በኢጣልያ በረሃዎች
ሻምበል አብዲሳ አጋ በአርበኛነት ጀብዱ የሠራ ኢትዮጵያዊ ታሪክ
click here for pdf- ሁለተኛ እትም ፡- 2004 ዓም
- አሳታሚ፡- ጃዕፋር የመጻሕፍት መደብር
- ዋጋ ፡- 50 ብር
ስለ አብዲሳ አጋ እሰማ የነበረው ሕፃን ሆኜ ነው፡፡ ይህንን መጽሐፍ ሳነብ ኀዘን ነበር የሚሰማኝ፡፡ ይህች ሀገር ግን ምን ዓይነት ሀገር ናት? እያልኩ ደጋግሜ እጠይቅ ነበር፡፡ መጽሐፉ ፋሽስት ኢጣልያ በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ግፍ ያሳያችኋል፡፡ ከኢትዮጵያ እስከ ሶማልያ፣ ከሶማልያ እስከ ጣልያን በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን መከራ እንደ ፊልም ታዩበታላችሁ፡፡ የነጻነት ዋጋው ምን ያህል እንደሆነ ትተምኑበታላችሁ፡፡ እነዚያ ወገኖች ለነጻነታችን የከፈሉትን ዋጋ እና እኛ በነጻነታችን የሠራነውን ሥራ ስትመዝኑት ታፍራላችሁ፡፡
አብዲሳ አጋ በምዕራብ ኢትዮጵያ በተረደገው ውጊያ ተማርኮ ነው ጣልያን የተወሰደው፡፡ በጣልያን እሥር ቤት ውስጥ ሰው ሊቀበለው ከሚችለው በላይ ግፍ ተውሎበታል፡፡ አንድም በእሥረኛነቱ፣ አንድም በጥቁርነቱ፡፡
በኋላ ግን ብርድ ልብሱን ተልትሎ እንደ መሰላል በመሥራት ከሌሎች ሀገር ዜጎች ጋር ከእሥር ቤት አመለጠ፡፡ በዚያው በጣልያን በማያውቀው ምድር የአርበኞችን ጦር እየመራ ወገኖቹን የሚያሰቃየውን ፋሽስት ተፋልልሞታል፡፡ በጀግንነቱ የተነሣ ጣልያኖች ስሙን ሲሰሙ ይሸበሩ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ የጣልያን ጎረምሶች ጥቁር ቀለም እየተቀቡ አብዲሳ አጋ ነን እያሉ ሕዝቡን ያስጨንቁት ነበር፡፡
ጣልያንን በጣልያን ምድር ተዋግቶ አሸነፈው፡፡ ከእንግሊዝ ጦር ጋርም በድል ተቀላቀለ፡፡ ጥቁር መሆኑ ከድል በኋላ ሽልማትን ሳይሆን መከራን አመጣበት፡፡ ዜግነቱን እንዲቀይር የተጠየቀውን ጥያቄ ባለመቀበሉ በአርበኛነቱ ጊዜ ወንጀል ሠርቷል ተብሎ እንዲከሰስ አደረገው፡፡ የተከሰሰበት ሳይገለጥለት፣ እንዲከራከር ሳይፈቀድለት በነጭ ዳኞች የ32 ዓመታት እሥር ተከናነበ፡፡
በኋላ ግን እሥሩ ወደ ገንዘብ ተለውጦለት የእንግሊዝ መንግሥት ከፍሎ አስወጣው፡፡ ከዚያም በኋላ ቢሆን ካናዳዊ፣አሜሪካዊ እና እንግሊዛዊ እንዲሆን ተለምኖ ነበር፡፡ ድኻዋ ሀገሬ ትበልጥብኛለች ብሎ እምቢ አለ፡፡
ሀገሩ ሲገባ ብዙ መከራ ነው የደረሰለት፡፡ እንግሊዞች የሻለቃ መዓርግ ቢሰጡትም ኢትዮጵያ ግን እንደገና ሠልጥነህ እቀጥርሃለሁ አለቺው፡፡ ስሙን የማጥፋት ዘመቻ ተከፈተበት፡፡ እንግሊዞች የከፈሉለትን ዕዳ የመክፈል ፈተና ገጠመው፡፡ ያ ዓለምን ያስደነቀ ጀግና፣ ያ እባክህ የኛ ዜጋ ሁን ተብሎ የተለመነ ጀግና፣ ያ ዓላም ታሪኩን ሊሰማ የሚጓጓለት ጀግና ሀገሩ ገብቶ ልጆቹን ማሳደጊያ አጣ፡፡
«ፍዳው ያላለቀለት በሬ ቆዳው ለነጋሪት ይሆናል» ይላል አብዲሳ በሀገሩ የገጠመውን መከራ ሲገልጠው፡፡
መጽሐፉን ግዙና አንብቡት፡፡ በዚያውም ግን ኢትዮጵያ ለጀግኖች የምትስማማ ሀገር ናት? ጀግና መፍጠር እንጂ ጀግና መንከባከብ የማንችለው ለምንድን ነው? አሁን አብዲሳ አሜሪካዊ ወይንም እንግሊዛዊ ቢሆን ኖሮ ዕጣ ፈንታው ይህ ይሆን ነበር? እያላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡
በሮም አደባባይ የኢትዮጵያ ባንዴራ ሲደፈር አይቶ በጀግንነት ጠላትን ያንጎራደደው አብዲሳ አጋ በእሥር ቤት ጠያቂ አጥቶ በብስጭት እንደ ሞተ በመጽሐፉ ውስጥ ሳነብ «ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ» የሚለውን ግጥም የገጠመው ሥጋ እና ደም አለመሆኑን ዐወቅኩ፡፡ በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ዘወር ብሎ አላየውም፡፡ ዘርዐይ የደረስን የገደለው የመረሳቱ ብስጭት ነው፡፡
እስኪ አንቡና እንደኔ ተቃጠሉ፡፡
wed D danal bagerachen yemedereg manegnawm neger hulu yemeyakatel yemenegebegeb new tenegero tenebo tesemeto yemayesetekakel silehon ulem mekatel new
ReplyDeletebetam yemigerm tarik new dani kezi befit yehenen tarik anbebwalehu neger gen endh alterdahutem esti kelbe hogne anbwalhu,tank you ,dani kalehywet yasmalen.
ReplyDeletehe was a man
ReplyDeleteEthiopia and cat mother are the same. They eat their hero with out heasitet.
ReplyDeleteTo whom does this country really belong? Fitsum
ReplyDeleteአዎ አዎ አዎ! ያማል ስለዚህ ጀግና ታሪክ ውለታ አመላለስ ሲሰማ:: ያንገበግባል!
ReplyDelete1. ሻምበል አብዲሳ አጋ:
2. ለተናል ጀነራል ጃገማ ቄሎ:(የበጋው መብረቅ የሚለው ታሪካቸውን ፍቅረ ማርቆስ ደስታ ከሽኖታል):: አሁን ድረስ በሕይወት አሉ፡ አንብበን ልብ እንበል::ዕድሉ ያለን በሀገር ቤት ያለን እንጠይቃቸው::
እነዚህስ ይህንን ታሪክ የሠሩት ከ15-18 ባለው ዓመታቸው ጀምረው ነው:: የትላንቱ የእነርሱ ተጋድሎ ለዛሬው ለእኛ በኩራት መሄድ ትልቅ ቦታ አለው:: ዛሬ ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጣንበትን ሳይሆን ያሸነፍንበትን ማክበራችን ትርጉሙ ሊገባን የሚችለው ወይ እነዚህን መጻሕፍት ስናነብ ወይም ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ጓደኞቻችን በቅኝ ግዛት የደረሰባቸውን መከራ ሲያወጉን ብቻ ይሆናል::
እነዚህ ጀግኖች በንግግራቸው: በተጋድሏቸው: እና በማንኛውም ውጣ ውረዳቸው ውስጥ የሚያስተምሩን እኔ ሠራሁ አይሉም፤ እግዚአብሐር ረድቶኝ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ብለው ነው የሚናገሩት::
ገንዘብ እና ዝና አይገዛቸውም፤ የግል ስብዕና:የራስ ወኔና ማንነት ብቻ ነው የሚገዛቸው::
አንድ ጊዜ በአንደበታቸው ሲናገሩ የሰማሁት ጀነራል ጃገማ ቄሎን ጃንሆይ ልዳርህ ቢሏቸው አሻፈረኝ አልፈልግም ብለው አቡነ ባስልዮስን ሽምግልና ልከው "እኔ የምወዳት ልጅ አለችኝ ከእርስዎ ጋር አልዛመድም" ብለው በእምቢታ የራሳቸውን መንገድ ሲመርጡ የጀነራል ፍላጎታቸውና ሀሳብ የነበረው "ከእርሳቸው ብዛመድ የንጉሱ አማች ሆኖ ነው ያለፈለት ይሉኛል" በሚል ነው::
ብቻ የእነርሱን ቅን ልቦናና ተግባራዊ ሀገር ወዳድነት ይስጠን እላለሁ::
On his grave, at Holy Trinity cathedral,Abdisa Agga is labled as Lieutenant colonel. That is a match higher post than Shambel "major". It shold be rectified, if its a histroy book! don't you think?
ReplyDelete"እኛ በነጻነታችን የሠራነውን ሥራ ስትመዝኑት ታፍራላችሁ፡፡ "
ReplyDeleteአይ ዳኒ
ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ሀገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሁነው መኖር ከጀመሩ ዘመናት አልፈዋል ያሁኑ የህውሀት አገዛዝም በዘርና በገንዘብ ላይ የተመሰረተ ጥላቻና በቀል የተሞላበት መንግስት እንጂ ታግየለታለሁ የሚለውን ነጻነት ትርጉሙን ለውጦ ልማት ብሎ ነጻነትን ረገጦ የልማት መንግስት ነኝ እያለ ሌላው ጣሊያን ሆኖ ከጫካ ካወጣበት ጊዜ ጀምሮ ራሱን በምኒሊክ ቤተመንግስት አስቀምጦ ንጉስ ሆኖ ተኮፍሷል:: ታድያ አርቲስት ታማኝ እንዳለው" ነጻነት የለም እንጂ ልማትንማ ጣሊያንም ባጭር ጊዜ በመንገድ ስራ ኢትዮጵያን አገናኝቷታል" እንዳለው እንዲያውም የወቅቱ ባንዳወችና የኢትዮጵያውያን ስቃይ የማይታያቸው ነጋዴወች ምነው ጥሊያን ትንሺ ቢቆይ ብለው ነበር እንደሚባለው ባሁኑም ሰአት የኢትዮጵያውያን ስቃይ የማይሰማቸው ነጻነት አለ ብለው ሲናገሩ ይሰማሉ :: እውነታው ግን እኛም ዝም እንድንል ስንደረግ ወያኔም የአብዲሳ አጋን ለጆችን እየበላ ይገኛል :: ጋዜጠኞች ስለጻፉ ታሰሩ ተገረፉ ተገደሉ እኛም ፈሪ ሆነን በአናኖመስ እንደ መንፈስ እንጮሀለን ከደፈርንም ባሺሙር እረወዲያ አያ እንዲያው ለነገሩ ለጨዋታው ነው እንጂ እኛኮ መንፈስ እንጂ ቁስ አይደለንም አይደል ዳኒ::
አይ ጫካ እ ጫካ ጠፋ አብዲሳጋን አምጥተህ የተኛውን ልቤን ትቀሰቅሳለህ?
hulem mekatel new.
ReplyDeleteዳኒ “ተቃጠሉ!” አልህ? እኔ ግን “እንኳን ወደ ተቃጣዮቹ ማኅበር በመቃጠል መጣህ እልሃለሁ፡፡”
ReplyDeleteእስካሁን ባነበብኋቸው መጻሕፍትና ባየሁት የተቃጠልሁት ይበቃኛል፡፡ እዚህ ሀገር የሚያዋጣ ሆኖ የሚታየው “ራስን ማዳን” ብቻ ነው፡፡ አጎብዳጅነት፣ አቆላማጭነት ባህላችን ሁኗል፡፡ ራስን ዝቅ በማድረግና ጫማ በመላስ መካከል ያለው ልዩነት ፈጽሞ አይታየንም፡፡ ይህንን ማየት የሚፈልግ የደቂቀ እስጢፋኖስን፣ የአጼ ቴዎድሮስን፣ የገብረ ሕይወት ባይከዳኝን፣ የራስ እምሩን ፣ የፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያምን፣ የበላይ ዘለቀን፣ የታላቁን ሰው የከበደ ሚካኤልን ታሪኮች እንዲሁም ስለ አብዮቱ የተጻፉ ጽሑፎችን ያንብብ፡፡ ሰው መሆን ማለት መብላትና መጠጣት የሚችል ፍጥረት ማለት እንዳልሆነ የሚያምን ከሆነ ጭንቅላቱን ይዞ ያለቅሳታል፡፡ (መምህር እሸቱ እንዳሉት “የማይነበብበት ዓይን ባዶ ቤት የሚበራ አምፖል” ነውና፡፡)
በቀደምለት ከአባቴ ጋር ስናወጋ ፊታውራሪ ዘውዴ ገብረ ሕይወት የተባሉ የንጉሡ ዘመን ባለሥልጣን በቤተ መንግሥት አካባቢ ምክራቸውን የሚቀበላቸው በማጣታቸው የተነሣ “ሙት ይዞ ይሞታል!” እያሉ ይማረሩ ነበር ብሎ አጫወተኝ፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ ድንቁርና የነገሠችበትና ከመጠየቅና ከመመርመር ይልቅ መልመጥመጥ የሠለጠነበት ማኅበረሰብ ሕያው ነው ብሎ መከራከር አይቻልም- ሙቷልና፡፡ አዎን ድብን ብሎ ሙቷል፡፡ (ለዚህ ሳይሆን ይቀራል ዘማሪዎቹ ኪነጥበብና ይልማ “ትንሣኤሽን ያሳየን” ያሉት?)
እንዲህ ዓይነቱ ማኅበረሰብ ታዲያ ክፋቱ መሞቱ ብቻ ሳይሆን መሞቱን አለማወቁ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ ያንን የዛገ ኑረት (ለመለወጥ የሚነሡት ሰዎች በሙሉ ስም ተለጥፎላቸው፣ ተንቀው፣ ተዋርደው፣ ተንቋሽሸው በብስጭት እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡ አንዳንዴ ሳስበውማ ኢትዮጵያውያን ከኢየሩሳሌማውያን (እስራኤላውያን) ጋር ከነበራቸው የጠበቀ የዘመናት ቁርኝት የተነሣ የወሰዱት “ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፤ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፡፡” የተባለውን እርግማን ወይም ክፉ ልማድ ይመስለኛል፡፡ ለዚህች ሀገር በጎ ሊሠራላት ብሎ የተጠቀመ ሰው እጅግ በጣም ጥቂት ነው፡፡ ሁልጊዜም የአእምሮ ሶፍትዌራችን ከማድነቅ ይልቅ ማነቅ ይበረታበታል፡፡ ተቃርኖውና ምጸቱ ደግሞ እንዲህ ዓይነት “በማኅበረ ዝእብ” ፍልስፍና የሚመራን ሕዝብ “ሃይማኖተኛ” ብሎ መጥራቱ ነው፡፡ እንዲህ አድርጎም ሃይማኖተኛ የለ! ድንቄም!
ዳኒ እኔም አንደኛ ደረጃ ሳለሁ እንዲሁ በለጋነት እድሜ እሰማው ስለነበረው ጀግና አንብበን እንድንረዳ ስለጋበዝከን አመሰግንሃለሁ፡፡ ያለሁት ከአዲስ አበባ 300 ኪ.ሜ ደብረ ማርቆስ ከተማ ስለሆነ እዚህ ባሉት የቤተ መጻህፍት መደብሮቻችን ካገኘሁት እኔም አንብቤ እንዳንተ እቃጠላለሁ!!፤ ከመቃጠል ባለፈማ አቅም የለማ፡፡ ለማንስ ይጮሃል?ዛሬም ቢሆን በተለያዬ የሙያ መስክ የተካኑ ጀግኖቻችን የእኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፤ እኛ ጋ ተፈጠሩ፤ ስላልተቀበልናቸው የሌሎች አገልጋይ ሆኑ፡፡ "ዴርቶ ጋዳ"ም መልዕክቱ ይኸው ነው፡፡
ReplyDeleteአገራችን በሁሉም አቅጣጫ በመሃይምነት ተወጥራለች፡፡
ReplyDeleteDear Dani
ReplyDeleteIt has been about 27 years since I read the first book written by Lt Colonel Abdissa Aga himself.For the እንደኔ ተቃጠሉ፡ you seem late.I have only one comment on his military position.He was Lt colonel when he was Dead.Please see his grave in The Holly Trinity Church(Arat Kilo)I spent nearly a month by visiting his grave daily.
now am going to buy the book how could we replace our fathers. "Ethiopia hagere yemotelish kerto yegedelesh bella" what a saying. thanks dan.
ReplyDeleteጎበዝ በሁሉም ነገር ተቃጥለን፣ ተቃጥለን፣ ተቃጥለን አለቅን እኮ። የማቃጠያውን፣ የአቃጣዩን፣ የአቀጣጣዩን፣ የማቀጣጠያውን ቢቻል ማጥፊያውን ካለቻልንም ማርከሻ እና ማስታገሻውን ከተቀበረበት ፈልፍለን አውጥተን መቃጠል በእኛ ይብቃ ትውልድ ይዳን እንበል እንጂ። እህህ እስከ መቼ??? ዛሬ መፍትሔ ፍለጋ ላይ ያላተኮረ ቃጠሎ ቃጠሎን ከማባባስ በቀር ምን ትርጉም አለው?
ReplyDeleteHul gizem meqatel new Dani.
ReplyDeleteena zare yabalata taqataleqo.................eseka mache nawe yehanen hezebe.......................
ReplyDeleteመልካም ስራ የሰራ ሰው ሁሌም ቢሆን የአለም ምላሹ በተቃራኒው ነው ይህ ድሪጊት ደግሞ የሚቆም አይደለም ይሁን እንጂ መልካም ስራቸው ሁሌም ከመቃብር በላይ ይውላላ ፡፡
ReplyDeleteHi Dani,
ReplyDeleteI always appreciate your views. But the problem in your inscriptions is that it is always one-sided. You donot see the issues from different perspectives. His detention was ceased by the British before 32 years because of the mercifulness.There are also other stories back home that made him far from the local government. You did not show us that.
Dear Daniel;
ReplyDeleteThank you for letting us remember this guy. Luckily I know his grand son, the son of Ejigayehu Abdissa, A choreographer at the Ethiopian Army.
By the way Abdissa died suddenly after he announced to fight Said Barre of Somalia. I read this from the then Addis Zemen Gazeta.
ወይ ጉድ ወይ ጉድ
ReplyDeleteስንት አለ ያገር ጉድ
ጀግና ባገሩ ሲዋረድ
በባዕድ ሲወደድ
ሃገሬ ሃገሬ ብሎ ሲዋደቅ
ለናት ሃገሩ ለ ሰንደቅ
አይ አበዲሳ ሞትህ
ሲያሳቅቅ…
አይ ጀግንነትህ
ሲደንቅ…
አይዞህ አብዲሳ የኛ
አርፈህ እንዳተኛ
ዛሬም ብረድልብስ ተብትበህ
ከመቃብር ሆነህ
አሳየን የ ጀግና ክበሩን
የሃገር ፍቅሩን
good job dani. never mind biased comments but try to implement z constructive ones.
ReplyDeleteዳኒ 3 ጥያቄ አለኝ፡፡ አንደኛ መቃጠል ለማን ሲበጅ አየህ፡፡ ሁለተኛ መምህር የኔሰው ተቃጥሎ ምን አመጣ፡፡ ሶስተኛ እንቃጠል ብንልስ በስንቱ ተቃጥለን እንዘልቃለን፡፡
ReplyDeleteIt is shame for you to comment like this. Dani was not one sided. There was no any history that made Abdissa far from the Hailesillases regim. If it was there, it was a quit forged history. The only reason behined is that government is a 'cat mother' i.e, a mother eating here child as one of my friend said above.
ReplyDelete10Q! Dani
the only thing why he was treated like that and Gen. Jagama Kello forgotten like this is the deep rooted racial abuse of the Ethiopian politics.I believe if these heroes are from northern we may see a different history....at least we may hear a lot about them on today's Ethiopian media like the FM radios and 'gazettas'.
ReplyDeleteAny ways Thanks for your contribution.
አድዋ፤፤፤፤፤
ReplyDeleteየሴትነት ክብሯን ድንግልናን ሊወስድ፤
ከሩቁ ጠይቆ ከጥቁር ሊዛመድ ፤
የመጣን እንገዳ ለምን አሳፈርሸው ?፤
ቀሚስሸን ገልጠሽ ውስጥሽን ብትሰጭው ፣
ለአንቺም ክብር ነበር ነጭ በማግባትሽ ፤
ዘር ይዳቀል ነበር የማህፀን ፍሬሽ፡፡
ግን ሳይሆን ቀረና ኣንቺ ተግደርደረሽ ፤
የሙሽራን ልማድ ዋጋ ወጉን ይዘሽ፤
ጠያቂ ባልሽን እርቃኑን አጋልጠሽ ፤
በመጣበት እግሩ ሰድድሸው መልሰሽ ፡፡
ያንን ድርጊትሽን አለም ሁሉ አውቆብሽ፤
አንቺን ለጋብቻ ማን ሰው ይጠይቅሽ፡፡?
ይኼው እስከ ዛሬ ድንግልሽ ሙሽራ ፤
አድዋ ስላንቺ ከቶ ማን ሰው ያውራ::?
ሰውማ ታሪክሽን አያወራ ያዛባል፤
የማይታመን እውነት እንዴት ይታመናል፤
ይልቅስ በይ አውሪ የጫጉላ ወግሽን፤
ተራራሽ ይናገር አድዋ ስራሽን፤
ሰውማ ዝም ይበል ምንም ቃል አይተንፈስ
ምድረሽ ሰያወራ ነው የታሪኩ መቅደስ ፤
ሰው አቅም የጥረዋል፣
ዝም ይበል አይተንፍስ፡፡
ዝነኛው መኮንን