Thursday, November 24, 2011

የተሰደዱ ስሞች


(ክፍል ሁለት)
ባለፈው እትም በልዩ ልዩ የዓለም ከፍሎች ተዘውታሪ የሆኑትን ስሞች አንሥተን ነበር የተሰናበትነው፡፡ የኢትዮጵያውያንን ተዘውታሪ ስሞች በተመለከተ በቂ የሆነ መረጃ ማግኘት ቸግሮኛል፡፡ ምናልባት የስታትስቲክስ መሥሪያ ቤታችን ከሕዝብ ቆጠራ ያገኘውን መረጃ ተጠቅሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉትን የሴት እና የወንድ ስሞች እንዲነግረን አደራ እያልኩ መጠነኛ ፍንጭ የሚሰጡንን ብቻ እንጥቀሳቸው፡፡
አንድ «ስቱደንት ኦፍ ዘወርልድ» የተሰኘ ድረ ገጽ በመረጃ መረብ እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች በጥቅም ላይ የዋሉትን የኢትዮጵያውያንን ስሞች በመሰብሰብ በስፋት ጥቅም ላይ ውለዋል ያላቸውን የወንድ እና የሴት ስሞች እስከ አንድ መቶኛ ደረጃ ዘርዝሯቸዋል፡፡
በዚህ ድረ ገጽ ዝርዝር መሠረት በስፋት ጥቅም ላይ በመዋል ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ያለውን ደረጃ የያዙት የሴቶች ስሞች «ኤደን፣ ሣራ፣ ቤቲ፣ ሕይወት፣ ቤዛ፣ ሜሮን፣ ትእግሥት፣ ቃል ኪዳን፣ ሩት እና ሰላም» ናቸው፡፡ የወንዶቹን ስናይ ደግሞ «ዳንኤል፣ ሰሎሞን፣ ብሩክ፣ ዳዊት፣ ሄኖክ፣ ሳሙኤል፣ ያሬድ፣ አቤል፣ ሀብታሙ እና አሸናፊ» ናቸው፡፡
 የእነዚህ ስሞች አካሄድ የሚያሳየን አንድ ነገር አለ፡፡ የኢትዮጰያውያን ወላጆች በተለይ ደግሞ ከተምቾ ወላጆች የስም አወጣጣቸው መቀየሩን፡፡ በጋዜጦች ላይ የሚወጡ የስም ለውጥ ማስታወቂያዎችም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ያሳዩናል፡፡ በአብዛኛው ስሞቻቸውን የሚቀይሩት በቀድሞ ዓይነት ስሞች የሚጠሩት ናቸው፡፡ የሚቀይሩት ደግሞ በዘመናችን መለመድ ወደ ጀመሩት ከላይ ወደ ጠቀስናቸው ዓይነት ስሞች ነው፡፡
በአሁኑ ዘመን ያለው የስም አወጣጥ መንገድ የአራት ነገሮች ተጽዕኖ ይታይበታል፡፡ የመጀመርያው ሃይማኖት ነው፡፡ በክርስቲያኖች ዘንድ አጠር ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞች እየተዘወተሩ ሲመጡ በሙስሊሞችም ዘንድ አጫጭር እስላማዊ ስሞች እየተለመዱ ናቸው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የእንግሊዝኛ ስሞች ተጽዕኖ ነው፡፡ አሜሪካኖች ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ሲወጡ ካደረጓቸው ነገሮች አንዱ የእንግሊዝን ስሞች እየቆራረጡ በማሳጠር አሜሪካዊ ስሞችን መፍጠር ነው፡፡ እነዚህ አሜሪካውያን ስሞች በኢትዮጵያውያን ስሞች ላይ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ተጽዕኖ አድርገዋል፡፡ እነ ዘውዱ «ዜድ» እነ ክንዴ «ኬነዲ» እነ ማርያማዊት «ሜሪ» እነ ቢንያም «ቢኒ» የሆኑት በዚህ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ አንዳንድ ስሞች የዘመናዊነት መገለጫዎች እየተደረጉ መታየታቸው ነው፡፡ ትርንጎ ከመባል «ሜሪ» ወዳጄነህ ከመባል «ሳሚ» ድፋባ ቸው ከመባል «» አስቻላቸው ከመባል «አስቹ» ቴዎድሮስ ከመባል «ቴዲ» ዘውዱ ከመባል «ዜድ» ሲሳይ ከመባል «ሲስ» ዘመናዊነትን እያሳዩ መጥተዋል፡፡
በውጭ ዓለም በሚኖረው ዳያስጶራ ዘንድ ደግሞ ለፈረንጆቹ ለአጠራር እንዲያመች ተብሎ ስሞች እንዲያጥሩ እየተደረገ ነው፡፡ በተለይም በሥራ ቦታ እና በትምህርት ቤት አካባቢ በአበሻዊ ስሞች መጠራት ፈረንጅ ቀጣሪዎችን እና መምህራንን ስለሚያስቸግር ስሙን ጎርዶ ለአጠራር የሚያመች ስም ማውጣት እንደ ቀላል መንገድ ተወስዷል፡፡ አንዲት እኅት ፍሬ ወርቅ የሚለውን fire work ብላ በመጻፏ ስሟ «ፋየር ዎርክ» ተብሎ መቅረቱን አጫውታኛለች፡፡
ስም የአንድ ሕዝብ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ፍልስፍና እና አመለካከት የሚያሳይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስሞቻችን ባይዘነጉ መልካም ይመስለኛል፡፡ አጫጭር እና ያልተለመዱ፣ ትርጉም ያላቸው እና ለአጠራር የሚቀሉ ዓይነት ስሞችንም ቢሆን ከኛው ውስጥ መርጦ ማውጣት የሚከብድ አይመስለኝም፡፡
በብዙ ሀገሮች የስም ማውጫ መጻሕፍት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በዚያች ሀገር በሚገኙ ሕዝቦች ዘንድ ከጥንት ጀምሮ የሚወጡትን ስሞች ከተቻለ ከነ ትርጉማቸው የሚያቀርቡ ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕ ፍት አያሌ ጥቅሞች አሏቸው፡፡ የመጀመርያው ጥቅማቸው የቅርስ መዛግብት መሆናቸው ነው፡፡ በዚያች ሀገር ታሪክ ውስጥ ለልዩ ልዩ ነገሮች መጠርያ ሆነው ከጥቅም ውጭ የሆኑትን ስሞች በቅርስነት ይይዙልናል፡፡
ለምሳሌ በሀገራችን እየተረሱ የመጡ የፈረስ ስሞች፣ የንግሥና ስሞች እና የመዓርግ ስሞች አሉ፡፡ እነ ደጃዝማች፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ራስ፣ ቢትወደድ፣ ፊታውራሪን የመሰሉት የመዓርግ ስሞች በአሁኑ ዘመን በሹመት እየተሰጡ ባለመሆናቸው የመረሳት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ወደፊት ልጆቻችን የጥንት መዛግብትን ሲያነብቡ እነዚህን ስሞች የሚተረጉምላቸው መዝገበ ቃላት ይፈልጋሉ፡፡ ከፖሊስ ቤት አገልግሎት የተሠረዙት እነ መቶ አለቃ፣ አሥር አለቃ፣ ሻለቃ፣ ሻምበል ወደፊት ከመረሳታቸው በፊት ከነ አገልግሎታቸው እና ታሪካቸው የሚመዘግባቸው ይሻሉ፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ እየጠፉ እና እየተቀየሩ የሚገኙ የአካባቢ ስሞች አሉ፡፡ መንግሥታት እና ሥርዓተ ማኅበሮች በተቀያየሩ ቁጥር የመለወጥ አደጋ ከሚያጋጥማቸው ቅርሶች መካከል የአካባቢ ስሞች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ስሞች ጥቅም ላይ ውለው በነበሩበት ዘመን የተጻፉ አያሌ መዛግብት አሉ፡፡ እነዚህን መዛግብት በሚገባ ለመረዳት እነዚህ ስሞች ከነአካባቢያዊ ምልከታቸው ተመዝግበው መቀመጥ አለባቸው፡፡
ማኅበረሰቡ ለአንዳንድ ነገሮች ከዘመኑ ክስተት ጋር የተያያዘ የመታሰቢያ ሰም የሚሰጥበት ጊዜ አለ፡፡ ምኒሊክ ብርጭቆ የሚባለው ብርጭቆ አሁን ይኑር አይኑር እንጃ፡፡ ተፈሪ ሚዛን የሚባል ዛፍ ላይ የሚንጠለጠል ትልቅ ሚዛን ትዝ ይለኛል፡፡ በደርግ ጊዜ ከሶቪየት ኅብረት የሚገቡ «ሞስኮብ» እየተባ የሚጠሩ የክፍለ ሀገር ሚኒባሶች ነበሩ፡፡ ኢሕአዴግ አዲስ አበባ በገባ ሰሞን የመጡት ዲኤክስ መኪኖች «ወያኔ ዲኤክስ» ሲባሉ፣ አባ ዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት በሆኑበት ዘመን የመጡት ነጫጭ ሚኒ ባሶች ደግሞ «አባ ዱላ» ተብለው ተሰይመዋል፡፡ ወደ ሀገር ባህል ልብስ ቤት ብንገባ ደግሞ ኦባማ ቀሚስ፣ ቢዮንሴ ቀሚስ እየተባሉ የሚጠሩ የሐበሻ ቀሚሶችን እናገኛለን፡፡ እነዚህ ሁሉ ስሞች ዘመንን ከነ ክስተቱ የሚያስታውሱ በመሆናቸው ቢቻል ከነ ፎቶ ግራፋቸው ቀርሶ የሚያስቀምጣቸው መዝገብ ይሻሉ፡፡
ሁለተኛው የመዝገበ ቃላቱ ጥቅም ደግሞ የወላጆችን ጭንቀት መፍታቱ ነው፡፡ ወላጆች ከምኞታቸው፣ ከሃሳባቸው፣ ከአመለካከታቸው እና ከእምነታቸው ጋር የሚሄድ ተወዳጅ ስም ማውጣት ፍላጎታቸው ነው፡፡ ችግሩ ይህንን ስም ከየት እንደሚያገኙት አለማወቃቸው ነው፡፡ ይህንን መሳይ የስም መዝገበ ቃላት ቢኖረን ግን ወላጆች እና አሳዳጊዎች በቀላሉ የሚፈልጉትን ዓይነት ስም ለማግኘት ይችሉ ነበር፡፡
ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን ወስደው የሚያሳድጉ የውጭ ሀገር ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከጠየቁኝ ነገር አንዱ ኢትዮጵያውያን ስሞችን የሚያገኙበትን አማራጭ እንድነግራቸው ነው፡፡ ለልጆቻቸው የቤት ውሻ ይሰጧቸዋል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጰያዊ የሆነ የውሻ ስም ይፈልጋሉ፡፡ እነ መቻልን፣ እነ ገሥግሥን፣ እነ ደምሳሽን በምን ይወቋቸው፡፡ እነዚያ ሕፃናት ልጆች ያድጉና እነርሱም ለልጆቻቸው ስም ይፈልጋሉ፡፡ ያደጉት በምዕራቡ ማኅበረሰብ ውስጥ በመሆኑ ከአበሻው ጋር ብዙም ቀረቤታ የላቸውም፡፡ ልጆቻቸውን የሀገራቸውን ቋንቋ ማስተማር ቢያቅታቸው እንኳን የሀገራቸውን ስም መስጠት ግን ይፈልጋሉ፡፡ ግን ከየት ይምጣ?
ሦስተኛው ጥቅሙ ደግሞ የማናውቃቸውን የሀገራችንን ስሞች ለማወቅ እና ለመጠቀም ማስቻሉ ነው፡፡ በየብሔረሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ፣ ትርጉማቸው እጅግ አስደናቂ የሆኑ፣ ሃሳባችንን እና እምነታችንን ሊገልጡልን የሚችሉ ስሞች አሉ፡፡ ያልተጠቀምንባቸው ባለማወቃችን ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህን ስሞች የምናገኝበት መዝገብ ቢኖረን ኖሮ የማንተዋወቅ ሕዝቦች ለመተዋወቂያ ምክንያት ይሆነን ነበር፡፡
ባሁኑ ዘመን ስም የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም፡፡ መንገዶች፣ ሕንፃዎች፣ መንደሮች፣ መኪኖች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች፣ ሌሎችም ስም እየወጣላቸው ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን ከሥራቸው እና ከሃሳባቸው ጋር ተስማሚ የሆኑ ስሞችን ማውጣት ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ተሠር ተው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመርተው የእንግሊዝኛ ወይንም የፈረንሳይኛ ስም የሚይዙ ምርቶች፣ አገልግ ሎቶች እና ሥራዎች አሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ ሀገርኛ ማድረግ ከምንችልባቸው መንገዶች አንዱ አማራጮችን ማቅረብ ይመስለኛል፡፡
በሀገራችን ባለቤት አልባ ውሾች ብቻ አይደለም ያሉት ባለቤት አልባ ሥራዎችም አሉ፡፡ ከነዚህ አንዱ ኢትዮጵያውያን ስሞችን መቀረስ ነው፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች ገንዘብ ተከፍሏቸው ለሰዎችም ሆነ ለድርጅቶች ተፈላጊ ስሞችን የሚያወጡ ድርጅቶች አሉ፡፡ መቼም ድርጅትን ኤም ኤን ኢንተርናሽናል፤ ትሬዲንግ፤ አስመጭ እያሉ ከመጥራት ከፍሎ ሸጋ ሸጋ ስም መውሰድ የተሻለ ነው፡፡
እናም ከጥንት መዛግብት፣ ከጥንት ጋዜጦች፣ የሰዎችን እና የድርጅቶችን ምዝገባ ከሚያካሂዱ መሥሪያ ቤቶች፣ ከመቃብር ሥፍራዎች፣ መታወቂያ እና ፓስፖርት ከሚሰጡ ተቋማት፣ ሀገር ዐቀፍ ፈተና ከሚሰጡ ድርጅቶች ወዘተ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ የሀገር ሽማግሌዎችንም በመጠየቅ ስሞችን የመሰብሰብ፣ የመመዝገብ እና የመቀረስ ሥራ መሥራት ታሪክን፣ ባህልን፣ ፍልስፍናን እና ማንነትን የመጠበቅ እና የመጠቀም አንዱ አካል ተደርጎ የሚቆጠር ይመስለኛል፡፡

© ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔትላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ    በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

17 comments:

 1. "ስም የአንድ ሕዝብ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ፍልስፍና እና አመለካከት የሚያሳይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስሞቻችን ባይዘነጉ መልካም ይመስለኛል፡፡" አንተ በርክትልን::
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 2. Dani ... Abet Sigerm Balefew Eyetngagern neber Ende Nechochu Eganm Ye Sem List Binoren Eyalen Yelbe Awqa Neh,,, Amelak Ke Fetena Hulu Ke Betsebhe Yetebkih... Gen Danny Ye Sem Ke Aseru West Ale Enam.......

  Ke Medre Germany

  ReplyDelete
 3. መቼም ድርጅትን ኤም ኤን ኢንተርናሽናል፤ ቢ ቲ ትሬዲንግ፤ ሲ ፊ አስመጭ እያሉ ከመጥራት ከፍሎ ሸጋ ሸጋ ስም መውሰድ የተሻለ ነው፡፡

  Great stuff Daniel as usual.

  ReplyDelete
 4. ርብቃ ከጀርመንNovember 24, 2011 at 9:17 PM

  አውነት አለክ ዳኒ ካነሳህውአይቀር እኔም አንድገጠመኘን ላጫውትህ በእንግድነት ከምኖርበት ከተማ ዘመዶቸን ለመጠየቅሌላከተማ ሂጀ ያለሁበት ቤትውስጥ እንግዶች ልጆቻቸውንይዘው መጥተውነበርና ስምሽማነው ብየስጠይቃት ማርሲላስ ብላነገረችኝ እኔም ግራስጋባ እናቱዋ አየችኝኝ እና አልሰማሻትም ማርሲላስ ነውያለችሽ አለችኝ እኔም የፈረንጆችስም መለሰኝእና ምንማለት ነውትርጉሙስላት ማር ሲላስ ብላ ነጣጥላ መርሲላስየሚሰጠውን ጣእም አስቢው አለችኝ እኔም በራሴአለማስታወል ተገርሜ በጣም ደስየሚልስምነው ያወጣሽላት ብየ አፍሬዝምልኩኝ:: ደኒ የማናስተውላቸው ስንትድንቅና ትርጉማቸው የሚያስደምም ስሞችአሉን እናም ዳኒ( ያንተንም ስምአሳጥሬ) እንዳልከው ስሞቻችን ተመዝግበው ቢቀመጡ መልካም ነው እላለሁኝ ::

  ReplyDelete
 5. መቶ አለቃ ቢትወደድNovember 24, 2011 at 9:51 PM

  ወይ ዲ.ዳኒ....
  በእውነት ሃሳቡ በጣም ጥያቄ የሌለው ምክር የማይሻ ነው: ግን ማን ይስራው? እኔ በበኩሌ እንደዚህ አይነት ስራ ቢጀመር ለመስራት እና ያልኝን ለማበርከት .....
  ስለዚህ ከምክር ይልቅ ወደ ተግባር ብንግባ: እንዲያውስ የጽሑፍ ስራ ልምድ ያላችሁ ብትጀምሩት እኛ ደግሞ የተቻለንን ያክል በእውቀት/በሙያ: በጉልበት: በገንዝብ: በሃሳብ ብንራዳ ይህንን ስደት ልንታድገው እንችላለን:: መታደግም ብቻ ሳይሆን ለመጪውም ትውልድ ቅርስ ትቶ ማለፍ ነው እላለሁ::

  ReplyDelete
 6. የሴቶች ስሞች «ኤደን፣ ሣራ፣ ቤቲ፣ ሕይወት፣ ቤዛ፣ ሜሮን፣ ትእግሥት፣ ቃል ኪዳን፣ ሩት እና ሰላም» ናቸው፡፡ የወንዶቹን ስናይ ደግሞ «ዳንኤል፣ ሰሎሞን፣ ብሩክ፣ ዳዊት፣ ሄኖክ፣ ሳሙኤል፣ ያሬድ፣ አቤል፣ ሀብታሙ እና አሸናፊ» ናቸው፡፡
  ለነዚህ ስሞች እንዲሁም ለሌሎች ሁሉ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲአን ባለዉለታ ናት ካለንበት የቦታ አቀማመጥ አጻር እነዚህን ትርጉም አዘል ስሞች ያለ እሱዋ እንኮን መሰየም ማሰብም አይቻልም ነበር እና !!!
  ሶፎኒያስ

  ReplyDelete
 7. ዳንኤል ስሞች አይደሉም እራቸው ሰዎች ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወደ ውጪ ባእድ ሀገር እየተሰደዱ አይደለም እንዴ፡፡ግማሾችም እኮ እራሳቸውን እያቃጠሉ ነው፡፡ለአሁኑ መቼም በክፍል ሁለት ይብቃህና ክፍል-3 ሳይመጣ እስኪ ደግሞ ፊትህን ወደ ሌላ እጅግ አንገብጋቢ ነገር አዙር፡፡ምነው ዳንኤል ስለ ሊቢያው ጋዳፊ ግጥም ስትፅፍ በቅርቡበማለት በሀገራችን የዋካ ነዋሪ የሆነውና እራሱን ቤንዚን አርከፍክፎ በእሳት አቃጥሎ ውድ የተከበረች ህይወቱን ስላጠፋው ስለመምህር የኔ ሰው ዝም ጭጭ አልክሳ፡፡ የኔሰው ውድ የተከበረች ህይወቱን ያጠፋው ፍትህና ነፃነት በሀገሬ ጠፋ ብሎ ነው ይባላል፡፡ቢያንስ በተረት ተረት አድርገህ እንኳን ዘገባ አድርግለት እንጂ፡፡ነው ወይንስ አንተም ይህን ታሪክ አልሰማህም ማለት ነው?አለምና ህይወት ውስጣ ውስጥ ዝክንትሎቿ ሰማይ ብራና ውቅያኖስ ቀለም ሆኖ ቢቀርብ እንኳን እንዲህ በቀላሉ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ስለዚህም አንዳንድ ጊዜ ቅድሚያ ለሚሰጠው አንገብጋቢ የሀገርና የወገን አጅንዳ ቅድሚያ መስጠት ግድ ይላል፡፡ኢትዮጵያዊው ወንድማችንና ልጃችን እውን ምን ያህል በደል ደርሶበት ቢሆን ነው እስከዚህ ድረስ እራሱን ቤንዚን አርከፍክፎ በእሳት አቃጥሎ ውድ የተከበረች ህይወቱን መስዋእት ያደረጋት?ይህ ለእኛ ኢትዮጵያውያን ያለው አጠቃላይ ስነ-ቦናዊ፣ማህበራዊ፣ባህላዊ፣ፖለቲካዊ፣ሃይማኖታዊ አንደምታው ምንድን ነው?የየኔ ሰው ነፍስ ጩኸት እያሰማቸ ነውና እናዳምጣት እንጂ፡፡ምናልባት ዝም እንደማትል እገምታለሁኝ ነገር ግን እንዴት አድርጌ ልዘግበው እያልክ እያሰላሰልክና እየተጨነክበት ሊሆን ይችላል፡፡መነገርና መወራት የሚገባውን ወቅታዊና አንገብጋቢን ነገር ቅድሚያ ሰጥቶ በሰዓቱ ይፋ አለማውጣትና አለመናገር በተቃራኒው ደግሞ ቀስ ብሎ ሊደርስ የሚችለውንና ቅድሚያ አትኩሮት የማያስፈልገውን ያን ያህልም ወቅታዊና አንገብጋቢ ያልሆነን ነገር ደግሞ እየዘገቡ ሌላውን እንዳይነሳ አዳፍኖ ማስቀረት ኢሞራላዊ የሆነና በራሱ ከወንጀሎች ሁሉ የከፋው አደገኛ ወንጅል ነው፡፡በስፋት ያለው የዘመኑ mainstream media ደግሞ ባብዛኛው እያደረገ ያለው ይህንን ነው፡፡አንተም እንደዚህ እንደማትሆን ተስፋ አደርጋለሁኝ፡፡
  አመሰግናለሁኝ

  ReplyDelete
 8. is your name did changed or is the origional one?

  ReplyDelete
 9. bemejemeria yhin coment post laderekewu sewu fetari mastewalun yisteh."ምነው ዳንኤል ስለ ሊቢያው ጋዳፊ ግጥም ስትፅፍ በቅርቡበማለት በሀገራችን የዋካ ነዋሪ የሆነውና እራሱን ቤንዚን አርከፍክፎ በእሳት አቃጥሎ ውድ የተከበረች ህይወቱን ስላጠፋው ስለመምህር የኔ ሰው ዝም ጭጭ አልክሳ፡፡ የኔሰው ውድ የተከበረች ህይወቱን ያጠፋው ፍትህና ነፃነት በሀገሬ ጠፋ ብሎ ነው ይባላል". Ante irasih anonymus bemil sim post adirigeh yemin sewun megefafat newu daniel newu yekerachihu yalaserachihut ahun isun lemasigebat newu "doron sideliluat bemechagna..." wondime Dani yelijoch abat newu ibakih lijochun yasadigibet woyanem likoh kehone Dany orthodox tewahido ina Ethiopia besiriat yasadegut antura habit newu ina isum indene Birihanu Nega,Dawit kebede... ke ageru tesedo indinor tifeligaleh? ibakih silefetereh wondime madireg yemitifeligewun besewoch tikash lay sayhon berasih adirg Dany yihin adirig tebilo yemineger sewu aydelem kenezih aremene seytanoch be sewu dem yesekeru sewoch gar atanekakawu.

  ReplyDelete
 10. I do agree .in fact there are things which we should think from different angle.once,years a go, i remember on the famous "EHUDEN KEGAN GA "radio program a guest raise a lots of good issues related to what we should think on names .
  As one of the comment i read ABOVE on "MARSELAS" which is great one ,there are names which we should not use them as there meaning in Amharic is not polite.
  H

  ReplyDelete
 11. yemigerm new Balefew samint abate yemiserabet mesriyabet gwadegnaw befit yeneberewin shiferaw yemibal sim keyro cheef mebalun negeregn, miknyatun eyatarahu new.

  ReplyDelete
 12. ‎5 chinese, Chu, Bu, Hu, Fu and Su decided to immigrate to the US. In order to get a visa they had to adapt their names to American standards. Chu became Chuck, Bu became Buck, Hu became Huck, Fu and Su decided to stay in China.

  ReplyDelete
 13. Replies
  1. Dani ewnet lemenager tasdestegnaleh gin endet new gizehn lenbab yemtitekemew bewnet ebakih tekom argegnina kenklfem kenshe lanbib. Berekete Estifanos yihdir Belaeleke.

   Delete
 14. Ene Dejazmach yemibal guwadegna alegn egna gin siniteraw asatiren DJ bilen new.

  ReplyDelete