Wednesday, November 30, 2011

እሳቱ ከሌለ ጢሱ አይታይም


click here for pdf 
ሰሞኑ ሀገራችን አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ለማዘጋጀት ሽር ጉድ በማለት ላይ ትገኛለች፡፡ አሥራ ስድስተኛውን የአይካሳ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ፡፡ ሀገሪቱ እንዲህ ያሉ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤያትን ማዘጋጀቷ ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ መልካም ገጽታዋን ለማስተዋወቅ፣ በጉባኤ ቱሪዝም የሚገኘው ገቢ፣ ከሚመጡ ባለሞያዎች ጋር የሚኖረው የዕውቀት ልውውጥ፣ የሚፈጠረው የገበያ እና የሥራ ዕድል፣ ሌሎችም፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ይህንን መሰል ጉባኤያት የሚያስከትሉት አሉታዊ ነገርም አለ፡፡ ቅርሶች ወደ ውጭ የሚወጡበትን መንገድ በመክፈት፣ ባህልን በማበላሸት፣ ዝሙት አዳሪነትን እና ቁማርን በማስፋፋት፣ ለትውልድ እና ሀገር መበላሸት ክፉ አስተዋጽዖም ያደርጋሉ፡፡

Monday, November 28, 2011


መጽሐፍ አዟሪው ሊቅ
 
            እንግዲህ መቃብር ጠንክረህ ተማር
            ድጓ ተሸክሞ መጣልህ መምር
           አራት ሰው ሞተ ተቀበረ ዛሬ
           ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ መዋሥዕት ዝማሬ
እነዚህን ግጥሞች ትዝ ያሉኝ አዲስ አበባ፣ ሃያ ሁለት አካባቢ "በታ" ሕንፃ ሥር ካለው ካልዲስ ቁጭ ብዬ ነው፡፡ ከፊቴ የመጽሐፍ ቁልል የተሸከመ ወጣት ቆሟል፡፡ ደጋግሜ መጽሐፍ ገዝቼዋለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን እነዚህን ዕውቀት የሚያከፋፍሉ ወጣቶችን ለመርዳት ስል በተቻለው መጠን ከእነርሱ መግዛት ደስ ይለኛል፡፡ ምን ዓይነት መጻ ሕፍት እንደምፈልግ ስለገባው እየመረጠ ማሳየት ጀመረ፡፡ ሁለቱን ገዛሁት፡፡

Thursday, November 24, 2011

የተሰደዱ ስሞች


(ክፍል ሁለት)
ባለፈው እትም በልዩ ልዩ የዓለም ከፍሎች ተዘውታሪ የሆኑትን ስሞች አንሥተን ነበር የተሰናበትነው፡፡ የኢትዮጵያውያንን ተዘውታሪ ስሞች በተመለከተ በቂ የሆነ መረጃ ማግኘት ቸግሮኛል፡፡ ምናልባት የስታትስቲክስ መሥሪያ ቤታችን ከሕዝብ ቆጠራ ያገኘውን መረጃ ተጠቅሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉትን የሴት እና የወንድ ስሞች እንዲነግረን አደራ እያልኩ መጠነኛ ፍንጭ የሚሰጡንን ብቻ እንጥቀሳቸው፡፡
አንድ «ስቱደንት ኦፍ ዘወርልድ» የተሰኘ ድረ ገጽ በመረጃ መረብ እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች በጥቅም ላይ የዋሉትን የኢትዮጵያውያንን ስሞች በመሰብሰብ በስፋት ጥቅም ላይ ውለዋል ያላቸውን የወንድ እና የሴት ስሞች እስከ አንድ መቶኛ ደረጃ ዘርዝሯቸዋል፡፡
በዚህ ድረ ገጽ ዝርዝር መሠረት በስፋት ጥቅም ላይ በመዋል ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ያለውን ደረጃ የያዙት የሴቶች ስሞች «ኤደን፣ ሣራ፣ ቤቲ፣ ሕይወት፣ ቤዛ፣ ሜሮን፣ ትእግሥት፣ ቃል ኪዳን፣ ሩት እና ሰላም» ናቸው፡፡ የወንዶቹን ስናይ ደግሞ «ዳንኤል፣ ሰሎሞን፣ ብሩክ፣ ዳዊት፣ ሄኖክ፣ ሳሙኤል፣ ያሬድ፣ አቤል፣ ሀብታሙ እና አሸናፊ» ናቸው፡፡

Wednesday, November 23, 2011

ወራጅ አለ

የኖኅ ርግብ
ከአራት ኪሎ በስታዲየም ወደ ሜክሲኮ በሚጓዝ ታክሲ ውስጥ ነኝ። በተሳፋሪ መቀመጫ ሁለተኛ ወንበር ላይ በግራ በኩል ተቀምጫለሁ። ብዙ ጊዜ የትራፊክ መጨናነቅ በሚስተዋልበትና ባቡር ጣቢያ ፊት ለፊት በሚገኘው መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደ ደረስን ከጎኔ የነበረች አንዲት ወጣት ባቡር ጣቢያ መድረስ አለመድረሳችንን ጠየቀችኝ። አኔም ሳናልፈው ጥሩ ሰዓት ጠየቅሽኝ በማለት በታክሲው በግራ በኩል ባለው መስኮት እያመለከትኩ ያውልሽ ደርሰናል አልኳት።

እኔ አመልካች ጣቴን ከመስኮቱ ሳላነሳ እኛ ባለንበት ታክሲ ውስጥ ያለውን ረዳት ሳይሆን በቀኝ በኩል ባለው መንገድ ታጥፎ ወደ ቸርችል ጎዳና በሚጓዘው ታክሲ ውስጥ ያለውን የታክሲ ረዳት የምትጠይቅ በሚመስል ድምጽ “ወራጅ አለ” ስትል ከድምጿ ቅጥነትና ኃይል የተነሳ ሁላችንም ደነገጥን። በተለይ እኔ…. እንዴት ብዬ ልንገራችሁ! በመጀመሪያ ስታናግረኝ የነበረው ለስለስ እና ዝግ ባለ ድምጽ ስለነበርና እንደዚያ ያለ ድምጽ በዚያ ቦታ ስላልጠበኩኝ ነው መሰለኝ ክው ነው ያልኩት።

Saturday, November 19, 2011

ለቤተ መጻሕፍትዎ


በኢጣልያ በረሃዎች
ሻምበል አብዲሳ አጋ በአርበኛነት ጀብዱ የሠራ ኢትዮጵያዊ ታሪክ
click here for pdf
  • ሁለተኛ እትም- 2004 ዓም
  • አሳታሚ- ጃዕፋር የመጻሕፍት መደብር
  • ዋጋ- 50 ብር
 ስለ አብዲሳ አጋ እሰማ የነበረው ሕፃን ሆኜ ነው፡፡ ይህንን መጽሐፍ ሳነብ ኀዘን ነበር የሚሰማኝ፡፡ ይህች ሀገር ግን ምን ዓይነት ሀገር ናት? እያልኩ ደጋግሜ እጠይቅ ነበር፡፡ መጽሐፉ ፋሽስት ኢጣልያ በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ግፍ ያሳያችኋል፡፡ ከኢትዮጵያ እስከ ሶማልያ፣ ከሶማልያ እስከ ጣልያን በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን መከራ እንደ ፊልም ታዩበታላችሁ፡፡ የነጻነት ዋጋው ምን ያህል እንደሆነ ትተምኑበታላችሁ፡፡ እነዚያ ወገኖች ለነጻነታችን የከፈሉትን ዋጋ እና እኛ በነጻነታችን የሠራነውን ሥራ ስትመዝኑት ታፍራላችሁ፡፡

Tuesday, November 15, 2011

ዝርዝሩ


እስኪ በከፍቾዎች ተረት በኩል አንድ ነገር እንይ፡፡
አንድ ሞኝ አሽከር የነበረው ሰው ነበር አሉ፡፡ ይኼ አሽከር አድርግ የተባለውን ካልሆነ በቀር አስቦ፣ አውጥቶ እና አውርዶ፣ ብሎም አመዛዝኖ የሚሠራው ሥራ አልነበረም፡፡ ምን ጊዜም የሚጠብቀው የጌታውን ትእዛዝ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ትክክል ነገር ማለት ጌታው ያዘዘው ሲሆን፣ ስሕተት ማለት ደግሞ እርሱ ያልነገረው ነገር ማለት ነው፡፡ ዓላማው ጥሩ ነገር መሥራት ወይንም አዲስ ነገር መሥራት ሳይሆን ጌታውን ማስደሰት ብቻ ነበር፡፡
ጌታው ከሳቀ ይስቃል፣ ካለቀሰ ያለቅሳል፣ ከተደሰተ ይደሰታል፣ ካዘነም ያዝናል፡፡ የወደደውን ይወድዳል የጠላው ይጠላል፡፡ ለርሱ የመደሰቱንም ሆነ የማዘኑን፣ የመሳቁንም ሆነ የማልቀሱን ምክንያት ማወቅ አይጠበቅበትም፡፡ ዋናው ነገር ጌታው መሳቁ ወይንም ማልቀሱ ነው፡፡ አንዳንዴ ሰዎች የሳቀበትን ምክንያት ሲጠይቁት «ጌታው ሳቁኮ አላያችሁም» ይላል፡፡ በዚህም የተነሣ ሰዎች «እንዳሉት»ብለው ይጠሩት ነበር፡፡

Monday, November 14, 2011

አቡነ አብርሃምን ሳውቃቸው


እኔ እና አቡነ አብርሃም የምንተዋወቀው ገና ወደዚህ መዓርግ ሳይመጡ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሳይሆኑ፣ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ሲማሩ ነው፡፡ ይበልጥ ያወቅኳቸው ግን ብዙ በሠሩበት እና ማንነታቸውንም ባስመሰከሩበት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አለቃነታቸው ነበር፡፡
የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ትምህርት ቤት ሲከፈት ከመድኃኒት ዘዋለ እና ከዳግማዊት ግርማይ ጋር የት/ቤቱ ቦርድ ሆኜ ሠርቼ ነበር፡፡ አቡነ አብርሃምን በሚገባ ያወቅኳቸው ያኔ ነው፡፡ እንደ አለቃ ይመራሉ፣ እንደ ባለሞያ ይሞግታሉ፣ እንደ አባት ይጋብዛሉ፣ እንደ ወንድም ስንጠፋ ይፈልጋሉ፣ እንደ ኃላፊ ይከታተላሉ፡፡
ትምህርት ቤቱን ለመስከረም ለማድረስ የነበረን ጊዜ ከሦስት ወር የማይበልጥ ነበር፡፡ ተማሪ መዝግበን፣ መምህር ቀጥረን፣ መዋቅር ዘርግተን፣ ቁሳቁስ አሟልተን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ አግኝተን ለማጠናቀቅ ሦስት ወር፡፡ መቼም በቦታው እርሳቸው ባይኖሩ ኖሮ ይሳካ ነበር ብዬ ለመገመት ይቸግረኛል፡፡

Friday, November 11, 2011

የተሰደዱ ስሞች

click here for pdf
በአዲስ አበባ ሲኤም አካባቢ በሚገኝ አንድ የግል ትምህርት ቤት የዐጸደ ሕፃናት በር ላይ ቆሜያለሁ፡፡ እንዴው አንዳች ነገር ገፋፋኝና በየበሩ የተለጠፈውን የተማሪዎች ስም ዝርዝር መመልከት ጀመርኩ፡፡ ቢያንስ በአንድ ክፍል በር ላይ እስከ ሃያ የሚደርሱ ተማሪዎች ስሞች ተለጥፈዋል፡፡
የአንድ የአምስት ክፍል ተማሪዎችን ስም ዝርዝር ስመለከት ከኢትዮጵያውያን ስሞች መካከል የተሰደዱ መኖራቸውን አየሁ፡፡ እነ ትርንጎ፣ ብርቱካን፣ ትጓደድ፣ ድንበሯ፣ ቻላቸው፣ እያቸው፣ ስማቸው፣ ውዴ፣ ሙሉነሽ፣ አየነው፣ ገበያው፣ ሙሀባው፣ አብዱል መጂድ፣ አብዱል ቀኒ፣ ገብረ መስቀል፣ ገብረ እግዚአብሔር፣ በላቸው፣ ደርበው፣ ጥሩ ወርቅ፣ የትም ወርቅ፣ የሚሉ ጥንታውያኑ ስሞች በዝርዝሮቹ ውስጥ የሉም፡፡
እነ ማርታ፣ ማኅሌት፣ አርሴማ፣ ጀሚላ፣ ሣራ፣ ማክዳ፣ አቤሜሌክ፣ ባሮክ፣ ሰሎሞን፣ ሐዊ፣ ሀቢብ፣ አዜብ፣ ግሩም፣ አትናቴዎስ፣ ቢንያም፣ የሚሉ ስሞች የዘመኑ ሻምፒዮ ናዎች ሆነው ይታያሉ፡፡

Wednesday, November 9, 2011

ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ


አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ከመቶ ዓመታት በፊት የሞራል እና የሥነ ምግባር ልዕልናን ከእምነት ተቋሞቻቸው ነጥቀዋል፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ በእምነት ተቋማቱ ውስጥ እና በእምነት መሪዎቹ ዘንድ የሚፈጸሙት ጥፋቶች፣ ኃጢአቶች እና ወንጀሎች የእምነቱ ተከታዮች ከሚሠሯቸው ይልቅ እየባሱ መምጣታቸው ነው፡፡
ሴትዮዋ ጉድጓድ ውስጥ ትወድቅና ትጮኻለች፡፡ አንድ ሰው ይሰማትና ይመጣል፡፡ እጅሺን አምጭ ብሎ እጇን ጎትቶ ሊያወጣት ሲሞክር እጇን ይገነጥለዋል፡፡ ሴትዮዋ ጉድጓድ ከመግባቷ ይልቅ የእጇ መገንጠል ይብስባታል፡፡ እናም «አውጣኝ ብለው ገነጠለኝ» አለቺ ይባላል፡፡ አውጭው ከጉድጓዱ ባሰባት፡፡
የሃይማኖት ተቋማት እና የሃይማኖት መሪዎች የማኅበረሰቡን ሞራላዊ እና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን የመጠበቅ፣ የማስተማር እና ለእነርሱም አርአያ ሆኖ የመገኘት ግዴታዎች አሉባቸው፡፡ ነገር ግን «ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡታል፣ ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡታል» እንደተባለው ራሳቸው የእምነት ተቋማቱ እና መሪዎቹ የችግሩ ሰለባዎች ሆነው ለማኅበረሰቡ አርአያ መሆን ሲያቅታቸው፤ ሕዝቡ በእነርሱ ላይ ያለው አመኔታ፣ እነርሱም በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ይሸረሸራል፡፡

Thursday, November 3, 2011

ጥርስ ወይስ እጅ - ማን ይቅደም ?


አሜሪካ ቨርጂንያ አሌክሳንድርያ ውስጥ ከሚኖር አንድ ወዳጄ ጋር ወደ አንድ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ሄድን፡፡ ይህ ወዳጄ እዚያ ነው የሚሠራው፡፡ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ እርሱ በሚሠራበት የእንግዶች ማስተናገጃ ቦታ (ፍሮንት ዴስክ ይሉታል) አንድ የርሱ ጓደኛ እየሠራ ነበር፡፡ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ እኔም ወዳጁ መሆኔን ነገረው፡፡ ያም ጓደኛው ሻሂ እንድንጋበዝለት ለመነን፡፡ እኛም ባንድ አፍ ብለን ሶፋው ላይ ዘና አለን፡፡
ያኔ ነው ይህ ወዳጄ ስለ ጋባዡ ጓደኛው የነገረኝ፡፡ ይህ ጓደኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነው፡፡ እዚህ ከትምህርት በሚተርፈው ጊዜ ነው የሚሠራው፡፡ ሌሎችም በዚህ መልኩ የሚሠሩ አሉ፡፡ የዚህኛውን ልዩ የሚያደርገው ግን ይህ ጓደኛው የሆቴሉ ባለቤት ልጅ መሆኑ ነው፡፡