Tuesday, November 1, 2011

ጥንቸል እና ዔሊ፡- አዲስ ታሪክ


የጥንቸልን እና የዔሊን ስም ሣነሣ ሁላችሁም የሩጫ ውድድራቸው ነው ትዝ የሚላችሁ፡፡ ሕንዶች ይህንን በጤና አያዩትም፡፡ ዔሊ ይህንን ውድድር ያሸነፈቺው በችሎታ ሳይሆን በወዳጇ ላይ በሠራቺው ተንኮል ነው ይላሉ፡፡ ሁለቱም በአንድ ጫካ ውስጥ ተስማምተው እና ተዋድደው፣ ተደጋግፈው እና ተመካክረው የሚኖሩ ነበሩ፡፡ ውድድሩም የተዘጋጀው ለመዝናናት እና ለአካል ብቃት እንጂ ለጠላትነት አልነበረም ባይ ናቸው፡፡ ሕንዶቹ፡፡
ግን ምን ያደርጋል፤ በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል ይል የለ የሀገሬ ሰው፡፡ አንዷ ዔሊ በሠራቺው ተንኮል በዔሊ እና በጥንቸል ቤተሰብ መካከል ጠላትነት ነገሠ፡፡ «ጥንቸል ውድድሩን ማሸነፍ ትችል ነበር፡፡ ነገር ግን ዔሊ እጅግ ወደ ኋላ ስለቀረች እርሷን ትታት መሄድ አልፈለገቺም፡፡ አንድ ነገር ብትሆንስ ብላ አሰበች፡፡» አሉ ሕንዶች ተረቱን ሲያሳምሩት፡፡ «ጥንቸል እንደ ዔሊ ጥሎ ማለፍ አታውቅም፣ ይዞ ማለፍ እንጂ፡፡» አሉና ጨመሩበት፡፡
 ጥንቸል የተኛቺው ብዙ ዘመን ስሟ ሲጠፋ እንደኖረው በትዕቢት እና ማንም አይደርስብኝም በሚል ስሜት አልነበረም፡፡ ዔሊን ለመጠበቅ ብላ እንጂ፡፡ ታሪክ በየፈርጁ ይባል የለ፡፡ ዔሊዎች ናቸው አሉ ይህንን ታሪክ የፈጠሩት፡፡ እኛ ለመቅደም አስበን ሳይሆን ጥንቸል ስለተኛች ላለመቀስቀስ ብለን ነው ይላሉ፡፡ እንግዲህ ታሪክን ጥንቸሎች ሲጽፉትና ዔሊዎች ሲጽፉት እንዲህ ያለ ልዩነት ያመጣል፡፡ ሲተኙ ችግር ውስጥ መውደቅ ደግሞ በጥንቸል አልተጀመረም፡፡ ታላቁ ሰው ኖኅም የወይን ጠጅ ጠጥቶ በተኛ ጊዜ ነበር ልጁ ካም የአባቱን ራቁትነት ያየው፡፡ ከሰዶም እሳት የተረፈው ሎጥስ ቢሆን ወይን ጠጥቶ በተኛበት ጊዜ አይደል እንዴ የገዛ ልጆቹ ከርሱ የፀነሱት፡፡
ጥንቸልም እንዲሁ ነው የሆነችው፡፡ ውለታ ቢሷ ዔሊ በችሎታዋ ሳይሆን በተንኮል ማሸነፍ ስለ ፈለገች እርሷን ለመጠበቅ በተቀመጠችበት በዚያው ዕንቅልፍ የወሰዳትን ጥንቸልን ሳትቀሰቅሳት በጎንዋ ቀስ ብላ አልፋ ውድድሩን አሸነፈች፡፡ ማሸነፍ ደስ የሚለው ውድድሩ ሰላማዊ ሲሆን ነው፡፡ ተንኮል እና ሤራ ያለበት ውድድር አንደኛው የሚያሸንፈው ሌላኛውን ሠውቶ ነው፡፡ ሕንዶቹ ታድያ «ሰው ወዙን፣ ጉልበቱን፣ ገንዘቡን፣ ዕውቀቱን እና ጊዜውን ሠውቶ እንጂ ወዳጁን ሠውቶ ማሸነፍ የለበትም» ባይ ናቸው፡፡ ያድርገው እንላለን እኛም፡፡
እኛስ ብንሆን አንደኛው ብሔረሰብ ሌላውን፣ አንዱ ፓርቲ ሌላውን፣ አንዱ መሪ ሌላውን፣ አንዱ እምነት ሌላውን፣ አንዱ ነጋዴ ሌላውን፣ አንዱ ምሁር ሌላውን፣ አንዱ አገልጋይ ሌላውን፣ አንዱ አርቲስት ሌላውን፣ አንዱ ደራሲ ሌላውን፣ አንዱ ባለ ሀብት ሌላውን፣ አንዱ ባለ ሥልጣን ሌላውን እየሠዋ ቢያሸንፍ መች ደስ ይለናል፡፡ ይህንንማ ነፍሳቸውን ይማረውና ከበደ ሚካኤል
አንድ የፋኖስ መብራት በሥራው የኮራ
እንዲህ ሲል ተጣላ ከብርጭቆ ጋራ
እያሉ «ፋኖስ እና ብርጭቆ» በተሰኘው ጥንታዊ ግጥማቸው በኩል መክረውን የለምን? ፋኖስ ብርጭቆውን ሠውቶ አሸንፋለሁ ሲል ድምጥማጡ መጥፋቱን ነግረውናልኮ፡፡
በታሪካችን ውስጥ አንዱ ሕዝብ በሌላው ላይ ተረማምዶ፣ ባህሉን እና ታሪኩን አጥፍቶ፣ ነገሥታቱን እና መኳንንቱን አሥሮ፣ ሀብቱን እና ንብረቱን ዘርፎ፣ ልጆቹን እና ሚስቱን ወስዶ የከበረበት እና የገነነበት ታሪክ ሞልቷል፡፡ አንዳችን ከሌላችን ጋር መኖር ብቻ ሳይሆን አንዳችን በሌላችን መሥዋዕትነት ያሸነፍንበት ታሪክም አለን፡፡ በአንድ በኩል ደግሞ እኛ የዛሬዎቹ ኢትዮጵያውያን የተሠራነው በሀገሩቱ ውስጥ በየዘመናቱ በተደረጉት ጦርነቶች መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ ይህንን መሳይ ታሪኮቻችን በተለይም በአሁኑ ዘመን በየቦታው ክብር አግኝተው እየተተረኩ ይገኛሉ፡፡
እገሌ የተባለ ብሔር ብሔረሰብ ገዝቶሃል፣ ነድቶሃል፣ አሥሮሃል፣ በዝብዞሃል፣ ጨቁኖሃል፣ ዘርፎሃል፣ ሽጦሃል፣ ለውጦሃል እያሉ የሚተርኩ ታሪኮች በይፋ እየወጡ ነው፡፡ ትውልድ የቂምን ታሪክ ቋጥሮ ጥርስ እየተናከሰ እንዲኖር የሚያግዙ መጻሕፍትም ይታተማሉ፡፡
እንዲህ መሳይ ታሪኮች የሀገራችን ክስተቶች ብቻ አይደሉም፡ በየሀገሩ በየዘመናቱ የዓለምን ሕዝቦች ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው፡፡ እንግሊዝ ብንሄድ የዌልስ፣ የስኮትላንድ እና የአየርላንድ ሕዝቦች በእንግሊዝ ሕዝቦች ላይ ተመሳሳይ ቅሬታ አላቸው፡፡ የአሜሪካ አፍሪካ አሜሪካውያን የካውካስ ዘር በሚባሉት ነጮች ላይ እንዲሁ ይተርካሉ፡፡ የአውስትራልያ አብሮጅያኖች በአውስትራልያ ነጮች መከራ ያዩባቸውን ታሪኮች ያነሣሉ፡፡
በየሀገራቱ መሥዋዕትነት የከፈሉ መከረኛ ሕዝቦች አሉ፡፡ ሀገሪቱ እንድታድግ፣ ሀብት እንዲከማች፣ ነጻነት እንዲከበር፣ ብልጽግና እንዲትረፈረፍ ያደረጉ፤ ነገር ግን የበይ ተመልካች ሆነው የመከራውን ገፈት የቀመሱ፡፡ እነርሱ በየዋሕነታቸው በቅንነታቸው፣ ነገሮችን በተንኮል ዓይን ባለማየታቸው፣ የተጎዱ ሕዝቦች አሉ፡፡
ታድያ የእነዚህ ታሪክ መነገሩ፣ የደረሰባቸው ገፍ መተረኩ፣ መገለጡ እና ለትውልድ ትምህርት እንዲሰጥ መደረጉ ችግሩ ምንድን ነው? እነርሱ ሲደርስባቸው የቻሉትን እናንተ ሲነገር መቻል ለምን አቃታችሁ? ይህንን እውነት ልንሸሸውስ እንችላለንን? ሌሎችም ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡
እውነት ነው፡፡ እውነትን መሸሽ አይቻልም፡፡ የትናንቱ ታሪካችን በጎውም ሆነ ክፉው ግልጥልጥ ብሎ መውጣት አለበት፡፡ ብርታታችንን አቅፈን፣ ድክመታችንን ነቅፈን መጓዝ እንድንችል በሚገባ የትናንት ጉዟችንን መፈተሽ አለብን፡፡ ዋናው ነገር የምንፈትሽበት ዓላማ ነው፡፡ ዓላማችን ቂምን ለመቋጠር እና ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስም ስለ ጥርስ የሚለውን የሐሞራቢ ሕግ ለመተግበር ከሆነ ጨቋኝን በጨቋኝ፣ ገዥንም በገዥ ከመተካት ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ የፊልሙን ጽሑፍ አንድ አድርጎ ተዋንያኑን መቀያየር ነው የሚሆነው፡፡ ትናንት አማራው የሠራውን ድራማ ዛሬ ኦሮሞው እንዲሠራው፣ ትናንት ትግሬው የሠራውን ድራማ ዛሬ ወላይታው እንዲሠራው ማድረግ አሮጌን ፊልም በአዳዲስ ተዋንያን እንደማየት ነው፡፡
ዓላማው ከትናንቱ መጣጣል ተምሮ የዛሬን አካሄድ ወደ መደጋገፍ እና መረዳዳት፣ መተጋገዝ እና መግባባት ለመለወጥ ከሆነ ግን ይበል ነው፡፡ ሕንዶቹ የዔሊን እና የጥንቸልን ሁለተኛ ክፍል ተረት እንዲህ ብለው ነው የሚነግሩን፡፡
ከብዙ ትውልዶች በኋላ ሁለት የዔሊ እና የጥንቸል ወጣቶች ዛፍ ሥር ተገናኙ፡፡ የአባቶቻቸውን የቂም ታሪክም ማውራት ጀመሩ፡፡ «ለምንድን ነው ግን የእኔ እና የአንተ ቤተሰቦች የማይገናኙት፣ ለምን ይጠላላሉ ሲል ዔሊ ጥንቸልን ጠየቀው፡፡ እውነቱን ነው አንዳንድ ነገሮችንኮ እየሁኑ መሆናቸውን እንጂ ለምን እየሆኑ እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም፡፡
«በድሮ ዘመን የአንተ እና የእኔ ጥንተ ጥንተ አያቶች ውድድር ገጥመው ነበር፡፡ የእኔ ጥንተ ጥንት አያት ሮጠችና ያንተን ጥንተ ጥንት አያት ቀደመቻት፡፡ ነገር ግን እርሷን በዚህን ያህል ርቀት ጥላ መሄድ አልፈለገቺም፡፡ ተጣጥሎ መጓዝ ቂምን እንጂ ደስታን አይፈጥርምና፡፡ እናም አንድ ዛፍ ሥር ቁጭ ብላ ጠበቀቻት፡፡ በዚያውም ዕንቅልፍ ወሰዳት፡፡
የአንተም ጥንተ ጥንት አያት ቀስ ብላ ስትደርስ የእኔ ጥንተ ጥንት አያት ተኝታ አየቻት፡፡ እርሷን ሳትቀሰቅስ ድምጿን አጥፍታ አለፈቻትና አሸነፈች፡፡ ጥንተ ጥንት አያትህ ያሸነፈቺው በእኔ ጥንተ ጥንት አያት መሥዋዕትነት በመሆኑ ቤተሰቦቻችን ቂም ተያያዙ፡፡ የተደረገባቸውንም እያሰቡ ሊስማሙ አልቻሉም» አለው፡፡
ወጣቱ ዔሊ የአያቱ ተግባር አናደደው፡፡ «ልክ ነው» አለ፡፡ «ማንም በሌላው መሥዋዕትነት ማሸነፍ የለበትም፡፡ ራስህን አንጂ አንዴት ሌላውን ትሠዋለህ፡፡ አያቶቻችን እዚህ ላይ ተሳስተዋል፡፡ እኛ ግን የእነርሱን ስሕተት መድገም የለብንም»
«ይህኮ አንድ ጊዜ የሆነ ነገር ስለሆነ ልትለውጠው አትችልም» አለው ጥንቸል፡፡
«ልንለውጠውማ እንችላለን» አለው ዔሊ፡፡ «የማይለወጥ ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ ያኛውን ታሪክ የሚያስረሳ አዲስ ታሪክ በመሥራት ልንለውጠው እንችላለን፤ዐዋጅ በዐዋጅ፣ ድል በድል፣ ታሪክም በታሪክ ይሻራል፡፡» ዔሊ ከድንጋዩ ውስጥ ራሱን አሥግጎ አወጣ፡፡
«እስኪ እንዴት አድርገን ጥንቸል ጠየቀ፡፡
«እኔ እና አንተ ነን መለወጥ የምንችለው፡፡ እኛ ከቀደምቶቻችን በጎ በጎውን እንጂ ሌላውን የመውረስ ግዴታ የለብንም፡፡ እነርሱ በዘመናቸው ኖረው በዘመናቸው መልካም የመሰላቸውን ሠሩ፡፡ ዛሬ ላይ ስናየው ስሕተት ሆኖ ተገኘ፡፡ እኛም በዘመናችን ኖረን በዘመናችን መልካም የሆነውን እንሥራ፡፡ እነርሱ ወደኛ ዘመን መጥተው ሊኖሩ እንደማይችሉ ሁሉ እኛም ወደነርሱ ዘመን ሄደን ልንኖር አንቸልም፡፡ ያኛውን ውድድር ተወው፡፡ አሁን እኔ እና አንተ በአዲስ ውድድር አዲስ ታሪክ እናስመዘግብ፡፡»
«እውነትክን ነው» አለ ጥንቸል፡፡ «እድሜ ልክ የጥንቱን ውድድር ብቻ እያነሡ ሲያወሩ እና ሲማረሩ መኖር ጥቅም የለውም፡፡»
ይህንን ሲነጋገሩ በእንስሳት መካከል የሚደረግ የሩጫ ውድድር ዜና ሰሙ፡፡ ሁለቱ በአንድ ላይ ለመወዳደር ተመዘገቡ፡፡
ውድድሩ የጫካው ንጉሥ ከሆነው ከድብ (ከቦፑ) መኖርያ ተነሥቶ የጫካው የፖሊስ አዛዥ አስከ ሆነው እስከ አውራሪስ (ሮሆ) መኖርያ የሚደርስ ነው፡፡ በውድድሩ መንገድ ላይ ሜዳ፣ ጫካ እና ወንዝ አለ፡፡ ተወዳዳሪዎች ይህንን ሁሉ ማቋረጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በማግሥቱ ውድድሩ ተጀመረ፡፡ የጫካው ንጉሥ ቦፑ ፊሽካውን ሲነፋ ጥንቸል ፈትለክ ብላ ሮጠች፡፡ እንደ አያቷ ግን ብቻዋን አልነበረችም፡፡ ዔሊን በጀርባዋ አዝላት ነበር፡፡ ጥቂት ድካም እና ጫና ቢሰማትም አዲስ ታሪክ በማስመዝገቧ እየተደሰተች ችግሩን ረሳችው፡፡ ጥንቸል ወንዙ ዳር ስትደርስ ሌሎች እንስሳት ቀድመዋት አገኘች፡፡ ነገር ግን ውኃው እጀግ ቀዝቃዛ በመሆኑ ማንም ሊገባበት አልደፈረም፡፡ አንዳንዶቹም የውኃውን ጥልቀት መገመት ስላልቻሉ ፈርተው ዳር ቆመዋል፡፡
ጥንቸልም ዳር ደርሳ ቆመች፡፡ ይኼኔ ዔሊ አስደሳች ሃሳብ አመጣች፡፡ «አሁን የኔ ተራ ነው፡፡ የአያቴን ስሕተት የማስተካክልበት ተራዬ አሁን ነው» አለቻት ጥንቸልን፡፡ ወዲያው ዔሊ ጥንቸልን በጀርባዋ አዘለቻት፡፡ በጠፍጣፋ እግሮቿ እየዋኘችም ወደ ወንዙ ውስጥ ገባች፡፡ ጥንቸልም በዔሊ ጀርባ ላይ ተፈናጥጣ በደስታ ወንዙን ስታቋርጥ የወንዙን ዐሦች እና የሰማይን አዕዋፍ የሳበ መዝሙር ትዘምር ነበር፡፡ በዔሊ እና በጥንቸል መካከል ያለው ቂም መፋቁን እና አዲስ ታሪክ መመዝገቡን እያዩ እንስሳቱ ሁሉ ከወንዙ ማዶ ቀሩ፡፡
ዔሊ ወንዙ ዳር ደረሰች፡፡ ጥንቸልም ወረደች፡፡ አሁን ደግሞ በተራዋ ጥንቸል ዔሊን አዘለቻትና ወደ ጫካው ፖሊስ ወደ ሮሆ መኖርያ ደረሰች፡፡ ማንም አልቀደማቸውም፡፡
በማግሥቱ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ተዘጋጀ፡፡ የጫካው ፕሬዚዳንት ሼሩ ሼር ክሃን ወደ መድረኩ ወጣ፡፡ ለጥንቸል እና ዔሊም መጠን የሌለው ሽልማቶችን ሰጣቸው፡፡ አንደኛ ስለወጡ፣ ሬከርድ ስለ ሰበሩ፣ ስለ ተባበሩ፣ ታሪክ ስለቀየሩ፣ ምኑ ቅጡ፡፡
ከሽልማቱ በኋላ ሼሩ ሼር ክሃን እንዲህ አለ «ወገኖቼ ከዘመናት በፊት የዔሊ እና የጥንቸል አያቶች እንደዚሁ ተወዳድረው ነበር፡፡ ያኔ ግን አንዱ በሌላኛው ላይ በሠራው ተንኮል ነበር ማሸነፍ የተቻለው፡፡ አንዱ አንዱን ሠውቶ አንደኛ ወጣ፡፡ ሽልማቱንም ለራሱ ብቻ ወሰደ፡፡ ይህ ግን ለማናቸውም አልጠቀመም፡፡ ቂምን ከማምጣት በቀር፡፡ አሁን ግን የልጅ፣ ልጅ፣ ልጅ፣ ልጆቻቸው ይህንን ታሪክ በዓይናችን ፊት ቀየሩት፡፡ ያኔ አንዱ ያንዱን ድክመት ተጠቅሞ አሸነፈ፡፡ ዛሬ ግን የአንደኛው ጥንካሬ ከሌላኛው ጋር ተባብሮ ሁለቱም አሸነፉ፡፡ ያኔ ጥሎ ማለፍ ነበር፤ አሁን ይዞ ማለፍ ሆነ፡፡ ያኔ በድክመታቸው ተጠቀሙ፣ ዛሬ ግን ከድክመታቸው ተማሩ፡፡ አንዱ ሌላውን እንዲወድቅ ሳይሆን እንዲያሸንፍ በመርዳቱ ሁሉም አሸነፉ፡፡»
እንስሳቱ ሁሉ ጫካው አስኪናጋ ድረስ አጨበጨቡላቸው፡፡

44 comments:

 1. «እኔ እና አንተ ነን መለወጥ የምንችለው፡፡ እኛ ከቀደምቶቻችን በጎ በጎውን እንጂ ሌላውን የመውረስ ግዴታ የለብንም፡፡ እነርሱ በዘመናቸው ኖረው በዘመናቸው መልካም የመሰላቸውን ሠሩ፡፡ ዛሬ ላይ ስናየው ያ ስሕተት ሆኖ ተገኘ፡፡ እኛም በዘመናችን ኖረን በዘመናችን መልካም የሆነውን እንሥራ፡፡ እነርሱ ወደኛ ዘመን መጥተው ሊኖሩ እንደማይችሉ ሁሉ እኛም ወደነርሱ ዘመን ሄደን ልንኖር አንቸልም፡፡ ያኛውን ውድድር ተወው፡፡ አሁን እኔ እና አንተ በአዲስ ውድድር አዲስ ታሪክ እናስመዘግብ፡፡»

  ReplyDelete
 2. ዲያቆን ዳንኤል

  መከርከን !አስተማረከን! ተባረክን!!!...
  .የቡድን መብት በማለት ቡድን ያንተን
  አባቶች ሲፈፍ የኖረ ነውና
  አንተም ፍፍ እያሉ ስንቱን ምስኪን አስረሱት፡፡

  !!!ስንቱን በጎሪጥ እንዲተያይ አደረጉት…
  በአንድ አገር እየኖረን የተለያየን ህዝቦች ሆንን …

  ስንቶች ሌሎችን ድጋፍ አድርገዉ ለድል ከበቁ
  በላ እኔ ነ ባለድል አንተን ለተሳተፎ ነበር የተመረከው
  ….የተባሉ ስንት አሳዛ ታሪኮች አሉን፡፡
  የአንተን ጦማር የጥንቸል እና ዔሊ ወጣቶች
  የተገናኙበት ቦታ ያድርግልን!!!

  ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን

  ReplyDelete
 3. Thank You D/n Dani
  Yihe lehulum neger bisera min alebet.Anidu anidun lemashenef sayihon huletum ashenafi lemehon mesrat bichal min alebet.Meche yihon ketilacha telaken abro silemehon yeminasibew?

  Hulachininm halafinet alebin..... Esti hulachinim yeyebekulachinin enweta..........

  ReplyDelete
 4. Sitetin kemedgem kesitet memar yemesele Bilihinet yelem...Betam konjo tarik ena dink atsatsaf new...God bless you...Tinchel ena Eli legna Ethiopiawiyanoch tiru misale nachew bedenib ketemeleketnachew..

  ReplyDelete
 5. enegedeh yanetane ttawatahe ebakachohe ega dagemo holachenem TINCHEL ena ELI enedenehone yehene ayenate malekete lalesamote enasetalalef

  ReplyDelete
 6. በጣም ደስ የሚልና አስተማሪ ጽሑፍ ነው: ተባረክ ዳኒ:: እኔም ሁልጊዜ አልገባኝ የሚለኝ: ቅድመ ቅድመ አያቶቼ በበደሉትና ባጠፉት እኔ የምሰቃየው ለምንድነው?? መቅጣት: ቂምን መወጣት ካስፈለገ እነርሱን ሄዶ:: በሌላ ጎኑ ደግሞ እኔስ ብሆን ይህ ትውልድ ባላጠፋው::አያቶቻቸው ባጠፉት ለበቀል ስል የከሌን ዘር የምወነጅል የምበቀል እኔ ማነኝ??

  "የፊልሙን ጽሑፍ አንድ አድርጎ ተዋንያኑን መቀያየር ነው የሚሆነው፡፡ ትናንት አማራው የሠራውን ድራማ ዛሬ ኦሮሞው እንዲሠራው፣ ትናንት ትግሬው የሠራውን ድራማ ዛሬ ወላይታው እንዲሠራው ማድረግ አሮጌን ፊልም በአዳዲስ ተዋንያን እንደማየት ነው፡፡" ከዚህ ነባራዊ ሁኔታ አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቃት::

  ድጋሚ ተባረክ ዳኒ: ሁሌም አድናቂህ ነኝ: እውነትም የሠላም አምባሳደር: በርታ ወደፊትም ጻፍ::

  ReplyDelete
 7. ርብቃ ከጀርመንNovember 1, 2011 at 10:40 PM

  ሰላም ዳኒ ባንተላይ አድሮ የሚመክረን የሚገስጸን አምላካችን የተመሰገነ ይሁን የኛንም የጠጠረ የተደፈነ ልባችንን አምላካችን ከፍቶ ለኛ ሲል የተሰዋልንን አምላካችንን አስበን እኛም ለወገናችን በትንሹንም ቢሆን መስዋዕት በመሆን መልካም አርያውን እንድንከተል የመድሀኒአለም ፈቃዱይሁንልን አሜን!

  ReplyDelete
 8. Many thanks Dn Daniel!! Please let this page be printed on news papers so that other people may get the chance to read and be benefited.

  ReplyDelete
 9. ዳኒ እግዜአብሄር ይባርክህ በእውነት ጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ እውነትን መሸፋፈን አቻልም ምናልባት ለጊዜው ካልሆነ በቀር ያ ደግሞ ይጎዳናል

  ReplyDelete
 10. እኔም ካለሁበት ኾኜ አጨበጨብኩ። እልል እልል እልል። የምሬን ነው እንዲ አይነቱ ታሪክ እኮ በስዕል እየተደገፈ የልጆች ታሪክ ይሆናል። ይህ ትውልድ ባይሆን መጪው ይተርፋል። ላንተም እኮ የኑሮ መደጎሚያ ይሆንሀል። ሳትቀደም ቅደም።

  ReplyDelete
 11. Let me share you the same story but in a different perspective.


  Once upon a time a tortoise and a hare had an argument about who was faster. They decided to settle the argument with a race. They agreed on a route and started off the race.
  The hare shot ahead and ran briskly for some time. Then seeing that he was far ahead of the tortoise, he thought he'd sit under a tree for some time and relax before continuing the race.
  He sat under the tree and soon fell asleep. The tortoise plodding on overtook him and soon finished the race, emerging as the undisputed champ.
  The hare woke up and realised that he'd lost the race. The moral of the story is that slow and steady wins the race.
  This is the version of the story that we've all grown up with.
  But then recently, someone told me a more interesting version of this story. It continues.
  The hare was disappointed at losing the race and he did some Defect Prevention (Root Cause Analysis). He realised that he'd lost the race only because he had been overconfident, careless and lax.
  If he had not taken things for granted, there's no way the tortoise could have beaten him. So he challenged the tortoise to another race. The tortoise agreed.
  This time, the hare went all out and ran without stopping from start to finish. He won by several miles. The moral of the story? Fast and consistent will always beat the slow and steady.
  If you have two people in your organisation, one slow, methodical and reliable, and the other fast and still reliable at what he does, the fast and reliable chap will consistently climb the organisational ladder faster than the slow, methodical chap.
  It's good to be slow and steady; but it's better to be fast and reliable.
  But the story doesn't end here. The tortoise did some thinking this time, and realised that there's no way he can beat the hare in a race the way it was currently formatted.
  He thought for a while, and then challenged the hare to another race, but on a slightly different route.
  The hare agreed. They started off. In keeping with his self-made commitment to be consistently fast, the hare took off and ran at top speed until he came to a broad river.
  The finishing line was a couple of kilometers on the other side of the river.
  The hare sat there wondering what to do. In the meantime the tortoise trundled along, got into the river, swam to the opposite bank, continued walking and finished the race.
  The moral of the story? First identify your core competency and then change the playing field to suit your core competency.
  In an organisation, if you are a good speaker, make sure you create opportunities to give presentations that enable the senior management to notice you.
  If your strength is analysis, make sure you do some sort of research, make a report and send it upstairs. Working to your strengths will not only get you noticed but will also create opportunities for growth and advancement.

  ReplyDelete
 12. The story still hasn't ended
  The hare and the tortoise, by this time, had become pretty good friends and they did some thinking together. Both realised that the last race could have been run much better.
  So they decided to do the last race again, but to run as a team this time.
  They started off, and this time the hare carried the tortoise till the riverbank. There, the tortoise took over and swam across with the hare on his back.
  On the opposite bank, the hare again carried the tortoise and they reached the finishing line together. They both felt a greater sense of satisfaction than they'd felt earlier.
  The moral of the story? It's good to be individually brilliant and to have strong core competencies; but unless you're able to work in a team and harness each other's core competencies, you'll always perform below par because there will always be situations at which you'll do poorly and someone else does well.
  Teamwork is mainly about situational leadership, letting the person with the relevant core competency for a situation take leadership.
  There are more lessons to be learnt from this story.
  Note that neither the hare nor the tortoise gave up after failures. The hare decided to work harder and put in more effort after his failure.
  The tortoise changed his strategy because he was already working as hard as he could. In life, when faced with failure, sometimes it is appropriate to work harder and put in more effort.
  Sometimes it is appropriate to change strategy and try something different. And sometimes it is appropriate to do both.
  The hare and the tortoise also learnt another vital lesson. When we stop competing against a rival and instead start competing against the situation, we perform far better.
  To sum up, the story of the hare and tortoise teaches us many things.
  Important lessons are:
  • that fast and consistent will always beat slow and steady;
  • work to your competencies;
  • pooling resources and working as a team will always beat individual performers;
  • never give up when faced with failure;
  • and finally, compete against the situation. Not against a rival.
  • In Short, BE STRATEGIC!

  ReplyDelete
 13. Betame dese ymil tmhert new yastemareken EgeziAbehere amelake asetwaye lebona yesetene

  ReplyDelete
 14. ግን እኮ ውድድር ካለ ደረጃ የግድ ነው፡፡ እነ አትሌት ኃይሌም እኮ መጀመሪያ ይረዳዳሉ በኋላ ግን ይቀዳደማሉ፡፡ ፍትሀዊ የሆነ ውድድር እንዲኖር መጣር ነው እንጅ አንደኛ እና ሁለተኛ መውጣትማ ግድ ይለናል፡፡ ውድድር ነዋ!!

  ReplyDelete
 15. «ወገኖቼ ከዘመናት በፊት የዔሊ እና የጥንቸል አያቶች እንደዚሁ ተወዳድረው ነበር፡፡ ያኔ ግን አንዱ በሌላኛው ላይ በሠራው ተንኮል ነበር ማሸነፍ የተቻለው፡፡ አንዱ አንዱን ሠውቶ አንደኛ ወጣ፡፡ ሽልማቱንም ለራሱ ብቻ ወሰደ፡፡ ይህ ግን ለማናቸውም አልጠቀመም፡፡ ቂምን ከማምጣት በቀር፡፡ አሁን ግን የልጅ፣ ልጅ፣ ልጅ፣ ልጆቻቸው ይህንን ታሪክ በዓይናችን ፊት ቀየሩት፡፡ ያኔ አንዱ ያንዱን ድክመት ተጠቅሞ አሸነፈ፡፡ ዛሬ ግን የአንደኛው ጥንካሬ ከሌላኛው ጋር ተባብሮ ሁለቱም አሸነፉ፡፡ ያኔ ጥሎ ማለፍ ነበር፤ አሁን ይዞ ማለፍ ሆነ፡፡ ያኔ በድክመታቸው ተጠቀሙ፣ ዛሬ ግን ከድክመታቸው ተማሩ፡፡ አንዱ ሌላውን እንዲወድቅ ሳይሆን እንዲያሸንፍ በመርዳቱ ሁሉም አሸነፉ፡፡»

  ዲ/ን ዳንኤል በጣም ግሩመ የሆነ ምልከታ ነው፡፡ ልብ ብናገኝና ብንጠቀምበት/ብንተገብረው ለአገር እድገት የሚጠቅም ትልቅ ምክር ነው፡፡ በጎ ምክርን የሚሰማ ጆሮ ከተገኘ፡፡
  እግዚአብሔር ይጠብቅህ ጸጋውንም ያብዛልህ፡፡

  ReplyDelete
 16. ያኔ አንዱ ያንዱን ድክመት ተጠቅሞ አሸነፈ፡፡ ዛሬ ግን የአንደኛው ጥንካሬ ከሌላኛው ጋር ተባብሮ ሁለቱም አሸነፉ፡፡ ያኔ ጥሎ ማለፍ ነበር፤ አሁን ይዞ ማለፍ ሆነ፡፡ ያኔ በድክመታቸው ተጠቀሙ፣ ዛሬ ግን ከድክመታቸው ተማሩ፡፡ take this for us!

  ReplyDelete
 17. በዚህ መወያያ መድረክ ላይ የህጻናት ተረት እንጂ ለ ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ ለውጥ የሚጠቅም አገራዊ ጉዳዮች ለምን እንደማይነሱ ይገርማል፡፡ነውረኛውን ነውርህን ተው የሚል ናታን ከየት ይምጣልን???ማየት ያለብንን አገራዊ ጉዳይ እንዳናይ በኃይማኖት ስም ባርነትን እንሰበካለን፡፡ግፍ እየሰራብን ያለው አካል ግፉን እንዲያቆም ሳይደረግ ተዛዘሉ እንባላለን፡፡አንተ የምትለጥፈው እንደ ኢቲቪ እና አዲስ ዘመን የአንድ ወገን ድጋፍ እና ጥላቻ እንጂ ምክንያታዊ የሆኑ አስተሳሰቦችን እና እውነቶችን ስላልሆነ ብዙ ማለት አይቻልም፡፡ሰዓት ከማባከን ውጪ፡፡የተለያዩ አስተሳሰቦችን በእኩልነት ለማስተናገድ ራሱን የቻለ ብቃት ይፈልጋል፡፡አስተሳሰቦችን እና አመለካከቶችን እየመረጠ የሚለጥፍ ብሎገር ምን ሊባል ይችላል???አዲስ አበባው ነኝ ከአዲስ አበባ ወያኔ ካፈረሰው ሰፈር፡፡

  ReplyDelete
 18. Dear Daniel,

  Nice article, it inculcates in our mind to inherit the good part of ancestors and forget the wrong part of our history. I like your explanation that entails cooperation is by far better than knock out.

  ReplyDelete
 19. እኔ ይህንን ተረክ ለቤተክርስቲያን አንድነት እመኘዋለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ቤተክርሰቲያን ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ የዓለም አብያተ ክርስቲያን እንዲህ ተቃቅፈው የአንዱን ዝርክርክ ሌላው ሰብስቦ፣ የአንዱን ድካም ሌላው ሸፍኖ፣ የአንዱን ኃጢአት ሌላኛው ይቅር ብሎ በፍቅር እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንሔድበት ቀን ይናፍቀኛል፡፡ አስቡት እስቲ! የግብጽ ክርስቲያኖች አናሳ መሆናቸው ሲቀርላቸው (የትልቁ የክርስቲያን ዓለም አካል ይሆናሉና)፤ የኢትዮጵያ ካቶሊኮች እንደአልፎንሱ ሜንዴዝ ወይም እንደሱሰንዮስ መቆጠርና መገለል ሲቀርላቸው፤ የአውሮፓ ክርስቲያኖች በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአፍሪካውያንና በላቲኖች የእምነት እሳት ሲነዱ፤ ሁላችን በአንዱ በእውነተኛው እረኛ በክርስቶስ አንድ ስንሆን፤ ሜታፊዚክስ ላይ መራቀቁና መነታረኩ ቀርቶ ፊዚካዊውን ዓለም በኑሯችን በፍቅራችን ስንለውጠው፤ ዓለም በፍቅራችን ክርስቶስን ሲያይ …
  እርግጥ ነው ለብዙ ሰዎች ይህ ቅዠት ይመስላል፡፡ ግን እውነት እላችኋለሁ! ከድንግል መውለድም ሆነ ከአምላክ ሰው መሆን አይበልጥም፡፡
  አምላኬ ሳልሞት አሳየኝ!

  ReplyDelete
 20. Daniel

  Thank you very much for the wonderful contribution.

  I thought that the article is based on or seemed to focus on the so called book '' Finote Gedil''

  Bisrat Amare made me of be cautious that there is still mission incomplete by Woyane. May be the dream to make come true of Great Tigray Republic is still the big Agendum of the group?

  May God Bless Ethiopia

  ReplyDelete
 21. ልጅ ዳንኤል ጥሩ ነገር እየነገርከን ነው፡፡
  ማንኛውም ፅሁፍ ሊያስተላልፍ የፈለገውን ዋና ትልቅ መልእክት ምንድን ነው የሚለውን መረዳት ትልቅ ፋይዳ ያለው ነገር ነው፡፡የውድድር ዋና መንፈስና አላማ አንድ ያለውድድር ካለው አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ የተሻለ ሌላ አጠቃላይ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለት ለመዝናናት ነው፡፡ነገር ግን አጠቃላዩ ህይወትና አለም እንደ ድር እርስ በእርሱ በረቀቀና በተወሳሰበ መልክ የተሳሰረ ስለሆነ ነገሮችን ሁሉ በውድድር ስሜት ወይንም መንፈስ ብቻ ማየት ተገቢ አይደለም፡፡እንዲያውም የሰው ልጅ ከማንኛውም ነገር በበለጠ በራሱ ላይ ሲሰለጥንና ራሱን ማሸነፍና መግዛት ሲችል ነው የመጨረሻው የብቃት ደረጃ ላይ ደረሰ የሚባለው፡፡ማለትም የሰው ልጅ ትልቁ ፈተናና ትግልም ሰው እንደ ሰው የተፈጠረበትን አላማ ተግባርና ምንነት ጥልቅ ሚስጥር መረዳት ሲችልና በዚህም ውስጣዊ ማንነቱንና እራሱን መግዛትና ማሸነፍ መቻል ነው፡፡ስለዚህም ስለ ውድድር ስናስብና ስንዘጋጅ ባለንጣዎቻችን ናቸው ብለን የምናስባቸውን የሌሎችን የመኖር ህልውናና ደህንነት በሚቀናቀንና በሚፈታተን ወይንም ጭራሽ በሚያጠፋ መልክ መሆን የለበትም፡፡ለጋራችን ለሆነ በህይወት የመኖር ህልውናና ደህንነት በጋራ ከመተባበርና ከመታገል ይልቅ ሁሉም በየራሱ መንገድና አካሄድ የራሱን ጠባብና ስግብብግብ ፍላጎት ለሟሟላት ሲል የሚያደርገው እጅግ ከልክ ያለፈ የጭካኔና የጥሎ ማለፍ ጤናማ ያልሆነ ውድድርና አጠቃላይ እንቅስቃሴና ተግባር መገታትና መቆም አለበት፡፡ብዙውን ጊዜ ሰዎች በደካማ አስተሳሰብ እየተመሩ እርስ በርስ ለመጠላለፍና ለመጣጣል የሚያባክኑት አላስፈላጊ ድካምና ጥፋት መጨረሻው ከንቱ ነገር እንደሆነ መረዳት ሲጀምሩ ነው ይህንን ከንቱ አካሄድ በማቆም ለጋራ ህልውናና ደህንነት በጋራ መስራት የሚጀምሩት፡፡በማን ላይ ቆመሽ ማንን ታሚያለሽ እንዲሉ ብዙውን ጊዜ ያንዳችን ስኬት በሌላው ላይ የተመረኮዘ እንደሆነ በስፋትና በጥልቀት አንረዳም፡፡ገዢዎቻችን በራሳችን ጫንቃ ላይ ያለፍቃዳችን በሀይል ተፈናጠውብን እየተቀመጡብንና እየተንፈላሰሱብን ሳሉ ያለአግባብ በማጭበርበርና በኃይል የተቆናጠጡት ስልጣንና ጣጣው የህሊና ረብሻና ጫና በፈጠረባቸው ቁጥር እየተረበሹ መልሰው እኛኑ አሸባሪ ወዘተ እያሉ ሀገር እንደሌለው እንደ መጤ ያስፈራሩናል ያሰቃዩናል፡፡ዛሬ ብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንኳን ጤናማና የተመቻቸ ቀና የሆነ የጋራ ፍትሃዊ የውድድር ሜዳ ሊፈጠርላቸው አይደለም በገዛ ሀገራቸው ከሁለተኛ ዜጋ በታች እየወረዱ ነው፡፡ዛሬ ኢትዮጵያውያን የህይወታችን አጠቃላይ ህልውናና ደህንነት በገዢዎቻችን መልካም ፈቃድ ስር የወደቀ እየሆነ ነው፡፡
  እንደ ሃይማኖተኛነታችንም በየእምነታችን አካሄድ የምናመልከው የምናከብረው የምንወደው የምንፈራው አንድ ፈጣሪ አምላክ እንዳለን ሁላችንም እናውቃለን በዚህም የተነሳ እሱን በፍፁም ልባችን በፍፁም መንፈሳችን በፍፁም ነፍሳችን እንወዳለን እንገዛለን እናመልካለን፡፡ይህንንም ባናደርግ እንኳን ፈጣሪያችን ለምን ይህንን አላደረጋችሁም ብሎ ወዲያውኑ አይቀጣንም እንዲሁም ለህይወታችን የሚያስፈልገንን አይከለክለንም፡፡ነገር ከዚህ በተቃራኒ መንፈስ በሆነ ያውም ሳንፈልጋቸው በግድ በጫንቃችን ላይ በሃይልና በማጭበርበር የተፈናጠጡብን የማይወዱን የማንወዳቸው ገዢዎቻችን ግን በእብሪትና በማናለብኝነት በሃይላቸውና በችሎታቸው ታብየው ከፈጣሪም በላይ እንደሆኑ በማሰብ በአጠቃላዩ የህይወታችን ህልውናና ደህንነት ላይ በዋናነት ብቸኛ ፋላጭ ቆራጭ ለመሆን በሚያሳፍርና በሚያሳዝን መልክ እየጣሩ ነው፡፡ዲያቆን ዳንኤል ዛሬ ኢትዮጵያዊ ዜጋ “ይዞታዬ ብለህ የያዝከው የምትኖርበት መሬትና ቦታ ያንተ አይደለም ወደድክም ጠላህም የእኔ የገዢህ ነውና መልሰህ በሊዝ ከእኔ ከራሴ ግዛኝ”እየተባለ መሆኑን ሰምተሃልን?የራስን ቦታና ንብረት መልሶ ለራስ መሸጥ፡፡እንግዲህ ያለንበት ተጨባጭ ነበራዊ ሁኔታ በተረት ተረት ብቻ የሚገለፅና የሚቀየር ነገር አይመስለኝም፡፡እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ለዚህም ነው አዲስ አባባ የተባለው መረር ያለ ቃል የተናገረው፡፡ዲያቆን ዳንኤል ያ የድሮው የየዋሁ ዘመን ማለትም እረኛ ምን አለ የሚባልበት ዘመንና ቅሬታንና አቤቱታን በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ እየተነገረ አዳማጭ ሰሚና መፍትሄ ሰጪ ገዢዎች የነበሩበት ዘመን አለፈ፡፡ዛሬ በተዘዋዋሪ በተረት ተረት አይደለም ፊት ለፊት በቀጥታ ለምን ይህ ይሆናል ብለህ ብትናገር መጀመሪያ ላይ ተዘዋዋሪ መልስ ይሰጥሃል፡፡ይህ ተዘዋዋሪ መልስ የማይገባህ ከሆነና እኝ ብለህ በተደጋጋሚ ለምን ይህ ይሆናል የሚል አሰልቺ አቤቱታና ቅሬታ ካቀረብክ መስዋእትነት የከፈልክ ታጋይ ወይንም ተጋዳላይ ነህ እንዴ ተብለህ ትጠየቃለህ፡፡ይህ ማለት ደግሞ እኛ መስዋእትነት ከፍለን ያገኘነው ስልጣን ስለሆነ የፈልግነውን ልናደርግ እንችላለን ወይንም ይገባናል ነው አጠቃላይ አንደምታው፡፡መስዋእትነት የከፈልክ ታጋይና ተጋዳላይ ካልሆንክ ደግሞ የስርዓቱ ዋነኛ አቀንቃኝና ደጋፊ አባል እንደትሆን ትጠየቃለህ፡፡ይህ የሚስማማህ ካልሆንክ ምናልባት የመጨረሻው እድልህ ተለጣፊ የውሸት ተቃዋሚ በመሆን አጫፋሪ እንድትሆን ትጠየቃለህ፡፡ከዚህ ውጪ ከሆንክ ግን አንተ ከ2ኛና 3ኛ ዜጋ በታች ትሆናለህ ማለት ነው፡፡ስለዚህም ከዚህ ውጪ ባለ ደረጃ የወረድህ ከሆንክ በንፁህ በኢትዮጵያዊነት ዜግነትህ የምታገኘው ነገር ከሌሎቹ ካንተ ከተሻሉት የተረፈውን ውድቅዳቂና ትርፍራፊ እንደውሻ ለመለቃቀም ይፈቀድልሃል፡፡እረ ምን ይህ ብቻ ይህንንም የሚፈቀድልህ እኮ በቀናኢ ኢትዮጵያዊነትህ ለሀገርህና ለወገንህ ተቆርቁረህ ይህ ለምን ሆነ ብለህ አደገኛ የሆነ ጥያቄና እንቅስቃሴ በማድረግ ስጋት እስካልፈጠርክ ድረስ ብቻ ነው፡፡ይህንን አይነት ስጋት ከፈጠርክ ደግሞ ጭራሽ አሸባሪ ተብለህ ወይንም አንድ የሆነ ታፔላ ስም ተሰጥቶህ ዘብጥያ ትወረወራለህ፡፡በእርግጥም ይህንን አይነት ስራ የሚሰሩ እነዚህ ገዢዎቻችን ይህንን ቁምነገር ያለውን ፅሁፍህን ቢያነቡት ይህ ደግሞ የማነው ሞኝ ብለው በውስጣቸው ከት ብለው ሊስቁብህና ሊያሾፉብህ ይችላሉ፡፡ለዚህም ነው አንዳንድ ጊዜ በቲዎሪ ደረጃ እጅግ የሚያምሩ ድንቅ ፅሁፎችና አስተሳሰቦች በተወሰነ ደረጃ በተግባር ካልተደገፉ በስተቀር እንዲያው ዝም ብለው ተረት ተረት የሚሆኑበት ጊዜ አለ የሚባለው፡፡

  ReplyDelete
 22. yaletanaka gelegel yawekale...........

  ReplyDelete
 23. መንግስት አሮጌ ቤቶቻችንን ብቻ ሳይሆን አሮጌ፣ ጭፍን፣ ማስተዋል የገጎደለው፣ ጨካኝ፣ ቂመኛና ሁዋላ ቀር አመለካከታችንን እና አስተሳሰባችንን አፍርሶ ጽሑፉ ላይ በሰፈረው እውነታ አዲስ አንድነትና ጉልበት የሚፈጥርልን ስራ ቢሰራ እንዴት መልካም ነበር፡፡

  ReplyDelete
 24. ትውልድ የቂምን ታሪክ ቋጥሮ ጥርስ እየተናከሰ እንዲኖር የሚያግዙ መጻሕፍትም ይታተማሉ፡፡
  እንዲህ መሳይ ታሪኮች የሀገራችን ክስተቶች ብቻ አይደሉም፡ በየሀገሩ በየዘመናቱ የዓለምን ሕዝቦች ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው፡፡ እንግሊዝ ብንሄድ የዌልስ፣ የስኮትላንድ እና የአየርላንድ ሕዝቦች በእንግሊዝ ሕዝቦች ላይ ተመሳሳይ ቅሬታ አላቸው፡፡
  betam yegeremegn , yewoyane sewoch yetsafutin and metsihaf ,GEHALAT SEGI yilal sile Amhara yetsafut neger betam yasazinal ,endet mengist endih aynet neger sitsaf yitebebral , bicha Amlak yifreden,Endenesu bihon yichi hager teshita ,ferisa neber , betam zeregna ena tebab nachewu.
  Alemu negn from ethiopia

  ReplyDelete
 25. Dn. Daniel, lately, I started to worry that you completely stop talking about God. What about some preachings from the Bible? Give us teching stories based on Prophets, Kings, and the many Saints we have in the Bible. Please don't forget who you are. You are not Daniel Kibret, you are Diacon Daniel Kibret. GOD BLESS YOU!!! Atlanta.

  ReplyDelete
 26. z blog is raising interesting issues that let us to see z other face of our world...z other points raised by others r also very important ... such as like PAB...
  friends i also learned that today not to look only towards leaders zy can be any type .... "religious", organizational or political leaders while zr grace, power, position ....becomes almost similar to z majority of we humans excpet very few things like making dicions on behalf of us....
  so i don't agree except respecting z ideas of some in complaining againest z so called political leaders or others...zr r a lot that where we have to look understanding majority r not touched n z world or creation of God at z same time is not few to fulfill our needs or demands....
  ya zr r points or sensitive issues where we have to focous on but most mothers say EYEYEM SIDELA NEW!!!!!....
  i thank you Dn. Daniel n others even who r againest his ideais respecting ur points reminding u now to narrow z midea we
  ......

  ReplyDelete
 27. ግርም ይለኛል!!!ኢትዮጵያ ናት ሰው የሌላት ወይስ ሰዉ ነው ኢትዮጵያ የሌለችው???ስንት እና ስንት ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብን የሚመለከቱ አገራዊ ጉዳዮች እያሉ በተረት ተረት ለውጥ ይመጣል ብሎ ማሰብ ምን ማለት ነው???አገራችን አሰብን የመሰለ የባሕር በር በድንቁርና ማጣቷ እና ለጅቡቲ በአመት 722 ሚሊዮን ዶላር መክፈሏ፡ሕልውናዋ በሌሎች አገሮች ይሁንታ ላይ መውደቁ፡ሕዝቡ በዘር መከፋፈሉ/ማሳያውም ሩቅ ሳንሄድ ድሬዳዋ የእኔ ነች የእኔ ነች እያሉ የሚጣሉ ሕዝቦች መኖራቸውና REFERENDUM ሊደረግ መሆኑ/፡ኢኮኖሚው በጥቂት ሰዎች እጅ መውደቁ፡ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት መሆን አለመቻሉ/ምርጫ 97/ሕዝቡ አገሩ ላይ ቋሚ ንብረት ማፍራት አለመቻሉ እና ንብረቱን ለልጁ ማስተላለፍ አለመቻሉ/ሰሞኑን የወጣው የሊዝ አዋጅ/ሰዉ በፈለገበት ጊዜ እና ቦታ ተንቀሳቅሶ እውቀቱና ጉልበቱ የፈቀዱለትን እንዳያፈራ መንቀሳቀሻ ክልል አበጅቶ ከዚህ ማለፍ አትችልም ማለት/ማሳያውም ባለታክሲዎችን በቀጠና መመደብ/፡በየመስሪያ ቤቱ የሰራተኛ ቅጥር በዘር እና በአድርባይነት የፖለቲካ ደጋፊ ሲሆን፡ሰብዓዊ መብቶች በችሮታ እየተሰፈረ ሲሰጥ፡……..ስንቱ ችግር ተዘርዝሮ ያልቃል ብላቹ ነው???አብዛኛው ሕዝብ ትውልድ ገዳይ ሕግ ሲወጣ “አህያም የለኝ ከጅብ አልጣላ” እያለ አገሪቷን የጅቦች አገር አደረጋት፡፡በዚህም ምክንያት መንግስት ሕዝቡን እየከፋፈለ ለመግዛት አመቺ ሁኔታ ተፈጠረለት፡፡በየአገሩ ያሉ የሕግ ጎዶሎዎች እኮ ተሰባስበው ኢትዮጵያ ላይ ነው የተጣሉት፡፡ከላይ ስማቸውን ያልጠቀሱ ፀሐፊ “መንግስት አሮጌ ቤቶቻችንን ብቻ ሳይሆን…..” ብለው ያሰፈሩት አዲስ አበባን ካለማወቅ የመጣ ነው፡፡ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት ያለው ቦታ ከታጠረ ስንት አመት ሆነው???ስራው እስከሚጀመር ድረስ እንኳን ድሆች ስንት ቤተሰባቸውን ያስተዳድሩበት ነበር???ናዝሬት ላይም በተመሳሳይ ሁኔታ ግንብ ገበያን መመልከት ይቻላል፡፡ሰዎችን የሰው ክብር ሳይሰጣቸው በኢኮኖሚ በቀላሉ ተጠቃሚ ሊሆኑበት ከሚችሉበት መሀል ከተማ አፈናቅሎ ወደ ከተማው ዳር ያለ ምንም ጥናት መውሰድስ ምን ይባላል??? ድሆችን አፈናቅሎ ገዢ መፈለግስ ምን ይባላል????ከተማዋ ለማን ልትሆን ነው???..............”መጀመሪያ የመቀመጫዬን “ እንዳለችው ዝንጀሮ ከላይ የተዘረዘሩት መሠረታዊ ጉዳዮች እልባት ማግኘት አለባቸው፡፡ከዛ በኋላ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ መነጋገር እንችላለን፡፡አዲሰ አበባው ነኝ ከአዲስ አበባ ወያኔ በግፍ ካፈረሰው ሰፈር፡፡

  ReplyDelete
 28. ቆንጆ ፅሁፍ ነው ልብ እና ህሊና ላለው፤ ግን ችግሩ ሳንባ ብቻ መሆናችን ነው፡፡

  ReplyDelete
 29. አምላካች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲተያስተምር በምሳሌ ነበር፡፡ ታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ ፅሁፎቹን ያቀርብ የነበረው በዲያሎግ መልክ ነበር፡ ወንድማችን ዳኒ ደግሞ በተረትና ምሳሌ ፡ ሁሉ በተሰጠው ፀጋ አይደለ የሚለው መፅሀፉ፡፡

  ReplyDelete
 30. it is really interesting idea

  ReplyDelete
 31. hirut You said well. I fully agree with you.
  those who say the jokes do not learn anything, I think they can not wait to go to war to kill as many souls as you could probably fix this by using their brain. brother Daniel, however, go ahead. You are teaching us a lot. God bless you.

  Sara

  ReplyDelete
 32. እነርሱ በዘመናቸው ኖረው በዘመናቸው መልካም የመሰላቸውን ሠሩ፡፡ ዛሬ ላይ ስናየው ያ ስሕተት ሆኖ ተገኘ፡፡ እኛም በዘመናችን ኖረን በዘመናችን መልካም የሆነውን እንሥራ፡፡ እነርሱ ወደኛ ዘመን መጥተው ሊኖሩ እንደማይችሉ ሁሉ እኛም ወደነርሱ ዘመን ሄደን ልንኖር አንቸልም፡፡ D/n Daniel,Egzyabher Yestlen...Yenafekege neger benore..habesahwoche yemnetebaberbet geze yalmenem mekefafel...abeet..menalebt?

  ReplyDelete
 33. አዲስ አበባው “ስንት እና ስንት ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብን የሚመለከቱ አገራዊ ጉዳዮች እያሉ በተረት ተረት ለውጥ ይመጣል ብሎ ማሰብ ምን ማለት ነው???”...ህእ..ወይስ እንዳንተ በሮሮ፣በብልግና፡ ብልግናው እንካን ካደክበት ከፈረሰው ሰፈርህ የወረስከው ነው የግል ባህሪህም ተጨምሮበት፡፡….ህእ …አንተ በምታቀርበው ፅሁፉ ነዋ ለውጥ የሚመጣው ፡፡ድንቄም አንተ ብሎ አስተያየት ሰጪ፡፡ፅሁፉ የሚያወራዉ በሰላምአብሮ ስለ መኖር እና ማደግ አንተ የምታወራው ስለ መሬት ሊዝ ጉዳይ፤፤አንተን ብሎ አስተያየት ሰጪ፤፤እንዲያዉም ይሄ ብሎግ አንተ የምትመጥነው መስሎ አልታየኝም፤ ዝም ብሎሰፈር ዉስጥ የሚወራ ሁሉ የሚወራ መሰለህ Be Rational

  ReplyDelete
 34. NICE DANI I APPRICIATE UR PERECPECTIVE ALWAYS GOD BE WITH U

  ReplyDelete
 35. Berketilen!
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 36. Ketesmamu zetegn(9)kita lebalenamist yebekal ale yagere sew.
  This is the starting point of civilization but i doubt in our people.

  ReplyDelete
 37. Thanks dn dani but you became completely towards the politics please write based on the holly bible.

  ReplyDelete
 38. “አዲስ አበባው” አፈርኩብህ!!

  ReplyDelete
 39. ለምን የመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርቶችን አታካትትም? ዳንኤል ትምህርቶችህንም እንወዳለን ተጨማሪ አስተያየት ነው

  ReplyDelete
 40. እኔ እና አንተ ነን መለወጥ የምንችለው፡፡ እኛ ከቀደምቶቻችን
  በዳዲ የተላለፈውን ልደግመው ወደድኩ በጎ በጎውን እንጂ ሌላውን የመውረስ ግዴታ የለብንም፡፡ እነርሱ
  በዘመናቸው ኖረው በዘመናቸው መልካም የመሰላቸውን ሠሩ፡፡ ዛሬ ላይ ስናየው ያ ስሕተት ሆኖ ተገኘ፡፡ እኛም በዘመናችን ኖረን በዘመናችን መልካም የሆነውን እንሥራ፡፡ እነርሱ ወደኛ ዘመን መጥተው ሊኖሩ እንደማይችሉ ሁሉ እኛም ወደነርሱ ዘመን ሄደን ልንኖር አንቸልም፡፡ ያኛውን ውድድር ተወው፡፡ አሁን እኔ እና አንተ በአዲስ ውድድር አዲስ ታሪክ እናስመዘግብ፡፡»ስማቸው ከአ.አ

  ReplyDelete
 41. እግዚኣብሔር ይባርክህ ወንድሜ፡ ታሪኩን ቀየርከው!በነበር እኮ በልቤ የከፈትኩት የቂም መዝገብ ሞልቶ ሌላ እንድከፍት ተገድጄ ነበር። ኣሁን ግን ኣበቃ!!!!

  ReplyDelete