Friday, December 2, 2011

ኩዋሻኮር

click here for pdf
በምግብ እጥረት በተለይም ደግሞ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት በሚጠቁ ሰዎች ዘንድ የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ በሽታው የያዘው ሰው የማቅለሽለሽ ስሜቶች እና ድካም ይታዩበታል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በሽታው የያዘው ሰው ሆዱ በልቶ ቦርጭ እንደ ያዘው ሰው ይነፋል፡፡
በርግጥ ኩዋሻኮር አካላዊ በሽታ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ኅሊናዊ በሽታም ሊሆን ይችላል፡፡ ኅሊናም ኩዋሻኮር የሚይዘው ጊዜ አለና፡፡ በቂ መረጃ የማያገኝ በተለይም ደግሞ የተመጣጠነ መረጃ የማያገኝ ኅሊና በኩዋሻኮር በሽታ ይጠቃል፡፡
 የኩዋሻኮር በሽታ የያዘው ልጅ ምግብ ሊያገኝ ይችል ይሆናል፡፡ ያንን ምግብ ግን እርሱ ምግብ አለው እንጂ ሊመገበው የማይገባ ምግብ ይሆናል፡፡ በአካባቢው የምግብ እጥረት በመኖሩ የተነሣ ወይንም በድህነቱ ምክንያት ሆድ ለመሙላት እንጂ ለሰውነቱ ግንባታ የማይጠቅሙትን ምግቦች ያሰባስባል፡፡ ይህም ሆዱን ከመንፋት በስተቀር ለአካል ጥንካሬው የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም፡፡
ኅሊናዊ ኩዋኻኮር የሚይዘው ሰውም እንዲሁ ነው፡፡ ምናልባት መረጃ ያገኝ ይሆናል፡፡ ያንን ግን እርሱ ወይንም ሌላ አካል መረጃ ነው አለው እንጂ ለኅሊናዊ ግንባታ የሚጠቅም፣ መንፈሳዊ ዐቅም የሚፈጥር እና ለአእምሮአዊ ጤንነት የሚበጅ መረጃ ላይሆን ይችላል፡፡ ምናልባት በአካባቢው የመረጃ እጥረት ተከስቶ ወይንም ሰውዬው መረጃዎችን በድህነቱ ምክንያት ባለማግኘቱ ተከስቶበት ሊሆን ይችላል፡፡
አንድ ሰው ጤንነቱን ለመጠበቅ የሚጠቅመው አንድን ምግብ በብዛት መብላት አይደለም፡፡ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግቦችን መመገብ እንጂ፡፡ ለአንድ ማኅበረሰብ ኅሊናዊ ጤንነትም ከአንድ ወገን የሚመጣ አንድ ዓይነት መረጃ ብቻውን አያገለግለውም፡፡ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚቃኙ ልዩ ልዩ ዓይነት መረጃዎች እንጂ፡፡ ምግብ ለመብላት ብቻ አይበላም፡፡ ወይንም ምግብ መበላት ያለበት የሚራብ ሆድ ስላለ ብቻ አይደለም፡፡ ከሆነ ሆድን በቀላል ነገር መሙላት ይቻል ነበር፡፡
የሀገሬ ሰው «ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል» ይላል፡፡ ሆድን ለመሙላት ጎመን ቀቅሎ እስኪ ጠግቡ መብላት ብቻ በቂ ነው፡፡ ነገር ግን ዳገቱ ላይ ሲደረስ ጎመን ኃይል እና ብርታት ሆኖ አያሻግርም፡፡ ያን ጊዜም ሰውዬው መጥገቡን እንጂ አለመመገቡን ያውቀዋል፡፡
እንደዚሁም ሁሉ የሚያይ ዓይን፣ የሚሰማ ጆሮ ስላለ ብቻ ለዓይን እና ለጆሮ የሚታይ እና የሚሰማ ነገር አይደለም የሚያስፈልጋቸው፡፡ ወይንም በሌላ ቋንቋ እንድናየው እና እንድንሰማው ሆኖ የቀረበ ነገር ሁሉ ያጠግብ ይሆናል እንጂ ጤና አይሰጥም፡፡ ሰው ለዕውቀቱ፣ ለምርጫው፣ ለስሜቱ፣ ለጥበቡ፣ ለኑሮ መንገዱ፣ ለፍልስፍናው፣ ለንቃቱ፣ ለርዕዮተ ዓለሙ፣ ለተዝናኖቱ፣ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ዓይነት መረጃዎችን ይፈልጋል፡፡ ያንን ሲያገኝ ነው ማኅበረሰብ ጤናማ የሚሆነው፡፡
በክርስቲያን ሙስሊም የአብሮነት ጉዞ ውስጥ የሚታይ አንድ መልካም ምሳሌ አለ፡፡ ክርስቲያኑ ድግስ ሲደግስ ለሙስሊሙ የሚሆን ምግብ በሙስሊሙ ሕግ እና ባሕል መሠረት ያዘጋጃል፡፡ ሙስሊሙም ድግስ ሲያዘጋጅ ለክርስቲያኑ የሚሆን ምግብ በክርስቲያኑ ባህል እና ሕግ መሠረት ያዘጋጃል፡፡ ደጋሹ ሙስሊም ከሆነ የክርስቲያኑን ምግብ እንደማይበላው እያወቀ ግን ለሚበሉት ለክርስቲያኖች ሲል ያዘጋጀዋል፡፡ ደጋሹ ክርስቲያን ከሆነም እንዲሁ፡፡ የማንበላው ምግብ ለምን ይዘጋጃል አይሉም፡፡ በመረጃ ሥርዓታችንም ይህ ባህል ቢሠርጽ እንዴት መልካም ነበር፡፡
በጾም ምግባችን በየዓይነቱ፣ በፍስክ ምግባችንም ማኅበራዊ የሚባሉ ምግቦችን የፈጠርንበት ምክንያት ቢመረመር ስለ ኩዋሻኮር በሽታ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳለን ያመለክታል፡፡ ሆድን በቀይ ወይንም በአልጫ፣ በቅቅል ወይንም በጥብስ ሞልተቶ ከማግሣት ከሁሉም ዓይነት ምግቦች በመጠኑ በመብላት ጤናን መጠበቁ እጅግ የተሻለ መሆኑን ማኅበረ ሰባችን ተረድቶታል ማለት ነው፡፡
ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የሠርግ ብቻ ሳይሆን የልቅሶ ቤቶቻችን እንኳን ቀይ ወይንም አልጫ ብቻ እየሠሩ በአሳላፊ በኩል ከመጨለፍ ይልቅ ቡፌ ደርድሮ እየመረጣችሁ የሚበቃችሁን አንሡ ማለትን እየለመዱት ነው፡፡ ቡፌ ባህላችን እየሆነ ከመምጣቱ የተነሣም ታላላቅ ምግብ ቤቶች እንኳን በዚህ እና በዚያ ወቅት ቡፌ እናዘጋጃለን እያሉ ደንበ ኞቻቸውን እስከ መሳብ ደርሰዋል፡፡
ለምን?
መመርመር ያለብን ይኼንን ነው፡፡
ሕዝባችን ውጥንቅጥ ሕዝብ ነው፡፡ የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የአመለካከት፣ የቋንቋ፣ የብሔር ውጥንቅጥ ነው፡፡ እነዚህ ውጥንቅጦች ደግሞ ውጥንቅጥ ፍላጎት እና ውጥንቅጥ ምርጫን ይፈጥራሉ፡፡ ይህንን ውጥንቅጥ ፍላጎት እና ምርጫም በአልጫ ወይንም በቀይ ወጥ ማትካት አይቻልም፡፡ ባለሞያዎቻችን ይህንን ተገንዝበውታል፡፡ ስለዚህም ለኅብር ሕዝብ ኅብረ ብዙ አማራጭ ማቅረብን ፈለጉ፡፡ እናም አደረጉት፡፡
በየዓይነቱ ወይንም ማኅበራዊ ሲመገቡ ብዙ ዓይነት ወጦች በአንድ ትሪ ይቀርቡልዎታል፡፡ እናንተ አምስት ሆናችሁ ብትሄዱ ቢያንስ አንድ የሚወድዱት የምግብ ዓይነት በማዕድዎ ውስጥ አያጡም፡፡ በአንድ ማዕ ሆናችሁ፣ ሁላችሁም የምትፈልጉትን መርጣችሁ፣ የማትፈልጉትን ደግሞ ለሚፈልገው ትታችሁ፣ ባለ መስማማት ተስማምታችሁ ትመገባላችሁ፡፡
ወደ ቡፌውም ስንመጣ ዋናው መነሻ ሃሳቡ በአንድ ዓይነት ምግብ ሁሉንም ዓይነት ፍላጎቶች ማርካት አለመቻሉ ነው፡፡ እናም ሁሉም ሰው የሚፈልገውን እና የሚበቃውን ከጠረጲዛው ላይ ያነሣል፡፡ የማይፈልገውን ይተዋል፡፡ ምክንያቱም እርሱ ያልፈለገውን የሚፈልግ ሌላ ተመጋ አለና፡፡ ሁሉም ከአንድ ጠረጲዛ ያነሣል፣ ግን የሚፈልገውን መርጦ፣ በአንድ አዳራሽ ይበላል፣ ተስማምቶ፡፡
ይህ ባህላችን ወደ መረጃውም ሊመጣ ይገባዋል፡፡ ለአንድ ማኅበረሰብ እንደ ምግብ ሁሉ ኅሊናውን የሚገነቡለት መረጃዎች ያስፈልጉታል፡፡ የሚነበቡ፣ የሚታዩ፣ የሚሰሙ፣ የሚጎበኙ፣ የሚነኩ፣ የሚዳሰሱ፡፡ እነዚህ ማኅበረሰቡን የሚገነቡ መረጃዎች በዓይነት እና በብዛት ተሟልተው መቅረብ አለባቸው፡፡ ዓይነት እና ብዛት፡፡ ብዙ ዓይነት መጻሕፍት፣ ብዙ ዓይነት መጽሔቶች፣ ብዙ ዓይነት ጋዜጦች፣ ብዙ ዓይነት የጥናት መጽሔቶች፣ ብዙ ዓይነት የመረጃ መረቦች ያስፈ ልጉናል፡፡ ያለ በለዚያ የኅሊና ኩዋሻኮር ይይዘናል፡፡
የተለያዩ ዓይነት የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች፣ የተለያዩ ዓይነት የርዕዮተ ዓለም አማራጮች፣ የተለያዩ ዓይነት የታሪክ ትንታኔዎች፣ የባህል ጥናቶች፣ የትምህርት አማራጮች፣ የኪነ ጥበብ ውጤቶች ያስፈልጉናል፡፡
ሰው የኅሊና ኩዋሻኮር ከያዘው ደካማ አእምሮ ይኖረዋል፡፡ አመዛዛኝ አይሆንም፡፡ ስሜታዊነት ያጠቃዋል፡፡ ከሆዱ አርቆ ማሰብም ይከብደዋል፡፡ ሰው በኩዋሻኮር ምክንያት ዐቅመ ደካማ ሲሆን ከአካባቢው ርቆ መራመድ ይቸግረዋል፡፡ ኅሊናም ኩዋሻኮር ከያዘው ከአካባቢው ወጣ አድርጎ ማሰብ ይከብደዋል፡፡ ጎጠኛ፣ መንደርተኛ የሚሆነውም ለዚህ ነው፡፡ ኩዋሻኮር በምግብ እጥረት የሚመጣ ነውና የኩዋሻኮር በሽተኛ የዘወትር ምኞቱ መመገብ ነው፡፡ ኅሊናም ኩዋሻኮር ሲይዘው ከመብላት እና ከመጠጣት ውጭ ሌላ ነገር አይታየውም፡፡
ኩዋሻኮር የያዘው ሰው ሆዱ እንደሚነፋው ሁሉ የኅሊና ኩዋሻኮር የያዘውም ሰው ኅሊናው ይነፋል፡፡ ያውም በትዕቢት እና በአጉል ኩራት፡፡ በቀሰም የተነፋች ዶሮ ይላ እናቶቻችን፡፡ ዶሮ ታርዳ በላይዋ ላይ የቀረውን ፀጉር መሰል ነገር ለማስለቀቅ ወረቀት አቀጣጥለው ይለበልቧታል፡፡ ታድያ በደንብ እንድትለበለብ በቀሰም ተነፍታ ማባበጥ አለባት፡፡ የዶሮ አካል እብጠት እንጂ ውፍረት አይደለም፡፡ ኅሊናው በኩዋሻኮር በሽታ የተያዘ ሰው ያብጣል እንጂ አይወፍርም፡፡
ሰው ሁለት ነገር ነው፡፡ ሥጋ እና ነፍስ፡፡ እናም መብላት እና መጠጣት ብቻ ሊያሟላው አይቻለውም፡፡ እንዲያውም የነፍስ ጠባይዐዓት መናገር፣ ማሰብ፣ ማወቅ እና ህያው ሆኖ መኖር ናቸው፡፡ እናም ሰው  ሥጋው ኩዋሻኮር እንዳይዘው የተመጣጠነ ምግብ፣ ጤናማ ምግብ፣ በቂ ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ፤ ኅሊናው ኩዋሻኮር እንዳይዘውም የተመጣጠነ መረጃ፣ ጤናማ መረጃ ብሎም በቂ መረጃ ያስፈልገዋል፡፡
ሰው መናገር አለበት፡፡ መወያየት፣ መነጋገር፣ ሃሳቡን መግለጥ አለበት፡፡ ነፍስ ያለቺው ፍጡር ነውና፡፡ ሰው ማወቅ አለበት፡፡ ማሰብ መቻል አለበት፣ ህያው ሆኖ ለመኖር መታገልም አለበት፤ ነፍስ ያለቺው ፍጡር ነውና፡፡
ለማሰብም ሆነ ለማወቅ፣ ለመናገርም ሆነ ህያው ሆኖ ለመኖር ደግሞ ወሳኙ መረጃ ነው፡፡ የሚነበብ፣ የሚታይ፣ የሚመረመር፣ መረጃ ወሳኝ ነው፡፡ ለማንበብ፣ ለመማር፣ ለመወያየት፣ ለማሰብ፣ ያልታደለ ሰው እንዴት ህያውነቱ ሊረጋገጥ ይችላል፡፡ የዚህ አለመኖር መሞት፣ የዚህም እጥረት የኅሊና ኩዋሻኮር የሚሆነውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡

25 comments:

 1. "የኩዋሻኮር በሽታ የያዘው ልጅ ምግብ ሊያገኝ ይችል ይሆናል፡፡ ያንን ምግብ ግን እርሱ ምግብ አለው እንጂ ሊመገበው የማይገባ ምግብ ይሆናል፡፡ በአካባቢው የምግብ እጥረት በመኖሩ የተነሣ ወይንም በድህነቱ ምክንያት ሆድ ለመሙላት እንጂ ለሰውነቱ ግንባታ የማይጠቅሙትን ምግቦች ያሰባስባል፡፡ ይህም ሆዱን ከመንፋት በስተቀር ለአካል ጥንካሬው የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም፡፡
  ኅሊናዊ ኩዋኻኮር የሚይዘው ሰውም እንዲሁ ነው፡፡ ምናልባት መረጃ ያገኝ ይሆናል፡፡ ያንን ግን እርሱ ወይንም ሌላ አካል መረጃ ነው አለው እንጂ ለኅሊናዊ ግንባታ የሚጠቅም፣ መንፈሳዊ ዐቅም የሚፈጥር እና ለአእምሮአዊ ጤንነት የሚበጅ መረጃ ላይሆን ይችላል፡፡ ምናልባት በአካባቢው የመረጃ እጥረት ተከስቶ ወይንም ሰውዬው መረጃዎችን በድህነቱ ምክንያት ባለማግኘቱ ተከስቶበት ሊሆን ይችላል፡፡"

  Yemigerm Agelalets new. Dn. Dani Ante Astemiren; Yihew Egnam Mekari Astemari Yalasatan Egziabihern Eyamesegen Enmaralen.
  Dani Egziabiher Tsegawun Yabzalih.

  ReplyDelete
 2. ሰው የኅሊና ኩዋሻኮር ከያዘው ደካማ አእምሮ ይኖረዋል፡፡ አመዛዛኝ አይሆንም፡፡ ስሜታዊነት ያጠቃዋል፡፡ ከሆዱ አርቆ ማሰብም ይከብደዋል፡፡ ሰው በኩዋሻኮር ምክንያት ዐቅመ ደካማ ሲሆን ከአካባቢው ርቆ መራመድ ይቸግረዋል፡፡ ኅሊናም ኩዋሻኮር ከያዘው ከአካባቢው ወጣ አድርጎ ማሰብ ይከብደዋል፡፡ ጎጠኛ፣ መንደርተኛ የሚሆነውም ለዚህ ነው፡፡ ኩዋሻኮር በምግብ እጥረት የሚመጣ ነውና የኩዋሻኮር በሽተኛ የዘወትር ምኞቱ መመገብ ነው፡፡ ኅሊናም ኩዋሻኮር ሲይዘው ከመብላት እና ከመጠጣት ውጭ ሌላ ነገር አይታየውም፡፡

  ReplyDelete
 3. Danny,the first paragraph is fun with real thoughts,yap,if we don't feed our mind,in this age of information...we ain't going to be confident and manage thing timely.i usually use to eat my diet from Google,may God bless Him..:-),and thank you Danny ,u rise perfect thoughts~

  ReplyDelete
 4. Dani, this is a very nice piece. I really like the way you try to convey your messages without confronting those who'r against free press and free media.
  Hope you'll continue like this.

  ReplyDelete
 5. tthank you dn daniel

  ReplyDelete
 6. Great stuff Daniel, wanted to say something but could not find a nice statement myself to appreciate all your analogies here. You are a good writer Dani, keep it up!

  GOD bless you,

  ReplyDelete
 7. wow i really likeit keepit up dani wr soooooo proud of uuuuu

  ReplyDelete
 8. Deacon Daniel, and hizib mereja endayagegn ketafene yemikerbilet mereja hulu be haset lay yetemeserete kehone,bizu aynet nen tebilo lemeleyayachin ber kekefetin,yihe hizb "kuwashakor" yeyazew ayimesilegnim...begid beshitaw yiyazih medhanitun wised tebale enji Elik bizu aynet nen bilen gizeyachinin kematifat and endehonin tenegagiren andinetachinin enatenkir..ye and agers ew and new, biher bihereseb eyalin eyatalelin anikefafilew,

  ReplyDelete
 9. We are denied from access of information from free sources. we Ethiopians are starved of lack of information. We are forced to relay only on ETV, Ethiopian herald and other few. We need freedom of speech, free sources of information,....God Bless Ethiopia!

  ReplyDelete
 10. ሰው የኅሊና ኩዋሻኮር ከያዘው ደካማ አእምሮ ይኖረዋል፡፡

  ReplyDelete
 11. i always wonder when u were going to have a say about this stuff. this is great but we need more. u guys /writers/ have more responsibilities.

  I just wanna tell u that u r a great person for writing what u think about every issue.

  ReplyDelete
 12. Yes you are right my brother, That is the problems of our socio-economic and political life of Ethiopia.This May be because of our culture.I mean our social culture, political culture.... Specially at this moment things are very surprised.Some times things makes me so upset.
  A man whose thinking is different with another ideology, educational policy, agricultural policy, political affiliation and attitude, is considered as a violator of constitution, a terrorist. Generally they interpret on the benefit of them.I was read some articles on ADDIS NEGER, whose country after all. I believe that Ethiopia is a home of diversity.These people is a right to have different idea, opinion and thought.I am really sorry for that, both of them is not applicable to Ethiopia. The system makes the Ethiopian peoples as lairs,cheaters,killers .... However, the bibles says that Both the color of the tiger and the behavior of Ethiopians peoples is always never change. Is that true? May be we are run out of Holly Bible.

  ReplyDelete
 13. What an interesting article!!!. I believe that this blog is started just to protect us from "Ye Hilina KUWASHAKOR". Thank you very much D/n Daniel. You are doing your best. God bless you.

  ReplyDelete
 14. sewoch bezih tsihuf laboratorynet hilinachew ke kowashekor netsa mehonun endiyaregagitu be hakimu D.dani sim eteyikalehu!...enea chek adirgea resultu ...........
  memihir dani...bebeshitaw letegodut hulu egiziabihear kebarekew ayimiroh medihanit mamretun yakoyilin amen!!!
  "sami12" negn

  ReplyDelete
 15. ዮናስ አርአያ ተገኝDecember 3, 2011 at 2:40 PM

  ሰላም ለከ ውድ ወንድሜ፤ ዳንኤል ለጤናህ እንደምን አለህ?

  ለቤተክርስቲያን ያለህን ፍቅር ስለምወደው ነው ከአቡነ ሺኖዳ ቀጥሎ እንደ መርህ የማይህ። ብዙ ላታውቀኝ ትችላለህ፤ ለንደን ቅ/ሥላሴ ቤተክርስቲያን መተህ ኮርስ አስተምረኸን ነበር።

  "ከልብ ለምወዳት ሰ/ት/ቤቴ" ያልዃትን ጦማር አይተህ ሁል ግዜ ከረጅሙ መንፈሳዊ የህይወት ተሞክሮህ ምክር ባይለየኝ እጅግ ይጠቅመኛል ብዬ አምናለሁ።

  http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ገና ታናሽ ልጅ ነኝና ብዙ ምክር እገዛ ከናንተ እጠብቃለሁ።

  ReplyDelete
 16. engidih mn yibalal...sewoch kuwashekor lalemeyazachew yemimeremir laboratory be hakim dani tekekefitowal!...enea temermirea......
  memihir dani ewiketina tibeb kefitu yemikedut amilak ... yebarekew ayimirohin bekewashekor letegodaw twilid yemihon migib siyabesilibet yinur!! amen!!!Sami negn
  I am happy of my first comment on your blog!!

  ReplyDelete
 17. አንተ በርክትልን። Mamush,MN

  ReplyDelete
 18. ውገን ዳንኤል!!! ህይል የእግዚአብሄር ስለሆነ ኢትዪጵያም ህይሏ በፌትም በኋላም አለም እስክሚያልፈም ድረስ መድህኒዓለም ነው፣ አሁን ነው በአገርም በአለምም ዞሪያ የምንኖር የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት በተውስነ ቀን/ ስዓት ውድ ህያው ዓምላካችን እግዜአብሄር ስለአገራችን/ህዝባችን በአንድነት መጬህ ያለብን፣ ይሂንን ዳቢሎስና መልክተኞቾን መዋጋት ያለብን ፣፣*** ኢትዮጵያ እጅዏችዋን ውድ እግዚአብሄር ትዘረጋለች ***

  ReplyDelete
 19. አምላከ እስራኤል ፀጋዉን ያብዛልህ ልክ ልኬን ነገርከጝ ወንድምዬ! ኑርልጘ ጨምሮ እድሜ ይስጥህ!

  ReplyDelete
 20. We,Ethiopians are deprived of information by this Government.

  ReplyDelete
 21. አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አንተን በእምነት ላይ ብቻ ዐንድታተኩሪ የፈልጋሉ ይሄ ነገር ትልቅ ስህተት ነው ምክንያቱም የጴንጤ እምነት ካየን የማይሳተፎበት፤የማይገቡበት፤የማይነካኩት ነገር የለም ለዚህም ነው ከአርቶዶክስ በተሻለ በመስፋፋት ላይ የሚገኙት የትምህርት አሰጣጣቸው አና የህይወት ዐካሄዳቸው መጨረሻው ባያምርም፡፡ የአርቶዶክስ ዕምነትም ከፓለቲካ፤ከመሀበራዊ ግንኙነት ከመሳሰሉት አንጻር መፈተሽ እና መዋሀድ አለባት፡፡የየራሳችን ፕሮፌሽን እንካን ቢኖረን ጠቅላላ እውቀት ግን አስፈላጊ ነው፡፡የኢኮኖሚ ሁኔታ ፤ስግብግብነት ለተለያየ መረጃ እንዳንሻ ጥላ ሆነዋል፡፡

  ReplyDelete
 22. Dear Daniel,

  One can not see like a horse who is pulling a cart. We should be engulfed with different sort of information, which enable us for a better judgement. Human being can not live only with food. Those who have junk foods will die soon without analyzing the surrounding world.

  ReplyDelete
 23. ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ይሏቹሃል ይሄ ነው፡፡ የተማረ ይግደለኝ፡፡

  ReplyDelete