Tuesday, October 4, 2011

ያዝማሪ ቀልባጣ


በኢትዮጵያ በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ ሰሞን የታላቁ ራስ ኃይሉ የልጅ ልጅ የወይዘሮ ድንቅነሽ እና የዳሞቱ ባላባት የደጃች ዘውዴ ልጅ የነበሩት ደጃች ጎሹ ዐፄ ቴዎድሮስን ድል አድርገው ኢትዮጵያን የመግዛት ሕልም ነበራቸው፡፡ ለዚህም እንዲረዳቸው መሣርያ ያከማቹ አዝማሪ መድበውም ያዘፍኑ ነበር፡፡
በተለይም ጣፋጭ የተባለው አዝማሪያቸው የእርሳቸውን እና የጦረኞቻቸውን ልቡና የሚቀሰቅስ፣ ደጃች ካሣን (በኋላ ቴዎድሮስን) ደግሞ የሚያንኳስስ ግጥም እየገጠመ ያዜምላቸው ነበር፡፡ አዝማሪ ጣፋጭ በፊት ከደጃች ካሣ ጋር የነበረ በኋላ ግን ምናልባት ደጃች ጎሹ ካሸነፉ ሹመት ሽልማት አገኛለሁ ብሎ ወደ ደጃች ጎሹ የታጠፈ እበላ ባይ አዝማሪ ነው ይባላል፡፡
አዝማሪ ጣፋጭ የነገሩን አመጣጥ፣ የታሪኩን አካሄድ፣ የዘመኑን ሁኔታ ሳይገመግም፤ ዛሬ የሚቀባጥረው ነገ ሊያመጣ የሚችለውን ፍዳም ሳይገመግም፣ እንዴው ደጃች ጎሹ ስላበሉት ብቻ በደጃች ካሣ ላይ መዓቱን ያወርድባቸው ነበር፡፡
የዐፄ ቴዎድሮስ ዜና መዋዕል ጸሐፊ አለቃ ወልደ ማርያም እንደመዘገቡት አዝማሪ ጣፋጭ በኅዳር 19 ቀን 1845 ዓም ጉርአምባ [ጎርጎራ] ላይ በደጃች ካሣ እና በደጃች ጎሹ መካከል ወሳኝ የሆነው ጦርነት ከመካሄዱ በፊት ደጃችማች ካሣ (ዐፄ ቴዎድሮስን) እያንቋሸሸ እንዲህ ብሎም ገጥሞ ነበር፡፡
አያችሁት ብያ የኛን እብድ
አምስት ጋሞች ይዞ ጉር አምባ ሲወርድ፣
ያንጓብባል እንጂ መች ይዋጋል ካሣ
ወርደህ ጥመድበት በሽንብራው ማሳ
ወዶ ወዶ
በሴቶቹ በነ ጉንጭት ለምዶ
ሐሩ፣ ቋዱ፣ ለውዙ፣ ገውዙ አለ ከቋራ
መንገዱ ቢጠፋ እኔ ልምራ፡፡
በጦርነቱ ደጃች ጎሹ በጥይት ተመትተው ወደቁ፡፡ ሠራዊታቸውም ተማረከ፡፡ ያም «ያንጓብባል እንጂ መች ይዋጋል ካሣ» ያለው አዝማሪ ጣፋጭ ተይዞ ደጃች ካሣ ፊት ቀረበ፡፡ ካሣም በነገሩ አዝነው «እንደምን ብለህ ሰደብከኝ ብለው ቢጠይቁት፡፡
አወይ ያምላክ ቁጣ አወይ የግዜር ቁጣ
አፍ ወዳጁን ያማል ሥራ ሲያጣ
ሽመል ይገባዋል ያዝማሪ ቀልባጣ»
ብሎ በራሱ ላይ ፈረደ ይባላል፡፡ በዚህም የተነሣ በሽመል ተደበድቦ ሞተ ሲሉ አለቃ ዘነብ ስለ ዐፄ ተዎድሮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ይነግሩናል፡፡
ንግግር ሰው ከእንስሳት ከተለየባቸው ጠብዐያቱ አንዱ ነው፡፡ መናገር ለሰው ሀብቱ ብቻ ሳይሆን መብቱም ነው፡፡ ለዚህም ነው ሃሳብን በንግግር መግለጥ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት ነው የሚባለው፡፡
አበው ካልታረደ አይታይ ስባቱ፣ ካልተናገረ አይታይ ብልሃቱ ይላሉ፡፡ ከብት ካልታረደ መስባቱ እንደማይታወቀው ሁሉ ሰውም ሃሳቡን ካልገለጠ በቀር ብልሃቱን ማወቅ አይቻልም ሲሉ፡፡ ሴትዮዋ «አፍ ያለው ያግባሽ ከብት ያለው» ተባለች አሉ፡፡ «አፍ ያለው ያግባኝ» አለች፡፡ «ከብት ከሌለው በምን አርሶ ያበላሻል ቢሏት፡፡ «አፍ ያለው ከብቱን ተሟግቶ ያመጣዋል» አለች ይባላል፡፡ የንግግርን ኀይል፣ ሃሳብን በሚገባ የመግለጥን ዐቅም ለማሳየት የተነገረ ነው፡፡
በተቃራኒው ደግሞ እንደ አዝማሪ ጣፋጭ ላሉት «በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ» ተብሎ ተተርቶላቸዋል፡፡
የሰው ቃል አካላዊ አይደለም፤ ዝርው ነው፡፡ ከወጣ በኋላ መመለሻ የለውም፡፡ ካፍ የወጣ አፋፍ እንዲሉ፡፡ ሰው ከተናገረ በኋላ እንዲህ ለማለት ነው፣ እንዲህ ስል እንዲህ ነው እያለ የሚሰጠው ማብራርያ እና መልስ የመጀመርያው ንግግሩን ያህል አያረካምም፤ አይታመንምም፡፡ አንድ ያስመለጠውን አይመልሰውም ይባላል፡፡
በባህላችን ሰው የተመታውን እንጂ የተሰደበውን አይረሳም፡፡ ሽመል አጥንት ንግግር ልብ ይሰብራሉና፡፡ የሽመሉ ስብራት በአጥሚት እና በቅቅል ይድናል፡፡ የንግግር ስብራት ግን በልቡና ውስጥ ተሰንቅሮ ሲያመረቅዝ የሚኖር ነው፡፡ ከንግግር ስብራት መፈወስ የሚችሉ የታደሉ ብቻ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ከመታኝ የተናገረኝ አመመኝ የሚባለው፡፡
ንግግር የሃሳብ መግለጫ እንጂ የችሎታ ማስመስከርያ አይደለም፡፡ ምላስን አእምሮ ሲቆጣጠራት እንጂ አእምሮን ምላስ ስትቆጣጠረው ማንም ጤና አይኖረውም፡፡ ምንም እንኳን ካለመናገር ደጃዝማችነት ቢቀርም፣ መናገር ያለብን ግን ደጃዝማችነቱ እንደሚመጣ ርግጠኞች ሆነን ወይንም ደጃዝማችነቱን ሊያመጣ በሚችል መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡
እብድ እና ዘመናይ የልቡን ይናገራል ይላሉ የሀገራችን ሰዎች፡፡ ያመጣላቸውን መናገር የዘመናዊነት መገለጫ የሚመስላቸው አሉ፡፡ የሚታወቅ ሁሉ አይነገርም፡፡ ወደ አፍ የመጣ ሁሉ ወደ ውጭ አይወጣም፡፡ ፈረንጆችን ሳያውቁ ፈረንጆችኮ ግልጽ ናቸው እያሉ የሚታለሉ የዋሐን አሉ፡፡ ግልጽነት ማለት ለማስቀየም መናገር ማለት አይደለም፡፡ ነገሮችን ሰው በቀላሉ ሊረዳቸው እና ከጀርባቸው ሌላ ዓላማ በሌላቸው መንገድ ማቅረብ ማለት እንጂ፡፡ «እኔ ታውቁኛላችሁ ግልጽ ሰው ነኝ» እያሉ ሰውን ልክ ልኩን የሚያቀምሱ ሰዎች ለስድብ የክርስትና ስም እየሰጡት መሆኑን ልንነግራቸው ይገባል፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንደ አዝማሪ ጣፋጭ ጊዜውን መስሎ ለመኖር ወይንም ደግሞ ሰዎችን በከንቱ ውዳሴ ለማስደሰት ብለን እንደዋዛ የምንናገረው ነገር በኋላ የአዝማሪ ጣፋጭን ያህል ከባድ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ የጉልበት እንጂ የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽምና፡፡
ዘጠኝ ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ይባላል፡፡ ምንጊዜም ንግግርን ማሰብ ሊቀድመው እንደሚገባ ለማመልከት፡፡ ሰው ከመናገሩ በፊት በልቡናው ማውጣት ማውረድ አለበት፡፡ ከንግግር በፊት ሂሳብ መሥራት፣ ትርፍ እና ኪሳራውንም ማመዛዘን ይገባልና፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዳመጣላቸው መናገርን የልበ ንጹሕነት ማሳያ አድርገው ያቀርቡታል፡፡ ሰዎችም ይህንን ተቀብለውላቸው «እገሌኮ እንዳመጣለት ይናገራል እንጂ ልቡ ንጹሕ ነው፣ በውስጡ ምንም አይዝም» ይላሉ፡፡
እንዲህ ዓይነቱ ሞኝነት ከምናየው ይልቅ ለማናየው ነገር ይበልጥ ዋጋ ከመስጠታችን የመጣ ብቻ ነው፡፡ ንግግሩን እየሰማነው፣ ንግግሩ እያስቀየመ፣ እየዘረጠጠ እና እያዋረደ የማናየው እና የማናውቀው ልቡ ንጹሕ ነው ማለት እንዴት ይቻላል? ሊቃውንቱ አፍ የሚናገረው ከልብ የተረፈውን ነው ይላሉ፡፡ ሰውዬው በልቡ ሞልቶ በአፉ ሲተርፍበት እያየን ልቡ ንጹሕ ነው ማለት፤ ክብሪት በውስጧ የሌለውን አሳት ስትጫር አወጣችው እንደ ማለት ያለ ነው፡፡
እንዲህ ባለ ጊዜ በልቡ ነገር ከሚቋጥር ሰው ይልቅ ሁሉንም ዝርግፍ አድርጎ የሚያወጣ ሰው ይሻላል ብለው የሚከራከሩ አሉ፡፡ አድራጊዎችም «እኔኮ ተናግሬ ይወጣልኛል እንጂ በልቤ ምንም ቂም አልይዝም» ብለው ይመጻደቃሉ፡፡ የማይመረጡ ነገሮችን ለምርጫ አቅርበናቸው ነው እንጂ ሁለቱም የሚመረጡ አልነበሩም፡፡ በጩቤ ከመወጋትና በቢላዋ ከመወጋት ምረጥ ዓይነት ነገር ነው ጨዋታው፡፡ የሰውን ሞራል እስኪነኩ፣ ልቡን እስኪያስቀይሙ፣ ስሙን እስኪያጠፉ፣ ክብሩን እስኪገሡ፣ ኅሊናው ሊቀበለው እስኪያቅተው፣ ድረስ መናገርም ሆነ፤ ነገሮችን ሁሉ በልብ አስቀምጦ ማቄም ሁለቱም የማይመረጡ ናቸው፡፡
አንዳንዶቹን የመጠጥ ሞቅታ እንደሚያናግራቸው ሁሉ ሌሎችን ደግሞ የዘመን ሞቅታ ያናግራቸዋል፡፡ ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ቃል አትናገር ይላል ብሩክ የተባለ የታክሲ ውስጥ ጥቅስ ጸሐፊ፡፡ ዘመን የማያልፍ እየመሰላቸው ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ እምነት ተቋማት፣ ስለ ፈጣሪ፣ ስለ ብሔረሰቦች፣ ስለ ተቃዋሚዎቻቸው፣ ስለ ባለ ሥልጣናት፣ አያሌ አሰቃቂ ነገር የተናገሩ ሰዎች ነበሩ፤ አሉም፡፡
በየስብሰባው፣ በየቃለ መጠይቁ፣ በየሰልፉ፣ በየበዓሉ፣ በየግብዣው የንግግር ብዛት፣ የመፈክር ጋጋታ፣ የውዳሴ መዓት፣ የሥልጣን ክምር፣ የገንዘብ አልኮል ያሰክራቸውና ያለሰቡበትን፣ አንዳንድ ጊዜም የማያምኑበትን፣ ባስ ሲልም የሚቃወሙትን ነገር ጭምር የሚናገሩ ሰዎች አሉ፡፡ የእነዚህ ሰዎች መጨረሻ በማይበርድ የፀፀት እሳት መቃጠል ነው፡፡
ፈረንጆች think twice before once ያሉት ብሂል እንደ እኛው አባባል ሁሉ ንግግርን ሞቅታ እና ስሜት ሳይሆን ማሰብ ሊቀድመው እንደሚገባ የሚያስረግጥ ነው፡፡ አንዳንዶች ግን ይህንን አልሰሙም መሰል ምላሳቸው ሳይሆን ጭንቅላታቸው ውስጥ ያለው፣ ጭንቅላታቸው ነው ምላሳቸው ውስጥ ያለው፡፡ አስበው ሳይሆን የሚናገሩት ተናግረው ነው የሚያስቡት፡፡
ሰው ጆሮው ሁለት ምላሱ ግን አንድ የሆነው ብዙ እንዲያዳምጥ ነገር ግን ጥቂት እንዲናገር ነው ይላሉ ትውፊታውያን ሊቃውንት፡፡ ጥቂት መናገር ማለት ዝምታን መምረጥ ማለት አይደለም፡፡ አስፈላጊውን ነገር፣ በአስፈላጊው ጊዜ እና ቦታ፣ ለአስፈላጊ ዓላማ፣ በአስፈላጊ መንገድ መግለጥ ማለት ነው፡፡
«እገሌ ቡና ይጠራ» ሲባሉ «አይ እርሱ ወጥ ይረግጣል» የሚሉ አክሰት ነበሩኝ፡፡ በርሳቸው ቋንቋ ወጥ መርገጥ ማለት ድንበር አልፎ መናገር ማለት ነው፡፡ ለአክስቴ ንግግር ድንበር ድንበር አለው፡፡ ልጅ የሚናገረው፣ ዐዋቂ የሚናገረው፣ የተማረ የሚናገረው፣ ሴት እና ወንድ የሚናገሩት፣ ሽማግሌ እና ባልቴት የሚናገሩት፣ የሃይማኖት አባት የሚናገረው፣ ባለ ሥልጣን የሚናገረው ድንበር ድንበር አለው፡፡
ላንዱ ተፈቅዶ ለሌላው የተከለከለ ይኖራል፡፡ አንዱ ቢናገረው የሚያስቀው ነገር ሌላውን ሊያስገምተው ይችላል፡፡ አንዱን ያስከበረው ንግግር ሌላውን ያዋርደዋል፤ አንዱን ያስመሰገነውም ሌላውን ያስነቅፈዋል፡፡ ይህንን ነው አክስቴ ወጥ መርገጥ የሚሉት፡፡
አንዳንዴ በመገናኛ ብዙኃን ታላላቅ ተብለው የሚቀርቡ ሰዎች ባህሉን፣ ወጉን፣ ትውፊቱን ረስተው በንግግራቸው ድንበር ሲሻገሩ ሳይ አክስቴ ስንት ጊዜ ወጥ ረገጥክ ሊሉ እንደሚችሉ አስባለሁ፡፡ አንዳንዶቹ የዕለቱን እንጂ የዓመቱን አያስቡትም፡፡ ሌሎቹም ርእዮተ ዓላማቸውን እንጂ ሕዝቡን አያስታውሱትም፡፡
ብዙ መናገር የሊቅነት መገለጫ የሚመስላቸው ወገኖችም አሉ፡፡ ወጥ የሚያስረግጥ ስሕተት ከሚፈጠርባቸው አጋጣሚዎች አንዱ አብዝቶ መናገር ነው፡፡ ነገር ሲበዛ ጥፋት፣ አጀብ ሲበዛ ሥጋት አይቀርም ይባል የለ፡፡ የሰው አእምሮ ሊቆጣጠረው የሚችለው የንግግር መጠን የተወሰነ ነው፡፡ ከልኩ ሲያልፍ አእምሮ ምላስን መቆጣጣር ያቆማል፡፡ ያን ጊዜ ቃላት ሳይበጠር እንደሚወጣ እህል በግዴለሽነት ያፈተልካሉ፡፡
ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም እያልን ለብዙ ዘመናት ብንተርክም ወሬዎቻችንን እና ንግግሮቻችንን ማሳጠር ግን አልቻልንም፡፡ ለረዥም ሰዓት መናገር፣ ለረዥም ሰዓት መምከር፣ ለረዥም ሰዓት ማስተማር፣ ለረዥም ሰዓት መልስ መስጠት፣ አሁንም ገንዘቦቻችን ናቸው፡፡ ነገር ከበዛ በምዕራብ ተጀምሮ በሰሜን ነው የሚያልቀው፤ መነሻው ስለ ሕይወት መጨረሻው ስለሞት ነው የሚሆነው፡፡ በፍቅር ተጀምሮ በጠብ፣ በደስታ ተወጥኖ በልቅሶ ነው የሚጠናቀቀው፡፡
አዝማሪ ጣፋጭ መሰንቆውን እርሱ መቃኘት ሲገባው እርሱን መሰንቆው ቃኘው፡፡ መሰንቆውን በአእምሮው መንገድ መውሰድ ሲገባው አእምሮውን በመሰንቆው መንገድ ወሰደው፡፡ መሰንቆውን መቃኘት ያለብን እኛ ነን፡፡ ሞቅታው፣ ዘመኑ፣ ፌሽታው፣ ሥልጣኑ፣ ቦታው፣ ግርግሩ፣ ውዳሴው፣ ሆይ ሆይታው፣ ሞራሉ፣ ጭብጨባው፣ ነው መሰንቆው፡፡ አንዳንዴም ብሶቱ፣ ንዴቱ፣ ቁጭቱ፣ ኀዘኑ፣ ተስፋ መቁረጡ፣ ነው መሰንቆው፡፡ እነዚህ ነገሮች እንደ አዝማሪ ጣፋጭ እየሳቡን ከቆይታ በኋላ የሚያስፀፅተንን፣ ምላሴን በቆረጠው፣ አንደበቴን በዘጋው፣ ዲዳ በሆንኩ፣ እንደ አባ አጋቶን ድንጋይ በጎረስኩ የሚያሰኘንን ንግግር መናገር የለብንም፡፡
«አለ እገሌ፣ አለች እገሊት» እያለ ቃልን ከትውልድ ወደ ትውልድ በሚዘክር ማኅበረሰብ ውስጥ ንግግር ከባድ ዋጋ አላት፡፡ የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ የሚል ብሂል ባለው ቃላዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ንግግር ትውልዳዊ ቦታ ሊያስገኝም ሊያሳጣም ይችላል፡፡ መታፈር በከንፈር እያለ በሚተርክ ሕዝብ መካከል ከንግግሩ አነጋገሩ ታላቅ ዋጋ እንዳለው ሊዘነጋ አይገባም፡፡
 ከዴንቨር ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣ . ኤስ. ኤይር ዌይስ አውሮፕላን ውስጥ
©ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

25 comments:

 1. I read it in my bed i am so wonder.realy dani because u touch me. I am one of them i talk much but i didnt think it my word may or may not upset someone.always i talk with out rest.one time my friend say 'i did not go with you'i ask him why? He answer you may talk what my girle friend hate.just i realized now why he say that.dani you open my cloth eyes thank you God with you.GOOD DAY.

  ReplyDelete
 2. Think twice before you speak once ይመስለኛል ትክክለኛው አባባል

  ReplyDelete
 3. ከበዛ ንግግር የሚመጣ ፈተና ከተግባር ፈተና ይበልጣል!!! ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥህ!

  ReplyDelete
 4. ከበዛ ንግግር የሚመጣ ፈተና ከተግባር ፈተና ይበልጣል!!! ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥህ!

  ReplyDelete
 5. ለዘመንህን ይባርክል ለመጀመሪያ ጊዜኮመንት ሳደርግ ነው ሁሌም ፅሁፍህ ይስማማኛል ይሔኛው ግን በተለይ ይችህ አንቀፅ በጣም ተሰማችኝና ነው፡

  እንዲህ ባለ ጊዜ በልቡ ነገር ከሚቋጥር ሰው ይልቅ ሁሉንም ዝርግፍ አድርጎ የሚያወጣ ሰው ይሻላል ብለው የሚከራከሩ አሉ፡፡ አድራጊዎችም «እኔኮ ተናግሬ ይወጣልኛል እንጂ በልቤ ምንም ቂም አልይዝም» ብለው ይመጻደቃሉ፡፡ የማይመረጡ ነገሮችን ለምርጫ አቅርበናቸው ነው እንጂ ሁለቱም የሚመረጡ አልነበሩም፡፡ በጩቤ ከመወጋትና በቢላዋ ከመወጋት ምረጥ ዓይነት ነገር ነው ጨዋታው፡፡ የሰውን ሞራል እስኪነኩ፣ ልቡን እስኪያስቀይሙ፣ ስሙን እስኪያጠፉ፣ ክብሩን እስኪገሡ፣ ኅሊናው ሊቀበለው እስኪያቅተው፣ ድረስ መናገርም ሆነ፤ ነገሮችን ሁሉ በልብ አስቀምጦ ማቄም ሁለቱም የማይመረጡ ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 6. ቅዱስ ያዕቆብ አንደበት እሳት ነው ብሏል፡፡ አንደባትችንን እንድንገታ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ የዛሬው ጽሑፍ ራሴን ዞር ብዬ እንዳይ የረዳኝ ጽሑፍ ነው፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ፡፡

  ReplyDelete
 7. The Almighty God bless you with his Holly blessings .I'm assure no one is free from this 'Abaze' so pls be selective on our talks!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 8. ልክ ብለሀል ዳኒ! አብዘኞቻችን ከተናገርን በኋላ ነው ማሰብ የምንጀምረው፡፡አጅግ በጣም አስተማሪ ጽሑፍ ነው፡፡ ሊማር ለፈቀደ ወይም ለሚያስተውል፡፡ የዚህ ብሎግ ቋሚ ተከታታይ ነኝ::በዕውነት ዕውቀትህና ማስተዋልህ ይገርመኛል“ልቡና ረሰየተከ መካና አዕምሮ ታጌብረከ ለምህሮ”፡፡መቼም እንዲህ ያለ ዕውቀትና ማስተዋል ከእግዚአብሔር ካልተሰጠ በቀር ከወዴት ይገኛል?ረዥም እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 9. የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም ይላሉ አበው

  ReplyDelete
 10. where ever you are God bless you and your family, I always read your articles even on magazine and newspaper but this is my first time to comment, I don't have equal words to express my appreciation And I understood you are passing through a lot of miserable situations but God was with you, is with you and will be with you. keep your faith with God, be strong. I feel the hardest time will come soon to you.you will be the next.... God keep Ethiopia!

  ReplyDelete
 11. Dani, When I was in school my class mate always raised his hands and teachers always gave him an opportunity to talk. He always said that I have 5 questions and 4 of them explained well by the teacher, the remaining one is not as such a question, actually it is an opinion. When I read your article I remember my friend whose mind is managed by his hand and tongue.

  ReplyDelete
 12. ይገርማል ብዙ ነገር አስተማርከኝ እግዚአብሔር ይስጥልን!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. በጣም አስተማሪ ነው

  ReplyDelete
 14. it is Good thing for us and to take a lesson here and change our selves ,you are doing your great responsibility as a citizen danie
  keep it up
  10q

  ReplyDelete
 15. Few years on I have been growing up much much talkative. I couldn't stop with right time, I couldn't address the right point, instead I tend to go round and round that is a stupid way of approach that bored my audience.

  Your article is , I don't know if there are many other than me, but its about me. You told me clearly and precisely.

  Thank You
  May God bless you

  ReplyDelete
 16. Dani! Itis about me. You told me clearly and precisely!.

  ReplyDelete
 17. ቅዱስ ያዕቆብ አንደበት እሳት ነው ብሏል፡፡ አንደባትችንን እንድንገታ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ የዛሬው ጽሑፍ ራሴን ዞር ብዬ እንዳይ የረዳኝ ጽሑፍ ነው፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ፡፡
  Hailemeskel z maputo

  ReplyDelete
 18. dear Dan

  i am one of those who talks more and most of the time without thinking on

  i really sorry i harrased my wife and your view reverted me

  many thanks !!

  ReplyDelete
 19. men temaren ,beka anbebo metew new weys .....

  ReplyDelete
 20. ዳኒ ትልቅ ትምህርት ያገኝሁበት ጽሁፍ ነው አመሰግናለሁ !!!

  ReplyDelete
 21. ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጥስ ስለ መናገር የተናገረውን አስታወስከኝ
  “ግልፅ ሁን ነገር ግን ግልፅነትህ ገደብ ይኑረው ፡፡ ባልተማሩ ወገኖች( ሰዎች) መሀል ይገልጥ ግልፅ በሆንክ መጠን አጠገብህ ካለሁት ጀምሮ ሁሉም በጭቃ እንደ ተከበበ ደረቅ መሬት እየረጋገጡ ሊራመዱብህ ይፈልጋሉ “
  “በሚገባ ለመናገር የማሰብ ችሎታ ወይም ለማድመጥ የማመዛዘን ችሎታ የሌለው ሰው በጣም መጥፎ ዕድል ነው የገጠመው” ብሎ ነበር

  ካርላይንድ ደግሞ “ዝምታ ታላላቅ ነገሮች በውስጡ ራሳቸውን የሚያስጌጡበት ባህሪይ ነው፡፡”ሲሉ ታላላቅ ሙሁራኖች በትክክል ለማሰብ የሚቻልበትን መንገድ ገልፅውልናል፡፡

  ReplyDelete
 22. So many thanks Dani !!!

  ReplyDelete
 23. ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም፡፡ነገር ያመለጠው ሞጥሟጣ ሲባል ራሱ የተመለጠው ደግሞ መላጣ ይባላል፡፡የመመለጡስ ይሁን ከላይ ነውና፡፡ ነገር ያመለጠው ነው ችግሩ፡፡ችግሩ ደግሞ እንደ አለመታደል ሆኖ በአገራችን ኢትዮጵያ ነገር የሚያመልጣቸው ትላልቅ ሰዎች መብዛታቸውና መሪ መሆናቸው ነው፡፡ስልጣናቸውን ለሚያራዝም ጦርነት ወጣቱን ለመማገድ ሲሆን ጨዋ/ደፋር እያሉ ያሞካሹትን ወጣት በምርጫ ሲሸነፉ አደገኛ ቦዘኔ ይሉታል፡፡አገር ለማፍርስ የሕዝቡን ታሪክ እና አገር ወዳድነት ለመናድ ጨርቅ ያሉትን ስልጣን ላይ ለመቆየት አስፈላጊ መስሎ ሲታያቸው ሰንደቅ አላማ ይሉታል፡፡የአንድ ተራ ሰው ስህተት እኮ በጣም ቀላል ነው፡፡ስህተቱ ራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም፡፡የመሪዎቻችን ስህተት ነው በትውልድ ተከፍሎ የማያልቅ እዳ ውስጥ የከተተን፡፡መወያየት እና መነጋገር ያለብን እኮ አንድ ሰውም ቢሆን ውጤቱ ሚሊዮኖችን የሚጎዳ ውጤት ያለውን ነውር ስለሚሰሩ የነፍስ እና የስጋ መሪዎቻችን ነው፡፡አዲስ አበባው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 24. The Lord Jesus was not defending himself before his accusers. He was salient. May God help us us to keep salient when needed and talk to the well being of our brother.
  From Ethiopia, Addis Abeba.
  God Bless you.

  ReplyDelete