Wednesday, November 30, 2011

እሳቱ ከሌለ ጢሱ አይታይም


click here for pdf 
ሰሞኑ ሀገራችን አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ለማዘጋጀት ሽር ጉድ በማለት ላይ ትገኛለች፡፡ አሥራ ስድስተኛውን የአይካሳ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ፡፡ ሀገሪቱ እንዲህ ያሉ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤያትን ማዘጋጀቷ ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ መልካም ገጽታዋን ለማስተዋወቅ፣ በጉባኤ ቱሪዝም የሚገኘው ገቢ፣ ከሚመጡ ባለሞያዎች ጋር የሚኖረው የዕውቀት ልውውጥ፣ የሚፈጠረው የገበያ እና የሥራ ዕድል፣ ሌሎችም፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ይህንን መሰል ጉባኤያት የሚያስከትሉት አሉታዊ ነገርም አለ፡፡ ቅርሶች ወደ ውጭ የሚወጡበትን መንገድ በመክፈት፣ ባህልን በማበላሸት፣ ዝሙት አዳሪነትን እና ቁማርን በማስፋፋት፣ ለትውልድ እና ሀገር መበላሸት ክፉ አስተዋጽዖም ያደርጋሉ፡፡

ኮንፈረንስ ቱሪዝም የተስፋባቸውን የዓለም አካባቢዎች ስንመለከት ከላይ ያነሣናቸው አሉታዊ ገጽታዎች ጎልተው ይታዩባቸዋል፡፡ አካባቢዎቹ ችግሩን ለመቋቋም የሚወስዱት ርምጃ እንደ አመለካከታቸው ይወሰናል፡፡ ኳታር እና ላስቬጋስ እኩል አመለካከት የላቸውም፡፡ በላስቬጋስ ኃጢአት ራሱ ኃጢአት አይሆንም፡፡ አደንዛዥ ዕጽ፣ ዝሙት፣ ቁማር፣ ግብረ ሰዶም እና የራቁት ዳንስ ፈቃድ እስከወጣባቸው እና ግብር እስከ ተከፈለባቸው ድረስ ሕጋውያን ናቸው፡፡
በሌላ በኩል በኳታር እነዚህ ነገሮች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡ ከሀገሪቱ የእምነት እና የሞራል ሕግጋት ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸውም እንደ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ተቆጥረው ርምጃ ይወሰድባቸዋል፡፡ ወደ ቦታው የሚሄዱ ሰዎችም እነዚህን ነገሮች ዐውቀው እንዲጠነቀቁ ቅድመ መረጃ ይሰጣቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ አያሌ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ሀብቶች አሏት፡፡ ዓይነተኛ የሰው ልጅ የጥበብ ውጤቶች ሆነው ለገበያ ሊቀርቡ የሚችሉ ባህላዊ ምርቶች ሞልተዋታል፡፡ የአየር ንብረቷ እና የተፈጥሮ አቀማመጧ ሊጎበኝ፣ ሊታረፍበት የሚገባም ነው፡፡ እነዚህን ሀብቶቿን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ከምትሆንባቸው መንገዶች አንዱ ልዩ ልዩ የቱሪዝም ዘርፎችን ማስፋፋት ነው፡፡ በተለይም የኮንፈረንስ ቱሪዝም፡፡
በኮንፈረንስ ቱሪዝም በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎች ወደ ሀገር ስለሚመጡ፣ ሆቴሎችን እና የመዝናኛ ሥፍራዎችን ስለሚጠቀሙ፣ የሚውሉባቸው ቦታዎች በአንድ አካባቢ መሆኑ ለጥበቃ ስለሚመች፣ የትራንስፖርት እና የመገናኛ ዘዴዎችን በአንድ ጊዜ በማንቀሳቀስ ገበያ ስለ ሚፈጥሩ፣ እንደ መልካም ዕድል የሚታይ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ ሀገሮች ታላቅ ጉባኤያትን ለማዘጋጀት ይወዳደራሉ፣ መሠረተ ልማት ያሟላሉ፣ የማረፊያ እና የመዝናኛ ሥፍራዎች ይገነባሉ፣ የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋሞቻቸውን ያጠናክራሉ፤ የመገናኛ እና ትራንስፖርት መንገዶችን ይዘረጋሉ፡፡
ኢትዮጵያ አሁን አሁን አያሌ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና አካባቢያዊ ጉባኤያት ከሚደረጉባቸው ሀገሮች አንዷ በመሆን ላይ ናት፡፡ ይህ ደግሞ መንግሥትንም ሆነ ዜጎቿን የሚያስደስት ነው፡፡
እንዲህ ያሉ ጉባኤያት ሲዘጋጁ ግን አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዳንሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ ከሕዝቡ ባህል እና የሞራል እሴቶች፣ ከሀገሪቱ ጥቅሞች እና ቅርሶች ጋር የሚቃረኑ ተግባራት እግረ መንገዳቸውን እንዳይሠሩ ክፍተት የሚኖርባቸውን ቦታዎች ሁሉ ሊፈተሹ ይገባል፡፡
ከሰሞኑ ከሚካሄደው የአይካሳ 16 ጉባኤ ጋር በተያያዘ የሚነፍሱ ወሬዎች አሉ፡፡ በተለይም ከግብረ ሰዶም ጋር በተገናኘ፡፡ በዚህ እና በዚያ ቦታ ጉባኤ ሊያደርጉ ነው፡፡ እነርሱም ተገኝተው ሃሳባቸውን ያካፍላሉ፤ የሚሉ ነገሮች እየተሰሙ ነው፡፡
በጎረቤታችን በኬንያ በዚህ ረገድ በይፋ የሚሠሩ ተቋማት ይህንን ጉባኤ ምክንያት በማድረግ ዓይናቸውን ወደ ኢትዮጵያ መጣላቸውን የሚያመለክቱ ፍንጮችም እየታዩ ነው፡፡ በድረ ገጾቻቸውም እየገለጡ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሃይማኖት ሀገር ናት፡፡ 90 በመቶ በላይ የሆነው ሕዝቧ በእምነቱ ግብረ ሰዶምን ይቃወማል ብቻ ሳይሆን ይጸየፋል፡፡ የሀገሪቱ ሕጎችም ግብረ ሰዶማዊነትን በወንጀልነት ይፈርጃሉ፡፡ ከሕዝቡ እምነት ብቻ ሳይሆን ከባህሉ ጋርም የሚጣረስ ጉዳይ ነው፡፡
እንዲህ ያለውን ነገር በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዲስፋፋ የሚሠሩ፣ ሕዝቡም ያልበላውን የሚያክኩ ተቋማት እና ግለሰቦች አጋጣሚዎቹን እንዳይጠቀሙ የሚመለከተን ሁሉ በርግጠኛነት መከላከል ይጠበቅብናል፡፡
ግብረ ሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ፣ የግበረ ሰዶማውያንን መብት ካልደገፋችሁ አንረዳም እያሉ የሚያስፈራሩ ምዕራባውያን ኃያላን አሉ፡፡ ራሳችንን አጥተን የሚመጣ ርዳታ ለቀብር ማስፈጸሚያነት ብቻ የሚውል ነው፡፡ እናም እንዲቀርብን እንንገራቸው፡፡
የጉባኤው አዘጋጆችም ቢሆኑ ወደ ጉባኤው ለሚመጡ እንግዶች የኢትዮጵያን ሕግ እና የሞራል እሴቶች አስቀድመው የመግለጽ እና የማስጠንቀቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ተሳታፊዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ እና ላስቬጋስ ውስጥ ሲሰበሰቡ ያለውን ልዩነት ዐውቀው መምጣት አለባቸው፡፡ በአዲስ አበባ እና በሳንፍራንሲስኮ መካ ከል ያለውን ልዩነት ሊረዱት ይገባል፡፡
የሀገራችን ሰው እሳቱ ከሌለ ጢሱ አይታይም ይላል፡፡ አሁንም ቢሆን ምናልባት በጎላ መልኩ አልወጣ ይሆናል እንጂ ያለ ምክንያት የግብረ ሰዶማዊነት ጉዳይ በዚህ ወቅት አልተነሣም፡፡ ጢሱ እንዳይታይ ከመጣር ይልቅ እሳቱ እንዲጠፋ ብንሠራ የተሻለ ውጤት እናመጣለን፡፡

55 comments:

 1. በቡኻ ላይ ቆረቆር ማለት ይህንን ነው፡፡ ከድህነት ወለል በታች ሰምጦ በእምነቱ እንኳን ተጠናክሮ ተስፋ እንዳይጥል በመተራመስ ላይ ባለ ሕዝብ ስብዕና የሚያጎድፍ ሕሊና የሚያቆሽሽ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር መሰማቱ አያሳዝንም፡፡ ምን ማድረግ እንደሚገባን የሚነግረን ባገኘንና የሆነ ነገር ባደረግን፡፡ መንግስት እንደሆነ እንዲህ ያለውን ትውልድ ገዳይ ነገር ያበረታታ ይሆናል እንጂ ይከላከለናል ብዬ በጭራሽ አላስብም፡፡ የሱን ነገር በጫት ቤት፣ በጭፈራ ቤት፣ በዝሙት ቤት፣ በሺሻ ቤት፣ በወሲብ ፊልም ቤት መስፋፋት አይተነዋል፡፡ ጠላትህን አትግደለው ቁማር መጫወት አስተምረው የሚል ብሂል የት እንዳነበብኩ ጠፋኝ፣ እንግዲህ ድምጽ በሌላቸው መሳርያዎች ተብሎ ተብሎ አላልቅ ያለ ትውልድ ምን ይበጀው ይሆን?

  ReplyDelete
 2. ለውይይት የሚሆን ጥያቄ አለኝ። 90% ያህሉ ግብረሰዶማዊነት ጀነቲክ ነው ይባላል። በዚህ ዙሪያ ብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንዳሉም ይነገራል። ታዲያ ጀነቲክ ከሆነ እነዚህ ሰዎች ላይ እንዴት መፍረድ ይቻላል? እግዚአብሔር በጥበቡ ነጻ እንዲያወጣቸው ከመለመን በቀር በማሰር በመግረፍ በመደብደብ የሚለቅ አይመስለኝም።

  ReplyDelete
 3. Gobez yichen hager temuagachua man new? Mengest tebyew zeme kale. If they couldn'r protect the right of more than 95% of the poplation? ooOOOOOOooooooo

  ReplyDelete
 4. ሰላም ዳኒ
  ትላንትና ማታ በvoa በዚህ ጉዳይ ላይ የሆነ ዘገባ እንደነበረ አንድ ጓደኛዬ አሁን ነገረኝ። እጅግ የሚሰቀጥጥ ጉዳይ ነው። መንግስት ለሀገሪቱ ህዝቦች የማንነት እሴቶች ላይ ቁማር አይጫወትም ብለን እናምናለን። አለበለዚያ ግን እሳቱ እንዲጠፋ መክፈል የሚገባንን ሁሉ እንከፍላለን። ቅዱስ እግዚአብሔር ይጠብቀን።

  ReplyDelete
 5. ትናንትና ከ12፡00 ሰዓት በኋላ አንድ መልዕክት በሞባይል ደርሶኝ ነበር በዚህ ሆቴል በግብረሰዶም ዙርያ ስብሰባ ይደረጋልና ስብሰባው እንዳይካሄድ ጸልይ የሚል፡፡ በእውነት ሁሉ ነገር ከገንዘብ ጋር የተያያዘበት ዘመን እጅግ ያሳፍራል፡፡

  ReplyDelete
 6. "ግብረ ሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ፣ የግበረ ሰዶማውያንን መብት ካልደገፋችሁ አንረዳም እያሉ የሚያስፈራሩ ምዕራባውያን ኃያላን አሉ፡፡ ራሳችንን አጥተን የሚመጣ ርዳታ ለቀብር ማስፈጸሚያነት ብቻ የሚውል ነው፡፡ እናም እንዲቀርብን እንንገራቸው፡፡"

  Dear Dn. Dani Egziabiher Yistilin.
  Egziabiher Kidist Hager Ethiopian Yitebikilin.
  Yihin kifu zemen kemayet yisewuren.

  ReplyDelete
 7. Egzio Meharine Kirstos! "Yetefaten erkuset be'Tekedese bota steayu, anbabiew yastewl!" weyew le'lejoche! thank you for bringing this to our att'n. Kesega fetena, Kemekera nefese yetebeken. Amen.

  ReplyDelete
 8. ዳንኤል እግዚአብሄር ይስጥልን እንድናዉቀዉ በማድረግህ
  ጉዳዩ ሁሉንም የሚመለከት ነዉና እሳቱ እንዲጠፋ መክፈል የሚገባንን ሁሉ እንከፍላለን።
  እግዚአብሄርም ይርዳን።

  ReplyDelete
 9. መንግስት ስለዚህ ጉዳይ ተኝቷል????ነገሩ ባህልን: ሀገርን: ቅርስን መሸጥ ....
  ጎበዝ ህዝቡስ ምን ይላል? በጥብቅ እንቃዎም: ባህላችንን እንጠብቅ::

  ReplyDelete
 10. Erebakachu alken eko!!!

  ReplyDelete
 11. It is very sad and hard news to read also in other mideas... Government even for his sake, the elites, religious people, the milioner wow very strange milioner poor ethiopians who are playing on the people from whom or his's collacting the money, others must think again and again as Daniel quote from this humble, gentle our father the stim is the sign of the time for the figer....so please every body do what you can do....I will what i can....especially christians you have a lot to do....we have been poor we might even continue but don't forget we never lost the gift from God.....let us try our best.I hope God will be on our front....

  ReplyDelete
 12. I have doubt that the government stop this evil act because they want this situation to take the advantage for their political agenda. why did the health minister suddenly appear to the press conference for religious heads and twist the program? can we provide demonstration against the conference? is there freedom of speech right now? do the government protect the peoples interest? we all know the answer. The government betrayed us so many times. we are confused. where is the end for our disaster? God help us

  ReplyDelete
 13. ወገኖቼ ይህንን አጸያፊ ተግባር ከልባችን የምንቃወም ሁሉ ተቃውሞአችንን በሕጋዊ መንገድ የማንገልጽበት ምክንያት ምንድን ነው? እባካቸሁን የምንችለውን ሁሉ በማድረግ የሃገራችንን ገጽታ እንገንባ!ይህንን ውርደት የማንቀበል መሆናችንን በመግለጽ የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን እንግለጽ:: ትናንት በጦርነት ያላገኝዋትን ሃገራችንን ዛሬ በማኅበራዊ ጉዳዮች ተገን ምዕራባዊያን የከፈቱብንን ጦርነት ለማሰነፍ እንነሳ::

  ReplyDelete
 14. This is what we want to read "--------""ራሳችንን አጥተን የሚመጣ ርዳታ ለቀብር ማስፈጸሚያነት ብቻ የሚውል ነው፡፡ """"
  """""ግብረ ሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ፣ የግበረ ሰዶማውያንን መብት ካልደገፋችሁ አንረዳም እያሉ የሚያስፈራሩ ምዕራባውያን ኃያላን አሉ፡፡ --እናም እንዲቀርብን እንንገራቸው"
  -----"ጢሱ እንዳይታይ ከመጣር ይልቅ እሳቱ እንዲጠፋ ብንሠራ የተሻለ ውጤት እናመጣለን፡፡ """" Dear reader PLease try to read and understand .selam lante tehun

  ReplyDelete
 15. ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

  እንኳን ለመስማትና ለመናገር ለማሰብም ከባድ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ የሃይማኖት አባቶችም መቃወም ይገባቸዋል፡፡ በእርግጥ አሁን ያሉት አባቶች በአብዛኛው ገንዘብ እንጂ ህገ እግዚአብሔር የሚያስጨንቃቸው አይደሉም፡፡ በግልጽ ባይነገርም ኢትዮጵያም ውስጥ ግብረሰዶም ፈጻሚዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ይህ ኮንፈረንስ ደግሞ እነዚህን የሚያበረታታና ቀጥሉበት የሚያስብል ነው፡፡

  ስለዚህ ሁሉም ማህበረሰብ ሊያወግዘው የሚገባ ነው፡፡ በተለይ የሃይማኖት ሰዎች ቴሌቪዥን ሬዲዮ ካለመክፈት፣ ሆቴላቸውን ካለማከራየት ጀምሮ ማንኛውንም እርምጃ በመውሰድ ሊያወግዙት ይገባል፡፡ በሎጥ ዘመን የወረደው መዓት አሁን አይመጣም ማለት እግዚአብሔር የለም እንደማለት ይቆጠራል፡፡

  አይ ስምንተኛው ሺህ ፡፡ አይ እማማ ኢትዮጵያ ፡፡
  ከሚመጣው መዓትና ቁጣ በድንግል ጸሎት ይጠብቀን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 16. if we are unit we can move mountains /goliad / from ethiopia oh GOD keep the holy land

  ReplyDelete
 17. FREEDOM AND RIGHT SHOULD HAVE RESTRICTION IN ETHIOPIA IN RELATION TO GAY ISM & LESBIANISM.WE HAVE TO SHOW 0 TOLERANCE OR SUCH MOVEMENT.

  ReplyDelete
 18. dani i allways affraid such type of new GOD BLESS ETHIOPIA DAGMAWIT FROM NAZRETH

  ReplyDelete
 19. ዲን ዳንኤል በትትክለኛው ሰዓት ነው ይህንን እይታ ያወጣከው፡፡ ከለፈ በኋላ ቢጻፍ ምን ሊረባ ስለዚህ ቤተክርስቲያን በአውደምረት ላይ ይህ ነገር ሐጢያት፣ አስፀያፊ እና የሞራል ውድቀት እንደሆነ ለልጆቿ በግልጽ ልታስተምር እና ልትታደጋቸው ይገባል ሌላው እያንዳንዱ ቤተሰብ ስለ ልጁ ምን አይነት ጉድ እንደመጣብን ሊነግረው ይገባል፡፡ በቼም ማስሚዲያ የንቃተ-ህሊና ስራ ይሰራልናል ብለን አንጠብቅም ስለዚህ ጐበዝ እኛው ለኛው ነውና ከእግዚያብሔር እና ካማላጃችን ከድንግል ማርያም ጋር ይህንን ቆሻሻ ባህል ከእኛ እናርቅ

  እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

  ReplyDelete
 20. በስነምግባር በኩል መንግስት ብዙ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ የስራ ብቃትን እና ስነምግባርን መለየት የጀመርንለት ነው ነገሩ የተበላሸው፡፡እኔ ባንድ ወቅት ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ እማር በነበረበት ጊዜ አንዲት ሴት ተማሪ ሌላኛዋን ሴት ተማሪ ፍቅር ካንቺ ይዞኛል ትላታለች ተፈቀረች የተባለችው ልጅ ለሴቶች ጋይዳንስ አገልግሎት ለምትሰጠው መምህር ባማከረቻት ወቅት ወሬው ለብዙ መምህራን ተዳርሶ ዐንደኛው መምህር በአባትነት መልኩ ክፍል ወስጥ ተቆጥቶ ከዚህም በሆላ እንዲአየንት ነገር ዕንዳይለመድ ገስጾ ቢወጣም ሴት አፍቃሪዋ ተማረ ግን የህንን ነገር በመቀጠል ከሌላ ተማሪ ጋር በመወዳጀት ባንድ ወቅት እንዲያውም ከነፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ ዕኔም በአይኔ ዐይቻለው፡፡የዚች ተማር ነገር በዚህ አላበቀም ወደ ትምህርት ቤቶች ለስራ ከተሰማራን በሆላ ራሱ ይህንን ነገር እንደቀጠለች ከሌሎች መምህራን ለመርዳት ችያለሁ፡፡ይባስ ብለው ይችን ሴት ያአንድ ትምህርት ቤት ምክትል ርእሰ መምህር አርገው እያሰሮት ይገኛል፡፡አኔም በሃሪዋ ዕንካን ለርእሰ መምህርነት ይቅር ዕና ለመምህርነት እናደማትበቃ ብናገርም ከመሾማ በፍት የህንን ዐናውቅም ነበር ሲሉ የተሾመ ሁሉ ዐየወርድም የሚል ይመስላሉ፡፡ነገሩ ግን ዕንደዛ ዐይደለም የድርጅትስራ ቀጥ ብላ ስለምትሰራ ነው፡፡ለድርጅቱስ እንደዝች አይነቱ ምን ይሰራል፡፡ከዚሁሉ ብልሹ ምግባር ላይ ደግሞ የመጠጥ፡የአደንዛዠ ዕጽ ተጠቃሚነቶ ጉድ እያሰኘ የገኛል፡፡

  ReplyDelete
 21. አምላከ እስራrል ሐገራችንን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 22. ቁመው የሰቀሉት ተቀምጠው ለማውረድ ይከብዳል
  ዛሬ ዛሬ በአገራችን የምንሰማቸው ፤የምናያቸው፤የምናዳምጣቸው የዕድገት ዜናዎች ሁላችን እንደሚያስደስቱን ሁሉ በተቃራኒው ከመሰልጠን/እኔ ግን ከስልጣኔ ጋር ተያይዞ የሚመጣ መሰይጠን ብየዋለሁ/ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አጉል ልምዶች፤ትውፊትን እና ባህልን የሚጎዱ ድርጊቶች እጅጉን የሚሰቀጥጡ እየሆኑ በመምጣታቸው ለእድገት እና ለለውጥ የተነሳውን ህዝብ ወኔ እና አልሸነፍ ባይነት ወደ ኋላ እንዳይቀለብሰው ያሰጋል፡፡
  ለኢትዮጲያ ስልጣኔ፤ብልጽግና፤እድገት አድስ ነገር አይደለም፡፡በርካታ አገሮች ምንም ሳይኖራቸው ከባዶ ተነስተው ዛሬ እድገት እና ስልጣኔ ማማ ደርሰዋል ምንም እንኳን ስልጣኔያቸው ለሁከት፤ ከጭንቀት፤ ከሰቆቃ፤ ከዕሮሮ፤ ከመከራ ፤ከዋይታ ፤ከሃዘን፤ ከመከፋት ፤ከባዶነት ስሜት--- እንዲወጡ ባያስችላቸውም፡፡አገራችን ኢትዮጲያ የስልጣኔ ምንጭ ከነበሩት ግሪክ፤ግብጽ፤ባቢሎን የምትመደብ ነች፡፡አግኝቶ ማጣትን፤አጥቶም ማግኘትን የምታውቅ አገር ነች ኢትዮጲያ፡፡የነአክሱም፤የነላሊበላ---ስልጣኔ ጠፍቶ በረሃብ ህዝቦቿ የተጎዱባት፤የውጭው ሚዲያ ሳይቀር የተሳለቀባት፤የረሃብ ምሳሌ ተደርጋ የተጻፈች አገር ኢትዮጲያ በቅርብ እያስመዘገበች ባለቸው እድገት መሰረት ደግሞ አጥቶ ማገኘትን በማጣጣም ላይ ትገኛለች፡፡ይህ አጥቶ በማግኘት ላይ የሚገኝ ህብረተሰብ በድህነት፤በረሃብ፤በችግር፤--በነበረበት ዘመናትም ቢሆን አነሰም በዛም ያጣው ነገር ከጎተራው ምርትን ፤ከሳጥኑ ገንዘብን ፤ከጓሮው አዝመራን--- እንጂ ባህሉን፤ወጉን፤ትውፊቱን፤መቻቻሉን፤መተባበሩን፤መረዳዳቱን አልነበረም፡፡
  በጥንቱ ስልጣኔዋም ሆነ በችግር ዘመናቶቿ ባህሏን እና ወጓን ጠብቃ እንዳላለፈች ሁሉ ዛሬ ዛሬ ኢትዮጲያ የባህል እና ወግ ወረራ እየተደረገባት ትገኛለች ፡፡በሞቴ ምን ያህል ቢደፍሩን ነው ደግሞ ብለው ብለው አገራችን ላይ የግብረ-ሰዶም ስብሰባ ለማካሄድ የተዘጋጁት?ለነገሩ እነርሱ እኮ (የባህል ወረራ ለማድረግ የተዘጋጀ ማንኛውንም የውጭ ዜጋ ያጠቃልላል) አሁን ዝም ከተባሉ ከዚህ የባሰ ፈተና በአገራችን ሊያመጡ እንደሚችሉ በተለያዩ አገራት የፈጸሟቸውን አሉታዊ ስራዎች መዘከር በቂ ነው፡፡
  አገር አገር ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው የራሱ ባህል እና ወግ ተጠብቆለት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ያ ካልሆነ ግን አንድ አገር አገር ነው ስንል ያካለለውን የቆዳ ስፋት ብቻ ይዘን ሳይሆን በውስጡ የሚኖሩትን ህዝቦችንም አካቶ በመሆኑ የእኛ ኢትዮጲያኖች ማንነት ሊጠበቅ የሚችለው ባህላችን ሲጠበቅ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም የግብረ ሰዶም ድርጊት በአገራችን ላይ እውቅና የሚያገኝ ከሆነ፡-
  1) ከ90%/?/በላይ ህዝቧ ሃይማኖተኛ በመሆኑ እና በአገራችን ያሉ ሁሉም ሃይማኖቶች ይህን ፀያፍ ተግባር ስለማይቀበሉ በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረው የተስፋ መቁረጥ ስሜት እጂግ ከፍተኛ ነው የሚሆነው
  2) ተስፋ የቆረጠ ህብረተሰብ ደግሞ ለአንድ አገር እድገት የሚኖረው አስተዋፅኦ አሉታዊ ነው የሚሆነው፡፡ ከዚያም ባለፈ ይህንን ተግባር በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ አጸፋ ሊወስድ ይችላል፡፡
  3) በርካታ ህብረተሰብ ላይ የአስገድዶ መደፈር እና በሽታ መስፋፋት መንስኤ ይሆናል
  4) የመንግስትን ህልውና መገዳደሩ አይቀርም ---እናም ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ
  ሀ.ይህ ሊደረግ የታሰበው ስብሰባ በአስቸኳይ ቢሰረዝ
  ለ.ማንኛውም ኢትዮጲያዊ ይህን ተግባር ለማስተባበር ከሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ጋር አብሮ ባያብር፡፡ለምሳሌ ህትመት ባለማተም፤ቢሮ እና ሆቴል ባለማከራየት፤አብሮ እንዲኖሩ ባለመፍቀድ--
  ሐ.ስብሰባው በአድስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመደረግ በመታቀዱ ከታሪክም ተወቃሽነት ለማምለጥ ይቻል ዘንድ የአድስ አበባ ህዝብ ድርጊቱን በተመለከተ አስቸኳይ ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግ
  መ.በአሁኑ መንግስታችን ውስጥ ካሉ ሚኒስትሮች አንዱ እና በህዝቡ ተወዳጅ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በእርሳቸው የጤና ሚኒስተርነት ይህ ጸያፍ ድርጊት እውቅና እንዳያገኝ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ቢወጡ
  ሠ.መንግስት እንደ መንግስት ይህ ጸያፍ ድርጊት በአገራችን እውቅና የማያገኝበትን ስራ ቢሰራ፡፡ በተለይም በእርዳታ እናቋርጣለን ሰበብ ድርጊቱ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ብለው ትንበያ ለሚተነብዩ ሰዎች የፈረንጆቹ እርዳታ ሳይሆን የህዝባችን የልማት ስሜት ብቻ ነው እዚህ ደረጃ ያደረሰን ብሎ ድርጊቱ እውቅና እንደማይኖረው ለእኛ ለህብረተሰቡ ቢያረጋግጥልን

  ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ድርጊቱ እውቅና ካገኘ በእኛ ዘመን በአገራችን ላይ እኛው እራሳችን ያወጅነው የእራስን ባህል እና ወግ በራስ የማጥፋት ክስተት ሆኖ ያልፋል፡፡ስለሆነም መንግስትም ሆነ እኛ ህብረተሰቡ ይህ ድርጊት እንዳይፈጸም ቆመን ሳለን አንድ ነገር እንበል እላለሁኝ፡፡

  ውብሸት ነኝ ከባህር ዳር!

  ReplyDelete
 23. ኢትዮጵያ የሃይማኖት ሀገር ናት፡፡ ከ90 በመቶ በላይ የሆነው ሕዝቧ በእምነቱ ግብረ ሰዶምን ይቃወማል ብቻ ሳይሆን ይጸየፋል፡፡ የሀገሪቱ ሕጎችም ግብረ ሰዶማዊነትን በወንጀልነት ይፈርጃሉ፡፡ ከሕዝቡ እምነት ብቻ ሳይሆን ከባህሉ ጋርም የሚጣረስ ጉዳይ ነው፡፡
  እንዲህ ያለውን ነገር በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዲስፋፋ የሚሠሩ፣ ሕዝቡም ያልበላውን የሚያክኩ ተቋማት እና ግለሰቦች አጋጣሚዎቹን እንዳይጠቀሙ የሚመለከተን ሁሉ በርግጠኛነት መከላከል ይጠበቅብናል፡፡

  ReplyDelete
 24. ' ጢሱ እንዳይታይ ከመጣር ይልቅ እሳቱ እንዲጠፋ ብንሠራ የተሻለ ውጤት እናመጣለን፡፡' Mamush,MN

  ReplyDelete
 25. Thank u for the information, dear blogger. It is irritating. Such immoral acts have been practiced in Ethiopia since several years. Even books were published (e.g Yesedom Nefsat). All religious organizations should try to save their followers by playing exemplary roles. Individuals, please save yourself like a righteous Lot. I would prefer dying to watching Ethiopia becoming the land of Sodomites. We are poor; but we feel that we are rich because of our precious faith. Amlak lezih aynetu kifu minyotina tseyaf tegbar midritun asalifo endayset rasachinin biniset yans yhonal enji aybezam. Yegzabher hizb hoy selfu kante gar newuna berta. We have the right to live in our country preserving our religious and social values!

  ReplyDelete
 26. እኔ የምልህ ዳኒ ይህን ነገር ጽፎ ከማሳወቅ በስተቀረ አንተ በበኩልህ የምትረዳን ነገር የለም ይሆን ? በሕጋዊ መልኩ ለመቃወም የሚያሰባስበን ማነው እንዴት ነው ዝም ተብሎ በወሬ ብቻ የሚታለፈው?

  ReplyDelete
 27. ራሳችንን አጥተን የሚመጣ ርዳታ ለቀብር ማስፈጸሚያነት ብቻ የሚውል ነው፡፡

  ReplyDelete
 28. ዮናስ አርአያ ተገኝDecember 1, 2011 at 4:46 PM

  ሰላም ለከ ውድ ወንድሜ ዳንኤል፤ እጅግ ከልቤ እንደራሴ ወንድም የማይህ ሰው ነህ፤ ለቤተክርስቲያን ያለህን ፍቅር በተለያዩ ሁኔታዎች በጣም ይገርመኛል፤ ሁሉን ታግሶ ሁሉን ችሎ ለአገልግሎት መትጋት ለእኛም ለምንከተለው ብዙ ያስተምረናል፤ ከአቡነ ሺኖዳ ቀጥሎ ለአገልግሎቴ እንደ መርህ የማይህም ለዚሁ ነው።

  እግዚአብሔር የፀጋን ልብስ አብዝቶ ያልብስልን።

  እኔን ብዙ ላታውቀኝ ትችላለህ፤ ለንደን ቅሥላሴ ቤተክርስቲያን ኮርስ አስተምረኸን ነበር፤ ምንአልባት ካላስቸገርኩኝ ከልብ ለምወዳት ሰ/ት/ቤቴ ያልዃት ጦማር አለችና አይተህ አስተያየት ብትለግሰኝ እጠቀማለሁ ብዬ አስባለሁ። የሁልግዜ አስተያየትህ ባይለየኝ ለመንገዴ ጠቃሚ እንደሚሆንም አምናለሁ።

  አድራሻዋ ይህች ናት፦

  http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ReplyDelete
 29. E/giz kantegar yihun Dn. Danil.
  Yihin Atseyafi neger bewondimochachin lay yametut meatoch e/zher yegesitsachew. Wondemochachin, lijochahin tebelashu. Min yadirgu beteleyaye mikneyat keager wotitew lezih asnewari neger yidaregalu. gimashu be lijinetu, gimashu besira mikniyat. besikar bemadenzez yih dirgit yifetsemibetal. Tadiya lezih medhanitu tsebel(holly water new)lelawin kemebekel yilik. erasu yemidinbetin menged mefeleg enji revenge ayawatam. please don't do that? we Cristian eniredachiwalen. Enega meatoch leave from our country.

  Government please do something about this. Lezih enkuan gov. zim bilo ayayim. Yihin kawegeze bewnet enkorabetalen.

  e/gzher yitebiken. pray! pray! pray!

  ReplyDelete
 30. ኧረ አዘበራረቁን ኡ ኡ ኡ አንተ የቅዱሳኑን ህይወት የምትክተል ህዝብ ሆይ ማንን ትከተላለ እኔ ለቤተመቅደሱ ሰጥቻለሁ እሱ ይጠይቃቸው የምትል እራስህን አዳምጥ

  ReplyDelete
 31. ....ዳንኤል ጥሩ ብለሃል ግን ኢትዬጲያ ምን መልካም ገጽታ ነገር ኖሯት ነዉ መልካም ገጽተዋን የምታስተዋዉቀዉ?!!!!

  ReplyDelete
 32. May God bless and protect our blessed land

  ReplyDelete
 33. hi dani i just want to correct u that it is not legal to use drug,prostitution & gay marriage in las vegas

  ReplyDelete
 34. በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል እንደሆነ በግልጽ ተቀምጦ ሳለና ከ97 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንደ አጸያፊና ኢሞራላዊ አድርገው የሚቆጥሩት መሆኑ እየታወቀ፣ ይህንን ስብሰባ ለማድረግ አምሸር ማቀዱ በኢትዮጵያ ሕግና ለኢትዮጵያውያን ሞራል ቦታ ያልሰጠ መሆኑን ያሳያል፡፡


  ግብረሰዶማዊነትን ለማውገዝ የተጠራው የሃይማኖት መሪዎች መግለጫ ተሰረዘ
  www.ethiopianreporter.com

  ReplyDelete
 35. ይህ እግዚአብሔር ዓለምን በመፍጠሩ የተፀፀተበት ሐጢአት መሆኑን እውነት የማያውቅ ይኖር ይሆን;;;
  ዓለም በንፍር ውሃ የጠፋችው በዚህ ሐጢአት አይደለምን;;;
  ሰዶምና ገሞራስ የጠፋት በዚሁ ምክንያት አይደለምን;;;
  ስለዚህ ይህን የሚያደርጉትንም የሚደግፏቸውንም ሁሉንም ሌላ ማድረግ የምንችለው ባይኖርም እንኳን እናወግዛቸዋለን!!!
  እግዚአብሔር ከእንዲህ ያለው ቁጣ ይጠብቀን

  ReplyDelete
 36. I am really surprised when i read this and some other related articles on this issue. It is hard even to hear this for Ethiopia, Please let us do what we can, and the almighty God will help us. Where are we going?' Keditu wede matu ale yehagere sew'. We are reach in culture and spiritual things, which anyone doesn't find it any where in Developed countries. Let the Almighty God with his beloved mother keep our mother land Ethiopia from this devilish activity and let us pray for our brothers who are supporting this activity and are gay.

  Thanks,

  Hailemariam

  Villa park, Chicago IL

  ReplyDelete
 37. ሳይቃጠል በቅጠል ማለት አሁን ነው ማድረግ የሚገባነን ነገር ካለ የትም ሀገር አነደሚደረገዉ ማድረግ አለብን እኛ ለየት የሚያደርገግን ነገረ ቢኖር ሀይማኖታቸን ሆነ ባህለችን ጠብቀን መኖራችን ነው ሆኖም እንደዚህ የህበብረተሰቡን ስነ ልቦና የሚበርዝ እና ሰላሙን የሚያናጋ ነገር ሲመጣ በትግስት ማለፍ ወይም ለድርድር የሚበቃ ነገር ነው በማለት ችላ ልንለው አይገባም ስለዚህ ይህን ያልትለመደ ጉባኤ ፈጸመሞ በሃገራችን ሊካሄድ አይገባም በመሆኑም ተገቢውን ተቃውሞ ለማድረግና እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን ይህንንም የሃይማኖት አባቶች በበላይነት ሊያንቀሳቅሱት ይገባል. እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ከዚህ አይነቱ አስነዋሪ ነገር ይጠብቅ ዘንድ እንጸልይ.

  ReplyDelete
 38. የግብረሰዶም እንቅስቃሴ ዋና አስፋፊ ሰይጣን ነው:: ከፍጥረት ጅማሬ አንስቶ ሰይጣን የእግዚሃብሄር ህግ ተቃዋሚ ስለሆነ በመሆኑም እነዚህ ሰዎች ከዚህ እስራት ነጻ እንዲወጡ ልንጸልይ ይገባል::

  ኢትዮጵያን እግዚሃብሄር ይጠብቅ:: አሜን!!!

  ReplyDelete
 39. እውነትህ ነው መምህራችን። ሰሞኑ በጂፑተር ሆቴል ከኬንያ የመጡ የግብረ ሶዶም አራማጆች ስብሰባ ኣያካሄዱ ነው። የዚህ ሰብሰባ ውጤትም በአይካሳ ሳያቀርቡት አይቀርም። እና ሳይቃጠል በቅጠል እናድርግ።

  ReplyDelete
 40. ¨ግብረ ሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ፣ የግበረ ሰዶማውያንን መብት ካልደገፋችሁ አንረዳም እያሉ የሚያስፈራሩ ምዕራባውያን ኃያላን አሉ፡፡ ራሳችንን አጥተን የሚመጣ ርዳታ ለቀብር ማስፈጸሚያነት ብቻ የሚውል ነው፡፡ እናም እንዲቀርብን እንንገራቸው፡፡¨

  ReplyDelete
 41. Dear Daniel,

  Your notice and alarm are timely and very important. Homosexuality in both ways are not acceptable to our cultural heritage and religious belief. We should, oppose and fight not to exist in our country. We should maintain our faith, "the fear of the Lord is the beginning of wisdom." God doesn't allow his creators to engage in homosexuality or Sodom. May God Bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 42. Not only conservative, but also primitive idea. This is exactly what people said about freeing slaves and giving equal rights to women. People should be free to live their lives as they want, as long as they don't harm others. So, drop this philosophy that's based on Jewish Mythology(i.e the Bible)and join the 21st century by studying science and use the power of your mind to think for your self.

  ReplyDelete
 43. ኢትዮጵያ የሃይማኖት ሀገር ናት፡፡ ከ90 በመቶ በላይ የሆነው ሕዝቧ በእምነቱ ግብረ ሰዶምን ይቃወማል ብቻ ሳይሆን ይጸየፋል፡፡ የሀገሪቱ ሕጎችም ግብረ ሰዶማዊነትን በወንጀልነት ይፈርጃሉ፡፡ ከሕዝቡ እምነት ብቻ ሳይሆን ከባህሉ ጋርም የሚጣረስ ጉዳይ ነው፡፡

  መንግስት ስለዚህ ጉዳይ ተኝቷል????ነገሩ ባህልን: ሀገርን: ቅርስን መሸጥ ....
  ጎበዝ ህዝቡስ ምን ይላል? በጥብቅ እንቃዎም: ባህላችንን እንጠብቅ::

  ReplyDelete
 44. what is our culture ? why are people only concerned about homosexuality ? how about adultery ? nepotism ,child abuse ? corruption? fanaticism ? rape ? the high rate of divorce ? prostitution which is so normal happening in day light ? are they allowed in OUR CULTURE ..

  have you realized where our children spend their times and get their information and values from? who is the keeper of our culture ? who decides what is wrong and right ? whatever is happening in Ethiopia in respect to culture and faith is the result of a confused society that tolerates more than it should ...traditional and religious morals are being replaced with diluted morals and imported and premature local laws that does not refer to the local context ...Just because we say we are religious and we our culture does not allow this will not stop what we are disgusted about or fear ..

  .this is beyond homosexuality and we should not only blame who ever wants to impose their ideas ..we have allowed moral degradation to happen by losing our moral shields wether by evolution, globalization, economy or whatever is the cause ...this is the time to reflect and analyze the core cause of the problems ...

  denying something will not stop it from happening ..after all YEFEREUT YEDERESAL YETELUT YEWERESAL NEWENA NEGERU ..HULULM YASEBEBET ...WE ALL SHOULD TAKE THE RESPONSIBILITY

  ReplyDelete
 45. ኤልያስ ከ/ማ
  እንደዚህ ያለውን ጸያፍ ድርጊት ከመብት ጋር ተያይዞ መቅረቡ ና ተቀባይነት ማግኘት አለባቸው እየተባለ መደስኮሩ እኛ የምናዳምጠውና የምንቀበለው ንግግር አይደለም ፡፡የሃይማኖት አባቶች ለያወግዙት ሲገባ ለምን መግለጫውን እንደተውት በቅጡ ባልረዳውም ፡፡የሀገሪቱ አቃቤ ህግ ጉዳዩን ተከታትሎ አንድ እልባት ይሰጣል ብዩ እገምታለሁ፡፡

  ReplyDelete
 46. ግብረ ሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ፣ የግበረ ሰዶማውያንን መብት ካልደገፋችሁ አንረዳም እያሉ የሚያስፈራሩ ምዕራባውያን ኃያላን አሉ፡፡ when will Ethiopia independent from this diabolic westerns......may GOD help us!!

  ReplyDelete
 47. እኔ የሚገርመኝ እንዲህ ዓይነት ለወሬ የሚመቹ ነገሮች ሲኖሩ የሚጽፈው እና የሚለፈልፈው ሰው መብዛቱ !!! እስከዛሬ የት ነበር ይሄ ሁሉ ሰው ?? ቀደም ባሉት ጊዜያት የግብረሰዶማውያን እና የነሱ አፈቀላጤዎች በተለያየ መድረክ ሲናገሩ (ሲቀባጥሩ ማለት ይሻላል) ግድ የለም ይናገሩ እነሱም የመናገር መብት አላቸው ሲሉ እኮ እናስታውሳለን:: ያኔ ለምን ይሄ ድርጊት ከህገ መንግስታችን ድንጋጌዎች ጋር ይጣረሳል አልተባለም ?? "ምነው እናቴ ያኔ በ ዕንቁላሉ ጊዜ..." ሆነ እኮ ነገሩ::
  በነገራችን ላይ እነኚህ ቅድመ, ጊዜ እና ድህረ ICASA ስብሰባዎች በደምብ የታሰበባቸው ናቸው :: በቅድመ ICASA ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ አሁን ከላይ ከላይ በደፈናው እንደሚቃወማቸው, የሃይማኖት አባቶች እንደሚቃወሟቸው ያውቁ ነበር እና እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው እኮ ያውቁ ነበር:: ለዚህም ነው የመንግስት ባለስልጣን እጁን ያስገባው ጉዳዩ ላይ:: በስብሰባው ወቅት እንዴት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው እራሱ አስቀድመው ተዘጋጅተውበታል እና እኔ ሳስበው አንድ እርምጃ የቀደሙን ይመስለኛል::

  ሰለሆነም አንዴ ጮሀን ዝም የምንለው ጉዳይ መሆን የለበትም... ጦማሪውም ሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያ በዚህ ኢተፈጥሯዊ ድርጊት እንዳትጎዳ የሚፈልግ ሰው ጩሀቱን መቀጠል አለበት... አደራ በዚህ እንዳይቆም... ልክ እንደው ወጥ ረገጥክ እንዳትሉኝ እንጂ ሴቶቻችን ላይ እንደሚደርሰው የአሲድ ጥቃት የ ሚዲያ እና የጦማሪ ሽፋን እንዳይሆን.... ለአንድ ወቅት ስለጥቃቱ በሰፊው ይነገር እና ከዛ ጉዳዩ የት እንደደረሰ ማንም የሚያውቅ የለም... እንደ እግር ኳሳችን ሁሉ... እንደ አትሌቲክሳችን ሁሉ...

  እስኪሰለቻቸው መጨቅጨቅ አለብን.... ውጤት እንዲኖረን ከፈለግን...

  በጊዜ እና ድህረ ICASA ደግሞ ምን እንደሚፈጠር አብረን የምናየው ይሆናል::

  ReplyDelete
 48. ወንድሞች ፀልዩ ሃይማኖታችሁን አክብሩ ተባበሩ ከዛስ ማን መሀላችን ላይ ይገባል የፈረንጅ ብር ከአመታት እንጂ ከክፍለ ዘመናት በፊት አልተቀበልንም ይቅርብን ከብራቸው ጋር ከፈለጉ ናሳ ይሰንጠቁ አለዚያ አንታርቲክ ውስጥ ይዘቅዘቁ

  ReplyDelete
 49. It is realy shame for ethiopians. specialy for the church leader

  ReplyDelete
 50. IN THE ERA WE ARE IN
  CULTURE... FOR GET IT !
  CONSTITUTION ,LOW AND THE REST ...is some thing which can be changed over night with a clap of few hands.
  SOCIAL VALUES ... this is some thing hunged at the far end of the universe.
  WEALTH...ha ! it is some thing to the near end of a lips which require a long tongue to talk and leak.
  ERDATA,...the only thing to be focused to get it AT ANY COST ! REGARDLESS OF WHAT .
  D.Daniel ,esatuma endefejen ale .EGZIABEHAIR YETADEGEN ENJE ,engedih men keren .Ebakachu men enadereg ?
  H

  ReplyDelete
 51. so...what r we gonna do? what is z govermnent expected to do? throw this homosexual ppl to prision? put them in quarantine? what about freedom of thinking n act? what about living z way anybody like unless he/she hurts others? what if they are born z way they r? can`t they live???? i hate homosexuality. but souldn`t i respect others choice? can i conclude this ppl r wrong b/c i hate homosexuality? pleeeeeese...let us c from z others angle.

  ReplyDelete
 52. the above one ," born the way they are" what do you mean by that? is there such thing ? IF AT ALL THERE IS, do you think SETTING A MEETING IN ETHIOPIA IS A SOLUTION FOR SUCH MEDICAL PROBLEM ? i guess "hospital"is a solution .HAVE YOU HEARD ONCE A FOREIGNER CAME TO ETHIOPIA AND PRACTICED THIS DISGUSTING ACT IN HOMELESS KIDS.THIS DEVIL MIGHT PRACTICED THE ACT ON THEM BY FORCE OR by THE POWER OF MONEY, AND OF COURSE THIS IS THE WAY HE WONT TO LIVE ,BUT DO YOU THINK LETTING DO SUCH THINGS EITHER BY FORCE OR BY MANIPULATING THE KIDS MIND IS FREEDOM , DO YOU THINK THE PROBLEM THAT WE ARE SEEING AND LISTENING IN THE OUTSIDE WORLD CAME DUE TO THE SO CALLED " BORN WITH IT " CASE ?WHAT DO YOU MEAN BY "LOOKING TO THE OTHER ANGLE " ,HAVE YOU CONSIDER THE EFFECT OF "LOOKING THE OTHER ANGLE",WHAT IF THE OTHER ANGLE THAT YOU ADVISE US IS SOME THING WHICH IS IRREVERSIBLE? HOW ABOUT THE OTHER MAJORITY OF PEOPLES FREEDOM ????? ,WHAT ONE OF YOUR LOVED ONE IS THE VICTIM OF SUCH ACT .I DO NOT GET IT ...LOOKING TO THE OTHER ANGLE !!!
  H.

  ReplyDelete
 53. Are deacon ande neger adreg? be ethiopia west gebresedomawi sebseba yekahed? yemigerem gize lay dersenal egna eko etiopia weyan ene endet.deacon yehen ye gebresedomawi neger lek denberachen yetewerer yahel new yetesemagn.lehulachenem amlak lebuna yesten.

  ReplyDelete
 54. Hi H (above the above one). i read your answer for my comment. u asked me if there is `born with homosexuality`. yes there is. check any possible medical information. 90% of them r born with it. that`s whay i said so.

  i told u that i hate it & i don want anybody be a victim of it. if it`s done by force as u said, it`s a crime. the doers must be penalized under law. but what if two men in the same behavior agree to do so & act? can we stop them? can z government either?

  ReplyDelete