Monday, September 19, 2011

የልብን ከሰይጣን

በ pdf ለማንበብ
ቀደምት አበው እና እማት የሰይጣንን ማንነት በሚገባ ከማወቃቸው የተነሣ ሰይጣን መዋጋት እና ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ሰይጣንን ራሱን ያታልሉት ነበር፡፡ ይህም መንፈሳዊ ብቃታቸው እና ዕውቀታቸው የቱን ያህል ይደርስ ደነበረ ከሚመሰክሩት ነገሮች አንዱ ነው፡፡
የትምህርተ ኅቡዓት መተርጉማን «ሰይጣን የተነገረውን እንጂ የታሰበውን አያውቀውም» ይላሉ፡፡ ሰይጣን የሚችለው በሰው ልቡና የታሰበውን መገመት ብቻ ነው፡፡ በሰው ልቡና የተመላለሰውን ማወቅ ስለማይችል ሰዎች የልባቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ይገፋፋቸዋል፡፡ ሔዋንን ስለ ዕጸ በለስ ያንን ሁሉ የጠየቃት ለማወቅ ወይንም ለመረዳት ፈልጎ ሳይሆን ሥላሴ በሔዋን ልቡና የጻፉትን ነገር ማወቅ ስላልቻለ ነው፡፡ ሔዋን ስትናገር ግን ሃሳቡን ዐወቀ፡፡ ዐውቆም ዝም አላለም ጠልፎ የሚጥልበትን ወጥመድ አዘጋጀ፡፡
እናቶቻችን ወደ ቅዱሳት መካናት ለመሳለም ሲሄዱ «ላሊበላ፣ አኩስም፣ ግሼን ልሄድ ነው» አይሉም ነበር፡፡ «እንጨት ልሰብር፣ ውኃ ልቀዳ፣ ዘመድ ልጠይቅ» እያሉ ነበር የሚጓዙት፡፡ ይህም ሰይጣን በልቡናቸው ያለውን ተረድቶ ዕንቅፋት እንዳያመጣባቸው ነው፡፡
ይህንን የሰይጣን ስንፍና ከሚያውቁ አበው መካከል አባ ሉቃ እና አባ ታድራ ያደረጉትን ከመጽሐፈ መነኮሳት አንዱ የሆነው መጽሐፈ ፊልክስዮስ ክፍል ፬ ተስእሎ ፶፮ ገጽ 91 ላይ እንዲህ ይነግረናል፡፡
በአንድ ገዳም ውስጥ አባ ታድራ እና አባ ሉቃ የሚባሉ መነኮሳት ነበሩ፡፡ እንጸናለን ብለው የመጡ ብዙ መነኮሳትን ሰይጣን ከበኣታቸው ሲያስወጣቸው ተመለከቱና እንዲሁ ውስጥ ለውስጥ ተግባቡ፡፡ «በቀጣዩ ክረምት ከበኣታችን ወጥተን በበረሃ ለብቻችን እንጋደላለን፤ በዚያም ሰይጣንን ድል እናደርገዋለን» ተባባሉ፡፡ ሰይጣንም እውነት መስሎት እነርሱን ከበኣታቸው ለማውጣት የሚያደርገውን ፈተና ተወው፡፡ በበረሃም ይጠብቃቸው ጀመር፡፡
ክረምት በደረሰ ጊዜም «አሁንማ በክረምት እንዴት እንሄዳለን፤ በጋ ሲወጣ በረሃ ወርደን ሰይጣንን እንቀጠቅጠዋለን፣ እስከዚያ ዝም ብለን እንቀመጥ» ተባባሉ፡፡ ሰይጣንም እውነት መስሎት ፈተናውን ሁሉ ትቶ በጋ እስኪደርስ ጠበቃቸው፡፡ በጋም በደረሰ ጊዜ «ወደ በረሃ እንሄዳለን ተባብለንኮ ሰነፍን፣ ምን ይሻላል፤በቃ በክረምት እንሄዳለን» ተባባሉ፡፡
እንዲህ እያሉ ሰይጣንን ሃምሳ ስድስት ዓመት ዘበቱበት፡፡ በዚህም የተነሣ የመልክአ ሥላሴ ደራሲ እንዲህ የሚል አርኬ ደረሰላቸው
ሰላም ለአክናፊክሙ እሳታውያን አክናፍ
እለ በማእከል ሀለው ወእለ ሀለው በጽንፍ
አለብወኒ ሥላሴ ቀትለ መስተጋድል መጽሐፍ
ከመ ወትረ ይትዋሥአኒ ትምይንተ ሉቃ ትሩፍ
ወጉሕልተ ታድራ ምስሌየ ይዛዋዕ በአፍ፡፡
በጎ ነገሮችን ከሰው ተማክሮ መሥራት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ቆራጥነትን የሚጠይቁ፣ ፈተናም የሚበዛባቸውን መልካም ነገሮችን ከመሥራት በፊት ማውራት ግን በራስ ፈቃድ መከራ መጋበዝ ነው፡፡ አበው እንዳሉት ሰይጣን የተነገረውን እንጂ የታሰበውን አያውቅም፡፡ ስለዚህም ስለምናስበው ነገር ሁሉ በየአጋጣሚው እንድናወራ ያደርገናል፡፡
ሥራን አንደበት ከሚገልጠው ራሱ ሥራው ራሱን ቢገልጥ እንዴት የተሻለ ነው፡፡ ብዙ እያወሩ ጥቂት ከመሥራት፣ ምንም ሳያወሩ ብዙ መሥራት እንዴት መልካም ነው፡፡ ሞያ በልብ ነው ይላል የሀገሬ ሰው፡፡
በየትዳሩ፣ በየማኅበሩ፣ በየጉባኤው፣ በየአጥቢያው ፈተና ከሚበዛባቸው ምክንያቶች አንዱ ይኼ ሊሆንስ ከቻለ? ሁሉንም ነገር ለሰይጣን ስለምንነግረው፡፡ ባል እና ሚስት ተያይተው ብቻ የሚግባቡባቸውን መንገዶች ገንዘብ ማድረግ አለባቸው፡፡ የምናስበውን ሁሉ አናውራ፡፡ በልቡናችን ተቀምጦ በተግባር ብቻ መገለጥ ያለበትን እንለይ፡፡
ኮሚቴ ሲበዛ፣ ስበሰባ ሲበዛ፣ ውይይት ሲበዛ፣ ሰው ሲበዛ በዙ ጊዜ መንፈሳዊ ሥራ መሠራት ከባድ ይሆናል፡፡ መሰናክሉም ይበዛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከተሰብሳቢዎቹ ጋር አጅሬም አብሮ ሳይሰበሰብ አይቀርም፡፡
ሴት የበዛበት ወጥ እና ወሬ የበዛበት መንፈሳዊ ሥራ ሁለቱም ይበላሻሉ፡፡
እስኪ ከወሬ ተግባር ይቅደም፡፡ የነ አባ ትዳራን እና የነ አባ ሉቃን ነገር ባንረሳው መልካም ነው፡፡

48 comments:

 1. D.DANIEL KALEHIWOT YASEMALEN!!God bless u more and more!!

  DANY MARRYLAND

  ReplyDelete
 2. continue others i wait to read.

  ReplyDelete
 3. ዲ.ዳንኤል ከአርብ እስከ ትላንት እሁድ Sep. 16-18 ድረስ በዳላስ ቴክሳስ ተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያን ባዘጋጀነው ጉባኤ ላይ ከመዘምራን ጋር ተገኝተህ በቃለ እግዚአብሔር ስታገለግለን ስለከረምክ በግሌ ተደስቻለሁኝ አመሰግንሀለሁ እንዲሁም በአገልግሎታችሁ በረኩ ጠቅላላ ምእመናንም ስም በጣም አመሰግናለሁ እናመሰግናለን። ወንድማችን ዳኒ ከዘማሪት ፋንቱ፣ ከዘማሪት ጸዳለ፣ ከዘማሪ ዳዊት፣ ከዘማሪ ያሬድ፣ ከዘማሪ አካሉ፣ ከዘማሪ ጌታቸው ጋር የቤተክርስቲያን አምላክ መድሃኔአለም ክርስቶስ የሁላችሁንም ጸጋችሁን ያብዛላችሁ እግዚአብሔር ይስጥልን። የሁል ጊዜ አድናቂህ፣ የብሎግህ የዘወትር ተከታታይ፣ ለቤተክርስቲያንና ለእውነት ያለህ ቅናት የሚያስቀናኝ ወንድምህ። ከዳላስ ቴክሳስ ተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያን ምእመናን አንዱ ነኘ ሰላም።

  ReplyDelete
 4. KALE HIWOTE YASEMALEN DANE betsam tsru neger newu masetewal lemechel sewu berta bezehu ketsel be tsuhuf becha sayehone kantem betegebarem masayeten enetsebekalen
  SOFONIYAS.

  ReplyDelete
 5. hi dany you have to write about satin more because this people they have to know the ta tick of satin you can see who our church got problem so please write more about him. wonde dc

  ReplyDelete
 6. Dear Dani, what a nice intervention is this?

  በጎ ነገሮችን ከሰው ተማክሮ መሥራት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ቆራጥነትን የሚጠይቁ፣ ፈተናም የሚበዛባቸውን መልካም ነገሮችን ከመሥራት በፊት ማውራት ግን በራስ ፈቃድ መከራ መጋበዝ ነው፡፡ አበው እንዳሉት ሰይጣን የተነገረውን እንጂ የታሰበውን አያውቅም፡፡ ስለዚህም ስለምናስበው ነገር ሁሉ በየአጋጣሚው እንድናወራ ያደርገናል፡፡

  ሥራን አንደበት ከሚገልጠው ራሱ ሥራው ራሱን ቢገልጥ እንዴት የተሻለ ነው፡፡ ብዙ እያወሩ ጥቂት ከመሥራት፣ ምንም ሳያወሩ ብዙ መሥራት እንዴት መልካም ነው፡፡ ሞያ በልብ ነው ይላል የሀገሬ ሰው፡፡

  በየትዳሩ፣ በየማኅበሩ፣ በየጉባኤው፣ በየአጥቢያው ፈተና ከሚበዛባቸው ምክንያቶች አንዱ ይኼ ሊሆንስ ከቻለ? ሁሉንም ነገር ለሰይጣን ስለምንነግረው፡፡ ባል እና ሚስት ተያይተው ብቻ የሚግባቡባቸውን መንገዶች ገንዘብ ማድረግ አለባቸው፡፡ የምናስበውን ሁሉ አናውራ፡፡ በልቡናችን ተቀምጦ በተግባር ብቻ መገለጥ ያለበትን እንለይ፡፡

  Remain blessed

  ReplyDelete
 7. Yezarews Algebagnm, Articlum Altamegnm. Dni degmo andand gize tasatirewuna yalgeban yibezall... Kesafk Tsaf Alebeleziya yesihufihn Abstract atasnebiben

  ReplyDelete
 8. kale hiwot yasemalin!

  ReplyDelete
 9. ሰይጣን ከመንገድ እንዳያስቀርብህ በጎ ነገር ለመፈጸም ባሰብክ ጊዜ ከመከናዎኑ በፊት አስቀድመህ አታውራ ይላሉ አባቶቻችን ጥሩ መልእክት ነው

  ReplyDelete
 10. Kale kiwoten yasemalen D.Dani bewnet tlk kum neger new yastemarkeign tsegawen yabzalh Feetari

  ReplyDelete
 11. ዲ.ን ዳንኤል አሁን ደግሞ ሌላ አንድ የሚጠቅመኝ ነገር ከጽሁፍህ አገኘሁኝ፡፡ ሥራን አንደበት ከሚገልጠው ራሱ ሥራው ራሱን ቢገልጥ እንዴት የተሻለ ነው ያልከው ነገር ብዙዎቻችንን ሳይገልጸን አይቀርም፡፡በፊት በፊት ሲባል የምንሰማው "ተግባር ከቃል በላይ ይናገራል ነበር" ዛሬ ግን በተቃራኒው ሆነና "ቃላት እና ቁጥር ከተግባር በላይ የሚናገሩበት ዘመን ላይ ደረስን"፡፡
  በተለይ አሁን ያስቸገረን ነገር እንድህ አቅደናል(በመንፈሳዊውም በአለማዊውም)፤እንድህ ስራ ፈጥረናል፤ስብከት አካሂደናል፤ትምህርት ቤቶች አሉን፤----- ነገር ግን ውጤቱ ሲታይ የተሰራው ስራ ተቃራኒ፡፡መጀመሪያ ፉከራ፤ቀራርቶ፤ሽለላ፤--- በኋላ ወገቤን ማለት የተለመደ ሆነ፡፡
  እኔ መንግስት በቅርብ የሆዱን በሆዱ አድርጎ መጨረሻ ላይ ተስፋውን እንካችሁ ያለን የአባይን ግድብ ስራ ነው፡፡ከ6 ወር በላይ ጥናት በማጥናት (ከሚዲያ የሰማሁት) መሬቱን አለስልሶ ዘሩን ዝሩ ብሎ አስተዋወቀን፡፡እንድህ ነው ተግባር ከቃል በላይ ሲናገር፡፡በሌላውም ዘርፍ እንድሁ ቢሆን እንደት ባማረ ነበር!!! የተራበ የለብኝም ከማለት በፊት ሰው እንዳይራብ ስራ መፍጠር፤ኪራይ ሰብሳቢ ይጥፋ ለማለት ከራስ መጀመር፤-----

  ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን በየመጽሄቱ፤በየቲሸርቱ፤በየኮፊያው፤በየሪባኑ፤በየስብሰባው፤ሲምፖዚየሙ ፤በየሰልፉ፤በየመድረኩ፤በየአውደምህረቱ፤በየመስክ ጉብኝቱ፤በየሚዲያው ----- እንድህ ልንሰራ ነው፤እንድህ ልናመጣ ነው፤እንድህ ልንባል ነው፤እንድህ ሊያደርጉን ነው --- እያልን አውርተን ያመጣናቸው ለውጦች ስንቶቹ ይሆኑ!!?!!
  ውብሸት ተንታው

  ReplyDelete
 12. nice,God Bless u again and gain

  ReplyDelete
 13. Im planning not to go to church this year

  ReplyDelete
 14. what amazing article!!!LONG LIVE TO DN. DANI, WE MISS U !!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 15. ************************************************
  እናቶቻችን ወደ ቅዱሳት መካናት ለመሳለም ሲሄዱ «ላሊበላ፣ አኩስም፣ ግሼን ልሄድ ነው» አይሉም ነበር፡፡ «እንጨት ልሰብር፣ ውኃ ልቀዳ፣ ዘመድ ልጠይቅ» እያሉ ነበር የሚጓዙት፡፡ ይህም ሰይጣን በልቡናቸው ያለውን ተረድቶ ዕንቅፋት እንዳያመጣባቸው ነው፡፡
  ************************************************
  የዘመናችን ሴቶች በብልጭልጭ ነገር ከመሽቀርቀርና ከአጉል ብልጣብልጥነት በዘለለ ከድሮ እናቶቻቸው ምናለበት ነበር ይህንን አይነት ትህትናና ብልህነት ቢማሩልን፡፡ወንዶቹስ ብንሆን ከአጉል ከንቱ ክርክርና ሃኬተኝነት ተላቀን መቼ ነው ከድሮ አባቶቻችን ብልህነትን ከየዋህነት አስተባብረን መያዝ የምንችለው፡፡ልጅ ዳንኤል እንዴት ጥሩ ነገር ነው ያነሳኸው፡፡ዛሬ እኛ አንዱ ግራ የገባንና የተምታታብን ነገር አጅሬ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ በእለት ተእለት ህይወታችን ውስጥ የሚያጠምድብንን የረቀቀ መሰሪ መጥመድና ፈተና በጥሞና አለመረዳታችንና ይህንን ወጥመድና ፈተና እንዴት አድርገን በብልሃትና በማስተዋል ማለፍና ድል ማድረግ መቻል አንዳለብን አለማወቃችን ነው፡፡በቅዱስ መፅኀፍ በሃዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ ኤፌሶን ሰዎች(6፡12) መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዥዎች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ የተባለው ለዚህም አይደለምን።በመንፈሳዊ እውቀት ያልታገዘ አለማዊ እውቀት ብቻውን የትም እንደማያደርስ ልንረዳ ግድ ይለናል፡፡ብዙዎቻችን ፀባችንና ትግላችን ከምን ጋር ጭምር እንደሆነ በቅጡ የገባን አልመሰለኝም፡፡ልጅ ዳንኤል በጣም ጥሩ ነገር ነው ያነሳኸው፡፡ብዙዎቻችን የዚህ ዓለም አጠቃላይ ሁኔታ እር በእርሱ እንደ ድር የተሳሰረና የተያያዘ እንደሆነ በቅጡ አልገባንም፡፡ከዚህ በመነጨም ነገሮችን ከተለያየ አቅጣጫና ሁኔታ እያስተሳሰርክ ስለ አጠቀላዩ ውስብስብ ህይወትና ስለዚህ አለም ያለውን እይታችንን ከጠባብነት ይልቅ በሰፋ ሁኔታ እንዲሆን በማስተዋል እያደረግህ ያለውን ጥልቅ የሆነ እይታ ያለበት ጥረትህን ከማድነቅ ይልቅ እንደ ዶሮ ብልት እየገነጣጠሉ ለምን በአንድ መስመር ብቻ አትሄድም የሚሉትን ጥራዝ-ነጠቅ ሰዎች አትስማቸው፡፡ዛሬ እኛ እንዲህ በጣሙን ግራ በተጋባንበትና በተጨነቅንበት ፈታኝ ወቅት እጅጉን የሚያስፈልጉን ነገሮችን ከተለያየ አቅጣጫ መጠየቅ ማየት መመርመርና መመዘን የሚችል ሰፊና ጥልቅ እይታ ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡አንድ በተወሰነ ሙያ የሰለጠነ ሰው ስለሚያውቀው ሙያ ብቻ ተርትሮና አብራርቶ ቢያወራልን ደመዎዙን የሚያገኝበት እንጀራው ነውና ብዙም ያን ያህል ሊያስደንቀን አይገባም፡፡ነገር ግን በአንድ ሰው በአንድ ግለሰብ ውስጥ የተለያዩ እውቀቶች(General Knowledge) ተጠረቃቅመው ተዋህደውና ተስማምተው ሲገኙና ሲገለፁ ሳይ እጅግ ድንቅ ነገር ነው፡፡የህይወታችንና የዚህም ዓለም ውስብስብ ችግር በተወሰነ መልክ መፍትሄ ማግኘት የሚችለው ደግሞ ነገሮችን ከተለያየ አቅጣጫ ለማየትና ለመመርመር እውቀቱና ጥበቡ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ነው፡፡We need a holistic approach from different perspectives for our deep-rooted and multifaceted problems we are entangled with so that we are able come out of the vicious-circle we are trapped in.ስለዚህም አንዳንዶች አቋምህን ለይ ወዘተ እያሉ ነገሮችን እጅግ በጠበበ እይታ እያዩ አንተንም እንደዚያው በዚህ እጅግ በጠበበ እይታ ብቻ ሊወስኑህና ሊመዝኑህ የሚፈልጉትን ብዙም አታዳምጣቸው፡፡የግድ አንድን የተወሰነ ነገር መደገፍም የሚያስፈልግ ከሆነ ታዋቂዋ ዘፋኝ “የማን ነሽ ይሉኛል የማን ልበላቸው አይቻልሞይ መኖር የማንም ሳይሆኑ ጊዜ የፈቀደውን እስኪወስን ቀኑ፡፡” ያለቸውን ማስታወስ ይቻላል፡፡
  መደገፍና መቃውም በሚባለው አጀንዳ ዙሪያ በዋናነት ማድረግ ያለብን ወሳኝ ነገር ደግሞ እውነትና መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ በመደገፍ ሀሰትና መጥፎ ሆነውን ነገር ሁሉ በመቃወም ነው መሆን ያለበት፡፡ስለዚህም እኔ የእውነትና የእውነት ብቻ ደጋፊ ነኝ ልትላቸው ትችላለህ፡፡እኛ ኢትዮጵያውያንም ዛሬ እጅጉን በጣሙን ግራ በተጋባንበትና በተጨነቅንበት ፈታኝ ወቅት እጅጉን የሚያስፈልገን ወቅታዊ አንገብጋቢ ጉዳይ ጥበብንና እውቀትን እውነትን ተከትሎ የሚገልጥልንና የሚመራን አስተዋይ ሰው ነው፡፡ይህንን ስናደርግ ደግሞ የምንደግፈውንና የምንቃወመውን በምክንያትና በእውነት ላይ ተመስርተን ሁሉን በእውቀትና በጥበብ በማስተዋል እንዳርጋለን ማለት ነው፡፡መመስረትና መገንባት የሚገባን ዜጋ ህብረተሰብና ሀገር ደግሞ በእንደዚህ አይነት አስተሳሰብና አካሄድ ነው መሆን ያለበት፡፡
  እንዲያው ዝምብለን ብቻ በአንጃና በጎጥ ተከፋፍለን በመደገፍና በመቃወም አባዜ ብቻ ታውረንና ታስረን በተወሰነ አስተሳሰብና አካሄድ ዙሪያ ብቻ መሽከርከርና ነገሮችን በጠባብ እይታ ማየት የትም አያደርሰንም፡፡ሰይጣን ድግሞ ከዚህ ከንቱና አጥፊ የሆነ አዙሪት ወጥተን ጥበብንና እውነትን በቅጡ አይተንና መርምረን እንዳንረዳና ከተተበተብንበትም ችግርና አዙሪት እንዳንወጣ ደንቃራ እያደረገብን ነው፡፡እንደዚህ አይነቱን የሰይጣንን መጥፎና መሰሪ ስራ ማጋለጥህ ደግሞ እጅግ የሚያስደንቅህ ስራ ነው፡፡በርታ ቀጥልበት፡፡
  አስተዋይ ፅኁፍ ነው፡፡
  እግዚአብሄር ከመጥፎ ነገር ሁሉ ይጠብቅህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dn Daniel, you are our inspiration through you we see thousands of starts such as the person who post such a wonderful thought. Let be open to the ultimate truth. God bless you all
   Dn Yitayew Ewunetu (Toronto)

   Delete
 16. yazare meseganaye labalabatteh nawe.yaeso eredattaa bayenorebate endehe laagalegelote manasate yekabede nabare.tagebare yagalattatte natte,yattabrako lejoche yehonolacheohe...

  ReplyDelete
 17. ቃለ-ሕይወት ያሰማልን በጣም መልካም ነገር አስተምረኸናል፡፡ ብዙ ጊዜ ከመሥራት ማውራትን ለምናስቀድም መልካም አርአያ ናቸው እነ አባሉቃ፡፡ ምናልባት ሴቶች ካልተቃወሙ “ሴት የበዛበት ወጥ እና ወሬ የበዛበት መንፈሳዊ ሥራ ሁለቱም ይበላሻሉ፡፡” የሚለውን አባባልህንም ወድጄዋለሁ፡

  ReplyDelete
 18. "ሥራን አንደበት ከሚገልጠው ራሱ ሥራው ራሱን ቢገልጥ እንዴት የተሻለ ነው፡፡ ብዙ እያወሩ ጥቂት ከመሥራት፣ ምንም ሳያወሩ ብዙ መሥራት እንዴት መልካም ነው፡፡ ሞያ በልብ ነው ይላል የሀገሬ ሰው::"

  ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ግሩም አገላለጽ ነው፡፡ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ፤ ይጠብቅህም፡፡

  ReplyDelete
 19. Dani Medihanialem abzto yibarkih! Betam amesegnalehu tiru timihirit asitemrehegnal.Dani Medihanialem abzto yibarkih! Betam amesegnalehu tiru timihirit asitemrehegnal.

  ReplyDelete
 20. DEACON DANIEL, WHO HAS TOLD YOU WHAT I TALKED ABOUT BEFORE I WENT EVEN MID WAY?

  I STARTED TRANSLATING A BOOK(SPIRITUAL) TWO YEARS AGO;IN THE MEANTIME I TOLD SOMEONE THAT I STARTED DOING SO.AFTERWARDS, I STOPPED THERE;I REDID MANY TIMES, BUT FOR NO RESULT.

  I HAVE BEEN WORRIED ABOUT THE WHY OF THE UNFINISHED WORK.TODAY, I HAVE GOT THE ANSWER:I MUST HAVE TOLD SATAN WHAT I THOUGHT.

  THANK YOU VERY MUCH.YOU HAVE REALLY SHOWED ME HOW MUCH TEMPTING THE TRIALS OF OUR FATHERS AND MOTHERS WERE.

  ReplyDelete
 21. Dani

  Egziabher yistilin, ebakih Menfsaw endzih tal adrgbin ... le enga ya new yemitekmin.... ye alm chuhet wekesa selchtongal....

  ReplyDelete
 22. Your article has flaws

  ReplyDelete
 23. እግዚአብሔር ይስጥልን። ታላቅ ምስጢር ነገርኸን። ስለአባቶቻችንና እናቶቻችን ስራዎች ሁሌም ኣንድ ኣንድ ነገር ንገረን።

  ReplyDelete
 24. ሰላም ዳኒ ቃለህይወት ያሰማህ በጻፍከው እስማማለሁ ግን ከመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ይባላል ሆንም ተመካክረው ያደረጉት ነገር መልካም ይመስለኛል ሳይበዛ ግን እንደ "ሃበሻ" መድሃኒት ቢደብቁት ትርፉ ውጤት አልባነት ነው. ወዳጄ ብርቱ ሰው ሁን አይደለም ወደሆላ ማለት ወደሆላም እንዳታይ

  ReplyDelete
 25. My God bless you! It is interesting article keep it up.
  I have got great messege.

  ReplyDelete
 26. ግሩም ነው፡፡ቃለሕይወት ያሰማልን!
  በዕውነት አስተውዬው የማለውቀውን ነገር ነው ያሣየኸኝ፡፡
  በጣም አድናቂህ ነኝ ረዥም ዕድሜ እና ሰፊ የአገልግሎት ዘመን እመኝልሃለሁ፡፡ከልብ፡፡

  ReplyDelete
 27. KALA HEIWATE YASAMALEN

  ReplyDelete
 28. EZI GA ...Leke LEK...Blehal..BETAM TEKEKEL NEAW..GEN KLEMED HULU..EHE LEMDE ARIF NEAW...LEMADEKO neaw YAGEGNEWEN HULU AWRU AWRU YEMELEN..THankyou DAni..i have been searching this kind of advise on the net but,no one gives me like this one direct..with my language...LEB YALEW LEB YEBEL!!!

  ReplyDelete
 29. LONG LIVE TO DN. DANI,I MISS U 10Q

  ReplyDelete
 30. trying to defeat satan by ourselves seems to be a good idea but is it an ultimate solution?
  henok L.

  ReplyDelete
 31. betame tiru neger negerkegn amesegenalhu

  ReplyDelete
 32. menfesawi tsihufochuih nafikewign nebere!!!

  ReplyDelete
 33. ግሩም የሆነ መልዕክት ነው፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ/ን!

  ReplyDelete
 34. Kale hiwot yasemalen mengesete semayate yawarselen!!!!

  ReplyDelete
 35. This a great message. We have to win satan, always. And, wud daniel, told us the secret.

  God Be with you and all of us.

  ReplyDelete
 36. በጣም ከምለው በላይ ግሩም የሆነ መልዕክት ነው፡፡በተማርነው ያፅናን!!! ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ/ን!

  ReplyDelete
 37. betam tekami mikir new ejigun fetena yemibezaw bemenager new

  ReplyDelete
 38. Thanks for sharing us it is really very intersting story!!!!!!!

  ReplyDelete
 39. Thank u daneal! You answered the question what i repeatedly think over for so many years. But, i do have another question. Do devil has a capacity to know what we face in the future? Do other angels including the good ones have such talents?

  ReplyDelete
 40. Thank you Dani!!!!

  ReplyDelete
 41. Danmy! lela men elehalehu.. Medhanialem kirestos melkam newna Tedarhen barco bemelkame yanureh enjy!!!!!!! Qale hiwot yasmalen!!!!!

  ReplyDelete
 42. እግዚኣብሀር ይስጥሊኝ ዳኒ ...ትልቅ ሚስጥር ነው ያስተማርከኝ...ምስግና ከ ኣርባሚንችህ ዩኒቨርሲቲ...

  ReplyDelete
 43. እግዚኣብሀር ይስጥሊኝ ዳኒ ...ትልቅ ሚስጥር ነው ያስተማርከኝ...ምስግና ከ ኣርባሚንችህ ዩኒቨርሲቲ...

  ReplyDelete
 44. ዲ/ን ዳንኤል የ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን
  ልጅ እግዚአብሔር ባለህበት ሁሉ ይጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete
 45. ዲ/ን ዳንኤል የ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን
  ልጅ እግዚአብሔር ባለህበት ሁሉ ይጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete