Thursday, September 29, 2011

መርዙ


እነሆ ሁለት እና ሚስቶች መኖራቸው ተነገረ፡፡ ግን ፈጽሞ ሊስማሙ አልቻሉም ተባለ፡፡ ቤታቸው የትዳር ቤት ሳይሆን አፍጋኒስታን ይመስል ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ለምን ሊጋቡ እንደቻሉ ሁለቱንም ያስገርማቸዋል፡፡ አንድ ደራሲ Men from Mars and women from Venus የሚል መጽሐፍ ጽፏል፡፡ እንደተፈጥሯቸው እና ጠባያቸው ቢሆን ኖሮ ወንድ እና ሴት ተጋብተው መኖር የማይችሉ ፍጡራን ነበሩ ነው ጠቅላላ ሃሳቡ፡፡ የትዳር የዘለቄታ ፎርሙላም ይህንን እውነታ ከመረዳት ይመነጫል ባይ ነው፡፡
ታድያ እነዚህኞቹ ከዚህም የባሱ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ እና ጣልያን፣ እንግሊዝ እና አርጀንቲና፣ አሜሪካ እና ቬትናም፣ ይመስላሉ፡፡
 አንዳቸው የሚናገሩት ለሌላቸው አይጥምም፡፡ እንዋደዳለን ብለው ሳይሆን እንበሻሸቃለን ብለው የተጋቡ ይመስላሉ፡፡ ሁለት ተቀዋዋሚ ፓርቲዎች አንድ መንግሥት መሥርተው እርስ በርስ መከራ የሚያዩበት ሀገር ሆኗል ቤታቸው፡፡ «ትዳር ማለት ከውጭ ያሉት እንግባ እንገባ፣ ከውስጥ ያሉት እንውጣ እንውጣ የሚሉበት ነው» የተባለው የተፈጸመው በእነርሱ ነው፡፡
በቤታቸው ቀስ ብሎ የሚናገር የለም፡፡ ባልም ይጮኻል፣ ሚስትም ትጮኻለች፤ እነርሱንም ተከትትሎ ቤቱ ራሱ ይጮኻል፡፡ የሚገርመው ነገር በሩ ሲከፈት ይጮኻል፤ ቴሌቭዥኑ ይጮኻል፤ ጠረጲዛው ሲሳብ ይጮኻል፤ ወንበሩ ሲጎተት ይጮኻል፤ ሁሉም ይጮኻል፡፡
ከአማርኛ ድምፆችች ሁሉ «» የምትባለው ድምፅ እዚህ ቤት እንዳትደርስ ተከልክላለች፡፡ «እንትናዬ» እየተባለ ሲጠራ ሰማሁ የሚል የለም፡፡ « አንተ፣ አንቺ፣ ስማ፣ ስሚ» ቤቱ የወታደር ካምፕ ነው የሚመስለው፡፡
እናም ሁለቱም መረራቸው፡፡ መፋታት አሰቡ፤ ግን ፍርድ ቤት ምን እንደሚወስን አይታወቅም፡፡ ለአንዱ አብልጦ ለሌላውም አሳንሶ ቢወስን ሞት መስሎ ተሰማቸው፡፡ ይኼ በቤታቸው ገብቶ የሚያነታርካቸው ሰይጣን ለሁለቱም በአንድ ጊዜ አንድ ክፉ ነገር አመለከታቸው፡፡ አንዱ ሌላኛውን በመርዝ ለመግደል፡፡ አሰቡ ሁለቱም፡፡ እናም ምናልባት መፍትሔ ይሰጠናል ብለው ወደሚያስቡበት አንድ ዐዋቂ ዘንድ ለመሄድ በየግላቸው ወሰኑ፡፡
መጀመርያ ባል ከሚስቱ ተደብቆ ዓርብ ዕለት ወደ ዐዋቂው ቤት ሄደ፡፡ እዚያም ደርሶ ችግሩን ሁሉ ነገረው፡፡ «እኔ ከሚስቴ ጋር መነታረክ ሰለቸኝ፤ አንድ ቀን እንደ ሰው ጥሩ ነገር ሳንነጋገር ይኼው አምስት ዓመት ሆነን፡፡ ነጋ ጠባ ጠብ ነው፡፡ አሁን መረረኝ፡፡ እርሷ ከግራ ጎኔ ሳይሆን ከምላሴ ነው የተፈጠረችው፡፡ የመጣሁት እርሷን ጸጥ አድርጎ የሚገድል መርዝ እንድትሰጠኝ ነው» አለው፡፡ ዐዋቂውም በሃሳቡ ተስማማ፡፡ «ነገር ግን» አለው ዐዋቂው «ሚስትህን በአንድ ቀን በመርዝ ብትገድላት ተጠርጥረህ ትያዛለህ፡፡ ስለዚህ ቀስ በቀስ የሚገድል መርዝ ልስጥህ» አለው፡፡ ባልም ተስማማ፡፡ «ይኼ መርዝ በምግብ፣ በመጠጥ፣ በአልጋ ላይ፣ በወንበር ላይ የሚደረግ ነው፡፡ ሚስትህ ጠርጣራ ናት፡፡ ልትደርስብህ ትችላለች፡፡ ጎረቤቶችህም እንደምትጣሉ ያውቃሉ፡፡ አንድ ነገር ብትሆን ይጠረጥሩሃል፡፡
ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ጠባይህን ቀይር፡፡ እያቆላመጥክ በስሟ ጥራት፡፡ አልጋዋን አንጠፍላት፣ ምግቧን ሥራላት፤ ከውጭ ስትመጣ ስጦታ አምጣላት፤ ሻሂ አፍላላት፤ ራት ጋብዛት፤ ልብሷን ተኩስላት፤ እንዴው በአጠቃላይ ተንከባከባት፡፡ ነገር ግነ ምግብ ስታበላት በምግብ ላይ፣ መጠጥ ስታጠጣት በመጠጡ ላይ፣ ልብሷን ስትተኩስ በልብሷ ላይ፣ አልጋ ስታነጥፍ በአልጋው ራስጌ በኩል ይህንን መድኃኒት ቀስ አድርገህ በትንበት፡፡ ቀስ በቀስ ይገድላታል፡፡ አንተም ትገላገላለህ» አለው፡፡
ባልዬው ተደሰተ፡፡ ያላሰበውን የመፍትሔ ሃሳብ ዐዋቂው በማምጣቱ ዘሎ አቀፈው፡፡ በኪሱ የነበረውን ገንዘብም እንዳለ አወጣ፡፡ ያን ጊዜ ዐዋቂው «አሁን አትከፍልም፤ መድኃኒቱ ሠርቶ ሚስትህ ከሞተች በኋላ ትከፍላለህ፤ አንድ ነገር ግን ጠብቅ፡፡ ሚስትህ  ምናልባት ጠባይዋን ለትቀይር ትችላለች፤ ያን ጊዜ መድኃኒቱ እየሠራ መሆኑን በዚህ ታረጋግጣለህ» አለው፡፡ እየፈነጠዘ መድኃኒቱን ቋጠሮ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
በማግሥቱ ደግሞ ሚስቱ ተደብቃ መጣች፡፡ «ባሌ ሊገድለኝ ነው፡፡ እኔኮ ባል ሳይሆን ሙቀጫ ነው ያገባሁት፡፡ ሥራው መጨቅጨቅ ብቻ፡፡ አሁን የመጣሁት ከዚህ ሰው ጋር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንድትለየኝ ነው፡፡ መርዝ የለህም ወይ» አለቺው፡፡ «ሞልቷል» አላት ዐዋቂው በፈገግታ፡፡ «የፈለግከውን ያህል ልክፈለህ ስጠኝ» አለቺው፡፡
ወደ ጓዳ ገባና በጨርቅ የተቋጠረ ነገር ይዞላት መጣ፡፡ «እይውልሽ ይሄ መርዝ ነው፤ ግን በአንድ ቀን አይገድልም» አላት፡፡ ተናደደች፡፡ «እኔ ኮርኳ የሚያደርገውን ነው የምፈልገው» አለቺው፡፡ «እርሱማ አደጋ አለው፡፡ ጤነኛ የነበረ ሰው በድንገት ሲሞት መመርመሩ፣ መጠርጠሩም አይቀር፡፡ ለእኔም ትተርፊኛለሽ» አላት፡፡ አሰብ አደረገቺና «ታድያ ምን ይሻላል አለቺው፡፡ «ቀስ በቀስ የሚገድል ይሻልሻል፤ እየታመመ ስለሚሞት ሰው አያውቅብሽም» አላት፡፡ ተስማማች፡፡
«አወሳሰዱ ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ በምግብ፣ በመጠጥ፣ በአልጋ፣ በወንበር፣ በልብስ፣ ነው የሚሰጠው፡፡ መጀመርያ ጠባይሺን ቀይሪ፡፡ ያለበለዚያ እሺ ብሎ አይወስድልሺም፡፡ የወደድሺው ምሰዪ፡፡ እቀፊው፣ ሳሚው፣ እጅ የሚያስቆረጥመውን ምግብ ሥሪለት፤ ልብሱን እጠቢለት፤ ፈገግ ብለሽ ተቀበዪው፤ አብራችሁ ተዝናኑ፤ ከጎኑ አትለዪ፡፡ ታድያ ምግብ ስታቀርቢ፣ መጠጥ ስትሰጭው ከዚህ መድኃኒት ትንሽ ብትን አድርጊበት፡፡ ስትተኙም አልጋው ላይ በግርጌው በኩል በተን አድርጊ፡፡ ልብስ ስታጥቢም ይህንን ጨምረሽ አብረሽ እጠቢበት፡፡ በየጊዜው ቤቱን በሚገባ አዘጋጅተሽ በየጥጋ ጥጉ ይህንን በተን በተን አድርጊ፡፡ ከዚያ የፈለግሺው ሁሉ ይሳካል» አላት ዐዋቂው፡፡
በቦርሳዋ የያዘቺውን ሁሉ ገንዘብ ሠፍራ ልትሰጠው ስትል፡፡ «የምትከፍዪው ባልሽ ከሞተ በኋላ ነው» አላት፡፡ ብታደርግ ብትሠራው ሊቀበላት አልቻለም፡፡ መድኃኒቷን ይዛ የሚሆነውን ሁሉ እያሰላሰለች ወጣች፡፡ ልትወጣ ስትል እንዲህ አላት «ባልሽ ጠባዩን መቀየር ይጀምራል፤ ያን ጊዜ መድኃኒቱ እየሠራ መሆኑን በዚህ ታውቂያለሽ»
ቤት እንደገባች ዐዋቂው ባዘዛት መሠረት ቤቷን ታዘጋጅ ጀመር፡፡ ያንን አይታው የማታውቀውን ጓዳ ጎድጓዳ መልክ መልከ ሰጠቺው፡፡ አቧራውን አራገፈች፤ ዕቃውን ቀየረች፤ ወንበር እና ጠረጲዛውን መልክ መልክ ሰጠቺው፤ ግድግዳው ታጠበ፤ አዳዲስ የጌጥ ዕቃዎች በየመልካቸው ተሰቀሉበት፡፡ ከዚያም ወደ ማዕድ ቤት ገብታ እጅ የሚያሰቆረጥም ዶሮ ሠራች፡፡ መጠጡ ተገዛ፤ ቡናው ተፈላ፤ ፈንዲሻው ተፈነደሸ፤ ቤቱ ዓመት በዓል መሰለ፡፡ ሁሉም ነገር ላይ ግን መድኃኒቱ በተን ተደርጓል፡፡
ባል እንደ ለመደው አምሽቶ ከሥራ ገባ፡፡ ዐዋቂው እንዳለው ለሚስቱ ስጦታ የሚሆን ሽቱ፣ ጫማ እና አበባ ይዟል፡፡ መንገድ ላይ ከመድኃኒቱ በተን አደረገበት፡፡ ምን እንደሚፈጠር ባለማወቁ ሲፈራ ሲቸር በሩን መታ፡፡ ድሮ «ምን ትደበድባለህ ከፍተህ አትገባም» የሚለው ድምፅ ነበር የሚሰማው፡፡ አሁን አንድ እጅ ከፈተለት፡፡ ቤቱ ብሏል፡፡ «ማርዬ ደኅና አመሸሽልኝ» ሲላት ልቧ ወከክ አለ፡፡ «መድኃኒቱ መሥራት ጀመረ ማለት ነው» አለች በልቧ፡፡ እቅፍ አድርጋ ሳመቺው፡፡ ዓይኑንም ጉንጩንም አላመነውም፡፡ ከመጠራጠሩ የተነሣ «እርሷ ናት የሳመቺኝ ወይስ እኔ ነኝ የሳምኳት» እያለ ይጠይቅ ነበር፡፡ ዐዋቂ ያለው እውነቱን ነው ማለት ነው፡፡
ያመጣላትን ሰጦታ ስታይ «በውኔ ነው ወይስ በሕልሜ፣ ወይስ በቴሌቭዥን» አለች፡፡ «የኔ ፍቅር፣ በጣም ነው የምወድህ» አለቺና ወደ ወንበሩ ወሰደቺው፡፡ አብረው ተቀመጡ፡፡ እርሷ ምግብ ልታቀራርብ ወደ ጓዳ ስትገባ በፍጥነት ጎንበስ አለና ወንበሩ ውስጥ መድኃኒቱን በተን አደረገው፡፡
ምግቡን አቅርባ መጠጡን ልታመጣ ሄደች፡፡ አሁንም አወጣና ወጡ ውስጥ በተን አደረገ፡፡
እንደ ጉድ ተበላ፡፡ ተጠጣ፡፡ ከተጋቡ ከሁለት ወር በኋላ ጀምሮ እንዲህ እየተጎራረሱ በፍቅር በልተው አያውቁም፡፡ በሞቴ፣ አፈር ስሆን፣ እየተባባሉ ጨረሱት፡፡ መድኃኒቱ ሠርቷል አሉ በልባቸው፡፡ አምስት ዓመት ሙሉ ያልተጫወቱትን ወሬ ሲያወጉት አመሹ፡፡ አምሽተውም አልቀሩ ወደ እልፍኛቸው ገቡ፡፡ እርሷ ቀድማ ባኞ ቤት ገባች፡፡ እርሱ ተሽቀዳድሞ በራስጌ በኩል መድኃኒቱን በተን አደረገው፡፡ መጣች፡፡ ደግሞ እርሱ በተራው ባኞ ቤት ገባ፡፡ እርሷም በግርጌው በተን አደረገች፡፡ ሁሉም በተኑ፡፡ እነርሱም በፍቅር ብትን አሉ፡፡
ሌሊቱ የፍቅር ሆኖ አለፈ፡፡ ሁሉም በየልባቸው በመድኃኒቱ መሥራት ተደሰቱ፡፡ የሟችን ቀን መቼ እንደሚሆን መገመትም ያዙ፡፡
ሕይወት ቀጠለ፡፡ መገባበዝ ነው፡፡ መዝናናት ነው፡፡ መጨዋት ነው፡፡ መደዋወል ነው፡፡ መነፋፈቅ ነው፡፡ አብሮ መውጣት ነው፡፡ አብሮ መግባት ነው፡፡ ያቺ የጠፋቺው «» ተመልሳ ገባች፡፡ እርሷም እነ «» ይዛ መጣች፡፡ «» «የኔ ቆንጆ፣ የኔ እመቤት፣ የኔ ጌታ፣ የኔ ማር» የሚባሉ ዘር ማንዘሮቿን ጋበዘቻቸው፡፡ እናም ቤቱ ሞቀ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ረስተውት የልብ የልባቸውን ያወሩ ጀመር፡፡ ለምን እንደዚያ ሊሆኑ እንደቻሉ፡፡ መደማማጥ እና መስማማት ለምን እንዳቃታቸው ያወራሉ፡፡ ወዲያው ትዝ ሲላቸው ደግሞ በየግላቸው ተደብቀው መድኃኒቷን በተን ያደርጋሉ፡፡
እየቆዩ ይኼኛው ኑሯቸው እየጣፈጣቸው መጣ፡፡ የማይጠገብ ሆነባቸው፡፡ ተገናኝተው ለመለያየት ሲጨነቁ፤ ተለያይተው ለመገናኘት ሲነፋፈቁ ጊዜ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡ የቤታቸው ሙቀት ሲጨምር፣ የልባቸው ትርታ ሲንር ጊዜ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡ አንዱ ለአንዱ ታዛዥ፣ አንዱ ለአንዱ አሳቢ፣ አንዱ ለአንዱ አዛኝ፣ አንዱ ለአንዱ መካሪ ሲሆኑ ጊዜ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡
ሁለቱም በየልባቸው፡፡ «ይህንን የመሰለ ኑሮ ለምጄ አሁን ቢሞትብኝስ/ ብትሞትብኝስ» ይሉ ጀመር፡፡ ሞት እንዳልናፈቃቸው፣ ሕይወት አጓጓቸው፡፡ ትዳር ምን እዳ ነው እንዳላሉ፣ ፍቺ ምን እዳ ነው ብለው አዜሙ፡፡
እናም ሁለቱም መድኃኒት አድርገዋል፤ ሁለቱም፣ ለመግደል አሢረዋል፡፡ ግን እንዲህ የሚሆን አልመሰላቸውም፡፡ ደግሞ ይህንን ምሥጢር አንዱ የሌላውን አያውቅም፡፡ በዚህ የፍቅር ሞቅታ ውስጥ አንዱ ከሌላው ይህንን ቢሰማ ምን ይላል? እያሉ ተጨነቁ፡፡
ባል ሲከንፍ ወደ ዐዋቂው ቤት ገሠገሠ፡፡
እርሱም እያለቀሰ ተንበረከከ «ሚስቴን መልስልኝ፤ እፈልጋታለሁ መልስልኝ በፊት ከከፈልኩህ ሦስት እጥፍ እከፍልሃለሁ፤ ብቻ መልስልኝ፡፡ እኔ እንደዚህ መሆንዋን መች ዐወቅኩ» እጁን እንደ ሚማጸን ሰው አቅንቶ ለመነው፡፡
«በል» አለ ዐዋቂው፡፡ «ከባድ ነገር ነው የጠየቅከኝ፤ ተነሣና እዚያኛው ክፍል ግባ» አለው፡፡ ተነሥቶ ወደዚያኛው ክፍል ሲገባ ዓይኑን ማመን አልቻለም፡፡ ሚስቱ ተንበርክካለች፡፡ እንዴት መጣች? አለ በልቡ፡፡ ሮጦ ተጠመጠመባት፡፡ «ይቅር በይኝ የኔ ማር» አለ አቅፏት እያለቀሰ፡፡ «አንተ ይቅር በለኝ እንጂ» አለቺው እንዳቀፈቺው፡፡
«ቁጭ በሉ» አለ ዐዋቂው፡፡
ተቀመጡ፡፡
«ሁለታችሁም ባልኳችሁ መሠረት መድኃኒቱን አድርጋችኋል ሲላቸው ተያዩ፡፡ ተደናገጡ፡፡ «አንቺም አድርገሻል አለ ባል፡፡ «አንተም አድርገሃል አለች ሚስት፡፡ «አለቅና» ተባባሉ፡፡
«አላለቃችሁም» አለ ዐዋቂው፡፡ «የሰጠኋችሁ መርዝ አይደለም» ሲላቸው ዘለው ተቃቀፉ፡፡ «እንዲሁ ተራ ቅጠል ነው፡፡ የናንተ ችግር አለመተዋወቅ ነው፡፡ ውስጣችሁ ፍቅር አለ፡፡ ግን ፍቅራችሁን መግለጥ አልቻላችሁም፡፡ ለፍቅር እድል አልሰጣችሁትም፡፡ ትዳር ብዙ በመነጋገር እና በመወያየት ሳይሆን አንዳችሁ ለሌላችሁ በማድረግ ነው የሚገነባው፡፡ አንዱ ሌላው የሚፈልገውን ካደረገ፣ ራሱ የሚፈልገውን እንዳደረገ ይቆጠራል፡፡ ባል ለሚስት፣ ሚስትም ለባል መኖር አለባት፡፡ ባል ራሱን በሚስቱ ውስጥ፣ ሚስትም ራስዋን በባልዋ ውስጥ ማግኘት አለባት፡፡
ብዙ ባል እና ሚስቶች ለመዳር እንጂ ለመጋባት አልታደሉም፡፡ አብረው ይኖራሉ እንጂ አንዳቸው በሌላቸው ውስጥ አይኖሩም፡፡ ትዳር ማለት የሁለት ወንድ እና ሴት ወደ አንድ ጎጆ መግባት አይደለም፡፡ ባል ወደ ሚስት ሚስትም ወደ ባል ውስጥ መግባት እንጂ፡፡ ባል ራሱን ሚስቱ ውስጥ ካገኘው፡፡ ለሚስቱ የሚያደርገውን ለራሱ እንዳደረገው ነው የሚቆጥረው፡፡ ሚስትም እንዲሁ፡፡
ለወደፊቱም ብዙ አታውሩ፣ ግን ብዙ አድርጉ፤ አትዘዙ፣ ታዘዙ፤ እግዚአብሔር ሴትን ሰጥቶሃል፣ ሚስት ማድረግ ያንተ ድርሻ ነው፡፡ ለአንቺም እግዚአብሔር ወንድን ሰጥቶሻል ባል ማድረግም ያንቺ ድርሻ ነው፡፡
እንደ ተቃቀፉ ከዐዋቂው ቤት ወጡ፡፡ እነሆ ለትውስታ እንዲሆን ዛሬም ያንን መድኃኒት ትንሽ ብትን ያደርጋሉ፡፡
ከቨርጂንያ ወደ ላስ ቬጋስ ጉዞ ላይ፣ ዩናይትድ አየር መንገድ
ማስገንዘቢያ
የሃሳቡ መነሻ መንግሥቱ አሰበ የላከልኝ የቻይና ተረት ነው

56 comments:

 1. it is interesting 10q dany,

  ReplyDelete
 2. ኤልያስ
  ትክክል ብለሃል ፡፡ ተረቱን ከዚህ በፊት አንብቤዋለሁ፡፡ በሚስትና በባል እናት መካከል ያለውን ንትርክ እንዴት የሰፈር አወቂ እንዳከመው የሚተርክ ነበር፡፡
  ዛሬ ደግሞ ተዋናዮቹን በመለወጥ መልእክቱን ለማሰተላለፍ አስችሎሃል፡፡ መልካም ነው !

  ReplyDelete
 3. ብዙ ባል እና ሚስቶች ለመዳር እንጂ ለመጋባት አልታደሉም፡፡ አብረው ይኖራሉ እንጂ አንዳቸው በሌላቸው ውስጥ አይኖሩም፡፡ ትዳር ማለት የሁለት ወንድ እና ሴት ወደ አንድ ጎጆ መግባት አይደለም፡፡ ባል ወደ ሚስት ሚስትም ወደ ባል ውስጥ መግባት እንጂ፡፡ ባል ራሱን ሚስቱ ውስጥ ካገኘው፡፡ ለሚስቱ የሚያደርገውን ለራሱ እንዳደረገው ነው የሚቆጥረው፡፡ ሚስትም እንዲሁ፡፡

  Thanks Dani!

  ReplyDelete
 4. ብዙ ባል እና ሚስቶች ለመዳር እንጂ ለመጋባት አልታደሉም፡፡ አብረው ይኖራሉ እንጂ አንዳቸው በሌላቸው ውስጥ አይኖሩም፡፡ ትዳር ማለት የሁለት ወንድ እና ሴት ወደ አንድ ጎጆ መግባት አይደለም፡፡ ባል ወደ ሚስት ሚስትም ወደ ባል ውስጥ መግባት እንጂ፡፡ ባል ራሱን ሚስቱ ውስጥ ካገኘው፡፡ ለሚስቱ የሚያደርገውን ለራሱ እንዳደረገው ነው የሚቆጥረው፡፡ ሚስትም እንዲሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. Marriage doesn't come through finding the right mate, but through being the right mate! ~Barnett R. Brickner

  ReplyDelete
 6. ዳኒ ቸሩ እግዚሐብሄር ይባርክህ ይህ በዚህ ዘመን ላሉ ባለትዳሮች ምክር ብቻ ሳይሆን ተግሳጽም ይሆናል

  ReplyDelete
 7. Thanx Dani you are teaching me a lot. I am reading your articles since 2010 and I found most of them are very helpful for me. May God bless you, your family and your service.

  ReplyDelete
 8. ዳኒ እኔ በትዳር ውስጥ ነው ያለሁት አንደኛ ዓመታችንን ከአንድ ሴት ልጃችንና ከሚዜዎቻችን ከቤተሰብ ጋር ለማስታወስ ያክል መስከረም 9 ቀን 2004 ዓ.ም. በመዝሙር አክበረነዋል፡፡ ይህ ጽሑፍ በተለይ በትዳር ላሉት እጅግ ጠቃሚ ነገሮችን የያዘ ነው፡፡ ፍቅር መስጠት ነው፡፡ ዳኒ በዚ አጋጣሚ ልልህ የምፈልገው ነገር አለኝ፡፡ ሦስት ጉልቻዎች የሚለውን ስብከት ሥስት ጊዜ አዳምጬዋለሁ፡፡ ለዋጭ የሆነ ነው፡፡ እባክህ አሁን ካለው ሁናቴ ጋር አዛምደህ በድጋሚ በሲዲ ቢዘጋጅ በየጓዳ ጎድጓዳው ገብቶ የብዙ ሰዎችን ትዳር ያድሳል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እግዚአብሔር ጥበቡንና ጉልበቱን ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 9. lebaltedarochu fiker wana mina yetechawetw eko balemerzu new manew beahuni seat yemiyastrk hasab yemifetire?enga engedih

  ReplyDelete
 10. Dear Daniel, What a nice advise is this? Enjoy your stay in US.

  ReplyDelete
 11. Dani

  thank you, it is so interesting and treachery.

  would you tip me the picture related to the article?

  Yours ,

  ReplyDelete
 12. kale hiwot yasemalen tiru timhrtawi new

  ReplyDelete
 13. I have read the china version, Dani to be honest I like this one more. Thank u GBU

  ReplyDelete
 14. ብዙ ባል እና ሚስቶች ለመዳር እንጂ ለመጋባት አልታደሉምባል ራሱን ሚስቱ ውስጥ ካገኘው፡፡ ለሚስቱ የሚያደርገውን ለራሱ እንዳደረገው ነው የሚቆጥረው፡፡ ሚስትም እንዲሁ፡፡እግዚአብሔር ሴትን ሰጥቶሃል፣ ሚስት ማድረግ ያንተ ድርሻ ነው፡፡ ለአንቺም እግዚአብሔር ወንድን ሰጥቶሻል ባል ማድረግም ያንቺ ድርሻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 15. dani betam temechitignal.egiziabher yitebikih

  ReplyDelete
 16. ለወደፊቱም ብዙ አታውሩ፣ ግን ብዙ አድርጉ፤ አትዘዙ፣ ታዘዙ፤ እግዚአብሔር ሴትን ሰጥቶሃል፣ ሚስት ማድረግ ያንተ ድርሻ ነው፡፡ ለአንቺም እግዚአብሔር ወንድን ሰጥቶሻል ባል ማድረግም ያንቺ ድርሻ ነው፡፡
  እንደ ተቃቀፉ ከዐዋቂው ቤት ወጡ፡፡ እነሆ ለትውስታ እንዲሆን ዛሬም ያንን መድኃኒት ትንሽ ብትን ያደርጋሉ፡፡

  ሰሎሞን ደጀኔ ከደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ

  ReplyDelete
 17. It is a good idae GOD bless you DANI....

  ReplyDelete
 18. It is a good Idea God bless you Dani

  ReplyDelete
 19. It is a good Idea God bless you Dani

  ReplyDelete
 20. አንዱ ሌላው የሚፈልገውን ካደረገ፣ ራሱ የሚፈልገውን እንዳደረገ ይቆጠራል፡፡ ባል ለሚስት፣ ሚስትም ለባል መኖር አለባት፡፡ ባል ራሱን በሚስቱ ውስጥ፣ ሚስትም ራስዋን በባልዋ ውስጥ ማግኘት አለባት፡፡

  ReplyDelete
 21. I believe as a human being we are blessed with the intelligence, method and desire to make permutations for a good effect and fix when it gets wrong. Daniels views on this subject as depicted above are one sufficient example. I also entirely agree with the idea that what ever I do for my wife is deemed as being beneficial for me too.

  ReplyDelete
 22. nice story ,we have to also encourage such አዋቂ ሰው!

  ReplyDelete
 23. thanx for being with us in Las vegas ...Demera be'al was so adorable!!!

  ReplyDelete
 24. ብዙ ባል እና ሚስቶች ለመዳር እንጂ ለመጋባት አልታደሉም፡፡ አብረው ይኖራሉ እንጂ አንዳቸው በሌላቸው ውስጥ አይኖሩም፡፡ ትዳር ማለት የሁለት ወንድ እና ሴት ወደ አንድ ጎጆ መግባት አይደለም፡፡ ባል ወደ ሚስት ሚስትም ወደ ባል ውስጥ መግባት እንጂ፡፡ ባል ራሱን ሚስቱ ውስጥ ካገኘው፡፡ ለሚስቱ የሚያደርገውን ለራሱ እንዳደረገው ነው የሚቆጥረው፡፡ ሚስትም እንዲሁ፡፡


  ምርጥ ታሪክ ነው፡፡

  ReplyDelete
 25. No words! Thank u so much! God bless you!

  ReplyDelete
 26. D.n daniel, GOD BLESS U.

  ReplyDelete
 27. many thanks Dn. Naniel for this important article.God bless you . . .

  ReplyDelete
 28. dani God bless you tanks so much

  ReplyDelete
 29. ዳኒ! በእውነት ጥሩ ባልና ሚስት ለመሆን የሚያችል ምክር ነው፡፡
  እግዚአብሄር ያበርታህ!!!

  ReplyDelete
 30. Dani igziabher yibarkihDani igziabher yibarkih

  ReplyDelete
 31. dani igziabher yibarkih

  ReplyDelete
 32. Dear Daniel,
  It is a Good advice for those partners who did not have peace in their marriage.After I read it,I want to share this fantastic view of yours for those who have no access to get it. I printed it and distributed to partners while we were celebrating MESKEL together with neighborhoods.After everybody read it we discussed over it. Really it is great contribution to maintain marriages at the eve of divorce.

  ReplyDelete
 33. Wow dani, u r so smart! 10q for what u r writing! Dingle maryam kekefu neger & fetena tetebekeh. Kalehiwoten yasemah mengiste semayaten yawerseh amen! r writing! Dingle maryam kekefu neger & fetena tetebekeh. Kalehiwoten yasemah mengiste semayaten yawerseh amen!

  ReplyDelete
 34. Betam astemari new dani Igziabher yistilin. Negeru misalie bihonim Gin Lemehonu indih yale sewun yemiafakir << awaki >> ale?

  ReplyDelete
 35. WOW! Thank you. Dani it is a good advice for those people in marriage as well for those who are planning to engage in marriage.

  Keep it up...

  ReplyDelete
 36. dani i like it le bale tidarochim hone gena lemiyagebu tekami miker alew good

  ReplyDelete
 37. Dear danie,it is intertesting article.good view,i advice all people should read this because it teach life.every bady fight unfightable event for to live better life.life is marrige in my opinion. ce all people should read this because it teach life.every bady fight unfightable event for to live better life.life is marrige in my opinion.

  ReplyDelete
 38. "ውስጣችሁ ፍቅር አለ፡፡ ግን ፍቅራችሁን መግለጥ አልቻላችሁም፡፡ ለፍቅር እድል አልሰጣችሁትም፡፡ ትዳር ብዙ በመነጋገር እና በመወያየት ሳይሆን አንዳችሁ ለሌላችሁ በማድረግ ነው የሚገነባው፡፡"

  ReplyDelete
 39. WOW,WOW,WOW,.what a cool story,first..thankyou...danny..ur real;y great!! and it very funny,intersteng,educational..it's AWSOME!!!

  ReplyDelete
 40. Your views are always interesting. keep up the good work.

  ReplyDelete
 41. lol,,,really very interesting,,,especially the conclusion. And I wish if those Awakis(tenkuays) could read this. They would have learned doing such holly thing than what evil wants them to do,,,z mutemtim

  ReplyDelete
 42. yechen ketel sageba efelegatalehu !!!!!!!!!enantem felegu!!!!!!!!

  ReplyDelete
 43. dany yetsafikew neger bewinet betam asitemary new andande gin yemiasasibegn neger men meseleh sewoch yihin guday bekeld bicha yayut endehon new behiwotih sitinor eyekelede yemiyastemirih sew ya bilih new bewinet kante ga friendship bimeserit destaw yene new ebakih.ameseginihalew.Bisrat worku negn ke dire dawa.

  ReplyDelete
 44. Hi dani, it is becoming my hobby to open your blog just after the BBC. i have read most of your writings which i use them as my personal advisory. i have read the book that you point out above by john gray but i haven't understood it in the way you easily put above. your writing are still changing us....i am now university student and learn from you a lot.......danish abo geta yanureh, kezi yebelete ewketun ena tibebun bante lay yeglet. Hule tselote new......

  ReplyDelete
 45. Bal ena mist Megbabat mechal Yesetanin joro yidefnewal!

  ReplyDelete
 46. WOW WHAT A FANTASTIC CONSTRUCTIVE HISTORY, THANKS DANI!

  MB

  ReplyDelete
 47. dani marriage is all about love and u showed me in this story tnx god bless

  ReplyDelete
 48. ውድ ወንድማችን ሆይ፤ እግዚአብሔር አምላክ ይባክህ። እግዚአብሔር ከፈቀደ ገና ብዙ ብዙ ለወገኖችህ የምትጠቅም ይመስለኛል። ጸጋውን፡ ጤናውንና ዕድሜውን ያብዛልህ።
  ጥበበ ኢየሱስ ከቶሮንቶ ቅ/ማርያም አጥቢያ

  ReplyDelete
 49. ለዲ/ን ዳንኤል
  በጣም መካሪ የሆነ ጽሁፍ ነው በርታ!!
  ፍካ.

  ReplyDelete
 50. ERE DANI ....BETAM YEMIGERM TSHUF NEW!!!!!!
  ENDEZIH AYNET BIZU 'TENKUAYOCH' ENFFELGALEN

  ReplyDelete
 51. Dear bro DN Daniel, it is great and really teaching view! it is a mirror via which we can see our self too. May GOD BLESS YOUR WORK EVER DAY GIVE YOU LONG LIFE!

  ReplyDelete