Friday, September 23, 2011

ይሁንተኞች

በአንድ ሀገር ውስጥ አንደ የዝንጀሮ አለቃ ነበር አሉ ኦሮሞዎች ሲተርቱ፡፡ በመልክ እና በቁመት፣ በትከሻ እና በክብደት የሚመስሉት በዛ ያሉ ዝንጀሮዎች በመንጋው ውስጥ ነበሩ፡፡ ታድያ ለንጉሡ አጎንብሱ በሚለው መመርያ መሠረት የሚመሩ ጥቂት ዝንጀሮዎች አለቃቸውን ለማስደሰት አሰቡ፡፡ አስበውም አልቀሩ እንዲህ አሉት፡፡ «እርስዎን ከሌሎች ዝንጀሮዎች መለየት አልቻልንምና፣ ለየት የሚያደርግ ምልክት ያድርጉ» አሉት፡፡ እርሱም በራሱ ላይ የብረት አክሊል ለማድረግ ወሰነ፡፡
 እነዚያ እበላ ባይ ዝንጀሮዎች እየተከተሉ አባራ ሳይነካው ልብሱን ያራግፉለታል፡፡ ሳያስነጥሰው ይማርህ ይሉታል፡፡ ሳያመው ተሻለዎት? ብለው ይጠይቁታል፡፡ ሳይቀልድ ይስቁለታል፡፡ ሳያዝን ያለቅሱለታል፡፡ ያልተናገረውን ይጠቅሱለታል፡፡ ባልሆነው ነገር ያወድሱታል፡፡

ይህንን ሲመለከት ጊዜ ጠባዩ እየተቀየረ መጣ፡፡ ተሳስተሃል የሚለውን ማንኛውንም ዝንጀሮ እንደ ጠላት ማየት ጀመረ፡፡ ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት የማይለውን ሁሉ ለመቅጣት ተዘጋጀ፡፡ እርሱ ከሚያስበው በተለየ የሚያስበውን ዝንጀሮ ዝንጀሮነቱን ይጠራጠር ጀመር፡፡
ቀስ በቀስ አለቃው ቤተ መንግሥት እርሱ ያለውን ብቻ በሚቀበሉ ዝንጀሮዎች እየተሞላ መጣ፡፡ በጥንት ጊዜ በቤተ መንግሥት ውስጥ ሦስት ዓይነት ባለሟሎች ይቀመጡ ነበር አሉ፡፡ ከንጉሡ የሚበልጡ፣ ከንጉሡ የሚስተካከሉ፣ ከንጉሡ የሚያንሱ፡፡
ከንጉሡ የሚበልጡት ይገሠጹታል፤ ከንጉሡ የሚስተካከሉት ይሟገቱታል፣ ከንጉሡ የሚያንሡት ይከተሉታል፡፡ ከንጉሡ የሚበልጡ ብቻ ከሆኑ ንጉሡ ሥራ መሥራት አይችልም፡፡ በእነርሱ ተጽዕኖ ውስጥ ብቻ ይወድቃልና፡፡ ከንጉሡ የሚተካከሉ ብቻ ከሆኑ ሲሟገት ብቻ መኖሩ ነው፡፡ ከንጉሡ የሚያንሱ ብቻ ከተሰበሰቡ ምክር ቤቱ በይሁንተኞች ይሞላና እርሱ ያለውን ብቻ እየተቀበሉ ገደል ሊከቱት ነው፡፡
ይኼኛው የዝንጀሮ አለቃ ግን ሁለቱን ዓይነት አማካሪዎች አጠፋቸው፡፡ ከእርሱ የሚበልጡትን እና ከእርሱ የሚስተካከሉትን፡፡ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ይሁንተኞች ብቻ ሞሉ፡፡ ምክሩን የሚቀበል እንጂ እርሱን የሚመክረው ጠፋ፡፡ ከእርሱ ዕውቀት የሚፈልገ እንጂ ሊያሳውቀው የሚሄድ ጠፋ፡፡ የሚያመሰግነው እንጂ የሚወቅሰው ጠፋ፡፡ የሚያደንቀው እንጂ የሚተቸው ጠፋ፡፡
ምን ጥቁር ቢበሉ ነጭ ነው ኩስዎ
ምን ከሩቅ ቢጮኹ ይሰማል ድምጥዎ
አሁን የርስዎን ልጅ ምን አገኘብዎ
ብለው አህዮች ለጅብ እንደ ተቀኙት ዓይነት ቅኔ ብቻ በየጊዜው ይዘንብለት ጀመር፡፡
የዝንጀሮው አለቃ በይሁንተኞች ብቻ መከበቡን ሲረዳ እንዲህ የሚል ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ «ከዛሬ ጀምሮ እኔ የምለውን ብቻ መቀበል እንጂ ለምን? እንዴት? ብሎ እኔን መጠየቅ ያስቀጣል፡፡ ማንኛውም የእኔ ባለሟል የማሳየውን ብቻ ያደርጋል፤ የምናገረውን ብቻ ይናገራል»
እናም ለብዙ ጊዜ እርሱ የተናገረውን እየተናገሩ እርሱ የሚያደርገውንም እያደረጉ ከሚኖሩ ባለሟሎቹ ጋር ኖረ፡፡ እርሱ ሲጮኽ ይጮኻሉ፡፡ ለምን እንደሚጮኽ እነርሱም ለምን አብረውት እንደጮኹ ግን አያውቁም፡፡ እርሱ ሲዘል ይዘላሉ፤ እርሱ ዛፍ ላይ ሲወጣ ይወጣሉ፡፡ እርሱ ሲንጠላጠል ይንጠላጠላሉ፡፡ የቆረጠውን ይቆርጣሉ፡፡ የጣለውን ይጥላሉ፡፡ የወደደውን ይወድዳሉ፤ የጠላውን ይጠላሉ፡፡
ኑሮ እንዲህ ሆነ፡፡
የዝንጀሮዎች አለቃ እየበላ እና እየጠጣ በሄደ ቁጥር እየወፈረ መጣ፡፡ ሲወፍርም በራሱ ላይ ያጠለቀው የብረት ዘውድ እያጣበቀው መጣ፡፡ ሊያወልቀው ቢሞክርም እምቢ አለው፡፡ አንድ ቀን በእልፍኙ እያለ ዘውዱ አጣብቆ ያዘው፡፡
ወዲያው እየተጣደፈ ከእልፍኙ ወጣና ባለሟሎቹ ወደ ተሰበሰቡበት አዳራሽ ገባ፡፡ ሁሉም ቆሙ፡፡ እየጮኸ «ይኼንን ዘውድ አውልቁልኝ» አላቸው፡፡ የምለውን ብቻ በሉ፡፡ የማደርገውንም ብቻ አድርጉ የተባሉት ባለሟሎቹ፡፡
«ይኼንን ዘውድ አውልቁልኝ» አሉና እርሱ እንዳለው አሉ፡፡
ተናደደ፤ ተናደዱ
«እውነቴን ነው» አላቸው
«እውነቴን ነው» አሉ እነርሱም፡፡
«አትቀልዱ» አለ
«አትቀልዱ» አሉ ተከትለውት፡፡
«ልትገድሉኝ እኮ ነው» አለ እየጮኸ፡፡
«ልትገድሉኝ እኮ ነው» አሉ እነርሱም እየጮኹ፡፡
ተበሳጭቶ እየሮጠ ወደ እልፍኙ ገባ፡፡ እነርሱም እየሮጡ ወደየ እልፍኛቸው ገቡ፡፡
ተመልሶ ከእልፍኙ ወጣ፡፡ እነርሱም ወጡ፡፡
ይበልጥ እያጣበቀው ሲመጣ ኡኡ ብሎ ጮኸ፡፡ እነርሱም ኡኡ ብለው ጮኹ፡፡ የዝንጀሮው መንጋም ኡኡ እያለ ተሰበሰበ፡፡
«ሞትኩ» ይላል አለቃቸው
«ሞትኩ» ይላሉ እነርሱም፡፡
እየሮጠ ወደ መድኃኒት ዐዋቂው ሄደ፡፡ ሁሉም ተከትለውት ወደ መድኃኒት ዐዋቂው ሄዱ፡፡
መንገድ ላይ አንድ ሰው አገኘ፡፡ «የመድኃኒት ዐዋቂው ቤት የት ነው ብሎ ጠየቀው፡፡ ያም ሰው መልሶ «የመድኃኒት ዐዋቂው ቤት የት ነው አለና መለሰለት፡፡
«የማትነግረኝ ከሆነ እቀጣሃለሁ» አለው፡፡ ሰውዬውም መልሶ «የማትነግረኝ ከሆነ እቀጣሃለሁ» አለው፡፡ ሲጨንቀው መንገዱን ቀጠለ፡፡ በየቤቱ እየዞረ ፈለገው፡፡ መንጋውም አብሮት ፈለገ፡፡ አንድ በር ሲከፍት መድኃኒት ቤቱን አገኘው፡፡ ነገር ግን በውስጥ ያለው ሌላ መድኃኒተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ያኛው መድኃኒተኛ እንደ አለቃው ሁሉ ሌላ መድኃኒት ቤት ሄዷልና፡፡
ዘልሎ አልጋ ላይ ተኛ፡፡ መንጋውም በየአልጋው ተረፈረፈ፡፡
«አጣብቆኛል» አለው ዐዋቂውን፡፡
ዐዋቂውም መልሶ «አጣብቆኛል» አለው፡፡
«አውጣልኝ ከራሴ» አለው የዝንጀሮው አለቃ፡፡
«አውጣልኝ ከራሴ» አለ መድኃኒት ዐዋቂውም፡፡
ከድካሙ ብዛት ተራበ፡፡ እናም «ራበኝ» አላቸው፡፡ እነርሱም «ራበኝ» እያሉ መጮኽ ጀመሩ፡፡ «እባካችሁ ውኃ» አለ፡፡ እነርሱም ተከትለውት «እባካችሁ ውኃ» አሉ፡፡
ሲጨንቀው ተነሣና ከተደረደሩት መድኃኒቶች አንዱን ቅጠል አንሥቶ በላ፡፡ ተከታዮቹም እንደርሱው እያነሡ በሉ፡፡ ባለ መድኃኒቱም ቅጠል እንደሚያሳብድ ቢያወቅም መከተል ስላለበት አብሮ በላ፡፡ እናም መላው የዝንጀሮ መንጋ አበደ፡፡
አለቃው በእብደት መንፈስ ተነሣና እየዘፈነ ይሮጥ ጀመር፡፡ መንጋው ሁሉ እየዘፈኑ ተከተሉት፡፡
እየጨፈረ፣ እየጨፈሩ ሄደው ገደል ዳር ደረሱ፡፡ ያንን ያጣበቀውን የብረት ዘውድ ከገደሉ ዐለት ጋር እያጋጨ ሊያላቅቀው ሞከረ፡፡ መንጋውም እንደርሱ ራሳቸውን ከዐለቱ ጋር ያጋጩ ጀመር፡፡
ራሱን ከዐለቱ ጋር ለብዙ ሰዓት ሲያጋጭ ዕብደቱ ጨመረ፡፡ የመንጋውም ዕብደት ጨመረ፡፡ አንዱን የዐለት ፍላጭ አንሥቶ የቅርብ ባለሟሉን መታው፡፡ መንጋውም እርሱን ተከትሎ የዐለት ፍላጭ እያነሣ የቅርብ ወዳጁን ይመታ ጀመር፡፡
እርስ በርስም ፍጅት ሆነ፡፡
ዕብደቱ ከልክ በላይ ሲያልፍ ዘለለና ገደል ውስጥ ተወረወረ፡፡ መንጋውም እርሱን ተከትለው ገደል ውስጥ ተወረወሩ፡፡   
እናም «ሰውን ከላይ ሆነው ከሚቆጡት፣ ከጎንም ሆነው ከሚሞግቱት ይልቅ ከሥሩ ሆነው የሚከተሉት ጀሌዎች ይበልጥ ይጎዱታል፤ ከላይ ሆነው ከሚያሳዩት ታላላቆቹ፣ ከጎን ሆነው ከሚገዳደሩት እኩዮቸ$ ይልቅ፣ ከሥር ሆነው ይሁን ብቻ የሚሉት አንጋሾቹ ይበልጥ ይጎዱታል» ተባለ፡፡
አሌክሳንድርያ፣ ቨርጅንያ

43 comments:

 1. ...እናም «ሰውን ከላይ ሆነው ከሚቆጡት፣ ከጎንም ሆነው ከሚሞግቱት ይልቅ ከሥሩ ሆነው የሚከተሉት ጀሌዎች ይበልጥ ይጎዱታል፤ ከላይ ሆነው ከሚያሳዩት ታላላቆቹ፣ ከጎን ሆነው ከሚገዳደሩት እኩዮቸ$ ይልቅ፣ ከሥር ሆነው ይሁን ብቻ የሚሉት አንጋሾቹ ይበልጥ ይጎዱታል» ተባለ፡፡....
  This is one of the valuble practical lessons we should learn from our ancestors .In Its recent past Ethiopia had seen such leaders from the last Emperor to the current regime,they fall under the same catagory.They should have learnt from history...He who has ears to hear, let him hear!

  Well, this is my take of the above article,if I were " yemetshaf Memihr" andim eyalku eketel neber....I will leave the andemta for the other readers...
  Mulugeta Mulatu
  Vancouver Island

  ReplyDelete
 2. እናም «ሰውን ከላይ ሆነው ከሚቆጡት፣ ከጎንም ሆነው ከሚሞግቱት ይልቅ ከሥሩ ሆነው የሚከተሉት ጀሌዎች ይበልጥ ይጎዱታል፤ ከላይ ሆነው ከሚያሳዩት ታላላቆቹ፣ ከጎን ሆነው ከሚገዳደሩት እኩዮቸ$ ይልቅ፣ ከሥር ሆነው ይሁን ብቻ የሚሉት አንጋሾቹ ይበልጥ ይጎዱታል» ተባለ፡፡
  this is awesome .

  ReplyDelete
 3. ደስ የሚል አፃፃፍ ነዉ
  ግን የመግሥቱ ሃይለማርያምን ታሪክ ነዉ እንዴ የፃፍከዉ ታድያ ምነዉ በአበሳ እንኮን በትመስለዉ
  sofoniyas.

  ReplyDelete
 4. ሰላም ወዳጄ ዳኒ እንዴት ነህ.መልካም ነገሮችህ እንደ ቀትር ጀምበር እየደመቁ ሄዱ ብእርህ ይባርክ. የሰው ልጅ ከተግስጽ ይልቅ ሙገሳን ከምክር ይልቅ ሃሜትን ልቡ አጥብቃ ትሻለች. የሚገርመው 3 አይነት ሰወች አሉ የመጀመርያዎቹ መምራት እንጂ መመራት የማያውቁ በወሬ, በመንገድ, በሁሉም ነገር መምራት የሚቅናችው ናቸው እነሱ ካልሰሩት የሚያር,የሚጎረና, ግቡን የሚስት የሚመስላቸው ናችው. ሁለተኛዎቹ ደግሞ መምራትም መመራትም የማይፈልጉ በራሳቸው መንገድ,ጫካ የሚኖሩ ተነግረው ሳይሆን አስበው, አይተው ሳይሆን ፈጥረው,መመሪያን ሳይሆን ህሊናን ፈርተው የሚሰሩ ሲሆኑ የመጨርሻዎቹ ግን ሁል ጊዚ መመራት ይየሚወዱ የሚበሉትንም ምግብ ካልነግሮቸው ለመብላት የሚዳዱ,ሁሉ ነገር ግራ የሚገባችው የተኙ መተኛታቸውንም የማያውቁ ተነግርው ብቻ የሚሰሩ ናቸው

  ReplyDelete
 5. Dani it's so nice keep on writing.God bless you.

  ReplyDelete
 6. wow i like the way u express our live thank you Dani
  hagere lemelewete yeteshale nuro endenenore mengesete bechawen ayechaleweme yehulachenem asetewasewo mechemere alebet gelawi teqemachenene lemasekebere yebelayochachenen yemenakeberebetena hasabachewen yemenqebelebet huneta erasachenene lenewetawe wedemanechelewe azeqete wesete eyeketeten new yehi demo teweleden yemigoda selehone sewoche endiwedun sayehon hagerachenen yeteshal wedemibal yedeget dereja liwesedat yemichel mekere new yesetehegne

  ReplyDelete
 7. Tnks! Adirbaynet meni yahil endemegoda yasayal kadirbayenet yesewren.

  ReplyDelete
 8. Thank you dani.Great lesson.

  ReplyDelete
 9. በተለያዩ ክፍሎች መሪ ሆነው የሚያገለግሉ ሁሉ ሰው መሆናቸውን ሳይዘነጉ ጉድለት እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው ይህ ጽሑፍ በማንኛውም እርከን ያሉ ኃላፊዎች ሊያነቡት ይገባቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 10. Betam tiru astemari ababal new.

  ReplyDelete
 11. What a great article, Dani. It has a lot of message behind it. You make me think about our leaders.

  That is a day-to-day practice of African leaders especially, our PM Meles. No body is there above and equivalent to him to help him understand with telling and advising what his problems are. Wise leaders have to be close to scholars, advisers, historians, professors, and others, who can help leaders in seeing different perspectives of this world. However, Meles doesn't want to be around those kind of people, he doesn't even respect their intelligence. All politicians under Meles are like a parrot to me, like the monkeys you mentioned them above in your article. Eventually they won't even help him; they rather fasten his death. I guess that may not be the case in countries like ours because the system works for Meles for the last twenty years.

  What I don't understand always is that why any of the followers don't try to use their own mind, as a human being (far from the monkey story).

  God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 12. ይህ አባባል ለጓድ መንግስቱ ሀይለማርያምና ለአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ እጅግ የሚስማማ ነገር ነው፡፡
  እንዲያውም ከጓድ መንግስቱ ሀይለማርያም ይበልጥ ደግሞ ለአቶ መለስ ዜናዊ የበለጠ የሚስማማ ይመስለኛል፡፡አቶ መለስ ከዛሬ 20 ዓመታት በፊት ስልጣን ላይ ሲወጡ ትዝ ይለኛል የ36 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ፡፡ትዝ ይለኛል ከግንቦት 20 ድል በኋላ ወዲያውኑ ልክ ስልጣን ላይ እንደተፈናጠጡ የወጪ የገቢ እንደሚባለው አይነት የተለመደ የባህላችን ግብዣ በሚመስል አይነት ወዲያውኑ ከታዋቂው ከፕሮፌሰር መስፍን ጋርና አንዳንድ ለጊዜው ስማቸውን በውል ከማላስታውሳቸው ከሌሎች ትላልቅ ምሁራንና ትላልቅ አዛውንቶች ጋር የተወሰነ ውይይት አድርገው ነበር፡፡የዚህን ወይይት ዝርዝር አሁን በደንብ ባላስታውስም ቅሉ ግን ዋናው መንፈሱ አቶ መለስና ወያኔ ስልጣንን ከበረሃ ትግል በድል አጠናቀው ከተማ ሲገቡ እንዴት ነው የምታስተዳድሩን እናንተ ጎረምሶች እስቲ እንመካካር አይነት እንደሆነ ተረድቻለሁኝ፡፡ምክንያቱም በዚህ ወቅት አቶ መለስ ገና የ36 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡አብዛኞቹ መሰሎቻቸውም በዚሁ የእድሜ ክልል ውስጥና ከዚህም ባነሰ እድሜ ክልል ያሉ ናቸው፡፡ከዚህ በመነጨም አብዛኞቹ ከዚህ በፊት የራሳቸውን ቤተሰብ እንኳን በቅጡ አስተዳድረውና መርተው አያውቁም ነበር ማለት ነው፡፡ታዲያ በዚያ የውይይት መድረክ ላይ በአቶ መለስ ላይ የሚነበበው አጠቃላይ ስሜትና መንፈስ ያሁኑ አይነት ፈፅሞ አልነበረም፡፡ቢያንስ የኢትዮጵያዊነት ወጉና ባህሉ ብዙም እንዳሁኑ ባልጠፋበት ወቅት ስለነበር ፕሮፌሰር መስፍንንና ሌሎቹን ያናግሩ የነበረው ትህትና በተሞላበት መንፈስ ነበር፡፡እነ ፕሮፌሰር መስፍንም ቢያንስ ከበሬታና ተደማጭነት ይኖረናል በሚል ስሜት በወቅቱ በውይይቱ ላይ ደረታቸውን ነፍተው ነበር ይናገሩ የነበረው፡፡ዛሬ ያ ነገር ሁሉ ተረት ተረት ሆነና ቀረ፡፡ያ ነገር በሆነ ከ15 ዓመታት በኋላ እነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በአቶ መለስ የደህንነትና የፖሊስ አባላት የቆየ ባህላችን የሆነው ሽማግሌ የማክበር ወጋችን ተጥሎ በመሳሪያ ሰደፍ ተጎሸሙ፡፡እነ ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስን የመሰሉ ብርቅዬ የሀገር ቅርስና ኩራት በአቶ መለስና በሻእቢያ የደህንነትና የፖሊስ አባላት ጎረምሶች ምራቅ እየተተፋባቸው በጥፊ ተመቱ፡፡አቶ መለስ በእውቀትና በሀይል ይቀናቀኑኛል ያሰጉኛል የሚሉትን ሁሉ ቀስ በቀስ በሂደት ከስራቸው አስወገዱ፡፡
  ዲሞክራሲን ከዛሬ 20 ዓመት በፊት አሰፍናሁ ብለው ለህዝባቸው ቃል የገቡ ሰውዬ ፅድቁ ቀርቶ በቅቱ በኮነነኝ እንዲሉ ከ15 ዓመታት በኋላ እንኳንስ ዲሞክራሲ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ አደርጋለሁ የሚለውን አይደለም ጣቱን አውጥቶ የ V ምልክት የሚያሳየውን ማርያምን ምሬም አልምረው ከዚህ ወስልቶ የተገኘውን ሁሉ ጣቱን እቅርጣለሁኝ አሉ፡፡ትንሽ ጭል ጭል የሚለው የነበረውን የሀገሪቱን ዲሞክራሲ መሳይ ነገር በ2002 በተደረገው ሀገራዊ መርጫ ጭራሽ ድምጥማጡን አጥፍተው እንዲያውም ከዚህ በኋላ እርማችሁን አውጡ ከዚህ በኋላ እኔ አቶ መለስ ዜናዊና ፓርቲዬ ኢህአዲግ ልማታዊ መንግስት ነን ብለው አውጀው ዛሬ ፓርላማቸው ውስጥ በጭፍን ከሚደግፏቸው በራሳቸው የአስተሳሰብ አምሳል ከተቀጠቀጡና ከተፈጠሩ የራሳቸው የፓርቲ አባላት ውጪ አንድም ተቃዋሚ ፓርላማው ውስጥ እንዳይገባ አደረጉ፡፡በእርግጥ ዛሬ አቶ መለስ እንደ ድሮው ፓርላማ ሲገቡ እነዚህ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ሰዎች ዛሬ ደግሞ ምን ሊነዘንዙኝ ይሆን እያሉ እንደበፊቱ አይጨናነቁም ወይንም አይበሳጩም፡፡ስለዚህ ይህም አንድ ትልቅ እፎይታ ነው፡፡ዛሬ የሀይማኖት ሰዎች ትላልቅ የሀገር ሽማግሌዎችና የተከበሩ ታዋቂ ሰዎች አቶ መለስን ለመምከርና ለመገሰፅ አይደለም በሙሉ አይናቸው እንኳን ቀና ብለው ለማየት የማይደፍሩ ሰዎች ሆነዋል፡፡Therefore today Ato Meles has gradually evolved in to an absolute power that no one as such dares to challenge. And there is a saying that”Absolute power corrupts absolutely”. There is also a saying that conceit comes before fall.የመላእክት አለቃ የነበረው ሳጥናኤልም ከድሮ ክብሩና ዙፋኑ ተሽሮ በስተመጨረሻ ለአሁኑ ውድቀቱና እርግማኑ የተዳረገው እርሱንና መላእክትን የፈጠረው እግዚአብሄር ለጊዜው ሲሰወርባቸው ከእኔ ሌላ ማን የበላይ ገዢ አላችሁ ብሎ በእብሪት መፈንቅለ መንግስት አካሂዳለሁ ብሎ እንደሆነ ከሃይማኖት ሰዎች ሰምቻለሁኝ፡፡በሀገራችን አባባል መካሪ አታሳጣኝ ማለት እንዴት ትልቅ አባባል ነው፡፡እውነተኛ ወዳጅ እውነቱን ያለመዳለል ሽንገላ ይናገራል ስለዚህም ከሚመጣ ጥፋትና ስህተት ይታደጋል ማለት ነው፡፡ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን አሸባሪ እየተባልን እስር ቤት እየተጋዝን ነው፡፡
  አሸባሪ ተብለው እስር ቤት እየገቡ ያሉት ሰዎች የትኛውን ህንፃ የትኛውን ንፁሃን ዜጋ በቦምብ እንደ ጎዱና እንዳጠፉ ግልፅ በሆነ መልክ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡አንገቱን የሚደፋ ጭምት ዝምተኛና ብሶሰቱን ካልባሰበት በቀር እንባውን ወደ ሰማይ እየፈነጠቀ ለፈጣሪ አቤት የሚል የ3ሺህ ዘመን አኩሪ ታሪክ ያለው ሃይማኖተኛ ኢትዮጵያዊ ሽብርተኛ ከተባለ ማን ንፁህ ሊገኝ ነው ማለት ነው ታዲያ፡፡አሸባሪነት በሚለው ተራ የሚለጠጥ ትርጉም ከሄድንማ እየሱስ ክርስቶስ የማርያም ልጅ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በስጋ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ጥንተ ጠላታችንን ዲያብሎስን ባልጠበቀው መንገድ ስለመጣበት አሸብሮት እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ሰዎች ለስልጣናቸውና ለጥቅማቸው ሲሉ እኮ ሊሸበሩ ይችላሉ፡፡ሰዎች በሰሩት ሃጢያት ክፋትና ወንጀል የተነሳም እኮ ህሊናቸው እረፍት እያሳጣቸው ሊሸበሩ ይችላሉ፡፡ይህች አለም እንዲያው በራሷ የሽብር መድረክ አይደለችም እንዴ፡፡ዛሬ በየሚዲያው የምንሰማው ነገር ሁሉ አብዛኛው ሽብር አይደለም እንዴ፡፡መላው ኢትዮጵያውያን ባሁኑ ወቅት በኑሮ ውድነት ግራ ገብቶን በየመንገዱ ለብቻችን እያወራን እየተሸበርን አይደለም እንዴ፡፡አቶ መለስ በስራቸው ያሉት አማካሪዎች እረ ለመሆኑ እነማን ናቸው፡፡አቦይ ስብሃት ነጋ?ጄኔራል ሳሞራ የኑስ? ከነዚህ ነባር ሰዎች ሌላ ገለልተኛ የሆነ ሌላ እውነቱን ተናግሮ የሚገስፅ ሃይ ባይ የለም ማለት ነው?ሚስትም እኮ መልካም አማካሪ ነበረች፡፡

  ReplyDelete
 13. This is an article everyone should read again and again. But for now, in my belief and understanding, it is a very good message to His Excellency PM Melese Zenawi.

  Although he used to seem democrat In the early period of his reign, he has grown, much much more than everyone can think of, up to be Goliath of Dictators. Today heterogeneity vanished totally in Ethiopian politics. The dialect of EPRDF is Melese; the scholars and the laity with no difference speak of him, his words, they tend to imitate even his emotions that is really embarrassing not to be of oneself.

  The article remind me of a good management word "YES MEN".Persons who are always suppose to be obedient to their leaders or bosses irrespective of the merit or demerit (possible outcome) of their action.

  Hello Addis Ababa this is really a folklore like message from a social critic ,first and foremost, addressed to the Ruling Front with special emphasis to the Head, what I prefer to call ONE MAN BAND.

  MAY GOD BLESS ETHIOPIA AND ITS PEOPLE

  ReplyDelete
 14. Dn. Danial qale hiwot yasemaln teru melekt new.
  HG the GA

  ReplyDelete
 15. ዲ/ን፡ ዳኒኤል፡ ካንተ ፡ የተማርኩት፡ብዙ፡ነው:: አመስግናለሁ፡፡ ማሙ

  ReplyDelete
 16. "Ewurin ewur bimerawu huletum teyayizew gedel yigebalu" antu antu yalut hulu yakeberut yimeslewal.

  ReplyDelete
 17. yegaremal ayalekebehem,10q

  ReplyDelete
 18. ዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባት!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 19. Keteret wust eko kumneger yigegnal.....

  ReplyDelete
 20. አንዳንድ አሰተያየት ሰጭዎች ህፃን እንዳትባሉ ትልቅ
  ትመሥላላችሁ ትልቅ እንዳትሉ ስራችሁ የህፃን ነው
  ሰማችሁ ባይጠቀስም ሀፍረት ይሰማችሁ።

  ReplyDelete
 21. ይህ የዝንጀሮ አለቃ እርሱንም መንጋውንም ለገደል የሚያበቃ መጥፎ ባህሪ ያመጣው በራሱ አይደለም በዙርያው ያሉ አድር ባዮች አጎብዳጆች ናቸው እንዲህ ላለ ለማይረባ ህሊና አሳልፈው የሰጡት። ይህ ከእውነት የተጣላ አካሄዳቸው ደግሞ በመጨረሻ ለመሪም ለተመሪም አልበጀ ሁለቱንም ለገደል አበቃቸው። ይህ የሆነው ከቀያቸው ባለአእምሮዎችን ካጠፉ በኋላ ነበርና ለምድራቸው ትንሳዔ ሩቅ ናት። ምክንያቱም የሚተካው በይሁንትኞቹ አመለካከት የተበከለ ስልብ ትውልድ ነውና ወይ ከቀደሙት ከፍቶ ባለፈው ጊዜ ያመለጠውን ለማካካስ የተቆጨ የከፋ ይሁንተኛ/አድር ባይ/ ወይም በፍርሃት የተሸበበ ከራስ በላይ ነፋስ ብሎ የራሱን ዓለም ፈጥሮ ከመቃብር ያልተሻለ ኑሮን የሚመርጥ ሙት ትውልድ ነውና ያች ምድር በተአምር ካልሆነ በስጋና ደም የሚደረስበት ትንሳዔ የላትም።
  ይህ ምሳሌ እኛን በሁለንተናችን ይመስለናል በቤተክህነቱ ሄድን በቤተመንግስቱ በየቢሮው በየእድር በየማህበሩ ከዚያም አልፎ ስም ባወጣችሁ ሰዎቻችን ሕይወትም በገሃድ የሚነበብ ሃቅ ሆኖብናል
  ያ እራሱን ያቃጠለው ቱኒዚያዊ እንዲህ ባለው ማኅበረሰብ ቢሆን ራሱን ያቃጠለው ማነሳሳቱ ቀርቶ ስንት ይባልበት ነበር መሰላችሁ እብድ ነው አማኑዔል ገብቶ ነበር ከዚህ ጸበል እየተጠመቀ ነበር ብቻ ሌላም ሌላም ይባልና ጀግና መባሉ ማነሳሳቱ ይቀርና መቀበርያ ሊከለከል ፍትሃትም ሊቀርበት ይችል ይሆናል።
  መሪ ከህዝብ ይወጣል በልካቸውም ይገዛቸዋል እናም አመራር እንዲስተካከል ማህበረሰብ መስተካከል አለበት ማህበረሰብ ተስተካክሎ አመራር ባይስተካከል ጠበብከኝ ብለው ያወጡታል። ምዕመናን ሲንስተካከል እግዚአብሔር ደግሞ መልካሙን እረኛ ከየትም ያመጣዋል።በዝሙትና በስርቆት በግፍና በማጭበርበር በተለያየ የኀጢአት ስራ የሰበሰብነውን መባ ብናደርገው እግዚአብሔር ናቀው ቢንቀዉም አባ ቁራ ሆኑበት መነዘሩት በተኑት። ታዲያ ለዚህ መፍትሄው ዘመናዊ የሂሳብ አሰራር ሳይሆን መንፈሳዊነት ነው ዘመናዊ አሰራር ብንዘረጋ ወደ ዘመናዊ አዘራረፍ እንሸጋገር ይሆናል እንጂ በኀጢአት የመጣ መባ መቸም ቢሆን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ሊዉል አይችልም በንጽህና ብናመጣው ደግሞ እራሱ ይፈርዳል።ሌላውም ችግራችን የመጣው እንዲሁ በኛ ድክመት በኛ ለዚያ ለምንመኘው ነገር የተገባን ሆነን ባለለመገኘታችን ይመስለኛል።እናም ለችግራችን መፍትሄው አንድም ማህበረሰብን መቀየር (አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ደግም አስቸጋሪ ነው ሰነፍ ስለሆንኩ ይሆናል ለኔ ግን የማይሳካ ይመስላል) አልያም ተአምር ነው።
  ታዲያ እንዲህ ባለው ይሁንተኛ/አድር ባይ/ ማህበረሰብ ለወገን ለሃገር የሚቃጠል ልብ መያዝ አስተዋይ አእምሮን ገንዘብ ማድረግ ከይሁንተኝነት ቢሻልም ከጥቅሙ ቅጣትነቱ ያመዝናል።
  ለምን ሲባል ድካም ጣእሩ
  ምን ሊያክል ነው ጭንቀት ጋእሩ
  በዚህ ዘመን በዚች ምድር ክፉ ነግሶ ጠፍቶ ጥሩ
  ሕልመኛ ልብ ለምኔ
  ብርሃን ላይሆንልኝ ለፈዘዘው ዓይኔ
  ድጋፍ ምርኩዝ ላይሆን ለደቀቀው ጎኔ
  ምን ያደርጋል የሸክም እዳ
  እርባና ከሌለው ካላመጣ ፋይዳ
  ውሰደው ይቅርብኝ ከበደኝ ዝምድናው
  በትኩ ይሰተኝ ነፈዙ ዳዲባው
  እንዲሁ የሚኖር ማይሰርጽ የማይደማው
  እርሱን ልብ ስጠኝ አርፌ ልተኛው። ያስብላል።

  ReplyDelete
 22. thanks dn daniel .did this also works in indvidual level?felling oriented and mind oriented leadership.some times felling becomes beyound mind and the mind chalenges to overcome this,in the second they debate each other equally,and at the third they gain their supporirity one follows the other with out reasoning(at this time we are in danger if our felling gets the supperiority).
  may God bless you and all Ethiopian

  ReplyDelete
 23. Andand Anonymous min Abesachechehu?????????????
  ewunetun selengerachehu, selebletachehu........................keshemoch atehunu! erasachehunem Atasgemitu!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 24. Who said Yeteret Abat

  Hi Dear,

  I have come up with the understanding that you are:

  1. really, really a hater inside.
  2. you are not optimist
  3. you are not grown up with good morale,
  4. you don't have such values as rituals and civics.

  After reading your comment that is really embarrassing, I began thinking of the wonderful productions of Hollywood that gets the whole world stunned. All of them are based on what you call for less TERET. Folklore (TERET) has a big impact in the history of the civilized world. They are still using it to make the invisible world make visible, touchable, and sensible.

  Please, don't be arrogant boasting of yourself! Don't be ignorant of the valuable contributions of TERET and CITIZENS for these two are the cornerstones of civilization and prosperity.

  There have been a number of Ethiopian novelists, writers who wrote TERET. Are blaming of them as Yeteret Abat? There have been distinguished figures in the history of literature who lived for writing TERET? How do you feel this?

  What would you like to say about such world class films as Braveheart, Lord of The Rings, Titanic. All of them were produced based on TERET.

  Believe or not every wonderful achievements of the past was based on such simple but powerful thoughts called TERET. And the succession of it (the powerful thoughts) is manifested in today's advanced world.

  Let you cleanse you heart and get meditation to dig your true identity out form these heap of rubbish attitudes and thoughts.

  ReplyDelete
 25. it's such a nice story please keep it reading keep it reading keep it reading keep it reading keep it reading keep it reading keep it reading

  ReplyDelete
 26. በጣም ደስ ይላል

  ReplyDelete
 27. ዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባትዳንኤል ክብረት የተረት አባት!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 28. ህጻን ልጀ አንዴ እከሌ እኮ እንዲህ ብሎ ሰደበኝ አለ እያለቀሰ ካባበልኩት በሃላ ለመሆኑ ምን ብሎ ሰደበህ ብየ ስጠይቀው እርሱ ያለውን ከደገምኩትማ እኔም ባለጌ ሆንኩ ማለት ነው አለኝ ካንዳንድ አላዋቂዎች ህጻናት ይሻላሉ ለማለት ነው ዲያቆን ዳንኤል ጥሩ መልእክት ነው ጆሮ ላለው

  ReplyDelete
 29. እናም «ሰውን ከላይ ሆነው ከሚቆጡት፣ ከጎንም ሆነው ከሚሞግቱት ይልቅ ከሥሩ ሆነው የሚከተሉት ጀሌዎች ይበልጥ ይጎዱታል፤ ከላይ ሆነው ከሚያሳዩት ታላላቆቹ፣ ከጎን ሆነው ከሚገዳደሩት እኩዮቸ$ ይልቅ፣ ከሥር ሆነው ይሁን ብቻ የሚሉት አንጋሾቹ ይበልጥ ይጎዱታል» ተ

  ReplyDelete
 30. Hope In this Blog, some Sycophant cadres or the beneficiaries of the incumbent Government are abusing this respected blog while we are using it.... Why You say Daniel a father of Tale! if it is taken positively I thumb up if not rebuke urselves!!! Dont fall at a trap!!!
  Danie This ill remarks make you strong!!!!!!!

  ReplyDelete
 31. min malet naw yeteret abat malet....you don't deserve even to read this article...

  ReplyDelete
 32. ሕግ አውጪው፡ሕግ ተርጓሚው፡ሕግ አስፈፃሚው፡ፍርድ ቤቱ፡ፖሊሱ፡ምርጫ ቦርድ፡የመገናኛ ብዙሀን በተለይ የመንግስት የሆኑቱ እና በስም የግል ሆነው በመንግስት የሚደገፉት፡ጋዜጠኞች፡…..አስቡበት፡፡ሌላው ቢቀር በሰፈራችሁበት ቁና ይሰፈርላቹሀል፡፡እናንተም አንድ ቀን አንድ ነገር እንቢ ብትሉ መንግስት ያለ ፍርድ አግባብ ባልሆነ መልኩ ይቀልድባቹሀል፡፡ያኔ ሁሉም ነገር ይገባቹሀል፡፡የዘራችሁትን ታጭዳላቹ፡፡ያ ከመሆኑ በፊት ለራሳችሁ ስትሉ እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ብርሐኑን ብርሐን ጨለማውን ጨለማ ማለት ልመዱ፡፡አምባገነኖችን አንፍጠር፡፡አናቅብጣቸው፡፡አረመኔ ገዢዎቻችን እኮ አንድ ቀን ጽዋው ሲሞላ ባይወዱም በግድ ስልጣኑን ይለቃሉ፡፡ያኔ እናንት ወዴት ማን ጋር ትሄዳላቹ???????? አስቡበት፡፡ቅድሚያ ለወገን፡፡በወገን ደም አትነግዱ፡፡አዲስ አበባው ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 33. ሰውን ከላይ ሆነው ከሚቆጡት፣ ከጎንም ሆነው ከሚሞግቱት ይልቅ ከሥሩ ሆነው የሚከተሉት ጀሌዎች ይበልጥ ይጎዱታል፤ ከላይ ሆነው ከሚያሳዩት ታላላቆቹ፣ ከጎን ሆነው ከሚገዳደሩት እኩዮቸ$ ይልቅ፣ ከሥር ሆነው ይሁን ብቻ የሚሉት አንጋሾቹ ይበልጥ ይጎዱታል» Tikikil new! \\ kelay yeteret abat yalkew antem indnezih zinjerowoci yaluhin teketileh indehone yastawukal. belu ingide teyayizacihu ...\\
  Wendim Daniel Berta Berta EmeBirhan Tiketelih!!!!
  ijih yibarek!!!!

  ReplyDelete
 34. hone bilew litiluh yalhone comment bememociacer yagodefuh mesilo betesemacew qutir Ante lemititsifacew Tsihufoci yalegn FIIKIR iyecemere meta. HULUM NEGER LEBEGO NEW. DANI BERTA!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 35. this is for Mengistu than Meles,because the former was more aggressive and shuts a bullet for any one who opposed him withot giving time and without any confirmation.This is not only for Mengistu,but for almost all African leaders at that era.

  ReplyDelete
 36. enezih adirbayoche "gebeya siyameche" bemilew sihufi lay yalut hilina bisoche gare temesasay yimesleghale. geni ande neger malet yemifeligew keseweche gare sawera yalikutni degmew yinegrughale ena hunetaw yastelaghe neber ahune geni kezeh sihuf endeteredawt minalbat diktater lihun eyalku yehun way ways enezeh aynet sewache maseb makom new lemelew neger endteyik argoghali

  ReplyDelete
 37. i can only said thank you. coz i dont have another word to say.

  ReplyDelete
 38. Niceeeeeeeeeee Article.

  ReplyDelete
 39. Hi Dani I love the story I know a guy like this he is the General manager of one NGO I love it

  ReplyDelete
 40. hummmmmmmmmmmm Good

  ReplyDelete