Wednesday, November 9, 2011

ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ


አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ከመቶ ዓመታት በፊት የሞራል እና የሥነ ምግባር ልዕልናን ከእምነት ተቋሞቻቸው ነጥቀዋል፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ በእምነት ተቋማቱ ውስጥ እና በእምነት መሪዎቹ ዘንድ የሚፈጸሙት ጥፋቶች፣ ኃጢአቶች እና ወንጀሎች የእምነቱ ተከታዮች ከሚሠሯቸው ይልቅ እየባሱ መምጣታቸው ነው፡፡
ሴትዮዋ ጉድጓድ ውስጥ ትወድቅና ትጮኻለች፡፡ አንድ ሰው ይሰማትና ይመጣል፡፡ እጅሺን አምጭ ብሎ እጇን ጎትቶ ሊያወጣት ሲሞክር እጇን ይገነጥለዋል፡፡ ሴትዮዋ ጉድጓድ ከመግባቷ ይልቅ የእጇ መገንጠል ይብስባታል፡፡ እናም «አውጣኝ ብለው ገነጠለኝ» አለቺ ይባላል፡፡ አውጭው ከጉድጓዱ ባሰባት፡፡
የሃይማኖት ተቋማት እና የሃይማኖት መሪዎች የማኅበረሰቡን ሞራላዊ እና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን የመጠበቅ፣ የማስተማር እና ለእነርሱም አርአያ ሆኖ የመገኘት ግዴታዎች አሉባቸው፡፡ ነገር ግን «ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡታል፣ ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡታል» እንደተባለው ራሳቸው የእምነት ተቋማቱ እና መሪዎቹ የችግሩ ሰለባዎች ሆነው ለማኅበረሰቡ አርአያ መሆን ሲያቅታቸው፤ ሕዝቡ በእነርሱ ላይ ያለው አመኔታ፣ እነርሱም በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ይሸረሸራል፡፡
 አሁን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በእምነት ተቋማት እና በእምነት መሪዎች ዘንድ እጅግ አሳዛኝ ነገሮች እየተሰሙ ነው፡፡ የገንዘብ ዝርፊያ፣ የዘመድ አሠራር፣ ዘረኛነት፣ ጉቦ፣ የመብት ጥሰቶች፣ ማታለል፣ ለሥልጣን መታገል፣ በገንዘብ መንፈሳዊ ሥልጣንን እና ሹመትን መግዛት፣ ኢሞራላዊ የሆኑ ድርጊቶች የዕለት ተዕለት ወሬዎች እየሆኑ ነው፡፡
እነዚህ ነገሮች አደጋቸው ለእምነት ተቋማቱ ብቻ አይደለም ሀገራዊ ጉዳትም አላቸው፡፡ 90 በመቶ በላይ ሃይማኖተኛ ነኝ ብሎ የሚያምን ሕዝብ ባለባት ኢትዮጵያ ውስጥ የእምነት ተቋማት ሚና ቀላል አይደለም፡፡ የማኅበረሰቡ የሥነ ምግባር እና የሞራል እሴቶች ምንጭ እና ጠባቂ፣ አስተማሪ እና አወራራሽ የእምነት ተቋማት ናቸው፡፡ የሀገሪቱን ቅርሶች አና ባህሎች የሚጠብቁ እነርሱ ናቸው፡፡ ለማኅበረሰቡ የበጎ ነገር አርአያ በመሆን የሞራል ልዕልና የሚያጎናጽፉ ናቸው፡፡
ሕዝቡ ስለ እምነት ተቋማቱ እና መሪዎቹ ክፉ ነገር እየሰማ በሄደ ቁጥር ግን እነዚህ ነገሮች ይቀራሉ፡፡ ከእምነት ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን ከአስተምህሯቸው፣ ከሞራል እና ሥነ ምግባር እሴቶቻቸውም ይሸሻል፡፡ ተቋማቱም ማኅበረሰቡን የመቅረጽ ሚናቸው ይቀንሳል፡፡
ይህ ሁኔታ የአይከን ለውጥ ያስከትላል፡፡ ለጨዋነት፣ ለትኅትና፣ ለንጽሕና፣ ለታማኝነት፣ ለድንግልና፣ ለትዕግሥት፣ ለይቅር ባይነት፣ አርአያ ያደርጋቸው የነበሩት የእምነት መሪዎቹ ከዚህ በተቃራኒ !ያገኛቸው ሌሎች አይከኖችን ያመጣል፡፡ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የእምነት አይከኖች ሲጠፉ ሚዲያ የፈጠራቸው አይከኖች ናቸው የተተኩት፡፡ አርቲስቶች፣ ዘፋኞች፣ የፊልም ተዋንያን፣ የፋሽን ሰዎች፣ ኳስ ተጫዋቾች፣ ወዘተ ቦታውን ተረክበዋል፡፡ እንግሊዛውያን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት በየመንደሩ የመንደሩ ጠባቂ ቅዱስ (patron Saint) የሚሉት ነገር ነበራቸው፡፡ ዛሬ የመንደሩ ጠባቂ ቅዱስ በመንደሩ ታዋቂ የእግር ኳስ ቡድን ተተክቷል፡፡
የኛም ሀገር ዕጣ ፈንታ እንደዚህ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ሰዎች ወደ እምነት ተቋማት ሲሄዱ ከፍ ያሉ ሞራላዊ ነገሮችን ያስባሉ፡፡ እነርሱ በዚህ ዓለም ሊያደርጓቸው ያልቻሉትን ሊያደርጉ የቻሉ ሰዎችን ይፈልጋሉ፡፡ አርአያ ይሻሉ፡፡ የጽናት፣ የትዕግሥት፣ የብርታት፣ የአልሸነፍ ባይነት፣ ምሳሌ ይሻሉ፡፡ እነርሱ እንደ ሰብአ ሰገል ሲመጡ እንደ አጥቢያ ኮከብ መንገድ የሚመራቸው ይመኛሉ፡፡
ይህንን ነገር ከማግኘት ይልቅ እነርሱ ሊያሸንፉት በሚፈልጉት ነገር፣ እነርሱ በተጸየፉት ነገር፣ እነርሱ ሊጋደሉበት በሚሰለፉበት ነገር አርአያ ያደረጓቸው አካላት ተሸንፈው ሲያገኙ ሞራላቸው ይወድቃል፡፡ ተስፋም ይቆርጣሉ፡፡ አንዳንዶቹም እያደረጉት ያለው ነገር ትክክል ነው ብለው እንዲያስቡ ይሆናል፡፡
እኔ በእምነት ስም ስለሚፈጸሙ ጥፋቶች እና ወንጀሎች ማኅበረሰቡ መወያየት ያለበት አሁን ነው እላለሁ፡፡ አሁን ውይይቱ ከተጀመረ ተቋማቱን ከግለሰቦች፣ እምነቱንም ከእምነቱ መሪዎች ነጥሎ ለማየት ዕድል ይሰጣል፡፡ በዝምታ ከታለፈ ግን «ዕባብ ግደል ከነ በትሩ ገደል» የሚለው ማኅበረሰባችን ሰዎቹን ከነተ ቋማቸው ርግፍ አድርጎ ወደ መተው መዞሩ አይቀሬ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ የሚፈጸሙትን ስሕተቶች መናገር ሃይማኖቱን እንደ መድፈር፣ ለጠላት አሳልፎ እንደ መስጠት፣ ገመና እንደ ማውጣት እየተቆጠረ በመምጣቱ አልባሌ ሰዎች እና አልባሌ አሠራሮች የእምነት ተቋማቱን ምሽግ አድርገው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ዕድል እየሰጣቸው ይገኛል፡፡
ዘመኑ የሚዲያ በተለይም የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን ነው፡፡ በዓለም ጫፍ የተተነፈሰች ነገር በሰከንድ ወደ ሌላው የዓለም ጫፍ ትደርሳለች፡፡ እንደ ትናንቱ ነገሮችን ደብቆ ይዞ መኖር አይቻልም፡፡ ሰዎች ይሰሙታል፣ ያታል፣ ይወያዩበታልም፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ ችግሩ እየተባባሰ እና እየጠነከረ ሲመጣ የፍትሕ አካላትን በር ማንኳኳቱም የማይቀር ነገር ነው፡፡
አንድ በር ሲከፈት በመጀመርያ የሚወጣበት እንጂ በመጨረሻ የሚወጣበት አይታወቅም ይባላል፡፡ ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት መድረስ ከጀመሩ ሌሎች የችግሮቹ ተጋላጮችም መንገዱን ይቀጥሉበታል፡፡ ይኼ ደግሞ የእምነት ተቋማቱን ሥነ ምገባራዊ እና ሞራላዊ ልዕልና ያሳጣል፡፡
በቅርቡ አንድ መነኩሴ በአንድ 15 ዓመት አዳጊ ልጅ ላይ በፈጸሙት የግብረ ሰዶም ተግባር ልደታ የሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14 ዓመት ጽኑ እሥራት ፈርዶባቸዋል፡፡ ልጁ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ሲመጣ መሆኑ ደግሞ ሁኔታውን እጅግ ከባድ ያደርገዋል፡፡
ይህንን የመሰለው ኢሞራላዊ ድርጊት ከሕዝቡ አልፎ ወደ እምነት መሪዎች ዘንድ መዛመቱ፣ የእምነቱ መሪዎችም ሥልጣናቸውን፣ አባትነታቸውን እና ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው እየፈጸሙት መሆኑ ለማኅ በረሰቡ እና ለተቋማቱ የመንቂያ ደውል ነው፡፡ «ጨው ለራስህ ብትል ጣፍጥ፣ ያበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው አውጥተው ይጥሉሃል» እንደ ተባለው የእምነት ተቋማቱ ያላቸውን ቦታ ከማጣታቸው በፊት ለዓላማቸው ሲሉ በፍጥነት ችግሮችን መፍታት ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡
በጳጳሳት፣ በመነኮሳት፣ በአጥማቂዎች፣ በሰባክያን፣ በፓስተሮች፣ በዘማርያን፣ ዘንድ እየተሰሙ ያሉ የመብት ጥሰቶች፣ ጥፋቶች እና ወንጀሎች አሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ነገ አደባባይ ወጥተው የማኅበረሰቡን ቅስም መስበራቸው አይቀርም፡፡ የእምነት ተቋማቱም የመረጡት ዝምታ እና መሸፋፈን ነው፡፡ አንድ ቦታ የተወነጀለ እና የተቀጣ ሰው ወደ ሌላ ይዛወራል፡፡ በሌላ ቦታ ጥፋት የተገኘበት ሰው ወደ ሌላ ይሾማል፡፡ ችግሩን ከምንጩ የመፍታት ሥራ አልተጀመረም፡፡
በሌላም በኩል የእምነት ተቋማቱ በልዩ ልዩ የአገልግሎት ቦታ ያሠማሯቸውን አገልጋዮች ብዛት፣ ማንነት እና ተግባር አያውቁም፡፡ በስማቸው የሚሠራውን ነገር የሚከታተሉበት መንገድ አልዘረጉም፡፡ ማነው ባሕታዊ? ማነው መነኩሴ? ማነው ካህን? ማነው ዲያቆን? ማነው ሰባኪ? ማነው ዘማሪ? ማነው ፓስተር? ማነው አስመላኪ? ማነው መጋቢ? ማነው አጥማቂ? በግልጽ የሚያውቅ የለም፡፡ እነዚህ አካላት ለሚያደርሱትስ ጥፋት ተጠያቂው ማነው? እጅግ አጠያያቂ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ አባቶች ተሰባሰቡ ሲባል «ጸለዩ፣ ጾሙ፣ ተአምር አደረጉ፣ ሃይማኖት አሰፉ፣ ሥርዓት ዐጸኑ» የሚለውን አይደለም ሕዝቡ እየሰማ ያለው፡፡ ተደበደቡ፣ ቤታቸው ተሰበረ፣ ማስፈራሪያ ደረሳቸው፣ ሰልፍ ተደረገ፣ አልስማማ አሉ የሚለውን ነው፡፡ እገሌ የተባት አባት ይነሡልን፣ እገሌ የተባሉት አባት አይምጡብን የሚል ምእመን በዝቷል፡፡ ወደ የአጥቢያው ሲሄድም ሙዳየ ምጽዋት ተዘረፈ፣ ሕንፃው በዘመድ ተሰጠ፣ እገሌ በጉቦ ተሾመ፣ እነ እገሌ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ መሬት ገዙ፣ ቤት ሠሩ፤ ንዋያተ ቅድሳት ጠፉ፣ ተዘረፉ የሚለውን ነው እየሰማ ያለው፡፡
አሁን አሁን በማኅበረሰባችን ዘንድ የምንሰማቸው እና የምናያቸው የሥነ ምግባር ጥፋቶች እና ኢሞራላዊ ድርጊቶች አንዱ መነሻ የሥነ ምግባር እና የሞራል አርአያ መጥፋት ሳይሆን አይቀርም፡፡ የእምነት ተቋማቱ ዋነኛ ሥራቸው ትተው ንግድ ወደ ማስፋፋት፣ ገንዘብ ወደ መሰብሰብ፣ ሥልጣን ወደ መቀራመት እና ቤት ንብረት ወደ ማፍራት ስለገቡ የሕዝቡን ሞራላዊ እና ሥነ ምገባራዊ እሴቶች የሚያስጠብቅ፣ አርአያ የሚሆን እና የሚያሰርጽ እየጠፋ ይመስለኛል፡፡
በማኅበረሰባችን ዘንድ ግብረ ሰዶማዊነት እየተስፋፋ ነው፡፡ ሕፃናትን መድፈር እየተለመደ ነው፤ ፍች የሰዓታት ዜና እየሆነ ነው፣ በወጣቶች ዘንድ ድንግልናን መጠበቅ ነውር እየሆነ ነው፤ ከዳቦ ቤቶች ይልቅ ጫት ቤቶች እየበዙ ነው፤ ጉቦ ማሳፈሩ ቀርቶ እየተወደሰ ነው፤ አሲድ በሰው ላይ መድፋት፣ ዓይን ጎልጉሎ ማውጣት፣ በቢላዋ የትዳር ጓደኛን ማረድ፣ ልጅን ቆራርጦ መግደል እውነት የሃይማኖተኛ ሕዝብ ጠባያት ናቸውን?
የሀገሪቱ ሕጎችም የሃይማኖት ተቋማት እንደ ሕጋቸው ሳይሆን እንደፈለጉ እንዲሆኑ የሚያግዙ ናቸው፡፡ ገንዘባቸው ቁጥጥር አይደረግበትም፡፡ ግብር አለመክፈል እና ቁጥጥር አለማድረግ የተለያዩ ናቸው፡፡ ገንዘብ በተዝረከረከበት ቦታ ሁሉ ወንጀል በልጽጎ መገኘቱ ደግሞ የማይቀር ነው፡፡ አወቃቀራቸው እና አሠራራ ቸውን ዘመናዊ እንዲያደርጉ፣ የቁጥጥር ሥርዓት እንዲዘረጉ፣ አገልጋዮቻቸውን እና አባሎቻቸውን መዝግ በው እንዲያውቁ የሚያስገድዳቸው ነገር የለም፡፡
በተቋማቱ ውስጥ እና በአባሎቻቸው ወንጀሎች እንዳይሠሩ፣ ቢሠሩም እንዲጋለጡ የሚያደርጉ አሠራሮችን እንዲዘረጉ ግዴታ ሊጣልባቸው ይገባል፡፡ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ነክ ከሆኑ ጉዳዮች በቀር በሌሎቹ ላይ ግልጽነት እንዲኖር መደረግ አለበት፡፡ ከሲመት በኋላ ነገር እንዳይመጣ የሚሾሙ ሰዎች አስቀድሞ ለሕዝቡ እጩነታቸው የሚገለጥበትን፣ አስተያየት የሚሰበሰብበትን መንገድ መፍጠር ያሻል፡፡ ምእመናኑ የመ ብት ጥሰቶችን፣ ኢሞራላዊ ተግባራትን እና ወንጀሎችን የሚጠቁሙበት ግልጽ አሠራርም መስፈን አለበት፡፡
ያለበለዚያ ግን «በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርዒነ» እንደተባለ፣ ዛሬ በጭምጭምታ በጆሮ የምንሰማቸውን ነገሮች ነገ በአደባባይ ማየታችን የማይቀር ነው፡፡ ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅም በርጥቡ ማለት አሁን ነው፡፡

90 comments:

 1. እግዚአብሐር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን! እነ አባ ሠረቀም ሌላ ቦታ ተሾሙ አሉ ቂቂቂቂ

  ReplyDelete
 2. D.Daniel qale hiywot Yasema .
  Egiziabehere bete kirsitiyanen Yetbiqilini Amen!!!

  Yidnekahew

  ReplyDelete
 3. d/n Daniel thank you for your perspective. as to me things are going wrong and we have to act now ,other wise ......we will end up with NOTHING !
  god bless Ethiopia and Ethiopian!

  ReplyDelete
 4. Dear Daniel,

  What a wonderful critics is this? Your intervention is too analytical. The message behind is the let's listen our self. In Amharic language there is one saying " Lib Yalew Lib Yibel." Furthermore, our society require transparent transparency.

  ReplyDelete
 5. This is wonderful saying! But, please, concentrate on your own church! You have many things to say here and also you have the courage to make critics as much as you wish.The extent of context on spiritual issues between yours' and others' are quite different. They may have different view on virginity, for example. The highness of the church is not reachable and so is her education. Please, please, please, don't mix things which are at far distances!

  ReplyDelete
 6. "እኔ በእምነት ስም ስለሚፈጸሙ ጥፋቶች እና ወንጀሎች ማኅበረሰቡ መወያየት ያለበት አሁን ነው እላለሁ፡፡ አሁን ውይይቱ ከተጀመረ ተቋማቱን ከግለሰቦች፣ እምነቱንም ከእምነቱ መሪዎች ነጥሎ ለማየት ዕድል ይሰጣል፡፡ በዝምታ ከታለፈ ግን «ዕባብ ግደል ከነ በትሩ ገደል» የሚለው ማኅበረሰባችን ሰዎቹን ከነተ ቋማቸው ርግፍ አድርጎ ወደ መተው መዞሩ አይቀሬ ነው፡፡
  አንዳንድ ጊዜ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ የሚፈጸሙትን ስሕተቶች መናገር ሃይማኖቱን እንደ መድፈር፣ ለጠላት አሳልፎ እንደ መስጠት፣ ገመና እንደ ማውጣት እየተቆጠረ በመምጣቱ አልባሌ ሰዎች እና አልባሌ አሠራሮች የእምነት ተቋማቱን ምሽግ አድርገው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ዕድል እየሰጣቸው ይገኛል፡፡"

  ዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
  ይህን በጎ ምክር ሰምተው፣ ሃሳቡን በመልካም ተረድተው፣ የቤተክርስቲያን መከራ ገብቷቸው ጸንተው የሚያጸኑ አባቶችን እግዚአበወሔር ያድለን፡፡ እንግዲህ ምን ይባላል? መፍትሔ ይሰጣሉ ብለን ተስፋ የጣልንባችው አባቶች የችግሩ አካል ሆነው አረፉት፡፡
  “ከፈረሱ ጋሪው” እነዲሉ አሁን የቀረው የመጨረሻው አማራጭ ምእመኑ ተወያይቶ የአባቶች ልብና አእምሮ የመመለሱ ሥራ ነው፡፡ እግኢኦ!! ኧረ እግዚአብሔር ይርዳን!

  ReplyDelete
 7. ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥህ: የአገልግሎት ዘመንህ ያብዛልህ:: በጣም ወቅታዊ ጽሑፍ ነው:: ከዚህ በታች የተገለጸው አሁን የኦርቶዶክስ ቤተ/ያን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያሳያል::

  በጳጳሳት፣ በመነኮሳት፣ በአጥማቂዎች፣ በሰባክያን፣ በፓስተሮች፣ በዘማርያን፣ ዘንድ እየተሰሙ ያሉ የመብት ጥሰቶች፣ ጥፋቶች እና ወንጀሎች አሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ነገ አደባባይ ወጥተው የማኅበረሰቡን ቅስም መስበራቸው አይቀርም፡፡ የእምነት ተቋማቱም የመረጡት ዝምታ እና መሸፋፈን ነው፡፡ አንድ ቦታ የተወነጀለ እና የተቀጣ ሰው ወደ ሌላ ይዛወራል፡፡ በሌላ ቦታ ጥፋት የተገኘበት ሰው ወደ ሌላ ይሾማል፡፡ ችግሩን ከምንጩ የመፍታት ሥራ አልተጀመረም፡፡

  ReplyDelete
 8. እግዜር ይሁነን! አንተ በርክተልን
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 9. የእምነት ተቋማቱ ያላቸውን ቦታ ከማጣታቸው በፊት ለዓላማቸው ሲሉ በፍጥነት ችግሮችን መፍታት ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡

  ReplyDelete
 10. yemifetsemu drgitoch,ahun ahun kehilinaye belay eyehonebign new.

  ReplyDelete
 11. ዘሶልያና ከአዲስ አበባNovember 9, 2011 at 2:49 PM

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል
  ይህን ጽሑፍ ጥልቅ በሆነ የሐዘን ስሜት ውስጥ ሆኜ አንብቤዋለሁ፡፡ በተለይ መንፈሳዊ ሕይወት ጸንቶ የሚያጸና ሰው ይፈልጋልና ጉዳዩ እንዳልከው እጅግ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ አሁን ያለው ትውልድ አንዳንድ ጊዜ የተደረጉ ተዓምራት ወመንክራት፤ የተፈጸሙ ገድላት ፈጠራ የሚመስለው በዘመኑ ያን የመሠለ ነገር ሲፈጸም ማየት ስላልቻለ ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው “ምነው በፊት ይኽ ይደረግ ነበር ትላላችሁ አሁን ምነው ይኽ ሲደረግ አይታይ?” እያሉ አንዳንድ ወገኖቻችን በጥያቄ ልባችንን ውልቅ የሚያደርጉት፡፡ ይኽን ስል “ሳያዩ የሚያምኑብኝ ብፁአን ናቸው” የሚለውን ወይም እምነት የማያዩትን ነገር እንዳዩ አድርጎ ማመን ማለት መሆኑን ዘንግቼው አይደለም፡፡ ሰው ለማመን የግድ ማየት አለበት ለማለትም አይደለም፡፡ ግን እየሆነ ያለው ይኽ ነው፡፡ በእርግጥ ሁሉም ተሰተካክሎ በድሏል ማለት አልችልም ነገር ግን አርአያ የሚሆኑት ሰዎች አንድም ስለ ትህትና ራሳቸውን ዝቅ ማድረጋቸው እንደዚሁም የኔ ብጤ ሰነፎች ከባለ መልካም ምግባሮች/ስሞች ይልቅ ባለ እኩይ ምግባሮችን ማየት ስለሚቀናን ነው፡፡
  ዞሮ ዞሮ ይኽ ጉዳይ ከእጃችን አምልጦ ከቁጥጥር ውጪ ሳይወጣ መፍትሔ ሊደረግለት ይገባል፡፡
  ሁላችንንም የሰው መሰናክል ከመሆን ይጠብቀን፡፡ አሜን፡፡

  ዘሶልያና
  ከቀጨኔ አዲስ አበባ

  ReplyDelete
 12. አስፈሪ ዘመን በሰንበት ትምህርት ቤታችን አማካኝነት ሕዝቡን እንዴት ማሳወቅ እንዳለብን እንዳስብበት አድርጎኛል ለማንኛውም መጻለይ ነው አለበለዚያ አያ ጅቦ ይቆረጥመናል

  ReplyDelete
 13. ኦርቶዶክስ ነኝ ከ ጎላNovember 9, 2011 at 3:36 PM

  ዳኒ አሪፍ ሓሳብ ነው ያነሳህው በተለይ በተለይ አሁን ባለው የቤተክርስትያናችን ጉዳይ ላይ በግልጽ መወያየት አለብን የቤተክርስቲየናችን ከፍተኛው የስልጣን ባለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሮችን የሚቀርፍ አልሆነም (መቅረፍ አላስቻላቸውም) ይህም ትልቅ ፍርሃት በውስጣቸው ወይንም በሌላ አካል ይፈጠርብናል ብለው አስበዋል ስለዚህ እነሱ ዝም ካሉ እኛ በተቻለን መጠን ስለችግሩ መፍትሄ መወያየት መነጋገር የመፍትሄ ሃሳቦችን ማቅረብና ማሳወቅ እና ማስፈጸም ይጠበቅብናል አለበለዚያ አሁን ያለው አካሄድ ትልቅ ችግር የሚፈጥር እና ቤተክርስቲያንን ትልቅ ፈተና ውስጥ የሚከት ስልሆነ እኛም እንደ ልጅነታችን ሓላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ እንዳልከው….. በዚህ ዙሪያም አንዳንድ ሓሳቦችን ብታጋራን በርታ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያናችንን ይታደጋት አባቶቻችንም ስለእውነት ብለው እውነተኛዋን ቤ/ክ ለመጠበቅ ስለ እርሰዋም ዋጋ የሚያስከፍል ስራ እንዲሰሩ ኃይልና ብርታቱን ይስጣቸው አሜን፡፡

  ReplyDelete
 14. አዎ! ልክ ነው ፡፡ ነገር ግን ችግሮችን ተመልክቶ ለመፍትሄ የተዘጋጀ ልብ ያላቸውን ...
  እግዚያብሄር ያድለን::

  ReplyDelete
 15. ዳኒ ጥሩ እይታ ነው፡፡
  ከያንዳንዱ ምን ይጠበቃል የሚለው ቢካተትበት

  ReplyDelete
 16. ለጉድ የታደለ ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ ይህን ማስተካከል የሚችል አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እባካችሁ ወገኖቼ ሁላችንም ተግተን እንጸልይ፡፡ ከመካከላችን አንድ ሁለት የዋህ ልብ ያላቸው ደጎችና ቅኖች መገኘተታቸው አይቀርም ይሆናል፡፡ ጌታ የእነሱን ጸሎት ይሰማና መላ ይሰጠናል፡፡

  ReplyDelete
 17. ወርቅ ከዛገ ብረት ምን ይሁን?

  ReplyDelete
 18. Please Lord send to us a respected and spiritual religious leaders. Ethiopia is always stretch her hand to Lord.

  ReplyDelete
 19. ዳኒ የሀይማኖት መሪዎቻችን ምን እናድርጋቸው ? ግራ ገባን እኮ፡፡ በራሳችን ሀጢያት እና በነሱ ገመና መሀል ሆነን እንደ ድፎ ዳቦ ተንገበገብን፡፡ የት እንሂድ? ምን እናድርግ ?................

  ReplyDelete
 20. Lib yalew Lib yibel!

  ReplyDelete
 21. ተንስእ ሊቅ ወአድኅነነ ከመ ኢንሙት

  ReplyDelete
 22. ተንስእ ሊቅ ወአድኅነነ ከመ ኢንሙት

  ReplyDelete
 23. God bless you dani he is right weyo lene

  ReplyDelete
 24. ዲያቆን ዳንኤል ያነሳኸው ርእስ እጅግ ወቅታዊና አንገብጋቢ ነገር ነው፡፡
  እዚህ ሀገራችን ውስጥ ብዙውን ጊዜ ዋናውን በሽታውንና የበሽታውን ዋና መንስኤ ከመጠየቅ ከመመርመርና ከመረዳት ይልቅ በይበልጥ ስለበሽታው የተለያዩ ምልክቶች ማውራትና መናዘዝ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ይህ ደግሞ እየሆነ ያለው በአብዛኛው ከእውቀት ማነስና በተወሰነ መንገድ ደግሞ እውነትን ለመናገር ከመፍራትና ከአድረባይነት በመነጨ ነው፡፡ከቻልን መጀመሪያ እራሱን በሽታውን እንወቅና በመቀጠል ደግሞ የበሽታውን ዋና መንስኤ በመጠየቅና በመመርመር ለመረዳት እንሞክር፡፡ያለበለዚያ ግን ከንቱ ድካም ነው የሚሆነው፡፡ሀገሪቱ የዛሬ ሃያ ዓመት ገደማ የመንግስትና የስርዓት ለውጥ በሃይል በተመሰረተ አካሄድ ስታካሂድ ብዙ ነገሮች ናቸው የተቀየሩት፡፡ስልጣን ላይ የወጣው አገዛዝና ጥንቱንም እራሱን የትግራይ ነፃ አውጪ ብሎ የጠራው ሃይል የተለመደውን የደርግ አለማዊ የመንግስት ስርዓት በሃይል አስወግዶ ስልጣን ላይ ሲወጣ በሀገሪቱ ቁኝጮና ግንባር ቀደም የሆነውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት የፓትርያርክና ሌላም ዋና የበላይ አመራር ጭምር ቀይሮ ነበር፡፡እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የመጀመሪያው የመንግስት ሰለባ ነበር፡፡እንደሚታወቀው ስልጣን ላይ ያለ ፓትርያርክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ በምንም መንገድ በመፈንቅለ መንግስት አይነት አካሄድ ስልጣን ላይ ሊወጣ አይገባም ነበር፡፡ዞሮ ዞሮ ይህ ህገወጥ ተግባር እንዲፈፀም ሆነ፡፡ይህም የሆነው ደግሞ ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የራሱን ስግብግብ ጠባብና መሰሪ የሆነ የአገዛዝ ስርዓት በቀጣይነት በአስተማማኝ ለማዝለቅ ህዝቡን በሃይማኖት ሽፋን ተብትቦ ለመያዝ ያቀደው ድብቅና መሰሪ አላማ አካል ነው፡፡በታሪክ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያውያን ፈሪሃ እግዚአብሄርና ፈሪሃ መንግስት ያለን ጨዋ ህዝቦች ነበርን አሁንም እንደ ድሮውም ባይሆን ይህ ፈፅሞ አልቀረም፡፡ስለዚህም የሃይማኖት አባቶቻችንና ተቋማት የሚነግሩንን ነገር ሁሉ በቀናነትና በትህትና እናከብራለን እንቀበላለን፡፡ይህንን የሚያውቀው ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ይህንን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ እጁን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመክተት የራሱ የፖለቲካ መሳሪያ አድረጎ ለመጠቀም ጥንቱንም አቅዶ በመነሳት በህገ-ወጥ መልክ ስልጣን ላይ ወዲያውኑ እንደወጣ የፓትርያርክ ለውጥ አደረገ፡፡እንግዲህ የዚህች ሀገር የሃይማኖት ተቋማት ችግር በዋናነት ከዚህ ይጀምራል፡፡የሃይማት ተቋማት ከፖለቲካ ስራ የፀዱ ለመሆን አልቻሉም፡፡የራሴን አገዛዝና ስርዓት ያቀነቅኑልኛል የሚላቸውን የሃይማት ሰዎች በሰፊውና በጥልቀት በማሰማራት ህዝቡን በሃይማኖት ሽፋን ለስርዓቱ ሰጥ ለጥ ብለው እንዲገዙ በተዘዋዋሪ የስነ ልቦና ተፅእኖ እያሳደሩ ነው፡፡ስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ በሚያደርስበት ከፍተኛ ጫና የተማረረው ዜጋና አማኝ ብሶቱንና በደሉን በሆዱ ይዞ ሁሉን ለፈጣሪ መማፀን የለመደው ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ሲገባ አንዳንድ ጊዜ የሚያፅናና ስብከትን የሚሰማውን ያህል በዚያውም ልክ ነገሮችን ሁሉ ያለ ምሬትና አቤቱታ አሜን ብሎ እንዲቀበል በሃይማኖት ሽፋን ተፅእኖ እየደረሰበት ነው፡፡በፓትርያርክነትና በሌላም ስልጣነ እግዚአብሄር የተሰየሙትም የሃይማኖት አባቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሃይማኖትና በመቻቻል ሽፋን ምእመናን ሁሉንም ነገር ያለ ምሬትና ተቃውሞ አሜን ብለው እንዲቀበሉ ተዘዋዋሪ የስነ-ልቦና ጫናና ተፅእኖ የሚያሳድሩትን ያህል ስልጣን ላይ ያሉትን የአገዛዙን ቁንጮዎች ግን ከእኩይና ጨካኝ ተግባራቸው እንዲታቀቡና ህዝባቸውንም በፍቅርና በአክብሮት በመልካም ሁኔታ እንዲያስተዳድሩ ደፍረው ሃይ የማለት የሞራል ብቃት የላቸውም፡፡ስለዚህም የሃይማኖት ተቋማት ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ዋና መሳሪያ ሆነዋል፡፡ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ደግሞ ያዛሬ 20 ዓመት በሃይል ስልጣን ሲረከብ ያለምንም ጥናትና ምርመራ በቀጥታ መከተል የጀመረው የምእራቡን አለም ነጭ ካፒታሊዝም ስርዓት ነው፡፡ስለዚህም ሀገሪቱና ህዝቦቿ ከዚህ በፊት አይተውት ወደማያውቁት የህይወት ዘይቤና መስመር ውስጥ ነው በቀጥታ የተዘፈቁት፡፡በዚህ የነጭ ግሎባል ካፒታሊዝም ስርዓት አማካኝነት ደግሞ የኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴቶች የሆኑ ታሪካዊ፣ሃማኖታዊ፣ማህበራዊ፣ባህላዊና፣ስነ-ልቦናዊና ሞራላዊ እሴቶቻችን ሁሉ በሂደት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ የክብር ቦታቸውን ለገንዘብና ለገንዘብ ብቻ እጃቸውን እንዲሰጡ ሆነና አረፈው፡፡ስለዚህም ለገንዘብ ሲባል ሀገር፣ሰፊና ለም መሬት፣ሃይማኖት፣ሞራል፣ህሊና፣ባህል፣ፅላትና የሃይማኖት ቅርሶች፣እህት፣ወንድም፣ባል፣ሚስት፣ልጅ ብቻ ገበያ ሲደራ ሁሉም ነገር ይሸጣል ይለወጣል፡፡ብቻ ሁሉም ነገር ቦታውንና ክብሩን ለገንዘብና ለጥቅም እንዲያስረክብ ሆነና አረፈው፡፡እውነት መናገር፣ትህትና፣ታማኝነት፣ቅንነት፣ታታሪነት፣እውቀት ወዘተ የሆነው ሞራላዊና መልካም ስነ-ምግባር ሁሉ እንደ ኋላቀርነት አስተሳሰብ ተቆጠረና በምትኩ ማጭበረብበር፣መዋሸት፣ማምታታት፣አድርባይነት፣ክህደት፣አጉል ብልጣብልጥነት፣ሸፍጠኝነት፣በአቋራጭ መክበር፣ ሌብነት፣ለገንዘብና ለጥቅም ሲባል ስጋንና ህሊናን መሸጥ ወዘተ መጥፎው የሆነው ነገር ሁሉ በተገላቢጦሽ መልካም ተግባር ጉብዝናና ስልጣኔ ሆኖ ተቆጠረ፡፡ይሁዳ አዳኙንና ፈጣሪውን ክርስቶስን ለ30 ዲናር አሳልፎ እንደሰጠው ሁላችንም እናውቃለን፡፡ዛሬ በይሁዳ ላይ ያደረ ሰይጣን ሁላችንንም እያታለለንና እየተጫወተብን ስለሆነ ሁሉን ነገራችንን ምናልባትም አንድያ ነፍሳችንንም ጭምር አላፊና ጠፊ ለሆነ ለጊዚያዊ ገንዘብና ጥቅም ሲባል በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ እንድንሸጥና እንደንለውጥ እያደረገን ነው፡፡ስለዚህም ሁላችንም ለዚህ ገንዘብና ጥቅም እንዲሁም ለስልጣን እንደባርያ ከተገዛን ሃይማኖትና ሞራላዊ እሴቶች ሁሉ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ እንዴት አደርገው ነው ተገቢው ክብርና ቦታ ሊኖራቸው የሚችለው፡፡ችግሩ ስር የሰደደና ሰፊ የሆነ አጠቃላይ የሀገርና የትውልድ ዝቅጠት ውጤት ነው፡፡ስለዚህም እንዲህ በቀላሉ በአጭር ጊዜ መፍትሄ የሚያገኝ አይመስለኝም፡፡አጠቃላይ የተቀናጀ የንቃተ-ህሊና ስራ መሰራት አለበት፡፡በብልጣብልጥነት ላይ በተመሰረተ በተራ ዲስኩርና በፕሮፖጋንዳም ብቻ የሚፈታ አይደለም፡፡
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ፡፡

  ReplyDelete
 25. ርብቃ ከጀርመንNovember 9, 2011 at 5:11 PM

  ሰላም እንደምን ከረምክ ዲያቆን ዳንኤል መቸም ደኒ በዚህ በሲኖዶስ ስብሰባጉዳይ ምንምአለማለቱ ለምንይሆን እያልን ካንዲት ጉደኛየጋር እያወራን ነበር እና በመጨረሻላይ ባጠቀላይ ጭብጡን አይቶ ጨምቆ አንድነገር ማለቱ አይቀርም እያልን ነበር እንዳልነውም የተለመደውንና ጣፋጭ ተግሳጽህንና ምክርህን ስለሰጠህን በጣም እናመስግናለን በያለንበት የተቸገርነው ነገርም ቢሆን እንዳልከው ባባቶቻችን የስነምግባር ችግር ላይ መወያየት እንደጋጠወጥነትና ክብራቸውን እንደመድፈር ቤተክርስትያንን እንደማርከስ በሚቆጥሩ ሰዎችዘንደ የሚደርስብን ጫናና ተለጣፊስም መሰጠት ባሁኑ ሰአት ቀላል አይደለም እራሳቸው ያልጠበቁትን ክብራቸውን እንዴትአድርጎ ምእመኑ ይጠብቅላቸው ቢሰርቁ እነርሱ ቢዘሙቱ እነርሱ ጉቦቢበሉ እነርሱ ባሁኑሰአት እኮ በክፋትና ተንኮል እኮ ሰይጣንን ቀድመውት የተገኙት እነርሱ እየሆኑ ነው እንዲህ ከሆነ ለምነ መነኮሳችሁ ስትላቸው እኛየመለኮስው ያለምን ጣም ሳናውቀው በልጅነታችን ነው ገንዘብ የተገኘው አሁን የኑሮን ጣምያወቅነው አሁን እንዴት እነሁን ነው መልሳቸው ታዲያ ካልቻላላችሁ ለምነ አታገቡም ሲባሉ ቤተክርስቲያናችንን አናሶቅስም አናሰድብም የሚሉት መልስአላቸው አሁን ማንይሙት እውነት ለቤተክርስቲያናቸው አስበውነው ቢሆንማ በመጀመሪያም ከንዲህያለቅሌት በታቀቡ ነበር እኔእንደሚመስለኝ ለጥቅማቸው ሰሉ እድሉከተገኘም ተንጠላጥለው ፓፓስ ለመሆን እና እድሜልካቸውን በቤተክርስቲያን ስም ሲነግዱ ሊኖሩካልሆነ አሁን ማንይሙት አለማዊሰው በሚዋኝበት የዋናቦታ መለኩሳቶች መዋኘት እና አለማዊው ሰዉእንዳሻው የሚሆንበት ዛዉና(ሳውና)እርቃናቸውን መግባት ለመነኩሴ የሚገባ ነገር ሆኖነው ለምን እንዲህታደርጋላችሁ ሲባሉ ተደፈርን ብለው አንጃየሚለዩት ካቃታቸው መቸም ቤተክርስቲያን ስንዱ እመቤትናት ለነርሱ የሚሆን ህግ ሰይኖራት ቀርቶ አይመስለኝም እናምእንዳልከው የሞራል ዝቅጠትን ምግባረብልሹነትን ልቅነትነ ሲልቅም ምንፍቅናን ካልሆነ እንደነዚህ አነት አባቶች ሌላምንያስተምሩናል እርሱባለቤቱ ቅዱስ ባለወልድ የሚበጀውንያምጣልን ልቡናቸውን ይመልስልን ካልሆነም ጠርጎያውጣልን ! ወላዲተአምላክ በምልጃዋ አስራትሀገርዋን ትጠብቃት አሜን ::

  ReplyDelete
 26. በማኅበረሰባችን ዘንድ ግብረ ሰዶማዊነት እየተስፋፋ ነው፡፡ ሕፃናትን መድፈር እየተለመደ ነው፤ ፍች የሰዓታት ዜና እየሆነ ነው፣ በወጣቶች ዘንድ ድንግልናን መጠበቅ ነውር እየሆነ ነው፤ ከዳቦ ቤቶች ይልቅ ጫት ቤቶች እየበዙ ነው፤ ጉቦ ማሳፈሩ ቀርቶ እየተወደሰ ነው፤ አሲድ በሰው ላይ መድፋት፣ ዓይን ጎልጉሎ ማውጣት፣ በቢላዋ የትዳር ጓደኛን ማረድ፣ ልጅን ቆራርጦ መግደል እውነት የሃይማኖተኛ ሕዝብ ጠባያት ናቸውን?
  በጭራሽ የሃይማኖተኛ ሕዝብ ጠባያት አይደሉም። ለኡል እግዚአብሔር ይጠብቀን!!!

  ReplyDelete
 27. Very nice analysis! I believe we need to pray for this generation. I always wonder that if our generation is corrupted like this, what will be the future for our kids. I see in my work place and other places as if homosexuality being accepted as natural being. Our kids in US learn homosexuals are born just like that and should not be discriminated against. Three month or so ago, I was reading an article about Michelle Bachman, the lady who is running for president, that her husband has a clinic that prays away gayness or something like that. I was like they are weird but when I really thought about it, I was blindsided just because Obama was black and I support him, it does not mean I should avoid this values. The article frames her how dare she is not pro gays. At first I agreed with the article. But it makes me realize that even without knowing we are in support of this directly or indirectly! It does not faze us anymore! we have accepted them without our knowledge. But what is even shocking is to know one of our Monks’ have to be in court for raping a young boy! Egzio Meharne Kirstos! Yebese atameta new yemibalew. God told Abraham that he was going to destroy the city of Sodom Abraham took a deep breath. He was about to argue with God! “What if there are some good people living there,” Abraham said. “If you destroy the city, they will die too. That wouldn’t be right.” So God said, “If you can find fifty good people there, I won’t destroy the city. I will save the whole city for the sake of the fifty good people. As we know the ending of the story, there were not even 10 people who were good people that God had to destroy the city of Sodom! So if those in charge of the church who should be praying and asking God to give us mercy are corrupted, who is going to pray for us from this evil time? Ke’sega fetena, Ke’mekera nefese yetebiken! Dingil beamalginetuwa kezi kefu zemen tetadegen AMEN!

  ReplyDelete
 28. Dn Daniel Man,Yesemona geza,Amekneyo ,,yehe sela personal guday yemyewar neger ,,,,Betbeza dani,,makawema Adelem,,,Gen yen hasb Neaw...personality kemenem neger belay..andega tekret yesetw beya neaw...lelaw..astesasebachen sekeyer ...yegebnal.....~ ebkhen,Seltsebayoche,psychology stuff...

  ReplyDelete
 29. i don't think religion is working this day for sure and for sure~

  ReplyDelete
 30. Abetu Amlak Hoy? Selekdusanu Setel yehenini Ken Asaterelen.Lante hulu yechalehal.Hulachenem bedelen.Bedelachen Ante endatayen Aderegen.Woyo!!! Betekresteyane yanchin tefat kemaye.Moten Temegnhu.Norem mene teqmekush?

  ReplyDelete
 31. u can comment as u like because u are far(uSA).we will be in trouble if we comment.Thanks

  ReplyDelete
 32. ዲን ዳኒኤል ጽሑፍህ አጠቃላይ የሀገራችን እና የሃይማኖት ትቕማትን ችግሮች የዳሰሰ ስለሆነ ጉልህ ጠቀሜታ ይኖረዋ።
  ነገር ግን አንተ ከገልጽሃቸው እና ርብቃም ከጀርመን ያነሳቻቸው አንዳንድ ችግሮች በእውነት መፈፀማቸውን ለማመን በጣም ይከብዳል። ርብቃ እውነት መነኮሳቱ እንዲህ በግልፅ አይን አውጠው ይናገራሉ ወይ? እራስሽ የሰማሽው ከሆነ ግድ የለም። ነገር ግን ከሌላ ሰው ሰምተሽ ከሆነ የጠላት ወሬ ሊሆን ስለሚችል ለእንደዚህ አይነቱ ነገር የካህናትን ታማኝነት ሊያሳጣ ይችላል።

  ReplyDelete
 33. WENATE NAWE YANAGA TATAKEWACHONE SASEBE YEZAGANENAGALE

  ReplyDelete
 34. ABETU ENDECHERENETH ENJE ENDE BEDELACHEN AYHUN
  H

  ReplyDelete
 35. dani Icon yemilwun kal wede amarigna bitimelisew 1 kal mechemer ayichalim neber ? I appreciate anyways
  thank you for the nice articel.

  ReplyDelete
 36. "Ye minagerutin enji yemiyadergutin atimelketu" bilonal eko...entewachew sewoch nache fitsuman ayidelum , endemanim yisasatalu, enitseliyilachew.anaganew , anasifafaw, tselot yemayimelisew yelem.kaganenew gin dirgitoch yibisalu.."zimita work new" yene opinion, hulum yalfal.

  ReplyDelete
 37. ዘመኑ የሚዲያ በተለይም የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን ነው፡፡ በዓለም ጫፍ የተተነፈሰች ነገር በሰከንድ ወደ ሌላው የዓለም ጫፍ ትደርሳለች፡፡ እንደ ትናንቱ ነገሮችን ደብቆ ይዞ መኖር አይቻልም፡፡
  አንዳንድ ጊዜ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ የሚፈጸሙትን ስሕተቶች መናገር ሃይማኖቱን እንደ መድፈር፣ ለጠላት አሳልፎ እንደ መስጠት፣ ገመና እንደ ማውጣት እየተቆጠረ በመምጣቱ አልባሌ ሰዎች እና አልባሌ አሠራሮች የእምነት ተቋማቱን ምሽግ አድርገው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ዕድል እየሰጣቸው ይገኛል፡፡
  SOFONIYAS.

  ReplyDelete
 38. Kale Hiwot yasemalin Dn. Daniel
  I'm so happy for you finally talk about our church issues which is very important. I thought you completely forgot about the church. I just want to say that a little while ago, about 5 years ago, me and my friend were talking about our church and she told me that she thinks the patriarch and some fathers in the sinod have a mission to destroy our church. I asked how, she said the fathers by becoming corrupt and careless about the church, they will remove any trust from the followers which finally will lead tochange of religion or even stop believing in God. That's what ther mission is. to make Ethiopia without any believe in GOD. You know what, I believe her now. Their plan is to destroy the life of all Ethiopians. It is not only about money. Atlanta

  ReplyDelete
 39. ርብቃ ከጀርመን የገለጸችውን እኔም ያረጋገጥኩት ስለሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ እንዲያውም “እናተ አለማውያን እኛ መነኮሳትን ለምን ትከታተሉናላችሁ ዝም ብላችሁ የራሳችሁን ኑሮ አትኖሩም ወይ” ነው ያሉኝ በተደጋጋሚ ያልሆነ ቦታ ባልተገባ ሁኔታ ላይ አግኝቸ ያነጋገርኳቸው መነኮሳት፡፡ ታዲያ ማንን እንይ ? ግራ ገባን እኮ ፡፡ ለዛውም ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ መነኮሳት ናቸው እኮ እንዲህ የሚሉን፡፡ አለም በቃኝ ብለው ገዳም የገቡት........ ኡኡኡኡኡ ኧረ ብዙ ጉድ አለ፡፡ ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል.......... ወደ መፍትሔው እንፍጠን፡፡

  ReplyDelete
 40. Believe or not, by now our Church is considered as private limited company for administrators,monks & preists.every body can prove it.

  ReplyDelete
 41. አንዳንድ ጊዜ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ የሚፈጸሙትን ስሕተቶች መናገር ሃይማኖቱን እንደ መድፈር፣ ለጠላት አሳልፎ እንደ መስጠት፣ ገመና እንደ ማውጣት እየተቆጠረ በመምጣቱ አልባሌ ሰዎች እና አልባሌ አሠራሮች የእምነት ተቋማቱን ምሽግ አድርገው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ዕድል እየሰጣቸው ይገኛል፡፡
  dani silenersu kifu sira lalsemaw masaweks hamet yihon?

  ReplyDelete
 42. egiziyabiher libonachinin yabralin

  ReplyDelete
 43. Hi Dani

  On July 7,2010. I sent email saying ..ወንድ ሕፃናት ላይ የሚደርሰው ወሲባዊ ጥቃት እየጨመረ??? I got this topic on Reporter news paper "Sorry for Writing the following:

  If the Police doesn't punish those animals who rape small childern(boys or girls), the Ethiopian people should start Kill those gays and sick animals. Where are the Church and Mosque leaders, they just watch and they let it go. In North America, crimnals who rape childeren and women most of the time they would be killed in jail by other cirminals.

  In North America other crimanls stand for Childern and women aginst those rapists. What a shame in my country Peace loving ethiopians, Religious leaders (people), Police, Government & Judges who let those repist let go free and watch attacking poor childern and women again and again. "

  I know you are busy, but it should be just a start this article to expose those evil issues. In the place I live in no one let his kids be with any one. The time is changing very fast as a result of globalization, but I don't think we have a government, a police, justice system or religious groups that understand the threat who capable of act accordingly.

  Dani, I admire your hard work, but please write more on those issues instead of writing some less important matters to our community.

  ReplyDelete
 44. ከህሊና በላይ ነው ስለእውነት እራሴን አሞኝ ነው ያደረው ከባድ ነገር ነው፡፡ ህሊና ከመስመር ሲወጣ በጣም አስቸጋሪነው ጌታ አምላክ እኛንም እነሱንም በቸርነቱ የጠብቀን ሁላችንም እንፀልይ………

  ReplyDelete
 45. People

  We are living in the era of end of the world

  1. Try to keep integrity of yourself, at least your family ,friends, etc


  2. Be knowledgeable in both spiritual and other general knowledge

  3. Struggle wherever and when ever possible for church

  4. Teach all the culture and orthodox relegion- there is internet ,websites and books and so on .


  5. Pray and be person.

  6. Do not lose hope, think of our good spiritual fathers and follow their preaching. Avoid those bad fathers and let them be consulted by good fathers.


  7 Whenever you listen of bad things , pray and be strong.

  8.Share your question ,concerns and information to all(true orthodox) and clarify your doubts

  9. Be ready in your life in God's will.


  God be with us.

  Sharing negn

  ReplyDelete
 46. Zemenun wajuuu!!!!!!!!!!! wedet eyameran newuuu tesfa yeminadergewu, arayaa yamihonen,,yeminimaribet neger eyetefa newuu...abetu becherinetih asiben zimim atibelen yalante an alenina

  ReplyDelete
 47. Your suggestion for public discussion is very timely. However, there is no public space for expressing our views. Which media is open for discussion? We may be considered as terrorist if we criticize logically the way our church is administered.

  ReplyDelete
 48. ርብቃ ከጀርመንNovember 10, 2011 at 1:24 PM

  እርብቃ የሰማሽውእውነትነው ወይስ የጠላት ወሬነው ላልው (ሽው) ምእመን ከራሴ አፍልቄ ወይም የሰውወሬ ሰምቸም አይደለም እኔእራሴ ጠይቄ የሰመሁት ነገር ነውእውነት ስለመሆኑም የእውነት አምላከ ያውቃል በተረፈግን ሌላም ሰው ከላይ እንደጻፈው ያላወራነው ብዙጉድ አለ ለሁሉም ግዜለው አይደል ጠቢቡ ያለው ይቆየን !

  ReplyDelete
 49. እንግዲህ በአገሬ አልኮራም!!!! የምመካበት ኃይማኖቴ ነበር እንጂ ሌላማ ምን አለኝ!!!! አንተ ግን ተባረክ::

  ReplyDelete
 50. የኔ እንካን እምነት የሚባል ነገር አላፈልግም ቢሆንም ግን የሌላውን ሀይማኖት ግን አከባራለሁ በይበልጥ ያኦርቶዶክስ ሀይማኖት ከኢትዮጲያዊነታጭን ጋር አያይዤ ዐመለከተዋለው ፤የሃይማኖት መሪዎች ከፍተኛ የሆነ ሚና በህብረተሰቡ ዘንድ እንዳላቸው፡ግን ትንሽ ግራ የሚገባኝ ነገር በአሁን ጊዜ ያሉት የሀይማኖት መሪዎች በገንዘብ ለይ ያላቸው አቀም ነው፡፡ለምሳሌ አንድ ነጋዴ ከዚያም ከዚህ ብር ሰብስቦ ራሱን በንግድ እያደራጀ ኢንቨስተር ለመሆን ይታገላል ፡፡አንድ የሀይማኖት አባት ግን ብር ሰብስቦ የት ሊደርስ ነው ለተቸገረ ሰው ካላከፋፈለው ለዚህ ደግሞ የዚህን ያህል ተሞነጫጭፎ ሊሆን አይችልም ፤ሌላው ደግሞ ሙሁራኖቻችን እንካን ከሀገሪቱ ባለሀብቶች አናናር ጋር ራሳቸውን ሲያፎካክሩ እና ሲማረሩ ሳይ ግራ ይገባኛል፡፡ከመነሻው ሰው እውቀትን ምርጫው የሚያደርገው ለአዕምሮ እርካታ ነው አለበለዚያ ደግሞ በእውቀት ፋንታ ገንዘብን ማሳደድ አይ ሁለቱንም ከሆነ ደግሞ የሌሎችን ሞራል ጠብቆ ከራስ ወዳድነት በፀዳ መልኩ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በተረፈ ሞራል ያለው ነው፤ ጨዋ ናት መባል ነውር እንደ ነውር መቆጠር ከተጀመረ ቆይቶል፡፡ ቢሆንም ግን እኔ የምፈራው ይሄ ባህሪ ለሁሉም ተዳርሶ በቅንነት ሰርቶ አገሪቱን የሚያቀና እንዳይጠፋ ነው ፡፡ሲያልፍም ፈላስፋው ቶማስ ሆብስ( Thomas hobbes)እንደሚለው ወደ(state of nature) ሀገሪቱን ለውጠን አንዱ ሌላውን በመዘረር ተብላልተን እንዳንጨራረስ ነው፡፡

  ReplyDelete
 51. "አንዳንድ ጊዜ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ የሚፈጸሙትን ስሕተቶች መናገር ሃይማኖቱን እንደ መድፈር፣ ለጠላት አሳልፎ እንደ መስጠት፣ ገመና እንደ ማውጣት እየተቆጠረ በመምጣቱ አልባሌ ሰዎች እና አልባሌ አሠራሮች የእምነት ተቋማቱን ምሽግ አድርገው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ዕድል እየሰጣቸው ይገኛል"
  ስለዚህ ምን የይደረግ? መፍትሄው እንዴት ይመጣል? ወደ እግዚአብሄር ማመልከት አንዱ መፍትሄ ነው? እኛስ ምን እናድርግ?

  ReplyDelete
 52. ዳኒ አሪፍ ሃሳብ ነው
  እኔ የምለው ነገር ቢኖር እስካሁን ችግሩ እንዳይባባስ ገበናችንን ለአህዛብ ላለመግለጽ ብለን ዝም ብለናል ነገር ግን ዝምታችን ካለማወቅ ወይንም ከፍርሃት ሳይሆን ለ ቤተክርስቲያናችን ካለን አክብሮትና ትህትና ምክንያት እና አባቶቻችን አገልግሎታቸውን የሚሰጡት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው ብለን ስለምናም ነው ነገር ግን በአሁኑ ስአት በአንዳንድ አባቶች ላይ ይህን የመንፈስ ቅዱስ አሰራር አናይባቸውም(ለግል ጥቅማቸውና ለክብራቸው ብቻ በመጨነቅ የቤ/ክ ችግር ለነሱ ግድ ስለማይሰጣቸው) አሁን ግን ችግሩ አይን እያወጣ ስለመጣ ገበናችንም አደባባይ ስለወጣ ስህተት የሰራውን አካል በግልጥ ስህተቱን መንገር እና እንዲታርም ማድረግ ይህም መፍትሄ ካላመጣ የቤተክርስቲየን ውክልናቸው እስኪነሳ ድረስ መንቀሳቀስ አቤት ማለትና በጸሎት ወደፈጣሪ መማጸን እንዳለብን ይሰማኛል፡፡ የቅዱሳን አምላክ እግአብሔር ቤ/ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን መንጋዎቹን የሚጠብቅ አባት ይስጠን አሜን፡፡
  ወየው ለአባቶች
  ለበጉ እረኞች
  በበረቱ መሃል
  ተኩላ አስገብታቹ
  ግልገሉን ላስበላቹ
  በቅድስናው ስፍራ
  በበጉ መሰማሪያ
  ፍየል ላሰማራችሁ
  ወየው ለአባቶች
  ለአደራበሎች
  ዛሬም ራሄል ታለቅሳለች
  ባባቶችዋ ተገፍታለች
  ስለስጋዋ እያነባች
  ነፍሷ ዛሬም ተጨንቃለች…..

  ReplyDelete
 53. ውድ ዲ. ዳንኤል
  ከዚህ በፊት ለብሎግህ የቤተ-ክርስቲያንን ነገር እንደተውከው፣ ከዚህም በላይ ደግሞ ለጊዜው በማይጠቅሙን ጉዳዮች ላይ እያተኮርክ የቤተ-ክርስቲያንን ጉዳዮች ረስተኸው፣ ሌሎችም እንዲረሱት እያደረግህ ነው ብዬ ወቅሼህ ነበር (አስተያየቴን አላወጠኸውም)፡፡ ይሁን እንጂ የአሁኑ ጡመራህ የቤተ-ክርስቲያንና የአገርህን ጉዳይ መቼም እንደማትተው እንድረዳ አድርጎኛል፡፡ ስለተሳሳተ አመለካከቴና ስለአልተገባ አስተያየቴ ከልብ ይቅርታ እላለሁ፡፡፡
  1. ጽሁፍህ በኅብረተሰባችንና በተቋሞቻችን በተለይ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን እያደገ የመጣው የስነምግባር ብሉሽነት በጣም አደገኛ ደረጃ መድረሱን ያስረዳል፡፡ በመንግስት ተቋማት ውስጥ እየሆነ ያለውን ትተን የቤተ-ክርስቲያናችን ግን ትልቅ አመጽ ነው፡፡ በመርህ ደረጃ ከእግዚአብሄር በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ፣የሰው ፊት አይተህ አታዳላ፣ ብርሀንህ በሰው ፊት ይብራ፣ አትስረቅ፣ አታመንዝር፣ ለባህርይ ያልተገባ ነገር አትፈጽም ወዘተ ብላ በምታስተምር ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ዘረኝነት፣ አድልኦ፣ አመዝራነት፣ ስርቆት፣ ግብረ ሰዶማዊነት ወዘተ እየተፈጸሙ ከሆነ በእግዚአብሄር ላይ ያመጹ ግለሰቦች አሉ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የሚፈራውን እግዚአብሄርን የማይፈሩ ከሆነ ሰውንም አያፍሩም፡፡ በቤተ-ክርስቲያናችን እየሆነ ያለው ይኸው ነው፡፡ እግዚአብሄን የማይፈሩ ሰውንም የማያፍሩ ሰዎች ተነስተዋል ማለት ነው፡፡
  እነዚህ ግለሰቦች ዝም ከተባሉ የሚያፈርሱት መንፈሳዊ ድንበሮቻችንን ብቻ አይደለም፡፡ ብሄራዊ ክብራችንንም ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ከየትኛው ጎሳ ቢመጣ፣ የትኛውንም እምነት ቢከተል ኢትዮጵያዊ በመሆኑ የሚጠነቀቃቸው ብዙ ተግባራት አሉት፡፡ ታላቅን ማክበር፣ እንግዳን መቀበል፣ የተቸገረን መርዳት ወዘተ ኢትዮጵያዊያንን ልዩ የሚያደርጉ ጠባያት ናቸው፡፡ እነዚህ ዋልጌ ግለሰቦች እንግዲህ የሚንዱት ይህንን ኢትዮጵያዊ ጠባይ ነው፡፡
  በአንድ የእምነት ተቋም የሚፈፀምን እኩይ ምግባር መከላከል የእምነቱ ተከታዮች ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሌሎች ኢትዮጵየዊያን ግዴታ ጭምር ነው፡፡ የኢትዮጵያ የሆኑ መልካም ጠባያትና ሠላም የመጣው በተወሰኑ ጎሳዎችና ኃይማኖት ብቻ አይደለም፡፡ለሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በእምነት ተቋሞቻቸው ሽብር ቢሠበክ የሚከተለውን ጥፋት ማሰብ ቀላል ነው፡፡ በአገራች ላለው መልካም ስነምግባር የእነሱንም የኛም ቤተ-ክርስቲያን አስተዋጽኦ አለበት፡፡ ቤተ-ክህነት የመልካም አመለካከት፣ ስነ ምግባርና አሰራር ምንጭ መሆኑ ቀርቶ የሌቦች፣ ግብረ ሰዶማዊያን፣ ዘረኞች፣ ወዘተ መደበቂያ ዋሻና ምንጭ ከሆነ ችግሩ የሚተርፈው ለኦርቶዶክሳዊያን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ኢትዮጵያዎያንም ነው፡፡ ቤተ-ክርስቲያን ለመሳለም በሄደ የ15 ዓመት ታዳጊ ላይ የግብረ ሰዶም ተግባር የፈጸው ‹‹መነኩሴ›› በአጋጣሚ ቤተ-ክርስቲያንን በመጣ ወጣት ላይ ፈጸመው እንጂ በሌላ ቦታ በሌላ ታዳጊ የሚፈጽመው ድርጊት ነው፡፡ እዚህ ላይ የማልጽፈው ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶችን አውቃለሁ፡፡ በመሆኑም በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው ሕገ ወጥነትን ማስተካከል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል በሚደረገው ጥረት ሌሎችም የሚገባቸውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  2. የተለያዩ አካላት በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት አድርገዋል፤ ለብዙ ዘመንም ታግለዋል፡፡ ችግሮቹ ግን ከዕለት ወደ ዕለት ከዘረኝነትና ከገንዘብ ዝርፊያ ተነስተው ወደ ከፋ የስነ-ምግባር ብሉሽነት አደጉ፡፡ ይህ የሚያመለክተው የብዙዎቹ አካላት ድካም የችግሮቹን ምንጮች በማድረቅ ላይ ሳይሆን ችግር ፈጣሪዎች የሚያነሱትን እሳት በማጥፈት ስራ ላይ ተጠምደው እንደነበረ ነው፡፡
  አንደማስበው አሁን በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለብንም፡፡ በህልውናችን ላይ አደጋ እየተፈጠረ ነው፡፡ ሰዎቹ ከገንዘባችን አልፈው ክብራችንን እየደፈሩ ነው፡፡ ስለዚህ ለውጥ መምጣት አለበት፡፡ ለውጥ ለማምጣት የችግሩን ምንጭ ማድረቅ ይገባናል፡፡
  በእኔ እምነት የችግሩ ምንጭ ቤተ-ክህነት ነው፡፡ ቤተ-ክህነት ከመንበረ ፓትሪያርክ ጀምሮ እስከ ሌሎች መምሪያዎች ለቦታው በማይገቡ ግለሶች ስለተሞላ የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካት አልቻለም፡፡ እነዚህን ዋልጌዎች ከየቦታው ለቃቅሞ በማሰማራት ትልቁን ሚና የሚጫወቱት ደግሞ አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡ ቤተ-ክርስቲያንን ከሕግና ሥርዓት ውጭ በመምራት ለአጥፊዎች ጥላ ከለላ በመሆን ችግሮችን ከዕለት ወደ ዕለት እያባባሱ ይገኛሉ፡፡ እሳቸው በየዕለቱ ለቤተ-ክርስቲያን አዲስ ችግር ከመፍጠረቸውም በላይ ለተሃድሶዎች ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም እሳቸውን ከቤተ-ክህነት እንዲወጡ ማድረግ ትልቁን የችግር ምንጭ ማድረቅ ነው፡፡
  ስለዚህ ምዕመናን ተደራጅተን ቅዱስ ሲኖዶስ በፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ማድረግ አለብን፡፡ ሲኖዶሱ ለሚወስደው ውሳኔ ድጋፍ በመስጠት መንግስት ውሳኔውን እንዲያስከብርና ለጳጳሳት ደህንነት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥት ተጽዕኖ መፍጠር ይገባናል፡፡
  3. በቤተ-ክህነት ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን አዲስ መዋቅር መተከል ይገባዋል፡፡ ይህ መዋቅር የቤተ-ክርስቲያኗን ካህናትና አገላጋዮች የሚመዘግብ፣ ፍቃድ የሚሰጥ፣ የሚያሰማራ፣ ዝርፊያንና ዘረኝነትን የሚያስቀርና ለሁሉም እኩልና ተገቢ የሆነ የአገልግሎት ክፍያን በግልጽ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡ ዝርዝሩ በባለሙያዎች የሚወሰን ቢወሰንም አሁን ማንም ከሜዳ ተነስቶ በቤተ-ክርስቲያኗ አውደ ምህረት የሌሎችን ሀይማኖቶች ዓላማ ለማሳካት የሚራወጡትን መናፍቃንን ያስቀራል፡፡
  4. በተለያየ የአውቀት ደረጃ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ልሂቃን ቸልተኝነቱ ማቆምና የመፍትሄ አካል የመሆን ሚናቸውን መጫወት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም አዋቂ በመሆናቸው ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የሙያና የሞራል ግዴታ አለባቸው፡፡ ተሳትፎአቸው ቤተ-ክርስቲያን ተቆርቋሪ ምዕመን እንዳላት ለወዳጅም ለጠላትም የሚነግረው ብዙ መልዕክት አለው፡፡ በተሳትፎአቸው የቤተ-ክርስቲያንን ወዳጆች ሲፅናኑ፣ጠላቶቿ እንዲጠነቀቁና ከጥፋት ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ያደርጋል፡፡

  ስለዚህ እንዳባቶቻችን እየሰራን እንጸልይ፣ እየጸለይን እንስራ፡፡ ትምህርታቸው ጸሎት ብቻ ወይም ስራ ብቻ አይደለችም፡፡ ሁለቱንም እንድነት ይዞ ነው፡፡

  ጥበበ ሥላሴ

  ReplyDelete
 54. It is a sad story really... im now doubting fathers when ever i see them... we should all pray. Danel thanks for sharing this view i can see many people relate to it. God be with us.

  ReplyDelete
 55. የመረጥከው ርእሰ ጉዳይ ወቅታዊና የማህበረሰቡን የልብ ትርታ ያደመጠ ነው፡፡ በርግጥ እንዳንተ ያሉ ጸኀፍት የሚፈተኑበትና መክሊታቸውን የሚመነዝሩበት ትክክለኛ ወቅት እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ህዝብ እንባውን ያነባል ቤተክርስትያንም በልጆቿ አዝናለች፡፡እውነት እግዛብሄርን እንፈራለን ኃጥያትንስ እንጠየፋለን የሞራል ክስረት ደርሶብናል እራሳችን ማየት አቶናል፡፡ ይህን አንተ ገለጽከው…….

  ReplyDelete
 56. Consider, for example the Greek and Romanian Orthodox Churches, and the provocative attitudes displayed by both of these entities. For several months, the impudence of high-ranking members of the clergy in Athens and Thessaloniki has known no bounds, now that the lost sheep demonstrating in the streets have begun to focus their attention not only on the rejection of austerity packages, but also on the redistribution of wealth and in particular the wealth of the Orthodox Church, which has never been evaluated [the Orthodox Churches in both Greece and Romania do not pay taxes and benefit from a certain number of privileges

  ReplyDelete
 57. Consider, for example the Greek and Romanian Orthodox Churches, and the provocative attitudes displayed by both of these entities. For several months, the impudence of high-ranking members of the clergy in Athens and Thessaloniki has known no bounds, now that the lost sheep demonstrating in the streets have begun to focus their attention not only on the rejection of austerity packages, but also on the redistribution of wealth and in particular the wealth of the Orthodox Church, which has never been evaluated [the Orthodox Churches in both Greece and Romania do not pay taxes and benefit from a certain number of privileges. the problem is every ware??

  ReplyDelete
 58. ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ !!!
  ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ!!!
  ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ !!!

  ReplyDelete
 59. how we starting that?
  let us starting talk every thing openly this is serious and I like the idea which is Dn Daniel's, let us keep on our mind every day.

  ReplyDelete
 60. ረብቃ ለችው እውነት ነው እኔ ራሴ እንደህ አይነት ስራ የሚሰርት አይቼ ባናግራቸው የራስሽን ኑሮ ኑሪ ምን አሳየሸ እኛን ነው የተባልኩት ያውም ከተጨባጭ መረጃ ጋር ታይተው

  ReplyDelete
 61. Hallo wendmoche ehtoche endwe men yeschalale endzeh yaleh yenate betkrstyane fetna bega zemen mehonu endet ende egre esate endmeyangebgebeg alengrachum becha yebzuhane enate kedste dengel maryame betkrstyanchen kendezeh yale fetna tetbeklene ene yemfraw kezeh yeblet fetna kefetachen eymeta new selzeh kerstena sew belelebet sew hone megget new teknanbo wede betkerstyane meto memeles menem wage yelwem selzeh hulachem beand lay betkrstyanachen metbek yetbekbenale .

  ReplyDelete
 62. thank you dani very good topic and this the time we act with the help of god

  ReplyDelete
 63. ዳኒ ቃለሕይወት ያሰማልን እንደሚገባኝ አሁን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማምራት አለብን ለዚህ የሚሆን መፍትሔ ሓሳብ ያስፈልጋል

  ReplyDelete
 64. ዳኒ! ቃለ ሕይወት ያሰማልን! በተለይም ማኅበራዊ ሚዲያዎች በየጊዜው ትኩስ መረጃዎች ማውጣታቸው ሁኔታውን ይበልጥ ፀሐይ ለማስመታት የቻሉ በመሆኑ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሃይማኖት አባቶቻችን ቅርበት ያላቸው ሰዎች ችግሩን በግልፅ እንዲያውቁት ቢያደርጉና ከሕዝቡ ጋር ውይይት ቢጀመር መልካም ነው

  ReplyDelete
 65. መነኩሴው በተክሊል ጋብቻ መፈፀማቸው አነጋጋሪ ሆኗል
  Sunday, 24 July 2011

  ምንኩስናው ቢፈርስ እንኳን በተክሊል ማግባት አይቻልም.. - ቤተክርስቲያን
  ከሳምንት በፊት ቆቤን ለቸገረው ሰጥቻለሁ.. - ሙሽራው
  ምንኩስናውን አፍርሻለሁ ስላለኝ ጋብቻውን ተቀብያለሁ.. - ሙሽሪት
  ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቁት ..መነኩሴ.. የምንኩስና ሥርዓቱን ጠብቀው ምንኩስናቸውን ሳያፈርሱ በሙሽሪቷ የትውልድ አገር በሀዲያ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ቤተ መቅደስ በይፋ በተክሊል ሥርዓተ ጋብቻ መፈፀማቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡


  ቤተክርስቲያን የጋብቻ እና የምንኩስና ሥርዓት እንዳላት የሚናገሩት የጉራጌ ከንባታና ሐዲያ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ቀለምጢዎስ፤ አንድ መነኩሴ ሥርዓቱን ፈሞ ምንኩስናውን ሲወስድ ከዓለማዊ ነገር ተገልሎ ቆቡን እንደሚስት አግብቶ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ቆቡን ሳያወልቅ ወይም ምንኩስናውን ሳያፈርስ ምንም ዓይነት ዓለማዊ ሥርዓት መፈፀም እንደማይችልም አስገንዝበዋል፡፡

  ነገር ግን መንፈሳዊ ሆኖ መኖር ካቃተው ወደ መነኮሰበት ገዳም አሊያም ጠቅላይ ቤተክህነት ቀርቦ ምንኩስናውን አፍርሶና ቆቡን ጥሎ አለማዊ ሆኖ መኖር እንደሚችል ገልፀው፤ ይህም ሆኖ ግን በተክሊል ማግባት ፈሞ እንደማይችል፤ ይህንንም ሥርዓቱ እንደማይፈቅድ ጠቁማዋል፡፡

  እሳቸው በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት ሥር አንድ መነኩሴ በይፋ በተክሊል ሥርዓተ ጋብቻ ፈሟል መባሉን ሰምተው፣ ጉዳዩን በጥብቅ እየተከታተሉት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  ጋብቻውን ፈመዋል የተባሉትን አባ ገብረክርስቶስ ታምሩ አነጋግረናቸው፤ ከሳምንት በፊት ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው ቤተክህነቱ ሥራ እንዲመድባቸው ሲጠይቁ ሊመደቡ እንዳልቻሉ እና እስኪመድባቸው እንኳን እዛው ኮሌጅ ውስጥ ማረፍያ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ከጊቢው በጥበቃ ሰራተኛ ተገፍትረው መውጣታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀው፤ በድርጊቱ ተናደው ቆባቸውንም እዛው ለቸገረው ሰጥተው ቤተክህነትን ጥለው ወጥተው ጋብቻውን መፈፀማቸውን አረጋግጠዋል፡፡

  ሙሽራዋን ቀደም ሲል በጓደኝነት ይዘዋት እንደነበር ያልሸሸጉት አባ ገብረክርስቶስ፤ እስከ ሰርጉ እለት ድረስ ግንኙነት አለመፈፀማቸውን ሰርጉ በተክሊል እንዲሆን የወሰኑትም ..ለልጅቱ ብዬ ነው.. ብለዋል፡፡

  ..መነኩሴው ሁሉ በየጓዳው የሚያደርገውን እኔ በአደባባይ ስላደረኩት ነው ወሬ የሚሆነው?.. ሲሉ የሚጠይቁት አባ ገብረክርስቶስ፤ ..ተክሊልም ሆነ ምንኩስና ሥርዓት ነው በሥርዓቱ መሰረት ቆቤን ጥዬ ትዳር መስርቻለሁ.. በማለት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

  የ26 ዓመቷ ሙሽሪትም በበኩሏ፤ ግንኙነት ከጀመረን ሁለት ዓመት አልፎናል በወቅቱ ..እግዚአብሔር ጋብቻ እንድፈም ፈቅዷል፤ ምንኩስናየን አፍርሼ መጥቻለሁ ብሎኛል እሱን አምኜ ጋብቻ ፈሜያለሁ፤ አሁንም እሱን ነው የማምነው.. ስትል መልስ ሰጥታለች፡፡

  ሙሽራው መነኩሴው ስለመሆኑ እንደማያውቁ የገለፁት የሙሽሪት ቤተሰቦች፤ በጉዳዩ ማዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ሙሽራው በበኩሉ ..እኔ ለቤተሰቦችሽ ንገሪ ብያት ነበር፤ ያልተናገረችው እሷ ናት.. ሲሉ መልሰዋል፡፡  Do you see what they are doing?
  Specially most of the guys who are graduated from spiritual college? all are die for money and women.

  ReplyDelete
 66. Diacon Daniel ,I remember u for ever for your good works.Now a days every thing is almost out of control such as ZEREGNENET,selfishness,etc.I don't think we will return back to the previous good ethical and spritual things.
  yours

  ReplyDelete
 67. ከዚህ የባሰ እያየን ነውና ስርአቱን አለመጠበቃቸው እንጅ ካልቻሉ የርሳቸው ይሻላል ምክንያቱም እግዚአብሄር የፈቀደውን የወንድናየሴት ጋብቻነውና የፈጸሙት እኔስየምሰጋው እንደነጮቹ የኛዎቹም መኖክሳት ወንድለወንድ ይፈቀድልን ብለው ባደባባይ እንዳይወጡነው እዚህ አገር እንዳሉት አባቶች ውይ ሚስጥር አወጣሁ እንዴ ይቅርታ!

  ReplyDelete
 68. ንእፁ ህሊና ከአገልጋዮቹ የተሰደደበት ምክንያቱ ከሰማንው ከምናውቀው ውጪ ምን ይሆን? ይቅርታ ና ንስሀ እንደ ተራራ የራቃቸው ለምን ይሆን ? ዳኒ በርታ ፀጋህን ያብዛው ይሄን አገልግሎትህን ጌታይባርክልህ::ዮናስ አበበ

  ReplyDelete
 69. baABONA PAULOSE TASHOME NAWE YEMATAHOTE SELALOTE KASE ENGLAND MANCHESTER SELAMENOROTE YAMETTAKOTEN AKAFELONE.TACHAGERANALE

  ReplyDelete
 70. ewente belehale.....enamesegenale

  ReplyDelete
 71. ...የሀገሪቱ ሕጎችም የሃይማኖት ተቋማት እንደ ሕጋቸው ሳይሆን እንደፈለጉ እንዲሆኑ የሚያግዙ ናቸው፡፡ ገንዘባቸው ቁጥጥር አይደረግበትም፡፡ ግብር አለመክፈል እና ቁጥጥር አለማድረግ የተለያዩ ናቸው፡፡ ገንዘብ በተዝረከረከበት ቦታ ሁሉ ወንጀል በልጽጎ መገኘቱ ደግሞ የማይቀር ነው፡፡ አወቃቀራቸው እና አሠራራ ቸውን ዘመናዊ እንዲያደርጉ፣ የቁጥጥር ሥርዓት እንዲዘረጉ፣ አገልጋዮቻቸውን እና አባሎቻቸውን መዝግ በው እንዲያውቁ የሚያስገድዳቸው ነገር የለም፡፡...
  esubalew,DMU

  ReplyDelete
 72. ዳን. ዳነኤል በጽሁፉ የገለጸው የክፋት ተግባር በሙሉ በመንፈሳዊውም ወነ በአለማዊው ኑሮ የእምነት ልዩነት ሳያግደን ልንታገለውና ልንነቅፈው የሚገባ ነው።

  ከተሰጡት አንዳንድ (ጥቂት) አስተያየቶች የማየው ግን ይህ በኦርቶዶክስ በቤተክርስቲያን ያለ የክፋት ተግባር ለማስመሰል ተሞኮራል። ይህ ወይ የመረጃ እጥረት ወይም አንዳንዶች ኦርቶዶክስን በጅምላ ለመክሰስ መሞከር መፍትሄ አያመጣም ለምሳሌ (Greek and Romanian Orthodox Churches) የነሱት አስተያየት ሰጭ፡

  እኔ በምኖርበት በሰሜን አሜሪካ፡
  የፕሮቴስታንት፤ የካቶሊክ፤ የእስልምና ... የእምነት ተቋማት ግብር(taxes) አይከፍሉም። so It is not fair just to say Greek and Romanian Orthodox Churches do not pay taxes and benefit from a certain number of privileges).
  እንዲሁም ደግሞ ሰዶማዊነት በግለሰቦ ( በአገልጋዮች) ደረጃ ፕሮቴስታንት፤ የካቶሊክ፤ የእስልምና ... የእምነት ተቋማት እንደሚፈጸም የተረጋገጠ ነው። ሰዶማውዊ ፓስተር እስከመሾም የደርሱ የእምነት ተቋማት አሉ።

  በእኔ አስተሳሰብ የሰዶማዊ ተግባር ለማስፋፋት አላማ ያንገቡ ክፍሎች ከበለጸጉ አገሮ ወደ ታዳጊ አገሮች(ኢትዮፕያ) ጨምሮ በመጓዝ አላማቸውን በገንዘብ፤ በቆዳ ቀለማቸው ጭምር በመጠቀም ያስፋፋሉ። በተለይ ሕጻናቱንና ወጣቱን በዚህ ክፉ ተግባር በመልከፍ ወደፊት ሕጻናቱ ሲያድጉ የነሱን ተግባር አራማጆች እንዲወኒ ማባድረግ ቁጥራቸውን ለማበራከት ይጥራሉ ( ከ14 አመታት በፊት በአንድ ህሳናት ማሳደጊያ የተፈጸመ ተግባር ለዚህ ማስረጃ ሊወን ይችላል)።

  ይህን ክፉ ተግባር የሚያራምዱ ግለሰቦች ህጻናትንና ወጣቶችን አላማቸው ጠደብቆ በደንብ ሊያገኙበት እንድሚችሉ የሚያስቡትን ስፍራ ሁሉ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ልንረዳ ይገባል። ስለውነም በመነኩሴነት፤ በፓስተርነት፤ በኢማምነት የእምነት ተቋማቱ ወስጥ ተደብቀው መጭውን ትውልድ በነሱ ክፋት ተግባር እንዳይበከል ነቅተን ልንጠብቅ ይገባል።

  ሓስቤን ለማጠቃለል፡ ተራውን ህዝብ ልጆቹን እንደአይኑ ብሌንን እንዲጠብቅ፡ ልጆቹንም እራሳቸውን እንዲተብቁ ሊያስተምር፤ ልጆቹም ማንም ይሁን ማ(በመንፈስዊውም ይሁን በአለማዊው የተከበረ) ያልተገባ ነገር ለማድረግ ቢሞክር(ቢያደርግ)ወይም ጥቃት ቢፈጽም ለቤተሰባቸውና ለፖሊስ ወዲያውኑ እንዲያስተውቁ፤ የግልጽነትን ባህል ማዳበር።

  በተጨማሪም ደግሞ በእንደዚህ ክፍ ተግባራት የተሰማሩትን ተገቢውን ቅጣት እንዲሰጣቸው የፍትህ አካሉ ላይና መንግስት ላይ እና የእምነት ተቋማቱ ላይ ግፊት ልናደርግ ይገባናል። እነዚ አካላት ሊያደርጉ የሚገባውን ትክክለኛ ትምህርትና ቅጣት ቸል ካሉ ግን፡ ከዚ በፊት በእንጊሊዘኛ ጽሁፌ እንደገለጽኩት፤ እራሳችን የሚገባውን ቅጣት እየሰጠን ለልጆቹ ልንቆምላቸው ይገባል።

  ReplyDelete
 73. egzyabher ystelne d.daniel.....ena malte yimflgew bemgmry ewntega kerctyanochen geleltgi! and sindo! belene mekfafelune enakumena andly honen lhiymanotchenen anadnte engadell wanaw andnete newna ytasibibet!!!ande honene endantagle telke chigier new elalhu!!!!!!!!!!!!!!!!!!unataw yasririgh krstyane negee!egzybhare yerdane becrentu amen!amen!

  ReplyDelete
 74. ዳኒ ይህንን ጽሑፍ www.ethiocist.org ላይ አገኘሁት፡፡ ለካህናትም ሁሉ ምክር ይሆናል ብዬ ስላሰብሁም እነሆ አካፍዬዋለሁ፡፡ በእኔ አመለካከት ሰው ሁሉ በተለይም ደግሞ ካህን ኃአትን የሚያፈቅረው የተጠራበትን ዓላማ ሲዘነጋ ነውና፡፡

  የካህን ዘለዓለማዊ ምርጫ

  ልጄ ሆይ! አንተን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣህ ያለ ምክንያት አይደለም፤ የክህነትንም ሥልጣን ያለበስህ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ አባቴ እኔ የሱ ካህን እንድሆን በወሰነ ጊዜ በዚያኑ ሰዓት አንተ የኔ አገልገይ እንድትሆን ወስኖሃል፡፡ ከዘለዓለመ ዓለም ጀምሮ በማይለወጥ ትእዛዝ ቦታህ ከኔ ቦታ አጠገብ ተወስኖ ስምህም በኔ እጅ ተጽፎ የካህናዊ ክብሬ ተካፋይ እንድትሆን ተመርጠሃል፡፡ መለኮታዊ አባቴ ከዘለዓለም ጀምሮ የሰውነት ባሕሪዬንና በመስቀል ላይ መሥዋዕት አድርጌ የማቀርበውን ሥጋ የምትሰጠኝ እናት እንድትኖረኝ ወሰነ፡፡ እንዲሁም አባቴ በዘለዓለማዊ ውሳኔው ካህናት እንዲኖሩኝ ፈለገ፡፡ እነርሱም ምሥጢራዊ ሕይወትን ለብዙዎች እንዲሰጡና በመንበረ ታቦት ላይ እንደገና ለአብ መሥዋዕት ሆኜ እንድቀርብ ያደርጉኝ ዘንድ ተወሰኑ፡፡
  አዬ ስንት መተሳሰሪያዎች ናቸው አንተን ከእኔና ከእናቴ ጋር አሰረው የሚይዙ! እነዚህም መተሳሰሪያዎች የተፈጠሩት ባንተ ፈቃድ ወይም ባንተ ሥራ አይደሉም፡፡ እኔን የመረጥኸኝ አንተ አይደለህም አንተ ሂደህ ፍሬ እንድታፈራ የመረጥሁህና ካህን ያደረግሁህ እኔ ነኝ፡፡ አባቴ አስቀድሞ ካልሳበው ማንም ወደኔ አይመጣም እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም የክህነት ሥልጣን ሊኖረው አይችልም፡፡ ኢምንትነትህን ኃጢአቶችህንና ወሮታ ቢስነትህን ሳልመለከት ከሺ መካከል አንተን መረጥሁ፡፡ በመንገድ ላይ ከሚገኘው ጭቃ አንሥቼህ የሕዝቤ መሪዎች ከሆኑት ጋር አጠገቤ አስቀመጥሁህ፡፡
  ልሞት አንድ ቀን ሲቀረኝ የክህነት ምስጢርን ስሠራ አንተን በተለይ አስቤሃለሁ፤ አንተ የኔ ካህን፣ የኔ ወዳጅ የሥራየ ተካፋይ መሆንህን ማሰቤ መከራን ለመቀበል አደፋፍሮኛል፡፡ ከመጨረሻ ራት በኋላ ስለ አርድእቶቼና በነሱም ቃል ስለሚያምኑት ሰዎች ሁሉ ጸሎት ባደረግሁ ጊዜ ዓይኖቼ በደስታ ባንተም ላይ ዓርፈዋል፡፡ ስላንተ በመጸለይም እነዚህን እጅግ ከፍ ያሉትን ሥራዎችህን አንድ ቀን ለመፈጸም እንድትበቃ ኃይል ታገኝ ዘንድ ጸሎት አድርጌልሃለሁ፡፡ በመስቀል ላይ ልሞት ሳጣጥር በእግሮቼ ሥር ታማኙን ረድእ አየሁ አንተም በሱ አማካኝነት እንደነበርህ ዓወቅሁ ስለዚህ አንተንና ክህነትህን እሷ እንድትጠብቅ በማለት አንተንም ከሱ ጋር ለእናቴ አደራ ሰጥቻታለሁ፡፡ ከሙታን ከተነሳሁ በኋላም በዓለም ላይ ከዳር እስከ ዳር ወንጌልን እንዲያስተምሩ ሐዋርያቶቼን ስልክ አንተም አንድ ቀን በቤተ ክርስቲያኔ የምትይዘውን ሥፍራ አስቀድሜ ወስኛለሁ፤ አሁን በአደራ የተሰጡህንም ነፍሶች አስቀድሜ አዘጋጅቼልሃለሁ፡፡
  ልጄ ሆይ! አንተ እኔን ማወቅ በማትችልበት ሰዓት እኔ አንተን ወደድሁህ፤ በኔ አጠገብ ሆነህ ሥፍራህን ለመያዝ በምድር ላይ የምትታይበትን ቀን በትእግሥት እጠባበቅ ነበር፡፡ በእንዴት ያለ ታላቅ ጥንቃቄ በልቤ ውስጥ ነፍስህን ከነፍሴ ጋር የሚያስተሳስረውንና በምሥጢረ ክህነት አማካይነት ከኔ ጋር ፍጹም አንድነትህንም የሚያዘጋጀውን አጽዳቂ ጸጋ ያን ጊዜ መረጥሁ! ገና በሕፃንነትህ ጊዜ ከጓደኞችህ የምትለይበት ገና ምንም ነገር ሳይኖር ቅዱሳን መላእክቶቼ በትጋት ያለማቋረጥ እየተከታተሉ ይጠብቁህ ነበር፤ እኔ የመረጥሁህ መሆንህን በማወቃቸው በክብር ይከቡህ ነበር፤ የነፍስና የሥጋ አደጋዎችን ከአንተ ወዲያ ለማራቅ በጥንቃቄ ይተጉ ነበረ፤ የክህነት ምኞት በልብህ እንዲያድር በውስጣዊ ምክር ቀስ በቀስ ያዘጋጁህ ነበር፤ መቸም አንድ ጊዜ የኔ አገልጋይ እንድትሆን መርጨሃለሁና ምንም እንኳ ብትበድለኝም እነርሱ ስለአንተ ይጸልዩልህ ነበር፡፡
  ክህነት በተቀበልክበት ቀን ከሌሎች ፍጡራን ሁሉ አንተን ለይቼህ ወደ ልቤ አስገባሁህ፡፡ በነፍስህ ገብቶ ባንተ ላይ አምላካዊ ማህተሙን ያተመውን የኔ የክህነቴ ማህተም ባንተ ላይ እንዲታተም የሚያደረገውን መንፈስ ቅዱስን ላክሁልህ፡፡ በሰማይ ሆነ በምድር የሥልጣን ተካፋዬ አደረግሁህ፤ በኔ ላይና በደሜ ባዳንኋቸው በጐች ላይም ሙሉ ስልጣን ሰጠሁህ፡፡ ያም ባንተ ላይ የታተመው ማህተም የማይደመሰስ ነው እግዚአብሔር ምሏል ቃሉንም አይለውጥም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ፡፡ ልጄ ሆይ! ሰለዚህ አንተ የኔ ነህ የመሥዋዕቴ አገልጋይ ነህ፤ ለኃጢአተኛ ሰው የምሕረቴ መሣሪያ ነህ፡፡ የኔ ካህን ነህ አንተ እንደራሴዬ ነህ፡፡ ባንተ ላይ ያለኝን ተስፋ በከንቱ አታስቀር፤ ለነፍስህ ውስጥ የተከማቸውን የወርቅ መዝገብ አታባክን፤ በሰጠሁህ ታላቅ ስልጣን ሳትጠቀምበት አትቅር፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ አንተ ሁል ጊዜ ከእኔ ጋር ሆነህ “ያባቴን ጉዳዮች መፈጸም ይገባኛል” ማለት አለብህ፡፡

  ReplyDelete
 75. ዳኒ የሀይማኖት መሪዎቻችን ምን እናድርጋቸው ? ግራ ገባን እኮ፡፡ በራሳችን ሀጢያት እና በነሱ ገመና መሀል ሆነን እንደ ድፎ ዳቦ ተንገበገብን፡፡ የት እንሂድ? ምን እናድርግ really this is true Gera Geban Eko Nededen !!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 76. Dear Dn. Daniel as always it is a great article but I have to be honest- I am not sure if the focus and the tone match with you and most importantly with what is going on against our orthodox church.

  God Bless you !

  ReplyDelete
 77. Dear Dn. Daniel as always it is a great article but I have to be honest- I am not sure if the focus and the tone matches with you and most importantly with what is going on against our Orthodox church.

  God Bless you !

  ReplyDelete
 78. አንዳንድ ጊዜ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ የሚፈጸሙትን ስሕተቶች መናገር ሃይማኖቱን እንደ መድፈር፣ ለጠላት አሳልፎ እንደ መስጠት፣ ገመና እንደ ማውጣት እየተቆጠረ በመምጣቱ አልባሌ ሰዎች እና አልባሌ አሠራሮች የእምነት ተቋማቱን ምሽግ አድርገው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ዕድል እየሰጣቸው ይገኛል፡፡አንዳንድ ጊዜ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ የሚፈጸሙትን ስሕተቶች መናገር ሃይማኖቱን እንደ መድፈር፣ ለጠላት አሳልፎ እንደ መስጠት፣ ገመና እንደ ማውጣት እየተቆጠረ በመምጣቱ አልባሌ ሰዎች እና አልባሌ አሠራሮች የእምነት ተቋማቱን ምሽግ አድርገው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ዕድል እየሰጣቸው ይገኛል፡፡

  እግዚአብሔር ይስጥልን ዲ. ዳንኤል

  ReplyDelete
 79. እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን!!
  ፀጋውን ያብዛልህ፡፡ዲ/ን ዳኒ
  ስማቸው አለምነህ ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 80. እኔ የምለው ይህ ሁሉ ሀጢያት እቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሲደረግ እግዚያብሔር ምነው ዝም አለ?

  እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

  ReplyDelete
 81. ምነው በአራት ኪሎ ድረፍት ቤቶች የድረፍት ጠርሙስ ጨብጠው የሚቀመጡትን ጥቁርለበሽ መነኮሳት ረሰሀቸው ዲያቆን ዳንኤል እኔማ ሳያቸው ደሜ ፍልት ነው የሚለው ያነ ጥቁር ልብስና ቢራይዘ ውሰሲታዩ ቢራየመያሰተ ዋዉቁ ነው የሚመስሉት ቤተክርስቲያንስ ለምንድንነ ው ዝM የምትለው ይህ የክብርል ልብስ በየመጠጥ በቤቱ ሲለበስ

  ReplyDelete
 82. እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን!!
  ፀጋውን ያብዛልህ ዲ. ዳንኤል
  Ameha Giyorgis ከZambia

  ReplyDelete
 83. እኔ የምለው ሲሰማ ራሱ ይዘገንናል፡፡ በዚህ ውስጥ መኖር ራሱ ትልቅ ፈተና ነው ቆይ አጠቃላይ የየትኛውም እምነት ተከታይ አላማ ምንድነው; የተለያየ አቋም ይኑር እንጂ ከዚህ ከሚያለፈው ዓለም ተስፋ ወደሚያደርገው ወደሌላኛው ዓለም በሞት አማካይነት መዛወር ነው ለዚህም የትኛውም የእምነት ተቋም የየራሱ መስፈርቶች አሉት በርግጠኝነት ደግሞ የትኛውም የእምነት ተቋም አንተ ከላይ የዘረዘርካቸውን ለጆሮ እንኳን የሚከብዱ ኃጢያቶች ተስፋ ለሚያደርገው ዓለም እንደ በጎ መስፈርት አያስቀምጥም፡፡ በእውነት ከቀድሞ አባቶቻችን ዘመን ከነበሩ መናፍቃን የበለጠ መናፍቃን የበዙበትና ትልቅ ተጋድሎ የሚጠይቅበት ዘመን ነው በጸሎትም፣ በማጋለጥም፣ በትግልም እግዚአብሔር ይህችን ሀገር ከመልካም ስብእናዋ ጋር ይጠብቅ፡፡
  እድሜ ይስጥህ ዳኒ!! ልክ እንደ አቡነ ሽኖዳ 3ኛ ታሳሳኛለህ እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ!
  አብነት ከሆሳዕና
  እኔ የምለው ሲሰማ ራሱ ይዘገንናል፡፡ በዚህ ውስጥ መኖር ራሱ ትልቅ ፈተና ነው ቆይ አጠቃላይ የየትኛውም እምነት ተከታይ አላማ ምንድነው; የተለያየ አቋም ይኑር እንጂ ከዚህ ከሚያለፈው ዓለም ተስፋ ወደሚያደርገው ወደሌላኛው ዓለም በሞት አማካይነት መዛወር ነው ለዚህም የትኛውም የእምነት ተቋም የየራሱ መስፈርቶች አሉት በርግጠኝነት ደግሞ የትኛውም የእምነት ተቋም አንተ ከላይ የዘረዘርካቸውን ለጆሮ እንኳን የሚከብዱ ኃጢያቶች ተስፋ ለሚያደርገው ዓለም እንደ በጎ መስፈርት አያስቀምጥም፡፡ በእውነት ከቀድሞ አባቶቻችን ዘመን ከነበሩ መናፍቃን የበለጠ መናፍቃን የበዙበትና ትልቅ ተጋድሎ የሚጠይቅበት ዘመን ነው በጸሎትም፣ በማጋለጥም፣ በትግልም እግዚአብሔር ይህችን ሀገር ከመልካም ስብእናዋ ጋር ይጠብቅ፡፡
  እድሜ ይስጥህ ዳኒ!! ልክ እንደ አቡነ ሽኖዳ 3ኛ ታሳሳኛለህ እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ!
  አብነት ከሆሳዕና

  ReplyDelete
 84. Thank you Daniel for your good view. You have commented that the people have to discuss on the issue. In fact through discussion, we could find meanses, but there are problems to do so. Firstly, we lack experience of discussion. Secondly we have not integrity. Now adays it is so difficult for us to agree even on single and simple issue. We correlate any matters with our party or ethnic. There are some people who like to disagree with the others in any issue. Thirdly; there is no any room that permits the society to discuss on such these issues. This is not only due to our political parties, but it is a result of our culture. Our culture never intiates for open discussion. We like backbite, mumur, and labling. I afraid when people proud of our cultures. This is not to degrade our forefathers and foremthers contributions. Infact there were few figures who played great role in our history, eccleciastical and secular. Though christianity have been in our land forsince 34 A.D, we could not touch every citizen of our land. Even we could not expand it out of three or four regions. Infact our saintly fathers such as St. Frumentius, kings Abraha and Atsebeha St. Abune Aregawi, St. Yared, Emperor Gebre Meskel, Ase kaleb, St. teklehaymanot with his desciples, St. Kiristos semra, Wolte Petros, and others had contributed much. Though we translated the scriptures to our language, we prefer to put them in our rooms, not to reveal their truth on the pulpit. Is there any body who colud mention me a single book on the teaching of Christian Ethics, that was written or translated for our church since the beginning? What does it mean? Sorry for concluding, we have not clear ethical teachings. Even in our theological issues the debates solved not according to the main teachings of orthodoxy, but according to the understanding of every traditional school teachers. This is not to neglect their contribution, but they have not any guide that holds them to the central teaching of the Orthodoxy. Look in one Ethiopian Orthodox Tewahido Church, there are two types of commentary systems, two types of sacred dances (aquaquam). The zema of Deguwa: Gonder, bethelhem, Qome,Tegulete, Achabir...,and also our liturgy (qidassie) debre abay, selelkula.....What do mean by all thse? For me all these, though somebody may claims as the gift of the Holy Spirit, show our lack of our church fathers integrity and unity. So dear; how possible to agree? Do you know the last version of our Holy Bible which we call the 81? It asked the church scholars more than 15 years. What was the matter? Nothing, but the members of the committee never could agree, even in using the good term. They were in great contradiction in chosing the Amharic word whether it to be according to the Shewa, or Gonder, or Gojjam, or Wollo. let me say again that we lack integrity. So let us start to have what we lack first with ourselves, then with our fellowmen and then in our Sunday schools. Finally, who knows what God will do through our Sunday brothers and sisters?

  ReplyDelete