to read in pdf, click here
(አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትምህርት ይሰጣል፡፡ እኒህ ምእመን ቁጭ ብለው ይሰማሉ፡፡ የሰባኪው ሁኔታ አልጣማቸውምና በልባቸው እንዲህ ያማርራሉ፡፡)
አምሳ ዳቦ ከመላስ አንደ ዳቦ መቅመስ አሉ፡፡ አሁን ይህንን ሁሉ ጥቅስ ከመዘርገፍ አንዱን ትንትን አድርጎ ቢያስተምረን አይሻልም፡፡ ስንት ሕፃናት አሉ፡፡ አረጋውያን አሉ፡፡ መጻፍ የማይችሉ አሉ፡፡ ምን ያደርጉታል አሁን፡፡ «ቀላል አይደለንም» ለማለት ካልሆነ በቀር፡፡
(አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትምህርት ይሰጣል፡፡ እኒህ ምእመን ቁጭ ብለው ይሰማሉ፡፡ የሰባኪው ሁኔታ አልጣማቸውምና በልባቸው እንዲህ ያማርራሉ፡፡)
«ምን ገባችሁ ገባችሁ ይላል፤ ይልቅ እንዲገባን አድርጎ አያስተምረንም፡፡ አሁን ኢየሱስ ከናዝሬት ወደ ገሊላ ሄደ ብሎ እልል በሉ ማለት ምን ማለት ነው፡፡ አሁን እኛ እልል የምንለው ገሊላ ስለ ሄደ ነው፤ ከናዝሬት ስለተነሣ ነው? ወይስ ስለሄደ ነው? እና ላይሄድ ኖሯል፡፡ ለምን ሄደ? እንዴት ሄደ? ሄዶ ምን አገኘን እያለ እንዲነግረን እንጂ ወደ ገሊላ መሄድማ እማሆይ አማረችስ ባለፈው ጊዜ ኢዬሩሳሌምን ሲሳለሙ ገሊላ ሄደው አልነበረም? ወይ አንተ ፈጣሪ፡፡
ልሂድ ልውረድ ልጄንም ላምጣው፣ እያሉ በርእስ መቀለድ ምን የሚሉት አባዜ ነው፡፡ ሰሞኑንማ የእብራይስጥ ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልጋችሁ ያንን ርእስ ካላደረጋችሁ ትታሠራላችሁ የተባላችሁ ነው የምትመስሉት፡፡
አምሳ ዳቦ ከመላስ አንደ ዳቦ መቅመስ አሉ፡፡ አሁን ይህንን ሁሉ ጥቅስ ከመዘርገፍ አንዱን ትንትን አድርጎ ቢያስተምረን አይሻልም፡፡ ስንት ሕፃናት አሉ፡፡ አረጋውያን አሉ፡፡ መጻፍ የማይችሉ አሉ፡፡ ምን ያደርጉታል አሁን፡፡ «ቀላል አይደለንም» ለማለት ካልሆነ በቀር፡፡
እኔ የምለው የስብከት ዓላማው ማስተማር መሆኑ ቀርቶ ማዝናናት ሆነ እንዴ፡፡ እነ ክበበው ገዳ ምን ሠርተው ሊበሉ ነው እንዲህ አገልጋዩ ሁሉ ቀልደኛ ከሆነ፡፡ ቅዳሴ ቢያልቅበት ቀረርቶ ሞላበት አሉ እማሆይ አማረች፡፡
ቆይ አሁን ምን አድርጉ ነው የሚሉን? ኑ ተባልን መጣን፤ አዋጡ ተባልን አዋጣን፤ ጹሙ ተባልን ጾምን፣ ጸልዩ ተባልን ጸለይን፣ ገዳም ሂዱ ተባልን ደርሰን መጣን፣ መጻፍ ግዙ አሉን ገዛን፣ ካሴት ግዙ አሉን ገዛን፣ እልል በሉ ተባልን አልን፣ አጨብጭቡ ተባልን አጨበጨብን፣ አሁንም ይመጡና ኃጢአታ ችሁ ነው ይህንን ሁሉ መዓት ያመጣው ይሉናል፡፡ እሺ ደግሞ ምን ቀረን?
አሁን ማን ይሙት ችግር ያለው ከኛ ነው ከእናንተ፡፡ የጥንት ሰዎች ዕድለኞች ሳይሆኑ አልቀሩም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ገድል እና ተአምር ሰምተው ነበር የሚመጡት፡፡ እኛ በናንተ ምክንያት ጭቅጭቅ እና ንትርክ ሆነኮ የምንሰማው፡፡ ስለ ጊዮርጊስ እና ተክለ ሃይማኖት፣ ስለ ጳውሎስ እና ጴጥሮስ፣ ስለ ክርስቶስ ሠምራ እና መስቀል ክብራ መስማት ትተን ስለ ሰባኪ እገሌ እና ሰባኪ እገሌ፣ ስለ እገሌ ቡድን እና እገሌ ቡድን ሆነኮ የምንሰማው፡፡ አይ ስምንተኛው ሺ፡፡
ስምንተኛው ሺ ቢሆን ነው እንጂ የማይጾሙ የሚጾሙትን፣ የማያስቀድሱ የሚያስቀድሱትን፣ የማይፋቀሩ የሚፋቀሩትን፣ ያልጸኑት የጸኑትን፣ የማይቆርቡ የሚቆርቡትን፣ ዓለምን ያልተው ዓለምን የተውትን፣ ያላመኑ ያመኑትን የሚያስተምሩት፤ ሌላ ምን ቢሆን ነው?
አሁን የት እንሂድ? ከዓለም ወደዚህ መጣን፤ ከዘህ ደግሞ ወዴት እንሂድ፡፡ እንዴው ለመሆኑ ስለ ፓትርያርክ፣ ስለ ጳጳስ፣ ስለ ሲኖዶስ፣ ስለ ካህን፣ ስለ ዲያቆን፣ ስለ ባሕታዊ፣ ስለ መነኩሴ፣ ስለ ሰባኪ ደግ ነገር የምንሰማበት ዘመን ይመጣ ይሆን፡፡ ስለ ገዳማት የምንሰማው ሁሉ ተራቡ፣ ተቸገሩ፣ አበምኔቱ ተማሪዎችን አባረሩ፣ መነኮሳቱ አበ ምኔቱን አባረሩ የሚል ሆነ፡፡ መቼ ነው ገድል ተጋድለው ተአምር አደረጉ የሚል የምንሰማው፡፡
ስለ ጳጳሳት የምንሰማው በራቸው ተደበደበ፣ በሑዳዴ ጾም ከበሮ አስመቱ፣ በሰው ሀገረ ስብከት ገብተው አተራመሱ፣ ቤት ገዙ፣ መኪና ገዙ፣ የሚል ሆነ፡፡ መቼ ነው እንደነ ዮሐንስ አፈወርቅ ለእውነት ተጋደሉ የሚል ወሬ የምንሰማው፡፡ ስለ ፓትርያርክ የምንሰማው እገሊት ትመራቸዋለች፣ ሐውልት ሠሩ፣ ውጭ ሀገር ሄደው ተዝናኑ፣ ገንዘብ አባከኑ፣ በዘመድ ሠሩ፣ የሚል ሆነ፡፡ መቼ ነው እንደ አትናቴዎስ ለሃይማ ኖታቸው መሥዋዕትነት ከፈሉ፣ እንደ ድሜጥሮስ ተአምር አደረጉ የሚል የምንሰማው፡፡ አልታደልንም መሰል፡፡
የጥንት ሰዎች በየ ደብሩ ሊቃውንቱ ምሥጢር እና ቅኔ ሲዘርፉ ነበር አልነበር እንዴ ያሉን፡፡ ምነው በኛ ዘመን ቅኔው ቀርቶ ሙዳየ ምጽዋት ብቻ ሆነ የሚዘረፈው፡፡ በየትምህርቱ ስንሰማ ታሥረው በግንድ፣ ተይዘው በግድ ተሾሙ አይደል እንዴ የምትሉን፡፡ ይኼ የነገራችሁን ነገር ተረት ቢሆን ነው እንጂ እንዴት በኛ ዘመን ሊለወጥ ቻለ ታድያ፡፡
አንዳንዴኮ እዚያው ተአምረ ማርያማችንን ብቻ እየሰማን፣ ከግብጽ በሚመጣ አንድ ጳጳስ እየተባረክን ውስጡን ሳናውቀው በቀረን ኖሮ ያሰኛል፡፡
እንዴው እነዚህ ሐዋርያት የሚባሉ ይህንን መጽሐፍ የጻፉት በምን ቀን ነው? የአባቶቻችን ተረት እንኳን ለዛ ነበረው፡፡ ማቴዎስ እንዲህ አለ፤ ሉቃስ ይህንን አለ፡፡ ጳውሎስ እንዲህ አለ፡፡ እሺ አለ፡፡ ደግሞኮ «አያችሁ» ይለናል፡፡ ምኑን ነው የምናየው፡፡ እግዚአብሔርንማ እንዳናየው አንተው ራስህ ጋርደህን፡፡ ምን አስተማረ? መባሉ ቀርቶ ማን አስተማረ ሆነ፡፡ ስንት ሰው ተለወጠ? መሆኑ ቀርቶ ስንት ሰው ተሰበሰበ ሆነ፡፡ እኛ የዚህን ዓለም የአለባበሰ ፋሽን እንድንተው አስተማራችሁን፡፡ እሺ ብለን ትተን ስንመጣ እናንተ የየቀሚሱን ዓይነት ፋሽን አመጣችሁት፡፡ ምንድን ነው ይኼ ሁሉ አሸንክታብ?
እናንተ መድረክ ላይ ገዝፋችሁ እየታያችሁ ጌታን በየት እንየው፡፡ የሚነገረው ስለ እናንተ ነው፡፡ «ጸጋ የበዛለት፣ታዋቂ፣ ልዩ፣ ልብ ሰባሪ፣አጥንት ነቅናቂ» ከበሮ ለምን ይጮኻል ቢሉ ውስጡ ባዶ ስለሆነ ነው አሉ አሉ፡፡ ተግባራችሁ ይነግረናልኮ፣ ብዙ ማስታወቂያ አያስፈልግም፡፡ እናንተ ስለ እግዚአብሔር ተናገሩ፣ እርሱ ስለ እናንተ ይናገራል፡፡ እናንተ ስለ ራሳችሁ ስለምትናገሩ ግን እርሱን ዝም አሰኛችሁት፡፡
እንዲያውም ብዙ ሕዝብ ከሌለ አንመጣም ትላላችሁ አሉ፡፡ ለመሆኑ ይኼ እናንተ የያዛችሁት መጽሐፍ ቅዱስ ጌታ አንዲት ሳምራዊትን ሴት ለብቻዋ ማስተማሩን አይናገርም ይሆን፡፡
ለመሆኑ ስብከት ለእናንተ ሥራ ነው ወይስ አገልግሎት? ይህንን ሕዝብ ምን እናቅርብለት ብላችሁ ትጨነቃላችሁ? ትጸልያላችሁ፣ ታነባላችሁ? ትጠይቃላችሁ? ወይስ? ምናልባት የማትኖሩበትን ስለምታስ ተምሩን ይሆን መለወጥ ያቃተን? የሌላችሁን ስለምትለግሱን ይሆን ብዛት እንጂ ጥራት ሊኖረን ያልቻለው?
ክርስቲያን ታደርጉናላችሁ ብለን ብንመጣ ቲፎዞ አደረጋችሁን፡፡ ለቲፎዞ ለቲፎዞማ አርሴናልና ማንቸስተር ነበሩልንኮ፡፡ ሲገባባቸው ተናደን ሲያገቡ ጨፍረን ቤታችን እንገባ ነበር፡፡ አሁንምኮ እንደዚያ አደረጋችሁት ሁሉም ቲፎዞ ሰብሳቢ ሆነ፡፡ የእገሌ ተከታይ ይባልልኛል፡፡ አስከትላችሁ አስከትላችሁ የት ታደርሱን ይሆን?
የታደሉት የዮሐንስ መጥምቅ ተከታዮች መጨረሻቸው ከክርስቶስ ጋር መገናኘት ሆነ፡፡ እኔ ዝቅ ዝቅ ልል እርሱ ግን ከፍ ከፍ ሊል ይገባዋል ብሎ አገናኛቸው፡፡ የርሱ ሥራ ድልድይ መሆን ነበረ፡፡ እኛ የናንተ ተከታዮችስ ታገናኙን ይሆን?
ቆይ ግን የሚያስፈልገንን ነው የምትነግሩን ወይስ የምትፈልጉትን? ልታሳውቁን ነው የምትመጡት ወይስ ማወቃችሁን ልትነግሩን፡፡ የምታስተምሩትንስ ታውቁታላችሁ ወይስ ታምኑበታላችሁ?
ቢቻል የምትታዩ ከዋክብት ሁኑልን፣ ባይቻል ደግሞ የማትታዩ ከዋክብት ሁኑ፡፡ ቢቻል አርአያችሁን ምሳሌያችሁን እንድንከተል የምትነግሩንን ብትኖሩት፣ የምታስተምሩትን በእናንተ ብናየው፤ ባይቻል ደግሞ የማታስተምሩንን በእናንተ እንዳናየው ብታደርጉ፡፡
እንዴው ግን እዚህ መሬት ስንቀመጥ የማናውቅ እንመስላችኋለን? እዚህ ቦታኮ በእድሜም በዕውቀትም የምንበልጣችሁ ሰዎች አለን፡፡ አጋጣሚውኮ ነው እናንተን ለመድረክ እኛን ለአግዳሚ ወንበር የዳረገን፡፡ ምናልባትም አንዳንዶቻችን በትኅትና ምክንያት እንጂ ርእሱን ስትናገሩ እንደ ነጣቂ ባለ ቅኔ መደምደሚያችሁንም እናውቀዋለንኮ፡፡ እኛኮ እየተማርን ያለነው ቃለ እግዚአብሔር ምግብ ስለሆነ ነው፡፡ ቃለ እግዚአብሔርኮ ዕውቀት ብቻ አይደለም ብለን ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገ ራል ብለን ነው፡፡
ተው ብታውቁበት ይሻላል፡፡ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣ ይችላል፡፡
(በዚህ ጊዜ ሰባኪው ትምህርቱን ጨረሰ፡፡ እልል ተባለ ተጨበጨበ)
ወይ ግሩም ቀበሌ ክርስትና ተነሥታ እዚህ መጣች፡፡ አሁን ደግሞ ሌላው ይመጣና ከዚያ የቀጠለ ይሁን፣ የበለጠ ይሁን፣ የተለየ ይሁን፣ ያንን የሚያፈርስ ይሁን፣ የሚቃወም ይሁን ደግሞ ያስተምራል፡፡ እንዴው ሥርዓት የሚያወጣ የለም፡፡ ምነው እንደ ቅዳሴው ግፃዌ ቢሠራለት፡፡ የትኛው ከየትኛው እንደሚቀጥል አይታወቅም?
ያም ይመጣና ጨፍጭፎን ጨፍጭፎን ጨፍጭፎን ይሄዳል፣ ይሄም ይመጣና ጨፍጭፎን ጨፍጭፎን ጨፍጭፎን ይሄዳል፡፡ ሁልጊዜ ተስፋ እንድንቆርጥ፣ እግዚአብሔር ቀጭ፣መዓት አምጭ፣ ተቆጭ፣ ብቻ ነው እንዴ? መሐሪስ አይደለም፣ ይቅር ባይስ አይደለም፣ ተስፋ ሰጭስ አይደለም፡፡ አንዳንዴኮ የሰባክያን እግዚአብሔር የተለየ እግዚአብሔር ሳይሆን አይቀርም፡፡ እናንተን ዝም ብሎ እኛን ብቻ የሚቀጣበት ምክንያት ምንድን ነው?
ችግሩኮ አንደኛው ሰባኪ ሌላው ሲያስተምር አይሰማም፡፡ ሊጨርስ ሲል ይመጣና የተለየ መስሎት ያንኑ ደግሞ ያስተምረናል፤ የባሰው ደግሞ የሚቃወም ነገር ይነግረናል፡፡ እኛም ለሁሉም እናጨበጭባለን፡፡
(ሰባኪው ስለ ራሱ መናገር ሲጀምር) በል ስለ እግዚአብሔር የምትነግረን መስሎኝ ነበር እንጂ ስላንተማ ብዙ ዐውቅ የለ ብለው ምእመኑ ልባቸውን ዘጉ፡፡
እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቦና ይስጥ ቃለ ሂወትን ያሰማልን ዳኒ
ReplyDeleteBETAM YAMRALG GIN DANI ALZEGEYEHIM? AHUN AHUNMA SBEKIW RASU YIMETANA "BZU SEBAKYAN ENDIH ENDIH YLALU.MECHE NEW YEMNSTEKAKELEW?...ENE GIN ENDEZA AYDELEHUM BLO MELKEA RAS TENAGRO YIHEDAL" ENDIH ENDIH AYNET BIBEZULN.BETELEYIM BESIBKETU DEREJA ATDEGMIM ENDE?
ReplyDelete"... ያመኑ ያላመኑትን የሚያስተምሩት ..." yemilew " ...ያላመኑ ያመኑትን የሚያስተምሩት ..." tebilo yistekakel.
ReplyDeleteእንደው ምንላድርግህ የኔል የልብአውቃ ሰባኪነን ባዮች መድረክ በያዙ ቁጥረ ላንቃቸው እስኪቀደድ ባዶጩሆትን እየጮሁ ያልበላንን እያከኩየሚያደናቁሩን በዝተው ተቸግረናል እንዲህ እንዳንገፈገፉን መድረሻእንዳጣን ንገርልንእንጅ ዳሩ ምንያደርጋል አያዩት አያነቡት እነሱ መድረክ ሲይዙ እንዴት እንደሚጮሁብን ምንየተለየ ቀልድ እንደሚቀልዱብን ምንየተለየ ልብስ ለብሰው ከሌላው ጎልተው እንደሚታዮ ነው ጭንቀታቸው መደርደሪያ ሙሉመጽሀፍ ይሄም አለን ይሄም አለን ለማለት አዋቂለመባል ይደረድሩታል እንጅ ምንእንደሚል አያዉቁት እንዳልከው እንደከቦሮውናቸው! ልቡናቸውን ይክፈትልንና በማስተዋል እንዲሆኑ ያድርግልን ለኛም ትእግስቱንይስጠን!
ReplyDeletebatame yegaremale.wanawe nagare BATA KERSTIANE enehede lage yatayane LAAMELAKACHENEMA...becha laagalegayoche lebe yesetachohe..dn daniel eske yaagalegayocheonome rooroo asamane.egehe yebarake
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ጥሩ ተመልክተኽዋል የሚገርመው ዛሬ ስለ ባህታውያን እያሰብኩኝ ነበር መቸ ነው እግዚአብሄር ምህረት አድርጎላችኋል ያሚለውን ቃል የሚነግሩን ሁል ጊዜ መአት መጣ ብቻ ነው ትምህርታቸው ያሁኑ ይባስ በየእለቱ የሚያስተምሩን ሰባክያን ደግሞ ከተስፋ ይልቅ ተስፋ መቁረጥን ያስተምሩናል የቅዱሳንን ገድልና ትሩፋት የእግዚአብሄርን ቸርነት ማን ያስተምረን?
ReplyDeleteDn Daniel you are juging yourself, no one else.
ReplyDeleteThanks Dn.O My God i do no why i hate that "KEMIS" Ahunima all preachers start having it in diff color.Please write detial info about it. Have hard time to accept it as ours.I do no who should have it zemari,dn, kese , papas or who it is confusing tomorrow it may be for femail zemarian too.I think it is to make themselves noticable among others i might be wrong but need details.I miss those who preachs with "NETELA"
ReplyDeleteIts very good.It is a time to correct it.A monk who lives with Abba Anthony in a same monastery said to Abba Anthony"pray for me."and Abba Anthony said to him,"i wiil have no mercy upon you,nor will God have any,if you yourself do not make an effortand if you do not pray to God." what i want to say is it starts from us.so we have to pray to God to make the rest time good. thank you.kale hiwot yasemaln.
ReplyDeleteበአውነት ነገሩ ዘመኑን የዋጀ ነው::
ReplyDelete¨ስምንተኛው ሺ ቢሆን ነው እንጂ የማይጾሙ የሚጾሙትን፣ የማያስቀድሱ የሚያስ ቀድሱትን፣ የማይፋቀሩ የሚፋቀሩትን፣ የጸኑ ያልጸኑትን፣ የማይቆርቡ የሚቆርቡትን፣ ዓለምን ያልተው ዓለምን የተውትን፣ ያመኑ ያላመኑትን የሚያስተምሩት፤ ሌላ ምን ቢሆን ነው?¨
የህይዎት ቃልን ያሰማልን::
This is great article, nice view. Amilak lehulachinim mastewalun yisten. Beyibelt degimo le Sebakiwoch, Zemariyan, Abatoch.
ReplyDeleteDani Kalehiwot Yasemalin. Egiziabiher regim yeagoligilot edime yistih.
enagnam ende setiyewa yasebinibet ken ale gin demo awititen tewun sanil eskahun alen sinitochu sebakiyan yihenin tsihuf yanebuti yihon anibewis yimaru yihon sinit miemenanis ekelai zare enitin betekiristiyan yasitemiral maletachewin titew ye egiziabiher kal yisemal bilew yihedu yihon? yihenin temirebetalew. yibel..........
ReplyDeleteወዮ ለኔ
ReplyDeleteNice! please write again and again simillar topics!! It quinched me! God bless you!!!!
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ጥሩ ምክር ነው
ReplyDeleteከርዕሱ በስተቀር ምርጥ ጽሑፍ ነው፡፡ በረከትን ድልልን፡፡ ርዕሱ ግን ‹‹ የአንድ ምዕመን…›› ሳይሆን ‹‹የኢትዮጵያውያ ምዕመናን…›› ቢባል ተገቢ ነው !! ችግሩ ከ ‹‹አንድ›› ምእመን በላይ የሚሊዮኖች ምእመናን ምሬት ሆኗል እኮ !!
ReplyDeletemecha yehon?wedshew metqom aqmen raschenee yemenay.ye zewater helme mecha yehon emnet abetoch tesmametou yemenay.be ahouno zemen benasho mernat chelat wedal tefat eyageban new.leahoun menam layemasel yechalae nage letweld men yehon yemrakoeb,melayayet....
ReplyDeleteebakh wendm yetrrqouten bego kemasbout gar honh ande endahonu argo.ant setansa egzabehar endameradh amenaleh.end abemalek ye ethiopian tefat ayasyen gat.
Selam. Here you go again with bad mouthing about the Fathers of our Church. Before we point fingers at others, why can we begin to examine our own faults? How is it that it come so easy for you to condem others? I understand that our time (zemenachen) is not so bright however let us only focus on the words of GOD instead of demenizing the Fathers of our Holy Church. Stop with your politics and preach the word of GOD! Amen. Teach me how to become a better Christian.
ReplyDeleteThank you for your posts. However, I would like you to think about how you would feel if a husband discusses his private affairs about his wife, his children, etc..or if a child tells the world about the weaknesses of his father. I believe that if the husband is not willing to be discrete about his issues at home, and does not respect his spouse, why should the listner or the enemy? As a Deacon of the Church, it is not your place to discredit the Patriarch of our Church. Afterall, I thought that a higher positions are only given by GOD, and only to be judged by GOD. Think about it...
ReplyDeleteክርስቲያን ታደርጉናላችሁ ብለን ብንመጣ ቲፎዞ አደረጋችሁን፡፡ ለቲፎዞ ለቲፎዞማ አርሴናልና ማንቸስተር ነበሩልንኮ፡፡ ሲገባባቸው ተናደን ሲያገቡ ጨፍረን ቤታችን እንገባ ነበር፡፡ አሁንምኮ እንደዚያ አደረጋችሁት ሁሉም ቲፎዞ ሰብሳቢ ሆነ፡፡ የእገሌ ተከታይ ይባልልኛል፡፡ አስከትላችሁ አስከትላችሁ የት ታደርሱን ይሆን?
ReplyDeleteYibarikih dani KHY.
ዲ/ን ዳንኤል ቃለሂወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteAA From AA
ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ከምዕመኑ ምንም ችግር የለም ችግሩ ሰባኪነን ብለን መድረክ የተቆናጠጥነው ነን፡፡ ቁጭ ሲል መድረክ የሚያምረው ሲቆም የሚደናገር በዝቶ ነው አሉን መምህራችን መምህር ደጉ፡፡ ቲዮሎጂ መንገድ የሚያሳየን እንጂ ጠቅልሎ ዕውቀት የሚሰጥ አይደለም፡፡ የበለጠ አንድንማር እንድንመራምር የሚያደርገን መሆኑን መረዳ አለብን አብነት የምናደርገው መምህር ፈልገን የበለጠ ማስፋፋት አለብን፡፡ ቲዮሎጂ ትምህርት በራሱ ችግር የለበትም ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ፡፡ ችግሩ ኮሌጁ የሚያስገባበት መስፈርት የላላ መሆኑ በተለይም በቀኑ ክፈለ ጊዜ በዘመድ አዝማድ ስለሆነ በቤተክርስያን ላይ ግዙፍ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ ድብቅ ዓላመቸውን ይዘው የመጡ ፈቃዳቸውን አግንተው በቤተክርስቲያን ስም እየነገዱ ነው፡፡
ReplyDeleteየህዝብን የዉስጥ ጩህት ሰባኪነትህ ሳያጋድል እዉነትን መግለፀ ዳኒ ልዩ ነው እላለው
ReplyDeleteሰባኪ የተባሉት በተራዉ የተሰበከዉ ህዝብን ቢያዳምጡት ብዙ ትምህርት ያገኙበት ነበረ
ReplyDeleteእንዴው ግን እዚህ መሬት ስንቀመጥ የማናውቅ እንመስላችኋለን? እዚህ ቦታኮ በእድሜም በዕውቀትም የምንበልጣችሁ ሰዎች አለን፡፡ አጋጣሚውኮ ነው እናንተን ለመድረክ እኛን ለአግዳሚ ወንበር የዳረገን፡፡ ምናልባትም አንዳንዶቻችን በትኅትና ምክንያት እንጂ ርእሱን ስትናገሩ እንደ ነጣቂ ባለ ቅኔ መደምደሚያችሁንም እናውቀዋለንኮ፡፡ እኛኮ እየተማርን ያለነው ቃለ እግዚአብሔር ምግብ ስለሆነ ነው፡፡ ቃለ እግዚአብሔርኮ ዕውቀት ብቻ አይደለም ብለን ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገ ራል ብለን ነው፡፡
የአሲሲው ቅዱስ ፍራንሲስ
ReplyDelete“Preach always. And if necessary use words.”
“ወንጌልን ዘወትር ስበኩ፡፡ አስፈላጊ ሲሆንም መናገርን ጨምሩበት፡፡” ማለቱ ይጠቀስለታል፡፡
አንድ ከአንድ ሀገር ላይ የ 0.8 በመቶ ብቻ ቁጥር ያላቸው ምእመናን ሊቀ ጳጳስ ደግሞ በአንድ ወቅት “ቤተክርስቲያኗ የምእመናን ቁጥር እንዲበዛላት” በሚል ሰበብ ልክ አሁን በእኛ ቤተክርስቲያን እየተደረገ እንዳለው ወጣቶችን የስብከተ ወንጌል ኃላፊነት የሚያሸክም ዕቅድ በአንዳንድ ሰዎች ሲቀርብላቸው የሚከተለውን ብለው ነበር:- “የሰው እጥረት የለብንም፡፡”
ቃለ ህይወት ያሰማልን በጣም የ ማመስግንህ:: ይህ ለስባኪ ብቻ ሳይሆን ለቤተክርስቲያናችን ይጠቅማል ሰሚ ካለ::
ReplyDeleteMamush,MN
“እናንተ መድረክ ላይ ገዝፋችሁ እየታያችሁ ጌታን በየት እንየው፡፡ የሚነገረው ስለ እናንተ ነው፡፡ «ጸጋ የበዛለት፣ ታዋቂ፣ ልዩ፣ ልብ ሰባሪ፣ አጥንት ነቅናቂ» ከበሮ ለምን ይጮኻል ቢሉ ውስጡ ባዶ ስለሆነ ነው አሉ አሉ፡፡ ተግባራችሁ ይነግረናልኮ፣ ብዙ ማስታወቂያ አያስፈልግም፡፡ እናንተ ስለ እግዚአብሔር ተናገሩ፣ እርሱ ስለ እናንተ ይናገራል፡፡ እናንተ ስለ ራሳችሁ ስለምትናገሩ ግን እርሱን ዝም አሰኛችሁት፡፡ . . . . . (ሰባኪው ስለ ራሱ መናገር ሲጀምር) በል ስለ እግዚአብሔር የምትነግረን መስሎኝ ነበር እንጂ ስላንተማ ብዙ ዐውቅ የለ ብለው ምእመኑ ልባቸውን ዘጉ፡፡”
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይጠብቅህ፣ ይባርክህ ይቀድስህም፡፡ እግዚአብሔር አንተን ሚተካ ሰው ሳያዘጋጅ በሕይወት ዘመኔ የአንተን ክፉ ነገር አያሰማኝ፡፡ ማስተዋል ከተባለ እንዲህ ያስተውሏል፡፡ ዳኒ እጅግ በጣም የሚደነቅ አስተዋይነት ነው፡፡ የልብ አውቃ ይሏል እንዲህ ነው፡፡ የተረዱትን፣ የተገነዘቡትን፣ ያስተዋሉትን በሚጠቅም አቀራረብ አዘጋጅቶ ግራ የተጋቡ ሕጻናተ አእምሮ ምእመናነ ክርስቶስን ማስገንዘብና ራሳቸውንም እንዲጠብቁ ማድረግ ደግሞ ታላቅ አርአያነት ያለው ነው፡፡
እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን፤ አንተንም በእድሜ፣ በጸጋ በጤና ይጠብቅልን፡፡
ምነው በኛ ዘመን ቅኔው ቀርቶ ሙዳየ ምጽዋት ብቻ ሆነ የሚዘረፈው፡፡
ReplyDeletewhat are u trying to say?. u are one of them, pls dont judge....
ReplyDeletetiru tegsats new!!!!
ReplyDeleteTnx! sile rasu sayhon sile kiristos yemeyasitemir memihir yesiten bilen lentsely yegebal.
ReplyDelete"ስምንተኛው ሺ ቢሆን ነው እንጂ የማይጾሙ የሚጾሙትን፣ የማያስቀድሱ የሚያስቀድሱትን፣ የማይፋቀሩ የሚፋቀሩትን፣ ያልጸኑት የጸኑትን፣ የማይቆርቡ የሚቆርቡትን፣ ዓለምን ያልተው ዓለምን የተውትን፣ ያላመኑ ያመኑትን የሚያስተምሩት፤ ሌላ ምን ቢሆን ነው?" ግሩም እይታ ነው።
ReplyDeleteዳኒ ቃለ-ህይዎት ያሰማህ. ግን ለምን በኔ ትፈርዳላችሁ? እናንተ አይደላችሁ ያበላሻችሁኝ. ስናገር ሰማችሁ.. አመናችሁኝ ስዋሽም አልመለሳችሁኝ. አታውቁኝም እንዳልል አብረን አድገን.. መቼ አስተዋላችሁ አብሮ ከማጨብጭብ በስተቀር ለምን እንዴት ወዴትስ ብላችሁ ታውቃላችሁ? አሁን ዳኒ ሲናገር አብሮ መናገር ምንድን ነው...ልጅ ያባቱን ፊት ከለመደ ገና ከኪሱ የገባል የናቱን መቀንትም ይቀጥላል.."በእንቁላሌ በቀጣሽኝ.." አይደል. ማንስ ተቆጣኝ.. ስለተኛችሁ ገና ብዙ አደርጋለሁ ከማውራት በቀር ያለፈ ምን ሰራችሁ ...ልብ ካለህ ለሃይማኖትህ ቁም ስሳሳት ተው በለኝ ባልሰማህ በአቆአምህ ጽና በቃ....ለምን ይሉኝታ ይዝሃል ዛሬ ነው የምታውቀኝ በልብህ ስታማ ቆይተህ ዳኒ ሲናገር ተደርበህ ትናገራለህ....ለነገሩ አሁንም እዛው ነህ እውን አባትህ አንተን ልበቢሱን ወለደ
ReplyDeleteMASETAWALE YESETACHOHE.AMEN balo sebakeyan bamawake badeferate balamawake basehetate EGIZEABEHARENEM memanonem yasazanachohe
ReplyDeleteለመሆኑ የእኛ ሚና ምንድን ነው? መቆርቆር? መቀስቀስ/መቆስቆስ/? መጦመር?መጦማመር፤ ጥናትና ምርምር ማድረግ? ማንበብ? ብዙ መፍትሄ የሚሆኑ በርካታ ነገሮችን ለማየት፤ ለመስማትና ለማንበብ እድል ገጥሞናል። እኔም ይሁን ቤተክርስትያናችም አልያም የሁላችን ህይወት የሚፈልገው ግን የቤተክርስትያናችንንም ይሁን የህይወታችንን ትንሳኤ ማየት ነውና ምን እናድርግ? እንዴት ተደራጅተን እንጸልይ ወይ እንስራ? ችግሩን እያወቅነው መፍትሄ ማጣታችን ለኔ የዘወትር እንቆቅልሽ ነው? ማን መቼ እንደሚፈታው አላውቅም? እግዚአብሄር ሊፈታው እንደሚችል ጽኑ እምነት ቢኖረኝም ዉሃው ወይን እንዲሆን ደቀመዛሙርቱ ታዘው እንደሞሉትና እርሱም እንደቀየረው፤ እንደደቀመዛሙርቱ የእኛ ሚና ምንድን ነው? እባክህ ዲ/ን ዳ/ል ወደ ተግባራዊ የለውጥ ነውጥ አመጣጥና አፈጻጸሙን ከእውነተኛዎቹ እረኞች ጋር ሆነህ እንዴት በረታችንን እንጠብቃት? እንጠራት? በሚለው ሀሳብ ላይ የግልህን ጥረት አድርግ። እንደባህላችን የደቦ ስራ እንዴት በችግሮቻችን ላይ በጥናትና ጸሎት ላይ የተመሰረተ የለውጥ ንቅናቄ እናድርግ? ያለማጋነን እኔ መፍትሄ በማይሆኑ ነገሮች ምክንያት ነፍሴ ደክማለች። ከምንጻጻፈው የዘለለ ስራ መሰራት ይኖርበታል።
ReplyDeleteአግዚአብሔር ይባርክህ ዳንኤል :: ዋናዉን የስብከት አላማ የሳቱ ስለሆኑ አይገርመኝም:: ሰው አንዲድን አንጂ አንዲጠፋ ይሰበካል ወይ? ቆይ ግን በመጮህ አግዚአብሔር ይገኛል አንዴ? በጣም የሰለቸኝ ነገር ጩሀታቸው ነው:: አባቶቼ ያስተማሩኝ ፍቅር የተሞላበት የለሆሳስ ድምፅ ነው:: ለንገገሩ ለማስተማር ሳይሆን አላማቸው ለማደናገር ነው:: የራሳቸው ሕይዎት ስለተዘበራረቀ የሌላዉም ሂዎት አንደነሱ አንዲሆን ይፈልጋሉ አንጂ የአግዚአብሔር ሰው አንደዚህ አያስተምርም:: አዉነት ለመናገር ካፋቸው ለዛ የሌለው ደረቅ ቃል አኮ ነው የሚወጣው:: ይህ ደግሞ ሕይወታቸው ደረቅ አንደሆነ ያመለክታል:: ስለዚህ መጀመሪያ የራሳቸዉን ሂዎት ዘወር ብለው ይመልከቱት:: "ለሌላው መሰናክል ከምትሆን ባንገትህ ላይ የወፍጭ መጅ ታስሮ ወደ ትልቅ ባህር ብትጣል ይሻልሃል" አንደተባለ:: ለመፅናናት ሂጄ ጭራሽ ብሶብኝ አመጣለሁ:: ምናለ አንድ ቀን አንቁአን ስለአግዚአብሔር ቸርነት አና ምህረት ቢነግሩን::
ReplyDeletesolution, solution, what we need.
ReplyDelete12፡00 / Local Time /
ReplyDeleteምእመናን
እንደምን ከረማችሁ ?
እንደምን ሰነበታችሁ ?
እንደምን ዋላችሁ ?
በጥበቃው ሳይለየን በቸርነቱ ጠብቆ በዚህ በተቀደሰ የቅድስና ስፍራ ያሰባሰበን የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመስገን ፡፡
አሁን ይህንን ስብከት ስንሰማ ያዘነ ካለ ይጽናናል ፣ የደከመ ካለ ይበረታል ፣ የወደቀ ካለ ይነሳል ፣ የተሰበረ ካለ ይጠገናል ፣ የተራበ ካለ ይጠግባል ፣ የተጠማ ካለ ይረካል፡፡
የዚህ ስብከት አላማ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈውን ቃል ምእመናን በሚገባ እንዲረዱት ተረድተውም እንዲፈፅሙት ማመላከት ነው፡፡
12:20
ምዕመናን ከትምህርታችን ጋር የሚሄድ አንድ መዝሙር እንዘምራለን፡፡ እባካችሁን ሰርግ ቤትና ጭፈራ ቤት ከምናጨበጭብ ለእግዚአብሔር ክብር እናጨብጭብ ቢቻል ተነስተን እንዘምር ፡፡ ወገኖቼ መዝሙር ስንዘምር እንደ ጳውሎስና ሲላስ ከልብ እንዘምር እስራታችን ይፈታል ፣ ተስፋችን ይቀጠላል፡፡ ይኸውላችሁ ጭብጨባ ለሰይጣን ጥፊ ነው፡፡ በደንብ ዘምሩ…
12፡30
ምእመናን ዘምሩ ልልልልልል የመጨረሻውን ስንኝ ሶስት ጊዜ እንደግመዋለን
12፡45
ምእመናን አሁን ወደ ስብከት እንሄዳለን፡፡ አደራችሁን ጊዜ የእግዚአብሔር ነው ሰው መሸታ ቤት እንኳን ያመሽ የለ ልጆች ያሏችሁ ለድንግል ማርያም አሳልፋችሁ ስጡ ፈጣሪ ይጠብቃቸዋል ፣ ክፉ ባል ክፉ ሚስት ያሏችሁ እዚህ ቆይታችሁ ስትሄዱ ሰላም ሆነው ይጠብቋችኋል፡፡
12፡55
ምእመናን የሚያስተምር ፈጣሪ ነው የኔን ደካማነት አትመልከቱ እኔ ሃጢአት እንኳን ስሰራ ብታዩ ቃሉን ብቻ ተቀበሉ፡፡ ድንግል ማርያም የሚስጥር መዝገብ ነችና ምስጢሩን ትግለፅልን፡፡ ቅዱሳን በአማላጅነታቸው አይለዩን፡፡ ስለኔ ስለደካማው ደግሞ ፀልዩልኝ፡፡
01፡05
ማስታወሻ የያዛችሁ ማስታወሻችሁን አዘጋጁ ፡፡ በቃል ያለ ይረሳል በመጽሀፍ ያለ ይወረሳል ፡፡ አደራችሁን በሚቀጥለው ስትመጡ ሁላችሁም ማስታወሻ ደብተራችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ፡፡ አያችሁ ምእመናን እርግጠኛ ነኝ መቼም እዚህ ውስጥ DV ያልሞላ የለም፡፡ እንዴው የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ DV ቢወጣላችሁ ማስታወሻ ደብተራችሁ ይጠቅማችኋል፡፡
01፡15
እንግዲህ ባለችን አጭር ሰዓት ፈጠን ፈጠን አድርጌ አስተምራችኋለሁ፡፡
ምእመናን የትምህርቱን ርዕስ ከኔጋር ጮክ ብላችሁ 3 ጊዜ ትላላችሁ
01:30
ወደ ትምህርታችን እንሔዳለን
ወደ ቤት ነው ወይስ ወደ ትምህርት ? ? ? ? ?
አልቅሰን አይወጣልን ነገር እንዲህ የልባችንን እየተነፈስክልን እንባ እያነቀንም ቢሆን እናንብብ እንጂ . . . . . . . . ሳነበው ውስጤ ተነክቷል ላለማልቀስ ታግያለሁ . . . . ለረጅም ሰአት ዝም ብዬአለሁ. . . አይ ፈጣሪ መቼ ትሰማ ይሆን????????????????????????????????????
ReplyDeleteየሚሰብክ ሁሉ ገዝፎ ሳይሆን ጎንበስ ብሎ (በትህትና፣ በለዛ፣ሲቆጣም ከምሩ) ይስበክ፣ እንደ ቅዱስ ዮሀንስ፡፡ እርሱ ጎንበስ ካላለ ጌታን ማየት “በፍጹም” አንችልም፡፡ ምክኒያቱም “ጌታ” አለም ሁሉ የማይበቃዉ ግዙፍ ሆኖ ሳለ፣ ነገር ግን የትሁቶች ሁሉ ትሁት በመሆኑ እራሱን በኛ መጠን አቅርቦ፤ ይባስ ብሎም የተማሪዎቹን እግር ለማጠብ ጎንበስ በማለቱ ነው፡፡ ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል፡፡
ReplyDeleteNever been late for anything.
ReplyDeleteHello Guys, Dani has wrote what he believes is wrong and which certainly needs urgent attention. And we should understand that it has never been late to start change to make difference. Daniel has told us the current situation (the truth). Us, can we start at least with: "by not supporting the wrong doings"? Of course it will be great if we could stand for the truth, but some people like me might not be privileged for such actions rather distractions "አለመታደል ሆኖ አንዳንዶቻችን መልካም ሥራ መሥራት አይደለምና ከመጥፎ ድርጊቶች መታቀብ አልቻልንም::"
So my message to Anonymous (October 13, 2011 11:06 AM) and others is that writers mainly play a role of bringing something into attention of the public. Moreover, show the people a different view (ምልከታ) of the thing. In this regard, Daniel is successful and probably spoke what was in every Ethiopian Orthodox followers. Solutions can be put into practice by whoever person is. For certain situations like this one, I believe that the first solution is "CHANGE WITH IN OURSELVES".ዳዊትስ ቢሆን "ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።" መዝ 141፡4
I promised to myself not to be "ቲፎዞ" anymore, hope others can do this. To make this happen may the grace and blessing of the Almighty GOD be with us as always, AMEN.
The Hawassawu
የሚሰብክ ሁሉ ገዝፎ ሳይሆን ጎንበስ ብሎ (በትህትና፣ በለዛ፣ሲቆጣም ከምሩ) ይስበክ፣ እንደ ቅዱስ ዮሀንስ፡፡ እርሱ ጎንበስ ካላለ ጌታን ማየት “በፍጹም” አንችልም፡፡ ምክኒያቱም “ጌታ” አለም ሁሉ የማይበቃዉ ግዙፍ ሆኖ ሳለ፣ ነገር ግን የትሁቶች ሁሉ ትሁት በመሆኑ እራሱን በኛ መጠን አቅርቦ፤ ይባስ ብሎም የተማሪዎቹን እግር ለማጠብ ጎንበስ በማለቱ ነው፡፡ ጌታኮ ሲቆጣም ሊገስጸን ነው ጅራፍ ያነሳው፤ የምናደርገውንና ያለንበትን ቦታ እንኳን ስለማናውቅ፡፡ መቅሰፍት ቢደርስብንም እኮ ሀጢያታችን ራሱ እንጅ ጌታ ያመጣብን አይደለም፡፡ በንስሀ ብንመለስ ግን ሀጥያታችን ሊያመጣብን የነበረውን መቅሰፍት እርሱ ይመልስልናል፡፡ አንድ ጊዜ ብቻም አይደለም፤ ደጋግሞ ይምረናል፤ ስለምንረሳ ነው እንጅ ደጋግሞ ሲምረንም አይተናል፤ ምህረቱ፣ አዛኝነቱ ወሰን የሌለው ነውና፡፡ ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል፣ በዚህኛው ጽኁፍ እግዚአብሄር ፈቅዶልህ ያስተማርከን ነገር በጣም ደስስ ይላል፡፡ እግዚአብሄር ደስ ያሰኝህ፣ እኛን እንዳስደሰትከን፡፡
ReplyDeleteእውር እውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ገደል ... ። ፅድቅን ለማስተማር እውነትን ማወቅ ያስፈልጋል። በአሉአሉ የገደል ማሚቱ መሆን ህይወት አያስገኝም።
ReplyDeleteindih neberku leka
ReplyDeleteሁሌም ይህን ነገር አስበው ነበር፡፡
ReplyDelete"......እግዚአብሔር ቀጭ፣መዓት አምጭ፣ ተቆጭ፣ ብቻ ነው እንዴ? መሐሪስ አይደለም፣ ይቅር ባይስ አይደለም፣ ተስፋ ሰጭስ አይደለም፡፡ አንዳንዴኮ የሰባክያን እግዚአብሔር የተለየ እግዚአብሔር ሳይሆን አይቀርም፡፡"
D.Danial Egzeabhar Edmahin yarzemew
ReplyDeleteእግዚአብሔር የሚወዳቸው አገልጋዮች ቢኖሩ!
ReplyDeletewhy guys are created with big mouth and the people do not internalize and stand for the truth?....... thank you Daniel!!!
ReplyDeleteyikrta adrigulign ene eyesakihu neger gin eyandandu sibket wode hualla eyastawosku new yanebebihut.hulachininm bigermenim manim alitsafewum neber. ER yesetehin tsega eyetetekemihibet newua berta, ER YISTILIN, Amen!!!
ReplyDeletethank you Dn. Dani God Bless You
ReplyDeleteit's cool and very interesting,real.....God bless u!
ReplyDeleteVery good message for all of us. Txs
ReplyDeleteእናንተ ስለ እግዚአብሔር ተናገሩ፣ እርሱ ስለ እናንተ ይናገራል፡፡ እናንተ ስለ ራሳችሁ ስለምትናገሩ ግን እርሱን ዝም አሰኛችሁት፡፡
ReplyDeleteአስተምር ተብሎ እርሱ ሳይለፋ የትራንስፖርቱ ተዘጋጅቶ ህዝበ ክርስያኑ ተሰብስቦ ሞንታርቦው ቆሞ ወንበሩ ተደርድሮ ሲጋበዝ... በዛን ቀን ወጭ እወጣለሁ ብሎ እዚሁ የሚገኝ... እሺ ብሎ ጉባዔው ሲደርስ ስልክ የሚያጠፋ... ከደብር ደብር፣ ከጉባዔ ጉባዔ እየመረጠ የሚያገለግል... ሰዓት አርፍዶ አምሽቶ ለማስተማር አይሉት ይቅርታ ለመጠየቅ የሚመጣ... በሁለተኛው ካልሆነ በመጀመሪያው መርሐ ግብር አላስተምርም መሚል... ራቅ ያለ ቦታ ሆኖ ኮንትራት መኪና ላኩልኝ የሚል... መጽሐፌን፣ ካሴቴን ካልሸጣችሁልኝ እያለ የሚያስቸግር... የሌላ ሁለተኛ ሰው ስልክ በመስጠት ደጅ የሚያስጠና......... ኸረ ስንቱ ተነግሮ ያልቃል "የሰባኪዎቻችን" ችግር።
ReplyDeleteእግዚአብሔር ብቻ ልቦናውን ይስጠን... ይስጣቸው... አሜን
እናንተ ስለ እግዚአብሔር ተናገሩ፣ እርሱ ስለ እናንተ ይናገራል፡፡ እናንተ ስለ ራሳችሁ ስለምትናገሩ ግን እርሱን ዝም አሰኛችሁት፡፡
ReplyDeletesilezih sebakiyan ebakachu sile Egzihabiher bicha sibekun (astemirun) sile Eresachu zina bemawrat ataselchwn.
"......እግዚአብሔር ቀጭ፣መዓት አምጭ፣ ተቆጭ፣ ብቻ ነው እንዴ? መሐሪስ አይደለም፣ ይቅር ባይስ አይደለም፣ ተስፋ ሰጭስ አይደለም፡፡ አንዳንዴኮ የሰባክያን እግዚአብሔር የተለየ እግዚአብሔር ሳይሆን አይቀርም፡፡"
ReplyDeleteGod bless u,u r true and honest orthodox.
ReplyDeleteGod Bless U .
Melikamun gize Yamitalin
ReplyDeleteSelerasachin maweqe segeban ene man negne menes eyeserahu new belen maweqe senoreben selesewoche becha maweratu tegebi new? zor belen erasachinenm enefetshi.
ReplyDeleteD,Danel. sawe egzabhare kalkabrue barsu aykbreme ena bawenate anta yegzabhare kidos manfase albhe kanta gare nau. saw ka egzabhare kaltasatu endanta aykabrem. Egzabhare taghene yabzalehe.Antane ayasatane,yetabkelene. Amane amane amane. wasebhate laegzeabhare.
ReplyDeleteYeleben new yetsafkew. Ene ejen yezo wodesgawe demu yemimeragnen yemefleg alemahwi negn gin yet lehid? Betkeristianu Bisual. Andande Kirstos yemetaw leza gize becha new? Egnan Yetetalnewen man yastawsen? Tsadikochus Bebitu alu enga gin teresan? Ye Petros Tila yaden neber ahun Tseliulegn Belo meteyek enkua mashofe meslognal. In englsih. I am an outsider who wants to be saved. I want to take the holy qurban and be one of the saved. But the church members are busy. They are not looking for people who are lost. Sometimes i asked my self did Jesus came just to save those who was born in his time? Why I do not see Petros and Pauols? who saved a man by their shadow? and when i read Hamer by accident I learned about the late Pole Kerlos, who did a lot of miracles. Where we should go? if the world is fire and the church is fire? where we should go for a rest? where?
ReplyDeleteእግዚአብሔር ለሁላችንም ንፁህ ልቦና ይስጠን። ቃለሕይወት ያስማልን።
ReplyDeleteእግዚአብሔር ለሁላችንም ንፁህ ልቦና ይስጠን። ቃለሕይወት ያስማልን።
ReplyDeletezufan from Australia
ReplyDeleteit's such a wonderful idea. i really apprecieate you. may God be with all the time.
Betam ewente yehone nigern asayehen .
ReplyDeletebetam eyaznana yemiyastemr new.... qal hiwot yasemalh
ReplyDeleteEgziabeher ende kidus Yohannis metmik,kidus Yohannis afework ,kidus Athinatewos yalutin Egziabeherin yemiyasayu mestawetochin yasnesalin !Eyasnesalinim new!
ReplyDeleteI like your comment. This is the right time to tell them about their methods of teaching the gospel.M
ReplyDeleteay god bless your life Dany
Dn. Daniel I really appreciate and share Ur view. Nowadays we are experiencing preachers who are aiming to make more fans than forwarding gospel. May God show them the right way for z sake of his people. But with all Ur respect, i have one question for u: so what should be done?
ReplyDeleteEgzyre ysethe Dany,U are right ,ylebachinene nwe ytenfesekwe
ReplyDeleteእግዚአብሔር ለሁላችንም ንፁህ ልቦና ይስጠን። ቃለሕይወት ያስማልን።
ReplyDeleteGod is with those who have pure heart. Our Service and worship must be to make happy God not people.
ReplyDeleteFrom Ethiopia, Addis Abeba.
TINSAHESHIN YASAYEN KIDIS BETEKIRSTIYAN;
ReplyDeleteEGZIHABIHER YATSINANASH ENNAT/WUDITUWA/ TEWAHIDO
DIAKON, MAY GOD BLESS YOU AND GIVE HIS STRENGTH
TADDISO YIWEGED
ReplyDeleteTEWAHIDO TITSINA
YEBETEKISTIYANACHIN TINSAE YASAYYEN
KALE HIWET YASEMALIN
YIKOYEN DN. DANI
ሰላም ላንተ ይሁን ወንወድሜ ዳንኤል አንድ ጥያቄ ለመጠየቅ እፈልጋለሁ ከከወፍለ ሃገር ወደ አዲስ አበባ እየመጣሁ አውቶብስ ውስጥ ጎኔ ተቀምጦ ጨዋታ ጀመርን በዚህ መሃል ስለማንነቴ ስለቤተሰቤ አሱ ደግሞ ስራሱ አንድ አንድ ጨዋታ ያጫውተኝ ጀመር በዚህ መሃል አንተ ያገባሃት አትሆንህም ከዚህች ሚስት ጋር ብትኖር እድሜህ አጭር ነው አትወለወድም አለኝ እኔም አግብአቼ የመምኖርና ያልወለድክ ስለሆና አመለካከቴን ቀይሮታል በዚህ ምን ትለኛለህ፤
ReplyDeleteበጣም ልክ ነው ዳኒ እኔ ሁልጊዜም የማስበው ነገር ነው ባይገርምህ አንዱ የኘሮቴስታንት አማኝ የሆነ ሰባኪ የእናንተ አስተማሪዎች ሁልጊዜም መጣባችሁ ወዮላችሁ ማለት ባያበዙ በደንብ መጽሐፍ ቅዱስን ያውቁታል ብሎኛል ቢነገራቸውና ይህንን የማስተማር ዘዴ ቢተውት ጥሩ ነው እላለሁ ዳኒ እግዚአብሄር ይባርክህ
ReplyDeleteልክ ነው ይሔ ነገር ሁልጊዜ ያሳስበኝ ነበር አንዳንዶቹ ሰባኪ ሳይሆን ኮሜዲ ይመስላሉ፡፡
ReplyDelete