Wednesday, September 21, 2011

አጉል ልማድ

በpdf ለማንበብ
ከአውሮፓ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አውሮፓዊ ገበሬ የጥንት መጽሐፍ አገኘ፡፡ መጽሐፉ አያሌ ምሥጢራዊ ነገሮች የተጻፉበት ባለ ብዙ ገጽ መጽሐፍ ነበር፡፡ ሰውዬው ግን ለማንበብ የቻለው በአንደኛው ገጽ የሚገኘውን አንድ አንቀጽ ብቻ ነበር፡፡
ያም አንቀጽ እንዲህ ይላል፡፡ «በጥቁር ባሕር ዳርቻ አንድ ልዩ ድንጋይ ይገኛል፡፡ ይኼንን ድንጋይ ማንኛውም ነገር ሲነካው የነካውን ነገር ወደ ወርቅነት ይቀይረዋል ይላል፡፡ ይህንን ድንጋይ ከሌሎች ተመሳሳይ ድንጋዮች ለይቶ ለማወቅ የሚቻለው በመንካት ነው፡፡ ድንጋዩ ከተመሳሳይ ድንጋዮች በተለየ ትኩስ እና ሲነኩትም የሚፋጅ ነው» ይላል፡፡
 ሰውዬው ሳይውል ሳያድር ወደ ጥቁር ባሕር ዳርቻ ተጓዘ፡፡ እዚያም ሲደርስ የባሕሩ ዳርቻ የተባለውን ድንጋይ በሚመስሉ ድንጋዮች ተሞልቶ አገኘው፡፡ አንዱን ድንጋይ ያነሣል፡፡ ይነካዋል፡፡ የሚያቃጥል ካልሆነ በድጋሚ እንዳይሞክረው ወደ ባሕሩ ይወረውረዋል፡፡ ሌላውንም ድንጋይ ያነሣል፡፡ ማቃጠል አለማቃጠሉን ይሞክራል፡፡ ቀዝቃዛ መሆኑን ሲያረጋግጥ ወደ ባሕሩ ይወረውረዋል፡፡
ቀናት ወደ ሳምንታት፣ ሳምንታት ወደ ወራት፣ ወራትም ወደ ዓመታት ተቀየሩ፡፡ ሰውዬው ባለ መሰልቸት ድንጋዮቹን እየሞከረ ወደ ባሕር ይወረውር ነበር፡፡ መጀመርያ አካባቢ ማንሣቱ፣ መሞከሩ እና መወርወሩ ብዙ ጊዜ ይፈጅበት ነበር፡፡ እየቆየ ግን እየለመደው ሲመጣ ድንጋዩን ሳያይ በፍጥነት አንሥቶ፣ ሞክሮ ይወረውር ጀመር፡፡ እየሰነበተ ሲሄድም በድካም ላይ ሆኖ እንኳን ቢሆን እየሞከረ መወርወር ቻለ፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላም ያለ ምንም ሃሳብ ያነሣል፣ ይሞክራል፣ ይወረውራል፡፡
አንዳንዴ እንቅልፍ እያሸለበው እንኳን በቀኝ እጁ ያነሣል፣ በግራው ሙቀቱን ይሞክራል፣ መልሶ በቀኙ ወደ ባሕሩ ይወረውረዋል፡፡ የሚያነሣቸው ድንጋዮች ሁሉ እንደ በረዶ የቀዘቀዙ ናቸው፡፡ እንኳን የሚያቃጥልና ትንሽ ሞቅ የሚል ነገር እንኳን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ብቻ ያነሣል፣ ይነካል፣ ቀዝቃዛ ሲሆን ይወረውራል፡፡ ዓመት፣ ሁለት ዓመት፣ ሦስት ዓመት፣ አሥር ዓመት፣ አሥራ አምስት ዓመት ማንሣት፣መንካት፣ ወደ ባሕር መወርወር፡፡
አንድ ቀን ጠዋት «ዛሬ ምንም ውጤት ካላገኘሁ የጥንት ጸሐፊ አታሎኛል ማለት ነው፡፡ ወደ ሀገሬ እመለሳለሁ» ብሎ አሰበ፡፡ በሌሊት ተነሥቶም እንደ ልማዱ ድንጋዮቹን እያነሣ፣እየነካ መወርወር ቀጠለ፡፡
ድንገት አንድ ድንጋይ ሲያነሣ ትኩስ ሆነ፡፡ ነገር ግን እጁ መወርወር ስለለመደበት፣ ሳያስበው ያንን የሚፈልገውን ድንጋይ ወደ ባሕር ወረወረው፡፡ ትዝ ሲለው ለካስ የነካውን ዕቃ ሁሉ ወርቅ የሚያደርገው ድንጋይ በልማድ የወረወረው ትኩሱ ድንጋይ ኖሯል፡፡
እያዘነ፣ እየተናደደ እና ባባከነው ጊዜ እየተቆጨ ወደ ሀገሩ ገባ፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ግቢ ስማር ትዝ የሚለኝ ነገር አለ፡፡ ብዙዎቻችን በዋናው በር በኩል ስንገባ በር ላይ ቆመን ወደ ውስጥ እንሳለም ነበር፡፡ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም እና የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ በሮች ከስድስት ኪሎ በር ጋር ተመሳሳይ ስለነበሩ ያንን ነገር በልማድ እናደርገው ነበር፡፡
ልማድ በጎም ነው ክፉም ነው፡፡ ልማድን አእምሮ ከተቆጣጠረው ልማድ መልካም ነው፡፡ አንድን ነገር እንዳንዘነጋው፣ ባለ ማቋረጥም እንድንከውነው፣ ብሎም ለረዥም ጊዜ ገንዘብ እንድናደርገው ያስችለናል፡፡ ነገሮችን ከምንማርባቸው መንገዶች አንዱ ልማድ ነው፡፡ አንድን ነገር ልማድ የሚያደርገው ደግሞ ነገሩን ደጋግሞ ማድረግ ነው፡፡
ችግሩ የሚከሰተው ልማድ አእምሮን ሲመራው ነው፡፡ ያን ጊዜ ሰው ባለ አእምሮ መሆኑ ይቀርና ደመ ነፍስ ይሆናል፡፡ ነገሮችን በምክንያት፣ በዓላማ፣ በጠቀሜታ፣ በአስፈላጊነት፣ የተነሣ ማድረግ ያቆምና በልማድ ብቻ ያከናውናቸዋል፡፡
በተለይም ደግሞ የሚያከናውነው ነገር ተመሳሳይ እና ለብዙ ጊዜያት የሚደረግ ከሆነ አእምሮ ለልማድ የመገዛት ዕድሉ ይጨምራል፡፡
አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ስሄድ የጥበቃ ሠራተኞቹ እጅ ወደላይ ብለው ይፈትሻሉ፡፡ አያሌ ዘመናት ከመፈተሻቸው የተነሣ የአብዛኞቹ የጥበቃ ሠራተኞች አፈታተሽ ተመሳሳይ ነው፡፡ በተለይ ወንድ ከሆናችሁ፡፡ ከብብታችሁ ጀምረው ወደ ታች በጎን በኩል እስከ ቁርጭምጭሚት መውረድ ነው፡፡ ያንን የሚፈራውን ሽጉጥ ጥንቅላቴ ላይ አድርጌ ኮፍያ ባጠልቅበት የሚፈትሸኝ የለም፡፡ እንዴው ብቻ ሁለት እጅን ዘርግቶ ከላይ ወደ ታች መውረድ፡፡
ውስጥ ግቡ ደግሞ፡፡ ባለጉዳዩ ራሱ ካልተሰለፈ፣ ተሰልፎም ካልተጋፋ ሥራ ያልተሠራለት አይመስለውም፡፡ ሁለት ሰዎች ብቻ ሆነው ለመግባት ሲጋፉ ታያላችሁ፡፡ ልማድ፡፡ ጸሐፊዎቹ ድረሱ ደግሞ፡፡ «ወጣ ብለዋል፣ የሉም፣ ስብሰባ ላይ ናቸው» ማለት ለምዶባቸዋል፡፡ yአፋቸው ስክሪን ሴቨር ነው የሚመስለውኮ፡፡ ገና ማንን እንደምትፈልጉ ሳትጠይቋቸው «ስብሰባ ላይ ናቸው» ይሏችኋል፡፡
እኔ አንድ ቀን ከአሜሪካ ዕቃ ተልኬ አንድ መሥሪያ ቤት ሄድኩ፡፡ የሄድኩት ጸሐፊዋን ለማግኘት ነበር፡፡ ያው መታለፍ ያለበትን ሁሉ አልፌ ቢሮው ደረስኩ፡፡ ለካስ የምፈልጋቸው የአለቅዬው ጸሐፊ ኖረዋል፡፡ ገና ከመግባቴ «ስብሰባ ላይ ናቸው» አሉኝ ጸሐፊዋ፡፡ «እንዴ ብቻቸውን መሰብሰብ ጀመሩ እንዴ» አልኩ ፈገግ ብዬ፡፡ ኮስተር አሉብኝ፡፡ «እኔኮ እርስዎን ፈልጌ ነው የመጣሁት፣ ቀጠሮዬን ረሱት» አልኳቸው፡፡ ቀዝቀዝ አሉና ስሜን ጠሩት፡፡ «ምን የሚመጡት ሁሉ አለቃ ካልገባሁ ስለሚሉ እንደዚያ መስለኸኝኮ ነው» አሉና ሻሂ አስመጡልኝ፡፡
እንዴው ግን በየላቦራቶሪው ደም እና ሌላም ነገር ሰጥተን ውጤታችንን ሲሰጡን እውነት በየራሳችን መርምረውን ነው? ወይስ በልማድ ወፈር ላለ ሰው ደም ብዛት፣ ቀጠን ላለ ሰው የምግብ እጥረት፣ ቀላ ላለ ሰው ስኳር፣ ኮስተር ላለ ሰው ጨጓራ አለበት እያሉ በልማድ ይሆን እንዴ የሚጽፉልን፡፡ አንዳንድ ቦታኮ የሁላችንም ውጤት ተመሳሳይ ይሆናል፡፡
ከሰው ጋር እያወሩ፣ ኧረ አንዳንዴም ስልክ እያወሩ የሚያክሙ አልገጠሟችሁም፡፡ እያወሩኮ መርፌ የሚወጉ አሉ፡፡ እየተጫወቱ ካርዳችሁ ላይ አንዳች ነገር ይጽፋሉ፡፡ ይባስ ብለውም እናንተን ሳይጠይቁ አይተዋችሁ በሽታችሁን የሚጽፉም አሉ፡፡ ለምደውታላ፣ ያስጦቢያን በሽታ፤ ለምደውታል፡፡
በልማድ ተሠርቶም አይደል እንዴ በትልልቆቹ ሆስፒታሎች የእናቶችን ልጅ እስከማቀያየር የተደረሰው?
ስብሰባ ተሰብስባችሁ ታውቃላችሁ መቼም፡፡ ሃሳብ እንሰጣለን ብለው እጃቸውን የሚያወጡ፣ ከዚያም «እኔ እንኳን የምናገረው ነገር የለኝም ግን» ካሉ በኋላ ፍቅር እስከ መቃብርን የሚተርኩ አልገጠሟችሁም፡፡ እንደ እዚያ አውሮፓዊ ገበሬ ስለ ለመደባቸው ነው እንጂ እጃቸውን ያወጡትኮ ብዙ ሊናገሩ ነው፡፡ ከእነዚህ የባሱ ደግሞ አሉላችሁ እንጂ፡፡ ክፉ ልማድ ተጠናውቷቸው «እገሌ እንዳለው» ብለው እገሌ ያላለውን የሚያወሩ፡፡ «ማርከስ እንዳለው፣ ሌኒን እንዳለው» እየተባሉ በአቶ እንዳለው ልጆች አድገውኮ ነው፡፡ ምን ያድርጉ፡፡
አሁን አሁንማ ማጨብጨብ እና እልልታ አጉል ልማድ ሆኖብናል፡፡ የት ይጨበጨባል? ለምን ይጨበጨባል? ብሎ መጠየቅ ቀረ፡፡ ከተነገረ ማጨብጨብ ብቻ ነው፡፡ ለድጋፍም ለተቃውሞም ነው ጭብጨባው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም ልማዱ ከመጽናቱ የተነሣ በስብሰባ ሰዓት ይተኙና ሲጨበጨብ ብቻ ተነሥተው ያስነኩታል፡፡ ምናልባት በራሳቸው ላይ ተወስኖባቸውም እንደሆነ አልሰሙም፡፡
አንድ ጊዜ ብላቴ እያለን አንድ መኮንን የነገረንን አልረሳውም፡፡ «በቀይ ኮከብ ዘመቻ ጊዜ እኔ ከአዳራሹ ፊት መሥመር ነበር የተቀመጥኩት» አለ፡፡ አንዱ ጓደኛችን ታድያ ስብሰባ ሲጀመር ይተኛና ሲጨበጨብ እየተነሣ ያጨበጭባል፡፡ «ጓድ ሊቀመንበር» ፊት ለፊታችን ሆነው ያዩናል፡፡ «ይኼ ሰውዬ አስበላን» አልን ከጓደኞቼ ጋር፡፡ ታድያ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡
እርሱ ሲጨበጨብ ብቻ እየተነሣ ማጨብጨብ ነው ሥራው፡፡ አንድ ጊዜ ቀስ አልኩና ሊቀ መንበሩ በንዴት እያወሩ እያለ በጆሮው በኩል እንደ ማጨብጨብ አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ነቃና የተጨበጨበ መስሎት ብቻውን መዳፉ እስኪቀላ አስነካው፡፡ ሊቀ መንበሩ ደነገጡ ንግግራቸውን አቁመው አፈጠጡበት፡፡ ደነገጠ፡፡ ቆሌው ተገፈፈ፡፡ ያን ጊዜ ያፈጠጠ እስካሁንም ዓይኑ መገጠሙን እንጃ» አለን፡፡
በየቤተ ክርስቲያኑስ እንደው በትልቅ በትንሹ እልል ሲባል አትሰሙም፡፡ እገሌ ተአምር አደረገ «እልልልልልልል»፡፡ እገሌ መከራ ተቀበለ «እልልልልል»፡፡ እንዴ ይኼ እልልታ የሚባለው ነገር ምሥጋና ነው ወይስ የአርፍተ ነገር መዝጊያ፡፡
በቴሌቭዥንም ሆነ በአካል፣ በሀገሪቱም ሆነ ከሀገሪቱ ውጭ የሚደረጉ ሰልፎችን እስኪ ተመልከቱ፡፡ መፈክር አያጣቸውም፡፡ ችግሩ በደርግ ዘመን ግራ ዘመም ነን ተብሎ በይፋ ስለተነገረ ስንፈክር ግራ እጃችንን አውጥተን፣ ክንዳችንን ፈርጠም አድርገን፣ ኢምፔርያሊዝምን እስክናደቀው ድረስ እንከነዳ ነበር፡፡ አሁን ግን በግራ በኩል እንቀጥል ወይም ወደ ቀኝ እንታጠፍ የታወቀ ነገር የለም፡፡ በየሰልፉ ግን የለመደብን መፈክር አሁንም አልቀረም፡፡ ታድያ አንዱ ቀኙን አንዱም ግራውን ያወጣል፡፡ መጀመርያ ነገር በዚህ ዘመን መፈክር አያስፈልግም ነበር፡፡ ካስፈለገም እንዴት እንደምንፈክር አንዳች መግባቢያ ነገር ሊኖር ይገባን ነበር፡፡ ምን ያደርጋል መፈከር ለምዶብን በውጭም በውስጥም እንፈክራለን፡፡
እስኪ በየሚዲያው በአብዛኛው የምንሰማቸውን እና የምናያቸውን ዜናዎች አስተውሉ፡፡ አስጠነቀቀ፣ አስታወቀ፣ አስገነዘበ፣ ተጠቆመ፣ ተመለከተ፣ ተገለጠ፣ አስገለጠ፣ አሳሰበ፣ ከዚህ የሚወጣ ዜና ማግኘት በስለት ነው፡፡ እንግዲህ አንዱ ጀምሮት በዚያው ልማድ የሆነ ይመስለኛል እንጂ በሌላው ዓለም የግድ በባለቤት ተጀምሮ በግሥ የሚዘጋ የዜና መግቢያ አምጡ ሲባል አላየሁም፡፡
ኦሳማ ቢን ላደን የተያዘ ጊዜ አንዱ ዕውቅ ጋዜጣ Obama gets Osama የሚል ዜና ሠርቶ ነበር፡፡ እኛ ሀገር ቢሆን ኖሮ በዚያው በልማዱ «ኦሳማ ቢን ላደን መገደሉን ፕሬዚዳንት ኦባማ አስታወቁ» ይባልለት ነበር፡፡ አወጣው፡፡
ይኼ በየስብሰባው፣ በየቃለ መጠይቁ እና በየንግግሩ ላይ «ያለበት ሁኔታ ነው ያለው» የሚለው አገላለጥ ያስለመደብን ማነው?፡፡ ትርጉሙስ ምንድን ነው? ገበሬው ብዙ እያመረተ ነው» ማለት ሲቻል «ገበሬው ብዙ እያመረተ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው» ብሎ አንድን ግሥ ሦስት ጊዜ መድገም ምን አመጣው? «ያለበት፣ ሁኔታ፣ ያለው» እነዚህ ሦስቱም ከአንድ ግሥ የወጡ ናቸው፡፡ በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው ብለን ካልሆነ በቀር፡፡ ወንድማማቾች ስለሆኑ፡፡
እኔማ አንዳንዱ ሰው ያሰለቸኛል፡፡ ሰላምተኛነቱ መልካም ሆኖ ሳለ
እንዴት ነህ? - ደኅና ነኝ
እሺ? - አለን
ታድያስ? - ይኼው አለን
ስላም ነህ? - ደኅና ነኝ
ምናለ የሁሉም መልስ አንድ ከሆነ፣ አንዱ ሰላምታ ቢበቃ፡፡ ልማድ ነዋ፡፡
«አሞኛል» ማለት የለመደባቸው ሰዎች አታውቁም፡፡ ከመልመዳቸው የተነሣ አእምሯቸው ሲያማቸው እና ሳያማቸው አይለይም፡፡ አንዳንዴም አሞኛል ማለት የታላቅነት ማሳያ ሲሆንም ይታያል፡፡ እንዴት ነው / እገሊት ተሻላቸው? ይባልላቸዋላ፡፡
እንዴ ስርቆትምኮ ልማድ ይሆናል፡፡ ሰውኮ ሲያጣ ብቻ አይደለም የሚሰርቀው ሲለምድበትም ነው፡፡ ቢሯችሁ መጥቶ ስክርቢቷችሁን ይዞ የሚሄድ ወዳጅ የላችሁም፡፡ አሁን እርሱ የስክርቢቶ መግዣ አጥቶ ይመስላችኋል? አጉል ልማድ ነው እንጂ፡፡ ገንዘብ ሳይቸግረው መጋበዝ ("" ጠብቃ ትነበብልኝ) ልማድ የሆነባቸውም አሉ፡፡ እንደው ልክፈል ብለው እንኳን የማይግደረደሩ፡፡ ሲብስ እንዲያውም ካልተጋበዙ የሚቀየሙ፡፡ የከፉት ደግሞ ተጋብዘው እንኳን እነርሱ የከፈሉ የሚመስላቸው፡፡ አያድርሰ ነው፡፡
የሰውን ሕይወት መከታተል አጉል ልማድ የሆነባቸው ወዳጆችስ የሏችሁም፡፡ እናንተ የዘነጋችሁትን ፋይል ከፈለጋችሁ እነርሱ ታገኙታላችሁ፡፡ ለክፋት አይደለም፣ ለጽድቅም አይደለም፡፡ እንዴው ለምዶባቸው የሰው ጫማ ቁጥር ሳይቀር ሥራዬ ብለው የሚያጠኑ አሉ፡፡ አንዳንዶቹ እንደዚያ እያደረጉ መሆኑን እንኳን አያስተውሉትም፡፡ ድንገት ባለቤቱ የማያውቀውን ወይንም የዘነጋውን፣ ወይንም ሌላ ሰው አያስተውለውም ያለውን የሕይወቱን ክፍል ሲተነትኑለት አስደናቂ ፊልም እንዳየ ተመልካች አፉን ይዞ ይቀራል፡፡ ያን ጊዜ «አንተ ግን እንዴት ልታውቅ ቻልክ ሲባሉ ነው እያደረጉት ያለውን ነገር የሚነቁበት፡፡
ነገር ዘጠኝ ጊዜ የሚደጋግሙትስ፡፡ እያወሩ አሁንም አሁንም «ገባህ» ይላሉ፡፡ ባይገባኝ ዝም እላለሁ እንዴ፡፡ «አየህ፣ አየህ» ይሉኛል፡፡ ምኑን እንደማይ ፈጣሪ ይወቀው፡፡ «እሺ፣ እሺ» ይላሉ ሕፃን የሚያወሩ ይመስል፡፡ «አይገርምህም፣ አይገርምህም» የሚሉስ አልገጠሟችሁም? በጉዳዩ ነው እንጂ በቅስቀሳ ነው እንዴ የምንገረመው፡፡ አንዳንዶቹማ እየነካኳችሁ ካላወሩ የምትሰሟቸው አይመስላቸውም፡፡ ለመሆኑ ነገር በወሬ እንጂ እንደ ኤሌክትሪክ በንክኪ መተላለፍ የጀመረው መቼ ነው? የማያውቁትን ነገር እየነገራችኋቸው I know የሚሉ አልገጠሟችሁም? ልማድኮ ነው፡፡
አጉል ልማድ ካልሆነ በቀር በአንበሳ አውቶቡስ እና በታክሲ ስንዞረው የኖርነውን ከተማ፣ የሠርጋችን ቀን መልሰን ስንዞረው የምንውለው ለምንድን ነው? ለዚያ ሁሉ መኪና፣ አጃቢ እና የቪዲዮ ቀራጭ ስንት ወጭ ሲወጣ፣ ለምን? ብሎ የጠየቀ መኖሩ አልተሰማም፡፡ እሺ ግዴለም እንዋብ፡፡ ግን ለምንድን ነው አደባባዩን ሁሉ የምንዞረው? ምንድን ነው ትርጉሙ? ምንድን ነውስ ጥቅሙ?
ዘመኑ ሲረዝም፣ ነገሩ ሲደጋገም፡፡ ይኼም ያም ሲያደርገው፤ እኛም ያለ ሃሳብ ተቀብለነው እንዲሁ በደመ ነፍስ የምንፈጽመው ስንት ነገር አለ፡፡ ለምን? እንዴት? መቼ? የት? ብሎ የሚጠይቅ ጠፍቶ፡፡ «ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ» ይላል መጽሐፈ መነኮሳት፡፡ ሰይጣን «በስመ አብ» ይሸሻል፡፡ ልማድን ማስቀረት ግን ከባድ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ልማድ ጸንቶ ጠባይ ሲሆን፡፡ እስኪ ግን እንዴው በዘልማድ የምንፈጽማቸውን ነገሮች ቆም ብለን እንመርምር፡፡ ምክንያት፣ ጥቅም፣ ዋጋ፣ ካላቸው ተረድተን እንቀጥላቸው፡፡ እንዴው አንድ ሞኝ የተከለውን ሃምሳ ሊቃውንት መንቀል አቅቷቸው ከሆነ ግን እናርመው፡፡
ዳላስ፣ቴክሳስ

35 comments:

 1. ነገር ዘጠኝ ጊዜ የሚደጋግሙትስ፡፡ እያወሩ አሁንም አሁንም «ገባህ» ይላሉ፡፡ ባይገባኝ ዝም እላለሁ እንዴ፡፡ «አየህ፣ አየህ» ይሉኛል፡፡ ምኑን እንደማይ ፈጣሪ ይወቀው፡፡ «እሺ፣ እሺ» ይላሉ ሕፃን የሚያወሩ ይመስል፡፡ «አይገርምህም፣ አይገርምህም» የሚሉስ አልገጠሟችሁም? በጉዳዩ ነው እንጂ በቅስቀሳ ነው እንዴ የምንገረመው፡፡

  ReplyDelete
 2. Beteamere lemebeltsege kememoker meseraten Lemade enaderege.

  ReplyDelete
 3. the thing that has been done I got on written sentence form.

  ReplyDelete
 4. KHY! Bedime betena yetebikelen!!!

  ReplyDelete
 5. ኦሳማ ቢን ላደን መገደሉን ፕሬዚዳንት ኦባማ አስታወቁ is the right sentence than reporting "Obama gets Osama"
  How are you sure that he really killed or get him. Obama can declare/bluff that "I have killed or /gotten" his prey.

  But a blogger or reporter is entitled only to brodcast or propagate what the predator says as he/she hasn't seen what happened.

  Limad honobin beneka ejachin dehinawim neger enachemalikewalen. ;-) I like it anyways.

  ReplyDelete
 6. Dear dani,
  That's really a thoughtful lesson it makes me to look my habits, in which they just are useless.
  MAY GOD BLESS YOU & ur Family, and may you live many many years,,,,,,,,,,
  yoseph, atl, GA

  ReplyDelete
 7. ነፍሴ ሶስት ነገሮችን ትጠላለች አራተኛውን ግን አጥብቃ ትጸየፋለች፤ ሶስቱ ነገሮች ለጊዜው ይቆዩኝና አራተኛው ግን በዚህ ብሎግ ላይ የምትለቃቸውን ጦማሮች ሳያነቡት "ዳኒ የዛሬው በጣም አሪፍ" የሚሉ ቃሉን ሳይሰሙ "ቃለ ህይወት ያሰማህ" የሚሉ ኢጭ እንዴት ያናድዱኛ አልፎ አልፎም ያስመንኑኛል (ከዚህ blog ማለቴ ነው)፤የልማድ ሁሉ መጥፎ መልእክቱን ሳያነቡ አስተያየት መስጠት እወደዋለው ማለት። አንድ ጎበዝ አንባቢ ጦማሩን ለማንበብ አምስት ደቂቃ ሊፈጅበት ይችላል፤ ጦማሩ post በተደረገ በሰከንዶች ልዩነት ውስጥ በርካቶች አስተያየት ሲሰጡ "like" የምትለውን ክሊክ ሲያደርጉ፤ አንዳንዴ ሰነፍ አንባቢ ብሆን ነው ብዬ እራሴን እወቅሳለሁ ሌሎች በሰከንድ ውስጥ አንብበው አስተያየት ሲሰጡ ስመለከት፤ ነገር ግን ይህ ክፉ ልማድ የተናወጣችሁ "shame on you" እኔ እያመመኝ ስለሆነ እባካችሁ ለኔ ስትሉ ይህ ክፉ የክፉ ክፉ ክፉ ልማዳችሁን አስወግዱ ዲያቆን ዳንኤል አድናቂዎችህን አንተም ምከራቸው። "ካጠጣህ አትንዳ ካላነበብክ ደግሞ አስተያየት አትስጥ" ለአባባሌ ኮፒ ራይት ይከበርልኝ እወዳችኃለሁ ምርጥ ኢትዮጰያዎች ውብሸት ተክሌ

  ReplyDelete
 8. thank u dani.i have a problem when i meet people the first time saying like dehena nehe?,selam newew?,....... to many greeting.i did it last week when i speak with you.any how it is a good thing to know it.i would not do it any more.just one of them is enough.God may help you and your family.

  ReplyDelete
 9. ሃሃሃ በጣም ይገርማል የሆነ አንድ ጛደኛ አለኝ በገረወይና እንደሚገፋ አጞት ሁሌም ሲያወራኝ እየወዘወዘ ፤ እየነካካ አንዳንዴ እየተራመድን የምናወራ ከሆነ ልብሴን ይዞ እያስቆመ ነዉ የሚያወራኝ ባጭሩ ዳኒ አመሰግናለሁ ይህንን ጽሁፍም እንዲያነብ እመክረዋለሁ

  ReplyDelete
 10. Whoooo.Danny ...nice Precpective ,Nice It Telling about my Self..LEmade..Keseytan Yekefal Sebal Semchalehu...Meterme Alebegie...Egzybher Yerdagen!!!

  ReplyDelete
 11. መጀመርያ ነገር በዚህ ዘመን መፈክር አያስፈልግም ነበር፡፡ ካስፈለገም እንዴት እንደምንፈክር አንዳች መግባቢያ ነገር ሊኖር ይገባን ነበር፡፡ ምን ያደርጋል መፈከር ለምዶብን በውጭም በውስጥም እንፈክራለን፡፡

  ReplyDelete
 12. ሰላም ዳኒ ብእርህን ይባርከው ህሊና ላለው ሰው ክፉ ልማድን ማሸነፍ ቀላል ነው. ከዚህ አስከፊ ዛር መላቀቅ ካልቻልን ግን ከራሳችን አልፎ ለማህበለሰቡ እንተርፋለን.የሚገርመው እኒህን መጥፎ ባህርያት እንደጌጥ ፈጥረናቸው ውይም ተውሰናቸው ነው ያኔ በአፍላነት እድሜችን, በስልጣን ዘመናችን, ጊዚ ባነስን ጊዚ ብቻ አለምን የያዝን በመሰለን ጊዚ ግን አይጠቅሙም. በሽታ ናቸው. መፍጠር ና መውርስ ደግ ደጉን ና ፍቅር ያለበትን ሳይሻል አይቀርም ባይ ነኝ./break a bad habit/

  ReplyDelete
 13. አንተ ሠውየ ግን በነክበበው እንጀራ እየመጣህ ነው:: ብሣቅ ገደልከኝ እኮ (ቁም ነገሩንም እየጨበትኩ ነው ግን!):: ግን አንዳንዴ ነገሮች አላስፈላጊ የሆነ ሂደት ደግመህ ደጋግመህ እንድትከተል ሲያደርጉህ በልማድ ትኖራለህ:: ለምሳሌ ሶፍትዊር ስትጭን አላስፈላጊ ብዙ ጥያቄዎች በትንሹም በትልቁም ይጠይቁሃል.....ማን ይሞታል Next Next እያሉ መቀጣል ነው::

  ReplyDelete
 14. Dn.Daniel the almighty God bless you. All ur articles are' astemari nachew'. I was thinking about this things yesterday, fortunately u wrote on bad habit/metfo limid/. Dani, i used to do a lot of things with out knowing what they mean.The same my Family. For example, i had had 'jeraf' for 'Buhe/debire tabor' starting from i was kid,i didn't know why i did that until i went to US and i begin to ask about my self. I used to 'metemek' during 'phagime' but i didn't know before i get here. A lot which looks like this one. Anyways, even most families do it as habit not with skill/bemawek/.Dani, after i came to US i have realized that Ethiopia is a country with where every family doing as habit has a meaning. Whether we like or not i thought Ethiopian is a country where God has promised some good thing, that is why every society is practicing Christianity knowingly or unknowingly/It was good if it was knowingly/. The other is, i am some times asking my self we are keeping some habits which shows Christianity with out trying to keep them, thanks to God it is due to his 'Chernet new biye etewewalehu'.At last, I believe a lot has to be done in every society to make them to know about what they are doing and living has precious meaning/E.g our date, months,names, our holidays..../. ...if we were able to feed our self/rehab betefa/, i don't want Ethiopia to be come like other developed countries,cuz we loose our Diamond Christianity habits. I have seen it within my edge. Anyways, we got the Arc of the covenant, Gimade meskelu and others..so what do we need more than this.....they are more than any thing. Why God give this thing to Ethiopians?... Is it due to our hard work/prayer? not i thought it is due to his 'chernet', even if our fathers were hard workers and good mannered who are obeyed to God. Anyways, let the almighty God keep all those things in our home land, and we don't need more but eradicate hunger... God, u have given all good things/the diamonds/ for us what you haven't given for others, we don't need to worry for the aluminum. 'yemiyabilechelich hulu werk ayidelem tebilo yele'. God bless World, love you all!

  ReplyDelete
 15. Nigusie from dz
  Qalehoyot yasemalin Dn.Dani!tiru gelitsehal bizuwochun sira yeminiseraw belimad new yihe degimo behulu neger yelewux sew mehon aqitonal lehulum igziabher yiran

  ReplyDelete
 16. ዳኒ አንዱ አንቀጽ ላይ እራሴን አግኝቼው በጣም አፈርኩ፡፡ ወይኔ ለካ እንዲ ያስጠላል፤ ጌታዬ እንድተወው እርዳኝ
  ማሂ

  ReplyDelete
 17. Reason Vs Habit:Part-1

  ************************************************ኦሳማ ቢን ላደን የተያዘ ጊዜ አንዱ ዕውቅ ጋዜጣ Obama gets Osama የሚል ዜና ሠርቶ ነበር፡፡ እኛ ሀገር ቢሆን ኖሮ በዚያው በልማዱ «ኦሳማ ቢን ላደን መገደሉን ፕሬዚዳንት ኦባማ አስታወቁ» ይባልለት ነበር፡፡ አወጣው፡፡
  ************************************************እንደምን ሰነበትክ ወንድም ዳንኤል፡፡
  ወንድም ዳንኤል በመጀመሪያ “ኦሳማ ቢን ላደን የተያዘ ጊዜ” ብለህ የፃፍከው በተለመደው በMainstream media ለብዙሀኑ የተወራውን መሰረት አድርገን ቢሆን እንኳን እኔ እስከማውቀውና እስከሰማሁት ድረስ ተገደለ እንጂ ተያዘ የሚለውን ፈፅሞ አልሰማሁኝም፡፡ቢን ላደን ቢያዝና አደረገ የተባለውን ነገር ሁሉ ለምን እንዳደረገ በገዛ አንደበቱ እየሰማን ለአለም ህዝብ ቢያስረዳማ ኖሮ እንዴት ትልቅ ተአማኒነትና ጀግንነት ይሆን ነበር፡፡ይኸው የሱ ዳፋ ለኛም ጭምር ተርፎን እኛንም ኢትዮጵያውያንን ከዚህ በፊት በታሪካችን የማናውቀውን አጉል አሸባሪነት አስተምሮን አረፈውና ዜጎቻችን ይኸው አሸባሪ እየተባሉ እስር ቤት እንዲገቡብን አደረገብን፡፡ምናልባት ቢን ላደንም እንደ አፄ ቴዎድሮስ እጅ አልሰጥም ብሎ ይሆን እንዴ እራሱን በራሱ የገደለው?ወንድም ዳንኤል ይህንን በደንብ ያልገባንንና ብዙ የተወሳሰብና የረቀቀ ነገር እንኳን አጉል ባትነካካው ጥሩ ይመስለኛል፡፡
  ሌላው ወደ ዋነው የፅሁፍህ መልእክት ስመጣ፡፡ልማድ ከሰው ልጅ Evolutionary process ጋርና ከመኖር ህልውና ጋር survival issue ጋር እጅግ በጣሙን የተሳሰረ ነገር ነው፡፡የሰው ልጅ በአእምሮው አእየተመራ ምክንያታዊነትንና(Logic and Rational thinking) እንዲሁም በልቦናው እየተመራ ስሜትን(Emotion and subconscious) አስተባብሮና አዋህዶ በሁለቱም ነገሮች እየተመራ የሚኖር እጅግ ውስብስብ የሆነ የፈጣሪ ስራ ነው፡፡አንዳንድ የስነ-ልቦና ጠበብቶች እንደሚሉት ከሆነ ለሰው ልጅ በመጀመሪያው ደረጃው የአኗኗር ሂደቱ ላይ ከመኖር ህልውናው(Survival issue) ጋር በአብዛኛው የተያያዘው በአእምሮው በምክንያታዊነት (Logic and Rational thinking) ላይ በመመስረት ሳይሆን በአብዛኛው ብልቦናው በስሜት(Emotion and subconscious) ላይ እንደሆነ ነው፡፡
  ወደዚህ ምድር ስንመጣ ሌላውን አሁን ጊዜና ዘመን ያመጣውን ስልጣኔ እንበለው ሌላም ሌላም ብዙ ነገሮችንና ጣጣዎችን ወደጎን ትተን ዋናው ትልቁ ቁምነገር የመኖር ህልውናችንና ደህንነታችንን ማስጠበቅ ነው፡፡ይህንን ደግሞ የምናደርገው ባብዛኛው በስሜት(Emotion and subconscious) ላይ ተመስርተን እንጂ በምክንያታዊነት (Logic and Rational thinking) ላይ በመመስረት አልነበረም፡፡የአንድን ህፃን ልጅ የእድገት ሂደት ስናይም የምንማረው ይህንን ነው፡፡ህፃኑ በመጀመሪያ የእድገት አመቶቹ(እስከ 7 ወይንም እስከ 10 ሊሆን ይችላል) በአብዛኛው የሚመራው በስሜት(Emotion and subconscious) ላይ በመመስረት ነው፡፡ይህንን ነገር አስፍተን ወደ ህብረተሰብ ወደ ህዝብና ሀገር ስንተረጉመው ደግሞ አንድ ህብረተሰብ ወይንም ህዝብ ወይንም ሀገር የራሱ የሆነ የተለየ ታሪካዊ የሆኑ ስነ-ልቦናዊ ማህበራዊ ሃይማኖታዊ ኢኮኖሚያዊ ፓለቲካዊ የእድገት ሂደቶች እንዳሉት እንረዳለን ማለት ነው፡፡ሰው ሆነን እንደመፈጠራችን መጠን በልቦናችን እየተመራን ልማድን ወይንም ስሜትን(Emotion and subconscious) ከአእምሮ ጋር ባለ በምክንያታዊነት (Logic and Rational thinking) ጋር አስተባብረንና አጣጥመን መኖር ግድ ይለናል ማለት ነው፡፡
  እንዲያውም ሴት ባብዛኛው በልቦናዋ ወንድ ደግሞ ባብዛኘው በእእምሮው ነው የሚመራው ይባላል፡፡
  እንግዲህ ፈጣሪ ሰዎችን ወንድና ሴት አድርጎና በባህሪ ጭምር እንድንለያይ አድርጎ በዚህ አይነት ተቃራኒ ፆታ ሲፈጥረን የራሱ ምክንያትና ምስጢር አለው ማለት ነው፡፡ስለዚህ አንድ ግለሰብ ወይንም ማህበረሰብ ወይንም ህዝብ ወይንም ሀገር ጤናማና የሰለጠነ ነው የምንለው ሁለቱን በአንድ ላይ አስተባብሮና አጣጥሞ መኖርና ህይወቱን በስርዓት መምራት ሲችል ነው፡፡ወደ አንደኛው ጫፍ ብቻ ያመዘነ አካሄድና ህይወት ጤናማ አይደለም፡፡ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ወይንም ማህበረሰብ ወይንም ህዝብ ወይንም ሀገር በምክንያታዊነት (Logic and Rational thinking) በመመራት አእምሮውን አስጨንቆና አስጠብቦ በፈጠረው በሳይንስና በቴክኖሎጂ እጅግ የመጠቀ ሊሆን ይችላል፡፡ነገር ግን በስሜቱ(Emotion) ያልተረጋጋ Emotionally unstable የሆነ ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡በሰለጠነው አለም የምናየው አንዳንድ ግራ የሚያጋባ አሳዛኝ ክስተትም አንዱ ከዚህ በመነጨ ነው፡፡
  በተቃራኒው ደግሞ አንድ ግለሰብ ወይንም ማህበረሰብ ወይንም ህዝብ ወይንም ሀገር ባብዛኛው በጥንቱ ባለው አይነት እንደተፈጠረና እንደወረደ በልማድ የሚኖርና በስሜቱ(Emotion) የተረጋጋ Emotionally Stable ይሆንና ነገር ግን ከዘልማድ ኑሮ ባለፈ በፈጠራ የደከመና አእምሮውን አስጨንቆና አስጠብቦ የማይኖርና በሳይንስና በቴክኖሎጂ እጅግ የደከመና ወደ ኋላ የቀረ ሊሆን ይችላል፡፡
  አንዳንድ ጊዜ የሰለጠነው አለም ዜጎች በቱሪስትነት እዚህ እኛ ሀገር ወደ ገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል እንደ ሀመር ብሄረሰብንና ሌሎችንም ለመጎብኘት የሚመጡበት አንዱ ዋና ምክንያት ድንግል የሆነ ተፈጥሮና ድንግል የሆነ እንደወረደ በዘልማድ ከሚኖር ማህበረሰብ ጋር የተወሰነ የስሜት ትውውቅና ትስስር ለመፍጠርና እራሳቸውንም ከውጥረት ዘና ለማድረግ እንደሆነ ልንረዳ ይገባናል፡፡ዛሬ የሰለጠነው አለም “Back to Nature” እያለ ያለውም ለዚህ ነው፡፡ነገር ግን ይህንን ስል ደግሞ አጉል በከንቱ እንዳንኩራራና እንዳንመፃደቅ ይገባል፡፡ምክንያቱም እኛና እንደኛ ያለው ታዳጊውና ኋላ ቀሩ አለም ዝም ብሎ በልማድ የሚኖር በመሆኑና አእምሮውን አስጨንቆ አስጠብቦና አሰርቶ በምክንያታዊነት አስተሳሰብ እየተመራ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ባለማደጉ ዛሬም እየተራብን ከሰለጠነው አለም የምግብ እርዳታ እየተመፀወትን እንደምንኖር እንዳንዘነጋ ግድ ይላልና፡፡
  continues to >>>>>>>>>

  ReplyDelete
 18. Reason Vs Habit:Part-2
  በቅዱስ መፅሀፍም እንደምታውቀው የሰው ልጅ በመጀመሪያ በህገ-ልቦና ይመራ እንደነበረ ከዚያ በብሉይ ኪዳን ዘመን አስርቱ ህግጋት እንደተሰጡትና በመቀጠል ደግሞ በአዲስ ኪዳን ዘመን በህግ ብቻ ሳይሆን በእምነት ጭምር መመራትና መኖር እንዳለበት እየተሻሻለ መጣ ማለት ነው፡፡እንግዲህ የሰው ልጅ የአስተሳብና የስልጣኔ እድገት ዝም ብሎ በተአምር በድንገት የሚፈጠርና የሚመጣ ነገር እንዳልሆና የራሱ ብዙ ውስብሰብ አዝጋሚ ሂደቶች እንዳሉት እንረዳለን ማለት ነው፡፡
  አንድ ወቅት ላይ ህሊናና መንገድ ብለህ የፃፍከውን በደንብ ታስታውስ ከሆነ ተመቸን ብለን ዝም ብለን በልማድ በምናደረግው ነገርና በህሊናችን መካከል ምን ያህል ፍጭትና ትግል እንዳለ ጭምር የሚያስረዳ ነው፡፡ልማድንና ህሊናን አስተባብረን አመጣጥነንና አዋህደን መኖር ስንችል ነው ጤናማና ስልጣኔ ያለበት ህይወት ኖርን ማለት የምንችለው፡፡ወደ አንዱ ጥግ ብቻ ያለው አካሄድ ጤናማ አይደለም፡፡እንደማስበው ከሆነ አሁን እኛ እንደ ዜጋ እንደ ህብረተሰብ እንደ ሀገር እነዚህን ሁለት ነገሮች በጥሞና የተረዳን አይመስለኝም፡፡ፊደል የቆጠረና የተማረ የተመራመረ ነው ተብሎ የሚታሰበው የህብረተሰብ ክፍል ነገሮችን በአብዛኛው ወደ አንድ ጥግ ብቻ ማለትም ወደ ምክንያታዊነት (Logic and Rational thinking) ብቻ በመጎተት ህይወትን በዚህ መልክ ለማየት ለመምራትና ለመኖር ይፈልጋል፡፡ፊደል ያልቆጠረና ያልተማረ ነው ተብሎ የሚታሰበው የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በተቀራኒው ነገሮችን ወደ አንድ ጥግ ብቻ ማለትም ወደ ልማድና በስሜት(Emotion and subconscious) በመጎተት ህይወትን ባብዛኛው በዚህ መልክ ለማየት ለመምራትና ለመኖር ይፈልጋል፡፡በእርግጥ ይህንን(የተማረ ያልተማረ በማለት)በዋናነት ለመለየት ሞከርኩኝ እንጂ ያን ያህል በጉዳዩ ላይ ብዙም ጥቁርና ነጭ የሆነ ልዩነት ላይኖረው ይችላል፡፡ነገር ግን እንደ ዜጋ እንደ ህብረተሰብ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር አሁን ያለንበት አጠቃላይ ግራ መጋባትና ምስቅልቅልም አንዱ ከዚህ ልማድንና ህሊናን አስተባብሮና አጣጥሞ በሰርዓት ለመኖር ካለመቻል የመነጨ ነው፡፡
  ሌላው ሲስተም(System)የሚባል ነገር አለ፡፡ሰዎች አእምሯቸውን በመጠቀም አስበውበት ተጠበውበትና ተጨንቀውበት ሳይንስና ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የሚፈጥሩትና የሚመሰርቱት አንድ ወጥ የሆነ የታመነበትና የሚያግባባ ዘለቄታነት ያለው ሲስተም ሊኖር ይገባል፡፡አንድ ዜጋ እንደ ዜጋ አንድ ህብረተሰብ እንደ ህብረተሰብ አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ አንድ ሀገር እንደ ሀገር ይህ ሲስተም የሚባል ነገር ሊኖሯቸው ይገባል፡፡ይህ ሲስተም አንድ ጊዜ ከተፈጠረና ከተመሰረተ ደግሞ ከዚህ በኋላ ይህንን ሲስተም መሰረት በማድረግ በልማድ ነገሮችን ማስኬድ ይቻላል ማለት ነው፡፡በእንደዚህ አይነት ሲስተም ጋር ተባብሮና ተጣጥሞ በልማድ የሚደረግ አካሄድና እንቅስቃሴ ደግሞ የተሻለ ውጤት የሚያመጣ Efficient ነው፡፡የዚህች ሀገርና ህዝቦቿ አንዱ ትልቁ ችግር ደግሞ አንዱ ስልጣን ላይ ወጥቶ ሌላው ሲመጣ ያለፈውን ሲስተም አፈራርሶ እንደገና እንደ አዲስ ጎጆ ወጪ ለራሱ የስልጣን ዘመን የሚመቸውን የራሱን አዲስ ሲስተም ይዞ ይመጣል፡፡ስለዚህም ለትውልድና ለሀገር በዘላቂነት የሚመሰረት አስተማማኝ መሰረት ያለው ሲስተም ሊፈጠር ሊመሰረትና ሊዘረጋ አልተቻለም፡፡ስለዚህም
  አንዱ ሄዶ ሌላው በመጣ ቁጥር የተራጋጋ ህይወትን ከመቀጠል ይልቅ ሁል ጊዜ ረብሻና ውጥንቅጥ የበዛበት ህይወት ነው እየኖርን ያለነው፡፡ዳንኤል እንዳልከውም ለስሜትና ለአእምሮ ጤናማና ገንቢ የሆነ ልማድ አለ በተቃራኒው ደግሞ ለስሜት እየተመቸ ነገር ግን እንደ አደንዛዥ እፅ አእምሮን የሚያደነዝዝና የሚያዝግ ጤናማ ያልሆነ ልማድ አለ ማለት ነው፡፡ይህ ሁሉንም ዜጎችና ህዝቦች የሚያግባባ ዘላቂና ወጥ የሆነ ሲስተም በሌለበት ሁኔታ ውስጥ በልማድ ሀገር መምራት፣በልማድ መቃወም፣በልማድ መደገፍ፣በልማድ መቃወም፣በልማድ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም፣በልማድ ልማት ማካሄድ፣በልማድ >>>>>>>>>>በልማድ አጠቃላይ ህይወትን መምራት እጅግ ግራ የሚያጋባና አደገኛ ነው፡፡ቅርብ ጊዜ “በምን እንግባባ” ያልከውም ፅሁፍህ አንዱ ከዚህ ከልማድ ጋር በጣሙን የተያያዘ ነገር ነው፡፡በማይሆንና ከንቱ በሆነ ነገር ላይ የተመሰረተ ልማድ ሁሉ መጥፎ ነው፡፡በተቃራኒው ደግሞ በሚበጅ መልካም ነገር ላይ የተመሰረተ ልማድ ሁሉ ደግሞ ገንቢ ነው፡፡ሁሉም የየራሱን ስሜት ብቻ ተከትሎ የራሱ ብቻ ፈጠራ የሆነ ከንቱ ልማድ የሚከተል ከሆነ እነዴት አድርገን በጋራ ልንግባባ እንችላለን፡፡እንደ ህብረተሰብ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር የራሳችን የምንለው የጋራ ሲስተምና በዚህም ላይ የተመሰረተ የጋራ የሆነ ወጥነትና ቋሚነት ያለው የጋራ ልማድ አልመሰረትንም፡፡ፊደል ቆጥረናል ተምረናል ተመራምረናል ብለን የምናስብ ሰዎች እንኳን አንድ አስር አስራሁለት ሆነን ትንሽ ሰብሰብ ብለን ተመሳሳይ ቋንቋ እያወራንና እየተናገርን በአንድ የተወሰነ አጀንዳ ላይ በስርዓት ለመመካከርና ለመወያየት እጅጉን እየከበደን እየመጣ ሆኗል፡፡ለምን ቢባል እያንዳንዳችን ባብዛኛው የየራሳችንን ጭፍንና ራስ ወዳድ የሆነ ልማድ ብቻ ይዘን ስለምንመጣና በአንድ ወጥና ዘለቄታ ባለው በሚያግባባ የተፈጠረና የተመሰረተ የጋራ ሲስተም ጋር የተጣጣመ የጋራ ልማድ ስለሌለን ማለት ነው፡፡
  ስለዚህም ዛሬ እኛ ኢትዮጵውያን እንደ ዜጋ እንደ ህብረተሰብ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር ጥሩና መጥፎ ልማዳችንን ለመለየት እንድንችል እራሳችንን ቆም ብለን በጥሞና መጠየቅ መመርመርና ማግኘት መቻል ያለብን ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡

  ReplyDelete
 19. «ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ» ይላል መጽሐፈ መነኮሳት፡፡ ሰይጣን በ«በስመ አብ» ይሸሻል፡፡ ልማድን ማስቀረት ግን ከባድ ነው፡፡

  ReplyDelete
 20. Its so great sewe yelebun sinegrut yekorekorut yakel yesekal mechaym anbebachehu yalesakachehu tadelachehu antegen dn dani txsnbebachehu yalesakachehu tadelachehu antegen dn dani txs

  ReplyDelete
 21. ለምሳሌ ሶፍትዊር ስትጭን አላስፈላጊ ብዙ ጥያቄዎች በትንሹም በትልቁም ይጠይቁሃል.....ማን ይሞታል Next Next እያሉ መቀጣል ነው::

  ReplyDelete
 22. «ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ» ይላል መጽሐፈ መነኮሳት፡፡ ሰይጣን በ«በስመ አብ» ይሸሻል፡፡ ልማድን ማስቀረት ግን ከባድ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ልማድ ጸንቶ ጠባይ ሲሆን፡፡ እስኪ ግን እንዴው በዘልማድ የምንፈጽማቸውን ነገሮች ቆም ብለን እንመርምር፡፡ ምክንያት፣ ጥቅም፣ ዋጋ፣ ካላቸው ተረድተን እንቀጥላቸው፡፡ እንዴው አንድ ሞኝ የተከለውን ሃምሳ ሊቃውንት መንቀል አቅቷቸው ከሆነ ግን እናርመው፡፡

  ድንቅ አባባል ተመችቶኛል፡፡

  ReplyDelete
 23. አንዴት ደስ የሚል ጽሁፍ ነው ዳኒ፡፡ አንተ የምትጽፋቸውን ነገሮች ማንበብ ምን ያህል እንደሚያስደስተኝ ፡፡አመሰግንካለሁ ተባረክ !!

  ReplyDelete
 24. FAIR OF UNKNOWN
  የሚገርመው ግን መጥፎ ልምዳችን አዲስ አሰራረ አዲስ ስልጣኔ አዲስ ጥሩ ነገር አዲስ.......... ለመልመድ እንቅፋት መሆኑ ነው አዲስ ጥሩ ነገር ከመጣ ዝም ብለን እንፈረዋለን ከለመድነው ውጭ የሆነ ነገር መስራት አንፈልግማ

  ReplyDelete
 25. yazarewa lane nate.....

  ReplyDelete
 26. Hi Dani God bless u.hule gize yanten blog eketatelalew betam astemare nachew egziabher yibarekeh.ande yemigermegn negere gin ale zim bilew yemisadebu(comment) enezih sewoch tenegna aydelum weye kinategna nachew.besew sitota(gift) endet yikenal?eketatelalew betam astemare nachew egziabher yibarekeh.ande yemigermegn negere gin ale zim bilew yemisadebu(comment) enezih sewoch tenegna aydelum weye kinategna nachew.besew sitota(gift) endet yikenal?

  ReplyDelete
 27. Esti endezu lek lekachin yenegeren. Nice view helps to watch ourselves. Thanks Bro
  Mzz

  ReplyDelete
 28. I like the whole article especially:ይኼ በየስብሰባው፣ በየቃለ መጠይቁ እና በየንግግሩ ላይ «ያለበት ሁኔታ ነው ያለው» የሚለው አገላለጥ ያስለመደብን ማነው?፡፡ ትርጉሙስ ምንድን ነው? ገበሬው ብዙ እያመረተ ነው» ማለት ሲቻል «ገበሬው ብዙ እያመረተ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው» ብሎ አንድን ግሥ ሦስት ጊዜ መድገም ምን አመጣው? «ያለበት፣ ሁኔታ፣ ያለው» እነዚህ ሦስቱም ከአንድ ግሥ የወጡ ናቸው፡፡ በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው ብለን ካልሆነ በቀር፡፡ ወንድማማቾች ስለሆኑ፡፡ betam temechetaganlech (to use the modern lexicon).
  The one other point I would like to make is ,when we say " I know..." in English it is to say "I understand " ," I agree with what you are saying..." also " I see...." have similar meaning.I noticed you metioned this on this article and one previous article.The person doesn't necessarily have any idea or knowledge of the subject matter you are just telling him ( as you put it) but can agree and express that he understood what you are explaing by saying " I know".This,however, doesn't mean that we need to abuse it to the level some use it like a comma....
  Mulugeta Mulatu
  Vancouver Island

  ReplyDelete
 29. ዳኒ ፅሁፍህን በጣም ወድጄዋለሁ፡፡ ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

  አንተም ለምዶብህ እንዳይሆን

  የምትነቅፋቸውን ግን አስተውለህ አስተያየት ብትሰጥ መልካም ይመስለኛል፡፡ ጋዜጠኞችን የነቀፍክበት አግባብነት አልታየኝም፡፡ በርግጥ ነገሮች መደጋገም የለባቸውም ግን ምስጢሩን እንጂ ዘይቤውን አትጠንቅቅ፡፡
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 30. የሄሮድያዳ ልጅ የቅዱስ ዮሐንስን አንገት አስቆረጠችው ሲባል እልልታውን የሚያቀልጡትን ምን ትላቸዋለህ ?

  ReplyDelete
 31. You are right dani every one of us should give utmost attention to this kind of advice on bad customs
  kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete
 32. almost i've all the problems u mentioned!
  dont forget dogmatic lessons

  ReplyDelete