Friday, November 11, 2011

የተሰደዱ ስሞች

click here for pdf
በአዲስ አበባ ሲኤም አካባቢ በሚገኝ አንድ የግል ትምህርት ቤት የዐጸደ ሕፃናት በር ላይ ቆሜያለሁ፡፡ እንዴው አንዳች ነገር ገፋፋኝና በየበሩ የተለጠፈውን የተማሪዎች ስም ዝርዝር መመልከት ጀመርኩ፡፡ ቢያንስ በአንድ ክፍል በር ላይ እስከ ሃያ የሚደርሱ ተማሪዎች ስሞች ተለጥፈዋል፡፡
የአንድ የአምስት ክፍል ተማሪዎችን ስም ዝርዝር ስመለከት ከኢትዮጵያውያን ስሞች መካከል የተሰደዱ መኖራቸውን አየሁ፡፡ እነ ትርንጎ፣ ብርቱካን፣ ትጓደድ፣ ድንበሯ፣ ቻላቸው፣ እያቸው፣ ስማቸው፣ ውዴ፣ ሙሉነሽ፣ አየነው፣ ገበያው፣ ሙሀባው፣ አብዱል መጂድ፣ አብዱል ቀኒ፣ ገብረ መስቀል፣ ገብረ እግዚአብሔር፣ በላቸው፣ ደርበው፣ ጥሩ ወርቅ፣ የትም ወርቅ፣ የሚሉ ጥንታውያኑ ስሞች በዝርዝሮቹ ውስጥ የሉም፡፡
እነ ማርታ፣ ማኅሌት፣ አርሴማ፣ ጀሚላ፣ ሣራ፣ ማክዳ፣ አቤሜሌክ፣ ባሮክ፣ ሰሎሞን፣ ሐዊ፣ ሀቢብ፣ አዜብ፣ ግሩም፣ አትናቴዎስ፣ ቢንያም፣ የሚሉ ስሞች የዘመኑ ሻምፒዮ ናዎች ሆነው ይታያሉ፡፡
ስም የአንድ ነገር መለያ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የሰዎች ስሞች የአንድን ሕዝብ እምነት፣ ባህል፣ ማንነት፣ ፍልስፍና፣ ርእይ፣ ታሪክ፣ ገጠመኝ፣ ይገልጣሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብረ መስቀል፣ ወልደ መስቀል፣ ወለተ መስቀል የሚሉ ስሞችን ስንሰማ የአውጭዎችንም ሆነ የወጣላቸውን ሰዎች እምነት ክርስቲያን መሆናቸውን የሚያሳዩ ሲሆን በሌላም በኩል ደግሞ አብዱል ቀኒ፣ አብዱል ሰመድ፣ መሐመድ፣ ከድጃ፣ የሚሉ ስሞችን ስንሰማ ደግሞ ባለቤቶቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሆናቸውን ይጠቁመናል፡፡
ስሞች ታሪካዊ ክስተቶችን እና የታሪክ ሂደቶችንም ያሳያሉ፡፡ ጉም፣ አስጎምጉም፣ ለትም፣ ተላተም፣ አይዙር፣ድድም፣ ውድድም፣ የሚሉትን ስሞች ስንሰማ የአኩስም ዘመን ትዝ እንደሚለን ሁሉ ስቡሐይ፣ ሐርበይ፣መይራረ፣ ጠጠውድም፣ ይምርሐነ፣ ላሊበላ፣ የሚሉትን ስንሰማ ደግሞ የዛግዌ ዘመን ይታወሰናል፡፡ በአብዮቱ ዘመን የተወለዱ ልጆች አብዮት፣ ገሥግሥ፣ መንግሥቱ፣ ድላቸው፣ ትቅደም፣ የሚሉ ስሞችን ወርሰው ቀርተዋል፡፡ እንዲያውም የአባትዬው ስም የሚገጥም ሆኖ ሲገኝ ገናናው መንግሥቱ፣ አንዳርገው መንግሥቱ፣ ምናለ መንግሥቱ፣ አሸናፊ መንግሥቱ፣ መሪነህ መንግሥቱ እየተባሉ ተጠርተው ነበር፡፡
ነጻ ፕሬስ እንደ ልብ የማይገኝበት እና በቃላዊ ፕሬስ ሃሳብን መግለጥ በተለመደበት የኢትዮጵያ ማኅበረ ሰብ ውስጥ ብሶት፣ ምሬት እና ጭቆና ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ በሚወጡ ስሞች ነው፡፡ ለልጆች፣ ለውሾች እና ለበሬዎች በሚወጡ ስሞች አማካኝነት የዘመኑን ብሶት እና ምሬት ወላጆች ይገልጣሉ፡፡ 
ባሕርዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሠራ የነበረ አንድ አባት በደርግ ዘመን ለጦርነት፣ ለድርቅ፣ ለርዳታ፣ ለፓርቲ፣ ወዘተ የሚከፈለው መዋጮ በዛበት፡፡ የሰውዬው ስም «በዛብህ» ይባል ነበር፡፡ እናም ልጆቹን ተቆራጩ፣ መዋጮው፣ ቅጣቱ ብሎ አወጣላቸው፡፡ የሚገርመው ነገር ሰውዬው ሦስቱንም ልጆች ከሚስቱ ሳይሆን ከሦስት የተለያዩ ሴቶች ነበር የወለደው፡፡ የልጆቹ እናቶች በየአሥራ አምስት ቀኑ የልጆቻቸውን ተቆራጭ ሊወስዱ ይመጡ ነበር፡፡ ተቆራጭ የሚወስዱት ሴቶች ይሰለፉና የልጆቻቸው ስም በጩኸት እየተጠራ ነበር የሚሰጣቸው፡፡
እናም በየአሥራ አምስት ቀኑ «ተቆራጩ በዛብህ፣ መዋጮው በዛብህ፣ ቅጣቱ በዛብህ» እየተባለ ሲጠራ ሰው ሁሉ በሳቅ ይፈነዳ ነበር፡፡ አንዳንድ ካድሬዎች ሰውዬውን ጠርተው የልጆቹን ስም እንዲቀይር አስፈራርተውት ነበር፡፡ እርሱ ግን ወይ ፍንክች ማለት ብቻ ሳይሆን ይህንኑ ነገር ለሰው ሁሉ ተናገረ፡፡ ሁኔታው ስላላማራቸው ሴቶቹ ስማቸው ሳይጠራ ቢሮ ገብተው እንዲወስዱ አደረጉ፡፡
ገበሬው
ሁለት ውሾች አሉኝ የማሳድጋቸው
አንዱ ሰምቶ ማለፍ ሌላው መቻል ናቸው
ብሎ ለውሾቹ በሰጠው ስም የኑሮ ፍልስፍናው ታግሎ ማሸነፍ ሳይሆን ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍ እና መከራውን ሁሉ ችሎ ማሳለፍ መሆኑን ገልጦበታል፡፡ 
አባቱ በሰው እጅ የተገደለ እንደሆነ በሰሜኑ ባህል ልጅ ተወልዶ የአባቱን ደም ይመልሳል ተብሎ ይታሰባልና እናቱ ደምመላሽ ብላ ትሰይመዋለች፡፡ ለልጇ አድጎ መሥራት ያለበትን የቤት ሥራ እየሰጠችው፡፡ የአባቱ ርስት እና ሀብት ተወርሶ እናቱን የሚቆጫት ከሆነ ደግሞ አንተ እደግና አስመልሰው ስትል አስመላሽ ትለዋለች፡፡ ልጂቱ ቆንጆ ሆና ያያት ሁሉ ይጠልፍብኛል ብላ ካሰበች ለልጅቱ ሳይሆን ለቤተሰቡ ማንቂያ እና ማስጠንቀቂያ የሚሆን ስም ትሰጣታለች፡፡ «ዘቢደር» ስትል፡፡ ይህቺን ልጅ ለመጠበቅ ዘመድ ወዳጅ ሁሉ ዘብ ይደር ማለቷም አይደል፡፡
ልጅ እምቢ ብሏቸው ከርመው እንዴው ባልታሰበ ጊዜ ያኙት እንደሆን ሰማኸኝ፣ አገኘሁ፣ ስጦታው፣ ተገኘ፣ እያሉ ሁኔታውን ያስታውሱበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወላጆች ስም የሚያወጡት ለራሳቸው ነው ወይንስ ለልጆቻቸው? ያሰኛል፡፡
እናት ጀግና የፈለገች እንደሆነ፣ ለልጇ ያላትን ምኞት የምትገልጠው በምትሰጠው ስም ነው፡፡ የበላይ ዘለቀ እናት ልጇን በላይ ዘለቀ ብላ ስትጠራው ስሙን ከአባቱ ጋር አስማምታ ነው፡፡ ልጇ የሁሉም የበላይ ሆኖ ለማየት ምኞት ስለነበራት፡፡ በላይም ይህንን አልዘነጋውም፡፡ እርሱ አብረውት ለዘመቱት አርበኞች የማዕረግ ስም ሲሰጥ ለራሱ አልሰየመም ነበር፡፡ በኋላም ነጻነት ተመልሶ ሠራዊቱን ንጉሡ የርሱን የመዓርግ ስም ሲጠይቁት «እኔንማ እናቴ አንድ ጊዜ በላይ ብላኛለች» ብሎ ነበር የመለሰው፡፡
የግጥም ችሎታቸውን በልጆቻቸው ላይ ያስመሰከሩ ወላጆችም
ፀሐይ ወጥታ እስክትገባ
አትጠገብ የኔ አበባ
የሚል ስም ለልጃቸው አውጥተዋል፡፡ ይህ ስም እንዴት መታወቂያ ላይ እንደሚጻፍ ማሰብ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ለልጆቻቸው ስም ማውጣትን አንደ ትልቅ ተልዕኮ ነው የሚያዩት፡፡ የቤተሰቡን ምኞት፣ ሃሳብ፣ እምነት እና አመለካከት፣ በልጁ እንዲቀረጽ የተፈለገውን ነገር ሁሉ ይይዛልና፡፡ ለዚህም ነው «አበሻ ሚስቱ ስታረግዝ እርሱ እንቅልፍ አይወስደውም» የሚባለው፡፡ ለምን? ቢሉ ስም ፍለጋ፡፡
በአሁኑ ዘመን በተለይም በከተማ አካባቢ ያሉ ብዙ ወላጆች የሚመርጧቸው ስሞች ቢቻል ከአምስት ፊደል ያልበለጡ፣ በብዙ ሰዎች ዘንድ ያልተለመዱ፣ ትርጉም ያላቸው፣ በእንግሊዝኛ ሲጻፉ «» እስከ «ኤፍ» ድረስ ባለው መሥመር የሚካተቱ ዓይነት ናቸው፡፡ አንድ ወላጅ ለልጃቸው ለምን «» እስከ «ኤፍ» የሚካተት ስም አውጣልኝ እንዳሉ ስጠይቃቸው «ልጄ መጨረሻ ሲሰለፍ ማየት አልፈልግም» ብለውኛል፡፡ አንዱ ጓደኛዬ ደግሞ እናቱ ለልጁ ያወጡላትን «ፈሰሰ ወርቅ» የሚለውን ስም ለምን እንደቀየረው ስጠይቀው «እንዴ ምን ብዬ ላቆላምጣት ነው?» ብሎ አስቆኛል፡፡ ይህም አለ ለካ፡፡
በአሁኑ ዘመን አጫጭር ስሞች ተወዳጅ ከመሆናቸው የተነሣ ረዣዥም ስሞችን ማሳጠርም እየተለመደ ነው፡፡ ቤተልሔምን «ቤቲ» መስተዋትን «መስቲ» አደራጀውን «አዱ» ወልደ መስቀልን «ወልዴ» አምኃ ሥላሴን «አምኃ» ደብረ ወርቅን «ደብሬ» ፈትለ ወርቅን «ፈትለ» ሣህለ ማርያምን «ሣህሉ» አብዱል ሁሴንን «አብዱ» ብለን ያሳጠርናቸው በዚህ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም፡፡ እነዚህም አጠሩ ተብለው ቲቲ፣ ኪኪ፣ ሊሊ፣ ሚሚ፣ ቺቺ፣ ጂጂ፣ ቲጂ፣ ሶል፣ ዳን፣ ጃክ፣ የሚሰኙ ስሞች እየተዘወተሩ ነው፡፡
ወላጆች ለየት ያለ ስም ለልጆቻቸው ያወጡ ቢመስላቸውም በብዙ ሀገሮች እጅግ የሚወደዱ እና ተደጋግመው የሚወጡ ስሞች ግን አሉ፡፡ ለምሳሌ በሊቢያ «መሐመድ» የሚለው ለወንዶች፣ «አያ» የሚለው ደግሞ ለሴቶች መጠርያነት በመዋል ቀዳሚ ስሞች ናቸው፡፡ ወደ ሞሮኮ ስንሻገር ደግሞ ለወንዶቹ እንደ ሊቢያ «መሐመድ» ቀዳሚውን ይይዝና ለሴቶቹ ግን «ፋጢማ» የሚለው ስም ለብዙዎች መጠርያነት በመዋል ተዘውታሪ ሆኗል፡፡
በእሥራኤል ለወንዶቹ «ኖዓም» የሚለው ስም በብዛት ጥቅም ላይ ሲውል፣ «ኖዓ» የሚለው ደግሞ የሴቶች መጠርያ በመሆን ቀዳሚውን ቦታ ይዟል፡፡ በደቡብ ኮርያ «ሚንጁን» የሚለውን ስም ብዙ ወንዶች ይጠሩበታል፤ ሴቶቹ ደግሞ «ሴዩአን» የተሰኘውን ስም በብዛት ተጠርተውበታል፡፡ በኦስትሪያ «ሉቃስ» በብዛት የወንዶቹ መጠርያ ሲሆን፣ «ሣራ» ደግሞ ለሴቶቹ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በጣልያን «ፍራንቼስኮ» በቤልጅየም «ኖኅ» በዴንማርክ «ዊልያም» በጀርመን «ሊኦን» በግሪክ «ጆርጂዮስ» በሩስያ «አሌክሳንደር» በስፔን «ዳንኤል» በስዊዘርላንድ «ናታን» ለወንዶቹ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ ስሞች ናቸው፡፡
ለሴቶቹ ደግሞ በጣልያን «ጊዩልያ» በግሪክ «ማሪያ» በሩሲያ «ኤለና» በስፔን «ሉቺያ» በስዊዘርላንድ «ኤማ» እና «ሌና» በዴንማርክ «ኢዳ» በቤልጂየም «ኤማ» እና «ማሪዬ» በጀርመን «ሚያ» እጅግ የብዙዎቹ መጠርያዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡
ወደ አሜሪካ ስንሻገር በሜክሲኮ «ሳንቲያጎ» በዩናይትድ ስቴትስ በነጮቹ ዘንድ «ያዕቆብ» በአፍሪካ አሜሪካውያን ዘንድ «ጃይደን» በአሜሪካ ሕንዶች ዘንድ ደግሞ «ዴቨን» ለወንዶች መጠርያነት በብዛት እያገለገሉ ናቸው፡፡ ለሴቶቹ ደግሞ በሜክሲኮ «ማርያ» እና «ፌርናንዳ» በነጭ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ዘንድ «ኢዛቤላ» በአፍሪካ አሜሪካውያን ዘንድ «ማዲሰን» በአሜሪካ ሕንዶች ዘንድ ደግሞ «አንያ» ተመራጭ ስሞች ናቸው፡፡ 
በኢትዮጵያውያን ዘንድስ ተመራጭ የሆኑት ስሞች እነማን ናቸው? ስሞቻችንስ ለምን እያጠሩ እና እየተለወጡ መጡ? በቀጣይ እንመለስባቸዋለን፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡
 © ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔትላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

34 comments:

 1. dani, it is always my surprise,too. now days, we might not to find anyone with names like abebe, kebede, chaltu, etc. how dare our parents mind set has been changed.

  eyasu

  ReplyDelete
  Replies
  1. hi dani eytah betam new yemigermew ... ketlbet ... enganm kemanbe wed hal anlem eshi EGZABHER YRDAH

   Delete
 2. ለዚህም ነው «አበሻ ሚስቱ ስታረግዝ እርሱ እንቅልፍ አይወስደውም» የሚባለው፡፡ ለምን? ቢሉ ስም ፍለጋ፡፡ hahahaha

  Thank you dani, sorry ዳንኤል yemin masater new!!

  Nice view as always, I love it and my children's name will be an Ethiopian (just promised to myself).

  ReplyDelete
 3. ዳኒ ተባረክ! አንተ በርክትልን
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 4. ሁለት ውሾች አሉኝ የማሳድጋቸው
  አንዱ ሰምቶ ማለፍ ሌላው መቻል ናቸው

  የከተሞቻችን ስሞችስ? the social, economic and political infulenes on naming...

  ሐብታሙ ከአዋሳ

  ReplyDelete
 5. What did you name your kids,Dani?

  ReplyDelete
  Replies
  1. that is ma favorite question?!!!

   Delete
  2. that is ma favorite question???? what is z name of ur kids Dani??

   Delete
 6. እነዚህ “የተሰደዱ ስሞች” ያልካቸው አንደተሰደዱ ይቅሩ፡ይሄንን የምለው የእራስን የሆነ ነገር ካለመቀበል ሰይሆን ስሞች ከወቅት ጋር የምሄዱ በመሆናቸው እና የግለሰቡን ማንነት የሚገልፁ ወይም የሚያሻሽሉ ባለመሆናቸው ነው፡፡እንደዛ ከሆነማ የእኔም ሆነ ያንተ ስም ሊለወጥ ነው ማለት ነው፡እስቲ ምን ለመቀየር ነው፡፡እኔ አሁን ትርንጎ ብባል ትርንጎ አልሆን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. koy ur name is Eleni right? so that means r u really queen Eleni?

   Delete
  2. wait a min,ur name is Eleni right?so that means r u real queen Eleni?? think twice dear Eleni.

   Delete
  3. wait a min ur name is Eleni right?so that means r u real queen Eleni?think twice.

   Delete
 7. ዲ/ን ዳንኤል እንደምን ግዜውም በጣም አስተማሪ ነው። ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  አኔም በዚህ ጉዳይ የጠበቀ እምነት አለኝ። እግዜር ይስጣት ባለቤቴም ደግፋኛለች። ስም ሳወጣ መስፈርቴ እንደቅደም ተከተላቸው 1 መንፈሳዊ 2 ኢትዮጵያዊ 3 ከአባት ስም ጋር ከተቻለ ቢገጥም ብዬ ነው። ሁለቱ ልጆቻችን ማኅሌታይ እና ዝማሬ ተብለዋል። መርቁልና።

  ያሬድ
  ያሬዶች ስም መኮረጅ አይቻልም (ሳ.በ.ሳ.-ሳቅ በሳቅ -lol (lough out loud) ከማለት።

  ReplyDelete
 8. Dear Daniel,

  Thanks for your deep insight. I knew that many of my friends even change their own name, because their children at school embarrassed by their father name. I am afraid that most Ethiopian original names will be find in museums.

  ReplyDelete
 9. ፈረንጆቹ "The grass on the other side of the fence is always green" የሚል አባባል አላቸው። እኛ ኢትዮጵያውያን ከመቼ ጀምሮ እንደሆን በትትክክል አላውቅም ይሄንን naming trend መጠቀም የጀመርነው። ትንሽ ሰንበትበት ብሏል። በአጠቃላይ ይዘቱ ግን የራስን ባህል ከማሳነስና የሌላውን ከፍ አድርጎ ከማየት የመነጨ ነው። በጣም የሚገርመው ግን ነጮቹ እኛ ያፈርንባቸውን ስሞች ጠብቀዋቸው አሁንም እንደቀድሟቸው ግዜ ይጠቀሙባቸዋል። ለምሳሌም ያክል፦ Johnson (ወልደዮሐንስ)፤ Jacobson(ወልደያዕቆብ)እንደኛ አባባል የሁዋላ ቀርነት ስሞች ሆነው አላገኟቸውም። ልጆቻችንን በጥሩ ባህልና በሃይማኖት ኮትኩተን ብናሳድጋቸው የበለጠ ይሆናል ብዬ አምናለሁ።
  ዲያቆን ዳንኤል በየግዜው የምታወጣቸውን ትምህርት አዘል ጽሑፎችህን ወድጃቸዋለሁ። ግፋበት እልሀለሁ።

  ReplyDelete
 10. ዋው! የያሬድ ልጆች ስም ተመችቶኛል፡፡ የዲ/ን ዳንኤል እይታዎችም በውስጤ ሳብሰለስለው የኖርኩትን ብሶት ስለተጋሩኝ ደስ ብሎኛል፡፡
  እኔም የልጀ ስም ኃይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ እንዲሆን ጽኑ ፍላጎት ስለነበረኝ ባኮስ ብየዋለሁ፡፡ ባኮስ ማለት በሐዋሪያት ሥራ ላይ የተገለጠው የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ስም ነው፡፡ በርግጥ እዚያ ላይ ባኮስ ተብሎ አልተፃፈም፡፡ ስሙን ያገኘሁት ከሐመር መጽሔትና ከዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የአፍሪካ ሐዋሪያ ከሚለው የስብከት ካሴት ነው፡፡ ስንክሳር ላይ አለ ሲባል ሰምቸ ልፈልግ ስሞክር የትኛው ወር ስንክሳር ላይ መሆኑን ባለማወቄ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ቋንቋውም ግዕዝ ይሁን የጥንት የሳባ ቋንቋ ማወቅ ቸግሮኛል፡፡ መረጃ ያለው ሰው ካለ እነሆ ትብብራችሁን እጠይቃለሁ! ሐበሻ ሚስቱ ስታረግዝ እንቅልፍ አይወስደውም የሚባለው በኔ ላይ ደርሶ ይሆን?

  ReplyDelete
 11. If we have noticed there are people who don't want to be called by their names(the names that their parents gave them)in schools or public places. I know friends get embarrassed when their names mentioned in public. Most of us prefer to have names which can be called in short. It seems there is no much attention that we give for the meaning. In the past it was the socio-political, cultural and other aspects in the country which countributed a lot for naming. Now,now, it is the degree of humilation!!! Natnael from Addis Ababa

  ReplyDelete
 12. wow Dani you always impress me by your papers /writings ..... i also thought about it and when i came to addis ababa for the first time i was surprised about those names that doesn't seems Ethiopian. good look brother !
  god bless Ethiopia and Ethiopians!!

  Fissiha

  ReplyDelete
 13. አቶ አለባችው ለልጆቻቸው ስም ሲያወጡ መማር አለባቸው፣ፍቅር አለባቸው፣ማስተዋል አለባቸው ብለዋል::አያስደስቱም እንዴ??

  ReplyDelete
 14. የታደለ ልጅ ታሪክ ባይሰራ ታሪክ ይሸከማል.... አንድም የራሱን እና የቤተሰቡን አለያም የሃገሩን:: ያልታደለ ልጅ የስም ደሃ ይሆናል (ማንነቱን የማይገልጽ የሰው ስም ይዞ ይዞራልና) ለዎትሮው እንኳ 'መልከ ጥፉን በ ስም ይደግፉ ይባል ነበር::' ዛሬ ዛሬ መልከ ጥፉ ሳይሆን ስመ ጥፉ በዛ:: በየትኛውም ህዝብ ታሪክ ስሞች አንዳች ትርጉም ይሰጣሉ:: እኛ ጋ እንዳለመታደል ሆኖ ስሞች ትርጉም አልባ እየሆኑ ነው:: እስኪ አሁን ማን ይሙት ለ አንድ ኢትዮጵያዊ እናት/አባት ቲቲ የሚል መጠሪያ ምን ትርጉም ይሰጣል? በርግጥ ፈረንጅኛ ስሞች በራሳቸው የራሳቸው የሆነ ትርጉም አላቸው ይሄውም ወላጆቻቸው በማንነታቸው የሚያፍሩ ፈረንጅ አምላኪነታቸውን አለያም ምንም ሳያውቁ እናውቃለን ባይነታቸውን (አስመሳይነት ባህሪ የተጠናዎታቸው መሆኑን)::

  ReplyDelete
 15. የእኔ ሁለት ጓደኞቸ የመጀመሪያ ዲግሪ ከያዙ ከአስር አመት በላይ ሆኖአቸዋል፡፡ የሁለተኛ ዲግሪም ከያዙ ወደ አምስት አመት አካባቢ ይሆናቸዋል፡፡ ነገር ግን እጅጉን የሚያስገርመው በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ቢያንስ ከ32ዓመት ዕድሜአቸው በ|ላ ስማቸውን ቀይረው “ከተሜ” በማድረግ በሚወዳደሩበት መስሪያቤት ሁሉ ጋዜጣ እና የድሮ ስማቸው ያለበትን ዶክመንት ይዘው ይዞራሉ፡፡ አሁን በዚህ ዕድሜ እና የትምህርት ደረጅ ስምን ማስቀየር ምን ማለት ነው? ደግሞስ ምን አለ የመጀመሪያ ስማቸው/ወላጆቻቸው ያወጡላቸው/ የሚያስቅ ወይንም ግራ የሚያጋባ ቢሆን፣ብትሰሙት እኮ በጣም ደስ የሚል ኢትዮጵያዊ ስም ነው/ነበር!/፡፡ ገጠር መወለድ ለምን ችግር አለበት ብለው እንዳሰቡ አይገባኝም፡፡ነገርግን እነርሱ መቀየር ሲያቅታቸው ነው መሰል ስማቸውን ቀየሩ፡፡

  አ.አ
  ከ አዲስ አበባ

  ReplyDelete
 16. መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንዲሉ፡፡ አንድ አባት ይበልጣል ይባላሉ እናም ስም ሲያወጡ አንደኛዋን ሀይወት ይበልጣል፣ ገንዘቤ ይበልጣል፣ ህሊና ይበልጣል፣ ማስተዋል ይበልጣል፣ ትግስት ይበልጣል እና በመጨረሻ ወንድ ይወልዱና ትዛዙ ይበልጣል አሉ ይባላል፡፡ አንዲህም አለ ለሁሉም ማስተዋሉን ይሥጠን፡፡
  ስማቸው ነኝ ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 17. ዲ/ን ዳንኤል ባለፈው የጠየቅሁትን ጥያቄ መመለስ በመጀመርህ ከልብ አመሰግናለሁ። እነ ጠጠውድም። እና መሰል ስሞች ሁሌም ጥያቄ ይሆኑብኝ ነበርና ዘመንን እንደሚያመለክቱ አሁን ገባኝ። ትርጉማቸው ግን ምን ይሆን? በቀጣይ ጽሁፍህ መልስ አገኝበታለሁ ብዬ አስባለሁ።

  ረድኤተ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 18. ኢትዮጵያ ማንደፍሮ
  አፍሪካ ማንደፍሮ
  አለምሰላም ማንደፍሮ
  ቤተልሔም ማንደፍሮ
  ነፃነት ማንደፍሮ

  የሚገርሙ ስሞች

  ReplyDelete
 19. my name is bewkete I dont like it why ?
  am not a man with knoledge it makes me ...? whate did you think ? I am looking to chang can you give me a name ?

  ReplyDelete
 20. እኔ ደግሞ የታዘብኩት ኦርቶዶክሶች ሆነው ለልጆቻቸው የጰንጤ ስም የሚያወጡ እየበዙ መምጣታቸውን ነው።

  በዕውቀቴ የምትባለው የዓለም ስምህ ከደበረህ በክርስትና ስምህ ተጠራ እርሱ ከደበረህ ግን እንጃ!

  ReplyDelete
 21. ፣ አብዱል መጂድ፣ አብዱል ቀኒ፣
  e dani?

  ReplyDelete
 22. Solomon -( surplus in ethiopian name economy),every person that i know with this name is wise.is that coincidence or .......

  ReplyDelete
 23. ወግ ነውና..አንድ ተቋም ውስጥ አብሮኝ የተማረ ልጅ ስሙ ይገርመኛል
  እግዚሩ እንቢአለ(ሙሉ ስም)መሆኑ ነው:የኔም ምኞቴ ብዙነው አያልቅም ተነግሮ ታድያ አይ አለመታደል የፊደል ጋጋታ እንጂ ስም አይመስልም?ያም ሆኖ መጠሪያው ሳይሆን ትርጉም ያለው
  ሰው መሆን ይጠይቃል መሰል:ይገርማል..ያም ሆኖ ብዙ ተማርንበት ጠቃሚ ወግ ነው:ዳ.ዳንኤል::ምኞቴ@ፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete
 24. it is good observation, keep it up!

  ReplyDelete
 25. ayenew ebalalehu endiyawm yene sem ye ethiopiawyan yedero sem teblo teteksoal tank you

  ReplyDelete
 26. ምናልባት አንድ ጊዜ ኃይሌ ገብረስላሴ ጋዜጠኞች ስሙን እያበላሹ ሲያስቸግሩት ጊዜ እንደ ቀልድ ለልጆቻችሁ ከሁለት ፊደል የረዘመ ስም አታውጡ ያለውን ሰምተን እንዳይሆን። በነገራችን ላይ እኔም ነፍሰ ጡር ነኝ፤ ነገር ግን የልጄን ስም ገና ድሮ ከማርገዜ በፊት ወስኜ ስለነበር እኔን ብዙም እንቅልፍ አልነሳኝም። ነገር ግን ያወጣሁት ስም የክርስቲያን ስም ስለሆነ ሌሎች ሰዎችን እንቅልፍ ነስቶኦቸዋል። የአጭርነትም ሆነ ሌሎች የዘመኑን መስፈርት ስለማያማላ ብዙዎች ስሙን ሊያስለውጡኝ ብዙ ጥረት አርገዋል፡ በማረግም ላይ ናቸው፡ ግን አልተሳከላቸውም። እናም በዚህ በምኖርበት በአሜሪካ ሁለት ስም (middle name) ማውጣት ስለሚቻል፡ ሁለተኛውን ስም እንዲያወጡ እድሉን ሰጥቻቸዋለሁ።

  ReplyDelete