Wednesday, December 28, 2011

ድልድይ ገንቢዎች


(click here for pdf) በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ የቅዱስ እንድርያስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ የሆኑት ቄስ እንድርያስ ቶምሶን 2011 «Christianity in the UAE´ የተሰኘ ምርጥ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡
መጽሐፉ የዛሬዋን የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን ጨምሮ በመላው የዐረቡ ዓለም ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ክርስትና ይተርካል፡፡ በመካከሉ ክርስትና እንዴት ሊጠፋ እንደቻለ በቁፋሮ የተገኙ የአርኬዎሎጂ መረጃዎችን እያጣቀሰ መልስ ለመስጠት ይሞክራል፡፡ ከዚያም ዛሬ በዓረብ ኤምሬት ያለውን የክርስቲያን ሙስሊም ግንኙነት ይተነትናል፡፡
እንድርያስ ቶምሰን መጽሐፉን ሲያጠናቅቁ እንዲህ ብለው ይጮኻሉ «Where are the bridge - builders?»
እስኪ እኔም ጩኸታቸውን ልቀማቸውና በሀገሬ እንደ እርሳቸው «ድልድይ ሠሪው ሆይ የት ነው ያለኸው?» ብዬ ልጩኽ፡፡

Monday, December 26, 2011

ውሾቹን «ተው» በሏቸው


በኦሮምኛ አንድ ድንቅ ተረት አለ፡፡ በአንድ የኦሮሞ መንደር ውስጥ ሮቤል መገራ የሚባሉ ጥበበኛ ሽማግሌ ነበሩ፡፡ አንድ ቀን የሁለት ጎረቤታሞች ንብረት የሆኑ ሁለት ውሾች ሲጣሉ ያያሉ፡፡ እኒህ ጥበበኛ ሽማግሌም «እነዚህን ውሾች እንገላግላቸው፤ ያለበለዚያ ችግራቸው ለሁላችንም ይተርፋል¿ በዓለም ላይ ችግር የሚነሣው ከአጥንት በላይ ማሰብ በማይችሉ ውሾች የተነሣ ነው» ይላሉ፡፡ በአካባቢው የነበሩ ሽማግሌዎች እና መንገደኞችም በሽማግሌው አባባል ተገርመው «ሁለት ውሾች ተጣልተው ምን ሊያመጡ ነው» እያሉ ሳቁባቸው፡፡

Thursday, December 22, 2011

መንፈሳዊነት ጠገግ ወይስ ሕይወት?

click here for pdf 
በዓለም ላይ በሃይማኖት መንገድ አያሌ የጽድቅ ሥራዎች ተሠርተዋል፤ በተቃራኒውም በሃይማ ሽፋን አያሌ ግፎች ተሠርተዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን የሕይወት መንገዳቸው ሳይሆን የሕይወት ጠገጋቸው በማድረጋቸው ምክንያት፡፡ የእምነቱን ሕግ እና ሥርዓት ለማክበር ሳይሆን በእምነቱ ስም ሊገኙ የሚችሉ ጥቅሞችን ለማነፍነፍ በመጠጋ ታቸው የተነሣ፡፡ ለፖለቲካ፣ ለኢኮኖሚ እና ለሥልጣን ዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሲሉ ሃይማኖትን ተጠግተው ለሃይማኖታቸው ሳይሆን በሃይማኖታቸው ይጠቀማሉ፡፡

Tuesday, December 20, 2011

የባላንጣዎች ደርግ


Doris Kearns Goodwin የጻፈቺውን Team of Rivals የሚለውን ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ሰሞኑን እያነበብኩት ነበር፡፡ መጽሐፉ ስለ ታላቁ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ስለ አብርሃም ሊንከን የተጻፈ ነው፡፡ በአሜሪካ ታሪክ እንደ አይከን ከሚታዩ መሪዎች አንዱ ነው አብርሃም ሊንከን፡፡
አብርሃም ሊንከን ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ሲወዳደር እጅግ የሚንቁት እና ብቃቱን የሚጠ ራጠሩት ተቀናቃኞች ገጥመውት ነበር፡፡ ከራሱ ከሪፐብሊካን ፓርቲም ሆነ ከዴሞክራቲክ ፓርቲ በሞያም፣ በልምድም፣ በታዋቂነትም እንልቃለን ብለው ከሚያስቡ ተቀናቃኞች ጋር ነበር የተፎካከረው፡፡
በወቅቱ የነበሩ ሚዲያዎች የአብርሃም ሊንከንን መመረጥ ዕድለኛ ስለሆነ ነው ነበር ያሉት፡፡ ምክንያቱም ተፎካካሪዎቹ ከእርሱ የተሻሉ ናቸው ተብለው ይታሰቡ ስለነበር ነው፡፡ አንድ በጥብቅና ሞያው እጅግም ያልታወቀ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አንድ ዙር ብቻ ያገለገለ፣ ለሁለት ጊዜያት ያህል ለሴናተርነት ተወዳድሮ ያልተሳካለት ሰው ፕሬዚዳንት ሲሆን ሚዲያዎች ምን ያድርጉ፡፡

Thursday, December 15, 2011

ስለ ታቦተ ጽዮን የማናውቀው

የአኩስም ጽዮን ያለቺበት እና እቴጌ መነን ያሠሩት መቅደስ

(click here for pdf) ሰሞኑን የአኩስም ጽዮን ያለቺበት እና እቴጌ መነን ያሠሩት መቅደስ እያፈሰሰ ነው የሚል ዘገባ በመውጣቱ አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙኃን ታቦተ ጽዮንን ለማየት ዕድል ይፈጥራል እያሉ ማውራት ጀምረዋል፡፡
ይህ ሁሉ የተዛባ ዘገባ የአኩስም ጽዮንን እና የአኩስም ሕዝብን ጠባይ ካለማወቅ የመነጨ ይመስለኛል፡፡ በዘመናዊ ታሪካችን የአኩስም ጽዮን ከነበረችበት መቅደስ ስትንቀሳቀስ ይህ የመጀመርያዋ አይደለም፡፡ በዐፄ ፋሲል ዘመን ከተሠራው ማረፊያዋ እቴጌ መነን ወዳሠሩት ማረፊያ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ተንቀሳቅሳለች፡፡ አንዳንድ ሚዲያዎች እንዳሉት ያን ጊዜ ለመታየት አልቻለችም፡፡

Wednesday, December 14, 2011

እንድንሟላ እንተጋገዝ

(click here for pdf) አንድ ቀበጥ ልጅ የነበራት አንዲት እናት ነበረች፡፡ ገጽታዋ ሁሉ በእሳት የተለበለበ ነበር፡፡ ያያት ሁሉ ይገረማል፡፡ አንዳንዱም ደንግጦ ይሸሻል፡፡ በተለይ ልጇ በእናቱ ገጽታ ስለሚያፍር አብሯት መታየትም ሆነ ትምህርት ቤት አብራው እንድትሄድ አይፈልግም ነበር፡፡ ለአንዳንድ ጓደኞቹ እናቴ ሞታለች፣ ለሌሎቹም እናቴ ውጭ ሀገር ሄዳለች እያለ ነበር የሚነግራቸው፡፡
ከፍ አለ፡፡ ከኮሌጅም ወጣ፡፡ ትልቅ ባለ ሥልጣን ሆነ፡፡ በየሚዲያውም ስሙ ይጠራ ነበር፡፡ ሰዎችም ከእርሱ ጋር መገናኘትን እንደ ብርቅ ያዩት ነበር፡፡ መቼም ቢሆን ግን ጓደኞቹንም ሆነ ሌሎች ወዳጆቹን ወደ ቤቱ ለማምጣት አይደፍርም ነበር፡፡ በድንገት ወደ ቤቱ ለመጡትም ቢሆን ያቺን ምስኪን እናቱን የቤት ሠራተኛዬ ናት እያለ ነበር የሚያስተዋውቃቸው፡፡

Monday, December 12, 2011

ኤፍ ኤሞቻችንን መልሱልንclick here for pdf 
ትናንትና በአንድ የኤፍ ኤም ራድዮ የሚተላለፍ ፕሮግራም ታክሲ ውስጥ ሆኜ እየሰማሁ ነበር፡፡ «ጋዜጠኛው» ቀብሩ በትናንትናው ዕለት ስለተፈጸመ አርቲስት ተናገረና «rest in peace ብለናል» አለ፡፡ የአፍ ወለምታ ወይንም ልማድ ነው ብዬ ዝም አልኩ፡፡ አሁንም ስለ ሌላ ስለ ዐረፈ ሰው ተናገረና ያንኑ ደገመው፡፡ ይኼኔ ደነገጥኩ፡፡ ይኼ የኤፍ ኤም ሬዲዮ በአማርኛ ቋንቋ ለሕዝበ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ፕሮግራም ነው፡፡ አሁን «ነፍስ ይማር» የሚለው የአማርኛ ቃል የሚጠፋው ጋዜጠኛ እንዴት ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጉዳዮች ሊያነሣ የሚችለው? ወይስ
የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አናግሪያቸው
እንደሚለው የሠርግ ዘፈን እንግሊዝኛ ማወቅ የዕውቀት መለኪያ ነው? ለነገሩ እርሱ ምን ያድርግ «ቢሾፍቱ አውቶቡስ? ብሎ መጻፍ ሲቻል «ቢሾፍቱ ባስ» ብሎ ጽፎ በከተማዋ ውስጥ በኩራት በሚዞርባት ሀገር፣ «ልዩ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ስፔሻል ክትፎ» «ተራ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ኖርማል ክትፎ» ተብሎ የጉራጌ ክትፎ እንግሊዛዊ በሚሆንባት ሀገር «ነፍስ ይማር» አለማወቅ ነውር ላይሆን ይችላል፡፡

Wednesday, December 7, 2011

«ያለ ግብረ ሰዶም ርዳታ የለም»


 
(click here for pdf) ዛሬ የወጣው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኦባማ ለግብረ ሰዶማውያን የሰጧቸውን ልገሳ ይዞ ወጥቷል፡፡ አሜሪካ ለሌሎች ተቋማትም ሆነ ሀገራት በምትሰጠው ርዳታ ተቋማቱም ሆኑ ሀገራቱ ለግብረ ሰዶማውያን መብቶች መጠበቅ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ እንደምታስገባ፣ የግብረ ሰዶማውያንን መብት እንዲከበር ለማድገረግ የውጭ ርዳታዋን እንደምትጠቀም መግለጣቸውን ጋዜጣው አትቷል፡፡
ይህንን ተከትሎም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ሂላሪ ክሊንተን ለዲፕሎማቶቻቸው የግብረ ሰዶማውያንን መብቶች እንዲያስጠብቁ እና የመብት ጥሰቶችንም ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

Tuesday, December 6, 2011

2 ሚልዮንኛ


ይህ ብሎግ ከተጀመረ ጀምሮ አያሌ አንባብያን ከመላው ዓለም እንደሚከታተሉት ይታወቃል፡፡ በአንድ መቶ ሁለት ሀገሮች የሚገኙት እነዚህ ተከታታዮች አስተያየት እና ጥቆማ በመስጠት፣ ሃሳብ እና ቁሳቁስ በመለገስ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፡፡
እነዚህ ተሳታፊዎች ቁጥራቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጥቶ ዛሬ ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ላይ የአንባብያኑ ብዛት 2 ሚልዮን ደርሷል፡፡
ሁላችንንም እንኳን ደስ ያለን፡፡

የሕይወት ታሪኬለቤተ መጻሕፍ
አዘጋጅ( ፊታውራሪ አመዴ ለማ (መጋቢት 1913 ( 2001 ዓም)
ኅትመት( 2003 ዓም
ዋጋ( 60 ብር
ፊታውራሪ አመዴ ለማ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የንግድ እንቅስቃሴ፣ ፖለቲካዊ ጉዞ፣ የሕግ አወጣጥ፣ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ሽምግልና እና ቅርስ ላይ የራሳቸውን አሻራ መተው የቻሉ ሰው ናቸው፡፡

Saturday, December 3, 2011

ይህ ስም ክቡር ነው


ኢትዮጵያ የሚለው ስም ተራ ስም አይደለም፡፡ ብዙ ሚሊዮኖች እንዲሠው ያደረገ ስም ነው፡፡ አያሌዎች በስፖርት አደባባይ ካገኙት ድል በላይ ይህ ስም ሲጠራ አንብተዋል፡፡ ይህ ስም በቅዱስ መጽሐፍ ከአርባ አራት ጊዜ በላይ የተጠቀሰ ነው፡፡ ይህ ስም ሲጠራ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ደማቸው ይሞቃል፣ ስሜታቸው ይንራል፣ ነርቫቸውነም ይነዝራቸዋል፡፡
ይህ ስም ከረሃብ እና ከእርዛት፣ ከድህነት እና ከችግር ጋር ሲነሣ የማያመው ዜጋ የለም፡፡ በዚህ ስም ሲለመንበት የማይቆስል ዜጋ የለም፡፡ በአንፃሩ ይህ ስም በክብር ሲነሣ ልቡ የማይሞቅ ሞራሉም የማይ ነሣሣ ዜጋ የለም፡፡ ተድባበ ጥላሁን ስለ ካዛንችስ የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት በጻፈው መጽሐፉ ላይ አንድ ግሩም እውነታ ይነግረናል፡፡ አብዛኛው ወደ ሴተኛ አዳሪዎቹ ቤት የሚመጣው ሰው የሚቀንሰው መቼ ነው? ለሚለው የነገረን ነገር፡፡