of the world don't give us their ear to lesson when we ask them to stop such generation distracting exercise.We have applied to them many times about such stupid doing.hence it is better to wait the solution from God!

  ReplyDelete
 44. እጂግ በጣም አስነዋሪ ነገር ነው

  ReplyDelete
 45. እጅግ በጣም አስነዋሪ ሥራ ነው በአገሩቱ መሪ ሳይሆኝ
  በአባቶቸ አዘንኩ መለኰሰ ማለት ሞተ ማለት ነበር፡፡
  እንሱ ግን ምን እንደፈለጉ አላውቅም በዚህ ጉዳይ ላይ
  እራሳቸውን ካላጸድ መቼ ሊሆን ነው ምዕራፍ ባላውቅም
  በጐቸን ጠብቁ፣ ጥቦቶቸን አሰማሩ የተባሉት እንሱ ነበር
  ግን ምን ይሆናል ሳይሆን ቀረ በጣም አዝናለሁ በአባቶቸ
  መቼም ከዚህ የባሰ አይመጣም ነገር ግን ነገ ሌላ ነገር
  ቢመጣ አድርጉ ብለው የሚያዙና የሚገዝቱ ይመስለኛል
  አቡነ ጵጥሮስን ምሳሌ እንድያደርጉ እግዚአብሔር ይርዳቸው
  አዘንኩ አባት በማጣታቸን አዘንኩ ለቃሉ ጠበቃ በማጣቱ ወይ
  ቤተ ሳይዳ

  ReplyDelete
 46. "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!!

  ReplyDelete
 47. አወይ ሃገሬ

  አወይ ሃገሬ
  ዛሬስ ላልቅስልሽ
  አምርሬ
  ዛሬስ ጥይት ይግባ
  በግንባሬ
  ለክብርሽ ለስምሽ ስል
  ሃገሬ
  ስሟ በክፉ አይነሳ
  በአረመኔ ክብር አይወሳ
  ትኑርልኝ ሃገሬ ተከብራ
  ተለይታ ትኑር
  ከሰዶም ከገሞራ
  ይህ ከሆነ ስልጣኔ
  የነጮቹ ልምላሜ
  እምቢ ብያለሁ አሻፈረኝ
  ግንባሬን እንካ
  አካሌንም ቆራርሰኝ
  ይህን ከፉ አልቀበልም ብያለሁኝ
  ደግሞም እጣራለሁ
  ቴዎደሮስ ምንይልክ
  አቡዩ አባጊርጊስ ብያለሁ
  ሰዶምን ኑ ተመልከቱ
  በሃገራችሁ ሲያበራክቱ
  አቡነ ጴጥሮስ ና ተመልከት
  አገርህን ለነጭ አሞራ
  ሲያደርጓት የሳት እራት
  አወይ ሃገሬ
  ዛሬስ ላልቅስልሽ
  አምርሬ
  ዛሬስ ጥይት ይግባ
  በግንባሬ

  ReplyDelete
 48. ዲ.ዳንኤል
  ይህ ፈጽሞ በሀገራችን ሊፈፀም የማይገባ ነው፤ ሁላችን በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ከአሁኑ ማስቆም የምችልበትን መንገድ ማግኘት አለብን ”ሳይቃጠል በቅጠል” ካልሆነ ይህ የዛሬው ሥር ነገ የማንገረስሰው ነው የሚሆንብን እባካችሁ የኢትዮጽያ ሕዝቦች አሁን ነው መጮህ የሚያስፈልገው እየጠፋን ነው እኮ!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 49. dengel maryam hoy ebakeshegne ye aserat hagershen Ethiopian tebekey....

  ReplyDelete
 50. ቱ! ቱ! ቱ!

  ምነው ከሚስቴ በፊት እኔን ባስቀደመኝ፡፡

  ReplyDelete
 51. we are Ethiopians we are not the people who have not ethics so it is really sham for the country as well as to all of as sorry and sorry to our government that do this one

  ReplyDelete
 52. Yes indeed this is embarrassing and paining. We have our own image and prestige that is running under our blood vessel. May God savior Ethiopia

  ReplyDelete
 53. ከአድዋ ድል ጋራ፤ ከአኩስም አና ከላሊበላ፣ ከሐረር አና ከጎንደር ሥልጣኔ ጋር የተጠራ ስም ከዚህ አስነዋሪ ተግባር ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ፈጽሞ፡፡ ከያሬድ እና ከአባ ጊዮርጊስ፣ ከቴዎድሮስ አና ከምኒሊክ፣ ከኃይሌ እና ከቀነኒሳ፣ ከደራርቱ እና ከመሠረት ጋር የተነሣ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር ሊነሣ አይገባውም፡፡ ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡
  በአዲስ አበባ የልማት ጀግኖች ይሰብሰቡ፣ መሪዎች ይሰብሰቡ፣ አትሌቶች ይሰብሰቡ፣ አርቲስቶች ይሰብሰቡ፣ ደራስያን ይሰብሰቡ፣ የፖለቲካ መሪዎች ይሰብሰቡ፣ የባህል እና የእምነት መሪዎች ይሰብሰቡ፡፡ ባልገው ልጆቻችንን የሚያባልጉ፣ ያልበላንን የሚያክኩ፣ እየወጣነው ላለው ገደል ተጨማሪ ጉድጓድ የሚፈጥሩ ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው፡፡
  ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡

  ReplyDelete
 54. Daniel i see someone's comment above at 2:25PM. Please; Can you ask him
  1.what his moral question is on the idea?
  2.What values this meeting transfer for the next generatins?(Human right? Sorry to say) there are so many things on these issue)
  3.What his moral obligation to defend the idea?
  As to me you do your job,legally & morally. Egziabhere edemehen yarezemew, endetastemer, endetasaweken

  ReplyDelete
 55. አባመላ ይነሳ


  ለመሆኑ እነዚህ ሀገር እየመራን ነዉ የሚሉ ሰዎች ከምን የተፈጠሩ ናቸዉ
  ሃያ አመት ሙሉ ለኢትዮጵያ ዉድቀት የሚጥሩ የቆሸሸ ህሊና ያላቸዉ፡፡ ይህ የሚያጠነጥኑት ደባ የነሱን ልጆች የማይነካ መስላቸዉ ከሆነ ተሳስተዋል፡፡ እምነት ባህል የሃገር ፍቅር የሰው ፍቅር ወኔ የሌላቸዉ ከጋዳፊ ዉድቀት ያልተማሩ
  እነሱን የተሸከምንበት ትከሻችን ቆስላል ተልጣል በቃችሁ ልንላቸዉ ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 56. "Ante ende Tarik balemuya tinageraleh egna eyanebebin zim enilalen. Ethiopia egnan aferach min waga alew Dani. Bahilachin tefa, kuratochachin afer lebesu, Eminetachin malagecha hone, yehager simetachin wuha tedefabet, wegenachin hager leqo besew hager bayitewar hone....lelochim....egna gin zimita meretin. Engdih min keren yihon??? "

  ReplyDelete
 57. yemeriwochachinen ayin yabralin.

  ReplyDelete
 58. ልክ ነህ ዳንኤል ይህ ቀፋፊ ድርጊት የኢትዮጵያ ወጣቶች በሕይወት እያሉ በታምር አይደረግም። ጉድና ጅራት ወደሁአላ ነው እንዲሉ፡ ስንት ለሀገር የሚጠቅም ነገር እያለ! ይህን ኮርጀው ተመለሱ? ወደሁአላ ጉዞ! ብታምኑም ባታምኑም ይህን ነገር ከፈቀደ የመጀመሪያው ተጠቂ ማንም ሳይሆን እራሱ መንግሥት ነው። ግን አያደርገውም!!

  ReplyDelete
 59. ሰሞኑን በየድረ-ገጹ አበሾችን ወደየኮምፒውተር ሰሌዳቸው (ክትበ-ገበራቸው) እየገፋፋቸው ያለው በአገር ቤት ግብረ-ሰዶማውያን በኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ ሊያደርጉት የተዘጋጁበት ስብሰባ ነው።

  ስለዚህ ጉዳይ መጀመሪያ ያነበብኩት አዲስ-ሪፖርተር ባለፈው ዕሮብ ያወጣው ዘገባ ሲሆን፤ ይኼም የሃይማኖት አባቶች ጉዳዩን ለማውገዝ ያዘጋጁትን ውሳኔ ለጋዜጠኞች እንዳይስተላልፉ የጤና ጥበቃው ሚኒስትር ባልተገለጸ ምክንያትና ‘ዘዴ’ እንዳስጣሏቸው ያበሰረው አንቀጹ ነው። ከዚኽ ቀጥሎ ያነበብኩት በዳንኤል ክብረት እይታዎች ላይ “እሳቱ ከሌለ ጢሱ አይታይም” በሚል ርዕስ በዚያው ዕሮብ እለት ያሰፈረው መጣጥፍ ነው፡፡ ዳንኤል፣ ቅዳሜ ደግሞ “ይህ ስም ክቡር ነው” በሚል ርዕስ ጠለቅ ያለ ዘገባ አስነበበን።

  እነዚህ ትንተናዎች አያሌ አስተያየቶችን ስበዋል። አብዛኛዎቹ ተችዎች የዚህ ዜና አዎንታ ስሜታቸውን የቱን ያህል እንዳብሰለሰለውና እንዳሳረረው ከአጻጻፋቸው እንረዳለን። ግብረ-ሰዶማዊነት ከባህላችንም፣ ከሃይማኖታዊ እምነታችንም (በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስትና) ጋራ የተጻረረ እና በጥብቅ የተከለከለ፤አስጸያፊ ድርጊት እንደሆነ እየደጋገሙ አስፍረውታል። አልፎ አልፎም ወቅታዊው የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግም ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደሚከለክል ከነአንቀጹ በመጥቀስ ያስረዱንም አሉበት።

  ዳንኤል “ኢትዮጵያ የሃይማኖት ሀገር ናት፡፡ ከ90 በመቶ በላይ የሆነው ሕዝቧ በእምነቱ ግብረ ሰዶምን ይቃወማል ብቻ ሳይሆን ይጸየፋል፡፡ የሀገሪቱ ሕጎችም ግብረ ሰዶማዊነትን በወንጀልነት ይፈርጃሉ፡፡ ከሕዝቡ እምነት ብቻ ሳይሆን ከባህሉ ጋርም የሚጣረስ ጉዳይ ነው፡፡” ብሎ እቅጩን ከነገረን በኋላ ከዚኽ ለጥቆም “ግብረሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ፣ የግብረሰዶማውያንን መብት ካልደገፋችሁ አንረዳም እያሉ የሚያስፈራሩ ምዕራባውያን ኃያላን አሉ፡፡ ራሳችንን አጥተን የሚመጣ ርዳታ ለቀብር ማስፈጸሚያነት ብቻ የሚውል ነው፡፡ እናም እንዲቀርብን እንንገራቸው፡፡” በማለት የችግሩን መፍትሄ በከፊልም ቢሆን ሲጠቁም፤ ማንነታችንን እንወቅ፣ የሰፊውን ሕዝባችንን እምነትና ባህል የሚያረክሱ፣ የሚበክሉ፣ ባዕዳዊ ልምዶችን በስመ-ሥልጣኔ ወይም እርምጃ ለሣንቲም ብለን እየተቅበልን እራሳችንን አናዋርድ፣ አንግደል፣ አንቅበር እያለን ነው ያለው።

  አንዱ ተች ደግሞ ምዕራገ ጸሎት፣ ዲቦ ቅድስት ድንግል ማርያም በምትባለው ገዳም ያሉ አባቶች በየዕለቱ በመላ አገሪቱ ውስጥ የተሰዋውን መስዋዕት የተጸለየውን ጸሎት እንደሚያሳርጉ ሲነግረን፤ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈጸምባት ቅድስት ሃገር በተቃራኒው ርኩስ አስጸያፊ በሆነው በግብረ-ሰዶማዊነትም ስም አብራ መጠራት እንደሌለባት ሲይስታውሰን ሌላው ደግሞ (ስሙን እንኳን ያልነገረን ተቺ) የግል መብት ከሁሉም የበላይ እንደሆነና በግል ውሳኔ/ምርጫ ካቶሊክነት ወይም ኦርቶዶክሳዊነት ወይም እስልምና ወይም ሃይማኖተ-አልባ መሆን እንደምንችል ሁሉ፣ እንደግብረ-ሰዶማዊነትንም ያሉትን ተግባራት በግል መርጠን ማካሄድ መቻል መብታችን ነው ባይ ነው፡፡ ይኼኛው አስተያየት ሰጭ ታዲያ ይፋ ከተደረጉት አስተያየቶች መኻል በጸረ ግብረ-ሰዶማውያን የተሰነዘሩት አስተያየቶች፣ ከሃይማኖት ወይም ከባህል ወይም ዝም ብሎ የመጥላት መንፈስ ውጭ ሌላ ምንም ዓይነት አስተያየት እንዳላየ ይተነትንና ሃይማኖታዊ የሆኑት ቅራኔዎች ለአማኞች ብቻ የሚሠሩ፤ ባህልን የተመረኮዙት ቅራኔዎች ደግሞ እንደማንኛውም ባህል ከጊዜ ሂደት ጋር እየተለወጡ መምጣት የማይቀርላቸው ናቸው ይለናል።

  ታዲያ ይኼንን ሁሉ አንብቤ፤ እንደአብዛኛው ወገኔ እኔም በሀገሬ ላይ ያለኝ ተስፋ እየመነመነ፤ ውስጤ እየተቃጠለ፤ እንደኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ተከታይም፣ ወደፈጣሪ አምላኬም ‘እስከመቼ ፊትህን ታዞርብናለህ!’ ብዬ መጮኼም አልቀረም። የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንስ በተለየ ስለዚህ የግብረ-ሰዶማውያን እንቅስቃሴም ኾነ ከፍተኛ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ባለ-ሥልጣን የሃይማኖት አባቶች ላይ አደረጉ ስለተባለው ኢ-ዴሞክራሲያዊ የአፈና ተጽዕኖ ምን ብለው ይኾን ብዬ ብፈልግ፣ በሽምግልና በደከሙ ዓይኖቼ ስንፈት አልታይ ብለውኝ ካልኾነ በሰትቀር አንድም ነጥብ ላገኝ አልቻልኩም።


  ሰይፈ ገብርኤል ኪዳኔ

  ReplyDelete
 60. ተከታይ
  እኔን ታዲያ ወደዚህ ጽሑፍ የገፋፋኝ ይኼ ሁለተኛው አስተያየት ነው። በሃይማኖታዊ መሠረት የሚደነገግም ሆነ በዓለማዊ አስተዳደር በየጊዜው የሚተገበር ሕግ ሥር መሠረቱ የሚመነጨው ከተፈጥሮ ሕግጋትም መኾኑን መዘንጋት የለብንም። ለምሣሌ ያህል ይኼንን ጉዳይ የሚመለከተው የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ክፍል ሁለት ሲሆን ርዕሱ ‹‹ለተፈጥሮ ባሕርይ ተቃራኒ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች›› ነው የሚለው። እንግዲህ በሰገላዊም ኾነ፤ ሃይማኖታዊ አገላለጽ ግብረ-ሰዶማዊነት “የተፈጥሮ ባሕርይ” ነው ብሎ መሟገት ማለት በፍጡራን ውስጠ አካል፣ እንደ መተንፈስ፣ መመገብ እና የአካልን ብክነቶች የማስወገድ የመሳሰሉ ጠባያት ከንቁ-አዕምሮ ቁጥጥር ውጭ ለመራባት እና ራስን ከማጥፋት ለማዳን አብረውን የተፈጠሩ ግዴታዎች መሆናቸውን መካድ ነው። ሰው የተባለው ፍጡር ከተፈጥሮ ባሕርያቱ አንዱ ከተቃራኒ ፆታ ሰው ጋር ዘሩን የማርባት ግዴታውን ሟሟላት ከንቁ-አዕምሮ ውጭ የሚካሄድ ባሕርይ ነው። ይኼንን ደግሞ በግብረ-ሰዶማዊነት ማሟላት አይቻልም። አይ ግድ የለም! የግል መብት ስለሆነ ይፈቀድ ማለት ደግሞ ከተፈጥሮ ሕግ ጋር በመቃረን የሰው ልጅ ዘር ይጥፋ፤ እንዲጠፋም እናድርግ ማለት ነው።

  በልጅነት ዘመኔ ባልንጀሮቼን የማታክትበት፤ እኔም ብሆን አሁን ከበሰልሁ በኋላ መለስ ብዬ ስገመግመው እኔውኑ የሚያሳፍረኝ አንድ ጠባይ ይዤ ነበረ። ደግነቱ እንደማንኛውም የልጅነት ጠባይ የጧት ጤዛ ሆኖ ነው የቀረው። ለትንፋሻችን የምንጠቀመው ‘ኦክሲጂን’ የተባለው አየር በዓይናችን የማናየው፤ በእጃችን የማንዳስሰው ነገር ሆኖ፤ ዙሪያችንን ከቦ የሚገኝ እና ለመኖር የሚያስፈልጋቸው ፍጡራን ሁሉ የጋራ ንብረት ነው። በጎኑ ደግሞ ይኼን የጋራ ንብረት እኩል የመጠቀም መብት የያንዳንዱ ፍጡር ተፈጥሮአዊ መብት ሲሆን የባልንጀሮቼን ዓይን እስካልጠነቆልሁ ድረስ ዓይናቸው ስር ድረስ ጣቶቼን እያወናጨፍሁ በዓየር ላይ የመጠቀም መብቴን ካላሳመንኋችሁ እያልኩ አታክታቸው ነበረ። እውነትም የሰውን አካል እስካልነካን ድረስ (እንቅስቃሴያቸውን እየገታን እንኳ ቢሆንም) መብቴ በምንለው ነገር ሁሉ ላይ እንዳሻን የመጠቀም መብት አለን ማለት በዚያ ባልበሰለ፣ ጨቅላ አዕምሮ አስተሳሰብ (በተለይም የጡንቻ ድጋፍ አለው ብለን ካመንን!) ማሳመን ይቻል ይሆናል። ነገር ግን የኔ አስተሳሰብ ጉድለቱ፤ መብት ማለት የሌላውን፤ ሃይማኖታዊም ይኹን ባህላዊ ወይም ተፈጥሮአዊ መብት እስካልነካ ድረስ ብቻ መሆኑን አለመገንዘብ ነበረ። እያንዳንዱ ፍጡር በሰውነቱ ዙሪያ እስከተወሰነ ርቀት ድረስ በዓይን የማይታይ፤ በእጅ የማይዳሰስ “የተፈጥሮ መንፈሱ (life-force) ወይም በባህላዊ ገለጻ፣ ውቃቢው የሚያስፈልገው ቦታ ሲወረርበት አይወድምም መብቱም እንደተነካበት ይቆጠራል።

  እንግዲህ ለዚህ መጣጥፍ ያነሳሳኝ ሰው “የግል መብት ከሁሉም የበላይ ስለሆነ፣ እንደግብረ-ሰዶማዊነትንም ያሉትን ተግባራት በግል መርጠን ማካሄድ መቻል መብታችን ነው” ሲል ልክ እኔ በዚያ በርጥብ አስተሳሰቤ “ዓይንህን እስካልነካሁ ድረስ በዓየሩ ላይ ጣቶቼን ማወናጨፍ መብቴ ነው” እል እንደነበረው አይነት እጅግ የተዛባ እና ያልበሰለ አመለካከት ነው። በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም ሕብረተ-ሰብ መገበያያ ተብሎ ጥቅም ላይ የሚገኘው በታተመ ወረቀት ወይም ከብረታ ብረት በተሠሩ ሣንቲሞች ነው። እኔም ሆንኩ ይኼ ወንድሜ ‘አይ እኔ መገበያየት የምፈልገው በአሞሌ ጨው ወይም አዝራር ነው” ማለት የግል መምረጥ መብታችን ቢሆንም ከሰው ፍጥረት ጋር እስካለን ድረስ የማይሠራ ባዶ-ቅል ኃሣብ ሆኖ እናገኘዋለን። ከኢትዮጵያ ሕብረተ-ሰብ ጋር ተቃራኒ የሆነ ተግባርንም በዚያ ሕብረተ-ሰብ መኻል የማካሄድ መብቴ ነው ማለትም እንደዚሁ ውዳሴ ከንቱ የኾነ አመለካከት ነው።

  የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተፈጥሮ ግዴታዎች ተነስቶ በሃይማኖትም፤ በባህልም ሆነ በዘመናዊ አስተዳደር ሕግጋትን መሥርቶ በውዱ ሲተዳደርባቸው እዚህ የደረሰ ሥልጡን ሕብረተ-ሰብ ነው። በሕብረተ-ሰብም ደረጃ ማሻሻልም ሆነ መለወጥ የሚያስፈልጋቸው ባህሎችም ሆኑ ልምዶች ቢኖሩትም ማንነቱን በማያዛባ እና ሁሉንም ወገን እኩል በሚጠቅም (ለዚያውም ተፈጥሮአዊ ግዴታን በማይቃረን መልኩ) እራሱ በራሱ ይለውጣቸዋል ወይም ያሻሽላቸዋል እንጂ ባዕድ ምዕራባውያን ባስቀመጡት መስፈርት ሊሆን አይችልም።

  ይኼ እንግዲህ ‘የግል መብት’ በሚል አጠራር የምንመጻደቅባቸውን አዲስ ፈሊጦችን ሁሉ ያካትታል። አብሮም ልንረዳው የሚያስፈልገው ሌላው አዎንታ ደግሞ፤ በዴሞክራሲ ሥርዓት እንኳ ሕዝቡን የመምራትን ሥልጣን ጨብጠናል የሚሉት መሪዎችም ቢሆኑ የኢትዮጵያ ሕብረተ-ሰብ ተፈጥሮአዊንም ኾነ፤ እምነትን ወይም ባህልን ተመርኩዘው የተመሠረቱትን ሕግጋቱን በስሙ የማስከበር ሥልጣን እንጂ የመደምሰስ ወይም ሲደመሰስ ዝም ብሎ የማየት፤ የመለወጥ፤ የመጣስ ወይም የማስጣስ መብት የላቸውም። በዴሞክራሲ ሥርዓትም ሥልጣንን የጨበጡት ለኢትዮጵያውያን አገልግሎት እንጂ ለምዕራባውያን እያጎነበሱ ክብሩን ለማስገፈፍ እንዳልሆነ በፍጥነት ሊገነዘቡት ይገባቸዋል። አንዳንድ ነገሮች እጅግ አሰቃቂ፤ ነውር እና አይነኬ ናቸውና።

  ሰይፈ ገብርኤል ኪዳኔ
  ለንደን ኅዳር 25 ቀን 2004 ዓ/ም

  ReplyDelete
 61. samie ke chichenya

  Dear D.Daniel

  why should we call them our fathers? they are a discrase to our church? why should we to them to be blessed by their cross? why do we call them bitsu,abune,and all the names when they don't deserve them? i think u probably tell me it is the synodos job? they all corrupt and discrase just like the head. I beleive there is 1% of them good why don't they say something? It is a very bad diseses

  ReplyDelete
 62. I wonder the youths who demonstrates to oppose the meeting and through to jail for an hour!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 63. loule egeziabehar ysdomawyanen astesaseb kemederegts yatefalen ebakachu legna sayhon lelegochchen enaseb enetseley enekawem,

  ReplyDelete
 64. To all Dear Ethiopian Brothers and Sisters,

  It is with great disappointment that I am writing this message. As Ethiopia and other African Countries are overwhelmingly mutilated by recurrent poverty and debilitating wars that subsequently underdeveloped Africa, it could have been a call for African youth to come together to make our predicaments part of history instead of ridding on us. Unfortunately enough however, we chose to bestow with incapacitating culture of homosexuality in our land. In country of lords of poverty, where even we are unable to drink pure water leave alone getting to bath ourselves for the act of homosexuality, choosing to domesticate homosexuality as a new wave of culture buy-in not only dwarf us but also question us our morality. It doesn't matter how you try to rationalize and justify your homosexuality, it is an act of being inhuman and against the law of Nature and God too. Letting this new wave of cultural colonization in Ethiopia is an act of aggression and the Government should call a national emergency for this.
  Dear Beloved Ethiopians,
  If we let this thing happen on the holy land of Ethiopia, not only we lost our sense of humanity but also it is a self-defeat. I am calling the Ethiopian government, and the General public to stand up together and curse this anti-biology, anti-nature, anti-God act of war. Homosexuality is indeed an act of war against humanity. We need to think about this: if homosexuality was part of our biology at least in the Ethiopian soil, why we haven't witnessed it back in time and in our own experiences? So, why the urgency now?
  Whatever intellectual discourse people may bring to justify this act, it is actually a dangerous demonic act which I think is the work of evil people who hate themselves and hate humanity.

  ReplyDelete
 65. ene lezi asafari dergit teteyaqiw mengest new by negn.lemen egna ethiopia weyan nen yemanem rekash astesaseb maragefiya aydelenem.yech ager bezuwoch bezu mesewatenet yekfelulat ager nat.egna ehtiopia weyan nen yetekeberech ager hizboc nen.gebresedomawi agerachen lay lidereg aydelam senesemaw yekefenal egna ethiopia weyan nen.lemeriwochachen leb yestelen.betam yemikef nerer egziyo------

  ReplyDelete
 66. "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!
  "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!
  "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!
  "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!
  "ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው"፡፡ "ይህ ስም ክቡር ስም ነው!

  ReplyDelete
 67. ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡ በመንፈስ ያልበለጸገ ሕዝብ
  በቁሳዊ ነገር ሊበለጽግ አይችልም፡፡ ቢበለጽግም ዘላቂ አይሆንለትም፡፡
  መንግሥት እንደ መንግሥት ይህንን ተግባር መከልከል ነበረበት፡፡ ይህ ስም ከግብረ ሰዶም ጋር አብሮ
  እንዳይነሣ መከልከል ነበረበት፡፡

  ReplyDelete
 68. አቤቱ ያባቶቻችንን ቃልኪዳን አስበህ ይህ ትውልድ ከሰዶም እሳት የሚያመልጥበትን ማስተዋልና እምነት ስጠው!ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መቅደስከ!!!
  ቃለ ህይዎት ያሰማልን መምህር!!!

  ReplyDelete
 69. ወገኖቼ ይህ ነገር ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊነት ጋር እንደማይሄድ የአገሪቱን ክብር የሕዝቦቿንና የታላላቆቿን ስም ማንሳትም አያስፈልግም፡፡ እንኳን ከታላቅነታችንና ከክብራችን ከነጩ ድህነታችንና ከውርደታችን ጋርም አይሄድም፡፡ የሚያሳዝነኝ ነገር ግን መንግስት ፈጽሞ ፈጽሞ ሕዝቡን አለማወቁ ነው፡፡ ወይም ሊያውቅ አለመፈለጉ፡፡ እኔ የምለው አንድ በስልጣን ላይ ያለ መንግስት ሕዝቡን ለማወቅ እንዴት ነው 20 ዓመት የማይበቃው? አንዳንድ ጊዜ ከውጭ የመጣ የቅኝ ገዥ የሚያስተዳድረን አይመስላችሁም? 97 በመቶ የሆነው ሕዝብ የማይፈቅደውንና እንደ ክብረነክ የሚያየውን ነገር መፈጸም ወይም ማስፈጸም ወይም ሲፈጸም ዝም ማለት ምን የሚሉት ንቀትና ድፍረት ይሆን?
  ወገኖቼ አደራ የምላችሁ ስለእምነታችሁ፣ ስለራሳችሁና ስለልጆቻችሁ ወይም ስለቤተሰባችሁ ደህንነት ስለአገራችሁ ክብር ብላችሁ ይህን ነገር እስከመጨረሻው እንቃወም በተገኘው መንገድ ሁሉ እንቃወም የአንድ ሰሞን የሆይ ሆይ ወሬ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር በየሙያችን በያለንበት ይህን ስብሰባ የፈቀደውን ደፋር እንፋረድ ፡፡

  ReplyDelete
 70. በእውነት በዚህ በተፈጠረው ነገር በጣም እናዝናለን፡፡ አፀያፊነቱና በህግ ጭምር ድጋፍ የሌለው መሆኑ የተደነገገ ሆኖ ሳለ በእርዳታ የተሰበሰበ ገንዘብ ሊተካው የማይችለውን ሞራል የሚያደቅና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የሚያደርገውን አፀያፊ ተግባር እውቅና ለመስጠት ለሚደረግ ስብሰባ መንግስት ደጋፊ ሆኖ በመቅረቡ እንደዜጋ ማንም ህሊና ያለው ሰው ዝም የሚለው አይመስለኝም፡፡ በአዲስ አበባ በድፍረት የሚመጣባቸውን ለመቀበል ወስነው ሰልፍ የወጡትን የቤተክርስቲያናችንን ወጣቶች አደንቃቸዋለሁ፡፡ ሌሎቻችንም ሰልፍ ለመውጣት ድፍረት ብናጣ እንኳን ባገኘነው መንገድ ሁሉ ይህን አገር የሚያረክስ፣ ትውልድ የሚያጠፋና እጅግ ነውር የሆነ ተግባር ማውገዝ አለብን፡፡ ዝም ብለን የምናየው አይደለምና እግዚአብሔር ይርዳን!!

  ReplyDelete
 71. zeraf!!zeraf!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!embi lagerie!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 72. IN ETHIOPIA?...REALLY, IT IS SHAME FOR AFRICA! ye'abune Petros atsimu yiwoganalieko...his last breath destroy our lives just like sedom-ena-gemora. INDEED, NO EXCUSE FROM THE PUNISHMENT FROM GOD, WHETHER IT IS A POLITICS OR NOT. MAY GOD SAVE THESE PEOPLE.

  ReplyDelete
 73. hagerachnin ytebkln...kalehwot yasemaln !

  ReplyDelete
 74. I wish to know what the President feels when he heard about this. I always respect him for his speech ending with ' God Bless Ethiopia'.

  I am really sorry for this happen in Ethiopia where we have a President who believes in God.

  God Bless Ethiopia

  ReplyDelete
 75. ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡
  ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡
  ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡
  ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡
  ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡
  ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡
  ከማንኛውም ሥልጣኔ እና ዕድገት በፊት የመንፈስ ልዕልና ይቀድማል፡፡

  ReplyDelete
 76. ''ማስተዋል ሀገርሽ ወዴት ነው?'' አረ አስተዋይ ካድሬ ያለክ! ድሮ ስስንዮስ ከአገራችን ሀይማኖት ውጪ የሆነ ትእዛዝ ተቀብሎ ነበር እስካሁንም ''እህ! በስስንዮስ ዘመን!'' እየተባለ በክፉ ታሪክ እስከዛሬ እየተነሳ ነው። አሁን ያለ መንግስትስ ለምን እንዲህ ዓይንት መጥፎ ትውስታ እንዳይተው አይጠነቀቅም? አሁንኮ ችግሩ ከላይ ያለ አሜን በሎ ከተቀበለው ታች ያለን እንዴት ነው ምናደርገው? ዶ/ር ቴዎድሮስ የሀይማኖት አባቶችን ''አፍ አፍ ዝም'' ካሉዋቸው ---

  ReplyDelete
 77. የምን ታመጣለህ ዘመን ትውልዶች አይዞአችሁ፡፡

  ReplyDelete
 78. "የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ። ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ " ሮሜ 1:20-28

  ReplyDelete
 79. ወንድሜ ዲ/ን ዳኒ ጸጋውን ያብዛልህ በቅርቡም ወደኛ ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤሜሬቶች በሚደረገው ዓመታዊ ጉባኤ እንደምትገኝ ስለሰማሁ በሰፊው እንደምንማር ተስፋ አለኝ

  ይህ ሁሉ ሊሆን ግድ ነው ያለው የጌታችን እና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይመስለኛል ይህን ሳያዩ ያለፉ ምንኛ ብጹዓን ናቸው ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ከሃጢዓታችን መብዛት እንደሆነ እንመን መልስ ከመንግስት ሳይሆን ሁሉን ቻይ ከሆነው እንድናገኝ አጥብቀን እንጸልይ የበጀውን ያሳየን

  ReplyDelete
 80. Ethiopiwinetin ena Gibre sodomawinetin basebikut gize Alekesiku,,,,,
  please we need to organize, pray and act now.

  ReplyDelete
 81. ጸሀፊውንም ሆነ በአስተያየት የተካፈላችሁትን የኢትዮጵያ አምላክ ይባርካችሁ፡፡ አገራችንንም ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 82. ዳኒ እንደሰለጠነ ሰው አስተያየትህን አከብራለሁ፡፡ በብዙ ነገር አድናቂህ ነኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ግን ትክክል አልሰራህም፡፡ የጾታ ተራክቦ ፍላጎት/ ምርጫ ከተፈጥሮ ያገኘነው ነው፡፡ ለምሳሌ ተፈጥሮ የአንተን ፍላጎት በዚህ መልክ አድርጎት ቢሆን ኑሮ ከሴት ጋር ሳይሆን ከወንድ ጋር ትኖር ነበር፡፡ ከዚህ ውጭ እናንተ በባህላችሁ ኑሩ፡፡ እኛ አልደረስንባችሁም፡፡

  ጽድቅና ኩነኔ ወይም የፈጣሪ ቁጣ ወይም የፈጣሪ ሕግ የሚያሳስባቸው እንደናንተ አይነቶችን በፈጣሪ መኖር የሚያምኑትን ብቻ ነው፡፡ በፈጣሪ የሚያምን ግብረ-ሰዶማዊ አይሆንም፡፡ ክርስቲያን ወይም ሙስሊም ነኝ ብሎ ግብረ-ሰዶም የሚፈጽም እሱ አጭበርባሪ ነው፡፡ እኛ ግን በፈጣሪ መኖር እስካላመን ድረሰ የፈጣሪ ህግ አያሳስበንም፡፡

  እናንተ ማድረግ ያለባችሁ እኛን ማስተማርና ማሳመን እንዲሁም ፈጣሪ እራሱን እንዲገልጽልን መጸለይ ብቻ እንጅ የእኛን መብት ማፈን አይደለም፡፡ እናንተ የማመን መብት እንዳላችሁ ሁሉ እኛ ደግሞ ያለማመን መብት አለን፡፡ ዲሞክራሲ ማለት እኮ የማመንና የማምለክ መብት ብቻ ሳይሆን ያለማመንም መብትም ጭምር ነው፡፡ በዲሞክራሲ የማታምኑ ከሆነ ደግሞ እንደ መለስ ባለ አምባገነንና ጨካኝ ገዥ ስትሰቃዩ ትኖራላችሁ፡፡ እነ አውሮፓና አሜሪካ እኮ በጥሩ መሪዎች የሚመሩትና ጥሩ ስርዓት ያላቸው ስለሰለጠኑና በዲሞክራሲ ስለሚያምኑ ነው፡፡ ሰለዚህ እኛ እናንተን እስካልነካን ድረስ በራሳችን የግል ሰውነት እንደፍላጎታችን እንድንኖር ፍቀዱልን፡፡

  ReplyDelete
 83. yichin kidist midir litareksu yemetachuuuuu enante weyolachu yekidusan amalk EGZIABHER yifaredachuhal
  Emebetachin hoy ye asrat agerishin Ethiopian tebikilin!!!!!

  ReplyDelete
 84. LO TU SEBHAT!!!OH GOD PLEASE BE WITH US AND BRING YOUR JUGEMENT.

  ReplyDelete
 85. ትክክል ብለሃል:: DANI
  በእርዳታ ሰበብ ግብረሰዶምን ለማስፋፋት የሚያደርጉት ትግል በጣም የሚያሳፍር ነው::
  እኔ የምለው ... የጣሊያን መንግስት ከፓፓ ጆቫኒ ፓዎሎ ጀምሮ አሁንም በፓፓ ራዚንገር ተቀባይነትን አለማግኘቱን እየገለጸ አሁንም ጥያቄአቸውን አላጸደቀም:: ለምን የአገራችን መሪዎችስ በተመሳሳይ ሁኔታ ነገሩን ወደፊት እንዳይሄድ ለማድረግ አይሞክሩም? እነ ላልይበላ ምን ይሉ?
  Sara

  ReplyDelete
 86. እግዚአብሔር ይባርክህ የምታደርገዉ አስተዋፅኦ እጂግ ጥሩ ነዉ በርታ ያፅናህ
  ዳንኤል

  ReplyDelete
 87. እረ ያሳፍራል ወገን

  ReplyDelete
 88. እውነትም ይህ ስም ክቡር ነው እግዚአብሔር ሀገራችንን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 89. ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው፡፡
  ይህ ስም ክቡር ስም ነው፡፡

  ReplyDelete
 90. እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ " ሮሜ 1:20-28 Egezio abetu bemehereteh bizat yiqer belen.Yalante tesfam yelen.

  ReplyDelete
 91. Yihinini new Meshesh?Hagere Hoy,Wogene Hoy,Hizibe Hoy,Mechershachi Min Yihon?ግብረ ሰዶማውያን እንዲሰበሰቡ መፍቀድ ግን በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በባህልም ነውር ነው፡፡Betarikim Metifo Tebasa Letiwulid Metew new::

  ReplyDelete
 92. እውነት ነው፤ የምንሰማውና የምናየው ነገር ከአዕምሯችን በላይ ነው። ስለእኛ በመስቀል ቤዛ የሆነልን መድህን ዓለም ሀገራችንን እና ህዝባችንን ከዚህ ፀያፍ ነገር ያድን፤ እባካችሁ የድንግል ልጆች የዘወትር ፀሎታችን ስለዚህ ነውር መጥፋት ይሁን!

  ReplyDelete
 93. እግዚአብሔር ይስጥልን ጸጋውንም ያብዛልን።

  ReplyDelete
 94. እግዚአብሔር ይስጥልን ጸጋውንም ያብዛልን።

  ReplyDelete
 95. Ethiopia yemilew simi tera simi ayidelemi
  Hi hi simi syitera bizuwechu Ethiopiyawiyan demachew yimokali
  Simetachew yinirali
  Nerivachewinim yinezirachewali
  Lik new ene beliribu bamericaw tv lay lelaw were bejoroye sayakachili Ethiopia yemilewin kali sisema gini sira layi mehoneni hulu resichew midinew yehagereni simi semahu silachew anduwa yeminigist balesilitani Ethiopiawiyiun legenizebi sitili . Agibitaw wezete neberi bicha ewineti New
  Yihi simi hayali New

  ReplyDelete