Wednesday, November 23, 2011

ወራጅ አለ

የኖኅ ርግብ
ከአራት ኪሎ በስታዲየም ወደ ሜክሲኮ በሚጓዝ ታክሲ ውስጥ ነኝ። በተሳፋሪ መቀመጫ ሁለተኛ ወንበር ላይ በግራ በኩል ተቀምጫለሁ። ብዙ ጊዜ የትራፊክ መጨናነቅ በሚስተዋልበትና ባቡር ጣቢያ ፊት ለፊት በሚገኘው መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደ ደረስን ከጎኔ የነበረች አንዲት ወጣት ባቡር ጣቢያ መድረስ አለመድረሳችንን ጠየቀችኝ። አኔም ሳናልፈው ጥሩ ሰዓት ጠየቅሽኝ በማለት በታክሲው በግራ በኩል ባለው መስኮት እያመለከትኩ ያውልሽ ደርሰናል አልኳት።

እኔ አመልካች ጣቴን ከመስኮቱ ሳላነሳ እኛ ባለንበት ታክሲ ውስጥ ያለውን ረዳት ሳይሆን በቀኝ በኩል ባለው መንገድ ታጥፎ ወደ ቸርችል ጎዳና በሚጓዘው ታክሲ ውስጥ ያለውን የታክሲ ረዳት የምትጠይቅ በሚመስል ድምጽ “ወራጅ አለ” ስትል ከድምጿ ቅጥነትና ኃይል የተነሳ ሁላችንም ደነገጥን። በተለይ እኔ…. እንዴት ብዬ ልንገራችሁ! በመጀመሪያ ስታናግረኝ የነበረው ለስለስ እና ዝግ ባለ ድምጽ ስለነበርና እንደዚያ ያለ ድምጽ በዚያ ቦታ ስላልጠበኩኝ ነው መሰለኝ ክው ነው ያልኩት።


አገር አማን ነው ብሎ በብርና በሳንቲም የተሞላውን ግራ እጁን ከፊተኛው ወንበር መደገፊያ ላይ ቀኝ እጁን ደግሞ በከፊል በተከፈተው የታክሲው የበር መስታወት ላይ አስደግፎ ይጓዝ የነበረው ረዳት ከድንጋጤ ይሁን ከንዴት እንጃ አይኑ በርበሬ መሰለ። ዞር ብሎ ተመለከተና ዝም አላት።

ራሰ ፍንጭቱ ሾፌርም “አዚህ ጋ መውረድ አይቻልም” አሏት በጎርናና ድምጽ። ልጅቱ የሾፌሩን ንግግር ትታ ረዳቱን “ክፈትልኝ” ስትል እንደገና ጮኸችበት። ረዳቱም “ታስከስሽኛለሽ አልከፍትም” አላት። ብትሰማውም ባትሰማውም “ተሻግረሽ ኮሜርስ ነው መውረድ የምትችዪው” ብሎ ሳይጨርስ “ባቡር ጣቢያ እንጂ ኮሜርስ እሔዳለሁ አልኩህ እንዴ? ዞር በልልኝ!” ብላ በሩን ልትከፍት መታገል ያዘች።

ሾፌሩ ታክሲውን ቀኝ መስመር በማስያዝና ፍጥነቱንም ቀነስ በማድረግ “ደግሞ ዛሬ ምኗን ነው የጣለብኝ? ኮሜርስ እንጂ አዚጋ መውረድ አትችዪም ስትባዪ አትሰሚም እንዴ?” አሏት ንዴት በተቀላቀለበት ቅላፄ። “ኮሜርስ መውረድ ያለበት ኮሜርስ የሚሄድ ነው እኔ ባቡር ጣቢያ ነው የሚሄደው ስለዚህ ባቡር ጣቢያ ነው የምወርደው። ለምን አይገባችሁም?” ይባስ ተናደደች።

እኔን ጨምሮ ከነበርነው ተሳፋሪዎች አንድም ደፍሮ የተናገራት የለም። ሁላችንም ፊልም የምናይ ነው የምንመስለው። እሷ ስትናገር እሷን፣ ሾፌሩ ሲናገሩ ሾፌሩን፣ ረዳቱ ሲናገር ረዳቱን እንመለከታለን።
“የኔ እህት እዚጋ ባወርድሽ እከሰሳለሁ! ታስከስሺኛለሽ” አሉ የልጅቷ አያያዝ ያላማራቸው ሾፌር።
“እኔ በወረድኩት ማን ምን አግብቶት ነው የሚከሳችሁ? የፈለኩት ቦታ የመውረድ መብት የለኝም እንዴ?” በማለት በሁኔታዋ ግራ ለተጋቡት ሾፌር ጥያቄዎችን አከታተለችባቸው።

ይህንን ስትናገር ምንም እንኳን በአነጋገሯ እና ሁኔታዋ የተማረች ብትመስልም አዲስ አበባ ስትመጣ ይህ የመጀመርያዋ ሳይሆን እንደማይቀር፣ የተነገራትም ምልክት ባቡር ጣብያ ስትደርሺ ውረጂ ከዚያ እንዳታልፊ! የሚል ሊሆን እንደሚችል፣ ሾፌሩና ረዳቱ ኮሜርስ ኮሜርስ የሚሏት ቦታም ከባቡር ጣቢያው በጣም የራቀ መስሎ የተሰማት እንዲሁም ስለ መንገድ ትራንስፖርት ህግ ያላት ዕውቀት ያነሰ እንደሆነ በመገመት ሽምግልና ገባሁ። 

ሾፌሩና ረዳቱ እሷን ለመጉዳት የተናገሩት አንዳች ነገር እንደሌለ፣ የአገላለጽ ችግር ቢኖርም ሃሳባቸው ትክክል እንደሆነ፣ኮሜርስ የሚባለው ቦታም (በታክሲው የፊት መስታወት እያሳየኋት) ቅርብ መሆኑን፣ እሷ ልውረድ የምትልበት ቦታ ለታክሲ ተሳፋሪን ለመጫንም ይሁን ለማውረድ በህግ የተከለከለ መሆኑን እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ እኔ ከሷ ጋር ወርጄ ባቡር ጣቢያ እንደምመልሳት ቃል ገብቼ የረዳቱን ሸሚዝ ጨምድዶ ይዞ የነበረውን እጇን አስለቅቄ በግድ አስቀመጥኳት።

አንዳንድ ጊዜ ሳስበው በስርዓተ ትምህርታችን ውስጥ መካተት እየተገባቸው ያልተካተቱ ነገር ግን በህይወት ዘመናችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችንን በብልሃትና በጥንቃቄ ለማከናወን ትልቅ ድርሻ ያላቸው ትሞህርቶች እንዳሉ ይሰማኛል። ለምሳሌም ስለ የመጓጓዣ ዓይነቶች (የአየር፣ የምድር እና የባህር) መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦቻቸውንና በአጠቃቀማቸውም ረገድ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ህግጋትና መመሪያዎችን ባማከለ መልኩ መሰረታዊ ዕውቀት ሊሰጥ የሚችል። ብዙ ጊዜ ስለ ትራፊክ አደጋ መከሰትና ስላስከተለው የአካል ጉድለት፣ የህይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት በተለያዩ የመረጃ ወይም የወሬ ማሰራጫዎች እንሰማለን። እንዲህ ዓይነቱን መረጃ ትናንት እንሰማው ነበር ዛሬም እየሰማነው ነው። ነገስ መስማት አለብን?

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በዓመት ከ2000 በላይ የሚሆኑ ወገኖች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጣሉ። ከ8000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ይዳረጋሉ። ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ንብረት ይወድማል። የመኪና አደጋ መንስዔ ተብለው ዘወትር የሚገለጹት ምክንያቶች፡ የአሽከርካሪው የብቃት ማነስ፣ የመንገዱ ደረጃውን ያልጠበቀ መሆን፣ የተሽከርካሪዎች ብልሽት እና የእግረኞች የግል ጥፋት ናቸው።

የእነዚህ ምክንያቶች ቁልፉ ደግሞ የዕውቀት ችግር ነው። ለአሽከርካሪው በተግባር ልምምድ የተደገፈ መሰረታዊ የማሽከርከር ዕውቀት፣ ለመንገድ ሰሪዎች እና አሰሪዎቸ አግባብና ጥራት ያለው የመንገድ አሰራር ጥበብና ዕውቀት፣ ለተሽከርካሪ ባለቤቶችም ስለ ተሽከርካሪው ዋና ዋና አካላት ጥቅምና ጉዳታቸው የሚያስገነዝብ ዕውቀት እንዲሁም ለእግረኞችም መሰረታዊ የሆነ የመንገድ አጠቃቀም ዕውቀት ያስፈልጋቸዋል። ይህ ዓይነቱ ዕውቀት በአንድ ጀንበር የሚገኝ አይደለም። አንድ አደጋ ከተከሰተ በኋላ በባለስልጣናት በሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዴት ተደርጎ የህዝብን አስተሳሰብ ማጎልበት ይቻላል?

ስለ መንገድ አጠቃቀም ለአሽከርካሪም ለመንገደኛም መሰረታዊ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ መጻሕፍት በግለሰቦች፣ በአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም በመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን በየጊዜው ይታተማሉ። ተጠቃሚው ማነው ሲባል ግን መልሱ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት የፈለገ/የፈለገች ነው። ነገር ግን እግረኞችም ሊያውቁትና ሊመሩበት ይገባል። እስቲ ለአብነት ያክል በሀገራችን የመንገድ ስርዓት መሰረት በሁሉም መጻሕፍት ውስጥ የሚገኝ አንድ መመሪያ እንመልከት። ለተሽከርካሪ ክፍት በሆኑ መንገዶች እግረኞች የግራ መስመራቸውን ይዘው መጓዝ እንዳለባቸው ያስቀምጣል።
ታድያ ይህንን መመሪያ እግረኞች መጽሐፍቱን አንብበውና አውቀው ካልተገበሩት አሽከርካሪዎች ብቻ ስላወቁት ምን ያክል ውጤታማ ሊሆን ይችላል? ህጉንና ስርዓቱን ሾፌሩ ያውቀዋል ተሳፋሪው ግን በአጋጣሚ በሰማው አሊያም በደመነፍስ ይጓዛል። ከዚያም በመግቢያችን ላይ እንደተመለከትናት እህታችን እኛ ደስ ባለን ወይም በፈለግነው ቦታ ላይ አውርዱን እያልን እንጨቃጨቃለን ሌላ ጊዜ ደግሞ ታክሲ በማይቆምበት ቦታ ላይ ቆመን ታክሲ እንዳይቆም የሚከለክለውን ታፔላ ተደግፈን ታክሲ በመጠበቅ ጊዜ እናጠፋለን። ለነገሩ አንዳንድ የታክሲ ሾፌሮችም ቢሆኑ በልምድ እንጂ በመጻሕፍቱ ላይ ያሉትን መመሪያዎች እና የመንገድ ዳር ምልክቶችን ትርጉም ገብቷቸው አይደለም የሚያሽከረክሩት። ምክንያቱም መጽሐፉን ያነበቡት ለፈተና ብቻ ስለሆነ።

ይህ ባይሆን ኖሮ በጥቃቅን ስህተቶች የብዙ ወገኖቻችን አካል ሲጎድል፣ ህይወት ሲጠፋ እና ንብረት ሲወድም በየጊዜው ባልተመለከትን ነበር። አንዳንድ አሽከርካሪዎች በአንፃሩ ዕውቀትን ከስነ ምግባር ጋር አስተባብረው የያዙና በሙያቸው ምስጉኖች አሉ። ይህ ልዩነት ታድያ ለምን ተፈጠረ? ለምንድነው ሁሉን አሽከርካሪዎች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ማርሽ ሲቀይሩ ፍሪሲዮን መርገጥ ብቻ
የሚሆነው? አሽከርካሪውንና ተሳፋሪውን ከአደጋ ለመከላከል ይቻል ዘንድ የደህንነት ቀበቶ አድርግ እየተባለ የሚገደድ እና በዚህም ምክንያት የሚቀጣ አሽከርካሪ ከየት መጣ? የትራፊክ ፖሊስን ካላየ በቀር የትራፊክ ህግን የማያክብር አሽከርካሪን ማነው የላከብን? በታክሲው ውስጥ “ፍቅር ካለ ታክሲም ባስ ይሆናል” የሚል ጽሑፍ ለጥፎ የታክሲንና የአንበሳ ባስን የተሳፋሪ ቁጥር ልዩነት ለማጥበብ የሚጥር አሽከርካሪ ከየት ተፈጠረ?

ቢያንስ ቢያንስ የመንገድ አጠቃቀም ህጉን ከእግረኛው ይልቅ እኔ በተሻለ አውቀዋለሁ በማለት በእግረኛ ማቋረጫ ላይ ለእግረኞች ቅድሚያ በመስጠት ፋንታ ማቋረጫውን እንደ ንቅሳት የሚቆጥሩት፣ ትምህርት ቤቶች ባሉባቸውና ህዝብ በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ ውድድር የሚያምራቸውና ደቂቃ የማትሞላ ትዕግስት በማጣት ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለሀገራቸው የሚሆን ታላቅ ዓላማ የነበራቸው ወገኖቻችንን በወጡበት ያስቀሩብንን አሽከርካሪዎች ፈትቶ የለቀቀብን ማነው?
የአሽከርካሪዎችን ያክል ራሳቸው ተጎድተው ለሌሎች ጉዳትና ለንብረት ጥፋትም መንስዔ የሚሆኑ እግረኞችም አሉ። መቼም የእሳትን መፋጀት ያወቅነው ሁላችንም አንድ አንድ ጊዜ ተቃጥለን አይደለም። እሳት ያቃጥላል ተባልን እኛም አመንን ራሳችንንም ከእሳት እንጠብቃለን። ራሳችንንም ከትራፊክ አደጋ ለመከላከል የግድ አስቀድመን አንድ አንድ ጊዜ መገጨት አይጠበቅብንም።

መኪና ሰው ሊገጭ እንደሚችል፣ ገጭቶም አካል ሊያጎድል ከዚያም ሲያልፍ ሊገድል እንደሚችል ለማወቅ የግድ መንጃ ፈቃድ ሊኖረን አይገባም። ይህንን ለማወቅ እና ለማገናዘብ ሰው መሆናችን ብቻ ከበቂ በላይ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ እንሰሳት እንኳን መንገድ ላይ ሆነው መኪና ሲመጣባቸው እንዴት አንደሚሸሹ እናያለን። በኣርአያ ስላሴ የተፈጠረው ሰው ታድያ ከእንሰሳቱ በተሻለ እንዴት አያገናዝብ ለዛውም ለገዛ ህይወቱ።

አንዳንድ ጊዜ ግን ከእንሰሳቱ አንሰን እንታያለን። ለአንድ አቅጣጫ ብቻ እንዲያገለግሉ ታስበው የተሰሩ ነገር ግን በሁለቱም አቅጣጫዎች ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግሉ አንዳንድ መንገዶች አሉ። በእነዚህ መንገዶች በተለይ ከሁለቱም አቅጣጫ መኪኖች ሲመጡ ፍጥነታቸውን ቀንሰው በጥንቃቄ ነው የሚተላለፉት። በእንደእነዚህ ዓይነት መንገዶች ላይ ያለ መንገደኛ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባው መቼም ሌላ አካል እንዲነግረው አይጠበቅም።

 አስፋልቱን ለመኪኖቹ ትቶ ሊጓዝ እየተገባው መሐላ ያለበት ይመስል አስፋልቱን ላለመልቀቅ ሲታገል ጉዳት ቢደርስበት መኪናው ገጨኝ ነው ወይስ ገጨሁት ወይስ ደግሞ ተገጫጨን ሊል የሚገባው? መኪና ሰውን ሊገጭ እንዲሁም ሊገድል እንደሚችል ያላመነ ወይም የተጠራጠረ የሚመስል ሰው አጋጥሟችሁ አያውቅም?

የአንዳንዶቹማ እኮ አያድርስ ነው። ዕቃ ተሸክመው፣ ህፃናትን ይዘው፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተነጋገሩ፣ ተቃቅፈው፣ እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ሦስት አራት ሆነው ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዘው በጠባብ መንገድ ላይ የሚጓዙቱ ወይ ዳ ር አይወጡ ወይ ደግሞ ታርጋ አያወጡ ምን ሊባሉ ይሆን? እንደ ፀረ 6 ፀረ መኪና ተከትበው ይሆን እንዴ? በዜብራ ላይ መሻገር ላለመገጨት እንደዋስትና የሚቆጥሩና ያለምንም ጥንቃቄ በደመነብስ ለመሻገር የሚሞክሩም እኮ አሉን።

“ከስህተቱ የማይማር ፈንጂ አምካኝ ብቻ ነው” የሚል ፅሑፍ ታክሲ ውስጥ ማንበቤ ትዝ ይለኛል። ይህንን ፅሑፍ ብዙም አልስማማበትም። ምክንያቱም ግራ እና ቀኝ ሳይመለከት፣ የእግረኛ ማቋረጫን ሳይጠቀም እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሳያደርግ  መንገድ አቋርጣለሁ ሲል ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሰው እንዴት ብሎ ነው ከስህተቱ የሚማረው? በስህተቴ ተፀፅቻለሁ ብሎ ጉዳቱን undo ማለት ይችላል እንዴ? እንደ እኔ አመለካከት ግን አብዛኛው አሽከርካሪ እና እግረኛ መሰረታዊ የሆነ የመንገድ ትራንስ ፖርት አጠቃቀም ግንዛቤ ይጎድለዋል።

ይህንን ዓይነት የግንዛቤ እጥረት እስከ ወዲያኛው ለማስወገድ ደግሞ በትምህርት ቤት ውስጥ እንደ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች በመደበኛነት ትምህርቱን መስጠትን የመሰለ ምን አማራጭ ይኖራል? ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለየክፍል ደረጃው የተማሪዎቹን የማገናዘብ አቅም ባማከለ መልኩ ስለ የመጓጓዣ ዓይነቶች፣ ስለ መኪና ምንነት፣ ዓይነት፣ አሰራሩ፣ አጠቃቀሙ፣ አገዛዙ፣ አሻሻጡ፣ የሞተር ዓይነቶች ከነመመዘኛቸው፣ የጎማ ዓይነት እስከነመስፈርቱ፣ ከእያንዳንዱ የመጓጓዣ ዓይነት ጀርባ ያለው የምህንድስና ጽንሰ ሀሳብ፣ የመንገድ አጠቃቀም መመሪያዎች ወዘተ በቂ መረጃ ሊያስጨብጥ የሚችል የትምህርት ዓይነት ቢኖረን ምን አለበት?

እንዲህ ዓይነቱ ትምህርት ከታች ጀምሮ ቢሰጥ የተማሪዎችን ወደ ተለያዩ የምህንድስና ሙያዎች እንዲሳቡና ጥሩ የሆነ ዝንባሌ እንዲኖራቸው በማድረጉ ረገድም ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል። 10ኛ ክፍልን ካጠናቀቁ በኋላ በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡት ተማሪዎችም ይህንን መሰረታዊ ዕውቀት ይዞ መግባት ምን ያህል ውጤታማ ሊያደርጋችወና የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት አንደሚረዳቸው መቼም ግልጽ ነው።

እኅቶች እና ወንድሞች ታድያ ይህንን ትምህርት በስርዓተ ትምህርታችን ውስጥ ተካቶ ልንማረው አይገባም ትላላችሁ?

ቸር ያሰማን።

34 comments:

 1. ባክህ እሷን ተዋት እንደወረደች ትሆናለች ፤ በሷ ምክንያት ደሞ ከሲቪክስ ቀጥሎ የማይረባ ትምህርት እንማር ትለናለህ እንዴ፤ ይህን ሀሳብ ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ ነው፤ እነሱ ያስቡበት ከኑሮ ዘዴና ሲቪክስ፤ጋር ያዳብሉት፡፡ የዚች ሀገር የትምህርት ፖሊሲ በየ6 ወሩ ስለሚቀያየር ፤ አሁን ሀሳቡን ብታቀርብላቸው ከ3 ወር በኋላ ይፀድቃል ፤

  ReplyDelete
 2. “ “ፍቅር ካለ ታክሲም ባስ ይሆናል” የሚል ጽሑፍ ለጥፎ የታክሲንና የአንበሳ ባስን የተሳፋሪ ቁጥር ልዩነት ለማጥበብ የሚጥር አሽከርካሪ ከየት ተፈጠረ?”
  እችን መልሶ ታክሲ ላይ መለጠፍ ነበር

  ReplyDelete
 3. ahiya ina jib ayiwadedum yibalal. min malet meselachiwu mekina ina zebra ayiwadedum malet newu. zebrawu ahiya newu, mekinawu demo jib. Dani tiru miliketa newu wulachinim siletirafik hig mawek alebin.

  ReplyDelete
 4. "አንዳንድ ጊዜ ግን ከእንሰሳቱ አንሰን እንታያለን። ለአንድ አቅጣጫ ብቻ እንዲያገለግሉ ታስበው የተሰሩ ነገር ግን በሁለቱም አቅጣጫዎች ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግሉ አንዳንድ መንገዶች አሉ። በእነዚህ መንገዶች በተለይ ከሁለቱም አቅጣጫ መኪኖች ሲመጡ ፍጥነታቸውን ቀንሰው በጥንቃቄ ነው የሚተላለፉት። በእንደእነዚህ ዓይነት መንገዶች ላይ ያለ መንገደኛ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባው መቼም ሌላ አካል እንዲነግረው አይጠበቅም።"

  Dn. Daniel Rejim Edime ke'mulu tenan gar Egziabiher Yadililin.

  Ejig betam wesagn yehone mikir new. Mekari wendim Ayasatan.

  ReplyDelete
 5. ahiya ina jib ayiwadedum yibalal. ahiyawu zebra newu, jibu degmo mekina. Dani tiru iyita newu wulum yetirafik hig mawek alebet

  ReplyDelete
 6. Dear Daniel,

  Your analytical view is highly constructing. An estimated 1.3 million people are killed in road crashes worldwide each year and as many as 50 million are injured. For every death, 20-30 people are disabled, many permanently.

  Road crash fatality numbers are already comparable to the global deaths caused by tuberculosis or malaria. Road traffic injuries are the leading worldwide cause of death among young people aged 15 to 29, and the second most common cause of death for those aged 5 to 14. If significant preventive actions are not taken, the World Health Organization (WHO) estimates that
  by 2020 road trauma will rank as the sixth biggest cause of death.

  This important article took me 20 years back. When I was a cadet at Ethiopian Police College (Aba Dina), there was a course which is known as "Traffic Safety". In this course, the main causes to the traffic accidents are the road, the condition of the vehicle and the human element (drivers and pedestrians). Proper road engineering,enforcing traffic rules regulations, strict annual cheek up of the vehicles, and training to the road traffic participants are the way out to reduce and prevent traffic accidents.

  When we analyze the risk factors influencing crash involvement include speed, pedestrians, young drivers, alcohol,medicinal and recreational drugs, driver fatigue, mobile phone, in adequate visibility, road related factors and vehicle related risk factors are among others.

  In this sense, the training on the road traffic safety should be included on the normal school system. I do remember that the Addis Ababa Traffic police in collaboration with Rada Barner (Norwegian Save the Children) and the Addis Ababa City administration education bureau had done a lot to include road traffic safety in the formal curriculum of the primary school. I didn't know the status of this move. As a veteran professional, I suggested that we should work comprehensively beyond Sergent Assefa Mezgbu's daily traffic fatal report.

  ReplyDelete
 7. Thank you and GOD bless you. There are many peole specially in Addis ababa who think crossing the street carefully means being not modernized person or being a person who comes from countryside or rural area. The reverse is true in western countries or highly modernized and developed countries specially in th United States and Europe.We copy bad culture from but not the useful one.

  ReplyDelete
 8. ውድ ዳንኤል ክብረት
  "በትክክል!"
  የትምሀርት ሰርአቱ በጣም በጥንቃቄ ለህግር ተቆርቁሪና አሳቢ በሆኑ ምሁራን ስርዓተ ትምህርታችን እንደግና ትውልድ ሊያንፅ በሚቺል መልኩ ሊቀረፅ ይግባል። ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለየክፍል ደረጃው የተማሪዎቹን የማገናዘብ አቅም ባማከለ መልኩ የህግራቺንን ባህል ፣ወግ ፣ ሥራዓት ባግናዘበ ሁኔታ ሊዘጋጅ ተግቢ ነው እላለሁ ሌሎችም ይመርቁበት።
  ዘርያቆብ ይሁን
  ክደብረ ማርቆስ

  ReplyDelete
 9. You are making a good point but who has time for that? Don't forget we are living in a country where failed educational policiy is intentionally exercised to kill our kids.

  ReplyDelete
 10. እንዴት ያለ ምርጥ ሃሳብ አመጣህ፡ኑሮ ዘዴ፤እርሻ፤ሙዚቃ እኮ ተምረናል ጎበዝ፡፡ ታዲያ ዛሬ የመኪናው ቁጥር ከሰው ቁጥር እኩል ለመሆን በሚሮጥበት ዘመን ይህ ትምህርት ባይሰጥ ብቻ ነው የሚገርመው፡፡

  ReplyDelete
 11. አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን የመኪና አደጋ አሳሳቢነት እና አስከፊነት ለማየት የፈለገ ሰው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ለትንሽ ደቂቃ ያክል ቆም ማለት ብቻ በቂ ነው። በመኪና አደጋ ምክንያት መላ አካላቸው በደም ታጥቦ የሚመጡትን ህጻናት፣ ወጣቶችና አረጋውያንን በየደቂቃው መመልከት እንዴት ያሰቅቃል መሰላችሁ።

  ReplyDelete
 12. metadel new ager bit huno slagerbit mawrut.yeesrueil aemalak sdetenyawn hulu temelketew: teru new bertu::

  ReplyDelete
 13. ማላገጥ ጀመርክ አንተም??አሁን ይህ ምን የሚጻፍ ነው? አንዳንድ ግዚ አንባቢን ማሰብ ሳይጠቅም አይቀርም:: አለዛ "ደሞ ዛሪ ምን ጻፈ?" ከማለት ላናልፍ ነው እንዲህ ከወረድክ ዳኒ::አራምባና ቆቦ አትሁን please

  ReplyDelete
 14. ስለ መንገድ አጠቃቀምና ስለትራፊክ ደህንነት በሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ already ተካትቶ እየተሰጠ ነው። ስለ ሞተር ዓይነቶች፣ ወዘተ. በቴክኒክና ሙያ እየተሰጠ ነው። ሥርዓተ ትምህርቱ የበኩሉን እየተወጣ እንዳለው ሁሉ እናንተም ይህው የበኩላችሁን እያስተማራችሁ ነው። ሁሉም በየፊናው ሲረባረብ ነው የማህበረሰብ ለውጥ የሚመጣው። በርቱ።

  ReplyDelete
 15. ዳኒ እጅግ ጥሩ ሐሳብ ነው ያነሳኸው የመሞትና የመኖር ጉዳይ ወይንም ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች የሚያደርግ አደጋ፡፡ የሕንዶችን መጽሐፍ መምህር በነበርኩበት ጌዜ ሰርቼ ነበር፡፡ በጣም የሚገርሙ ጽሑፎችን የስነምግባር ትምህርቶችን ተካቶ ታገኝበታለህ፡፡ ለምሳሌ ወደ መኝታ ሲሄድ መታጠብ ፒጃማ ማድረግ መጸለይ መጸለይ በሁሉም አለና በሂንዱ በእስላም በክርስቲያን፡ ስለ የሕዝብ ስልክ አጠቃቀም ስለ ቧንቧ ውኃ፡፡ ትልቅ ስብከት ሊወጣው የሚችል ጽሑፍ unwise use of television የሚለው ለሰባት ዓመት ዕድሜ ልጅ የሚገርም ትምህርት ነው፡፡ እናም ምንም እንኳን ለብቻው ይሰጥ የሚለው ከበጀት ከፍላጎት አንጻር ቢከብድም በማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ውስጥ ተካቶ ቢሰጥ እጅግ መልካም ነው እላለሁ፡፡ ያውም በመጀመርያ ሳይክል መሆን አለበት በእኔ እምነት፡፡

  ReplyDelete
 16. ተው አንድአድርገን አንተ ግራ ገብቶህ ሰው ግራ ለማጋባት አትሞክር ዳኒ አሁን በያዝካት መረጋጋት ቀጥል ብዙዎች ያልታያቸው ነገር አለ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ፡፡ዐለበለዚያ ግን ዳኒ መስመር ትስታለህ

  ReplyDelete
 17. ማጨስ ክልክል ነው!
  ማፏጨት ክልክል ነው!
  መሽናት ክልክል ነው !
  ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል፣
  የቱ ነው ትክክል?
  ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ ፣
  “መከልከል ክልክል ነው” የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡

  በዕውቀቱ ስዩም ነው እንደዚህ ያለው፡፡ ዳኒ አንዳን ቦታዎች ማውረድም ሆነ መጫን ክልክል ነው የተባለባት ምክንያት አሳማኝ አይደለም፡፡ ለምሣሌ ከሜክሲኮ አራት ኪሎ በሚሄድ ታክሲ ውስጥ ተሳፍረህ ስላሴ አካባቢ ለመውረድ ብትፈልግ ክልክል ነው፡፡ የተከለከለውን ቦታ ርዝመት አስበው፡፡ ሁሌም ያበሳጨኛል፡፡

  በአጠቃላይ እኛ አገር የሚከለከሉ ነገሮች ብዙ ናቸው አንዳንዴም አስቂኝ ይሆናሉ፡፡ ደብረዘይት አየር ኃይል ማሰልጠኛ በር ላይ “ፎቶ ማንሳት ክልክል ነው” ተብሎ ተለጥፎ ታገኛለህ፡፡ ምኑን? በሩን ነው አጥሩን ? ለምን? የአባይ ድልድይን ፎቶ ማንሳት ክልክል ነው ይባላል፡፡ እኮ ለምን ? የሚገርመው ግን በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን እነዚህ የተከለከሉ ቦታዎች ምስል ማለፊያ መንገዳቸው፣ በርና መስኮታቸው ሳይቀር ማየት እንደሚቻል አያውቁም ?

  ለነገሩ አትውረዱ ከተባልን ምን ምርጫ አለን የረዳት እና የሾፌር ልብ ዝቅ ማድረግ አያስፈልግም ዝም ብሎ መጓዝ ነው፡፡
  ሌላው የሚያስቀኝ ክልክል ደግሞ ልንገራችሁ፣ ጠቅላይ ሚንስትራችን ወይም ደግሞ ከአሜሪካ ብቻ የሆነ ባለስልጣን በመንገድ ሲያልፍ፣ ባለመኪናው ባለበት እንዲቆም ፣ እኛ እግረኞቹ ደግሞ ፊታችንን ከመንገዱ በተቃራኒ አዙረን እንድንቆም ይታዘዛል፡፡ ምን ምርጫ አለ መቆም ነው፡፡ በግንባራችሁ ተደፉ ብንባለስ ?

  ReplyDelete
 18. ግራ እና ቀኝ ሳይመለከት፣ የእግረኛ ማቋረጫን ሳይጠቀም እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሳያደርግ መንገድ አቋርጣለሁ ሲል ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሰው እንዴት ብሎ ነው ከስህተቱ የሚማረው? በስህተቴ ተፀፅቻለሁ ብሎ ጉዳቱን undo ማለት ይችላል እንዴ? እንደ እኔ አመለካከት ግን አብዛኛው አሽከርካሪ እና እግረኛ መሰረታዊ የሆነ የመንገድ ትራንስፖርት አጠቃቀም ግንዛቤ ይጎድለዋል። Thank u Dani. Wektawi guday new yanesahew.

  ReplyDelete
 19. Biniam from Nashville TNNovember 24, 2011 at 6:45 PM

  ዳኒ እኔ ይህን ሳነብ ስስቅ ጀምሬ፥ በውሰጤ እያለቀስኩ ጨረስኩት ፣በእውነት ሁሌ ጸሁፍህ የረቀቀ ነው ምን አለ ሌሎቻችንም ከመተቸት ፣ የተማርንበትን እንዳንተ በሰራንበት ።
  ታድያ ዳኒ ይህን ሳነብ ያስቀመትከው ችግር እንዳለ ሆኖ ፣ እኔ ግን እያንዳንዱን ከቤ/ክ ችግር ጋር ሳያይዝ ጨረስኩት ። ሁሌም እንደምትለው ችግሩን ማወቅ መፍትሄውን ያመጣልና ማወቅም ብቻ .... ፦ ምንአለ አንተን እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ መሪ ቢያደርግህ እንደ ብላቴናው ቅዱስ ዳዊት
  ለውዳሴ ክንቱ ያይደለ ...

  ReplyDelete
 20. ለምንድነው ሁሉን አሽከርካሪዎች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ማርሽ ሲቀይሩ ፍሪሲዮን መርገጥ ብቻ የሚሆነው?
  Well said!!

  ReplyDelete
 21. አትተቹ ባይባልም ፣ ሁሉም ሃሳቡን በነጻነት የመስጠት መብት ቢኖረውም አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ግን ከነባራዊ ሁኔታዎች ወጣ ባለ መልኩ ሲተቹ ያሳዝናል። ለምሳሌ "ምን አገባን" ያሉ አንባብያን አሉ። እንዴት አያገባንም? እንዴስ አያስጨንቀንም። እየጠፋ ያለው የወገን ሕይወት ነው። ምናልባት ጥንቃቄው አያስፈልገንም በሚል ድርቅና ከጸናን የነገዎቹ ተረኛ ጉዳተኞች እኛ ልንሆን እንደምንችልም መታሰብ ያለበት ይመስለኛል። በተጨማሪም "የወረደ ሃሳብ" በማለት አስተያየት የሰጡም አሉ። የአመለካከት ችግር ይመስለኛል። ከሕይወት በላይ ከፍተኛ ነገር ኖሮ ነው አሁን የመንገድ ትራፊክ አደጋ የወረደ የተባለው። ይህ እንዲህ ከተባለስ "የወጣው ነገር" የቱ ነው? ለማንኛውም ነገሮችን ስናስብ በሰፋ አዕምሮ እንደ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ሊሆን ይገባል እላለሁ። አለበለዚያ ግን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንዳለው "አንድ አንድ ጊዜ ካልተገጨን፣" የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ጉዳይ የማይገባን ልንሆን ነው ማለት ነው። ልብ ይስጠን።

  ለጸሐፊው ያለኝን አክብሮትና አድናቆትም አያይዤ መግለጽ እወዳለሁ። በሁሉም መስክ ቁም ነገር ስታስጨብጠን እንደኖርክ ሁሉ አሁንም ስለመንገድ ትራፊክ ደኅንነት በጣፋጭ ቃላት ቀምመህ አቅርበህልናልና ዕድሜ ከጤንነት ተመኘሁ።

  ReplyDelete
 22. Tnx Dani GIN ENEM AND NEGER "WERAJ ALE" LILIH ASEBKU. YAN BOTA ENEM TENKIKE AWKEWALEHU, KALWEREDIKU BIYEM TEKERAKREBETALEHU. LECHEMIRILIH YEFELKUT SETYEWA BICHA AYDELEM YETESASATECHIW, BIZU GIZE SHAGER BILEW LEGEHAR MENEHARIAW FITLEFIT YAWERDALU. ENDEWUM "GIBU, COMMERCE SANASHAGER LEGEHAR FITLEFIT ENAWEDACHIHUWALEN BILEW EKA YEYAZU YERUK MENGEDEGNOCHIN YEMICHINUBET WEKIT ALE. ENA ENEM YIHE EDIL BIZU GIZE TETEKIME AND KEN YIZIGN SIHED ZERAF BIYALEHU. YEGHA CHIGIR ZERFE BIZU NEW. ENDE ANTE SETYO ADDIS ABEBAN MAWEKINA ALEMAWEK BICHA AYDELEM. ENDEWUM LAWEKUTINA LENORUT GIRA YAGABAL. HIGU BEMENOR YEMITAWEK SILALHONE. HIGU SEWOCHIN KADEGA YEMITEBIKINA, GUZOWACHEWUNIM YEMIYASALIT AYDELEM ANDANDE. LEMISALE ANTE ENDETEKESKEW HUNETA YETAXI MEWUREJA ENA YEKIFLE HAGER MENEHARIA ARAMBANA KOBO NACHEW. BEMEKINAWOCH WUSIT EZIH LELAW HAGER LETESAFARI MEREJA KEMNIGERINA KEMELETEF YILIK "SHOFERUN MANEGAGER ...." ENA MESEDADEB YIBEZAL.......lemanignawun bizu bizu yemiyanegagir re'es silanesah tnx again

  ReplyDelete
 23. kabetachen masetamare enejamer.thankyou dn

  ReplyDelete
 24. እግረኛ እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ የምታውቀው መኪና ስታሽከረክር ነው፡፡ ለምሳሌ ባለ ሁለት መተላለፊያ መንገድ ላይ የእግረኛ መንገዱን ትቶ ለዛውም ለሚማጣው መኪና ጀርባውን ሰጥቶ የሚሄድ እግረኛ የሒወቱን ነገር ለአሽከርካሪው አደራ ሰጥቶ የሚጓዝ ሰው ያለበት ከተማ ማየት እንዴት እንደሚጨንቅ አሽከርካሪ ያውቀዋል፡፡

  በሰላም ውለን እንድንገባ እግዚያብሔር ይጠብቀን

  ReplyDelete
 25. አስፋልቱን ለመኪኖቹ ትቶ ሊጓዝ እየተገባው መሐላ ያለበት ይመስል አስፋልቱን ላለመልቀቅ ሲታገል ጉዳት ቢደርስበት መኪናው ገጨኝ ነው ወይስ ገጨሁት ወይስ ደግሞ ተገጫጨን ሊል የሚገባው? መኪና ሰውን ሊገጭ እንዲሁም ሊገድል እንደሚችል ያላመነ ወይም የተጠራጠረ የሚመስል ሰው አጋጥሟችሁ አያውቅም? በትክክል አይተህልኛል! አንዳንዱ እኮ ጥሩንባ እንኳን ብትነፋለት በጭራሽ አይሰማህም። ሲያናድድ!!

  ReplyDelete
 26. I support Tade Tekle's idea Tnx Dani.

  ReplyDelete
 27. ታድያ ዳኒ ይህን ሳነብ ያስቀመትከው ችግር እንዳለ ሆኖ ፣ እኔ ግን እያንዳንዱን ከቤ/ክ ችግር ጋር ሳያይዝ ጨረስኩት ። ሁሌም እንደምትለው ችግሩን ማወቅ መፍትሄውን ያመጣልና ማወቅም ብቻ .... ፦ ምንአለ አንተን እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ መሪ ቢያደርግህ እንደ ብላቴናው ቅዱስ ዳዊት
  ለውዳሴ ክንቱ ያይደለ ...

  ReplyDelete
 28. ዲ/ን ዳንኤል ዛሬ ጠዋት በኢቴቪ ከአንድ ሰዓት ዜና በኋላ ጉዞ በሚለው ፕሮገራም በመኪና አደጋ ልጆቻቸውን ያጡ እናቶች እና አንድ ባለቤቱን ያጣ ወጣት የተሰማቸውን ሀዘን እና የደረሰባቸውን ጉዳት ሲገልፁ እንዴት አንጀት ይበላ ነበር መሰለህ። ግን መፍትሔው ምንድነው???

  ReplyDelete
 29. "መቼም የእሳትን መፋጀት ያወቅነው ሁላችንም አንድ አንድ ጊዜ ተቃጥለን አይደለም። እሳት ያቃጥላል ተባልን እኛም አመንን ራሳችንንም ከእሳት እንጠብቃለን። ራሳችንንም ከትራፊክ አደጋ ለመከላከል የግድ አስቀድመን አንድ አንድ ጊዜ መገጨት አይጠበቅብንም።" Very amaizing I'm Alemu

  ReplyDelete
 30. hi dani arif new ke facebook ketye yehen new yemthkemew

  ReplyDelete
 31. የመንገድ ደህንነት ትምህርት በአንደኛ ደረጃ በተለያዩ ትምህርቶች ውስጥ ተካቶ እየተሰጠ ሲሆን በእርግጥ ከችግሩ ስፋት አንጻር ሰፋ ባለ መልኩ ሊሰጥ ይገባል

  ReplyDelete