Tuesday, November 15, 2011

ዝርዝሩ


እስኪ በከፍቾዎች ተረት በኩል አንድ ነገር እንይ፡፡
አንድ ሞኝ አሽከር የነበረው ሰው ነበር አሉ፡፡ ይኼ አሽከር አድርግ የተባለውን ካልሆነ በቀር አስቦ፣ አውጥቶ እና አውርዶ፣ ብሎም አመዛዝኖ የሚሠራው ሥራ አልነበረም፡፡ ምን ጊዜም የሚጠብቀው የጌታውን ትእዛዝ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ትክክል ነገር ማለት ጌታው ያዘዘው ሲሆን፣ ስሕተት ማለት ደግሞ እርሱ ያልነገረው ነገር ማለት ነው፡፡ ዓላማው ጥሩ ነገር መሥራት ወይንም አዲስ ነገር መሥራት ሳይሆን ጌታውን ማስደሰት ብቻ ነበር፡፡
ጌታው ከሳቀ ይስቃል፣ ካለቀሰ ያለቅሳል፣ ከተደሰተ ይደሰታል፣ ካዘነም ያዝናል፡፡ የወደደውን ይወድዳል የጠላው ይጠላል፡፡ ለርሱ የመደሰቱንም ሆነ የማዘኑን፣ የመሳቁንም ሆነ የማልቀሱን ምክንያት ማወቅ አይጠበቅበትም፡፡ ዋናው ነገር ጌታው መሳቁ ወይንም ማልቀሱ ነው፡፡ አንዳንዴ ሰዎች የሳቀበትን ምክንያት ሲጠይቁት «ጌታው ሳቁኮ አላያችሁም» ይላል፡፡ በዚህም የተነሣ ሰዎች «እንዳሉት»ብለው ይጠሩት ነበር፡፡
አንድ ቀን ጌታው እና እንዳሉት ወደ መንገድ ወጡ፡፡ እርሱ በእግሩ ከኋላ እየተከተለ፤ ጌታው ደግሞ በፈረስ ከፊት እየበረሩ፡፡ መንገድ ላይ ጌታው የገንዘብ ቦርሳቸውን ጣሉት፡፡ እንዳለውም ቦርሳውን አልፎት ሄደ፡፡ጌታው ያሰቡበት ከተማ ገብተው ኪሳቸውን እስኪቀደድ ቢበረብሩ ቦርሳቸውን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም ወደ እንዳሉት ተጠጉና «የገንዘብ ቦርሳ አላየህም» አሉት፡፡ እንዳሉት «አይቻለሁ፣ መንገድ ላይ ጥለውታል» አላቸው፡፡
ጌታው ደንግጠው እና ተናድደው «ታድያ ለምን አንሥተህ አልሰጠኸኝም» አሉት፡፡ እንዳሉት ደንግጦ አሰበ፣ አሰበ፣ አሰበ፡፡ ግን የተሰጠው መመርያ አልነበረም፡፡ ተከተለኝ ከማለት በቀር የነገሩት ነገር አልነበረም፡፡ «እንዴ እርስዎ የገንዘብ ቦርሳዬ ሲወድቅ አንሥተህ እንድትሰጠኝ መች አሉኝ» አላቸው፡፡ እርሳቸውም «በል ከዛሬ ጀምሮ እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካየህ ሰብስበህ እንድትሰጠኝ» አሉት፡፡ ከእሺ በቀር ሌላ የማያውቀው እንዳሉት በጸጋ ተቀበለ፡፡
በቀጣዩ ጊዜ ጌታውን ተከትሎ መንገድ ጀመረ፡፡ መመርያው በልቡ ነበር፡፡ የሚያሳ በው የተነገረው ነገር ነው፡፡ በልቡ ውስጥም ከተነገረው ነገር በቀር ምንም ሌላ ነገር አልነበረም፡፡ የርሱ ልብ አዲስ ነገር አያመነጭም፤ አዲስ ነገር ማመንጨት የሚችሉት የርሱ ጌታ ብቻ ናቸው፡፡ የርሱ ሥራ ያለ ጥርጥር ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት ማለት ብቻ ነው፡፡ ለምን? ማለት አያውቅም፡፡ ለምን? ማለት ከጀመረማ አሽከር አይሆንማ፡፡ አሽከር ደግሞ ይጠይቃል? ይጠየቃል እንጂ? አሽከር ደግሞ ያስባል? ይታሰብለታል እንጂ? አሽከር ደግሞ ይመረምራል? ይመረመራል እንጂ? አሽከር ደግሞ ይገመግማል? ይገመገማል እንጂ? አሽከር ደግሞ ያፈልቃል? ይፈልቅለታል እንጂ? ምን ሲባል፡፡
እናም ተከትሎ ሄደ፡፡ የታዘዘው ትእዛዝ ብቻ ነበር ትዝ የሚለው፡፡ «እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካገኘህ ሰብስበህ እንድትሰጠኝ» የሚለው፡፡ ይህ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ አንዳች ነገር እንዲወድቅ ተመኘ፡፡ ያለበለዚያማ ትእዛዝ ፈጻሚ ላይሆን ነው፡፡ የሚወድቅ ነገር ከሌለማ እርሱ የወደቀን ሰብሳቢ መሆኑ እንዴት ይታወቃል? ስለዚህ ለመሰብሰብ ሲባል ብቻ መጣል አለበት፡፡
ጥቂት እንደተጓዙ አንዳች ነገር መውደቅ ጀመረ፡፡ እርሱም እያነሣ በቀረጢት ከተተ፡፡ ሲወድቅ ሲያነሣ፣ ሲወድቅ ሲያነሣ፣ ሲወድቅ ሲያነሣ በመጨረሻ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡ ጌታውም «እህሳ፣ ዛሬስ የወደቀ ነገር የለም?» አሉት፡፡ «አለ እንጂ» አላቸው፡፡ ደንግጠው ኪሳቸውን ዳበሱት፡፡ ቦርሳቸው ከነ ገንዘቡ እንዳለ ነው፡፡
«ምንድን ነው የወደቀው?» አሉት ጌታው፡፡ እንዳሉት ግን ቀረጢቱን ይዞ መጣ፡፡ ሲከፍተው የፈረሱ ፋንድያ ነበር፡፡ ተናደዱ ጌታው፡፡ ለምን ግን ይናደዳሉ፡፡ እርሳቸው እንዲህ ያለ አሽከር አይደል እንዴ የሚፈልጉት፡፡ ግንኮ ጌታ ካልተናደደ ምኑን ጌታ ሆነው፡፡ በጌታ እና በአኽከር መካከል ትልቁ ልዩነት የሚናደዱበት ማግኘት ነው፡፡ ጌቶች የሚናደዱባቸው አሽከሮች አሏቸው፡፡ አሽከሮች ግን በራሳቸው እንኳን መናደድ አይችሉም፡፡
«ይህንን ምን ሊጠቅምህ ሰበሰብከው?» አሉት ጌታው፡፡
«እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካገኘህ ሰብስብ ብለውኛላ» አላቸው፡፡ እውነቱን ነው፡፡ አሽከር አንድ ነገር ይጠቅማል፣ አይጠቅምም፤ ያስፈልጋል፣ አያስፈልግም ብሎ እንዲወስን ማን ፈቀደለት? አሽከር ማለት የታዘዘውን ብቻ የሚፈጽም ማለት ነው፡፡ አሽከር ከአንገት በታች እንጂ ከአንገት በላይ አለው እንዴ? ከአንገቱ በላይ ያለው ከጌታው ዘንድ ነውኮ፡፡
«በል» አሉት ጌታው፡፡ «ከዛሬ ጀምሮ የምታነሣው ቦርሳዬ፣ ካባዬ፣ ባርኔጣዬ፣ ጅራፌ፣ ገንዘቤ፣ እንዲሁም ከፈረስ ዕቃዬ አንዱ ነገር ከወደቀ ብቻ ነው»፡፡ እንዳሉት በፈገግታ ተቀበለ፡፡ ግን ፈራ፡፡ ይህንን ዝርዝር ቢረሳውስ፡፡ ቁጭ ብሎ በአንድ ወረቀት ላይ ጻፈው፡፡ መጻፍ ብቻ አይደለም እንደ ውዳሴ ማርያም ደጋገመው፡፡ በሄደበት፣ በተቀመጠበትም ይህንኑ ዝርዝር ብቻ ነበር የሚናገረው፡፡ ሰው ለሚጠይቀው ማናቸውም ነገር መልሱ ይሄ ዝርዝር ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ዝርዘሩን የሰጡት ጌታው ናቸዋ፡፡
ከሰዎች ጋር ሲያወራ በየንግግሩ ጣልቃ ዝርዝሩን ማንሣት አለበት፡፡ አብረውት የሚያወሩት ሰዎች ግራ ይገባቸዋል፡፡ ለርሱ ግራ ቢገባቸው፣ ቀኝ ቢገባቸው ግዱ ነው፤ ዋናው የጌታውን ትእዛዝ አለመርሳቱ፣ እርሱንም የንግግሩ ማሟሻ ማድረጉ ነው፡፡ እርሱ ዋጋውን ከጌታው እንጂ ከሕዝቡ አያገኝ፡፡ ሌሎች ሰዎች ቢወዱት እንጂ አይሾሙት፤ ቢያደንቁት እንጂ አያበሉት፡፡ እንጀራውም ሹመቱም ያለው በጌታው ዘንድ ነው፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ መንገድ ተጓዙ፡፡ እንዳሉት እና ጌታው፡፡ በሄደበት መንገድ ሁሉ የሚጓዝበትን አካባቢ፣ ዛፎቹን እና እንስሳቱን፣ መንደሩን እና መስኩን አያይም፡፡ እየደጋገመ የሚያየው ዝርዝሩን ነው፡፡ አንዴ ዝርዝሩን፣ አንዴም መንገዱን ያያል፡፡ ከዝርዝሩ መካከል መሬት የወደቀ እንዳለ ብሎ፡፡
እርሱም ዝርዝሩን እንዳየ ጌታውም እንደሸመጠጡ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
«እህሳ ዛሬስ የወደቀ ነገር አለ?» አሉት፡፡
«የለም፤ ከዝርዝሩ ውስጥ የወደቀ ነገር የለም» አላቸው፡፡ ለእርሱ ዋናው የሚጠቅም ነገር ወድቋል? የሚለው አይደለም፤ ከዝርዝሩ መካከል፤ ከታዘዘው መካከል ወድቋል ወይ? የሚለው ነው፡፡ ከዝርዝሩ ውጭ ምን ነገር አለ? ማንኛውም ነገር ያለው በዝርዝሩ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ከዝርዝሩ ውጭ ያለ ነገር አንድም እንዳለ አይቆጠርም፤ ያለበለዚያም የማይጠቅም ነገር ነው፡፡ ዋናው ዝርዝሩ ነው፡፡ ለርሱ ዝርዝሩ ቁጥሩ ከወንጌል፣ አንዳንዴም ከወንጌል በላይ ነው፡፡
ደስ አለው፡፡ ከዝርዝሩ መካከል የነጠበ ነገር የለምና፡፡
«ዝርዝሩን ይጠብቅልን» ብሎ ጸልዮ ተኛ፡፡ ያለ ዝርዝሩ እንዴት መኖር ይቻላል፡፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዳሉት እና ጌታው ለአራተኛው ጉዟቸው ተነሡ፡፡ እርሳቸውም ፈረሳቸውን እርሱም ዝርዝሩን አዘጋጁ፡፡
ሄዱ፡፡ ሸመጠጡ፡፡ እርሳቸው ፊት ፊታቸውን፣ እርሱም ዝርዝሩን እያዩ፡፡ ዋናው ዝርዝሩ ነው፡፡
ሲሄዱ፣ ሲሄዱ፣ ሲሄዱ
መንገድ ላይ ፈረሱ አደናቀፈውና ጌታውን ይዟቸው ወደቀ፡፡ ፈረሱም የሲቃ ድምጽ አሰማ፡፡ ጌታውም ጮኹ፡፡
«አንሣኝ አንሣኝ» እያሉ ጮኹ ጌታው፡፡
እንዳሉት ዝቅ ብሎ በእጁ ያለውን ዝርዝር አየ፡፡ ጌታው ሲወድቁ እንዲያነሣ የሚያዝ በዝርዝሩ ውስጥ የለም፡፡
«አላነሣዎትም» አላቸው፡፡
«ለምን ለምን፤ ኧረ ተላላጥኩልህ አንሣኝ» አሉት በልመናም በትእዛዝም፡፡
«የለም ጌታው በዝርዝሩ ውስጥ እርስዎ የሉም»
በመካከል ፈረሱ ተነሣ፡፡ አሽካካ፡፡ ጌታው ግን ሰውነታቸው ተላልጦ እየደማ እዚያው ያቃስቱ ጀመር፡፡
ፈረሱ መንገዱን ይዞ ሸመጠጠ፡፡ ጌታው እጃቸውን እያርገበገቡ «እባክህ ስለ ፈጠረህ አምላክ አንሣኝ» እያሉ እንዳሉት ለመኑት፡፡ እርሳቸው ያንን ዝርዘር ሲሰጡት ቃላቸውን ለማስጠበቅ እና ከቃላቸው እንዳ ይወጣ እንጂ እርሳቸው ሊወድቁ እንደሚችሉ መች ገመቱ፡፡ ደግሞስ ጌታ እወድቃለሁ ብሎ እንዴት ይገምታል፡፡ ጌታ አይደሉ፡፡
አሁንም እጃቸውን እያርገበገቡ ለመኑት «አንሣኝ አንሣኝ እባክህ» እንዳሉት ግን ፈረሱን ተከትሎ አሁንም ዝርዝሩን እያየ ትቷቸው ሮጠ፡፡
ብቻውን «እንዴ እዚህ ዝርዝር ውስጥ የሌሉትን እንዴት ብዬ ላንሣቸው፡፡ በኋላ ደግሞ ከዝርዝሩ ውጭ አነሣህ ብለው ራሳቸው ቢቆጡኝስ፡፡ እኔ ካዘዙኝ ውጭ ሠርቼ ዐውቃለሁ? አሁን ማንን ክፉ ለማድረግ ነው» እያለ ያጉረመርም ነበር፡፡

39 comments:

 1. Cool...... Such kind of bureaucratic attitude and unnecessary wavering loyalty to their boss and to the corrupted system have one of the causes of poverty in Ethiopia.This culture is so deep rooted in our country. Starting from th feudal system of our history up to the so called ¨democratic system¨, such kind of culture is so prevalent. we should avoid and fight such kind of culture from our society through process. We should give lessons for those who are acting like ENDALUTE via different methods. However,the methods by itself should not be in a violent form.
  PJ from DebreMarkos University

  ReplyDelete
 2. ዳኒ ተባረክ! አንተ በርክትልን
  Mamush,MN

  ለምን? ማለት አያውቅም፡፡ ለምን? ማለት ከጀመረማ አሽከር አይሆንማ፡፡ አሽከር ደግሞ ይጠይቃል? ይጠየቃል እንጂ? አሽከር ደግሞ ያስባል? ይታሰብለታል እንጂ? አሽከር ደግሞ ይመረምራል? ይመረመራል እንጂ? አሽከር ደግሞ ይገመግማል? ይገመገማል እንጂ? አሽከር ደግሞ ያፈልቃል? ይፈልቅለታል እንጂ? ምን ሲባል

  ReplyDelete
 3. ዳኒ እንዲህማ አትቀልድብንም!!
  ምንም እንኳን እንዳሉን ብንሆንም ቅኔ በመፍታትና ሰምና ወርቅ በመለየት አንታማም፡፡

  ReplyDelete
 4. ...........እንዳሉት ግን ቀረጢቱን ይዞ መጣ፡፡ ሲከፍተው የፈረሱ ፋንድያ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 5. የጨካኝ መሪዎች/አለቃዎች ፍጻሜ

  ReplyDelete
 6. ውደ ዳንኤል
  ያሃገራቼን መረውቼ ከዜህ አየታ አጅገ በጣመ የቀረቡ ናቸው ::
  በወነቱ የምገርም አይታ ነው::ከላዬ አስካ ታቸ ያሉኤ አመራሮቼ አንዴ ካለ አንዴ ቁአንቁአ ነው የሚናገሩ የምዛመሩ ያ ቃለ ያማየለወጥ ይማየቃየር "ለነርሱ ዝርዝሩ ቁጥሩ ከወንጌል፣ አንዳንዴም ከወንጌል በላይ ነው፡፡"
  "የሀገሬ ሚኒስቴሮች...ቢያንስ ቀበሌ አስተዳድረው የሚያውቁ እንዲሆኑ"ብላል::
  እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ የሚያስብ መረ እንድሰጠን በአንድነት በፀሎት አንለምን::
  አሜን!!

  ReplyDelete
 7. Why don't call a spade a spade, is it difficult?

  ReplyDelete
 8. ወይ ዳኒ ዛሬ ደግሞ ምን የሚገርም ነገር አመጣህብን፡፡
  ዛሬ በሀገራችን በተለያዩ መንገዶች ይህ ነገር እየተለመደ የመጣ ነገር እየሆነ ነው፡፡በብዙ ቦታዎች በተለይም ትንሽ ሰልጠንና የተሻሉ ናቸው የሚባሉ ሰዎችና አካላት የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ምንም ሳይጠይቁና ሳይመረምሩ እንደወረደ መቀበል የተለመደ ነገር እየሆነ ነው፡፡ዛሬ ዛሬ ምግብ ቤትም ወይንም የሆነ አገልግሎት ቦታ ሄደህ የሚሰጥህንና የሚቀርብልህን ነገር ሁሉ ያለምንም ቅሬታና ማቅማማት መቀበል አለብህ፡፡ይህ ለምን ይሆናል ብሎ የተለየ ሃሳብና ቅሬታ የሚያቀርብ ማንኛውም የተለየ ሰው በቁጣ ወይንም በንቀት መሳይ ነገር “ይህ ደግሞ የማነው” ተብለህ ትገለላለህ ወይንም ትገረመማለህ፡፡ከነባራዊው ሲስተም ጋር ትንሽ ለየት ያለ ጥልቀትና ፋት ያለው አዲስና ወጥ አስተሳሰብ የቱንም ያህል ለሀገርና ለትውልድ ጠቃሚ ቢሆን ከተለመደው የዘመናችን የዝርፊያ ቢዝነስ ስታይል አስተሳሰብና አካሄድ ጋር የማይመች ከሆነ ወዲያውኑ ይወገዛል ይጣጣላል ወይንም ኋላ ቀር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡በተመሳሳይ መልክ አንድ አይነትና ወጥ የሆነ ተራና የተለመደ አስተሳብ ለስርዓቱ እንደሚመች አድርጎ መቅረፅና ማምረት የስርዓቱና የህብረተሰባችን ዋና መገለጫ ባህሪ እየሆነ መጥቷል፡፡መሃይምም ቢሆን ታማኝ ሎሌና አገልጋይ በመሆን የኢህአዲግን ፖለቲካና ስርዓት እስካራመደ ድረስ ሹመትና ስልጣን እንሰጣለን የሚል የአገዛዝ ስርዓት ባለበት ሀገር ውስጥ ምን የተለየ መልካም ነገር መጠበቅ ይቻላል፡፡እንግዲህ ትውልድና ሀገር እየተገነባም ሆነ እየጠፋ ያለው በዚህ አይነት የተጣመመ አስተሳሰብ ላይ በተመሰረተ አገዛዝ አማካኝነት ነው፡፡ትንሽ ጭል-ጭል ሲል የነበረው ዲሞክራሲ መሳይ ነገርም ጭራሹን ደብዛው ጠፍቶ ዛሬ አሁን ባለው የሀገሪቱ ፓርላማም ውስጥ ያለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ከዚህ ከአንተ ተረት ጋር በደንብ የሚስማማ ነው፡፡
  የተወሰኑ ሰዎችን በጥይት መግደል አንድ የተወሰነ ወንጀል ነው፡፡ነገር ግን ትውልድን እንዳለ በተጣመመ አስተሳሰብና ፍልስፍና ማላሸቅ ማኮላሸትና መግደል ግን ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ትልቅ ከፍተኛ ወንጀል ነው፡፡ለምንና እንዴት ብሎ መጠየቅ በዘመናችን የማይፈለግ ችግር ፈጣሪና ለስሜት የማይመች ጥያቄ እየሆነ ነው፡፡ብዙሀኑ ሰዎች ሲያብዱ አብሮ ማበድ፣ ሲፈርሹ መፈረሽ፣ሲቃወሙ አብሮ መቃወም፣ሲደግፉ አብሮ መደገፍ ፣ሲያዋጡ አብሮ ማዋጣት፣ሲ …..አብሮ መ………. ወዘተ የዘመኑ ስታይል ነው፡፡እረ ለመሆኑ ምን አይነት አስተሳሰብና ንቃተ-ህሊና ያለው ማህበረሰብና ትውልድ ነው እየፈጠርን ያለነው?

  ReplyDelete
 9. the famous View!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 10. «እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካገኘህ ሰብስብ ብለውኛላ» አላቸው፡፡ እውነቱን ነው፡፡ አሽከር አንድ ነገር ይጠቅማል፣ አይጠቅምም፤ ያስፈልጋል፣ አያስፈልግም ብሎ እንዲወስን ማን ፈቀደለት? አሽከር ማለት የታዘዘውን ብቻ የሚፈጽም ማለት ነው፡፡ አሽከር ከአንገት በታች እንጂ ከአንገት በላይ አለው እንዴ? ከአንገቱ በላይ ያለው ከጌታው ዘንድ ነውኮ፡፡

  ReplyDelete
 11. Thanks Dani,this is true in our mother church (EOtc) that got us in the middest of messes where we are now. You gonna see that all ashkers of Aba Pawlos "H.H." will live him when he fails.

  Esqemaezenu...

  ReplyDelete
 12. patirareku nachew einae min atefahu... yemelutis? Dni

  ReplyDelete
 13. እንደ እስፖንጅ የፈሰሰላቸውን ብቻ ለሚመጡት ሁሉ አሪፍ የመንቂያ ደውል ነው፡፡እንዲሁም ለአፍሳሾቹ፡፡

  ReplyDelete
 14. ‹እኔን ለምን ትወቅሱኛላችሁ፤ ... ሄደህ አገልግል ብለው ፓትርያርኩ ስላዘዙኝ ነው፤›› kalewu gar temesaselebign. Thanks!

  ReplyDelete
 15. በአግባቡና በአካሄዱ ሳይሆን ሲቀር እንጂ በእርግጥ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል ታማኝና መልካም የሆነ ታዛዥ መፍጠርና ማግኘት መጥፎ ነገር አልነበረም፡፡ሁሉም ገዢና ጌታ ሊሆን አይችልም አይገባምም ፡፡እንደዚሁም ሁሉም ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል ታማኝና መልካም የሆነ ታዛዥ ሊሆን አይችልም አይገባምም፡፡ሁሉም እንደ ችሎታውና እንደ ተሰጥኦው በተሰማራበት መስክና የህይወት ዘርፍ ለአጠቃላዩ ህይወትና የሰው ዘር አጠቃላይ እንቅስቃሴና መስተጋብር መልካም ተግባርን ማበርከት ተገቢ ነገር ነው፡፡ብቻ ትልቁ ችግር መልካም አዛዥ ጌታም ሆነ መልካም ታዛዥ አገልጋይ እየጠፋ የመጣበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ለምሳሌ ገዢዎችንና ባለስልጣናትን ስለማክበርና በስርዓት ስለመገዛት በቅዱስ መፅሀፍ ሮሜ ምዕራፍ 13፡1 ጀምሮ የሚከተለው ተፅፍ እናገኛለን፡፡
  ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤ ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው። ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና። ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።
  ትልቁ ችግር ገዢዎቻችን የሚያስተዳድሩትን ህዝባቸውን በፍቅርና በቀናኢነት በመልካም አስተዳደር ማስተዳደር አልቻሉም፡፡እኛም ብዙሃኖች ሌሎች ተራው ዜጋና ህዝቦች እንደ ተገዢ ለሚያስተዳድሩን ገዢዎቻችን በአክብሮት ልንታዘዝና ልንገዛ አልቻልንም፡፡ለምሳሌ የሰውነት ብልቶቻችንን ብንመለከት ሁሉም አንድ አይነት ስራ አይደለም ያላቸው፡፡አይን ከማየት ውጪ የጆሮን ስራ ተክቶ ሊሰራ አይችልም፡፡እንደዚሁም ጆሮ ከመስማት ውጪ የአይንን ስራ ተክቶ ሊሰራ አይችልም፡፡አይንና ጆሮም የአእምሮን ስራ ተክተው ሊሰሩ አይችሉም፡፡ አእምሮም እንደዚሁ የአይንንና የጆሮን ስራ ሊተካ አይችልም፡፡አይንና ጆሮ ለአእምሮ ባይታዘዙ ምን ይጠቅማሉ፡፡አእምሮስ ሌሎች አካላት ከሌሉት በራሱ ምን ጥቅም አለው፡፡ነገር ግን ሁሉ ስነ ፍጥረት በፍቅር በመግባባትና በመከባበር ድርና ማግ ሆኖ በመተባበር ተቀናጅቶና ተስማምቶ አንድ ትርጉም ያለው ስራ ሊሰራ ህይወትና ተፈጥሮ ግድ ይሉ ነበር፡፡አውራ ያለ ተራ ንብ ትርጉም የለውም እንደዚሁም ንብ ያለ አውራ ትረጉም የለውም፡፡በጥልቀትና በስፋት ማስተዋል የሚችል አእምሮ ካለን መላው የፈጣሪ ስራ የሆነው ተፈጥሮ ሁሉ በራሱ ትልቅ አስተማሪ ትምህርት ቤት ነው፡፡ገዢዎቻችን እራስ ወዳድ እብሪተኞችና ፍቅርን የማያውቁ ጨካኞች በመሆን እኔ ብቻ አዋቂ እኔ ብቻ አራጊ ፈጣሪ ስለሆንኩኝ ስለዚህም የማዛችሁን ብቻ አድርጉ እንዲሁም አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ አይነት የአምባገነንነትና የብልጣብልጥነት በሌላ በኩል ደግሞ ሲታይም የሞኝና የግትር አካሄድ የሚከተሉ ከሆነ ተራው ህዝባቸው በአክብሮትና በፍቅር ሊገዛላቸው ከቶ አይችልም፡፡ሁሉ ተፈቅዷል ሁሉ ግን ለበጎ አይሆንም እንዳለው ቅዱስ መፅሀፍ እንደዚሁ ህዝብም ዲምክራሲ የሚባሉ አይነት ከውጪ የመጡ ባእድና ዘመን አመጣሽ ነገሮችን በቅጡ ሰፋና ጠለቅ አድርጎ ሳይመረምርና ሳያገናዝብ እንደወረደ ተቀብሎ በጭፍን በመመራት ተግባራዊ አደርጋለሁ ቢልና እንዲያው ከስርዓት አልበኝነትና መደዴነት በመነጨ እንደዚሁ መሪዎቹን የማያከብር ሃኬተኛና ተመፃዳቂ ከሆነ መልካም መሪዎችን ለማግኘት ይከብደዋል እንደዚሁም ስልጣን ላይ ያሉትንም በተቃራኒው ለወገናቸው የማያስቡ ጨካኝና አረመኔ እንዲሆኑ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡በማንኛውም ደረጃ አቅጣጫና መስመር ላይ ገዢዎች የሆናችሁም ሁሉ በስራችሁ የምታስተዳድሯቸው ሰዎች በክርስቶስ አርዓያ የተፈጠሩ ትርጉምና ክብር ያላቸው ፍጥረቶች መሆናቸውን መረዳት ይኖርባችኋል፡፡ሰዎች ውጪያዊ በሆነው ጊዚያዊና አላፊ ጠፊ ነገር ሁሉ የተወሰነ ልዩነት ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ሰው በመሆናችን ባለው ወሳኝ ነገር ስንመጣ ግን ሁላችንም በክርስቶስ አርዓያ የተፈጠረች ክብርትና ብርህት የሆነች ትልቅ ዋጋ ያላት ውድ ነፍስ ያለችን ነን፡፡ይህንን ማመንና መቀበል መልካም ይመስለኛል፡፡ስለዚህም ሃይልና ስልጣኑ አለን ብለን በመታበይ የእንጀራ ጉዳይ ሆኖባቸው በአክብሮትና በመታዘዝ የሚያገለግሉንን ሰዎች ከተገቢውና ጤናማ ከሆነው መስመር አልፈንና ፍፁም ሰብዓዊነታቸውን ረስተንና ክደን ከልክ በላይ በራሳቸው ላይ በመሰልጠን ፍትህ እያጓደልን ልናስመርራቸውና ልናገጣብራቸው አይገባንም፡፡እንደ ገዢ እንዲወዱንና እንዲያከብሩን የምንፈልግ ከሆነ እኛም በተራችን እንደ ተገዢ ልንወዳቸውና ልናከብራቸው ግድ ይለናል፡፡እግዚአብሄር ፍቅር ነው ፍቅርም ደግሞ የህግ ሁሉ መፈፀሚያ ነው እንደተባለው ሁሉ በፍቅር ስለፍቅር በማስተዋል ቢሆን ሁሉ ነገር መልካም ይሆናል፡፡ከሺ ሰላምታ አንድ ሜታ እንደተባለው ማስታወቂያ ገዢዎቻችን እራሳቸውን ወደ ውስጥ መርምረው ብዙ አይነት የህግ ጋጋታዎችን በየቀኑ ከሚተበትቡብን በዋናነት በፍቅር ህግ ጭምር ቢመሩን ሁሉ ነገር እንዴት መልካም በሆነ ነበር፡፡ይህ ሲሆን ደግሞ የዳንኤልንም እጅግ አስተማሪ የሆነ ተረት በአሳዛኝ ጎኑ ያለውንም ብቻ ሳይሆን በጥሩ ጎኑ ያለውን የመልካም ታዛዥነትን አስፈላጊነት ወደ መልካም ለመቀየር ይቻል ነበር፡፡

  ReplyDelete
 16. Dear Daniel,

  Thank you for the article.

  I have read that Abe Tokichaw has become the latest victim destined for exile. It is not because of bomb plotting or being terror mastermind; it is because he is a social critic (writer).

  He has vigorously awakening the blunt mind of the citizens deformed by ETV's anesthetic injection called Drama and Zefen.

  Journalists and writers are becoming endangered species of Ethiopia as the likes of Kebero (Red Fox).

  Presumably, the draw for the next "Prize" I guess is for you unless you are being involved in what is called in Abe Tokichaw's word "DOUBLE AGENT''

  The Proverb is likely foretold for EPRDF may be hundreds or thousands of years before and you quoted it fashionably and without ambiguity.

  That is gorgeous, And Finally what you are trying to hint is exactly the same as what Abe Tockichaw already said.

  “ኢህአዴግ ጌታ ነው”

  Many Thanks to you

  May God Bless Ethiopia

  Amen

  ReplyDelete
 17. u know dani u kinda use hypothetical stories to prove ur point.4 ex.there is no man or a slave that stupid or that can be made that stupid.try to use more realistic stories.

  ReplyDelete
 18. እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን!!
  ፀጋውን ያብዛልህ ዲ. ዳንኤል
  Ameha Giyorgis ከZambia

  ReplyDelete
 19. Wow! Great. It's our deep rooted problem of both z boss and servant!

  ReplyDelete
 20. aye dani min ayenet COMPUTER yeheon ashekere ametaheben . qale hiwot yasemalen betam yegeremale .

  ReplyDelete
 21. "...እርሳቸው ያንን ዝርዘር ሲሰጡት ቃላቸውን ለማስጠበቅ እና ከቃላቸው እንዳ ይወጣ እንጂ እርሳቸው ሊወድቁ እንደሚችሉ መች ገመቱ፡፡ ደግሞስ ጌታ እወድቃለሁ ብሎ እንዴት ይገምታል፡፡ ጌታ አይደሉ፡፡አሁንም እጃቸውን እያርገበገቡ ለመኑት «አንሣኝ አንሣኝ እባክህ» እንዳሉት ግን ፈረሱን ተከትሎ አሁንም ዝርዝሩን እያየ ትቷቸው ሮጠ፡፡"
  እሱባለው፣ ደማዩ

  ReplyDelete
 22. Dear Daniel,

  Quiet interesting article. Stay Blessed

  ReplyDelete
 23. ዳንኤል ንስር ዘከዌኖቱ ምጡቅ
  በአክናፈ አእምሮ ሖረ ፍኖተጥበብ ርኁቅ

  ReplyDelete
 24. HI Dani,U have got my heart.'ZIRZRU' becomes the manifesto of Our religious leaders.

  The same is true about our political leaders.They are talking the talk rather than working the work.They serve us like pipelines.From the same pipelines we can both water and natural oil.From our leaders we are getting intangible words.They have a gut to promise to do one thing at morning but they could deceive you afternoon.

  ReplyDelete
 25. «እንደምሄድ እንጂ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም፡፡ ተሳቢ መሳቡን እንጂ መንገዱን አያውቅም፡፡»

  ReplyDelete
 26. dani k lib sew nehi. ye abune pawilosina ye aba fanuealin tarik bemisale ametahew.

  ReplyDelete
 27. አቤ ቶኪቻዉ የረሳዉ ነገር “ዳኒዔል ጌታ ኔዉ”! የሚለዉን ነዉ። ምነዉ ቢባል ዳኒኤልን መዉቀስ “ስለሚያስኮንን” ነዉ። እሱን የሚመለከት አስተያየት ስንጽፍ አንድም ጊዜ ወጥቶ አያዉቅምና። ማንነቱን ካወቅን ቆይቷል፣ አሁንም ይህንን አታወጡትም። አይ አይነኬዉ ዳኒ!

  ReplyDelete
 28. «እባክህ ስለ ፈጠረህ አምላክ አንሣኝ»
  ግን ፈረሱን ተከትሎ አሁንም ዝርዝሩን እያየ ትቷቸው ሮጠ፡፡
  God bless you.
  Aragaw kibret

  ReplyDelete
 29. Dear Dani!
  Thank you Dani for the history. by the way is that real history for Our country.

  ReplyDelete
 30. Hey Dani!
  Thank you for history. By the way is that real history for our country.

  ReplyDelete
 31. «ምንድን ነው የወደቀው?» አሉት ጌታው፡፡ እንዳሉት ግን ቀረጢቱን ይዞ መጣ፡፡ ሲከፍተው ‹‹‹የፈረሱ ፋንድያ››› ነበር፡፡ ተናደዱ ጌታው፡፡ ለምን ግን ይናደዳሉ፡፡ እርሳቸው እንዲህ ያለ አሽከር አይደል እንዴ የሚፈልጉት፡፡ ግንኮ ጌታ ካልተናደደ ምኑን ጌታ ሆነው፡፡ በጌታ እና በአኽከር መካከል ትልቁ ልዩነት የሚናደዱበት ማግኘት ነው፡፡ ጌቶች የሚናደዱባቸው አሽከሮች አሏቸው፡፡ አሽከሮች ግን በራሳቸው እንኳን መናደድ አይችሉም፡፡...

  ይሄው ነው እየሆነ ያለው፡፡ ወታደር ተኩስ ሲባል መተኮስ አቁም ሲባል ማቆም ግዴታው ነው፡፡ አበለዚያ አንድ ጦር በጠላት ሳይሆን በራሱ መፈረካከሱ ነው፡፡ ነገርግን ይሄ የሚሰራው በጦር ሜዳ ብቻ ነው እሱም ቢሆን ገደብ አለው፡፡ የማይሆን ትዕዛዝ ከሆነ ለምን ብሎ መጠየቅ መብቱ ይመስለኛል፡፡ ስህተቱ አለቃ ሁል ጊዜ ትክክል ነው ብሎ ማሰቡ ላይ ነው፡፡ ይሳሳታል ሲሳሳት ደግሞ ተሳስተሃል ተብሎ መናገር ያስፈልጋል ለምን ቢባል ሰው እንደ እርግብ አይደለም አንዷ እርግብ ስትበር ሌሎቹም አብረዋት እንደሚበሩት አይነት ግም ለግም አብረህ አዝግም እንዲሉ፡፡ አለቃው ወይም መሪ ደግሞ ተሳስተሀል ሲባል ምንድነው የተሳሳትኩት ብሎ ማዳመጥ ግድ ይለዋል ምክኒያቱም እሱ አምላክ አይደለማ!! ይሳሳታላ!! ፡፡ ለምን ተሳስተሀል ተባልኩ ብሎ ካኮረፈ እንግዴ ምን ይደረጋል ያኩርፍ የፈረስ ፋንድያ ለቃሚ ከምሆን አስር ጊዜ አሱ ቢያኮርፍ ቢናደድ ቢቆጣ ቢደነፋ ቢማታ ይሻላል፡፡ እኔኮ ሰው ነኝ አስባለሁ አመዛዝናለሁ ክፉና ደጉን አውቃለሁ ታዲያ አንዴት አይኔ አያየ ጎኔ እየተወጋ ዝም እላለሁ፡፡

  ….ብቻውን «እንዴ እዚህ ዝርዝር ውስጥ የሌሉትን እንዴት ብዬላንሣቸው፡፡ በኋላ ደግሞ ከዝርዝሩ ውጭ አነሣህ ብለው ራሳቸውቢቆጡኝስ፡፡ እኔ ካዘዙኝ ውጭ ሠርቼ ዐውቃለሁ? አሁን ማንን ክፉለማድረግ ነው» እያለ ያጉረመርም ነበር፡፡
  አንሳ ያሉኝን ሁሉ ከማነሳ አንድ ጊዜ አይደለም ሺ ጊዜ ክፉ ይበሉኛ ፡፡ የገደል ማሚቶ ሆኜ እሳቸው ሲስቁ አብሬ አልስቅም እሳቸው የተናገሩት ልዩ ቃል ምንድነው ብዬ እሱን ሳንፀባርቅ አልገኝም የቃል ፋሽን ምን ያደርጋል በየጊዜው ተሰምቶ የማያውቅ ቃል እያመጡ ማሰልቸት ምን ያደርጋል ጉዳዩ ያለው ከቃሉ ሳይሆን ከቃሉ ትርጉምና ቁም ነገር ላይ ነው፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ ምናምን ብሎ ስም በመለጠፍ ብቻ ሙስና አይጠፋም ፡፡ ለማንኛውም ሸምዳጅ ትውልድ ከመሆን ያድነን፡፡ ዳኒ ይመችህ ቻዎ፡፡

  ReplyDelete
 32. Seriously Dani???!!! I expect better from you, and I know you are better than this ... But I know some times this happens, and great writers like yourself indulge in such triviality.
  Hope next time I will get your usual sober and enlightening opinions.

  Am big fan!

  ReplyDelete
 33. Dani

  It is so nice article

  ReplyDelete
 34. i like your article

  ReplyDelete
 35. hi dani tewon tekatlen eyenorn eko new yalenew.tiru maseb berasu wonjell behonebet hager.

  ReplyDelete
 36. ግን እኮ ጌታዉ አንሳኝ እያሉት፡እያዘዙት ለምን አላነሳቸዉም? ይህ ደግሞ አለመታዘዝ አይደል።

  ReplyDelete
 37. ግልፅ ቢሆንም መልእክቱ ቢተነተን መልካም ነበር። እንዲሁም መጨረሻ አነሣቸው ወይስ ጥሏቸው ሄደ?

  ReplyDelete