Monday, September 26, 2011

የመጀመርያው የቁንጅና ውድድር በኢትዮጵያ


የዛሬ አንድ መቶ ሃምሳ ዓመት በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን እንዲህ ሆኖ ነበር፡፡
የመስቀል በዓል በዋለ በሁለተኛው ቀን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ምናልባት በኢትዮጰያ የመጀመርያው የቁንጅና ውድድር በጎንደር ከተማ ተደርጎ ነበር፡፡
ከልደታ ምሥራቅ ለአበራ ጊዮርጊስ ሰሜን  ከሆነችው በቀሃ ወንዝ አጠገብ ከምትገኘው አጤ ሰቀላ ከምትገኘው ኮረብታ ላይ የንጉሠ ነገሥቱ ሸራ ድንኳን ተተከለ፡፡ ከጧቱ ከሶስት ሰዓት ጀምሮ በዓሉ ወደሚከበርበት ሜዳ የከተማውና የገጠሩ ሕዝብ ይጎርፍ ጀመር፡፡ 4 ሰዓት ሲሆን ምርጥ መሣርያ የያዙ ወታደሮች እና አጋፋሪዎች ሰለፈኛውን ለማስተናበር ጸጥታውን ለማስከበር በበዓሉ ሜዳ ተሠማሩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ፊታውራሪ ገብርዬ በሠራዊቱ ታጅቦ ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ አጤ ሰቀላ ደረሰና የዙፋኑን አቀማመጥ ተመለከተ፡፡

 እንዲሁም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ በፈረሶች በሚሳብ ሠረገላ ተቀምጠው ሊቀ መኳስ ዮሐንስ ቤል ባሠለጠናቸው ወታሮች እየታጀቡ መጥተው በዙፋናቸው ላይ ደተቀመጡ እምቢልታ እና መለከቱ ተብላላ፡፡ ነጋሪት አጅብር አጅብር ውጋው ውጋው እያለ ይጎሰም ጀመር፡፡ ዘፋኞች ይዘፍናሉ፡፡ አዝማሪዎች ይዘምራሉ፡፡ ወታደሮች ይጨፍራሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ይዞታ ተድላ ደስታ ሆኖ ሲደባለቅ በመካከሉ ለውድድሩ የታጩት ወይዛዝርት ጥልፍ ቀሚሳቸውን እያንሰረተቱ፣ ተቀብተው፣ ተኩለው ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ያልፋሉ፡፡
ቀጥሎም ምርጫው በሚፈጸምበት ጎል እየገቡ ውበታቸው እና ደም ግባታቸው፣ የላሕየ ገጻቸው አወራረድ፣ የፀጉራቸው ሥሬት፣ የቁንዳላቸው እርዝመት፣ ሽንጣቸው ዳሌያቸው እና ተረከዛቸው እየተመረመረ የምርጫው ሥነ ሥርዓት ይጀመራል፡፡
በመካከሉ በሰቀልት ወረዳ ከመቋሚያ ማርያም የመጣችው ትውልዷ ከመቄት አዝማቾች ወገን የሆነ የደጃዝማች ይልማ አሰፋ ልጅ ልጅ፤ ጣይቱ ይልማ አንደኛ ስትሆን፤ እንዲሁም ከጎንደር አዲስ ዓለም የመጣችው የመሐመድ ኩርማን ሚስት የሼህ መሐመድ ጌታ ልጅ ተዋበች በጠጉሯ ማማር፣ በቁንዳላዋ አወራረድ እና መርዘም ሁለተኛነትን አግኝታለች፡፡
ከዚህ በኋላ ዮሐንስ ቤል እና ፊታውራሪ ገብርዬ የምርጫውን ውጤት ለንጉሠ ነገሥቱ  ለመንገር ወደ ዙፋኑ ይቀርባሉ፡፡ ወዲያውም ጣይቱ ይልማ አንደኛ፣ ተዋበች መሐመድ ጌታ ሁለተኛ ከገለጹ በኋላ ተመራጮች ከዙፋኑ ፊት በመቅረብ እጅ እየነሡ ሽልማታቸውን ተቀብለው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖ በሰባት ሰዓት እንደተለመደው ለመሳፍንት፣ ለሊቃውንት፣ ለመኳንንትና ለካህናት የምሳ ግብዣ ተደረገ፡፡
ከውድድሩ በኋላ ጣይቱ ይልማ (ወርመር) ኦርማኤል የተባለውን በጋፋት የመድፍ ሠራተኞች አለቃ በሚስትነት አግብቶ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ወልደዋል፡፡ አሁንም ጋይንት ውስጥ በኦርማኤል ስም የሚጠራ መሬት አለ፡፡
ከ ገሪማ ታረፈ
የቋራው አንበሳ  አባ ታጠቅ ካሣ

18 comments:

 1. This is quite a story , Daniel.

  ReplyDelete
 2. Di Daniel betam enamegenalen mekeneyatum be PDF aderegeh yehene kemare yetafetu tsehufoche enedenanebe selareken eseke zare techegeren nebere ::yehe aseteyayet Ye 11 sewche newu 11 chenem techegeren nebere tanks a lot amelak wagahene yekefele

  ReplyDelete
 3. Inspiring where we were even then. Love it

  ReplyDelete
 4. it's show haw much we are
  reach on story
  thankx dani

  ReplyDelete
 5. it's shows haw much we are
  reach on story
  thanks Dani!

  ReplyDelete
 6. እና ምን ይጠበስ?

  ReplyDelete
 7. We have walked this far even then.

  ReplyDelete
 8. ደሳለኝ ወንድሙSeptember 27, 2011 at 2:20 PM

  በጣም ደስ የሚል ጽኁፍ …በእዉነት…አንዴ እንከልስላችሁ፡፡
  አሸናፊዎች፡ ጣይቱ ይልማ እና ተዋበች መሐመድ … ቆንጆዎች
  ዳኞች፡ ፊታውራሪ ገብርዬ (ሐበሻ) እና ዮሐንስ ቤል (ፈረንጅ) … ጽዱ ከመድሎ
  የበአሉ ድምቆች እና አድማቂዎች፡ አዝማሪዎች፣ ወታደሮች፣ለውድድሩ የታጩት፣
  ወይዛዝርት፣አጋፋሪዎች፣ ሰለፈኛው
  ንጉሠ ነገሥት፡ ቴዎድሮስ … ያንድነት አለቃ
  ሁሉም ለተፈጠረዉ ድንቅ ዉበት የበኩላቸውን እንደየድርሻቸው አዋጥተዋል፡፡ ከነሱ መካከል አንዱ እንኳን ቢጎድል አንዳች ዉበት ይቀነሳል ወይም በዓሉ ራሱ ለመኖር አይችልም፡፡ በዓሉ የአንድነት ዉጤት ነው፡፡ አንድነት ደግሞ ያለፍቅር ከቶ አይገኝም፡፡ ፍቅር ደግሞ መልካም ነዉ፡፡ መልካም ደግሞ ወደድንም ጠላንም እግዚአብሔር ነው፡፡
  ለበአሉ ድምቀት በተቻለን መጠን እንደየድርሻችን መልካም ነገር ለማዋጣት ‘እንሞክር’፡፡ ሠው ደግሞ “መልካም ለመሆን” ይሞክራል እንጅ ከቶ “አይሆንም”፤ ሠው ስለሆነ፡፡ እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሰን፡፡
  እናመሰግናለን ዳኒ፤ የጋሽ ገሪማ ታረፈን አስደሳች ጽኁፍ ስላስነበብከን፡፡

  ReplyDelete
 9. ግና "ጥቁር ነኝ ግን ውብ ነኝ"

  ReplyDelete
 10. wow my dear bro dk daniel. i heard this story from my friend father whose age is almost about 80. so he told us this story 5 years ago and i was impressed with the story because i thought that beauty contest is just new in ethiopia i think the same is true for the whole ethiopians think like that. any ways i really appreciate ya because you tell us the true which has been hidden from us......Gr8 work

  ReplyDelete
 11. dk.daniel ene yehe yekungina wedider bekome sili ante cherashe betaric tatenakerwalehoye!yemalkebelbet hulet mikiniyat aleghe 1.yekunigina wedider sidereg megemeria "Body"endewdader tedrego ashenafiwa beteleyaye mahiberawe gudayoche lay endtisera sidereg yemititekemw gene"mind"yehonale selezeh kemeneshaw lemini yeaemro wededer ayhonim neber 2.yesilase fiture lewededer yikerbal way yehenini sili yanche melik mini behone new litileghe tichelaleh gesitaye kongo kemebal aynet sihoni negerune kelea angle endatayew new

  ReplyDelete
 12. i am really proud by you.because the way of your finding it.that person is you.i am eager to get or read such historical event from u.thanks aloooooooooooooooooot!!

  ReplyDelete
 13. i am sorry to say this
  1. Beauty context is not recognizable as to me appreciating one and telling the other u r not b.e.a.u.t.y full
  2. A women should not be a market.
  bay the way How was there dreaching

  ReplyDelete
 14. SO WHAT?????? DONT U GET ASHAMED WHEN U POST THIS??? WE ARE NOT EXPECTED TO KNOW EVERY THING THAT HAS HAPENED IN THE PAST!
  WRITE THINGS ONLY IF ZEY R VALUABLE!
  WRITE THINGS ONLY IF ZEY R VALUABLE
  WRITE THINGS ONLY IF ZEY R VALUABLE
  WRITE THINGS ONLYIF ZEY R VALUABLE

  ReplyDelete
 15. What is valuable to you mr?....( I mean the anonymous right before me).

  ReplyDelete
 16. this is what we all are talking about !!!!.there are values that we do not wont to keep them ,this attitude of "so what" is the core element that expose the society TO BE ON THE VERGE OF DEATH! MY THE "SO WHAT" FRIEND LEARN FORM PAST AND ADJUST YOUR SELF IN ORDER TO FIT IN THE FUTURE.

  ReplyDelete
 17. Dani i think people who lives far behind us has got original look and tremendous national passion. However only two women were volunteer to take part from among all the beauty at that instant time, in the first historical beauty contest. That is amazing dani.......

  ReplyDelete
 18. እግዚአብሄር ይስጥልኝ

  ReplyDelete