Thursday, September 15, 2011

ገበያ ሲያመች

በድሮ ዘመን ነው አሉ፡፡ ልጂቱ ምጣድ ልትገዛ ገበያ ትወጣለች፡፡ ጥሩ ምጣድ መርጠው እንዲገዙላት እናቷን አስከትላለች፡፡ ገበያ ስትገባ እንዴው ሁሉም ነገር ቀልጧል፡፡ የማይሸጥ የማይለወጥ ነገር የለም፡፡ «ምነው «ስትል ጦር ሊመጣ ነው ተብሎ ሁሉም ነገር ተወዷል» ይሏታል፡፡ «ምን ምን ይሸጣል ብላ ትጠይቃለች፡፡ «ምን የማይሸጥ ነገር አለ፡፡ ከብት ይሸጣል፣ ወርቅ ይሸጣል፣ እህል ይሸጣል፣ ልብስ ይሸጣል፣ ሰውም ይሸጣል» ይሏታል፡፡
«ደግሞ ሰው ለምን ይሸጣል ብላ ትጠይቃለች፡፡ «ባርያ መሸጥ መለወጥ ሊቀር ስለሆነ ሁሉም አሁን እየገዛ ነው» ትባላለች፡፡ እናቷን አንድ ጥላ ሥር አሳርፋ ሄዳ ስታይ እውነትም ልጅ ዐዋቂው፣ ባልቴት ሽማግሌው ሁሉ በባርያ ፈንጋይ እየተያዘ ይሸጣል፡፡ ስትሮጥ ሄደችና እናቷን ይዛ መጥታ በአራት ከብት ለወጠቻት፡፡ ነገሩን የሰማው የሀገሬ ሰው ጉድ ጉድ ብሎ ሲያበቃ «ገበያ ቢያመቻት እናቷን ሸጠቻት» የሚል ተረት አወጣላት፡፡
የሁኔታዎች መመቻቸት የሚያመጡትን ኢሞራላዊነት ከገለጥንባቸው ነባር አባባሎቻችን አንዱ ነው ይኼ፡፡ «የአንዳንዱ ሰው ትክክለኛነት፣ ቆራጥነት፣ ሞራላዊነት፣ ጥንካሬ፣ የዓላማ ጽናት፣ እምነት፣ ገበያው እስኪ ያመቸው ድረስ ነው፤ ገበያ ካመቸው ሁሉንም ሽጦ ለማትረፍ ዝግጁ ነው» ነው የሚሉን ቀደምቶቻችን፡፡
ገበያ ሲመች የማይሠራ ኢሞራላዊ ሥራ የለም፡፡ ገበያ ሲመች ሀገር ይሸጣል፣ ኅሊና ይሸጣል፣ መሬት ይሸጣል፣ ቅርስ ይሸጣል፣ ስም ይሸጣል፣ ባህል ይሸጣል፣ ፍትሕ ይሸጣል፣ እናት ይሸጣል፣ አባት ይሸጣል፣ ልጅ ይሸጣል፣ አካል ይሸጣል፣ ሞያ ይሸጣል፣ ሰርተፊኬት ይሸጣል፣ ክህነት ይሸጣል፣ እምነት ይሸጣል፡፡ ምን የማይሸጥ ነገር አለ፡፡
አንዳንዶች ለመኖር ኅሊናን መሸጥ የሚያዋጣ ከመሰላቸው ከመሸጥ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ገበያ ካመቸ ኅሊናን ይሸጡታል፡፡ መመዘኛቸው ትክክል ነው አይደለም፣ ሞራላዊ ነው አይደለም፣ እውነት ነው አይደለም፣ ሕጋዊ ነው አይደለም የሚለው ሳይሆን ያዋጣል ወይስ አያዋጣም የሚለው ብቻ ነው፡፡ እየሠሩ ያለው ነገር ከሚያምኑበት ነገር ጋር ቢጋጭም ባይጋጭም፣ ትናንት ሲያስቡት ከነበረው ነገር ጋር ቢለያይም ቢስማማም፣ ቀድሞ ከተናገሩት ነገር ጋር ቢሠመርም ባይሠምርም ዋናው ነገር አሁን ያዋጣል ወይስ አያዋጣም ብቻ ነው፡፡
እንደዚህ ዓይነት ሰዎች የሚሞቱለት አቋም፣ ሃሳብ፣ ርእዮተ ዓለም፣ መሥመር፣ እምነት፣ ማንነት፣ ራእይ የላቸውም፡፡ እንኳንስ ሃሳባቸውን እና አቋማቸውን የሚያዋጣ ሆኖ ካገኙት የትውልድ ቦታቸውን፣ ብሔረሰባቸውን እና ወላጆቻቸውን ጭምር ለመቀየር ዝግጁ ናቸው፡፡ ትናንት አዋጥቷቸው ጎጃም ተወልደው እንደሆነ የዛሬውን ገበያ አይተው ጎንደር ሊወለዱ ይችላሉ፡፡ ጎንደር መወለዳቸው የረከሰ ከመሰላቸውም ትግራይ ወይንም ወለጋ ከመወለድ ወደ ኋላ አይሉም፡፡
እነዚህ ሰዎች አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ፣ ሶማሌ ወይንም ጉራጌ የሚሆኑት ከዚያ ማኅበረሰብ ስለተወለዱ ወይንም እዚያ ስላደጉ፣ ያለበለዚያም ቋንቋውን ስለሚናገሩ አይደለም፡፡ ያዋጣል ወይስ አያዋጣም? ነው መመዘኛው፡፡ ገበያው ካመቼ ማንነትም ይቸበቸባል፡፡ 
ሰው አመለካከቱን፣ አቋሙን ወይንም ርእየቱን ሊቀይር ይችላል፡፡ ነገር ግን ተአምራዊ በሆነ ድንገቴ መንገድ ሰው እነዚህን ነገሮች ሊቀይር አይችልም፡፡ የሰው ኅሊና እንደ ኮምፒውተር በፈለጉት ጊዜ የፈለጉትን ሶፍትዌር በፍጥነት የሚጭኑበት አይደለምና፡፡ ማሰብ፣ ማብሰልሰል፣ ከራሱ ጋር መሟገት፣ መረዳት፣ ማስረዳት፣ መመዘን፣ ማመዛዘን ይፈልጋል፡፡ ሲያምንም በምክንያት ነው፣ ሲለወጥም በምክንያት ነው፡፡
የገበያ ሰዎች ግን እንደዚህ አይደሉም፡፡ አንድን አቋም ወይንም አስተሳሰብ፣ አመለካከት ወይንም ርእዮተ ዓለም የሚመዝኑት ከአቋማቸው እና ከአስተሳሰባቸው አንፃር አይደለም፡፡ ትክክል ነው ወይንስ ስሕተት፣ ያስኬዳል ወይስ አያስኬድም፣ ያሳምናል ወይስ አያሳምንም፣ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም፣ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም፣ የሚል መመዘኛ የላቸውም፡፡ ይሸጣል ወይስ አይሸጥም ነው ጥያቄአቸው፡፡
ያለ ምንም አሳማኝ ምክንያት ሰው ይዞት ከነበረው አቋም በድንገት በተቃራኒው ከተገኘ አንዳች የሚያዋጣ ገበያ አግኝቷል ማለት ነው፡፡ ሰው እንዴት በድንገት ከተቃዋሚነት ወደ ደጋፊነት ከደጋፊነትም ወደ ተቃዋሚነት ሊቀየር ይችላል፡፡ አስተሳሰብ ሂደት እንጂ ተአምር አይደለማ፡፡ 
በሀገራችን የየከተማውን መሬት ቸብችበው ቸብችበው የጨረሱት እነማን ናቸው? ለገበያ እንጂ ለኅሊናቸው የማይሠሩ ናቸዋ፡፡ መሬት ውድ ነው? አዎ፡፡ ሚሊየን ብር ያስገኛል? አዎ፡፡ የተቀመጡበት ቦታ ሊያስቸበችብ የሚያስችል ነው? አዎ፡፡ እነ እገሌ የከበሩት መሬት ሽጠው አይደለም? አዎ፡፡ ታድያ እኔስ የምችለውን ያህል ሽጬ የድርሻዬን ብወስድ ምናለ? እንዴ ኅሊና የለም እንዴ፡፡ ገበያው ያመች ይሆናል፡፡ ግን ገበያ ስላመቸኮ እናት አትሸጥም፡፡
የሀገር ሕግ ሊላላ ይችላል፡፡ ሁኔታዎች ሊያመቹ ይችላሉ፡፡ ገበያው ደርቶ ይሆናል፡፡ ዕድል እንደ ትኩስ ኬክ ፊት ለፊት ቀርቦ ይሆናል፡፡ እድሜ ልክ ተሠርቶ የማይገኝ ገንዘብ በካሬ ሜትር ይገኝ ይሆናል፡፡ ግን ኅሊናስ፡፡ አእምሮስ፡፡ ኢትዮጵያ የኛስ ሀገር አይደለችም እንዴ፡፡ ትውልድስ? ነገስ? አይታሰብም እንዴ፡፡
ሰውኮ ከእንስሳ ከሚለይባቸው ነገሮች አንዱ እርሱ ህልው ሆኖ ከሚኖርባቸው ዘመናት በኋላ ላለው ህልውናውም ስለሚያስብ ነው፡፡ በዐጸደ ሥጋ እያለ በአካል ህልው ይሆናል፡፡ በአካልም ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ከዐጸደ ሥጋነት ሲያልፍ ደግሞ በታሪክ ውስጥ ህልው ይሆናል፡፡ ወይንም በዐጸደ ነፍስ ህልው ይሆናል፡፡ ሰውኮ ስለ ሁለተኛ ህላዌውም መጨነቅ አለበት፡፡ እኔ ከሞትኩ ያለችውኮ ማን እንደሆነች እናውቃታለን፡፡
ከጣልያን ጋር አምስት ዓመታት የተዋጉት አርበኞች በዘመናቸው ለመጠቀም አልነበረም መሥዋዕትነት የከፈሉት፡፡ እንዲያውም በዘመናቸው ለመጠቀም ከጣልያን ጋር መሞዳሞዱ የተሻለ ይሆንላቸው ነበር፡፡ ሀገራቸውን እና ክብራቸውን ሽጠው የዕለት ክብር የዓመት ግብር ማግኘት ይችሉ ነበር፡፡ ግን ሌላም ነገር አለ፡፡ ታሪክ አለ፡፡ ማንነት አለ፡፡ ሀገራዊ ክብር እና ኩራት አለ፡፡ የዜግነት ግዴታ አለ፡፡ ይህ ነው አስገድዶ ጫካ ያስገባቸው እንጂ ሀገር ለመሸጥማ እንደዚያ ጊዜ አመቺ ገበያ አልነበረም፡፡ እነርሱ ግን ገበያ አመቸ ብለው እናታቸውን አልሸጡም፡፡
ሰው ጉቦ ለመቀበል መሟገት ያለበት ከኅሊናው ጋር ነው፡፡ ሁኔታዎቹ ጉቦ ለመቀበል ያመቻሉ ወይስ አያመቹም አይደለም መመዘኛው፡፡ ሰው በዘመድ አዝማድ ለመሥራት መመዘኛው የነገሩ ትክክል መሆን እና አለመሆን እንጂ ጊዜው ለዘመድ አሠራር ያመቻል ወይስ አያመችም መሆን አልነበረበትም፡፡
አሁን አሁንኮ ገበያ ኅሊናን እና ልቡናን እየተካ ነው፡፡ የሞራልን እና የእምነትን ቦታ እየወሰደ ነው፡፡ ሁሉ ገበያ መር ከሆነ ለዚህ ሕዝብ የሚያዝንለት ታድያ ማነው? ነጋዴውም ለገበያው፣ ባለ ሥልጣኑም ለገበያው፣ የሃይማኖት መሪውም ለገበያው፣ ገበሬውም ለገበያው ብቻ ከታዘዘ ለኅሊናው የሚታዘዝ ማን ሊሆን ነው፡፡ ይህ እኛ የምናገለግለው፣ የምንሸጥለት፣ የምንወስንለት እና የምንወስንበት ሕዝብ የኛ አይደለም እንዴ፡፡
ገበያው አመቼ ተብሎ የአንድ ብር ጨው አሥር ብር፣ የሁለት መቶ ብር በግ ሦስት ብር፣ የአሥር ብር ዘይት መቶ ብር፣ የሰባት ብር ስኳር ሃምሳ ብር፣ የሦስት መቶ ብር ጤፍ ሁለት ብር፣ የሁለት ብር ሽንኩርት ስድሳ ብር መሸጥ አለበት እንዴ፡፡ ይህኮ ዕቃ መሸጥ አይደለም የገዛ ሕዝብን መሸጥ እንጂ፡፡ እንዴት ባህል አንድ ያደረገንን፣ እንዴት ታሪክ አንድ ያደረገንን፣ ገበያ ይለያየናል፡፡ እንዴት እምነት ያፋቀረንን፣ ኢትዮጵያዊነት ያስተዛዘነንን ገበያ ያጨካክነናል፡፡
እንዴው ለመሆኑ እኛ ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ ፓስተር፣ ቄስ፣ ሼክ፣ አስመላኪ፣ አስዘማሪ፣ አስ ሰጋጅ፣ ነቢይ፣አጥማቂ፣ መጋቢ፣ አለቃ፣ መልአከ እገሌ፣ ጳጳስ፣ የተባልነው ሰዎች እውነት እንነጋገርና ለቦታው ተገቢ ስለሆንን፣ ዕውቀቱ ስላለን፣ ቦታውን የሚመጥን ጸጋ እና ቅድስና ስላለን ነው ወይስ ገበያው ስላመቼ ነው የተቀመጥነው፡፡ ለመሆኑ የያዝነው ቦታ ክብር፣ ዝና፣ ገንዘብ እና ጥቅም፣ የማያስገኝ ቢሆን ኖሮ አሁን ባለንበት ቦታ ተለምነን እንኳን እንቀመጥ ነበር? ገበያ ስለሚያመች ግን ለቦታው የተሠራውን ሥርዓት ሸጥነው፤ መመዘኛውን ቸበቸብነው፡፡ የፈጣሪን ጸጋ በገንዘብ ለወጥነው፡፡ እኛ ወደ ቦታው መሄድ ሲገባን ቦታውን ወደ እኛ አመጣነው፡፡
ይኼ በየቤተ እምነቱ የምንሰማው ትርምስ፣ ግርግር፣ ውጣ ውረድ፣ ትግትግ፣ ጭቅጭቅ፣ ሙግት በዋናነት የገበያ ግርግር ነው፡፡ ዛሬ ገበያው ከሚገባቸው ሰዎች ይልቅ ለጮሌዎች ያመቻል፡፡ ዛሬ ገበያው ኅሊናቸውን በጥሩ ዋጋ መሸጥ ለሚችሉ ሰዎች ያመቻል፡፡ የሚገባቸው ሰዎች በየጓዳው እና በየፍርክታው ቀሩና የማይገባን ሰዎች ቦታውን ያዝነው፡፡ እነዚያ ለምን ቀሩ? ኅሊናቸውን መሸጥ ባለመቻላቸው፡፡
«በከንቱ የተቀበላችሁትን በከንቱ ስጡ» ያለውን የፈጸሙትማ ኩርማን እንጀራ በልተው፣ አጎዛ ላይ ተቀምጠው፣ መደብ ላይ ተኝተው ለፈጣሪ ሲያገለግሉ ኖሩ፡፡ እነዚያማ እውነትን ለገበያ ከማቅረብ ይልቅ ለያዙት እውነት መሞትን መረጡ፡፡ እነዚያማ በአቋማቸው ላይ ከመደራደር ይልቅ ከነ አቋማቸው መሰቃየትን መረጡ፡፡ እነዚያማ ጥያቄያቸው ስንት? የሚል ሳይሆን ለምን? የሚል ሆነ፡፡ እውነተኞች እንጂ ገበያተኞች መሆን ስላቃታቸው ከገበያ ውጭ ሆኑ፡፡
ገበያ ካመቸ ልጅም ትዳርም እንደሚሸጥ በዘመናችን አየንኮ፡፡ እዚህ አሜሪካ ብቻቸውን ለሆኑ እናቶች መንግሥት የሚሰጠው የተለየ ክብካቤ እና የገንዘብ ርዳታ አለ፡፡ ታድያ አንዳንዱ ባለ ትዳር የሀገሬ ሰው ተስማምቶ በፍርድ ቤት ይለያያል፡፡ ከዚያም ባልም ለብቻ ሚስትም ለብቻ በመኖር ይህንን ርዳታ ይቀበላሉ፡፡ ባህል ደኅና ሰንበት፣ ይሉኝታ ደኅና ሰንብት፣ ሃይማኖት ደኅና ሰንብት ማለት ይኼኔ ነው፡፡
አንዳንድ ቦታማ ይኼ ተለያይቶ መኖር ይለምድባቸውና በዚያው ተፋትተው የሚቀሩ ብዙ ናቸው፡፡ የአሜሪካ ገበያ ትዳርን ሽጦ ገንዘብ ያስገኛል፡፡ ገበያ ካመቸ ምን የማይሸጥ ነገር አለ፡፡
በአሜሪካ ምድር የቅንጦት መኪኖችን ከሚነዱ የሀገሬ ልጆች መካከል ጥቂቶቹ ልጆቻቸውን በመሸጥ የገዙት መሆኑን ሰምቻለሁ፡፡ ልጅ ለማሳደግ አልቻልኩም ብለው ለአሳዳጊ ሰዎች ያስረክባሉ፡፡ ከዚያም በአንድ በኩል ለልጆቻው ያወጡት የነበረውን ቆጥበው፣ በሌላ በኩል ደግሞ በልጆቻቸው ቁጥር የታክስ ተመላሽ አሠርተው በሚያገኙት ገንዘብ ደልቀቅ ያለ መኪና ገዝተው ደልቀቅ ብለው ያሽከረክራሉ፡፡ አይቆ ረቁራቸውም፣ አይሰማቸውም፣ አያንገበግባቸውም፣ አያሳፍራቸውም፡፡ ገበያ አመችቷቸው ኅሊናቸውንም ልጆቻቸውንም ሽጠዋልና፡፡
ባህላችን ካቆየልን በጎ ነገሮች አንዱ ለኅሊና መሞት ነው፡፡ በልማዳችን የጠፋ ከብት ያገኘ ሰው እንኳን እስከ ሰባት ዓመት ባለቤቱን ይጠብቅ ነበር፡፡ ሞራላዊነት ከማየሉ የተነሣ ተገፍቶ እና ተጨቁኖ ያደረገው ሞራላዊ ነገር እየቆረቆረው
ልጅ አሳድግ ብዬ
ካገር እኖር ብዬ
ላባሻ ዳርኩለት ሚስቴን እቴ ብዬ
እያለ ያንጎራጉር ነበር፡፡ አንድ ባላባት ተከትሎ የመጣ ጦረኛ በየገበሬው ቤት ይሠማራና ይቀመጣል፡፡ የገበሬው ሚስት ቆንጆ ከሆነች «ይህቺ እኅትህ ናት አይደል» ይለዋል፡፡ አይደለችም ካለ ይገድለዋል፡፡ ወይንም ያሳሥረዋል፡፡ እናም «አዎን» ይላል፡፡ በግድ አዎ አሰኝቶ ሚስቱን ይዞበት ያድራል፡፡ ይህንን ነው በእንጉርጉሮ የገለጠው፡፡
ዛሬኮ ተሰምቶት የሚያንጎራጉር የለም፡፡ እንዲያውም በኩራት ይነገራል፡፡ አራዳነት፣ ቀልጣፋነት፣ ብልጥነት፣ ሆኗል፡፡ ገበያ መር ኢኮኖሚ እንጂ ገበያ መር ማኅበረሰብ በሰላም እና በአንድነት መዝለቅ አይችልም፡፡ የማኅበረሰቡ እሴቶች በሙሉ ለገበያ እየቀረቡ እንዳመቺነቱ ከተቸበቸቡ ያን ሕዝብ አንድ አድርጎ የሚያስተሳስር ምን ነገር ይተርፈዋል?
አንጀቴ ተቆርጦ ከሆዴ ከወጣ
እንግዲህ ሐኪሙ ምን ሊቀጥል መጣ
አይደል ያለቺው ዘፋኟ፡፡

40 comments:

 1. እንዴው ለመሆኑ እኛ ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ ፓስተር፣ ቄስ፣ ሼክ፣ አስመላኪ፣ አስዘማሪ፣ አስ ሰጋጅ፣ ነቢይ፣አጥማቂ፣ መጋቢ፣ አለቃ፣ መልአከ እገሌ፣ ጳጳስ፣ የተባልነው ሰዎች እውነት እንነጋገርና ለቦታው ተገቢ ስለሆንን፣ ዕውቀቱ ስላለን፣ ቦታውን የሚመጥን ጸጋ እና ቅድስና ስላለን ነው ወይስ ገበያው ስላመቼ ነው የተቀመጥነው፡፡ ለመሆኑ የያዝነው ቦታ ክብር፣ ዝና፣ ገንዘብ እና ጥቅም፣ የማያስገኝ ቢሆን ኖሮ አሁን ባለንበት ቦታ ተለምነን እንኳን እንቀመጥ ነበር?

  ReplyDelete
 2. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel. Atlanta

  ReplyDelete
 3. ውድ ወንድሜ ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት ሰላም እና ጤና ላንተ ይሁን!!!ወደ ዓለም አደባባይ ሳትወጣ በፊት በመንፈሳዊ/ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት ከረዥም ዘመን በፊት አውቅሀለሁ::አሁንም ጥሩ እየሰራህ ነው::ግን አንዳንዴ ለምትጽፋቸው ርዕሰ ጉዳዮች ምን አይነት መልስ /አስተያየት መስጠት እንዳለብኝ ይማታብኛል::ምክንያቱም አቋምህን ማወቅ ስለማልችል::አቋምህን ግን ማወቅ ያልቻልኩት ስላልገለጥከው ነው::በተለይ በተለይ በተለይ ፖለቲካዊ አቋምህ ::ሲጀመር ለየብቻ እንኳን መወያያ ርዕስ ቢሆኑ እድሜ ልክ የማያልቁትን የኢትዮጵያ ታሪክ:ባሕል:እምነት:ፖለቲካ እና ትውፊት በአንድ ሰው መመልከት በጣም ይከብዳል::ምክንያቱም ስለፖለቲካው ስታነሳ ኃይማኖትን ታስታክከዋለህ::በተጨማሪም አንድ ሰው በነዚህ ሁሉ ነገር ምልዑ መሆን ይከብደዋል::ወይም አይችልም::መወያየት ያለብን እኮ አቋሙ እና ፍላጎቱ በግልጽ ከታወቀ ሰው ጋር ቢሆን መማማር ይቻላል::ብዙ መንፈሳዊ ጽሑፎችህ ክርስትናን አሳበው ባርነትን ነው የሚሰብኩት::የማይቻለውን እንድንችል ትሰብከናለህ::ከብዙ ነገሮች ውስጥ ራስህን አውጥተህ ነው የምትጽፈው::አንተስ እዚያ ጹሑፍ ውስጥ ቦታህ/አቋምህ የቱ ጋር ነው?ለምሳሌ እዚህ ምልከታ ላይ እራስህን አይተሀል ወይ??? ስለማከብርህ ብዙ ልልህ አልደፍርም::ስለዚህ ብትችል ብትችል ሁሉን ትተህ ገጹን ኦርቶዶክሳዊ ገጽ አድርገው እና እንማማርበት::ታሪክን ለባለታሪክ/ፖለቲካን ለፖለቲከኛ ተወው እና ከኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ጋር የተያያዙ ታሪክ:ባሕል:እምነት እና ትውፊት መወያያ ገጽ አድርገው::አዲስ ነገር ላይ እና እዚህ ገጽህ ላይ የምትጽፋቸው ክርስትናን አሳበው ባርነትን የሚሰብኩ አጻጻፎችህ በጣም ይቆረቁራሉ::ያናድዳሉ::ፖለቲካውን ከዚህ በኋላ የምትጽፍ ከሆነ አቋምህን በግልጽ አስቀምጠህ ዳር ዳር ሳትል ክርስትናን ሳታስታክክ ጻፍ::ማለትም አገሬን ያለባህር በር ያስቀረ:ኢኮኖሚውን በተወሰኑ ሰዎች እጅ እንዲሆን ያደረገ:የአገሬን ሕዝብ በዘር:በጎሳ:በወንዝ የከፋፈለ:አሳፋሪ ስምምነቶችን ከጎረቤት አገሮች ጋር የሚፈራረም ...ዘረኛ መንግስት ደጋፊ መሆንህን በግልጽ አስታውቅ::ከዛ መልስ መስጠት ይቀለኛል::ማስረጃ ስላለኝ ከምንም በላይ እውነት ስላለኝ አሸንፍሀለሁ::የሰዉ አገር ብሎገር ምን አይነት ለውጥ እንዳመጡ አላየህም እንዴ?ሰለዚህ እኛንም የምትረዳን ከሆነ አቋምህን በግልጽ አሳውቀህ ጻፍ::ክርስትናውን ለስውር የፖለቲካህ አላማ አታውለው::መቻቻል:ለምጣዱ ሲባል:...እያልክ የጻፍካቸው ነገሮችህ በተለይ የዘረኛ መንግስት ደጋፊ እንደሆንክ በግልጽ አሳብቀውብሀል::ለምን የዘረኛ መንግስት ደጋፊ ሆንክ ብዬ አልልህም::ሙሉ መብትህ ስለሆነ ካንተ በላይ ያንተን መብት አከብርልሀለው::ግን በክርስትና ስም ባርነትን አትስበከን!!! ቦታው ባይሆንም ይህን አልኩህ ከተረዳኸኝ::
  አዲስ አበባው ነኝ::

  ReplyDelete
 4. Dani, this is really an amazing article. This is the central issue of our society. We know the right thing but just don't do it. May God help all of us to respect our values. Dani, you are one of the best thinkers this country got. This days, we also come to understand the fact that we should pray to you to live the life you are preaching. May God keep you safe from temptation by devil. Really thank you!

  አንዳንዶች ለመኖር ኅሊናን መሸጥ የሚያዋጣ ከመሰላቸው ከመሸጥ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ገበያ ካመቸ ኅሊናን ይሸጡታል፡፡ መመዘኛቸው ትክክል ነው አይደለም፣ ሞራላዊ ነው አይደለም፣ እውነት ነው አይደለም፣ ሕጋዊ ነው አይደለም የሚለው ሳይሆን ያዋጣል ወይስ አያዋጣም የሚለው ብቻ ነው፡፡ እየሠሩ ያለው ነገር ከሚያምኑበት ነገር ጋር ቢጋጭም ባይጋጭም፣ ትናንት ሲያስቡት ከነበረው ነገር ጋር ቢለያይም ቢስማማም፣ ቀድሞ ከተናገሩት ነገር ጋር ቢሠመርም ባይሠምርም ዋናው ነገር አሁን ያዋጣል ወይስ አያዋጣም ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. mr አዲስ አበባው ,do u know democracy? and peolpe right if u dont like just dont visit the blog as simple as this . sewu endet new yetebelashew , ebakih keep writing those good articles ,but one thing ,yihichin melkam medrek liatefa eyashetete new pls take care.

  ReplyDelete
 6. Dear Mr Addis Ababa, with all your respect did you read what you wrote before you post?
  Just listen to yourself, you claim to be a christian and I smell hatred in your comments.
  I may not be as smart and out spoken as you are, but there are some good things we can admit from any government/regime/person or organization, we complement that and tell them that they are not doing right whenever they do wrong. That is as a citizen. If you claim to be a member of a political party that is a different story...
  Trust me you would rather hear Deacon Daniel talk about "woyane, politics,.... all hatred" I think that's what you want to hear.
  If you just read only this article, you can see what his position about politics, culture, economy, religion, etc
  "fetary melkam yeminasibebetin libona lehulachin yadil"

  Sorry if I offended you, also that I wrote in English, I don't have Amharic software for now. Oh one more thing I personaly don't like "woyane" and woyane mentality.

  ReplyDelete
 7. Dear Addis Abebaw,

  I respect your rights to express your justification either way. Your are not the only one who is questioning about Daniel's stance. He may be or may not ,irrespective of membership, be favoring the ruling party one way or the other. It is up to him and no one dead surely know unless he speaks of it.

  But what surprises me every time is that in the course of each and every articles he has recently posted, the question is about his stance. Does a man who is supporter or member of the ruling party is generally supposed to be distractive?

  When he first conceived the idea of blogging, I felt that he has made his mind clear of the vision and then the mission he has to accomplish times to come. For me, I don't know how far is true by his side, I guess that the blog is created to address the multi-faceted affairs of Ethiopia. And this can be proved by going through all his articles posted so far.

  I believe that from the articles he has been delivering since the start, I concluded that he is getting to be come SOCIAL CRITIC. In doing so a writer can't stop and shall not bound himself from inhaling and breathing what he sees, feels, believes, out to share the public.

  As a writer, author, critic, spiritual servant and traveler, I wonder if he is limited to preaching. But he never stop there, instead he prefers to bound himself in all walks of life.

  Let us raise questions on the bases of the justifications of each and every article regardless of his stance. He may make mistakes, for sure he does and has done before because he is human. I believe he is a guy who take the advantage to learn from his mistakes that is what I witnessed not afar but recently.

  Many Thanks to Daniel and Who always give valuable opinions

  May God Bless Ethiopia and its People. Amen

  ReplyDelete
 8. ምንአለበት አስተያየት የምንሰጥ ሰዎች ሁሉን ነገር ከፖለቲካ ጋር ባናያይዘዉ እዉነት ሲነገረን ለምን ይቆረቁረናል? ኢትዮጵያዊ ጨዋነታችን የት ሄደ የመናገር መብት ሲባል መሳደብ ብቻ ሆነ ነገሮችን ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እስቲ እናመዛዝናቸዉ ነገ የተሪክ ተወቓሽ ከመሆን አንድንምና መልካሙን ሁሉ ለማዲረግ እንተባበር ለጦርነትና ለሰላማዊ ሰልፍ ብቻ መተባበር መፍትሄ አያመጣም።


  ልባርጋቸዉ ከሚኒሶታ

  ReplyDelete
 9. እንዴው ለመሆኑ እኛ ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ ፓስተር፣ ቄስ፣ ሼክ፣ አስመላኪ፣ አስዘማሪ፣ አስ ሰጋጅ፣ ነቢይ፣አጥማቂ፣ መጋቢ፣ አለቃ፣ መልአከ እገሌ፣ ጳጳስ፣ የተባልነው ሰዎች እውነት እንነጋገርና ለቦታው ተገቢ ስለሆንን፣ ዕውቀቱ ስላለን፣ ቦታውን የሚመጥን ጸጋ እና ቅድስና ስላለን ነው ወይስ ገበያው ስላመቼ ነው የተቀመጥነው፡፡ ለመሆኑ የያዝነው ቦታ ክብር፣ ዝና፣ ገንዘብ እና ጥቅም፣ የማያስገኝ ቢሆን ኖሮ አሁን ባለንበት ቦታ ተለምነን እንኳን እንቀመጥ ነበር? ገበያ ስለሚያመች ግን ለቦታው የተሠራውን ሥርዓት ሸጥነው፤ መመዘኛውን ቸበቸብነው፡፡ የፈጣሪን ጸጋ በገንዘብ ለወጥነው፡፡ እኛ ወደ ቦታው መሄድ ሲገባን ቦታውን ወደ እኛ አመጣነው፡፡
  G from MN ,USA

  ReplyDelete
 10. @ አዲስ አበባው፦ በወንድምህ አይን ያለውን ጉድፍ ከምትመለከት በራስ አይን ያለውን ምሰሶ አውጣ። አቶ አዲስ አበባው እኔ እንደገባኝ ከሆነ የዲ/ን ስነጽሁፍ የተደበቀ አጀንዳ ያለው መስሎሓል። ይህ አንተን ሊወክልም ላይወክልም ቢቺልም እንኳ ብዙዎቻችን ለነገሮች ያለን ግንዛቤ ከግል አመለካከታችን ጋር የተዛመደ ይሆናል። ግን ህሊናህን ከወገንተኛነት ነጻ አድርገህ ጽሁፎቹን ብትመለከተው ነጥቦቹ የሚያመለክቱት የእኛን የዘወትር አመለካከትና ማህበራዊ ድርጊት ነው ብዬ አምናለው። የኢትዮጵያ ውድቀት እኮ ከመንግስት ባለስልጣናት ብቻ እንዳልሆነ በጣም እሙን ነው። የአገሬው ህዝብ አንድ ቢሆን ሁላችንም በየዘርፋችን ይህችን ሀገር ባንቸረችራት ለዛሬ ብለን እራእይ አልባ ባናደርጋት የኢትዮጵያ ትንሳኤኮ ሩቅ አይደለም። የሕዝብ ንስሐ ሀገር ያስምራል፤ ፍቅርን ያመጣል፤ መንግስትን ለህዝብ ያስገዛል (ሌባም ይሁኑ ጥሩ የመሪዎች እስትንፋስ እኮ በፈጣሪ እጅ ነው)። አሁን የሚባለውስ "እናንተ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ እኛም እንዲሁ እናደርጋለን"።
  ለዚይ አይነት አጻጻፍ ግን ጸሐፊው የፓለቲካ አቁዋሙን የማሳወቅ ወይም ያለማሳወቅ መብቱ የተጠበቀ ይመስለኛል።
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 11. ወይ ፈጣሪ ምን አይነት አስተያየት ነው ሰሞኑን የምናነበው? 'አዲስ አበባው' ደሞ አንተም መጣህ? እስኪ የሚፃፈውን ከሰው ማንነት ነጥለህ ለማንበብ ሞክር :: የሱ ፖለቲካዊ አቋም ላንተ ምን ይረባሃል? ዝም ብለህ የቀረበልህን አንጓለህ አታነብም? ከጀርባ ያለን ማንነት ለባለቤቱ ! ለኛ እስካልጠቀመን ድረስ በጥልቀት የሰውን አቋም መመርመርና ለመንቀፍ መቸኮል ምንድነው ?
  ይልቅ ዳኒ በዛሬው ጽሁፍህ የልቤን ነው የገለፅክልኝ ህሊናን መሸጥ ሀገራችንን እያጠፋት ነውና እንኳን ተነፈስክልን:: ለማይጠቅሙ አስተያየቶች ቦታ አትስጥ በእውነት በቅንነት የሚሰጡ እንከኖችህን እንድታስተካክል የሚጠቁሙ አስተያየቶች ያስታውቃሉ እነሱን አንተም አትጠላም እኔም እደግፋለሁ ዘለው ነቀፋ ሊያውም ረብ የሌለውን ትችት ለሚሰጡ ጆሮ አይኑርህ! በርታልን ብቻ !!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 12. ውድ ዲያቆን ዳኒኤል የሚማርባቸው እና የሚአስተውላቸው ሰው ቢኖር ኖሮ በዚህ ብሎግ ላይ የምትጽፋቸው ቁምነገሮች እጅግ አስተማሪዎች እና እየሞተ ያለውን የዚህን ትውልድ ሞራል የሚታደጉ ናቸው።ነገር ግን አሁንም ሞራላቸውን በመሸጥ ላይ ያሉ አንዳንድ ህሊና ቢስ ሰዎች ይባስ ብለው ያንተን ትክክለኛ እና እውነተኛ ምክሮችህን ለመኮነን ሲሞክሩ እናያለን።ለምሳሌ አዲስ አበባው ነኝ ያለው። እነሱን ተዋቸው። አንተን ብዙዎቻችን እናውቅሃለን። የምትጽፈው የምትናገረው የምታስተምረው እና የምትሰብከው ሁሉ እውነት ነው። የምትተቸውም በትክክል ነው።
  እኔ ካለኝ የጊዜ እጥረት አኳያ ብዙ ጊዜ አስተያየት አልጽፍም። ነገር ግን በምትጽፋቸው ቁም ነገሮች ሁልጊዜም እረካለሁ እደሰትማለሁ።

  ReplyDelete
 13. Ato Adis Abebaw,hilinachewun kemishetu sewoch andu ante timeslegnaleh.Koy ahun ezih lay yesewun maninet mawek lante min yadergilhal?
  Yekerbelihin zim bileh lemin yemitekimin atwesdim?

  ReplyDelete
 14. ሰላም ዲ. ዳንኤል እንደምን አለህ የምትጽፋቸው ቁምነገሮች እጅግ አስተማሪዎች ናቸውና በርታ ግን አንድ አልገባኝ ያለ ነገር እዚህ ለምታወጣቸው ጽሑፎች " ቃለ ሕይወት" ያሰማልን ማለት ይቻላልን? ስላልገባኝ ነው ከተባለማ ለምን Ethio media ሌሎችም ላይ ለሚወጡ ጽሑፎች አንልም? ከተሳሳትኩ አርመኝ እና እስኪ ይህንን ጉዳይ በደንብ እየው። አስተያየት የምትጽፉም ብትሆኑ መንፈሳዊውንና ስጋዊውን እየለያችሁ ቢሆን መልካም ነው።
  አክባሪህ ከቴክሳስ

  ReplyDelete
 15. ከላይ አዲስ አበባው አቁመህ የቱ ጋር ነው የማን የምን ደጋፊ ነህ ልወቅ ያልከው ሰው ስለ ሀገራዊ ነገር ይሁን ስለሐይማኖት ማወቅ ያለብንን በንፁህና በማስረጃ የተደገፉ የሚጣፍጡ ወጎችን እያስኮመኮመን ስለሆነ ሰውየው የገዢውም ይሁን የተቃዋሚ እሱ አይመለከተንም መብቱ ነው፡፡ ለዚህ መልስ ከመለሰልን በቀን ስንቴ ትበላለህ ለምን ገዳም አትገባም አይነት ጥያቄ ውስጥ እንገባለን /ዳኒ ምንም ይሁን እኛ እውቀት ነው የምንፈልገው ጻፍ እናነባለን
  ይሄ ጥያቄ ለምን አስፈለገ ጸሀፊውን እሱ የነዛ ወይም የነዚ ደጋፊ አድርጉ ተደራሽነቱን ለማቀጨጭ ካልሆነ በቀር፡፡
  ለሀገር የሚያስብ ሰው ይሄን ጥያቄ ብሎ አይጠይቅም ጣማሪው ከዚህ በፊት ይሄንን ጥያቄ በጥሩ ሁኔታ መልሶላታል፡፡ የማንም ሳይሆኑ ጥሩ ነገር መደገፍ ይሄንን ለማምጣት ይጥራል፡፡ ከዛ ውጭ ለኔ ታርጋ መለጠፍ የምትፈልጉ የፈለጋችሁትን ለጥፉ ዳኒ ታርጋው ኢትዮጵያ ነው፡፡ ደስ የሚሰኝይሄ ብቻ ነው፡፡ ጡምራውም ተደራሽነቱ ለደጋፊ ለተቃዋሚ ለአገር ቤተ ለዲያስፖራ አይደለም ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ነው፡፡ እና ከላይ ጥያቄ የጠየቁት ሰው ጥያቄውም መልሱም ለኔ አያስተምረኝም ይሄኛው ይህኛውን ዙር አይመጥንም
  በነዚህ ጥያቄዎች ስንቱን አጠፋንው ስንቱን ለሀገር ብሎ የተነሳ ብዕረኛ እጁን ህሊናውን አሳጣን ምንም ላንጠቀም ብዙ ልንማርባቸው የሚችሉ ብዕሮች ተሰደዱ ምን ተጠቀምን ምንም በጎ ሲሰሩ ለምን ክፉ ክፉ እንደምታየን ስራችንን እንጠይቅ ከዛ ውጭ መማሪው በሁለት በኩል የተሳለ ስለት ሲሆን ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ልንኮራ ይገባና እኛ ለሀገር ምን ሰራን ምን አበረከትን;
  ዳኒ ጻፍ እያነባለን ገበታውን ለማንሳት ከመጣር የሚበላውን ጨምሩልን ያን ካልቻላችሁ ልክ እንደኛ ባለሙያውን
  እያደነቃችሁ መዕዱን ብሉ እንደው አወኩብሎ ለሰው ታርጋ መለጠፍ መሮጥ ግን ትዝብት ነው፡፡ ዳኒበርታ እግዚአብሄር ጭምሮ ጨምሮ እውቀትን ይግለፅልህ ለኛም አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡ዮናስአበበ

  ReplyDelete
 16. Dani what should every body do b/c the root of aplant fixed on stoned soil what do u think of its fruit will give it to the beneficiary. 10Q

  ReplyDelete
 17. Dear Daniel,

  I have no words to express my sincere appreciation. You thoroughly observed the actual world. Let us stand together to change the mentality of market oriented personality. As far as my observation is concerned, even the market economy requires an invisible hand. Like the late Adam Smith acclaimed that:
  "[The rich] consume little more than the poor, and in spite of their natural selfishness and rapacity…they divide with the poor the produce of all their improvements. They are led by an invisible hand to make nearly the same distribution of the necessaries of life, which would have been made, had the earth been divided into equal portions among all its inhabitants, and thus without intending it, without knowing it, advance the interest of the society, and afford means to the multiplication of the species."

  ReplyDelete
 18. Dear D/Daniel,
  Thank you for your important and valuable article and it is a hot issue for all of us " Joro yalew yisma" Twlid eyetefa new...Twld ketefa degmo hager yemibalew neger aytasebm....Kale Hiywet Yasemaln .
  Again God bless You!
  Yohannes
  Houston,Texas

  ReplyDelete
 19. ሰላም ዳኒ እግአብሄር ያበርታህ በጣም የሚገረም መንእክት ነው. ግን አንተ በማንኛውም አስትያየት እንዳትፈራ. ለህሊናህ ጻፍ ማንም ምን ሊል ይችላል አንተ ግን እውንትን ብቻ መስክር. አንድ ቀን የተኛው ይነቃ ይሆናል,ማን ያውቃል የነገን.መተቸት እንጂ አይደለም መጻፍ ማንበብ የተሳነውን የኔ ቢጤ አትቀየመው ለምዶበት ነው "የሚያደርጉትን አያውቁም ና ....."ብለህ ለቆምህበት አላማ ሙት.

  ReplyDelete
 20. "Ajeb new " ale degu Yagere sew, Ajeb new....
  Mulugeta ,Vancouver Island

  ReplyDelete
 21. Nigusie from Dz
  kalew hiyot yasemal Dani1 Tiru tazibehal zarem le miyalif gize selamachewn, hayimanotachew, inat betekiristiyanachew yeshexu bet yiquxerew lemeshex kewisti wuci kalew delala gar iyetederaderu yaluutin degmo bet yikuxerewu

  ReplyDelete
 22. wow i like the article but why some of the guys read & understand directly simply this is about our values not political

  ReplyDelete
 23. እንዴት ነህ ዲ.ን ዳንኤል?መቸም አንተ ስትጽፍ እኛም እያነበብን እዚህ ደረስን፡፡እኔ አሁን ግራ ያጋባኝ ነገር ቢኖር ሰዎች የአንተን ጽሁፍ በፈለጉት መልኩ እየተረዱ እንደፈለጉ አስተያየት ሲጽፉ ነው፡፡ቋንቋችን አማረኛ ነው፤የጻፍከውም በአማረኛ ነው አይደለ?ይህ ከሆነ ለምን በትክክሉ መረዳት አቃተን?ከፊሉ ከፖለቲካ ጋር ለማላተም ይሞክራል፡ሌላው ከሃይማኖት ጋር፤ሌላው ደግሞ ከጥቅማ ጥቅም----- ወዘተ፡፡
  አንተ የጻፍከውን እያመሰገኑ ከጽሁፍህ የሚረባቸውን ብቻ እየያዙ ሌላውን መተው ሳይችሉ ቀርተው ይሆን ወይስ ሌላ ተልዕኮ ኑሯቸው እንዳመጣላቸው አስተያየት የሚሰጡት፡፡መጻፍ፤መናገር፤--- መብት ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ በጭፍን ጥላቻ ሰውን ማደነጋገር አይበጅምና አስተያየት ስንሰጥ መልካም እና መጥፎውን ለይተን ቢሆን ሁላችንንም ያስተምራል ባይ ነኝ፡፡በዚህ በኩል እኔ ብሎግህን የምከታተል ቢሆንም በአብዘሃኛው አንተን ደግፎ ወይም ተቃውሞ ነው እንጂ አስተያየት የሚሰጠው ሃሳብህን ነቅሶ ትንታኔ በመስጠት የአንድ ጽሁፍህን ጠንጋራ እና ደካማ ጎንህ የሚያሰፍር ሰው አልገጠመኝም ማለት እደፍራለሁ፡፡እኔን ጨምሮ፡፡ለምን እንደሆነ ግን እስካሁን ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው፡፡
  ስለሆነም የብሎግህ ተከታታዮች ልብ ሰጥቶን የሚረባንን እንድንይዝ የማይረባንን ደግሞ ለይተን ለማውጣት ጌታ ይርዳን፡፡
  ውብሸት ተንታው!!!!!!!!

  ReplyDelete
 24. Wenderful. ዳኒ፣ በጣም አደንቅሃለው፡ በዚሁ፡ቀጥል። Mamush,Minnesota

  ReplyDelete
 25. Money Vs Humanity Part-1
  ልጅ ዳንኤል ይህንን ፅሁፍህን ሳነብ የተሰማኝን ነገር ለመግለፅ እጅግ ቃላቶች ያጥሩኛል፡፡ወንድ ስለሆንኩኝ ወደ ውጪ ሳይሆን ወደ ውስጥ ማልቀስ ግድ ነበረብኝ፡፡ልጅ ዳንኤል አንተ ከፖለቲካ ሰውነትህ ይበልጥ የሃይማኖት ሰው ነህ፡፡ስለዚህም ሃይማኖታዊ ንግግር ብናገር በደንብ ይገባሃል ብዬ አስባለሁ፡፡አውሬው ክብር የሆንነውን የሰውን ልጅ ከሰውነት ክብር በሂደት አስውጥቶን ወደ ቁሳቁስ አምላኪነትና ተከታይነት እየቀየረን ነው፡፡ኤሳው ብኩርነቱን ለሆዱ ብሎ ለምስር ወጥ አልለወጠምን፡፡ክርስቶስን በ3 ዋና ዋና ፈተናዎች የፈተነው አውሬው በስተመጨረሻ በ3ኛው ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህንን ሁሉ የአለም ስልጣንና ክብር እሰጥሀለሁ ብሎ ጌታን ሊያስትበት የሚችለውን የመጨረሻውን የጆከር ካርድ በተስፋ መቁረጥ ተጠቅሞ አልነበረምን፡፡ይሁዳም ፈጣሪውና አዳኙን ክርስቶስን የሸጠው በሰላሳ ዲናር አይደለምን፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ማንነታችንን ክብራችንን ስብእናችንን በእጃችን ያለውን የሚበጀንን መልካሙን ነገር ሁሉ ለብልጭልጭ ነገር ለፍርፋሪና ለገንዘብ በልዋጭ አልሰጠንምን፡፡ክብራቸው በነውራቸው ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው የተባለው መፅሀፍ ቅዱሳዊ አባባል ህገ እግዚአብሄርን ለዘመናት ጠብቃ በኖረችው ሀገር ውስጥ ባለን በእኛ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመብን አይደለምን፡፡በመንፈስ የበላይነት ሳይሆን በገንዘብና በቁሳቁስ የበላይነት መርህ የሚመራውና ገንዘብንና ቁሳቁስን በቀዳሚነት የሚያመልከውን የምእራቡን አለም ስር የሰደደ አስተሳሰብና አካሄድ በዘመነ ግሎባለይዜሽን በራችን ወለል አድርገን እልል እንኳን ደኅና መጣህ ብለን የዛሬ ሃያ ዓመት መንግስት ስንቀይር አጨብጭበን ተቀበልነው፡፡ነገሮችን ሁሉ እንደሚላክልን ወይንም እንደምናስገባው ሸቀጥ እያግበሰበስን ምንም ሳንመረምርና ሳንመዝን እነደወረደ ተቀበልነው፡፡እጅግ በጣም የተራበ ሰው ምናልባት ለጊዜው ርሃቡን እስኪያታግስ ድረስ ያገኘውን ነገር ሁሉ ሳይመርጥ ያለ መጠን አግበስብሶ ይጎርሳል፡፡ነገር ግን ርሃቡ ካለፈለት በኋላ በቀጣይ በማስተዋል የሚበላውን እንዲጠቅመው አድርጎ መርጦ ሊመገብ ግድ ነው፡፡እኛ አኮ ከሰለጠነው የምእራቡ ዓለም ባብዛኛው የወሰድነው የሚረባንንና የሚጠቅመንን ሳይሆን በተቃራኒው ባብዛኛው የማይረባንና የማይጠቅመን ብልጭልጭና አርቲ ቡርቲ የሆነ ነገር ጭምር ነው፡፡እንዴት የ3 ሺህ ዘመን የመንግስት የሀይማኖትና የባህል ታሪክና ማንነት ያላት ሀገር በ20 ዓመታት ውስጥ እነዲህ መላቅጡ የጠፋበት ውዥንብርና ትርምስ ውስጥ ትገባለች?እኔ እስከማውቀው ድረስ አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ ያውም በእንደዚህ አይነት አኩሪና መልካም የሆነ የ3ሺ ሺህ ዘመናት የመንግስት የሀይማኖትና የባህል ታሪክና ማንነት ያላት ሀገር ውስጥ ያለ ህዝብ በእንደዚህ ያለ የብርሃን ፍጥነት ማንነቱንና ክብሩን በእንደዚህ ያለ አጭር ጊዜ ውስጥ ሲያጣ በታሪክ አልሰማሁም አላየሁም፡፡ይህ በሽታ አጠቃላይ የትውልድ ዝቅጠት (Generational Crisis) ውጤት ነው::ነገሮችን እጅግ በጥንቃቄ የሚያይ የሰላ እምሮ ከሌለን በስተቀር እርስ በርሳቸው እጅግ በጣም የሚያምታቱና የሚያሳስቱ Paradoxical የሆኑ ብዙ ነገሮች አንዳሉ መረዳት አለብን፡፡ምናልባት ዛሬ እኛ ብዙም ያን ያህል እእምሯችን አስጨንቀንና አስጠብበን ያልደከምንበትንና ያልፈጠረንነውን የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በገንዘባችን እየገዛን እንደ ማንኛውም ሸቀጥ ወደ ሀገራችን ስላስገባንና ስለተጠቀምን እየሄድንበት ያለውን የጥፋት መንገድ ቆም ብለን ለማየት ብዥታና መምታታት ፋጥሮብን ሊሆን ይችላል፡፡ነገር ግን ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነገር ግን ውድ የሆነችውንና መተኪያ የሌላትን ነፍሱን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል የተባለውን የቅዱስ መፅሀፍ አባባል ልናስታውስ ግድ ይለናል፡፡የሰው ልጅ የፈለገውን ያህል ቢሰለጥንና የፈለገውን ያህል የሳይነስና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ቢጠቀም ሰብዓዊ ማንነቱንና ክብሩን አሳልፎ ለራሱ ለሰራው ቁሳቁስ ነገርና ገንዘብ በልዋጭ ከሰጠ የመጨረሻ ፋይዳውና ትርጉሙ ምንድን ነው?ሰብዓዊነት የሰውነት ክብርና ማንነት ዛሬ ወደየት አቅጣጫ እየሄዱ ነው?ልጅ ዳንኤል እጅግ በሚገርም ሁኔታ ያብራራውን አሳዛኝ ሁኔታ ስናይ እኮ የነብሩ ጅራት አይነት ነገር ሆኖ እኛም ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን በስም ካልሆነ በስተቀር በተግባር ፈፅሞ ልናጣው ጫፍ ላይ ነው እኮ የደረስነው፡፡የቀረን ልቅላቂው ብቻ ነው እኮ፡፡እሱንም በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን አንድ ቀን ጭራሹን እንደፋው ይሆናል፡፡ህሊናቸውንና የስብእና ክብራቸውን ከሸጡ በተራ የፖለቲካ አካሄድና ከሌላም በተራ ጥቅም ከታወሩ ሰዎች ውጪ ነን ብለን የምናስብና የምናምን ተምረናል ፊደል ቆጥረናል የምንል ቀናኢና እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን ነገር በቻልነው አቅም ሁሉ ያለማሰለስ መዋጋትና ወደ አንድ ዘለቄታዊ መፍትሄ ወዳለው ቀና መስመር እንዲያመራ ከፍተኛ የሆነ የዜግነትና የሰብዓዊነት ግዴታ አለብን፡፡ልጅ ዳንኤልም በዚህ አይነት ይህንን አይነት ወሳኝና አንገብጋቢ ርእስ አንስቶ የራሱን አስተያየትና ሀሳብ ሲፅፍልንና ለእኛም መወያያ ሲያደርግ ይህንን ግዴታውን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተወጣ እንደሆነ አምናለሁኝ፡፡
  እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋና እንደ አጠቃላዩ የሰው ዘር የሰውነት ክብራችንና ማንነታችን መጠየቅ መመርመርና መገንባት ግድ የሚለን ታሪካዊ ወቅት ላይ ነን፡፡ይህ የማያስማማው እንድም ጤናማ የሆነ ሰብዓዊ ፍጡር አለ ለማለት ይከብደኛል፡፡ምናልባት ለጥቂቶች እውነተኛው የሰውነት ክብር ማለት ትርጉሙ የራሱን የወጣበትን ህብረተሰብና ወገኑን እረግጦ፣ ዘርፎ፣አራቁቶ፣አደህይቶ፣አስርቦ፣አሰድዶና ገድሎ ምርጥ ፎቅ መገንባት ወይንም ምርጥና ውድ አውቶሞቢል የቤት መኪና ማሽከርከር ወይንም ምርጥ የስልጣን ወንበር ላይ መቀመጥ ወይንም በሀገር ውስጥና በውጪ ባሉ ምርጥና ውድ የዘመናችን የመዝናኛ ቦታዎች እራሱንና እወደዋለሁ የሚለውን ቤተሰቡን ማዝናናት ወዘተ ወዘተ ሊሆን እንደሚችል በተግባር እያየነው ስለሆነ ይህንን መገመት ብዙም አይከብድም፡፡ነገር ግን በዚህ መልክ የገዛ ወገናችንን የሰውነት ክብርና ማንነት አዋርደንና ክደን ያገኘነውን ማንኛውንም አይነት ጥቅምና እርካታ ከህሊናችን ጋር ሞግተን ቆም ብለን በጥሞና እስኪ ሂሳብ እናወራርድለት፡፡በእርግጥ አንድ ግለሰብ ስለራሱ ጠልቅ ያለ ሰብዓዊ ፍቅር ክብርና ማንነት የሌለው ከሆነ በተመሳሳይ መልክ እንደዚሁ ስለ ሌሎች ሰዎች ሰብዓዊ ፍቅር ክብርና ማንነት ግንዛቤውና ደንታው ያን ያህል ሊኖረው አይችልም፡፡
  continues >>>>

  ReplyDelete
 26. Money Vs Humanity Part-2
  ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግናባር እንደተባለው የደረግ ዘመን አይነት የዛሬውና የአሁኑ የዘመኑ ሀገራዊና አለም አቀፍ ዋና መዝሙርና መፈክር ደግሞ ሁሉም ነገር ወደገንዘብ፣ስለገንዘብ፣በገንዘብ፣ከገንዘብ፣እንደገንዘብ፣አስከገንዘብ የሚል ነው፡፡
  ብዙዎቻችን ያልተረዳነው እጅግ ቁልፍና ጥልቅ ቁምነገር ይህንን ነገር ይመስለኛል፡፡ሰብዓዊነትና የሰብዓዊነት ፍቅርና ክብር በሁለተኛ ወይንም በ3ኛ ደረጃ ያለ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡አንድ ወቅት ከብር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሶማሊያ ጦርነት ወቅት ስለጠፋው የሰው ህይወት ሲጠየቁ ይህ እንኳን ለፓርላማው ምንም አይሰራለትም ነበር ያሉት፡፡እኝህ ሰው እስከዛሬ ስልጣን ላይ ካወጣቸው የሀገሪቱ ፓርላማ በላይ እንደሆኑ በደንብ የተረዳሁት የዚያን ጊዜ ነበር፡፡ምናልባት ለሟች ቤተሰቦች እንዳይሰሙ አዝነው ሊሆን ይችላል ይህንን ያሉት፡፡ነገር ግን በዚሁ ፓርላማ ወድ ከሆነው የሰው ልጅ ህይወት በላይ አትኩሮት ተሰጥቶት ስለአንዳንድ የገንዘብ ቁጥሮችና እሁን አሁን እራሱ በራሱ ሌላ ተጨማሪ አሸባሪ ነገር እየሆነ ስለመጣው ስለአሸባሪነት ህግ ጭምር በሰፊው ይተረካል፡፡
  በምእራቡ አለም በተለይም በአሜሪካና በእንግሊዝ ትላልቅ ኮርፖሬት ድርጅቶችና ተቋማት ከተራው ሰው የበለጠ ከብርና ማንነት ተሰጥቷቸው ከፍተኛ የሆነ የህግና የደህንነት ጥበቃና ድጋፍ እየተሰጣቸው ነው፡፡ታላቁ የሀገራችን የጥበብ ሰው ጥላሁን ገሰሰ ከአንድ አስርት አመታት በፊት በዘፈኑ “እያለህ ካለሆነ አያለህ የለህም” ያለው ነገር እሱ ዘፈኑን ከዘፈነበት ወቅት በተሻለ አሁን ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡ከአጀማመሩና ከአስተሳሰቡ ገንዘብ የሰውን ልጅ የሚያገለግል ነገር እንዲሆን መሆኑ ቀርቶ ሰው የገንዘብ ባሪያ የሆነበት ምክንያት እንደገና በጥሞና ሊመረመር ግድ የሚልበት ታሪካዊ ወቅት ላይ የደረስን ይመስለኛል፡፡በቅርቡ የተፈጠረው አለም አቀፍ የፋይናንስና ተከታዩ ኢኮኖሚ ቀውስ እንዲሁም በተለይ በግሪክ የታየው በእዳ የመተብተብ ነገርና በእኛም በሀገራችን እየተፈጠረ ያለው ከልክ ያለፈ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ሌሎችም ነገሮች ሁሉ ይህ ለምን ሆነ ብለን በጥሞና ቆም ብለን እንደንጠይቅና እንደንመረምር ግድ የሚለን ይመስለኛል፡፡
  አዳም ከገነት ከሂዋን ጋር ሲወጣ ጥረህ ግረህ በላብህ በወዝህ ብላ ተብሎ ነው በፈጣሪው የታዘዘው፡፡
  ከዚህ ውጪ ምንም ሳይደክሙ የሌሎችን ድካምና ወዝ በግፍ እየጋጡ በሌሎች ትከሻ ላይ መኖር ከኃይማኖትም አንፃር ሲታይ እጅግ ኃጢያት የሆነ ነገር ይመስለኛል፡፡ነገር ግን አሁን በዝርፊያና በሌብነት በተጨማለቅንበት የእንብላው ዘመን ”ቢዝነስ መስራት” ወይንም “ሙስና” የሚለው ዘይቤና አባባል እንደ No-Fly-Zone ለሰሚውና ለተናጋሪው ቀለል ያለና ብዙም የማያጨናንቅ አባባል የችግራችንን ስፋትና ጥልቀት ቆም ብልን እንዳናይና እንዳንመረምር ትልቅ ብዠታ ፈጥሮብናል፡፡
  እንደ እኔ ብዙም በማይስብ የአስተያየት አቀራረብ ሳይሆን ዳንኤል ደግሞ እጅግ በሚማርክ አቀራረብ ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ እያሳየን ነው፡፡ብዙዎቻችን ነገሮች ለምን እንደዚህ ይሆናሉ ብለን ጠንከር ያለ ጥያቄ አስተያየትና ትችት ከመስጠት ይለቅ ነገሮችን ስንሸፋፍንና አብረን ከሚለቀቀው ዘፈንና መዝሙር ጋር ግማሾቻችን በብልጣብልነትና በአደርባይነት ግማሾቻችን በራስ ወዳድነትና ስግብግነት ግማሾቻችን አርቆ ባለማስተዋልና በየዋህነት እየተመራን በአቀናባሪነትና በአጃቢነት እየተቀበልን በሰፊውና በሀይለኛው ከተለቀቀው ድምፅ ጋር ስንጨፍርና ስናጫፍር አዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ስናሳትፍበትና ስንሳተፍበት የነበረው ግርግርና ሁካታ ያለበት የምሽት ፓርቲው ጭፈራና ፌሽታ ሲያበቃ በነጋታው ነው ምን አይነት ነገር እንደተፈጠረና ምን እንደሆነ ከቀልባችን ሆነን ገምግመን የምንረዳውና የምናውቀው፡፡ዛሬ እኛ ኢትጵያውያንን ገንዘብ፣ከዚህ በፊት በደንብ አይተነው የማናውቀውና ከራሳችን ጋር በደንብ ያለተዋሃደ ብልችልጭና ቁሳቁስ ነገር፣መጤ አስተሳሰብና መጤ የኑሮ ዘይቤ ወዘተ አፍዝዘውንና አደንግዘውን ነባርና የቆየ ኢትዮጵያዊ ክብራችንና ማንነታችን በሂደት ሸርሽረውት ዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ ደረስን፡፡ስለዚህም ዛሬ በዚህ በፈታኝና በችግር ወቅት ጭምር ያ ወገናዊ ጨዋነት መተሳሰብ መረዳዳትና መተማመን ያለበት የኢትዮጵያዊ ማንነታችን በስግብግብነት በሸፍጥ በጭካኔ በመጠፋፋትና በመከዳዳት ተተካ፡፡እርስ በእርሳችን እርስ ብርሱ የሚበላላ የቀን ጅብ ሆንን፡፡ይህ እንግዳ ነገር ግራ የገባቸው አንዳንድ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረባቸው ልበቀናና የዋህ ሰዎች በሚያዩት፣በሚሰሙትና በሚደርስባቸው ግራ የሚያጋባ እንግዳ ነገር እተገረሙና እያዘኑ በየመንገዱ ላይ ለብቻቸው ማውራት ጀመሩ፡፡እረ ምን አይነት እንግዳ የሆነና እስከዛሬ የማናውቀው አዲስ መንፈስ ነው ሀገሪቷ ውስጥ የገባው ሳናውቀው?የሙዚቃው ምት ዜማው ቅላፄውና እንቅስቃሴው ሁሉ ትንሽ ግራ የሚያጋባ እንግዳ ነገር አይደለም እንዴ ነው ወይንስ ዝም ብለን ወጊድ ህሊና ወጊድ ኢትዮጵያዊነት ብለን አብረን እያበድን አብረን እየጨፈርን አሸሼ ገዳሜ እንበል?ከፋም ላማም አኩሪና መልካም የሆነ የ3ሺ ሺህ ዘመናት የመንግስት የሀይማኖትና የባህል ታሪክና ማንነት ያላት ሀገር እንደ ዳይኖሰር ስትጠፋ እንዴት ዝም እንላለን?ነው ወይንስ ይህ አይነቱ ለውጥ ወይንም ትራንስፎርሜሽን እየተዋራ ያለው የእድገትና የትራንስፎርሜሽኑ አንዱ አካል ነው?በፍፁም በፍፁም እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁኝ፡፡ብንወድቅም ብንነሳም፣ብንለማም ብንጠፋም፣ብንራብም ብንጠግብም፣ብንሰለጥንም ብንሰየጥንም እረሳችንን ሆነን የኢትዮጵያዊነትና የሰብዓዊነት ማንነታችንንና ክብራችንን ጠብቀን ነው መሆን ያለበት፡፡በእውነተኛ ማንነታችን ላይ ያልተመሰረተ ማንኛውም ነገር ሁሉ ለጊዜው ቢመስለንም እንኳን በስተመጨረሻ ግን ከንቱ እንደሆነ ልናውቅ ይገባናል፡፡ልማታዊ መንግስት እንደሆኑ ዘወትር የሚነገሩን ገዢዎቻችንን ልማታዊነታቸውን(ይህም ልማታዊነት ነው የሚባለው ነገር በራሱ የሚያጠያይቅ መሆኑ ሳይረሳ) የምንገመግመውና የምንመዝነው በዋናነት ለሚያስተዳድሩት ዜጋ ህዝብና ለአጠቃላዩ ለሰብዓዊ ፍጡር ባላቸው ክብርና ፍቅር ጭምር ሊሆን ይገባል፡፡ልማት የሚመዘነው በዋናነት ለሰው ልጅ ጥቅምና ደህንነት ባለው የመጨረሻ ፋይዳ እንጂ በግልባጩ ባለው ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ብዙም ትርጉም ለሌለው ልማት ሲባል በሚከፍለው አላስፈላጊና ትርጉም የሌለው መስዋእትነት አይደለም፡፡
  ገንዘብ ስልጣኔ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ሁሉም በስተመጨረሻ ሊገመገሙና ሊመዘኑ የሚገባቸውም ከዚህ ክቡር ከሆነው ከሰው ልጅ አጠቃላይ ህልውናና ደህንነት አነፃር ሊሆን ግድ ይላል፡፡
  Continues >>>>>>>

  ReplyDelete
 27. Money Vs Humanity Part-3

  ልጅ ዳንኤል በሚስብ አቀራረብ የገለፃቻው ነገሮች ሲጠቃለሉ አንድ ከውስጣችን የሚረብሸንና የሚሰማን ትልቅ ስር የሰደደ ችግርና አዘቅት ውስጥ እንዳለንና ነገር ግን ችግሩንና መንስኤውን በጠራ ቋንቋ ግልፅ አድርገን ይህ ነው ብለን ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ለመንገርና በቅጡ ለማስረዳት የከበደን ነገር እንዳለ ይሰማኛል፡፡ስለዚህም በነፃ-ገበያ ሽፋን እያራመድነውና እየተከተልነው ያለውን አጠቃላይ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ስርዓትና ሲስተም ከዚህ ትልቅ ትርጉምና ፋይዳ ካለው ከሰብዓዊነትና ከህይወት(Humanity and Life) አጠቃላይ ህልውናና ደህንነት አንፃር ቆም ብለን በጥሞና ልንጠይቅ ልንመረምር ልንመዝንና ከዚህም ተነስተን አስተሳሰባችንና አካሄዳችንን ወደ አንድ የተወሰነ ትክክለኛ አቅጣጫና መስመር ልናስተካክል ግድ ይለናል፡፡በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በዚህ በነፃ-ገበያ ሽፋን ከሰፈነ ስርዓት በተጓዳኝ ለዜጋቸው ለህዝባቸውና ለሀገራቸው ተገቢው ፍቅርና ክብር የሌላቸው ሃላፊነት የማይሰማቸውና ፈሪሃ እግዚአብሄር የራቃቸው ማናቸውም ሀይሎች የአንድን ሀገር የመጨረሻ የስልጣን እርካብ ያለ ማንም ተቀናቃኝና ሃይ ባይ በብቸኝነት በሞኖፖል ሲቆጣጠሩ ውጤቱ እጅግ የከፋና ስር የሰደደ የሥነ-ልቦና፣የሞራል፣የማህበራዊ፣የባህላዊ፣የኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ የማይቀር እጣ ፈንታ ነው የሚሆነው፡፡የዚህ አይነት ስርዓት ውጤት ደግሞ ጥቂቶች በብዙሀኖች ድህነት፣ስቃይና መከራ የነፍሳቸውን ባላውቅም ለስጋቸው ምድራዊ የገነት ህይወትን እንዲኖሩ እያደረጋቸው ነው፡፡የታላቁ የሰብዓዊነት ፍቅርና ክብር በተቃራኒው በተራ በገንዘብና በቁሳዊ ነገር እንዲተካ እየሆነ ነው፡፡በዘመነ ‘ግሎባላይዜሽን’ እና በዘመነ ‘ዲሞክራሲ’ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ እንደ ተራ ውዳቂ ነገር ረከሰ፡፡‘ዲሞክራሲ’ ሲነግስና ቁሳቁስ ሲወደድ በተቃራኒው የሰው ልጅ ግን ከክብሩ ተዋርዶ እረከሰ፡፡ማንኛውም አይዲኦሎጂ ወይንም የፖለቲካ አስተሳሰብና ፍልስፍና ወይንም ሃይማኖት ለሰብዓዊነት ተገቢውን ፍቅርና ክብር መስጠት እስካልቻለ ድረስ ከንቱ ነው፡፡በነፃ-ገበያ ሰርዓት ሽፋን ስርዓት-አልበኝነት ነፃ-ዝርፊያና ነፃ-ነጠቃ በጣሙን እንዲነግስ ሆኗል፡፡በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች በአቋራጭ በብርሃን ፍጥነት የሀብት ጣሪያ ላይ ተፈናጠዋል፡፡ባብዛኛው በዚህ በንፁሃን ዜጎችና ህዝቦች ስቃይና ግፍ ስጋቸውን በልቶ ደማቸውን መጥጦ ከህይወት በታች ከሞት በላይ ያደረገ የገንዘብ ምንጭ ለረጃጅም ህንጣዎችና ፎቆች የህልውናቸው አጥንት፣ጅማት፣ስጋና ደሞ ሆኗቸው ህይወት ዘርተውና አምረው በግርማ ሞገስ ምስኪን ዜጎችን የቅልቁለት በንቀት እያዩ ነው፡፡በዚህ አይነት ሁኔታ ህይወት የዘሩት እነዚህ ህንጣዎችና ፎቆች ለታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ነገር ግን የብዙ ሚሊዮኖች ምስኪን ዜጎች ሆድ በርሃብ ጣርና ስሜት ሲጮህና ሲያጓራ ተንቀጥቅጠው እንዳይፈርሱ እንጂ፡፡
  ከእያንዳንዱ ሀብት ጀርባ ወንጀል አለ የሚባለውን ነገር ከአባባልነት ውጪ ብዙም ሳልረዳው ቆይቼ ብኖርም ዛሬ ዛሬ ግን እጅግ ትክክል ነገር እንደሆነ በተግባር እያየሁትና የተረዳሁት ነው፡፡ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር ወደገንዘብ፣ስለገንዘብ፣በገንዘብ፣ከገንዘብ፣እንደገንዘብ፣አስከገንዘብ በሆነበት አስከፊ ዘመን ውስጥ አባባሉ በግልባጩ ከእያንዳንዱ ወንጀል ጀርባ ሀብት ወይንም ገንዘብ አለ ወደሚለውም ጭምር እያመራ ይመስለኛል፡፡ዛሬ ሙስና የሚል ያማረ ስም የተሰጠውን ዝርፊያና ዱርዬነት በረቀቀና በተቀነባበረ መልክ የሚያከናውኑት ከውጪ ሲታዩ ያማረ ቁመና ያማረ አለባበስ ያላቸው ባማሩና በተሸለሙ ቢሮዎች በሚመች የተሽከርካሪ ወንበር ላይ በግርማ ሞገስ የተኮፈሱ ግለሰቦች ናቸው፡፡ስለዚህም ዛሬ ዱርዬነትና ሌብነት የግድ የተንጨራቆሰ ልብስ ለለበሱና ሰው አየኝ አላየኝ እያሉ እነደ ውሻ ለሚሽቆጠቆጡ የኔ ቢጤዎች ብቻ አይደለም የሚያገለግለው፡፡አጠቃላዩ የብዙ ዘመናት የሰው ልጅ የታሪክና የስልጣኔ ጉዞ በገንዘብ መሪነትና የበላይነት እንዳይጠናቀቅ እጅግ የሚያስፈራ አካሄድ ነው ያለው፡፡ከገንዘብ ይልቅ ቅድሚያ ሰብዓዊነት ይፈቀር ይከበር፡፡አዎ አይካድም እኛ ገንዘብ ለህይወታችን የሚያስፈልገንን ነገር ለማድረግ ያስፈልገናል፡፡ነገር ግን እኛ እንደ ሰው ከገንዘብ የበለጥን ክቡር ፍጥረቶች እንደመሆናችን መጠን ለገንዘብ የራሱ የሆነ ሰይጣናዊ ኡደት በግብአትነት ጭዳ በመሆን ልናስፈልገው አይገባም፡፡ድሮ በአደባባይ በግልፅ ባሪያ ፍንገላ ነበር፡፡
  ዛሬ ያ በግላጭ ሊሆን ባይችልም ግን ቅሉ እጅግ በረቀቀ በተቀነባበረና በተዘዋዋሪ መንገድ መልኩን ቀይሮ በዘመናዊ መልክ ተግባራዊ እየሆነ እንደሆነ ስንቶቻችን አስተውለናል፡፡
  ዛሬ ቆነጃጅት ሴቶቻችን አረብ ሀገር ለግርድና በዘመናዊ ባርነት እየተሸጡ አይደለም እንዴ፡፡
  በላብ በወዝ ጥሮ ግሮ ኑሮን ማሸነፍና ለራስ መኖር የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር ተግባር ባይሆንም ቅሉ አካሄዱ ግን በዚህ አይነት መልክ መሆን አልነበረበትም፡፡የቤት ሰራተኛም እንደ ቤት ሰራተኛ ሰብዓዊ ክብሩና ማንነቱ ሊታወቅለትና ሊጠበቅለት ይገባል እንጂ አገልግሎቱን እንደጨረሰ እቃ ማሸጊያ ፌስታል ወይንም ካርቶን በበረንዳ ከፎቅ ሊወረወር አይገባም ነበር፡፡ዛሬ ሰዎች ዘመናዊ ባርነት ውስጥ እየከተቱን ያሉት እንደ እባብ ተቅለስለሰውና ለስልሰው በሰለጠኑ ዲፕሎማሲያዊ አነጋገሮችና አቀራረቦች “sorry” “ይቅርታ” “የኔ ቆንጆ” ወዘተ በሚሉ ከላይ ሲታዩ ጣፋጭ የሆኑ ቃላቶች ነገር ግን ውስጣቸው በደንብ ሲፈተሸ እጅግ መርዛማ በሆኑ አቀራረቦች ጭምር እየሸወዱን መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡በውጫሌ ውል ላይ ጣሊያን ንጉሳችንን የሸወዳቸውና ወደ ጦርነት የገባነው በቃላት አደራደርና አጠቃቀም አይደለምን፡፡ነፍሴ እጅ እንዳትሰጪ ለኪሴ ነው ያለው ታዋቂው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ፡፡ስለዚህም እጅ ወደላይ ተብለን ለገንዘብና ለስልጣን እጅ ሰጥተን ህሊናችንን ሸጠን ዘላለማዊ የሆነውን የሰውነትና የኢትዮጵያዊነት ክብራችንና ማንነታችንን እንዲሁም እንደ ህዝብና እንደ ሀገር ለዘለቄታው መፃኢ ህይወታችን ህልውናና መሰረት የሆኑ ትልልቅ ወሳኝ ነገሮችን ለከንቱ አላፊና ጠፊ ለሆነ ገንዘብ አሳልፈን እንዳንሰጥ እግዚአብሄር በቸርነቱ ይርዳን፡፡ዘመኑን ዋጁት እንደተባለው ይህ ዘመን የጉድ ዘመን እንደሆነ ልንረዳና በማስተዋል ተጠንቅቀን ህይወታችን እንድንመራ ግድ ይለናል፡፡ልጅ ዳንኤል ይህንን አጅግ ወሳኝና ወቅታዊ የሆነ አጀንዳ በማንሳትህ ላመሰግንህና ላደንቅህ ዘንድ ግድ ይለኛል፡፡ለእውነት ስለእውነት እንደትቆም እግዚአብሄር በቸርነቱ ይጠብቅህ ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 28. በጣም ነው የማደንቅህ እግዚያብሄር ደጉን ዘመን ያምጣልን፡፡

  Eyerusalem

  ReplyDelete
 29. Hi Dani. Betam tiru melikt new yemittsifew. Geta yibarkih. Pls. Lehilinah sitil tsaf. Bealubaltegnoch endatidenakef.

  ReplyDelete
 30. @addisu where is the barinet , you simply create it in your imagination , it is rather about free dome of your slavery from all things that comes from the money(the market) preserving your free dome by not selling it(yourself) for the sake of the market b/c all what you have is hilina...(yourselfe) where do you want to go after selling your self ........enastewil ...let us just understand the contex!!...thank you dani...egiziyabher tibebun yichemirilh

  ReplyDelete
 31. SELAM ADDISABAW WENDEMA Idon't know what's your problem...why are connecet the idea with poletics??why? pls think before you writhing some thing.do u know when you write something bad about d daniel...you are making mad to millions peoples seriusly..pls some thimes let
  be konest with our selves.
  bewnetu from usa

  ReplyDelete
 32. poleticans please leave him alone our brother
  he just writhing his idea.thankyou!

  ReplyDelete
 33. hilinani mini ashetwi belo mateyekemi tru new endene asteyayet gein yeresouse etret ena yeheglobalization yefeterut cheger yemesleghali behonimigeni bezi chiger hulu lerasachini legebanew kali mader yenoribinal.yetesasate menged bengeba enkoni hilinachi benakabet gize tolo wede kedimo melkam sibienachini memelesi yeteshale yimesleghali. mikeniyatum hiwot balance eyehonechi new yemithedew latefanew neger hulu yeminikeflew neger yinorenal latanewm endezw yeheninim lemgenzwb ahunim hilina senori bechanew.

  ReplyDelete
 34. •ረ እኔም ተቃጠልኩ ዳኒ፡ ስለጥቅሙ ብቻ የሚያስብ ሰው አቃጥሎ ቢደፋኝ ነው፡፡ በሚመጣው ሁኔታ ሁሉ እራሱን ቀርፆ ያስተካክላል ምንም ህሊናውን አይከብደውም ሁሉም ቤተሰብ አንድ አይነት ይሆናል ብር ካለህ ብቻ በሰደበ አፋቸው መልሰው ይስማሉ፤ በገላመጠ ትከሻቸው ያለአፍረት በሰው ፊት ያዝላሉ፡፡ “መቻልን ቢሰጠን በዝምታ በኖርኩ” ግን አልቻልኩም •ረ ተቃጠልኩ


  ማሂ

  ReplyDelete
 35. አጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ አይታ ነው ዲ/ን
  ፩። ቃለ ሕይወትን አግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ ቢያሰማ አጅግ በጣም ጥሩ ነው ፣ (ምንም አይነት አመለካከት ቢኖረው ማለ ነው)

  ReplyDelete
 36. ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያስማልን። እግዚአብሔር ደጉን ግዜ ያምጣልን።

  ReplyDelete
 37. አዲስ አበባው
  የምትፈልገውን ሳይሆን የተጻፈውን አንብብ፤ የአማርኛ እጥረት ካለብ ደግሞ በአግባቡ የተረዳን ሰዎች መቼም እንዲ ስትቀባዠር አይተን ዝም አንልሕም፡፡ ዳኒ አምላከ ቅዱሳን አብዝቶ ይባርክ፡፡
  ማሂ

  ReplyDelete
 38. በእዉንት ነዉ የምልህ ዬሀገሬን ሰዉ እንዲህ ልክ ልኩን የሚነገረዉ አጥቶ ነዉ የተደበላለቀዉ
  በምትሰፈዉ ነገረ “”አየን የይቶ ልበ ይፈረደል!”-ማንም እንደንተ ቤዘህ እንገበገቢ ሰአት አለየሁም
  እንደአንተ አየነት ሰወች ብዙ በንሆን ንሮ ሀገር **** ግን ዳኒ በዚ blog የሚመጣበህን ነገረ ሁሉ እንደ weakLikis-እሰከመጨረሻዉ በእወቀቴ ላገለገለህ ዘግጁ ነኝ !! እ/ር ይሰጥልኝ!!!

  ReplyDelete
 39. Moral Degradation

  As Individuals, Society and as a Nation we are all Immoral by omission or by commission.

  Every aspect of our life; be it political, religion, commerce etc.is guided by corrupt values.

  Go to any kindergarten Speaking Amharic is a big sin.

  Do we have role model religious leaders?
  Which of our political leaders enjoy respect from their public? Fear and respect are not one and the same.

  These days as far as it will have value for money, people may not hesitate to sell their Country, Families & their religions. We are all morally Prostitutes.

  Soon or latter the fate of our nation is destined to die like a beast who eat itself

  ReplyDelete