Monday, November 28, 2011


መጽሐፍ አዟሪው ሊቅ
 
            እንግዲህ መቃብር ጠንክረህ ተማር
            ድጓ ተሸክሞ መጣልህ መምር
           አራት ሰው ሞተ ተቀበረ ዛሬ
           ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ መዋሥዕት ዝማሬ
እነዚህን ግጥሞች ትዝ ያሉኝ አዲስ አበባ፣ ሃያ ሁለት አካባቢ "በታ" ሕንፃ ሥር ካለው ካልዲስ ቁጭ ብዬ ነው፡፡ ከፊቴ የመጽሐፍ ቁልል የተሸከመ ወጣት ቆሟል፡፡ ደጋግሜ መጽሐፍ ገዝቼዋለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን እነዚህን ዕውቀት የሚያከፋፍሉ ወጣቶችን ለመርዳት ስል በተቻለው መጠን ከእነርሱ መግዛት ደስ ይለኛል፡፡ ምን ዓይነት መጻ ሕፍት እንደምፈልግ ስለገባው እየመረጠ ማሳየት ጀመረ፡፡ ሁለቱን ገዛሁት፡፡
 ንግግሩን ስሰማው የቤተ ክህነት ለዛ አገኘሁበትና ለምን አልጠይቀውም አልኩ፡፡
«የቤተ ክህነት ትምህርት ተምረሃል?» አልኩት
«በመጠኑ» አለ በኢትዮጰያዊው ትኅትና፡፡ የቤተ ክህነት ሰው መሆኑ ገባኝ፡፡ የቤተ ክህነት ሰው ባይሆን ኖሮ «በሚገባ» ነበር የሚለው፡፡
«ምን ምን ተምረሃል?»
                      ዝም ብሎ አንገቱን አቀረቀረ፡፡
            «ደስ ካላለህ አትመልስልኝ» አልኩት፡፡
         «ድጓ ተምሬያለሁ» ሲለኝ መብረቅ እንደወረደበት ሰው የከሰልኩ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡
                 «የት?»
               «ቤተ ልሔም»
                         «አስመስክረሃል»
                «ነበረ»
             «ርግጠኛ ነህ»
አንዳች ነገር ከኪሱ ጎረጎረና አወጣ፡፡ የተጣጠፈ የምስክር ወረቀት፡፡ በግሩም የብርዕ አጣጣል የተቀመረ፡፡ እውነትም ድጓ አስመስክሯል፡፡ አንድ ስሙን የረሳሁት ገጣሚ በአንድ ወቅት ለልመና ከፊቱ አንድ ሰው ይቆማል፡፡ የዐቅሙን ከለገሰው በኋላ እንደኔ ነገር ነገር ብሎት ስለ ማንነቱ ይጠይቀዋል፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ ነዳይ የቅኔ መምህር ኖሯል፡፡ እናም እንዲህ ብሎ ገጥሞ ነበር፡፡
የሳንቲም ድቃቂ የሰጠው ስስቴ
ለካስ ሊቁ ኖሯል የቆመው ከፊቴ፡፡
ይህ ሰው ቤተ ልሔም ወርዶ ድጓ ብቻ አልተማረም፤ ቅኔ እና አቋቋምም ተምሯል፡፡ የተሻለ ሥራ ይገኛል ሲሉት አዲስ አበባ መጣ፡፡ በየቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ጠና፡፡ በአንዳንድ አድባራት መቼም መጥተው የማይቀድሱ ደጅ ጠኚዎችን በአሥር ብር እየቀጠሩ የሚያስቀድሱ፣ ደመወዙን ግን እነርሱ የሚወስዱ ሰዎች አሉ፡፡ ከእነርሱ ጋር ጥቂት ዓመት ሠራ፡፡ ገንዘብ አጠራቅምና ጉቦ ነገር ሰጥተህ ትቀጠራለህ አሉት፡፡
እርሱ ገንዘብ ሲያጠራቅም የጉቦው መጠን ሲያድግ፣ እርሱ ገንዘብ ሲያጠራቅም የጉቦው መጠን ሲያድግ ሊደራረሱ አልቻሉም፡፡ ከዚያም በላይ ደግሞ የደጅ አስጠኚዎችን ግልምጫ እና ጫና መቋቋም አቃተው፡፡ ድሮስ የተማረ ሰው ችግር ይኼ አይደለ፡፡ ኅሊናውን ለሆዱ ማስገዛት ይከብደዋል፡፡
ሲያማርር የሰማው አንድ ጓደኛው ለምን መጽሐፍ እያዞረ እንደማይሸጥ ነገረው፡፡ አስቦት አያውቅም ነበር፡፡ ጓደኛው ልምዱን አካፈለው፡፡ እርሱም ቢሆን ቀላል ሰው አይደለም፡፡ አሁን ሜክሲኮ አካባቢ መጽሐፍ የሚያዞር የቅዳሴ መምህር ነው፡፡ እንዲያውም እርሱ ጎጃም ውስጥ በአንድ ደብር ወንበር ተክሎ የተወሰኑ ደቀ መዛሙርትንም አፍርቷል፡፡ የተሻለ ሥራ ፍለጋ መጥቶ ይኼው እዚህ ቀረ፡፡
ሦስት ብሩን አወጣና መጽሐፍ ማዞር ጀመረ፡፡ ምንም እንኳን ተሸክሞ ማዞሩ፣ ፀሐዩ፣ የአንዳንድ ሰዎች ተረብ አስመራሪ ቢሆንም ሠርቶ ማግኘቱ፣ ከግልምጫ እና ቁጣ ነጻ መውጣቱ፣ እግረ መንገዱንም መጽሐፍ ለማንበብ መቻሉ እርካታን ይሰጠዋል፡፡
የድጓው ሊቅ እንደነገረኝ ከሆነ በአዲስ አበባ ውስጥ መጽሐፍ ከሚያዞሩት ወጣቶች ብዙዎቹ ቢያንስ የአንድ ወንበር ሊቅ ናቸው፡፡ እንጀራ ሆኖባቸው ከየኔታነት ወደ መጽሐፍ አዟሪነት ተለውጠው ነው፡፡ የተማሩት ትምህርት ለጽድቅ እንጂ ለእንጀራ ሊሆናቸው አልቻለም፡፡
እንዴው ለመሆኑ ግን እነዚህ መጽሐፍ ተሸክመው እባካችሁ አንብቡ እያሉ የሚለምኑት ወጣቶች በኢትዮ ጵያዊ ዕውቀት የጎለመሱ መሆናቸውን ገምተን ዕናውቃለን? አንዳንዶቻችን እንገላምጣቸዋለን፤ ሌሎቻችን አንብቡ ባሉ የለመኑን ያህል እንቆጥረዋለን፤ አንዳንዶቻችንም እናሾፍባቸዋለን፡፡
እንዲያውም በአንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ እነዚህ ወጣቶች በሁለት እጆቻቸው መጻሕፍት በመያዛቸው እጆቻ ቸው እየረዘሙ ነው ተብሎ ሲቀለድባቸው ሰምቻለሁ፡፡ ጫት በጉያው፣ ሲጋራ በጣቱ ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ያልወረደበት መዓት በእነዚህ ወጣቶች ላይ መውረዱ የእነርሱን ማንነት ሳይሆን የእኛን የአመለካከት ውርደት የሚያሳይ ነው፡፡
ብዙዎቻችን ሥጋ ቤቶችን አድነን እንሄዳለን እንጂ የመጻሕፍት መደብሮችን አፈላልጎ መጻሕፍትን የመግዛቱ ባህል የለንም፡፡ እነዚህ ወጣቶች ይህንን ስንፍናችንን አበርትተውልናል፡፡ ደግሞስ አዲስ መጽሐፍ መው ጣቱን በምን እናውቅ ነበር? ይኼው ያለ ክፍያ መረጃ እየሰጡን አይደል፡፡
በርግጥ እነርሱም ይህቺን ዋጋዋን ፋቅ አድርገው አዲስ የሚለጥፏትን ነገር ቢተው ሕዝቡም በእነርሱ ላይ ክፉ ስም እንዳይለጥፍ ይራዱታል፡፡
እነዚህ ዕውቀት ይዘው የሚዞሩ ወጣቶች ንቀት ሳይሆን ክብር፣ ስላቅ ሳይሆን ትኩረት የሚሹ ናቸው፡፡ እነሆ በፊታችን ሲያልፉ ብንችል ከያዙት መጽሐፍ በመሸመት፣ ካልቻልን አድናቆታችንን በመግለጥ፣ ያም ካልሆነ ደግሞ ደግሞ ክፉ ቃል ባለመናገር እንቀ በላቸው፡፡
ማን ያውቃል የተሸከመውን አንብቦ ከተሸከመው በላይ የሚጽፍ ሊቅ ከመካከላቸው ይወጣ ይሆናልኮ፡፡

46 comments:

 1. ማን ያውቃል የተሸከመውን አንብቦ ከተሸከመው በላይ የሚጽፍ ሊቅ ከመካከላቸው ይወጣ ይሆናልኮ፡፡
  Well said Dani.

  ReplyDelete
 2. ልክ ብልሀል ዳኒ!ችግሩ ይህንን ነገር የሚረዳው የማንበብ ልምዱ ያለው ሰው ሲሆን ይመስለኛል። እኔም የታዘብኩት ይህንኑ ነው ብዙዎቻችን በየሆቴሉ ባርና ካፍቴርያ ስንዝናና ለህይወታችን ምግብ ሊሆን ሁሉ የሚችል መፅሀፍን ያለንበት ድረስ እያመጡልን እነሱን ከመግዛት ይልቅ ስንት ፀሀይ ሲመታው የዋለን ኦቾሎኒ ቆሎና እንቁላል አዞሪዎችን ስናሳድድ እንኖራለን። የማንበብ ጥቅሙ የገባቸው እነዲህ ይላሉ 'A reading nation is a leading nation' እየመሩን ያሉት እያነበቡያሉት ናቸው እንደማለት። ወደድንም ጠላንም ሙሉ ሰው መሆን የምንችለው እስካነበብን ድረስ ነው። አዕምሮ መብሰል የሚችለው ሊያበስለው የሚችል የንባብ ማገዶ ሳየቆረጥ ሲቆሰቆስበት ብቻ ነው። እንደውም ማንበብ ብልጠት ነው።

  ReplyDelete
 3. ከምድሪቱ በላይ ሰማዩን አካፍሎ
  አየሁት ደመናን ከታች ተንገዋሎ
  ለጊዜው አየሁት ከላይ ተቀምጪ
  ተመልሼ እስካየው ከታች አንጋጥጨ
  (ትእግስት ህሩይ)

  ReplyDelete
 4. Hi! Dn- Dani betam wesagn guday new. temesasay gudayochin adrisen. Kale hiyiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 5. «በመጠኑ» አለ በኢትዮጰያዊው ትኅትና፡፡ የቤተ ክህነት ሰው መሆኑ ገባኝ፡፡ የቤተ ክህነት ሰው ባይሆን ኖሮ «በሚገባ» ነበር የሚለው፡፡ surprising!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 6. Thats right Dani, your previous blog about reading (Title of the blog: Fidel Eyalew Yemayaneb Manew?) makes me read a lot. Your books are also very interesting (Geographies of the bible). God bless you.

  ReplyDelete
 7. ማን ያውቃል የተሸከመውን አንብቦ ከተሸከመው በላይ የሚጽፍ ሊቅ ከመካከላቸው ይወጣ ይሆናልኮ፡፡

  ReplyDelete
 8. ማን ያውቃል የተሸከመውን አንብቦ ከተሸከመው በላይ የሚጽፍ ሊቅ ከመካከላቸው ይወጣ ይሆናልኮ፡፡
  Well said Dani.

  ReplyDelete
 9. Dear Daniel,

  I met one guy who is selling books, he told me that he first read the book then explain about the book for those who should buy it. He gives a brief summary of the book in front of his clients. Truly speaking, he is a very nice book reviewer. When I was a post graduate student at AAU, I do remember how we were challenged when we had a book review assignment. In fact, most of the students copy and paste from internet. However, that guy who sell books review the book easily. Thus, this article entails us to respect people who stand in front of us.

  ReplyDelete
 10. እንዲያውም በአንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ እነዚህ ወጣቶች በሁለት እጆቻቸው መጻሕፍት በመያዛቸው እጆቻ ቸው እየረዘሙ ነው ተብሎ ሲቀለድባቸው ሰምቻለሁ፡፡ ጫት በጉያው፣ ሲጋራ በጣቱ ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ያልወረደበት መዓት በእነዚህ ወጣቶች ላይ መውረዱ የእነርሱን ማንነት ሳይሆን የእኛን የአመለካከት ውርደት የሚያሳይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 11. Superb.
  God bless you.

  ReplyDelete
 12. ሁሌም ሳያቸው የሚያሳዝኑኝ የህብረተሰባችን ክፍል:: እብዛኛውን ጊዜ በፀሐይ እየተቃጠሉ ነው የሚያዞሩት:: አንዳንዴ ምናለ በማሕበር የሚያደራጃቸው ቢኖር ብየ አስባለሁ: ከዛ በኋላ በሱቅ በተደራጀ መልኩ ሥራቸው ያስኬዳሉ:: ምናለ ሥራን የማክበር ልምድ ቢፈጠር::

  Great stuff Daniel as usual.

  ReplyDelete
 13. እርሱ ገንዘብ ሲያጠራቅም የጉቦው መጠን ሲያድግ፣ እርሱ ገንዘብ ሲያጠራቅም የጉቦው መጠን ሲያድግ ሊደራረሱ አልቻሉም፡፡ ከዚያም በላይ ደግሞ የደጅ አስጠኚዎችን ግልምጫ እና ጫና መቋቋም አቃተው፡፡ ድሮስ የተማረ ሰው ችግር ይኼ አይደለ፡፡ ኅሊናውን ለሆዱ ማስገዛት ይከብደዋል፡፡

  ReplyDelete
 14. እንዲያውም በአንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ እነዚህ ወጣቶች በሁለት እጆቻቸው መጻሕፍት በመያዛቸው እጆቻ ቸው እየረዘሙ ነው ተብሎ ሲቀለድባቸው ሰምቻለሁ፡፡ ጫት በጉያው፣ ሲጋራ በጣቱ ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ያልወረደበት መዓት በእነዚህ ወጣቶች ላይ መውረዱ የእነርሱን ማንነት ሳይሆን የእኛን የአመለካከት ውርደት የሚያሳይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 15. yamenaragawen anawekemena yekere balane,

  ReplyDelete
 16. anetase dn yarasehen eyatawatahe nawe .wayawe lane
  tabarake

  ReplyDelete
 17. እንዲያውም በአንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ እነዚህ ወጣቶች በሁለት እጆቻቸው መጻሕፍት በመያዛቸው እጆቻ ቸው እየረዘሙ ነው ተብሎ ሲቀለድባቸው ሰምቻለሁ፡፡ ጫት በጉያው፣ ሲጋራ በጣቱ ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ያልወረደበት መዓት በእነዚህ ወጣቶች ላይ መውረዱ የእነርሱን ማንነት ሳይሆን የእኛን የአመለካከት ውርደት የሚያሳይ ነው፡፡

  እግዚአብሄር ያስታዉስህ የሚገርም ነገር ነዉ ያስተዋልከዉ::
  ሶፎኒያስ

  ReplyDelete
 18. Geter abyate kirstiyanat agelgay kahin atew bemichegerubet zemen inezihi "metsihaf azuari like "akenajto yemiyasemara aderejajet metfatu ijige yasazinal dani!

  ReplyDelete
 19. "እንዲያውም በአንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ እነዚህ ወጣቶች በሁለት እጆቻቸው መጻሕፍት በመያዛቸው እጆቻ ቸው እየረዘሙ ነው ተብሎ ሲቀለድባቸው ሰምቻለሁ፡፡ ጫት በጉያው፣ ሲጋራ በጣቱ ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ያልወረደበት መዓት በእነዚህ ወጣቶች ላይ መውረዱ የእነርሱን ማንነት ሳይሆን የእኛን የአመለካከት ውርደት የሚያሳይ ነው፡፡"

  ይገርማል ለካ እንዲህም ማሰብና ማስተዋል ነበረብን? ግን እኮ ብዙዎቻችን እየተነገረንም አንሰማም አናዳምጥም የምንል እንቢተኞች ነን፡፡ ይኸው ዛሬ እንድናስተውል ተነገረን ባይሆን ከአሁን በኋላ እንኳን እስኪ እናስተውልና ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ፡፡

  ወንድማችን ዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን፤ ረዥም እድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ያድልልን፡፡

  ReplyDelete
 20. ዳንኤል እነዚህን የቅኔ ምሁራን ሰዎች ለምን ሰብስበህ አታደራጃቸውም የኛንም ድርሻ ንገረን በወር ብንረዳቸውና ቅኔ ቤቱ እንዳይዘጋ ብናደርግ ለምን አንተ ድልድይ አትሆነንም እባክህ ወደ ስራ እንግባ

  ReplyDelete
 21. "ብዙዎቻችን ሥጋ ቤቶችን አድነን እንሄዳለን እንጂ የመጻሕፍት መደብሮችን አፈላልጎ መጻሕፍትን የመግዛቱ ባህል የለንም፡፡ እነዚህ ወጣቶች ይህንን ስንፍናችንን አበርትተውልናል፡፡ ደግሞስ አዲስ መጽሐፍ መው ጣቱን በምን እናውቅ ነበር? ይኼው ያለ ክፍያ መረጃ እየሰጡን አይደል፡፡" ዳኒ አንተ በርክትልን
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 22. የምትጽፈፋቸው በሙሉ አስተማሪ ፣መካሪ፣ ድክመቶታችንና ኋላ ቀርነተታችን የመሚስተምረን በመሆናቸው እግዚአብሄር ጤናና እድመሜ የያብዘዛልን፡፡
  እንዳልካቸው

  ReplyDelete
 23. Hello Daniel

  I would like to say thank you for your great comment about self motivated booksaler. I'm happy to read this article about those indiviual booksale man who give us numerous education. I respect them,I pround of them,they are our eye we can see across the dark world.Even though I live in USA, I went to Addis to see my family last year. I bought a dozen books which I gave to my friends half and I kept half to myself. I got very good idea about my county history and culture very well:therefor, If I didn't get those books, I wouldn't get those wonderful idea. I wish we have a habit like giving a book as gift. Finally, Danie THANK YOU for your time to write a very good artic about those unknow hero who nobody appreiciate their magnificent task.

  ReplyDelete
 24. Yasaznal yegna mecheresha! It seems z general ignored by z private. Zim new!!

  ReplyDelete
 25. tiru milketa new....


  gin degmo kebete kristian chigirna timihirt lay..tinish yerak meselegn...hulunim gudayoch mizanawi temetatagn argachew...sibitrun malete new(yezarew tinish yikerb yihonal)

  lemisale semonun awezagabi film bekirstos lay beabatoch ina bemengist fikad lisera teblo betemariwoch birtat ...liker chilual.....silezih guday yanten ina leloch bilogochin mk chemro minim altebalebetim....


  iwnet newey..abatoch indet fekdew siraw tegemere....etc angebgabi silehone ibakih adera timihirtim silemihon...mankiyadewel new

  and belibet...adera adera

  ReplyDelete
 26. እነዚህ ልጆች ለምን ቱቶር ማድረግ አይጀምሩም- ማለቴ ቅዳሴውን፣ አቋቋሙን፣ ድጓውን፣ ቅኔውን? ብዙ መማር እየፈለገ ጊዜው አልመቻች ብሎለት እንደናፈቀው የሚቀር በየቦታው አለ፡፡ ስለዚህ ከመጻሕፍት ማዞር በተጓዳኝ ማታ ማታ እንኳን ቢሆን የቤት ለቤት ትምህርት ቢያስተምሩ የተሸከሙትን ዕውቀት ለትውልድ እንዲተርፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ሲሆን ተደራጅተው ቢጀምሩት ሳይሆን በየግላቸውም ቢሆን ቢሞክሩት ጥሩ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ረገድ እኔ የተወሰኑ መማር የሚፈልጉ ሰዎችን አውቃለሁ፡፡

  ReplyDelete
 27. Dear Daniel, it is amazing article, and after now I promise, I will buy books from them than book stores.
  By the way people those who read this blog, why copy and paste those article again????? I can't understand ur point just copy and paste Daniel's writing. You might be amazed by the way he explain but just try to keep on ur mind and try to change it just to live in your life

  ReplyDelete
 28. D/n Daniel Egziabhere Yeagelgilot Zemenihen Yibarklih Betesebochihen Yitebklih. Yemanasbewn, Yemanawkewn Tasawkenalehna Tebarek!
  Kalehiwoten Yasemalin. Yemebetachenin Amalaginet Yekidusan Teradaenet Ayleyen!
  Amen!

  ReplyDelete
 29. wede tegebaru benehade hulachenem yedershachenene enewetalen D.Daniel ante lemaderajet moker

  eneredachew ena yekuekamu pls

  ReplyDelete
 30. it touches so much, nice view as always

  ReplyDelete
 31. Well said,and very educating. You invite all of us to see where we are and what we are. Thanks a lot and keep on revealing such interesting stuffs which we always attach less weight to them.
  Kagnew

  ReplyDelete
 32. «በመጠኑ» አለ በኢትዮጰያዊው ትኅትና፡፡ የቤተ ክህነት ሰው መሆኑ ገባኝ፡፡ የቤተ ክህነት ሰው ባይሆን ኖሮ «በሚገባ» ነበር የሚለው፡፡yesss....sssssssssssssssssss!!!

  ReplyDelete
 33. Thanks Deacon.
  You remind me the person who thought us Geez in Kaleai class in "Arada giorgis, genete tsige." When i see him selling books in piaza, i was amazed how strong this guy is. Unfortunately i am not sure about his name.

  ReplyDelete
 34. Dani,
  Excellent observation as usual. I too always buy from these young people if I can get the book I want to buy.

  ReplyDelete
 35. yemigerm new endezim ale leka.ahunem lebete kehenet sewoch leb yestelen belenal.

  ReplyDelete
 36. ዳኒ በጣም ጥሩ እይታ ነው ሥራ ከራስ ይጀመራልና አንተ በራስህ ለዚህ ሊቅ ምን ረዳኸው ካለህ የቤተክህነት ቀረቤታነት ወይስ ቃሉን ብቻ ተቀብለህ ለጽሑፍ ብቻ።ጉቦውን ማን እንደጀመረው እናውቃለን።

  ReplyDelete
 37. ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡአኡ
  እረ ልፈነዳ ነው
  ስንቱን እንሰማለን
  ስንቱን እናያለን
  ስንቱ ይገርመኛል
  ስንቱ ያሳዝነኛል
  ስንቱ ያበግነኛል
  ስንቱ ያስቆጨኛል
  እንባ እንባ አስብሎ
  ስንቱ ያስለቅሳል
  እረ ስንቱ…ስንት
  ኡኡኡኡኡ
  የሃገር ያለህ
  የወገን ያለህ
  ቅኔ ዘራፊው
  መጽሃፍ አዟሪው
  ቅዳሴ መምሀሩ
  መጽሃፍ ሲያዞሩ
  ኡኡኡኡኡ
  ወንበር ታጠፈ
  የቅኔው መምህር
  ዕውቀቱ ተዘረፈ
  ዕውቀቱ ታለፈ
  የቅዳሴም መምህር
  ሰአቱ አለፈ
  እንግዲህ እረፉት
  ድጓ ጾመ ድጓ
  ምዕራፍ መስዋእት
  ኡኡአኡኡኡኡኡኡ………

  ReplyDelete
 38. First I could say thanks a lot to share your view for us. I read most of your view but I strongly sorrow with it. As we know, our church is one of the richest organization in the world with any direction such as skill man power and also financial but not use properly......

  Let God give a righteous leader for our church

  ReplyDelete
 39. ግሩም ነው ዳ.ዳንኤል!መነሻው ማድረቅ እንጂ ..እንደአይሁድ ፍየል ፍለጋ ምን ይጠቅማል:ሁሉም የበኩሉን
  ቢያደርግ የዛሬውን መፅሀፍ አዧሪ የትላንቱን የኔታ እንታደግ ነበር:..በሰለጠነው ዓለም ለቤት እንሰሳቱ ታዛ እና ሕክምና ፍለጋ የደከማል:እኛስ ለራሳችን ምነው አቃተን???ምኞቴ ብዙነህ@ፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete
 40. What a sad real life history! D.Daniel I thank you for yr best efforts.I have one comment, why dont we lead these amazing people to the right place? we need them, they have basic knowlege for ehthiopian orthodox people.we are the one who should follow and give them a specal place.We must start now.please lets gather These dimonds of our church to shine for future generation.

  From S.C

  ReplyDelete
 41. i saw and read most of ur papers, i happy for u b/se u see things in different ways, that makes me always surprise. keep looking and writing

  ReplyDelete
 42. ማን ያውቃል የተሸከመውን አንብቦ ከተሸከመው በላይ የሚጽፍ ሊቅ ከመካከላቸው ይወጣ ይሆናልኮ፡፡

  ReplyDelete