Monday, November 14, 2011

አቡነ አብርሃምን ሳውቃቸው


እኔ እና አቡነ አብርሃም የምንተዋወቀው ገና ወደዚህ መዓርግ ሳይመጡ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሳይሆኑ፣ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ሲማሩ ነው፡፡ ይበልጥ ያወቅኳቸው ግን ብዙ በሠሩበት እና ማንነታቸውንም ባስመሰከሩበት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አለቃነታቸው ነበር፡፡
የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ትምህርት ቤት ሲከፈት ከመድኃኒት ዘዋለ እና ከዳግማዊት ግርማይ ጋር የት/ቤቱ ቦርድ ሆኜ ሠርቼ ነበር፡፡ አቡነ አብርሃምን በሚገባ ያወቅኳቸው ያኔ ነው፡፡ እንደ አለቃ ይመራሉ፣ እንደ ባለሞያ ይሞግታሉ፣ እንደ አባት ይጋብዛሉ፣ እንደ ወንድም ስንጠፋ ይፈልጋሉ፣ እንደ ኃላፊ ይከታተላሉ፡፡
ትምህርት ቤቱን ለመስከረም ለማድረስ የነበረን ጊዜ ከሦስት ወር የማይበልጥ ነበር፡፡ ተማሪ መዝግበን፣ መምህር ቀጥረን፣ መዋቅር ዘርግተን፣ ቁሳቁስ አሟልተን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ አግኝተን ለማጠናቀቅ ሦስት ወር፡፡ መቼም በቦታው እርሳቸው ባይኖሩ ኖሮ ይሳካ ነበር ብዬ ለመገመት ይቸግረኛል፡፡
ሁሌም የማደንቀው አንድ አመለካከት አላቸው የተሻለ ሃሳብ ያመጣ ያሸንፋቸዋል፡፡ በስብሰባችን ላይ እርሳቸው አስተዳዳሪ መሆናቸውን እንኳን እኛ እርሳቸው ራሳቸው አያስታውሱትም ነበር፡፡ ክርክር ነው፣ ሙግት ነው፣ የተሻለ ነገር አምጡ ነው፡፡ በመጨረሻ የተሻለ ነገር ያለው ያሸንፋል፡፡ የርሳቸውን ሃሳብ የጣልንበት ብዙ ጊዜ ነበር፡፡ አንድም ቀን ግን ቅር ብሏቸው ወይንም አለቅነታቸውን ተጠቅመው ድምፅን በድምፅ ሽረውት አያውቁም፡፡
ሌላም የሚገርመኝ ጠባይ ነበራቸው፡፡ የሚሠራ ሰው ካገኙ ሥልጣናቸውን ጭምር ለዚያ ሰው ለማስረከብ ምንም አይቆጫቸውም፡፡ የሚያምኑት ሰው የሚሠራን ሰው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሲናገሩ የምሰማው አንድ ነገር ነው፡፡ «እናንተ የምትችሉትን ሥሩ፤ ሰዎች እኔን ሲጠይቁኝ አላውቀውም እንዳልል ግን ምን እንደ ምትሠሩ ንገሩኝ፤ ብታጠፉ እኔ ኃላፊነት እወስዳለሁ»ÝÝ በዚህ አስተሳሰብ ባይሆን ኖሮ ዛሬ አፍ አውጥቶ ሥራቸውን የሚመሰክረው የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ትምህርት ቤትን መሥራት ቀርቶ ማሰብ አይቻልም ነበር፡፡
አቡነ አብርሃምን በአሜሪካ የተሳካ ሥራ እንዲሠሩ ያደረጓቸው እነዚህ ሁለት ጠባዮቻቸው ከሌላው ዋና እና ብዙዎቻችን ካጣነው ጠባይ ጋር ተደምሮ ነው፡፡ አቡነ አብርሃም እንደ ግብጻዊው ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ለቅዳሴ እና ለሌሊት ጸሎት ልዩ ትኩረት አላቸው፡፡ እያመማቸው እና ሐኪም እየከለከላቸው እንኳን ሰዓታት፣ ኪዳን፣ ሰርክ ጸሎት እና ቅዳሴ አያስታጉሉም፡፡ እኔ በአጭር የሕይወት ታሪኬ ዲያቆንም፣ ካህንም፣ ጳጳስም ሆኖ ያገለገለ አባት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡
ክብርን ማዋረድ እና በሰዎች ዘንድ መተቸት የሚሉትን ነገሮች ሁሉ ለታላቁ የጸሎት አገልግሎት ሠውተው እንደ ዲያቆን «ተንሥኡ» ብለው ሠርክ ጸሎቱን ያደርሱ ነበር፡፡ ብቻቸውን ተነሥተው ለኪዳን ይገሠግሡ ነበር፡፡ ዲያቆናቱ ሲጠፉ ቤተ ልሔም ይወርዱ ነበር፡፡ ምንጣፍ ለማስተካከል፣ መጋረጃ ለመትከል፣ ዕቃ ለማሰናዳት ሲነሡ ጳጳስ መሆናቸው ትዝ አይላቸውም፡፡ አገልግሎቱ እንጂ፡፡
የአቡነ አብርሃም ድፍረት ከአቋም ጋር ነው፡፡ አዲስ አበባ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጥተው እያለ በፓትርያርኩ እግድ የትም ቤተ ክርስቲያን እንዳያስቀድሱ፣ በኋላም ከሀገር እንዳይወጡ ብዙ ጫና ነበረባቸው፡፡ ከዚህም ሌላ እርሳቸው የሚያውቁት ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን «የፓትርያርኩን ስም ካልጠራችሁ ከእናንተ ጋር ኅብረት የለኝም» የሚለው አቋማቸው አልተቀየረም፡፡ ሲፋጅ በማንኪያ፣ ሲበርድ በእጅ እንደሚሉት እንዳንዳንዶቹ ጊዜ እና ሁኔታ አይተው ቢለዋወጡ ኖሮ ተለዋዋጮቹ ያገኙትን ሁለት ሀገረ ስብከት አያጡትም ነበር፡፡
አቋም አቋም ነው፡፡ በችግሮች እና በሁኔታዎች አይለወጥም፡፡ አቋም የሌለው ሃይማኖት ሊኖረው አይችልም፡፡ ከአሥር አብያተ ክርስቲያናት በላይ በእናት ቤተ ክርስቲያን ስም እንዲጠቃለሉ ያደረጉት በዚህ አቋማቸው ነበር፡፡ «ከሕዝብ ከሚጣሉ ይህንን አቋምዎን ይተውት» ሲባሉ «ከእግዚአብሔር ከመጣላት ከሕዝብ መጣላት ይሻላል» ይሉ ነበር፡፡
በአሜሪካን ሀገር ታላላቅ ሥራዎች እየሠሩ የሚገኙ ሦስት ታላላቅ ማኅበራት አሉ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን፣ የሰንበት /ቤቶች አንድነት እና ማኅበረ በዓለ ወልድ፡፡ በተለይም የኋለኞቹ ሁለቱ በራሳቸው መዋቅር ነበር የሚጓዙት፡፡ እነዚህን ማኅበራት ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መሥመር ለማስገባት ከወጣቶቹ ጋር በመከራከር፣ በማሳመን እና አብረውም በመሥራት ያደረጉትን ተጋድሎ ሳስበው አቋም እና ሃይማኖት ያለው አባት ካገኘ ወጣቱ የት ሊደርስ እንደሚችል ይታወሰኛል፡፡
በተገኘው አማራጭ ሁሉ እየተጓዙ በጉባኤያቸው ላይ ይገኛሉ፡፡ መሥመር ያልያዘ መስሎ በተሰማቸው ነገር ሁሉ ሃሳብ ይሰጣሉ፡፡ ጉባኤያቱ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ የመውጫ መንገድ ያመለክታሉ፡፡ ራሳቸውን እንደ አንድ ተሰብሳቢ ቆጥረው ይከራከራሉ፣ እንደ አባት ይመክራሉ፣ እንደ ወንድም ያበረታታሉ፡፡
ትዝ ይለኛል የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ሲቋቋም እርሳቸው የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ዴንቨር ተደርጎ በነበረው የሰንበት /ቤቶች ጉባኤ ላይ የወጣቱ መንገድ ምን መሆን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ሁላችን እንፈራው የነበረውን አቋም ሠነዘሩ፡፡ ክርክር ተፈጠረ፡፡ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነው መጓዝ እንዳለባቸው በድፍረት ተከራከሩ፡፡
ከጉባኤው መልስ በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ቀስቃሽነት የተሰባሰቡ ወጣቶች የአቡነ አብርሃምን ሃሳብ ይዘው ተነሡ፡፡ በተለይም ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እያሉ ከፍተኛው ችግራቸው ማረፊያ ነበር፡፡ ይህ ነበር ወጣቶቹን ያንገበገባቸው፡፡ አባቶቻችን በልመና ቤት አያርፉም፡፡ መንበረ ጵጵስና ያስፈልጋቸዋል አሉ፡፡ ሌላም ችግር ነበር፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ እና በአካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የተሠራ ቤተ ክርስቲያን አልነበረም፡፡ በዚህም ምክንያት ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚቀድሱበት ቤተ መቅደስ አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹም ፖለቲካውን ፈርተው እንዳይመጡብን ብለው ወስነው ነበር፡፡
 ይህንን የወጣቶች ሃሳብ ሲሰሙ አቡነ አብርሃም ከኒውዮርክ ወደ ዲሲ በአውቶቡስ መጡ፡፡ በወይዘሮ ሐረገ ወይን ቤት ከወጣቶቹ ጋር ውይይት አደረጉበት፡፡ መቼም ወጣት የያዘው ነገር ኃይል እንጂ አቋም ለማግኘት ጊዜ ይፈጅበታል፡፡ ወጣቶቹ በልዩ ልዩ ሃሳብ ሲላጉ ከኒውዮርክ በአውቶቡስ እየተመላለሱ መክረዋል፣ አስተምረዋል፣ አሠርተዋልም፡፡ ጉባኤያት በተደረጉ ቁጥር ሳይሰለቹ ይገኙ ነበር፡፡ በአንድ በኩል ከገለልተኞች፣ በሌላም በኩል ከስደተኞች፣ ሲብስ ደግሞ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ነን ከሚሉ ዘረኞች የደረሰባቸውን ጫና ሁሉ ተቋቁመው በስም ብቻ የነበረውን ሀገረ ስብከት በሕግ እንዲቋቋም፣ መንበረ ጵጵስና እና የመንበረ ጵጵስና ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረው አድርገዋል፡፡
ከኒውዮርክ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመጡ በኋላ አናጺ ሆነው መንበር እየሠሩ፤ እንደ ልብስ ሰፊ መጋረጃ እያዘጋጁ፣ እንደ አካውንታት ሂሳብ እየሠሩ፣ እንደ ፕሮግራም መሪ ገንዘብ እንዲዋጣ እያደረጉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል፡፡ የአሜሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች ጳጳሳትን ሲፈትሹ ክብር በሚነካ ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን የፈታሾች ሥርዓት አልበኛነት ሊታገሡት ባለመቻላቸው የአንድ ቀን መንገድ ያህል በመኪና እየተጓዙ ነው አያሌ ሥራዎችን ያከናወኑት፡፡
አቡነ አብርሃም ከዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ወደ ሐረር እንዲዛወሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢኖርበትም ዋናው ምክንያት ግን የአቋም ሰው መሆናቸው ነው፡፡ የአበው ሊቃነ ጳጳሳት በር ሲደበደብ እና፣ አቡነ ሳሙኤል ከሥርዓት ውጭ ሲታገዱ «ይህ ከሥርዓት ውጭ ነው መታረም አለበት» ብለዋል በድፍረት፡፡ ተሐድሶ የለም የሚል ደብዳቤ ከመንበረ ፓትርያርኩ ሲደርሳቸው «ተሐድሶማ አለ፤ በዓይናችንም አይተነዋል» ብለው ነው በአደባባይ የተናገሩት፡፡ ከሀገረ ስብከት በላይ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ሲቋቋም ከማንም ቀድመው ነው ስሕተት ነው ያሉት፡፡ በመጨረሻም «የሲኖዶሱን ውሳኔ ባልስማማበትም አክብሬ ወደ ታዘዝኩበት እሄዳለሁ» ያሉትም የአቋም ሰው በመሆናቸው ነው፡፡
አሜሪካ አቡነ አብርሃምን አጣች እንጂ አቡነ አብርሃም አሜሪካን አያጧትም፡፡ ለአንድ ሐዋርያ ሀገሩ ሁሉም ነው፡፡ ምናልባትም ሰው ካልሄደ አይመሰገንምና ከእርሳቸው በኋላ የሚመጣው ሰው እርሳቸውን የሚያስመሰግን ይሆናል፡፡ «ትሻልን ሰድጄ.....» አይደል የሚባለው፡፡
አሁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት ሊቀለበስ ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ከአቡነ አብርሃም ይልቅ ከባዱ ቀጣይ ዕዳ ያለው በሲኖዶሱ እጅ ነው፡፡ አቡነ አብርሃምማ ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደውም ሥራ ይሠራሉ፡፡
መልካም የአገልግሎት ዘመን

80 comments:

 1. እግዚአብሔር አምላክ ለብፁዕ አባታችን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ይስጥልን!! ሁሉ ነገር ለበጎ ነው፤ ምናልባትም ብፁዕ አባታቸን ወደዚያ ቦታ መሄዳቸው ለአሕዛብ ሁሉ መዳኛ ምክንያት ሊሆን ይችላልና እግዚአብሔር ይመስገን!!
  እሱባለው፤ ከደብረ ማርቆስ

  ReplyDelete
 2. Dear D/N Daniel, thank you very much! I am very happy today on you: 1) You made me know Abba Abraham & 2) you fully concentrated on the Church, you never mixed things. You are loyal and have the right to write such things. You have invaluable products when you are writing on issues related to the Church! I could not find a book/script comparable to , for example. You can address Social things though spiritual matters, as Abba Shinouda is doing or Abba Yohannes Afework did. Others, let them write their own. You have many assignments here! Thank you again!

  ReplyDelete
 3. Danie please continue ur writing,just underlining the right is right and the false is false!

  ReplyDelete
 4. Betam Desyemile tshuf newu Egzeabher yistlen. Abatachinem kezhi befit bakabetut limdena be tselot ye Hararen akababi chiger endmifetut emnete newu. Le Abatachine Egzeabher amlak regime edme ke tena gar yisteline amen.

  ReplyDelete
 5. Dn. Daniel Thank you very much that you share knowledge about our Courageous an d true Father.
  Please tell us about other fathers who are like Abune Abraham so that we know our true fathers.
  O God! Please give us thousands of such Fathers so that we will be saved from death!!!!

  ReplyDelete
 6. The EOT church needs determined fathers like Him. A devoted and spiritual father! I'm sure He will change Harar too. Dear Your Grace, We love you so much! We heartily wish you long life with a good health. Endih new Hawaria!! Dani thanks for sharing! KHY!

  ReplyDelete
 7. Dani thank u አሜሪካ አቡነ አብርሃምን አጣች እንጂ አቡነ አብርሃም አሜሪካን አያጧትም፡፡ ለአንድ ሐዋርያ ሀገሩ ሁሉም ነው፡፡ ምናልባትም ሰው ካልሄደ አይመሰገንምና ከእርሳቸው በኋላ የሚመጣው ሰው እርሳቸውን የሚያስመሰግን ይሆናል፡፡ «ትሻልን ሰድጄ.....» አይደል የሚባለው፡፡

  ReplyDelete
 8. የሆነው ሁሉ ለበጎ እንደሆነ እናምናለን
  10q dani

  አቡነ አብርሃምማ ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደውም ሥራ ይሠራሉ፡፡

  እኝም ከእግዚአብሄር የተሰጡን ናቸውና አብዝተን እናከብራቸዋለን እንተባበራቸዋለን
  habtamu Z Hawassa

  ReplyDelete
 9. ዳኒ ተባረክ! አንተ በርክትልን
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 10. እግዚአብሔር አምላክ ለብፁዕ አባታችን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ይስጥልን!! መጽናኛ አባት አያሳጣን፡፡

  ReplyDelete
 11. የአባቶች ስራ ይህ ነው፡፡ እ/ር ይጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete
 12. የአባቶች ስራ ይህ ነው፡፡ እ/ር ይጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete
 13. still the world has few good fathers like Abune Abraham

  ReplyDelete
 14. thank you d/n Dani for letting me know this respected father of us!!!!!!!!! god bless Ethiopia and Ethiopians!!!!!!!

  ReplyDelete
 15. Aba Abreham we all gonna miss you may be we have to pray more like harer.any ways becarful we need you alive.aba pawols did not like ur good work & his gets sick when he thinks of ur hard work.since he do not like orthodoxy.

  ReplyDelete
 16. endi new abat yesemen america lgocho hule kegonot nen

  ReplyDelete
 17. ""ተሐድሶ የለም የሚል ደብዳቤ ከመንበረ ፓትርያርኩ ሲደርሳቸው «ተሐድሶማ አለ፤ በዓይናችንም አይተነዋል» ብለው ነው በአደባባይ የተናገሩት፡፡""እንደእኔ አስተሳሰብ ተሐድሶው መንበረ ፓትርያርኩ እራሳቸው ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 18. Bazehe zemene enedehe ayenate abate manoro batame
  dase yelale.anetane cher ware yasamahe.laabatachenem yadakamolate bata keresttaine ferawane enedayo harerrem yabalata fera aferetawe lamayate edema katanenate yestote

  ReplyDelete
 19. thanks to god.abune abrhamen yale abat ayasatan.yebetekristiyanachen chiger ewnetegn abat newena

  ReplyDelete
 20. እግዚአብሔር አምላክ ለብፁዕ አባታችን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ይስጥልን
  ከሐረር

  ReplyDelete
 21. ኢትዮጵያ እያሉ ባላውቃቸውም አሜሪካ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የሚሰሩትን በቅርብ ስለማውቅ ለታታሪነታቸው ምስክር ነኝ:: ከኒው ዮርክ ዲሲ ስንት ጊዜ በቻይና አውቶቡስ ( ንጽህናው ያልተጠበቀ እና የመንገድ ላይ ደህንነቱ ባልተጠበቀ) የራሳቸውን ህይዎት አደጋ ላይጥለው ያደርጉት የነበረው ምልልስ አይረሳኝም:: እሳቸው ከመምጣታቸው በፊት በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ይመሩ የነበሩትን አባት አቡነ ማትያስን እነ አባ ሰረቀ ከፓትርያርኩ ጋ በነበራቸው ከመዋቅር ውጭ ያለ ግንኙነት ምንም እንዳይሰሩ የጀመሩትን እያፈረሱ እና ከፓትርያርኩ እያጋጩ ሲያስቸግሯቸው እንዳልነበር ይህን ሁሉ ፈተና ማለትም ከገለልተኛው፣ ከስደተኛው፣ ከመዋቅር ውጭ ለሲኖዶሱ የማይታዘዙ ነገር ግን በአገር ልጅነት ይሁን በአላማ ለፓትርያርኩ በግል ያሚታወቁ እና የአቡነ ጳዉሎስ እምባ ጠባቂዎች ነን ከሚሉት ሁሉ የተደራረበውን ፈተና ትችት ችለው የእናት ቤተ ክርስቲያን እንድትታወቅ ያደረጉት ሥራ ቀላል አይደለም:: እዚህ ቢሆኑ ከዚህ በበለጠው ሊሰሩ እንደሚችሉ የታወቀ ነገር ነው ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ማፍረስ አላማቸው የሆነው አባ ጳውሎስ ስራና ሰራተኛን ማለያየት የዘወትር ልማዳቸው ነውና አስነስተዋቸዋል:: ለቤተ ክርስቲያን ግን ከዚህ በበለጠ ሃረር ላይ ብዙ ሊሰሩ ያሰበው እግዚአብሔር ያሰበው ነገር ይኖራልና በዚያም ሰራተኝነታቸው የተሳካ እንዲሆን በጸሎታችን እናስባቸው:: ሃረር በአሁኑ ጊዜ የተሃዲሶ መፈንጫ መሆኗ የአደባባይ ሚስጢር ነው ለዛ ደግሞ ተዋጊ ያስፈልገዋል::

  ReplyDelete
 22. Lol,here is another voice of Mahibere Kidusan/Deje selam. Yes,this father was under an intense and forcible indoctrination of Mahibere Kidusan members here in the States and he was reflecting the Mahiber's set of fixed beliefs and ideas. Mk was using him as the time is very taugh for them these days and wants to have someone to represent them from every corner.

  What makes interesting after all is the establishment of the new Kidane Meheret church here in silver spring (Mary land)under the pressure of the top members of MK here before he leave the states for good.

  As you mentioned in your post, you are reflecting your ideas like the Mk members here that the new ordained father(Abune Fanuel) is not likeable by the members and it is for that reason that this father and the MK members wants to have their own church not to work with him. And who knows ,may be this new church might be a seat for Abune Abreham in the future as this was the trend of the church in USA.

  I might agree with your testimony that this father tries to bring together the other two mahiber to work together under the control of Maibere Kidusan and made a big favor for the MK to hijack others and put their Mahiber's name on top of the church as an idol.

  Here in the areas where I reside in Abune abreham was cursing the other churches and putting some false allegations on the church's fathers and Synod using the web Deje selam which is sponsored and written by MK.

  Abune ABREHAM didn't even try to bring together in one ;let alone the "Sedetegna Synod"/"Geleltegna church"; the other couple of churches who are claiming that they are under the EOTC synod and adminstration.Rather he was trying to make them come under his power by force without listening to their problems.

  Hey Dani please try to be fair to your witness since his weakness are known by most of the people here and didn't match with what we saw and heard.YES EVERY MENBERS OF MK IS A FAN OF THIS FATHER.

  Ewnetu

  ReplyDelete
 23. እንዲህ ነው ዳንኤል አሁን ወደ ርምጃ መጣህ አንጀቴን አራስከው ቤተ ክርስቲያን እንዲህ አካፋውን አካፋ ዶማውን ዶማ የሚልላት ነው የምትሻው የሚመሰገን ይመስገን የምወቀስ ይወቀስ ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ

  ReplyDelete
 24. Dani enameseginalen endezih cher cherun yaseman bezih gize endih aynet Abat new yemiyasfelgat le Betkirtiyan eshi bilo yemitazez abat kerasu michotina zina befit lehayimanot kidimiya yemiset abat!EGZHABHER yagelgilot zemenachewn yabzaw!

  ReplyDelete
 25. Egziyabhey her rejim edme ena Tena le Aba Abrham yistilin..betam betam bizu dekimewal in America, bizum tebesachitew neber bemiseraw sihitet hulu ...God be with Aba Abrham...behedubet teketelachew

  ReplyDelete
 26. መልካም አባትNovember 14, 2011 at 9:33 PM

  አባቶችማ ነበሯት: አሏት:: ለአንድ ሰው ነው የምንታዘዘው ወይስ ለእግዚአብሔር?..." ያሉት አቡነ በርናባስ: እንደ እርሳቸው በህይዎት ያሉም:: ነገር ግን ወደ ፊት ማን ይሆን የሚትካችው???

  ReplyDelete
 27. ሰላም ዲን ዳንኤል

  ስለ ብጹዕ አባታችን በጻፍከዉ ጽሁፍ የልቤን ስለተናገርክልኝ እግዚአብሔር ይባርክህ ፅሁፉን ሳነበዉ በዉስጤ አምቄዉ የነበረዉ ብሶቴ ፍንቅል ብሊብኝ በጣም አለቀስኩ። አቡነ አብረሃም መጽናኛዬ፣የወለደኝ አባቴ ሲሞትብኝ ባልወልድሽም አባትሽ ነኝ ብለዉ አበራታች አባቴ፣ለችግሬ ደራሽ፣ ለመንፈሳዊ ሕይወቴ ጥንካሬ፣ በወሬ ሳይሆን በእዉነት የሚሰሩ፣ የምኮራጋቸዉ አባቴ ናቸዉ። እንዳልከዉም እኛ አጣናቸዉ እንጂ እሳቸዉማ መከራ የመረጡት ሕይወት ነዉና ምን ይሆናሉ።

  አባታችን የፍቅር አባት፣ ብርታትን ሰጪ፣ መንገድ መሪ፣እ ዉ ነ ተ ኛ አባት ስለሆኑ ምንም እንደማይሆኑ አዉቃለሁ። በሔዱበት እማምላክ ትከተሎት እላለሁ። እርስዎን በማጣቴ እንደምጎዳ ሳልጠቁም አላልፍም።

  የመንፈስ ልጅዎት

  ReplyDelete
 28. enate yamettesadeken nafese gorabate yawekatale tele nabare..enda abatachen malate nawe.holachenem kasachawe enemare

  ReplyDelete
 29. ቸሩ፡አምላክ፡በሄዱበት፡ሁሉ፡ይጠብቃቸው!
  የወላዲት፡አምላክ፡ምልጃ፡አይለያቸው!
  የቅዱሳን፡መላእክት፡ጥበቃ፡አይለያቸው!
  የጻድቃን፡ሰማዕታት፡ፀሎት፡አይለያቸው!

  ReplyDelete
 30. ግዚአብሔር እንዳንተያለ እውነተኛ ምስክር ለተክርስቲያናችን አያሳጣን
  ዲ. ዳን ኤል አቡነ አብርሃምን እኔ ልጅ እያለሁ ነው የማቃቸው መርካቶ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ነው ያደኩት በዚያ ቦታ ብዙ ታላላቅ ስራዎችን አክናውንዋል ለዚህ ተግባር አላማ አድርገው የተነሱት ስብክተወንጊልን በማስፋፋት ነው በዚህም ምክኒያት የአጥቢያችን ቤ/ክ የራሱ ግቢ እዲኖረ ከማስቻላችው ባሻገር ለሌላ አጥቢያ ቤ/ክ አራያ እዲሆን ያስቻሉ ታላቅ አባት ናችው ይህንን ሁሉ ስራ ሲስሩ ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ አልነበርም ለሳችው የተለያዩ ተቃውሞዎች በየጊዜ ይደርሱባቸው ነበር ዲ. ዳን ኤል እንደጠቀስው ሁሌም ክአገልግሉት የማይለዩት ብፅዎነታቸው በደቡሩ አስተዳዳሪ በነበሩ ጊዚ ሁሌም በስብክተወንጊል አይለዪም ነበር ይህ ጥንካሪአቸው በጣም ያስደምመን ነበር ስለሆነም በቃለወጌል ህዝቡን በማስተማር ለቤ/ክ ቅን የሆኑ ህዝበ ክርስቲያንን በማስባስብ ብዙ ስራዎችን ስርተዋል ህዝቡም ይህንን ሰራቸውን በተግባር በማየቱ እና ሁሌም በቃለወጌል ህዝቡን በመምከር ሁሉም ለቤ/ክ ልማት በአንድነት እዲነሳ አድርገዋል በመጨረሻም ህዝቡ ሁሉን ተረድቶ አላማቸው ሳይገባቸ የትቃዎሟቸው ይቅርታ ጠይቅው ረጅም እድሜ እና ጤና ይመኙላችዋል እስካሁን '' ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ ን''ነው እና ነገሩ ወደታላቅ ሹመት የተዛወሩት ብፅዎነታቸው ህዝቡ ለሳቸው ያለው አክብሮት እን ፍቅር ይበልጥ እየጨመረ መጣ በበአላት ጊዜ ሲገኙ ህዝቡ ግልብጥ ብሎ ይመጣል ይባትነቱን ፍቅር ለመግለጽ በዝህ ምክኒያት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያ እንዳሄዱ ተከልክለዋል :: እግዚአብሔር ፍቃዱ ሆኖ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በአሜሪካ በኒዎርክ ለማግኝት ችያለሁ በኒዎርክ የሚገኝው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ቅ.ስላሴ በስሜን አሜሪካ በመጀመሪያ ያን ቤ/ክ ሳዬው እና ችግሩን ስረዳ እንደ ታሪካዊነቱ በጣም አዘንኩ በደጉ ንጉሥ ጃንዎ ዘመን አሁን ላለነው ትውልድ በሎም ለመጪው ትውልድ አስበው ነው የገዙት ባለው አስተዳደራዊ ብልሽት ነገ በመግስት እንደሚወስድ ጥርጥር የለኝም::
  የቤ/ክ ይዞታ ትልቅ ስለነበረ ኒዎርክ በሚያክል ከተማ : በፅሎቴ ወደ እግዚአብሔር ብፅዎነታቸው ወደኛ እንዲመጡ ስጽልይ በሌላ መልኩ ቤ/ክ ለሚገኚ ወንድሞች እና እህቶቼ ሁሉ ለዝህ ቤ/ክ እኒህ አባት ነበሩ የሚያስፈልጉ እያኩ ሳጫውታችው በዝህ ሁኔታ እያለን አንድ ዜና ስማን ለኒውዮርክ ሀገረ ስብከትሊቀ ጳጳስ መመደቡን በዚህ ጊዜ እውንት ፅሎቴ እንደስመረ ያውኩት በመጡ በሁለተኛ ቀን ነብር : እጅግ በጣም እግዚአብሔርን አመስገኩ::
  ቤ/ክ ተዟዚረው ካዩት በኋላ በዙ ስራ እንደሚጠብቃቸው የተረዱት ብፅዎነታቸው ሳይውሉ ሳያድሩ ወገባቸውን ታጥቀው ተንሱ ከመቅደስ ሀ ብለው የጀመሩት ስራቸው ጊቢውን አልፎ ወደውጭ የግረኛ ምንገድ ዘለቀ እንደአናጺ የተስበረውን ሲያቀኑ እንደፅዳት ስራተኛ ሲያፅዱ እንደነበር የቅብ ጊዜ ትዝታ ንው::
  የመጡበት ጊዜ የፍልስታ ፆም ሊገባ ጢቂት ግዜ ሲቅርው ነበር ተሞክሮ እና ታስቦ በማይታወቅበት በዚያ ቤ/ክ በጠዋት በመነሳት ኪዳን ማድረስ ጀመሩ በመጀሪያዋ ፍልስታ ፆም በመጀሪያ ሃሳቡን ሲያቅርቡላችው እንቢታቸውን የገለጽት የደብሩ አስተዳዳሪ ተስፋ ቆርጠው እንደማቆሙ ሲረዱ አብርዋቸው በመፀለይ የፍልስታ ፆም ዘልቀዋል::
  በቤ/ክ ውስጥ ያልበላይ ተቆጣጣሪ ሲኖሩ የነበሩ አዝማሚያው ስላላማራቸው በተለያዬ አቀራረብ ለመቅረብ ሞከሩ ምግብ በማቅረብ
  የተልያዩ እንክብካቤዎችን በማድረግ '' ለኔ ጥሩ ናችሁ ነገር ግን ለቤ/ክ ጥሩ አድላችሁም'' በማለት በድፍረት ይገስፃችው ነበር;;
  ብፅዎነታቸው ከመምጣታቸ በፊት ቤ/ክ ውስጥ ከሐሻው ቁጥር ይልቅ የጀማይካዊያ ቁጥር ያዬለ ነበር እሳቸው ክመጡ በኋላ ብዙ ሐበሾች ሊመለሱ ችልዋል ሁለቱንም ዜጋ በማስተባበር ያገር ቅርስ መሆኑን በማሰርዳት በማስተማር በዙ ደክመዋል ቤ/ክኑን አዲስ ፕላን ዎቶ ይሀም የ ኢትዪ ጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ አስራር ይዘት ያለው ነበር በዝህ ጅማሮ ላይ እያሉ ወደ ዲሲ ተዛወሩ:;
  በዲሲ ምን እንደስሩ የዲሲ ምፅመናን የሚመስክረው ነው '' ቤ/ክ እዳግለግላት ልካኛለች '' ሁሌም እንድሚሉት ''በመሽሽ እና በማኩረፍ ለውጥ አይመጣም ሁሉንም ችግር በቤ/ክ ውስጥ ሆኖ ነው መጋፈጥ'' እግዚአብሔር እድሜእና ጤና;;
  ተስፋዬ ክፍሌ ከሲያትል

  ReplyDelete
 31. Abetu!! Sele Degage Abatoch Setele Yehenen Kifu kene Asaterelen? Lela Mene enelalen

  ReplyDelete
 32. what is ur point daniel mekfafelen eyastmark yemselale

  ReplyDelete
 33. "እኔ በአጭር የሕይወት ታሪኬ ዲያቆንም፣ ካህንም፣ ጳጳስም ሆኖ ያገለገለ አባት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡"

  That is true!! I witness this!! Thank you Dn. Daniel. There are a lot to be said about Abune Abrham.

  ReplyDelete
 34. Dear Dn. Daniel,
  Abune Abrahamn letinish gize awuqchewalehu. Yalkew hulu ewunet new. Abune Abraham yesira ena ye aquam sew nachew.

  እግዚአብሔር አምላክ ለብፁዕ አባታችን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ይስጥልን!

  ReplyDelete
 35. Dersane Abune Abrham written by Dn Daniel.

  ReplyDelete
 36. you are as always a great writer.

  ReplyDelete
 37. Eyalekesku anebebkut. Lela min malet yichalal. Yekidus sinodos fetena kezih behuwala new. Dani gin lemin simeten korkureh enbayen bekebourd lay teb adergkibign? You know Dani I can't answer one question, serious question, "why his holiness Abune Pawulos is doing all these things?" The worst thing is that it is increasing every day. What is the root reason behind? YOU MADE ME CRYING. ANY WAY THANK YOU Dn DANI

  ReplyDelete
 38. ዳኒ ፤ምስጋና ለሚገባው ምስጋና እና ምስክርነት ይሉዋል ይሄ ነው የማናውቅ እንድናቅ የምትከፍለው መስዋእትነት አንተንም ያስመሰግናል ፡፡ ዮናስአበበ

  ReplyDelete
 39. dear ato eshtu i have seen ur comments on daniel blog. i am very sorry that for the way u comment though it is ur right to say what ever u want it hurts me if people say such stupid comments against our fathers. i realy sorry for my words but u are not from the church rather u are among the tehaddso or menafik i can not see the problem that mahibere kidusan and other mahiber are working together but as i can see it is ur problem. pls u see things fairly not daniel do not tuch him.

  ReplyDelete
 40. You did great! Kal hiwot yasemalin.

  አባታችን ብርቱ እነደሆኑ መስክረህላቸዋል፡፡ ወደፊትም እነደዚሁ በርትተው የምንኮራባቸው ይሁኑ፡፡ የሲኖዶሱን ውሳኔ አክብረው መመለሳቸው በራሱ ትልቅ ያሰኛቸዋል፡፡ ይበረቱልን ዐባታችን፡፡ እንወድዎታለን!

  ReplyDelete
 41. ኣሁን እኔ የምኖረው ካናዳ ነው። በአዲስ አበባ ቅ. ራጉኤል ቤ/ክ እንዴት ለክርስቶስ ወንጌል ይደክሙ እንደነበር እኔና ሌሎች ክርስቲያኖች ምስክሮች ነን። ማን ያውቃል በሓረርና አካባቢው ክርስቶስን ሊሚያወቀው ወገን ማስናኛ፡ ለሌላው ወገን ደግሞ የክብሩን ወንጌል እንዲሳሰፉ የእግዚአብሔር አላማ ጠርቶአቸው ቢሆንስ።

  እግዚአብሔር አምላክ ለብፁዕ አባታችን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ይስጥልን!

  ReplyDelete
 42. መልካም እረኞች በባለሙያተኞች ተውጠው እንዳይቀሩ እንዲህ ታሪካቸውን ብናውቀው መልካም ነው፡፡ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 43. ዳኒ እግዚአብሔር ብርታቱንና ጽናቱን ይስጥኅ፣ለቤ/ክ በምትከፍለው መስዋእትነት ኮራሁብህ

  ReplyDelete
 44.  አቡነ አብርሃምን አላውቃቸውም፡፡ እውነትን መመስከርና መልካም የሰራን ማመስገን እንደኔ ለማያውቁና መረጃ ለሌላቸው የእውነትን ብርሃን ይገልጣልና ይህን ስለጻፍክልን እናመሰግንሃለን፡፡ እኔ ጭንቅ የሚለኝ ግን ቃለ እግዚአብሄርን የምትሰብክ ቤተክርስቲያናችን ከቂመኝነት፣ ከአድልኦ፣ ጥቅምን ከማሳደድ፣ ራስን ከመውደድ፣ በብሔር በቋንቋና በጎጥ ከመለያየት የምትድነው መቼና እንዴት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 45. YeAbatachin Burakeachew ayleyen yagelglot edmeachewin yarzmlin...antenim kalehiwot yasemalin dani !

  ReplyDelete
 46. Hey Dani, the reason why you wrote this about Abune Abreham is to get the credibilty that you lost back from the members of mahibere kidusan!!! otherwise I am definately sure that you knew the truth about him. Luckily your poor psycology drama is working here I think.

  Sorry for my hash comment,just to let my feeling out.

  ReplyDelete
 47. Re: moges said...

  Hey Ato Moges, sorry if my comment offends you but I think I have a right to put my ideas depending on the fact and reality that everyone can see if one is not his biased mood. Please try to accept others who are different from what you normally brain washed and don't rush to say "tehadiso" or "manafik".
  This shows me from which group you are from as I mentioned earlier ( FROM MAHIBERE KIDUSAN).

  Thanks for Daniel Kibret( you Ex-top representative), he mentioned that whoever IS against the ideas of the mahiber or whoever is challenging the mahiber; he will be given the name MENAFIK OR TEHADISO.

  Please my brother Moges in Christ, try to make your base and foundation of your faith on the words of the Lord and on the true righteous fathers. But not on some of the political dogma drama style enforced in your brain by someone whose intellectual credentials are derived solely from their experience of your TOLAY(amharic word) life.

  ReplyDelete
 48. ዳኒ ሰለ አቡነ አብርሀም የፃፍከው ቢያንስ እንጅ አይበዛም
  እኛም ያየነው ይህንኑ መልካም አባትነት ከፀሎትናከትህትና
  ጋር አባታችን አሜሪካ ቀረባት እንጅ እሳቸው አልቀረባቸውም
  መልካሙን ፍሪአቸውን አይተናል የአገልግሎት ዘመናቸውን
  ያርዝምልን።
  ብርሀነ ትንሣኤ።

  ReplyDelete
 49. ብጹዕ አባታችን

  የእርስዎ መኖር ለእኛ ተስፋ ነዉና እባክዎትን ከእነዚህ ተኩላዎች ራስዎን ይጠብቁ
  እንደነ አቡነ በርናባስ እንዳናጣዎት አባ ጳዉሎስ ከሆኑ ለምንም ወደ ኋላ የማይሉ ናቸዉና
  ለቤተ ክርስቲያን ያላዘኑ ለጳጳስ ለዝያዉም ለእዉነተኛዉ?

  ቡራኬዎት ይድረሰን

  ReplyDelete
 50. Thank you for sharing what you want to share with us. Did he accumulate personal properties such as house in AA, cars,cash in banks, etc. Also, did he work more in uniting christians or divide them. Please be critical when you write. I don't think abo,abo mebabal is good for us who seek good leadership by example.In my humble personal opinion articles like this hurt our church more than it benefits it.Please take the full picture of a persons account.This is 21st century.

  ReplyDelete
 51. አቡነ አብርሃም ድፍረት ከአቋም ጋር ነው፡፡ አዲስ አበባ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጥተው እያለ በፓትርያርኩ እግድ የትም ቤተ ክርስቲያን እንዳያስቀድሱ፣ በኋላም ከሀገር እንዳይወጡ ብዙ ጫና ነበረባቸው፡፡ ከዚህም ሌላ እርሳቸው የሚያውቁት ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን «የፓትርያርኩን ስም ካልጠራችሁ ከእናንተ ጋር ኅብረት የለኝም» የሚለው አቋማቸው አልተቀየረም፡፡ ሲፋጅ በማንኪያ፣ ሲበርድ በእጅ እንደሚሉት እንዳንዳንዶቹ ጊዜ እና ሁኔታ አይተው ቢለዋወጡ ኖሮ ተለዋዋጮቹ ያገኙትን ሁለት ሀገረ ስብከት አያጡትም ነበር

  ReplyDelete
 52. Egzeabehr amelak le abatachen rejem yeagelgelot zemen yestelen.
  Hareroch Ahun kefet yelke Bertu...

  Welettsadke

  ReplyDelete
 53. በቅ. ሲኖዶስ ውሳኔ ባዝንም በብጹዕ አባታችን አቋም ተጽናንቻለሁ:: ቃላቸውን ያላጠፉ, ያስተማሩንን በተግባር ያሳዩን ናቸው - ብጹዕ አባታችን:: መንፈሳዊ ማዕረግ ማለት አገልጋይነት መሆኑንም አሳይተውናል:: ምዕመናን በአገልጋዮች በንቀት በሚታዩበት በዚህ ዘመን ዝቅ ብለው አገልግለውናል::የጻፍከውን በዓይኔ አይቸዋልሁ:: ምስክርነትህም እውነት ነው!

  Astatke

  ReplyDelete
 54. Aba we love and respect you. you did a great job here in U.S. May the almighty God protecet you from tehadesow pawelos.

  ReplyDelete
 55. he is a good father.pure faith.dedicated.may God help him

  ReplyDelete
 56. I didn't know that we have such a father... unless someone like you tells us about such fathers, how can we know about them? I wish we had many more of them who are as firm and devout as Abune Abraham. Imagine where our church can get if we had such a patriarch... I have a dream that one day we will have a pope who will be a source of pride for the church rather than a cause of disgrace.

  ReplyDelete
 57. ዲ.ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡

  ብጹዕ አባታችን ለሌሎችም አባቶች አርአያ የሚሆኑ ናቸው፡፡
  በአሁን ጊዜ እንኳን ከአሜሪካ ወደ ሐረር ለመመለስ አ.አ. ውስጥ እንኳን ከደብር ደብር ለመቀየር ስንት ነገር እየተሰራ ነው፡፡ ግን ይህንን ውሳኔ እንዳይለውጡ በፀሎት ማገዝ አለብን፡፡

  ማን ያውቃል ከምን ሊሰውራቸው እንዳሰበ፡፡ እርሱ እግዚአብሔር ነው በስራውም ስህተት ከቶ የለበትም፡፡ የአባታችንን በረከት ያሳድርብን፡፡

  ሐረሮች ደግሞ አብረው ለመንፈሳዊ ስራና ለልማት ለመነሳት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  ሰው ናቸውና ደግሞ ከውዳሴ ከንቱ ጠብቆ ለበለጠ ክብር ያብቃልን፡፡

  ReplyDelete
 58. Biniam from Nashville TN Debra keraniyo MedhanialemNovember 16, 2011 at 12:25 PM

  DN. Daniel :- we need more writers like you . the following are a few that I do know very well :-"ክርክር ነው፣ ሙግት ነው፣ የተሻለ ነገር አምጡ ነው፡፡ በመጨረሻ የተሻለ ነገር ያለው ያሸንፋል የርሳቸውን ሃሳብ የጣልንበት ብዙ ጊዜ ነበር፡፡ አንድም ቀን ግን ቅር ብሏቸው ወይንም አለቅነታቸውን ተጠቅመው ድምፅን በድምፅ ሽረውት አያውቁም፡፡" ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረን'ነው.very true !
  አሁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት ሊቀለበስ ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ it time for all of as to pray!
  እርሱ እግዚአብሔር ነው በስራውም ስህተት ከቶ የለበትም፡፡ Amen !Amen!

  ReplyDelete
 59. Hi. D.Daniel. I know I am a little bit late on this to add my comment, but it is better than keeping quite. All what you said about Betsu Abune Abraham is 100% true. I know His Holiness for short time, but very close and accept that all your writing about him is very true. He is one of the best people I met in my entire life. Open, friendly, trusted, hard working and like very close family person. All the people I know admire him for his being one of the few numbered true EOT Church fathers. I have closely followed the situation in the past few years and activities around him. Specifically in DC and the surrounding Churches. It is very hard to accept the idea of his transfer from his current position. I cannot say he is trnafered, but removed un fairly. We all understand that, non of us have guarantee to live permanently any where in the world. Pre-conditions declare wheather some thing happened right or wrong. According to the Church's procedure, in his case it was wrong. Any negative comment on him would mean abnormal, sick, short of real information or should be purposefully defamatory. Spiritually nobody should be againest any one, but love only. People do it any way; what can we do? I wish he stayes here and finish the work he started. But if not I wish him all the best where ever he goes. Betsu Abune Abraham if in case you read this message, please remember us in all your prayers.

  ReplyDelete
 60. ለምን ሊሰራ የተነሳዉን በእንቅፋት ለመጣል እንደሚሞከር አይገባኝም ፤ እኚ አባታ በአሜሪካ ዉስጥ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ቡዙ ስራ ሰርተዋል ማዘዋወሩ ለምን አስፈለግ። ግድ የለም ፣ ልቤን በነካዉ ለመዝጊያ በተጠቀምከዉ ሁሉን ለመድሃኒያለም አሳልፈን እንሰጣለን፦

  "አቡነ አብርሃምም ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደዉም ሥራ ይሠራሉ።"

  San Jose, CA

  ReplyDelete
 61. እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን!!
  ፀጋውን ያብዛልህ ዲ. ዳንኤል
  Ameha Giyorgis ከZambia

  ReplyDelete
 62. selehulum neger egziabher yimesegen

  ReplyDelete
 63. ዘሶልያና ከቀጨኔ አዲስ አበባNovember 17, 2011 at 10:09 AM

  ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን
  እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ያሉ አባቶች አያሳጣን፡፡ እንደ አቡነ አብርሐም አርአያ ሊሆን የሚችል ሥራ ሠርተው ያለፉ አሁንም በሕይወት ያሉ አባቶች አሉ፡፡ የእነዚህ አባቶች መልካም ሥራ በዚህ መልኩ መመስከር ለውዳሴ ከንቱ ወይም ለእነሱ የሚጨምርላቸው ነገር ኖሮ ሳይሆን እንደ እኔ ዓይነቱ ከቀቢጸ ተስፋ (አሁንማ ምን አባት አለ ጳጳሳቱ ሁላ ለቤተ ክርስቲያን መቆርቆር ትተዋል ብሎ ተስፋ ለምንቆርጥ) እንዲጠበቅ ይረዳ እንደሆን እንጂ፡፡ ለአባታችን ረዥም የአገልግሎት ዘመን ከጤና ጋር ይስጥልን፤ ከዚህ አቋማቸው አይለውጥብን፡፡ ሐረሮችንም እግዚአብሔር አምላክ ያበርታልን ከእኚህ አባት ጋር በፍቅር፣ በስምምነት ለጋራ ቤታችን (ቤተ ክርስቲያናችን) ብዙ እንደሚሠሩ እምነቴ ነው፡፡
  ዘሶልያና
  ከቀጨኔ አዲስ አበባ

  ReplyDelete
 64. አሜሪካ አቡነ አብርሃምን አጣች እንጂ አቡነ አብርሃም አሜሪካን አያጧትም፡፡ ለአንድ ሐዋርያ ሀገሩ ሁሉም ነው፡፡ አቡነ አብርሃምማ ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደውም ሥራ ይሠራሉ፡፡

  ReplyDelete
 65. when my doughter,she is only 4,didn't see Abune Abreham in our church she ask "where is the papas?" now it is hard for me to answer .if i told her He went to ethiopia she will ask me "WHY?" so i have to tell her the truth that the patriarch don't like people working hard for their church,"why?"" why? " it is her age to ask "why?" and it is my responsibility to tell the truth.

  ReplyDelete
 66. May be the "kidus synod" is hijacked, Don't you think? by whom? i don't know but i have suspicion as every body might know. however; it is not the matter of who hijacked it, it is the matter of the true fathers who has the ability to dismantle the problem with the power of God. So far we haven't seen one. Fathers like Abune Abraham need prayer so they stay in the course of good deed as well as the disguised devil in the chair of Mark. Forgive me for the strong words. May God be with us.

  ReplyDelete
 67. this is a real story to prove ur idea,and an exiting also inspirational.

  ReplyDelete
 68. ዳኒ እንወድሃለን!
  እግዚአብሔር በረድኤቱ ከከንቱ ውዳሴ ፈተና ይሰውርህ!!!

  ReplyDelete
 69. nigusie
  dani kalehiyot yasemalin ibakihin yemitawuqachewun abatoch tarik hule tsafilin

  ReplyDelete
 70. መልካም የአገልግሎት ዘመን

  ReplyDelete
 71. "አቡነ አብርሃምም ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደዉም ሥራ ይሠራሉ።"

  ReplyDelete
 72. "ይህች ቤተክርስትያን በእጅ የሚቆጠሩ አባቶች ቀርተዋታል ከእነርሱ አንዱ አቡነ አብርሃም ናቸው"
  Tibebe Selasie, VA

  ReplyDelete
 73. ዲ. ዳንኤል
  ስለ አቡነ አብርሃም የፃፍከፍ እጅግ ትክክልና እውነት ነው

  ReplyDelete
 74. አሁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት ሊቀለበስ ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡

  ReplyDelete
 75. Long live to Our Pope Abune Abraham. i am very sad by what happened to our church. as usual we know who did good to God the the people, not the patriarch. sometimes i don't understand that when our dogma and qenona demolished by some '"sin fathers" you guys don't say much while you have the ability to use your writings.there is no clear way that Our Pope get transferred to Ethiopia,as you and we know.i believe there is a sabotage. Let Our God give you strength to do and say what is right to our church. i admire you a lot. see you in peace.

  ReplyDelete
 76. ብፁእ አቡነ አብርሃም በዚሁ በአሜሪካን ሀገር ቢቆዩልን ኑሮ ምን ነበረበት። እሳቸው ድካምን የማያውቁ ለሥራ የተፈጠሩ ብልህነት እና ትጉህነት ድፍረት እና ችሎታን አስተባብረው የያዙ አባት በመሆናቸው ከዚህ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያሉባትን ልዩ ልዩ ችግሮች ለመፍታት ገና ብዙ ተስፋ ጥላባቸው ነበር።
  ሆኖም ግን ጠላት እንጋስወራባቸው ሳይሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ አክብረው ወደ ሀገር ተመልሰው በተመደቡበት ሀገረ ስብከት ለመስራት መወሰናቸው በጣም አስደስቶኝል። ብፁእ አባታችን መልካም የሥራ ጊዜ እመኝልወታለሁ።

  ReplyDelete
 77. ዳኒ ቃለህይወት ያሰማልን!! ረጅም እድሜ እና ጽናት ለአባታችን ይስጥልን!!

  ReplyDelete
 78. እምላክ ለአባታችን እርጅም እድሜ ይስጥልን እሳችው የቅድስ ወንጌልን ት እዛዝ እጽንተዋል." መታዘዝ ክሁሉም ይበልጣል" እኛ ግን ስው ነንና የምንናገርውን እናውቅም ስለዘህ ለጸሀፍውም የብእሮች እጣጣልን ጥንቃቄ እንድታከልብት፣፡ ለእንባቢው ድግማ እንብቦ ይሕይወት ብርሃን የሚይግኝብት እንዲሆ ትግስትን ና ማስተዋልን ይስጠን።

  ReplyDelete
 79. አቡነ አብርሃምማ ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደውም ሥራ ይሠራሉ፡፡

  ReplyDelete
 80. I am so pleased cause we have such a wonderful father Thanks God

  ReplyDelete