Thursday, September 8, 2011

በምን እንግባባ?

 እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሁሉም የሃይማኖት፣ የፖለቲካ፣ የአስተሳሰብ እና የጎሳ ጎራዎች የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ሲያግባቧቸው የማያቸው ሦስት ነገሮች ነበሩ፡፡ ሰንደቅ ዓላማ፣ ሩጫ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ፡፡ 

ሰንደቅ ዓላማ በብዙ ዘመናት ውስጥ የልዩነቶቻችንን ቋሚዎች አስደግፈን አንድ ጎጆ የሠራንበት ምሶሶ ነበር፡፡ በጎሳ፣ በእምነት እና በሥልጣን የተጣሉ መኳንንት እና መሳፍንት ለሰንደቅ ዓላማ ያላቸው ክብር፣ ፍቅር እና አመለካከት ተመሳሳይ ነበር፡፡ ከተለያዩ ወንዞች የተገኙ ወገኖች በማዕከላዊው መንግሥት አመራር እና አሠራር ባይረኩ፣ ባይስማሙ እና ባይደግፉ እንኳን ለሰንደቅ ዓላማ ያላቸው ክብር እና ፍቅር ግን አይለወጥም ነበር፡፡

ከተወሰኑ ዘመናት ወዲህ ግን እርሱም ሊያግባባን አልቻለም፡፡ በሰንደቅ ዓላማው ላይ በሚቀመጡት የየመንግሥታቱ ዓርማዎች የማይስማሙ ወገኖች አሉ፡፡ መሰቀል ያለበት የትኛው ሰንደቅ ዓላማ ነው? የሚል ሕግ እስከ መውጣት ያደረሰ አለመግባባት አለ፡፡ አንዳንዳንዶች የአንበሳ ምልክት በላዩ ሲያደርጉ ሌሎች የኮከብ ምልክቱን ያደርጋሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሌጣውን ሰንደቅ ዓላማ ያውለበልባሉ፡፡

ከዚህ ባስ ብሎም ይህንኑ ሰንደቅ ዓላማ የ«ሀበሻ» እንጂ የኛ አይደለም የሚሉ ወገኖችም ተከስተዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች ኢትዮጵያውያን ሆነውና ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልደው ኢትዮጵያውያን አይደለንም ይላሉ፡፡ ሰንደቅ ዓላማውንም የነጻነታቸው፣ የአንድነታቸው እና የማንነታቸው መገለጫ አድርገው አይቀበሉትም፡፡ ጂብሲዎች በግዳጅ እነዚህኞቹ ግን በፈቃዳቸው ሀገር አልባ ሆነዋል፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ቦታ «ሀገራችሁ የት ነው?» ተብለው ሲጠየቁ «ምሥራቅ አፍሪካ» ብለው እስከመሙላት ይደርሳሉ፡፡
ከነዚህ መለስ ያሉት ደግሞ ሰንደቅ ዓላማውን የአንድ ወቅት ታሪክ፣ የተወሰኑ ወገኖች ክብር እና አንዳንዴም የጭቆና መገለጫ አድርገው ያዩታል፡፡ በዚህም የተነሣ ለሰንደቅ ዓላማው በሕግ የተሰጠውን ክብር እና ቦታ ለመስጠት እንኳን ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ በአንዳንድ መሥሪያ ቤቶች የተሰቀሉት ሰንደቅ ዓላማዎች እዚያው ተቀዳድደው ነፋስ ካላወረዳቸው በቀር በክብር የሚያወርዳቸው የለም፡፡ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሰንደቅ ዓላማን መስቀል እና ማውረድ «ድሮ የነበረ» ታሪክ ሆኗል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎችም ስለ ሰንደቅ ዓላማ መናገር፣ ሰንደቅ ዓላማን መያዝ እና የሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ያሉበት ነገር መልበስ ከትምክህት እና ነፍጠኛነት ጋር ይያያዛል፡፡

ሌሎች ደግሞ ሰንደቅ ዓላማን ከአንድ ሃይማኖት ጋር ብቻ በማያያዝ የእምነት ዓርማ አድርገው ስለውታል፡፡ አንዳንዶች የኛ ብቻ ነው ሲሉ ሌሎችም የእነዚያ ብቻ ነው ይላሉ፡፡ በርግጥ የእምነት ተቋማት አንዱ እሴት የሀገር ፍቅርን በትውልዱ ላይ ማሥረጽ በመሆኑ ሰንደቅ ዓላማውን ከእምነታቸው መገለጫዎች ጋር መያዛቸው የሚያስመሰግን ነው፡፡ በአሜሪካ በአብዛኞቹ የሀገሬው አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በክብር የተሰቀለ የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ማየት በኛ ሀገር በቤተ ክርስቲያን መስቀል፣ በመስጊድ ጨረቃ የማየት ያህል ነው፡፡

እኛ ሀገር ችግሩ እነ እገሌም የእነርሱ ብቻ፣ እነ እንቶኔም የነ እገሌ ብቻ አድርገው ማየታቸው ነው፡፡ 

እነዚህ ነገሮች ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ተግባቦት ሊያመጣልን እንዳልቻለ ያሳዩናል፡፡

አትሌቶቻችን ኢትዮጵያዊውን መልክ እና መታወቂያቸው የሆነውን አረንጓዴ ማልያ ለብሰው እንደ አቦ ሸማኔ ሲፈተለኩ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ልቡ የማይመታ፣ ደሙ የማይሞቅ፣ ዓይኑ የማይጎለጎል የለም፡፡ በተለይማ አሸንፈው ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ሲያደርጓት የብዙዎች ዓይን በዕንባ ይታጠባል፡፡ በዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች ስማችን በአብዛኛው በክፉ ሲነሣ ይሰነብትና የአትሌቶቻችን እግር አንድ ሰሞን ክፉውን ዜና ወደ በጎ ይለውጠዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ባሉባቸው አብዛኞቹ የዓለም ሀገሮች ስጓዝ፣ መንግሥትን ከልባቸው የሚደግፉም ሆነ ከሆዳቸው የሚቃወሙ ቡድኖች በአትሌቶቻችን ድል እኩል ሲረኩ እና ሲያለቅሱ አይቻለሁ፡፡ ሀገራችን ምሥራቅ አፍሪካ ነው የሚሉ ወገኖቼም ቢሆኑ ያን ጊዜ ነፍሳቸው ትስባቸውና ለደቂቃዎች ኢትዮጵያውያን ይሆናሉ፡፡ 

አሁን አሁን ግን ይህኛው የመግባቢያ ሀብታችን እንደ ዋልያ ሊጠፋ ደርሷል፡፡ አትሌቲክስ ለኢትዮጵያ ቅርስ ለኬንያ ፋሽን እየሆነ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ አትሌቲክሱንም ለማየት የግድ ሁለት ጨጓራ እያስፈለገ ነው፡፡ በመላው ዓለም ያሉትን፣ በየጎራቸው የተከፋፈሉትን፣ በየፖለቲካ እና ጎሳ በኣታቸው የጸኑትን ሁሉ ወደ አንድ መንፈስ አምጥቶ፣ ባይግባቡም አግባብቶ፣ ባይተዋወቁም አስተዋውቆ የሚያስፈነድቃቸው አንድ ሀብት ሊጠፋ ነው፡፡ ምናልባት አትሌቲክሱን የሚመሩት፣ የሚሮጡት፣ የሚያሯ ሩጡት፣ የሚያሠለጥኑት ሰዎች ይህንን ነገር ያሰቡት አይመስለኝም፡፡

አሁን የቀረን አንደ ነገር ነው፡፡ አሠራሩ ቢያረካንም ባያረካንም፣ ሂሳቡ ወገባችንን ቢጫነውም ባይጫነውም፣ ቢፈጥንም ቢዘገይ፣ ዘመናዊም ቢሆን ኋላ ቀር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብዙዎችን ይሁንታ ያገኘ አንዱ አይከናችን ሆኗል፡፡ የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገዛው አውሮፕላን ከሲያትል የቦይንግ ካምፓኒ ግቢ ወደ አዲስ አበባ ከመሰናበቱ በፊት የከተማው ኢትዮጵ ያውያን የመሸኛ ፕሮግራም አዘጋጅተውለት ነበር፡፡ እዚያ ፕሮግራም ላይ የነበሩት አብዛኞቹ በፖለቲካው፣ በጎሳው እና በእምነቱ የማይግባቡ፣ ከመንግሥትም በቀኝ እና በግራ የቆሙ ነበሩ፡፡ ያ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ተሸክሞ «የኢትዮጵያ» የሚለውን የክብር ስም የያዘ አውሮፕላን ነቅነቅ ሲል ግን 

ዘር ቢለያቸው

እምነት ቢለያቸው

ፓርቲ ቢለያቸው እነዚያን ወገኖች

ዕንባ አገናኛቸው፡፡ 

አንዳንድ ጊዜ የአየር መንገዱ ቦርዶች እና አመራሮች፣ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ይህንን ተቋም ሲያንቀሳቅሱ ትርፍ እና ኪሳራው ብቻ ይሆን የሚታያቸው? እላለሁ፡፡ ሕግ ሲያወጡ፣ ዋጋ ሲተምኑ፣ መጽሔት ሲያሳትሙ፣ ማስታወቂያ ሲያስነግሩ፣ ንግግር ሲያደርጉ፣ ሠራተኛ ሲያሠለጥኑ ይህንን ታላቅ እሴት ያስቡት ይሆን? እላለሁ፡፡ 

እስቲ እዚህ ጋ እረፍት እናድርግ፡፡

እረፍት ስናደርግ እና ወደ ልባችን ስንመለስ አንደ ከባድ ዕዳ ላይ እንደርሳለን፡፡ ሰማንያ ሚሊዮን ሕዝብ፣ ከሰማንያ ስምንት በላይ ብሔረሰብ፣ አሥራ አንድ ክልሎች ያሉባት ሀገር የመግባቢያ እጥረት አለባት ማለት ነው፡፡ የሦስት ሺ ዘመን ታሪክ የምትተርክ፣ ዓለምን የመሩ ታላላቅ እምነቶች ያሉባት፣ የራስዋ ፊደል እና ኪነ ሕንፃ ያላት፣ በራስዋ ዜማ የምታዜም እና በራስዋ ብሩሽ የምትስል ሀገር የመግባቢያ ችግር አለባት ማለት ነው፡፡ ነጻነትዋን አስከብራ የኖረች፣ ቅኝ ገዥዎችን ያንበረከከች፣ ማንነቷን ጠብቃ የኖረች ሀገር የመግባቢያ ችግር አለባት ማለት ነው፡፡

ሕገ መንግሥቱን የሚደግፉ እና የሚቃወሙ አሉ፣ ክልል እና አከላለልን የሚደግፉ እና የሚቃወሙ አሉ፣ የመንግሥትን የሥራ ቋንቋ የሚደግፉ እና የሚቃወሙ አሉ፡፡ የመንግሥትን አወቃቀር የሚደግፉ እና የሚቃወሙ አሉ፡፡ ታድያ ሁላችንም ልንደግፈው የምንችል ነገር ምንድን ነው? የሺ ዓመታትን ታሪክ እንናገራለን፡፡ ግን አልተግባባንበትም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? የጋራ ትርጉም የለንም፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት ምንድን ነው? የጋራ ትርጉም የለም፡፡ ታድያ የሚያግባባን ምንድን ነው?

ደበበ ሰይፉ በአንድ ግጥሙ ላይ ከባሌ እስከ መቀሌ፣ ከጋምቤላ እስከ ጅጅጋ አንድ ያደረገን ድህነታችን ነው ብሎ ነበር፡፡ እያንዳንዱ የሀገሪቱ አካባቢ ተርቦ ለሌላው እህል እንዲልክለት የላከው ባዶ ስልቻ ለሁሉም ነበር የተዳረሰው፡፡ አሁን እርሱም አላግባባንም፡፡ ሀብታሙ እና ድሀው እንደ ግሼን ወንዝ ተለያይቷል፡፡ የሀብታሙ መንደር እና የድሀው መንደር ለየብቻ ሆኗል፡፡ አብርሃም ነዌን «ከእናንተ ወደኛ ከእኛም ወደ እናንተ እንዳንመጣ በመካከላችን ትልቅ ገደል አለ» እንዳለው በሀብታሙ እና በድሀው መካከል ትልቅ ገደል ተፈጥሯል፡፡ በድሆች መንደር ውስጥ ሀብታም፣ በሀብታሞቹ መንደር ውስጥም ደሀ ማግኘት ብርቅ ሆኗል፡፡

በጎሳ፣ በርእዮተ ዓለም፣ በእምነት፣ በአመለካከት፣ በዕውቀት፣ በፓርቲ፣ በሀብት፣ በሥልጣን፣ ብንለያይ እንኳን ሊያግባቡን የሚችሉ፣ ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር የምትመሠረትባቸው መግባቢያዎች ያስፈልጉናል፡፡ እነዚህ ከፓርቲ፣ ከመንግሥት፣ ከጎሳ፣ ከእምነት እና ከድንበር በላይ ሆነው የምንቀበላቸው፡፡ ሌሎች ነገሮቻችንን በፈቃዳችን የምናስገዛላቸው እሴቶች ናቸው፡፡

መንግሥታት ሲቀያየሩ፣ መሪዎች ሲገለባበጡ፣ ሕገ መንግሥቶች ሲለዋወጡ፣ ዘመናት በዘመናት ሲተኩ፣ ርእዮተ ዓለም በርእዮተ ዓለም ሲቀየር፣ ሊቀየሩ የማይችሉ፣ ሊቀየሩም የማይገባቸው አንድ የሚያደርጉን እሴቶቻችን ተለይተው መታወቅ አለባቸው፡፡ መታወቅ ብቻም አይደለም ልንግባባቸውም ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ነን እንድንል የሚያደርጉን ነገሮች መንጠር አለባቸው፡፡ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተመሠረተባቸው መሠረተ ሃሳቦች መጉላት አለባቸው፡፡ 

ሊያለያዩን በሚችሉ ነገሮች ላይ በዚህም በዚያም ወገን ሆነን በሚገባ እየሠራን ነው፡፡ ልዩነቶቻችንን አውቀናቸዋል፡፡ ገብተውናል፡፡ ከሰማንያ ስምንት በላይ ቋንቋዎች ያሉን ብሔረሰቦች መሆናችን ገብቶናል፣ አሥራ አንድ ክልል ውስጥ መኖራችንን አውቀናል፣ እስላም እና ክርስቲያን መሆናችንን በደንብ ተረድተናል፣ ደጋፊ እና ተቃዋሚ መሆናችን ተተንትኖልናል፣ ቤተኛ እና ዳያስጶራ መሆናችንን ነግራችሁናል፣ የረሱ እና የተረሱ ክልሎች መኖራቸውን ተገንዝበናል፣ ሊበራል እና አብዮታዊ ዴሞክራሲ መኖራቸውን ሰምተናል፣ የግል እና የመንግሥት ፕሬስን ልዩነት አሥምረናል፡፡ 

ልዩነቶቻችንን በተመለከተ አንብበን፣ ተርጉመን፣ ምሥጢር አደላድለናል፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ በአዲሱ ዓመት አንድ ሊያደርጉን በሚችሉ ነገሮች ላይ እንሥራ፡፡ ልዩነት የማይከበርበት አንድነት፣ አንድነት የማይገለጥበትም ልዩነት ሁለቱም የሞቱ ናቸው፡፡

መኪና በአራት ጎማዎች መሄዱ አይደለም የሚጠቅመው፡፡ አራቱ ጎማዎች ተግባብተው ወደፊት ወይንም ወደ ኋላ መሄድ ከቻሉ ነው እንጂ፡፡ የሚጎዳውም አራት ጎማዎች ስላሉት አይደለም፡፡ አራት ጎማዎችን የሚያግባባቸው አንዳች ነገር ጠፍቶ በአራት አቅጣጫ እንሂድ ካሉ ነው እንጂ፡፡ አዎ ጎማዎቹ አራት ናቸው፣ እያንዳንዳቸውም በየራሳቸው ነው የሚሽከረከሩት፣ ግን የሚያግባባቸው ነገር መኖር አለበት፡፡ ልዩነቶቻቸውን ብቻ ይዘው በአራቱ አቅጣጫ እንሂድ ካሉ ወይ መኪናው ይቆማል፣ ያለ በለዚያም መኪናው ይወድቃል፡፡ አራት ጎማ አያስፈልግም፣ አንድ ጎማ መሆን አለባችሁ ተብለው ተጨፍልቀው አንድ ትልቅ ጎማ ቢሆኑ ደግሞ መኪናው መሄዱ ቀርቶ ላንቲካ ይሆናል፡፡ አራቱም ይኑሩ፣ አራቱም ይሽከርከሩ፣ ግን ወደ አንድ አቅጣጫ ይሽከርከሩ፡፡

የእምነት ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የፖለቲካ ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ተሰሚነት ያላቸው አካላት፣ የጎሳ መሪዎች ከአዲሱ ዘመን ጀምረው የመግባቢያ እሴቶቻችን ላይ መሥራት አለባቸው፡፡ የለበለዚያ ግን በምሥራቅ አፍሪካ ከመገኘታችን በቀር አንድ የሚያደርገን ነገር ሊጠፋ ነው ማለት ነው፡፡

አትላንታ፣ ጆርጂያ 


©ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

76 comments:

 1. Dn.Danial selam nehe wey qale hiwot yasemalen. Betam des yemil sehuf new "neber zengurgurnetu..." yemilew ababal ahun ahuyn zenbelo yemeslegnal bemayageban eyegeban bemaymeleketen telq eyalen yethiopiawinet melkachenen derash abatun atefanew. Ena gen yemigermegn beseletenew alem yemenenor ethiopianoch nen andada sasbew yenesanet tergumun yegeban aymeslegenm belyntoch lay tengagro wed and metat sichal tekrakro meleyayet honal yegna mecheresh becha begna besoal Amlak bechernetu and yadrgen.
  HG from GA

  ReplyDelete
 2. የህዝብ ነጻነቱ ክብሩ ሲጠበቅ ነው ሰንደቅ ዓላማዎች ትርጉም የሚያገኙት። ክብርና ነጻነት ደግሞ ከአሁን ይልቅ በቀድሞዎቹ መንግስታት ነበር። ለዚህ ነው እስከ ንጉሱ ዘመን የነበረው ሰንደቅ ዓላማ ልዩ ክብር እና የጋራ ተቀባይነት የነበረው። በደርግ ዘመን ብዙ ግፎች የተሰሩ ቢሆንም ቢያንስ ግን የሀገራዊ ስሜት ግን በሁሉም ዘንድ ስለነበረ በዚያ ዘመንም የነበረው ሠንደቅ ዓላማ ተቀባይነቱ የተሻለ ነበር። አሁን ግን ከግፍም በላይ ሆን ተብሎ በዘር እንድንከፋፈል እና እንድንበላላ ስለተዘጋጀን፤ የአሁኑ ሰንደቅ ዓላማ መንግስት ከጨመረበት ምልክት ጋር ህዝቡ የሚያየው የግፍ ምልክት አድርጎ ነው። ስለዚህ ስፍር ቁጥር በሌለው በደል ውስጥ አሁን ያለው ባለዓርማ ሠንደቅ ዓላማ ያንኑ አምባገነነ ያስታውሳን ካልሆነ በስተቀር አንድ ሊያደገን አይችልም። ዋናው ነገር ግን ይህ መንግስት ምልክት የጨመረውም የነበረውን የጋራ ስሜት ለማደብዘዝ መሆኑ ሀቅ ነው፤ እውን አንተ ይህ ጠፍቶህ ነው?.?ወይ ጊዜ!!!

  ReplyDelete
 3. <> Dani Igziabher yistilin dinq iyita new ketetegebere meriwochachin yemisemu kehone

  ReplyDelete
 4. "ልዩነት የማይከበርበት አንድነት፣ አንድነት የማይገለጥበትም ልዩነት ሁለቱም የሞቱ ናቸው፡፡"
  ዳኒ የመጨረሻ ተመችቶኛል
  መልካም አዲስ አመት

  ReplyDelete
 5. እውነተኝነት አንድ ያደርጋል።አንተን ጨምሮ እውነተኛ ጠፋ። ባለፈው በኢቲቪ በሰጠኸው ኢንተርቪው ላይ ህዝቡ በፈቃዱ ገንዘብ እንዳዋጣ ተናገርክ ፤ ሰማንያ ሚሊዮን ሃሰተኝነትህን በቋሚነት የመዘገበበት አጋጣሚ ነበር።ህዝቡ ቤተ ክርስቲያን ለማሰራት እንኳ በፈቃዱ የሚያዋጣው ሳንቲም እን ጥቂት ብሮች በሆነበት ሀገር ፤ ለሚጠላው መንግስት ለማያምነው መንግስት ደመወዙን በፈቃድ ሰጠ? ፈቃደኝነቱን የሰጠው ነው ወይስ አንተ የምታውቀው?አንተ አስመሳይ ስለሆንክ የምትለው ሁሉ ተቀባይነት የለውም። መንግስታትበተለዋወጡ ቁጥር ሰንደቃ ዓላማ መለዋወጥ እንደሌለበት በደንብ ታውቃለህ። ታዲያ ለምን የቃድሞውን ብዙ ህዝብ የሚቀበለውን አላወጣኸውም? ምክንያቱም እንዳልጋጭ እንዳልጣላ ብለህ ሁለት ቤት ለመብላት አይደለ? አንተ ዘዴኛ ሆነህ ጥላ ጥላውን ትሔዳለህ፤ እዚህ ደግሞ እውነተኛ መስለህ አስታራቂ አንድ አድራጊ ሆነህ ትቀርባለህ። ይህን ጽሑፍ ያወጣኸው የወያኔን ሰንደቅ ዓላማ ልታለማምደን እና ከእነሱ ቡራኬን ለማግኘት ካልሆነ በስተቀር ሌላ መልዕክት የለውም።ባለጊዜ ነህ፤እውነት ግን ባንተ ዘንድ የለችም።ሁላችሁም አንድ ቀን ዕዳችሁን ትከፍላላችሁ።

  ReplyDelete
 6. Wonderful. God bless you Daniel.You wrote what there is in my mind. I always argue with people regarding being an Ethiopian. Some polititians believe that Ethiopia has only 100 years long history and many believe it has more than 3000 years. How can thesse different groups be an Ethiopians? There are a lot of major things which make differences in being an Ethiopian. This problem hasn't been for long time. Difference in ideas of minor things is ok,but differences which affect being a citizen is dangerous.There is no development in the country on a 100 and 3000 years long history differences.

  ReplyDelete
 7. Oh dani le hulum meriwochachin be addisu amet addis libona yistachew

  ReplyDelete
 8. መንግሥትን ከልባቸው የሚደግፉም ሆነ ከሆዳቸው የሚቃወሙ::የሚደግፉ ከልባቸው የሚቃወሙ ከሆዳቸው I am not happy with your expression.

  ReplyDelete
 9. Bakih tewen wedajie. Dirom miyawatah poletica new. Haymanot lante wedepoletika meshgageriana yeenjera mawcha new. Ay enjera kifu! kesemayawi poletika wede meretawi poletika tashegagiralech. Bandiram poletikam alafi tefi nachew. Yemayalifina yemaytefaw yetewkew Kirstos new. Begize bitineka yshalihal. Yebedeluhinna yebedelikachewn ykir bitil yawatahal. Egizeryewko libihnina kulalitihin mimeremir enji yesheftina yeadirbay tebabari adelem.

  ReplyDelete
 10. መንግሥታት ሲቀያየሩ፣ መሪዎች ሲገለባበጡ፣ ሕገ መንግሥቶች ሲለዋወጡ፣ ዘመናት በዘመናት ሲተኩ፣ ርእዮተ ዓለም በርእዮተ ዓለም ሲቀየር፣ ሊቀየሩ የማይችሉ፣ ሊቀየሩም የማይገባቸው አንድ የሚያደርጉን እሴቶቻችን ተለይተው መታወቅ አለባቸው፡፡ መታወቅ ብቻም አይደለም ልንግባባቸውም ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ነን እንድንል የሚያደርጉን ነገሮች መንጠር አለባቸው፡፡ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተመሠረተባቸው መሠረተ ሃሳቦች መጉላት አለባቸው፡፡

  ReplyDelete
 11. Dear Daniel,

  As usual you shows us a very nice and wonderful insight. God Bless you, I share your idea unity in diversity is needed. Even husband and wife have their own natural and social differences and yet they are living together by bringing their difference as a color to build up their unity. Thus, we Ethiopians should have common point that we should agree.

  ReplyDelete
 12. ዳኒ ትክክለኛው የኢትዮጵያ ባንድራ መካከል ላይ ያለውን አይጨምርም ::

  ReplyDelete
 13. ሊያለያዩን በሚችሉ ነገሮች ላይ በዚህም በዚያም ወገን ሆነን በሚገባ እየሠራን ነው፡፡እስኪ አሁን ደግሞ በአዲሱ ዓመት አንድ ሊያደርጉን በሚችሉ ነገሮች ላይ እንሥራ

  ReplyDelete
 14. i believe that truth can make peoples united i agree with the person commented above. whatever. There is truth behind any ideology and interest.

  ReplyDelete
 15. Betame Arife Tshefe newe.

  ReplyDelete
 16. ርብቃ ከጀርመንSeptember 9, 2011 at 11:46 AM

  ዳኒ በመጀመሪያ እንኩዋን አደረሰህ! ከዚህበመቀጠል ግን ስለጻፍከው ነገር የምለው ነገር ቢኖር ሰንደቃላማችንን በተመለከተ መንግስት በግዴታ የጫነብብን ልዩነት ለማድመቅ እሽብለን ስንቀበልና ባንድ ሀገራችን ላይ የተለያየ አይነይ ባንዲራ ስንሰቅልነው ነገሩ የተበላሸው ያኔ ነበር ስለባንዴራው ክብርና ስለአንድነታችን ስንል አይሆንም ብለን ወደላይም(ወደፈጣሪ) ወደታችም (ወደመንግስት) መጮህ የነበረብን አሁን ግን ይሄመንግስት በስልጣን ለይ እስካለድረስ ወደነበረበት ይመለስ ብሎ መጮህ ጉንጭ አልፋ መሆን ነው ባይሆን ያለውንም ሰንደቅ አላማ በክብር መስቀልና ሲቀደድ እንዲቀየር ማድረጉ መልካም ይመስለኛል በተረፈግን ድንግል ማርያም አስራት ሀገርሽን አስቢያት ማለት ነው! ዳኒ ካላይ አስተያየት እንደሰጠህ ሰውየ በ E, TV, ላይ ህዝቡ ገንዘቡን በፈቃደኝነት ነው የሚሰጠው ብለህ ተናግረህ ከሆነ አዝናለሁኝ ሁላችንም የምናውቀውን እውነት በተባብዕርህ አትሸፍጥበት የንስር አይኖችህ ማስተዋል እንዳይጎላቸው ተጠንቀቅ!

  ReplyDelete
 17. ወዳጄ ልቤ ዳንኤል ሆይ ይህ ጽሑፍ መንግስታችን የሰንደቅ አላማችንን ቀን ሊያከብር ጠብ እርግፍ በሚልበት ዋዜማ መቅረቡ ልዩ ያደርገዋል፣ በተረፈ እንደኔ እንደኔ አገራዊ የአንድነት ስሜት የጠፋው ባንዲራው ባለምልክት በመሆኑ፣ አትሌቶች ሮጠው ባለማሸነፋቸው ብቻ አይመስለኝም፡፡ የአንድ ጽሑፍህ ርዕስ አድርገህ ያወጣኸውን አባባል ልጠቀምና አንድ የሆነ ነገር ሳይኖር አይቀርም፡፡ እርግማን ይሁን መተት ይሁን ቡዳ ይሁን በኮሚቴ መጠናት በስነ አእምሮ ጠበብት መመርመር ያለበት የሆነ ነገር አለ፡፡ አንድ አደረገን፣ አፋቀረን፣ አዋደደን፣ አስተሳሰረን ብለን ቀልባችንን ያሳረፍንበት ነገር አይናችን ስር እየፈረሰ መልሶ ሲያናክሰን ይገኛል፡፡ ልዩነቶቻችን ከመብዛታቸው የተነሳ ሁለት ሰው በአንድ ሃሳብ ተስማምቶ የሚቆምበት ነገር ጠፍቷል፡፡ በዚህ አያያዛችን ከቀጠልን ደግሞ በቀጣይ ሰማንያ ሚሊዮን ፓርቲ በመመስረት፣ ሰማኒያ ሚሊዮን ሃይማኖት በመማቋቋም፣ ሰማኒያ ሚሊዮን ጎሳ በመፍጠርና ሰማኒያ ሚሊዮን ክልል በማዋቀር በዓለም የሚስተካከለን ልናጣ እንችላለን፡፡ ሳስበው ተግቶ መጸለይ ብቻ ነው መፍትሔው፡፡

  ReplyDelete
 18. አካሄድህን አልወደድኩትም

  ReplyDelete
 19. ዳኒ የጠቀስኸው የደበበ ሰይፉ (1967) ተራኪ ግጥም ላይ ስለ አንድነት ሲያወራ እነዚህን ስንኞች ማሰቡ እኔን ያስደስተኛል- ፋንታሲ ቢሆንም (ቢመስልም) ቅሉ፡፡
  “እኔና ወንድሞቼ” አለ በለዘብታ
  ለራሱ እንዲያወራ የራሱን ስሞታ፤
  “እኔና ወንድሞቼ ሁላችን… ሁላችን
  ከባዶ አቁማዳ ነው የሚዛቅ ፍቅራችን
  ይህ ነው አንድነታችን
  ይህ ነው ባህላች
  ዘመን ማዛጋቱ በያንደበታችን”
  በደበበ ግጥም ውስጥ ዘመን በእኔና በወንድሞቼ ውስጥ የሚያዛጋው አንድ አቁማዳ እህል ጠፍቶ ነው- ረኀብ፡፡ በእኛ አንደበት ዘመን የሚያዛጋው ደግሞ …

  ReplyDelete
 20. ANDE ADEREGANE GATA HOY ANDE ADERGAN
  SALAMEHEN FEKEREHENEM ADELANE
  ya2004 tsalotachen yeha behones?
  Daniel baewenate anegaten arasekawe.
  bakage yakomeh kanabatasabeh....

  ReplyDelete
 21. Black people in the US hate the confederate flag because in their mind it is a sign of slavery. White southerners don't see it that way. They think flying the confederate flag as just an expression of appreciation of your heritage. The mainstream thinking in America is that is justified for black people to hate that flag. It is actually considered offensive to fly the flag.

  A similar dynamic may be happening for people who hate the Ethiopian flag. Even though most Ethiopian consider it as a sign of expression identity and appreciation their heritage, there might be some who look at as sign oppression. And they might justified to have such feelings. So we have to be really careful when writing things like this. It is very difficult to understand the feeling of minorities if your are from a majority.

  ReplyDelete
 22. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል
  አሁንስ የሰናኦር ግንብ ሰርዎች ሆን መሰለኝ  አሁን የሚንግባባበት ነገር አደባልቆ መጀመርያ ሲንግባባበት የነበርነው ነገር ያምጣልን ከማለት በቀር ምንም ማለት አልቻልኩም የሚልም አይመስለኝም አልችልምምወይኔ በተለይ የሰ ን ደ ቅ ዓለማችንና የአ……ት…..ሌቶቻችን……………..

  ReplyDelete
 23. እውን አንተ ይህ ጠፍቶህ ነው?.?
  I like this comment
  የህዝብ ነጻነቱ ክብሩ ሲጠበቅ ነው ሰንደቅ ዓላማዎች ትርጉም የሚያገኙት። ክብርና ነጻነት ደግሞ ከአሁን ይልቅ በቀድሞዎቹ መንግስታት ነበር። ለዚህ ነው እስከ ንጉሱ ዘመን የነበረው ሰንደቅ ዓላማ ልዩ ክብር እና የጋራ ተቀባይነት የነበረው። በደርግ ዘመን ብዙ ግፎች የተሰሩ ቢሆንም ቢያንስ ግን የሀገራዊ ስሜት ግን በሁሉም ዘንድ ስለነበረ በዚያ ዘመንም የነበረው ሠንደቅ ዓላማ ተቀባይነቱ የተሻለ ነበር። አሁን ግን ከግፍም በላይ ሆን ተብሎ በዘር እንድንከፋፈል እና እንድንበላላ ስለተዘጋጀን፤ የአሁኑ ሰንደቅ ዓላማ መንግስት ከጨመረበት ምልክት ጋር ህዝቡ የሚያየው የግፍ ምልክት አድርጎ ነው። ስለዚህ ስፍር ቁጥር በሌለው በደል ውስጥ አሁን ያለው ባለዓርማ ሠንደቅ ዓላማ ያንኑ አምባገነነ ያስታውሳን ካልሆነ በስተቀር አንድ ሊያደገን አይችልም። ዋናው ነገር ግን ይህ መንግስት ምልክት የጨመረውም የነበረውን የጋራ ስሜት ለማደብዘዝ መሆኑ ሀቅ ነው፤ እውን አንተ ይህ ጠፍቶህ ነው?.?ወይ ጊዜ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. First, I extend my greeting to our good teacher Dn. Daniel. I read this comment and I wanted to reply. People are above the flag. The additional symbol on the flag shouldn't bother us because we give a strength to the flag, the flag doesn't give strength to us. If we see a hero holding the flag, we give respect to the hero because it's his/her deeds that brought the flag up. It's every one of us who brings unity, love, and tolerance. We should care for people first not for the flag.

   Delete
 24. ወንድም ዳንኤል የምታቀርባቸው ጽሁፎች ሁሉ አስደሳች በመሆናቸው ሁሉም አድናቆቱን በመቸር ላይ ብቻ ያተኩራል። እኔ ደግሞ ፣ እንደአድናቆቴ ሁሉ ቅር የሚያሰኙንም ልግለጽልህ። አንደኛ ፣ ፍሬከርስኪ የሆነ የፖለቲካ አቋም በመያዝ ኢትዮጵያዊነትን ለሚያናንቁ ሁሉ የአንተ ብዕር ድምጻቸው ብቻ ሳይሆን መሆን ያለበት ፣ የተሳሳተው አመለካከታቸውንም መተቸት የሞራል ግዴታ አለብህ።
  ሁለተኛ ፦ በዚህ መጥጥፍህ ክፉኛ ያስደነገጠኝ ግን “የመንግስት የልብ ደጋፊ እና የሆድ ተቃዋሚ” የሚለው አገላለጽህ ፣ ዛሬን ብታልፍበትም ነገ የሚያስጠይቅህ ስህተት ይመስለኛል። በአሁኑ ሰዓት ያለውን ስርዓት የሚደግፍ “ልባዊ” የሚቃወም ግን “ሆዱ የጎደለበት” አድርገህ የምታምን ከሆነ ፣ አንተ ሌላውን “በታሪክ የተኛ” እንደምትለው ፣ አንተም ‘በወያኔ ፕሮፖጋንዳ ላይ የተኛህ’ ያስመስልብሃል። እንዴውም እስከዛሬ በአንተ እና “በነበውቀቱ ስዩም ፣ ቴዲ አፍሮ ፣ ጌትነት እንየው “… ላይ እስከዛሬ ሳምንበት የነበረው ዋናው እና አንዱን ዓመለካከቴን እዚሁ ልግለጽልህ። ለኔ እናንተ የዚህ ትውልድ ፈርቀዳጅ እና ነገም ይህን ትውልድ በበጎ የምታስጠሩ አድርጌ ነበር የማምንባችሁ። ነገር ግን ፣ በውቀቱ በስነጽሁፍ ያለውን ጸጋ በማያውቀው ሃይማኖታዊ ሂደት ውስጥ ሲያጨማልቀው ጸጋው ተገፈፈ። አንተ ደግሞ በሃይማኖትና በሞራል ያለህን ጸጋ ፣ ለአለው ስርአት እና ደጋፊዎቹ ያልተፈለገ ክብር በመደረብ እራስህን ትዝብት ውስጥ እየጣልህ ነው። እነ ጋዳፊ እና ሙባረክ ላይ ያልኸው ሁሉ መለስ ላይ ላለመድረሱ ምንም የምታውቀው አይኖርም። የሚቃወሙ ሰዎች ሆዳቸው የጎደለባቸው ሳይሆኑ ፣ ሆዳቸው ሞልቶ መንፈሳቸው ፍትህ የተራበ ለመሆኑ እኔ ምስክር ነኝ። ብቸኛ ርሃቤ እኔ በፈረንጅ አገር ያለኝ ነጻነት ያገሬ ህዝብ በአገሩ እንዲኖረው ብቻ ነው።

  በስጋየ ምንም ያልጎደለብኝ ፣ በህዝቤ የሰቆቃ አገዛዝ ግን የምቃጠለው “በለው” ነኝ ከካናዳ።

  ReplyDelete
 25. "አህያውን ፈርተው ዳውላውን" እንዲሉ ትችትህ ችግሩን ወደፈጠሩት አለማመላከቱ ገርሞኛል! አሁን አንተ የኢትዮጵያ ባንዲራ ህወሀት በምን አይነት ሁኔታ እንደለወጠው ሳታውቅ ቀርተህ ነው?! ህወሀት ባመጣው ""ብሄር ብሄረሰብ"" የፖለቲካ ግርግር ብዙ ኢትዮጵያውያን ጎሳን የሚያመላክት ባንዲራ በጎሳቸው በነብስ ወከፍ እንዲኖራቸው መደረጉ ሳያንሳቸው የኢትዮጵያን ባንዲራ ለመለወጥ ጥራዝ ...ነጠቅ በሆነ እና ጥላቻ በተሞላበት ሁኔታ ያደረጉት ስብሰባ ለታሪክ ምስክርነት አለ::

  መጀመሪያ ባንዲራ መሰረታዊ ነገር ነው:: የቅንጦት ነገር አይደለም:: ህወሀቶች

  እንደሚያስቡትም ጨርቅ ብቻ አይደለም:: እንደቀላል ነገር "በዚህ እንኳን እንስማማ' የሚባል አይደለም:: እኔ እንዳየሁት ኢትዮጵያውያን ከፋሺስቶች ጋር ሲፋለሙ ይዘውት የነበረው ባንዲራ ልሙጥ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው::

  http://www.diretube.com/sami-abdella-presents/interview-with-diyakon-daniel-kibret-part-1-video_db1ba2d76.html

  ከላይ ባስቀመጥኩት ሊንክ ላይ ስለ "መንጸባረቅ' ያልከው ነገር ስላለ አንተን ራስህን ኮት ላድርግህ:: በጽሁፍህ ውስጥ እምነትህ ይንጸባረቃል ብሎ ሲጠይቅህ እምነትህ በተወሰነ መልኩ መንጸባረቁ አይቀርም ብለህ ነበር:: ለኔ ግን ሌላም የሚንጸባረቅ ነገር አለ:: ከረዢም ጊዜ ወዲህ ብልጣብልጥ በሆነ መንገድ የህወሀትን ፖለቲካ ልታንጸባርቅ እንደምትሞክር አስተውያለሁ:: ፖለቲካቸውን መደገፍህን በራሱ እንደችግር አላየውም:: እንደችግር የማየው በተድበሰበሰ መንገድ ማህበራዊ ጉዳይን ተገን በማድረግ ልታደናግር የምትሞክረውን ነገር ነው:: በተደጋጋሚ አስተውየዋለሁ:: በዚህ በላይኛው ክሊፕ ራሱ ደርሰህ ስለ ግድብ የምትናገረው ሚዛኑን የሳተ ፕሮፓጋንዳ አይሉት ነገር የሚገርም ነው:: ቅኔ ዘረፋ ከሆነ ኦዲዮንሱን ልብ ያልክ አልመሰለኝም:: ግን እንደዛ እንዳልሆነ ያስታውቃል:: የዘነጋህ የመሰለኝ ነገር የኢትዮጵያ ሕዝብ ማክበርም ያውቃል ; ሰው ክብሩን ሲረሳ ደሞ በተለይ በማንነት ጉዳይ ላይ ክብር መንሳትንም ያውቃል:: ከልደቱ መማር ያለብህ ነገር ያለ ይመስለኛል::

  ፕሮፌሰር መስፍን "ሥልጣን ባህል እና አገዛዝ በሚለው' መጽሀፋቸው መቅድም ላይ ""...የእግዚያብሄርንም ሆነ የሰውን ሕጎች ረግጠው በሕገ አራዊት ማህበረሰቡን የሚያምሱት ሁሉ የአንድ ሕዝብ የታሪኩ ጉድፎች [ በጨዋነት ይዘውት ነው እንጂ ከጉድፍም በላይ ናቸው] ናቸው : ለሆዱ የገበረ ጸሀፊና ባህል እነዚህን ጉድፎች ቀባብቶ ያሳምርና በጣም ልዮና የሚያምር መልክ እየሰጠ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፋቸዋል:: ጉድፍ ወደ ወርቅነት ይለወጣል:: ቅሌት ክብር ይሆናል:: ውድቀት ትንሳኤ ተብሎ ይዘመርለታል: ሆድንና ባህልን በተሽለመለመ ፈረስ ላይ አስቀምጠው ያስጋልብታል::"" ብለዋል:: እየሆነ ያለው ነገር እርሳቸው በማይጎብጥ ስብዕናቸው የተናገሩት ነገር ነው::

  ግልጽ ሁንህ የሆንከውን ሁን!

  Dimetros Birku

  ReplyDelete
 26. Kale hiwot yasemalin, Dn Daniel
  Just be careful. I don't like you to involve in politics. Atlanta

  ReplyDelete
 27. ለምን እንደዚህ ያለ ከፋፋይ ጽሁፍ ጽፈህ እንድንስማማ እንደምትጠብቅ አልገባኝም። ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ከአስተማሪነት ወደ አደናጋሪነት መቀየርህ ይታየኛል። ዋ!በዝና ዘነዘና ራስህን እንዳትፈጠፍጥ ተጠንቀቅ።

  ReplyDelete
 28. እኔ የምለዉ ሰንደቅ ዓላማ ሃይማኖታዊ ምልክታችን መሆኑ ቀረ እንዴ!? አንተ የሃይማኖት መምህር ሆነህ ሳለህ የኖህ ቀስተ ደመና ምልክትነቱ፡ የአገራችን እና ንግስታችን ወላዲተ አምላክ ምሳሌ መሆኑ እንዴት ይጠፋሃል? ወይስ እዉነትም ወያኔ ሆንክ?

  ReplyDelete
 29. መልካም ብለሃል ... ግና እስኪ ልጠይቅህ ... በሁሉም የሃይማኖት፣ የፖለቲካ፣ የአስተሳሰብ እና የጎሳ ጎራዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚግባቡባቸው ጉዳዮች ቁጥር አነስተኛ የመሆን ምክንያቱ ምንድን ነው ትላለህ? .... መቸም እንደ አንድ አንባቢህ “ቀሽም ስለሆኑ ነው” እንደማትል እምነቴ ነው ... እና ለምንድን ነው? ... ነው አንተም እንደ አንዳንድ ድካሞች ሀበሻ እና የሀበሻ የሆነ ሁሉ ከሌላው የሰው ዘር አንሶ ይታይሃል? ... እንዲያ ካልሆነ ኢትዮጵያዊ የሚገባባበት ለምን ያጣ ይመስልሃል? ... ለምን? ... እህ ያ እኮ ነው ጥሩ ጸሃፊ የሚያሰኘው ... ምንን ጠቅሶ ... ለምንን ተንትኖ ... እንዴትን ሲያመለክቱ ነው እኮ ሸጋው ነገር ... ያለበለዚያ እኮ አጉል ወዲያ ወዲህ ብቻ ይሆናል ... እንዲያም ሲል ያስተዛዝባል እኮ ... “በነገራችን ላይ መኪና በአራት ጎማዎች መሄዱ አይደለም የሚጠቅመው፡፡ አራቱ ጎማዎች ተግባብተው ወደፊት ወይንም ወደ ኋላ መሄድ ከቻሉ ነው እንጂ፡፡ የሚጎዳውም አራት ጎማዎች ስላሉት አይደለም፡፡ አራት ጎማዎችን የሚያግባባቸው አንዳች ነገር ጠፍቶ በአራት አቅጣጫ እንሂድ ካሉ ነው እንጂ፡፡ አዎ ጎማዎቹ አራት ናቸው፣ እያንዳንዳቸውም በየራሳቸው ነው የሚሽከረከሩት፣ ግን የሚያግባባቸው ነገር መኖር አለበት፡፡ ልዩነቶቻቸውን ብቻ ይዘው በአራቱ አቅጣጫ እንሂድ ካሉ ወይ መኪናው ይቆማል፣ ያለ በለዚያም መኪናው ይወድቃል፡፡ አራት ጎማ አያስፈልግም፣ አንድ ጎማ መሆን አለባችሁ ተብለው ተጨፍልቀው አንድ ትልቅ ጎማ ቢሆኑ ደግሞ መኪናው መሄዱ ቀርቶ ላንቲካ ይሆናል፡፡ አራቱም ይኑሩ፣ አራቱም ይሽከርከሩ፣ ግን ወደ አንድ አቅጣጫ ይሽከርከሩ፡፡” ያልከው ነገር ቆንጆና ገላጭ ነው! ሌላ ሌላውን ግን አንተ ታውቃለህ ... መልካም በዓል

  ReplyDelete
 30. 'አለማወቁን የማያውቅ ተኝቶአልና ቀስቅሰው' ነው ያሉት። የአብዛኞቻችን አስተያየት በጣም ያሳዝናል። ማንም ይበለው በእውነት አገራችንን የምንወድ ቢሆን ይህን ጽሑፍ ባልተቃወምን ነበር። በቅንነት ለሚያየው የዚህ ጽሑፍ መልእክት ይህ ነው።

  '....እስኪ አሁን ደግሞ በአዲሱ ዓመት አንድ ሊያደርጉን በሚችሉ ነገሮች ላይ እንሥራ፡፡
  ዲ/ን ዳንኤል ለእውነት ከቆምክ ጽና። እግዚአብሔር ያግዝህ።

  ReplyDelete
 31. ዳንኤል ፤ ዛሬም እንደ ባለፈው አደንቅሃለሁ

  ችግሩ ወዲህ ነው ።
  የኢትዮጵያችንን ታሪክ በጥልቀት ስንመለከተው ፤ እንደ ሌላው ዓለም ሁሉ ፣ ብዙ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች አሉበት ።

  ጠንካራዎቹ
  . አገሪቱን ከውጭ ቅኝ ገዢ ተከላክሎና አሸንፎ ማቆየት (ባለ ወኔ ጀግና)
  . የራሱ ፊደል ያለው ቋንቋ ባለቤት መሆን
  . እንግዳ ተቀባይና አክባሪነት
  . ባለ ዕድሜ ጠገብ ቅርሶች ባለቤተ መሆን መቻል ወዘተ….

  ደካማዎቹ
  . ከጥንት ጀምሮ ያለው የመንግስት አወቃቀር ሁሉንም እኩል ያሳተፈ አለመሆኑ
  . ባህሉ፣ ሃይማኖቱ፣ ቋንቋው ስልጣኑ እና የመሳሰሉት መሰረታዊ የጋራ እሴቶች ወደ ሰሜኑ ያጋደሉ ሆነው መኖራቸው ።
  . ከአፄ ቴድሮስ በፊት የነበረው የራስ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ በአንድ ክፍል ብቻ መጠቅለሉ
  . አንዱ ጎሳ ሌላውን ጎሳ፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣.. በንቀት፣ በጥርጣሬ፣ በበታችነት የመመልከት ችግር
  . ራሳችንን ባለቤትና ታማኝ፤ ሌላውን ግን ባይተዋርና እንደ ሁለተኛ ዜጋ የማሰብ አባዜ
  . ገዢዎቻችንም እነዚህን ልዩነቶች እያስፋፉና አዳዲስ እየጨማመሩ እንድንከፋፈል ማድረጋቸው

  በጣም ብዙ ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል ። ግን እነዚህን በድንብ እናጣጥማቸው ። በአጠቃላይ ዋናው ችግራችን ፤ የራሳችንን ድክመትና ስህተት እያወቅነው ለመቀበል አለመፈለጋችንና “ለምን ተነካሁ” እያልን አገር ይያዝ ማለታችን ።

  ወደ አንድነት ለመምጣት
  . በመጀመሪያ ደረጃ, መንግስት ፈቃደኛ መሆን አለበት ። አለበለዚያ መንግዶችን ሁሉ እየቀደመ ይዘጋጋቸዋል ።
  . ወደ ውስጣችን የመመልከትና የድሮ ዘመዶቻችን በሌሎች ላይ ፈጸሙት ግፍ ካለ ፣ የችግሩ እኩል ተካፋይ ሆነን መገኘትና ስህተቱን መኮነን ።
  . መቻቻል ፣ ይቅር ማለት ፣ መተው ፣ የደከመውን በድካሙ ሳይፈርዱ ወደ ጥሩ ነገር እንዲመጣ ማገዝ ።
  . ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚጠላንንም ቢሆን በቤተ ሰብነት ዓይን ማየት ፡ ሌሎች ወደ እኛ እንዲመጡ ሳንጠብቅ ገፍተን መሄድና ልዩነቱን የመስበር አቅምን ማዳበር ።
  . በሌሎች መፍረድን ቢቻል ማቆም ካልቻልንም ትንሽ በትንሽ እያልን መቀነስና ስለ ሌላው መልካም የሆኑ ነገሮችን ማውራት ።

  እሰቲ ለዛሬ ይብቀኝ

  ReplyDelete
 32. ግቢ በነበርኩበት ጊዜ የአንደኛው ሃይማኖት ተከታዮች የዩኒቨርስቲውን አስተዳደር የዚያኛው ሃይማኖት ተከታዮች ምግብ ከመመገባቸው በፊት የሚያሳዩትን ምልክት ማየት ስለማንፈልግ ዩኒቨርስቲው የሆነ መፍትሄ ያምጣ ብለው ጠየቁ።ከዚያም የካፌው አንዱ ኮርነር በችፕዉድ ተከልሎ እንዳናያቸው እንዳያዩን ተደረገ ያን ቀን የተማሪዎች ዲን ፕሬዘዳንት በምሳ ሰዓት መጥተው ስራውን ጎበኙ እንዲያውም ያሉትን አልሰማሁም እንጂ “ይህ የትግላችሁ ውጤት ነው ለወደፊም በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ታሪክ ውስጥ ሲወሳ ይኖራል” ምናምን ያሏቸው ይመስለኛል።ታዲይ ያኔ ጓደኛችን እነንትና አይናቸውን ከሚጨፍኑብን ለምን አንደኛውን ጥግ አናስከልል ብሎን ነበር ግን ረስተነው ይሁን ፈርተን ተውነው እንጂ።
  ያኔ የቋጠርኳትን ስንኝ ሃገሬ ብያት ነበር
  ሀዘኔ በዛ ስላንቺ
  መቅንሽ ሲፈስ ስትደክም ስትረች
  አንቺ እናቴ እንዲያው በከንቱ ደከምሽ
  ወጣሽ ወረድሽ ላይሳካ ላይሰምርልሽ
  እደግልኝ ልጄ ብለሽ ደግፈሽው
  በሌለ አቅምሽ ተቸግረሽ አድልበሽው
  ውለታሽን ረሳ በደነ
  ዞሮ ባንቺ ላይ ደገነ
  ካጥፊወችሽ ጋር አብሮ ጥፋትሽን አፋጠነ
  እናታለም ላንቺማ ይታዘን ይለቀስ ባያሌው
  ዘርተሽ መራራ ለለቀምሽው
  ገዳይሽን ለታቀፍሽው
  እርጉሙን ለመረቅሽው
  የእዉር መሪ አበጅተሽ
  በተስፋ ቢስ ተስፋ ጥለሽ
  ሁሉም ጠፋ ገደል ገባ
  ደሃሽ የደም እንባ አነባ
  ነገ አይናፍቅም ባንቺ ምድር
  ርእይ የለም ነፍስን ባሴት አለምልሞ የሚያሳድር
  ነገወችሽ ሞተናልና እውቀታችን መርዝ ሆኖብን
  ሃገሬ ሰው አልባ ሃገር የለም
  እናም አንቺም ነገ አትኖሪም። ትላለች
  እናም ይህች ሃገር በልጆቿ እየተፈተነች ያለች ሃገር ነች በተለይም ተማርን በምንለው።ዛሬ በየፊናው ተማርኩ ተመራመርኩ አንደበቴ ሰላ ንግግሬን ሰው ወደደልኝ እያለ ስራው ሃገር ማጥፋት የሆነውን ወገኔን ሳይ አንድ የምረቃ መጽሄት ላይ ያነበብኳትን ላስት ወርድ አስታውሳለሁ “የተማረ ይግደለኝ ይላል ያገሬ ሰው
  ተመርቀን መጣን ይኸው ልንጨርሰው” ይላል ታዲያ እዲህ እየፎከረ ሲመጣ ምን ይባላል ጨርሱን እንጂ …

  ReplyDelete
 33. ለሐገሬና ለሕዝባችን በጣም አዘንኩ:: ኢትዮጵያውያን መግባባት አንችልም ማለት ነው? ያነበብኳቸው ብዙዎቹ አስተያየቶች የዳንኤልን ጽሁፍ የሚኮንኑ ናቸው:: ግን ለምን? የዚህ ጽሁፍ ጎጂነቱ ለኔ ምንም ሊታየኝ አልቻለም:: ዳንኤል እንኳን ወያኔ ቀርቶ የፈለገው ቢሆን ምን ቸገረን? እንኳን ዳንኤል ቀርቶ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቢጽፈው ጽሁፉ ጠቃሚ ከሆነ ምን ቸገረኝ? እኔ እንደተረዳሁት ከሆነ የዳንኤል ጽሁፍ ዋና ሃሳቡ ሁሉም የራሱን አመለካከት (ፖለቲካዊ, ሐማኖታዊ, እና ሌሎቹንም) እንደያዘ ልዩነታችንን አክብረን; በፖለቲካዊ አመለካከታቸው ከወያኔ ስለተለዩ ወገኖቻችንን ወያኔ እንደሚያንገላታቸው ሳይሆን ሰው በማንኛውም መልኩ በሚኖረው ልዩነቱ ሳንነቅፈው ተከባብረን ግን ሁላችንንም አንድ ሊያደርገን የሚችል ነገር ይኑር ነው::

  ታዲያ ይህ ምን ክፋት አለው? እባካችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ አንድ ሰው ጥሩ ሃሳብ ሲያመጣ በጥሩ መልኩ ብንመለከተውና ብንወያይበት ጥሩ ነው:: ዳንኤል ያመጣው ሃሳብ ጥሩ መስሎ ካልታየን በመሳደብና እንዲህ አይነት መልካም ሃሳቦችን የሚያመጡ ሰዎችን ወደፊት ምንም አይነት ሃሳብ እንዳይሰነዝሩ አፍ አፋቸውን በማለት ሳይሆን በሰለጠነ መልኩ የራሳችንን ሃሳብ ብንሰነዝር መልካም ነው:: ወገኖቼ እርስ በርሳችን እየተራረምን ሀገራችንን ለመለወጥ ብንጥር መልካም ነው:: ምናልባት ብዙዎቻችን ለሃገራችን መልካም ነገርን ለማምጣት ከአሜሪካ ወይም ከሌሎች ምእራባውያን ሃገሮች ትጠብቁ ይሆናል: ግን በፍጹም አትጠብቁ:: እነሱ የአፍሪካውያንን እድገት ወይም መለውጥ በፍጹም አይፈልጉም:: ግን ባለንበት አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆነን እንድንኖር ነው የሚፈልጉት:: እርስ በርስ የሚያባላን ወያኔ እንዳይመስላችሁ:: ወያኔማ ዛሬ በስልክ ተደውሎ ስልጣን ልቀቅ ቢባል የሚለቅ መንግስት እኮ ነው:: ከወያኔ ጀርባ ግን ወደዳችሁም ጠላችሁም አሜሪካ አለች:: ወያኔ ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የአሜሪካ ስራ አስፈጻሚ ነው:: ስለዚህ ከቻልን ወያኔ እንዲራራ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ እንዲያዝን መጀመሪያ አሁን ዳንኤል ለውይይት በሚያቀርበው መልኩ በነገሮች ላይ ተወያይተን እርስ በርስ ተግባብተን የወያኔንም መንግስት ወደኛ እንዲመጣና የአሜሪካና የሌሎች ምእራባውያን አሽከር እንዳይሆን ማግባባት መልካም ነው:: ያን ማረግ ካልቻልን ግን ቢያንስ እርስበርሳችን በሃሳብ መግባባት ብንችልና ለኢትዮጵያ ህልውና ያለን አመለካከት አንድ እንዲሆን በንደዚህ አይነት ሃሳቦች ላይ መወያየቱ እጅግ ጠቃሚ ነው:: የኢሃዲግ መንግስት ለአሜሪካ አሽከር እንደሆንኩ እቀጥላለሁ: እኔን የሚያሳስበኝ የኔ ስልጣን እንጂ የኢትዮጵያ ህልውና አይደለም ብሎ አሻፈረኝ ካለ የኢትዮጵያ አምላክ በኢሃዲግ ስልጣናትና በልጅ ልጆቻቸው ላይ በልበ ደንዳናው ፈርኦን ላይ ያወረደበትን መቅሰፍት የሚያወርድበት ጊዜ ሩቅ አይደለም:: ዳንኤል ባመጣው አይነት ሃሳብ አንድ መሆን ካልቻልን ግን ኢሃዲግ ቢጠፋም ዋጋ የለውምና እባካችሁ ቢያንስ ሁላችንም የሁሉም ብሔረሰብ ተወላጅ, የሁሉም ሐይማኖት ተከታይና ባጠቃላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያ ህልውና ያለን አቋም አንድ ይሁን:: "ድሮ ይህ ብሔር ገዝቶን...እንዲህ አድርጎን..ወዘተ" እያልን የድሮ ያለፈውን ታሪክ እየዘረዘርን ብንኖር ዋጋ የለውም:: ምንም ትርጉም አይኖረውም: የባሰ ኢትዮጵያ የምትባል ምድር እንዳትኖር ነው የምናረገው:: ያ ደግሞ ለማናችንም አይጠቅመንም:: ስለዚህ እባካችሁ በኛ ዘመን ነገሮችን ለማስተካከልና አንዲት ነጻነት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩል የሰፈነባት ሀገር ለመመስረት ጥረት እናድርግ:: ለልጆቻችንም እንደዚች አይነት ኢትዮጵያ ለማስተላለፍ እንሞክር:: ለዚህ መሳካት ደግሞ ዋናው በሃሳብ መግባባትና እያንዳንዱ ዜጋ የሚሰነዝረውን ሃሳብ ስናከብር ነው:: ለሁሉም ፈጣሪ ይርዳን! ሐገራችንን ይጠብቅ!

  Geta

  ReplyDelete
 34. I love what Birhan Ze-Be'aman said.

  ReplyDelete
 35. ከዚህ በላይ አለመግባባት ከየት ይምጣ
  ጌታ ድውያንን ሲፈውስ አስቀድሞ መዳን ትፈልጋህ ብሎ ይጠይቅ ነበር
  እና እኛም መጀመርያ እስቲ ሁላችንም ራሳችንን መግባባት እንፈልጋለን ብለን እንጠይቀው ከዛ በእርግጠኛነት ምን እንደምንፈልግ ስለምን እንደምናወራ ብሎም ማን እንዲህ እንዳንግባባ እንደመሚያረገን እናውቃለን ከዛ ለመፍትሄ አያስቸግረንም

  በትረ ሙሴ

  ReplyDelete
 36. 'ሊያለያዩን በሚችሉ ነገሮች ላይ በዚህም በዚያም ወገን ሆነን በሚገባ እየሠራን ነው፡፡እስኪ አሁን ደግሞ በአዲሱ ዓመት አንድ ሊያደርጉን በሚችሉ ነገሮች ላይ እንሥራ' የለያየንና አነድነታችንን ያፈረሰውን አንድነታችንንም እንዳናጠናከር የሚያደርገውን ኃይል ለማስወገድ ቆርጠን እንነሳ ከሆነ ጥሩ ነው። ጽሑፉ ግን የፈሪና ያድርባይም ይመስላል። ወይ እንደ እስክንድር ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ! ወይ እውነትን ፃፍ ወይ አርፈህ ተቀመጥ። ለዚህች ለቀረችህ አጭር እድሜ ለምን በስጋህ ትጠላለህ? ለምንስ በነብስህ ላይ ትፈርዳለህ? አንተ ምላጭ በትክከል ላጭ!

  ReplyDelete
 37. sometimes its difficult to see one shared thing differently but its possible to see one thing from different angle and working on that common thing that is better for us and everybody who loves this country the above dani article says about common icon of one country that all different people in that country stands for and i think its positive idea for who have positive feeling about their country and gov TEWODROS THAZEZA sarbet sometimes its difficult to see one shared thing differently but its possible to see one thing from different angle and working on that common thing that is better for us and everybody who loves this country the above dani article says about common icon of one country that all different people in that country stands for and i think its positive idea for who have positive feeling about their country and gov TEWODROS THAZEZA sarbet

  ReplyDelete
 38. እንኳ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሃንስ በሰላም በጤና ያሸጋገረህ

  ሰላም ዳኒ የበአል ግብዣ ቢኖርህ

  ReplyDelete
 39. ልዩነቶቻችንን በተመለከተ አንብበን፣ ተርጉመን፣ ምሥጢር አደላድለናል፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ በአዲሱ ዓመት አንድ ሊያደርጉን በሚችሉ ነገሮች ላይ እንሥራ፡፡ ልዩነት የማይከበርበት አንድነት፣ አንድነት የማይገለጥበትም ልዩነት ሁለቱም የሞቱ ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 40. I read the article time and again. Nothing rubbish; it is all about the facts, what we are doing against our Mother Ethiopia one way or the other. For me, Daniel produced a very good article surely coincided with the new year.

  We can't build or keep track of what was formerly orchastrated unitary Ethiopia with the notion of "one" (nation, religion, culture,party ...). Believe or not this is the ideology that already evaporated once and for all.

  What is evil if Daniel speaks of Solidarity?

  I read all the comments; few are good. But I realized from the comments that most of the writers let them willingly blind of seeing the ongoing global processes or simply slammed their mind hard not to accept the truth.

  Instead of damning specific group/s for all the shortcomings the country has been experiencing for generation and instead of getting into brawl on account of such allegations, let's start contributing our share to rebuild Our Home. No matter how deep and vast the problem of the country; no matter who and to what extent contribute the distractive role in shattering the image of Ethiopia, let stand firm with the notion "Yichalal". Let's have a heart for forgiveness, vigor, heart that ignites enlightenment of the future Ethiopia.

  No matter how long the dark the dawn will break

  HAPPY ETHIOPIAN NEW YEAR

  ReplyDelete
 41. @ጌታ፥ እኛም ያልነው ለምእራባውያን አሽከር ከሆነውና በዘር ከከፋፈለን ጋር አትሁን ነው። በዘር የሚከፋፍሉትና ባነዳዎችን እንደ አንድ ልዩነት ወስደን እናክብራቸው ማለትህ ያሳፍራል። ይህማ ከሆነ ቅኝ ገዥዎችን ለምን እምቢ አልን? ልዩነት ፈጣሪዎችን ከመቃወምና ከማስወገድ በቀር አንድ በሚያደርገን ጉዳይ ላይ የሚባል ማጭበርበር ቦታ የለውም። ልዩነት ማለት እንዲህ ሀገርን ህልውና ፈጽሞ እንዳልነበረና አዲስ አገር እንመሰርታለን ከሚል ጋር አይደለም። ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አንድ ጊዜ ተሰርታለች በውድም በግድም። አሜሪካንም በውድም በግድም የተሰራ ሀገር ነው። እንገነጠላለን ብለው ያወጁትን ካሮላውያን በግድ በጦርነት ነው እንዲቀላቀሉ የተደረገው።(the beginning of the civil war was denial of secession act of the Carolinas) እንደ አንድ ልዩነት ተገንጣይነትንና አስገንጣይነትን እንውሰድና በጋራ ነገሮች ላይ እንነጋገር አልተባለም። ሊባልም አይገባም። ስለዘህ ጽሑፉ በማር የተለወሰ መርዝ ነው! ከጣልያን ጋር አንድ በሚያደርጉን እንደ መንገድ ስራ ድልድይ ስራ ወዘተ መደራደር ነበረብን? መጀመሪያ አገራችንን መልቀቅ ነበረበት በውድም በግድም። አሁንም ያመው ነው።

  ReplyDelete
 42. dani befekadegnet yalkew nager altemchegnm

  ReplyDelete
 43. አሁን አሁን በጣም ግራ እያጋባኸኝ መጥተሃል! ኢሕአዴግን የሚደገፈውን «ከልቡ» ካልከው በሁዋላ የሚቃዎመውን «ለሆዱ ብሎ የሚቃዎም» ማለት ምን ማለት ነው?? እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ካለመኖር ወደ መኖር እንዳመጣ ሁሉ አንተና በአንተ እሸት የአገልግሎት ዘመን አብረውህ የወንጌል ገበሬ የነበሩት ወንድሞችህ እኛን «በእግዘአብሔር ቤት ካለመኖር ወደ መኖር» አምጥታችሁናል ብለን የምናንን ሁሉ በእጅጉ ግራ የሚያጋባ ማንነት እያመጣህ ነውና ለራስህ ስትል ብትባንን መልካም ነው ወንድም ዓለም!

  ReplyDelete
 44. Please!!!!!! To my mind your time is going to expire. Something went wrong with you my brother. Directly or indirectly you used to complain about the diaspora. Are you asking us now to accept the flag or to demonstrat against it? How could we agree with someone who try to change our family name without our permition?....Please be cute!!

  ReplyDelete
 45. wuy wuy wuy egna gin endet eyetebelashen new, dear dani- do u know what most people need to put some one as a hero just write blame and criticize EPRDF. poleticalize madreg siwedu , endet endemiqeyirut ayitaweqim , but forget them and keep the good work, follow your heart,
  weyane andinetachinin asatan bitil noro gin ,yageligilot zemen yibiza kale hiwot yasemah bemil comment betechenaneq neber
  happy new year!!!

  ReplyDelete
 46. ዉድ ዳንኤል
  ምንም ይሁን ምንም በአሁን ግዜ ባንዲራችን ላይ ያለው ፔንታግራም ከጥንቆላ (ፍሪሜሶናሪይ)ጋር እንጂ ከኢትዮዽያ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፥፥

  http://en.wikipedia.org/wiki/Pentagram

  የዮሐንስ ራእይ 5:5 "ከሽማግሌዎቹም አንዱ። አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።"
  እውነተኛው የኢትዮዽያ አርማ ይህ እንደ የዋህ በግ ለእኛ የተሠዋ፣ ደግሞም እንደ አንበሳ ሞትን ድል ነስቶ በምሥራቅ ያረገ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፥፥የእርሱን ዳግም ምጽአት የምንጠባበቅ እኛ ኢትዮዽያዊያን ይህን ጥንታዊ ሰይጣናዊ የፔንታግራም ምልክት በ ቃልኪዳናዊ ሰንደቅ ዓላማችን ላይ መቀመጡን እንቃወማለን፥፥

  ReplyDelete
 47. አንዳንድ ሰውች የምትሰጡት አስተያይት በትክክል ማንነታችሁን ይገልጽባችሃልና ዝም ብትሉ ጥሩ ነበር ።የሆነ ሁኖ አውቀናችሃልና ብትጸፉም ባትጽፉም ለውጥ የለውም ትርፉ ትዝብት ነው።
  አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ይባላል።


  ለሁሉም ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

  ReplyDelete
 48. I was really surprised to see comments like SendekAlama's (Posted on Sept 13). ኢሕአዴግን የሚደገፈውን «ከልቡ» ካልከው በሁዋላ የሚቃዎመውን «ለሆዱ ብሎ የሚቃዎም»

  This is what is called "Hair Splitting". You even changed it a bit so that it gives you a a meaning with bad connotation. Don't you really know that both «ከልብ» and «ከሆድ» have the same meaning? Be honest for yourself.

  Please, look at the bright ideas. Plz ask the question, as a citizen, what can I do to restore our unity, promote our heritage and help at least one poor person to eat today. You don't have to be a politician to do this.

  Addis from Ethiopia

  ReplyDelete
 49. I read this blog once in a while but I never commented about the content. but reading after this one, I couldn't resist not to comment. It's true that it isn't good to dwell on more on our difference, however, the flag is a symbol of TPLF which I personally consider as Enemy of my people (mind you I never say, enemy of Tigray). you can make your political point as supporter of TPLF and the present flag, but I assure you that like Libyans, we will wave our flag sooner or later.

  ReplyDelete
 50. ዲ/ን ዳንኤል፣ ለአንተም መልካም አዲስ ዓመት እመኝልሃለሁ። ለጽሑፍህ የመረጥከው ርዕስ ግሩም ነበር። ነገር ግን የማያግባቡን ነገሮች ብለህ እንደ ምሣሌ ያቀረብካቸው አንዳንዶቹ ነገሮች ለምሣሌ፡- ሠንደቅ ዓላማ እና ተቃዋሚነትን የሚመለከቱቱ ትንሽ ከእውነት የራቁ ሆነውብኛል። ሠንደቅ ዓላማን በተመለከተ፣ ሁላችንንም የሚያግባባን ቀለሙ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ መሆኑ ነው። ከዚያ በተረፈ ላዩ ላይ የሚለጠፈው ዓርማ አገሪቱን የሚያስተዳድረው መንግሥት ልዩ መለያ እንጂ እንደ አገሪቱ ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ሊወሰድ አይገባም። እንደዚህ ዓይነት ዓይን ያወጣ ሸፍጥ ያየነው በአሁነኛው መንግስት ብቻ ነው። ኢህአዴግ ኮከብን መርጧል፤ የዘውዱ አስተዳደር የተጠቀመው ደግሞ አንበሳን ነበር። ደርግ ግን ማጭድና መዶሻ መጠቀሙን አላስታውስም፤ ቀዩ ባንዴራ ላይ ካልሆነ በስተቀር። ሠንደቅ ዓላማችን በጃንሆይ ጊዜ ታላቅ ክብር ነበረው። እንዲያውም ሲወርድ እና ሲወጣ ልዩ መዝሙር እንደ ነበረው አስታውሳለሁ። በደርጉ ዘመነ መንግሥትም መዝሙር ባይዘመርለትም ጠዋት ተሰቅሎ ማታ 12 ሰዓት ይወርድ እንደነበረ ትዝ ይለኛል። ኢህአዴግ ሲገባ "ከጨርቁ ጉዳይ የለንም" ተባለና መከበሪያችን፣ መኩሪያችንን አቃለሉብን። በአጠቃላይ፣ ያላግባባን ሠንደቅ ዓላማው ላይ የተለጠፈውን ድሪቶ "እንደ ብሔራዊ መለያ ተቀበሉት" መባላችን ብቻ ነው። የ 2003 influential person ተብለህ መመረጥህን የሆነ ቦታ ያነበብኩ በመሆኑ ይኸው ዝናህ እየጎላ እንዲሄድ በዚህ ጉዳይ ልንግባባ የምንችለው ድሪቶውን ሲያነሱ ብቻ እንደሆነ ለነሱም ሹክ በልልኝ።

  ከዚያ በተረፈ ስለ ደጋፊ እና ተቃዋሚ ባነሳኸው ነጥብ ላይ “ከልቡ ደጋፊ” እና “ለሆዱ ሲል ተቃዋሚ” ብለህ ያስቀመጥከው ሃሳብ ከምን መነሻ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። “ለሆዱ ሲል ተቃዋሚ” ያለው የኢህአዴግ ፓርላማ ውስጥ ነው። ይህ የሚጠፋህ አይመስለኝም። ስም ጥራ ብትለኝ፣ 1/ ልደቱ 2/ እገሌ … እያልኩ ልዘረዝርልህ እችላለሁ። ከማን ምን አገኛለሁ ብዬ ይሆን ወያኔን የምቃወመው? ዲ/ን ዳንኤል፣ ወያኔን የምቃወመው ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ዘረኛ፣ ከፋፋይ፣ አረመኔ ድርጅት ስለሆነ ነው። በዚህም ምክንያት ነው ከአገር የተሰደድኩት። ካለመንከኝ ጠይቃቸው ይነግሩሃል። አንተ ከየትኛው ጎራ ትመደባለህ? “ከልቡ ደጋፊ” ወይስ “ከሆዱ ተቃዋሚ”? ቁርጡን ንገረንና እርሜን ላውጣ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምትጽፋቸው ነገሮች አልጥም እያሉኝ ተቸግሪያለሁ፤ “ምናልባት እኔ ያልገባኝ ነገር ይኖር እንደሆን” ብዬ ከራሴ ጋር ስሟገት ሰነባብቻለሁ። ለምሣሌ፡- በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ስላለው ችግር ለመግለጽ የተጠቀምክባቸው ቃላት በጣም ዘግናኝ ነበሩ። እስከ መጨረሻው ድረስ አንብቤ ለመጨረስ ስለ ተሳነኝና ማመን ስላቃተኝ “እንዲህ ብለው ጽፈውብሃል” ብዬ ላኩልህ። ግና ችግሩ አንተ ጋር እንደሆነ ሌሎችም ወገኖች ከሚጽፉት አስተያየት ለመረዳት አላዳገተኝም። ሌላው፣ በአባይ ግድብ ዙሪያ ሕዝቡ በፈቃዱ ገንዘብ እንደሚሰጥ፣ ቦንዳም እንደሚገዛ ኢቲቪ ላይ ቀርበህ የሰጠኸው የምስክርነት ቃል የሚያስተዛዝብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ወገኔ ምን ነካህ? እኔ በእውነቱ እንደዚህ አላውቅህም። ዲሲ ሜትሮ አካባቢ ሬድዮ ከፍቶ የሚያደነቁረንን ንጉሤን ነው የመሰልከኝ። ይቅርታ አድርግልኝ ወንድሜ፣ ከሁለት ዓመት በፊት በአካል የማውቀው ዲ/ን ዳንኤል አልሆንክብኝም። እውን የቤተ ክርስትያኑን ነገር ትተኸዋል? ይህንን አስተያየቴን ካልፈለግህ አታውጣው፤ እኔ ግን ካንተ መልስ እፈልጋለሁ። እግዚአብሔር ይማርህ!
  አድናቂህ

  ReplyDelete
 51. Hello Dears

  Was the article first conceived to tell us about FLAG? I didn't think so. The THEME of the article was that about HOW TO AVOID DIFFERENCES AND MAKE INTEGRATION. Flag, Athletes, Ethiopian were presented to exemplify how our differences are getting wide and worse.

  Almost all the critics forgot about the theme. Let us focus about the common agenda.

  ReplyDelete
 52. አንድ ጥያቄ ላቅርብ። የባንዲራው አርማ ቀድሞ የይሁዳ አንበሳ ነበረ፤ አሁን ደግሞ የሰሎሞን ኮከብ ሆነ። እግዚአብሔር ባወቀ አንድ ወገን አድርጎታል። የዳዊት ኮከብ ባለስድስት ሲሆን የሰሎሞን ግን ባለ አምስት መሆኑን ልብ በሉ። ታዲያ አንበሳውም የይሁዳ ኮከቡም የሰሎሞን የአንድ ቤተሰብ አይደሉምን? ምን ያጣላናል?

  ReplyDelete
 53. Hello Brothers and Sisters,

  If we hate each other for whatever reason (religion, politics, ethnicity, ...), forget about change in Ethiopia. Whether Woyane is on power or not, there will be no stability. Because, always there is some group of people who are not happy with the ruling government.

  So the first step for change is trying to understand each others' views. Most importantly, to respect differences. To find common grounds, To engage in civilized discussions... Otherwise, it is going to be a vicious circle. When Woyane is gone, an extremest in the opposite direction may come to power.

  Lets find our common grounds, lets keep on discussing.... This is the basic idea behind this article. Why can't we try to look at it from this angle?


  Addis from Ethiopia

  ReplyDelete
 54. sorry, DD, say the truth, why you are afriad to say the truth?, Daniel, your are looking for another award from TPLF Leaders. You are good writer , but nowdays you are on the wrong truck. Remember , Martin Luther King , JOhn the baptist, Yohnnes Aferwork (you know him better than me ), the true fathers , they spoke and stood for their oppressed people . I don't know Daniel ?

  ReplyDelete
 55. ይገርማል ለመሆኑ የዚህን የጡመራ መድረክ ተገንዝባችኋል? ይሄ እኮ የስብከት ቦታ አይደለም የመዎያያ እንጂ:: ለመሆኑ

  "የዳንዔል ክብረት እይታዎች" የጡመራ መድረክ " ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ:ባህል:እምነት:ፕኦለቲካ እና ትውፊት " ምልከታዎች የሚቀርቡበት መሆኑን አላይ ብላችሁ ነው? ዲ. ዳንዔልን ለመተቸት እና ለመፍረድ የቸኮላችሁት? ሰው ሁሉ በ እናንተ አይን እንዲመለከት አትጠብቁ ማንኛውም ሰው የራሱ የሆነ የስሜት ህዋሳት እና አእምሮ አለው እናም የ እናንተንም እይታ ማየት ይችል ዘንድ እድል ስጡት እንጂ አትጨፍልቁት  በመቀጠልም ከ ላይ ስለቀረበው ጽሁፍም ሆነ ስለ አስተያየቶች ጥቂት ነገር ለማለት ወደድሁ ይኸውም:
  1ኛ የልብ ደጋፊ የሚደግፈውን ድርጅት አቋም እና ፕኦሊሲ ያስፈጽማል እንጂ እንቅፋት ሲሆን አይገኝም:: በተጨባጭ እያየነው ያለው ግን የተጻፉ ህጎችም ሆነ ደንቦች ከዎረቀት አልፈው መሬት ላይ አይታዩም:: ስለሆነም ከሆዱ የሚደግፍ የሚል ቢሆን ኖሮ እንዴት እዉነታውን በገለጸ ነበር::
  2ኛ ከሆድ የሚቃዎም ማለት ሃገሪቱን የሚጎዳም ሆነ የሚጠቅም ነገር ሲሰራ እኩል የሚጮህ ማለት ነው:: ይሄንንም 2003 አሳይቶናል እናም በርግጥም ከሆዱ የሚቃዎም ሞልቷል:: ስለዚህ ይህ አባባል የተቃዋሚውን ጎራ በ ትክክል የገለጸው ይመስለኛል::
  3ኛ ስለ ባንዲራው የተነሳው ውዝግብ የሚገርም ነው:: በ መሰረታዊው የ ሃገራችን ባንዲራ ላይ የየመንግስታቱ አርማ ሁሌም እንደተለጠፈ ነው የ አሁኑን ለየት የሚያደርገው በ አዋጅ መደገፉ እና የ አስገዳጅነት ህግ መውጣቱ ነው::

  እኔ በበኩሌ የምፈልገው የዚህችን አገር ጥቅም የሚያስከብር እና እድገቷን ወደፊት የሚያራምድ መንግስት እንጂ የባለስልጣናት ፊት ሲቀያየር ማየት አይደለም:: የ አሁኑ መንግስትም በ አሁኑ ወቅት ከ አለፈው ስህተቱ የተማረ ይመስለኛል እና ጥሩ ጅምሮችን እያሳየኝ ነው:: ተቃዋሚዎች ሆይ እናንተ አንድ ላይ ቁማችሁ ስትጮሁ እና በየ ብሎጉ በየሚዲያው ሰው ስትዘልፍ ደጋፊዎቻችሁን እንዳታጡ እራሳችሁን ከዎቅቱ ጋር እና ከ እኛ ከ ኢትዮጵያውያን ባህሪ አንጻር የተቀየሰ የትግል ስልት ብትነድፉ መልካም ነው:: በተረፈ ምራባውያንን ያስተዳደረ ህግ ኢትዮጵያውያንንም ያስተዳድራል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ አትሳሳቱ:: እኛ የ እኛ የሆነ ባህላችንን እና እድገታችንን የሚመጥን ህግ ብቻ ነው የሚመራን ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያውያን መሪዎቻችንን እየዎለድን ስንመራ እንኖራለን እንጂ ከውጭው አለም አናስገባም::

  ስለዚህ እራሳችሁ ለእራሳችሁ ልብ ግዙ እና በልዩነቶቻችን ተከባብረን ብንዎያይ መልካም ይመስለኛል ካለበለዚያ መዘላለፍ የትም አያደርሰንም::

  ReplyDelete
 56. UNITY Part-1
  ውድ ወንድሜ ዳንኤል እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰህ፡፡
  ከዚህ በፊትም እንዳልኩህ አንተ ፍፁም ልትሆን አትችልም እንዲሁም ፍፁም እንትድትሆን አልጠብቅም፡፡ስለዚህም ይበልጥ የማተኩረው በምታነሳቸው ምርጥ የሆኑ የመወያያና የመከራከሪያ አርእስቶችህ ላይ ነው፡፡በመጀመሪያ ዳንኤል ዳንኤልን ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ማንንም ሌላ ሊሆን አይችልም መምሰል ካልሆነ በስተቀር፡፡ስለዚህም እኔ የወያኔ ደጋፊም ሆንክ ወይንም ተቃዋሚም ሆንክ ወይንም መሃል ሰፋሪ ይህንን አስተሳሰብህን እንደአስተሳሰብ በራሴ አስተሳሰብ ልሞግትህ ብችልም ነገር ግን ይህንን ሰብዓዊ መብትህን እጅግ አከብርልሃለሁ፡፡የሚወራውን ሁሉ ልትሆንም ላትሆንም መቻልህ እንዳለ ሆኖ ግን ብቻ መጀመሪያ ላይ እራስህን እውነተኛውን ዳንኤልን መሆንህን ግን በጣም የምፈልገውና የማከብረው ነው፡፡የወያኔ ደጋፊ መሆን አለመሆን ወይንም ተቃዋሚ መሆን አለመሆን ወይንም ገለልተኛ መሆን አለመሆን አይደለም ትልቁ ቁምነገሩ ይህንን ሁሉ ለመሆን ስናስብና ስንወስን ግን በምክንያትና በእውነት ላይ ተመስርተን እራሳችንን ሆነን ያመንበትን ማድረጋችን መሆኑ ላይ ይመስለኛል ትልቁ ቁምነገር፡፡እኔ ይየማተኩረውም በፅሁፎችህ ላይ በጥቃቅን ዝርዝሮቹ ላይ ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ሊያስተላልፍ ከፈለገው ዋና ጭብጥና መልእክት ምንድን ነው የሚለው ጭምር ላይ ነው፡፡በምን እንግባባ የሚለው ሊመለስ የሚገባው እጅግ መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡ማለትም እንደ ኢትዮጵያዊ አንድ ሊያደርጉን የሚችሉትና የሚያግባቡን ነገሮች ምንድን ናቸው የሚለውን ለመመለስ እንዲረዳን ማለት ነው፡፡እንደሚመስለኝ ከሆነ ሁላችንም በውሰጣችን እጅግ ስር የሰደደ ግራ መጋባት ፍርሃት ጥርጣሬ አለመተማመን በጣሙን ነግሶብናል፡፡ይህ ደግሞ በዋናነት የሚመነጨው በዋናነት እውነቱን ካለማወቅና ከንቃተ-ህሊና ማነስ የሚመነጭ ነው፡፡የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል እንዲሉ ብዙዎቻችን ጥሩ ናቸው የኛን ሃሳብ ይቀበላሉ እውነተኛ ናቸው የምንላቸውን ሰዎች ጭምር የግድ በእያንዳንዱ ጥቃቅን ነጥብ ላይ ጭምር ከእኛ ጋር አንድ እንዲሆኑ እንጠብቃለን፡፡ከዚህ በመነጨም ባለፈው ልጅ ዳንኤል ያነሳው የነበሩ ጅራት አይነት መጨረሻ ላይ የራሳቸው ስብእናና ማንነት ያላቸው ጭምር መሆናቸውን እስክንረሳ ድረስ ወደሚመቸንና ወደራሳችን ማንነትና እውነታ ጥግ ልንጎትታቸው እንደርሳለን ማለት ነው፡፡ስለዚህም ዳንኤል እራሱን ዳንኤልን ሆኖ ነው እውነታን መመዘንና ማየት የሚችለውና መመዘን ያለበት፡፡ይህንንም አስተያየት የሚሰጠው እንደዚሁ፡፡ሁላችንም በጥርጣሬ በፍርሃትና በግራ መጋባት የተነሳ ሊያግባባን የሚችለው የጋራ አጠቃላይ እውነት ላይ ለመገናኘት አልቻልንም፡፡ሁላችንም ምሽግ መሽገን በየራሳችን ጎጆና ዋሻ ውስጥ ነው ያለነው፡፡አንዳንዶቻችን በብልጣብልጥነት አንዳንዶቻችን ደግሞ በግትርነት አንዳንዶቻችን ደግሞ በአደርባይነትና በመሰሪነት ከእውነት ጋር ተጣልተን ትልቅ የፀብ ግድግዳ ገንብተናል፡፡እውነት አርነት ያወጣችኋል እንደተባለው ሁሉ እውነተን ከተከተልን አርነት እንወጣልን፡፡አርነት ያለውና በነፃነት ማሰብ መናገርና መኖር የሚችል ግለስብና ህብረተሰብ ደግሞ ከፍርሃት ነፃ ነው፡፡ስለዚህም መጀመሪያ ከራሱ ጋር ተግባብቶ በሰላምም ይኖራል ከዚያ ደግሞ ከአካባቢው ጋር እንደዚሁ፡፡
  ለምን ሰዎች እንደሚወዱን እንዲነግሩን የምንፈልገውን ያህል በተቃራኒው ጠልተውን ከሆነ ደግሞ በግልፅ እንደሚጠሉንም ጭምር እንዲነግሩን የማንፈልገው?ሰዎች በሃሳብና በስሜት እንዲግባቡን የምንፈልገውን ያህል ይህ መሆን ሳይችል ሲቀር ደግሞ በተቃራኒው እንዲቃወሙንና እንዳይስማሙን እድሉን ለምን እንነፍጋቸዋለን?ማንኛውም ነገር እኮ የራሱ የተፈጥሮ ስርዓት ህግና ሂደት አለው እኮ፡፡ለዚህ ህግና ስርዓት ለምንድን ነው ተገዥ ለመሆን ያልቻልነው?ማንም ሰው ህይወትንና ይህንን አለም ከራሱ የህይወት ተሞክሮ አንፃር ጭምር ነው የሚመለከተው፡፡ስለዚህም ከዚህ በመነጨ የራሱን የመሰለውን የህይወት ተሞክሮና እውነት ተከትሎ በሚሄድበት ጊዜ በሌላው እይታ አንፃር ሲሄድ ትክክልም ሊሆን ይችላል ወይንም ስህተትም ሊሆን ይችላል፡፡ከዚህ እይታ አንፃር ትክክልም ይሁን ስህተት ቢያንስ ሰዎች የየራሳቸው የእኔ የሚሉት ልማድ እውነትና እምነት እንዳላቸው መረዳትና ማመን መቻል ይጠበቅብናል፡፡ትንሽ ለመረዳት እንደሞከርኩት ከሆነ ትልቁ ችግር ያለው ሰዎች በያዙት አስተሳሰብና አመለካካት በሌሎች አንፃር ትክክል ወይንም ስህተት የመሆናቸው ነገር ብቻ ሳይሆን መጀመሪያውኑ ይህ የአስተሳሰብና የአመለካከት ልዩነት በሌሎች ዘንድ ሊኖር እንደሚችል ያለመጠበቅና ያለመገንዘቡ ላይና ይህ ልዩነት እንዴት ከቶ ሊሆን ይችላል ብሎ አካኪ ዘራፍ ማለቱ ላይ ነው፡፡ይህ ትልቅ ችግር ባይኖርማ ኖሮ የሌሎችን ስህተትና የአስተሳሰብና የአመለካከት ልዩነት በትእግስት የማዳመጥ የማስተናገድና ከተቻለም በምክንያታዊነት ላይ በተመሰረተ ውይይትና ክርክር የማስተካከል ባህል በኖረን ነበር፡፡እንደተረዳሁት ከሆነ ትልቅ ችግር እየተፈጠረ ያለው ልዩነቶች በመኖራቸው ላይ ብቻ አይደለም እንዲያውም ችግሩ ይበልጥ ያለው ይህንንም ልዩነት የምናስተናግድበት አካሄድ ላይ ጭምር ነው፡፡ማለትም አንዳንድ ጊዜ አለመግባባቶች ወይንም ችግሮች ከሚፈጥሩት የማይቀር ጥፋት ይልቅ አለመግባባቶቹ ወይንም ችግሮቹ የሚፈጥሩትን ጥፋት ለማስወገድ የምንጠቀምበት አካሄድና አስተሳሰብ በራሱ ሌላ የባሰ ተጨማሪ ችግር ፈጣሪ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ልክ ለአንድ በሽታ የምንወስደው መድሃኒት ሌላ የባሰ ያልታሰበ ሌላ በሽታ እንደሚፈጥረው አይነት ማለት ነው፡፡
  Continues....

  ReplyDelete
 57. UNITY Part-2
  ሁላችንም ንቃተ-ህሊናችን የሰፋና የዳበረ እንዲሁም በምክንያታዊነት አስተሳሰብ ላይ ጭምር ተመርኩዘን የምንመራ ከሆነ እኮ እርስ በርስ መጠራጠርና መለያየት ያን ያህል አይኖርም፡፡
  ወይንም ሌላው ለምን የተለየ የሚቃወመን ሃሳብ ሰነዘረ ብለን እድገቱን እንዳልጨረሰና ነፍስ እንዳላወቀ ህፃን አናኮርፍም፡፡ስለዚህም እያንዳንዳችን እውነት ነው ብለን ያሰብነውንና ያመንበትን ነገር በፊት ለፊት ያለምንም መሸማቀቅና መዳለል እንናገራለን፡፡ይህንን ያመንበትን ነገር በፊት ለፊት የመናገር ባህል ስናከብርና ስናዳብር ከንቱ የሆነ የመሰሪነት የብልጣብልጥነትና የድብቅነት አካሄድ ብዙ እርቀት የሚያስኬድ ስላማይሆን በሂደት እርግፍ አድርገን እንተወዋለን፡፡ዳንኤል እኮ እሱ በደንብ በሚያውቀው በአንድ የተወሰነ ነገር ላይ ዛሬ በብልጣብልጥነት አንድ የተወሰነ ድብቅ ፍላጎት ያለው የተወሰነ ሃሳብ በራሱ ፅሁፉ ውስጥ ሰንቅሮ ለጊዜው አምኜው ሊያታልለኝና ሊያሳምነኝ ይችል ይሆናል፡፡ይህንን ሁለት ጊዜና ሶስት ጊዜ ሊያደርገውም ይችላል፡፡ነገር ግን አንድ ቀን እራሱ ያላቸውን ነገሮች አንድ በአንድ አገጣጥሜ ሳያቸው እርስ በርስ የሚጣረሱ ሆነው ካገኘኋቸው ይህ ሰው እያታለለኝ እንደሆነ አንድ ቀን እደርስበትና ከዚያ በኋላ ይህንን ሰው ዳግም ፈፅሞ ላከብረውና ላምነው አልችልም ማለት ነው፡፡የአንድን ሰው ወይንም እምነት አባባልና አስተሳሰብ የምንገመግምበትና ፍርድ የምንሰጥበት አንዱ የሚታወቀው ዘዴ በግልፅነት የተነገሩና አቋም የተያዘባቸውን ነጠላ ነገሮችና አባባሎች በስርዓት በማገጣጠም እርስ በርስ ሳይጣረሱ መስማማትና አብረው መሄድ መቻላቸውን በመገምገም ነው፡፡ስለዚህም ሰዎች እንዳያታልሉንና እንዳይዋሹን ከፈለግን አንዱ ዋነኛ መፍትሄ እውነተኛ ስሜታቸውንና ሃሳባቸውን ከማፈንና ከማሸማቀቅ ይልቅ ከውስጥ አውጥተውት እንዲገልፁልን ማበረታት መቻል አለብን፡፡ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ላለፉት 20 ዓመታት ያህል የተከተለው አካሄድ ባብዛኛው ጥሩ ያልሆነና መሰሪነትና አጉል ብለጣብልጥነት የበዛበት ነው፡፡በአዲስ አበባ ውስጥ በ97 የምርጫ ዋዜማ ለኢህአዲግና ለተቃዋሚዎች ድጋፍና ተቃውሞ ተብሎ የታየው የህዝብ ሰልፍና በተከታይ የታየው የምርጫ ውጤቱ ምን እንደሆነ ሁላችንም የምንረሳው አይደለም፡፡ይህ ክስተት የሚያመላክተው የሰዎች ስሜትንና ሃሳብን በነፃነት መግልፅ ያለመቻል የሚያመጣውን ጣጣና ስህተት ነው፡፡ሰዎች በእውነት አንዲደግፉንና አጋር እንዲሆኑን የምንፈልግ ከሆነ ባንደግፈውም ቅሉ አስተሳሰባቸውንና እምነታቸውን አከብረን አንደዚሁ በተቃራኒው መቃወም ሲገባቸውም ያለመሸማቀቅ እንዲቃወሙን እድሉን ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ነገር ግን ሁላችንም በውስጣችን የየራሳችን ግለሰባዊ ፍርሃት ግራ መጋባትና ያለመተማመን በውስጣችን በጣሙን ስለነገሰና በራሳችንም ላይ እምነት ስላጣን ይህንን የውስጥ ችግራችንን ወደውጪ እያንፀባረቅን ሌሎች ጭፍን አጋሮችንና ደጋፊዎችን ለማፈላለግና በስራችን ለማሰለፍ እንፈልጋለን፡፡ይህም በስተመጨረሻ ያልሆነ ውድቀት ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል፡፡ከዚህ በመነጨም ትንሽ በቀናነት የሚቃወሙንን ጭምር ተቃውሟቸውን ለመልካምና ለገንቢነት ለመጠቀም ስንችል ጭራሽ ለምን ይህ ይሆናል ብለን ቁም ስቅላቸውን እያሳጣን እናወግዛቸዋለን ስልጣንና ሀይልም ካለን እንዲያም ሲል ሌላ ችግር ሁሉ እነንፈጥርባቸዋለን፡፡እኛ ቀድሞውኑ ያለመንበትን ነገር ለራሳችን ጠባብና ስግብግብ ፍላጎት ስንል ሌሎች ተቀብለውን እንዲያምኑት መገፋፋትና ማስገደድ ደግሞ ከወንጀሎች ሁሉ የከፋው ትልቅ ወንጀል ነው፡፡የሰዎችን ግለሰባዊ ነፃነትና የሀሳብ ልዩነት(ትክክልም ይሁን ስህተት) አክብረንና አምነን ልንቀበለውና በስርዓት ልናስተናግደው እስካልቻልን ድረስ እንደ ኢትዮጵያዊ አንድ የሚያደርገንና የሚያግባባንን ነገር ለመፍጠርና ለመመስረት እጅጉን ይከብደናል፡፡አጉል ብልጣብልጥነትና ከልክ ያለፈ ስግብግብነትና እራስ ወዳድነት አንድ እንዳንሆን እጅግ ትልቅ እንቅፋት ሆኖብናል፡፡እኔ ብቻ ነኝ ብልጥ የተሻልኩና አዋቂ ስለዚህም ሌሎቻችሁ ሞኝና አላዋቂ ስለሆናችሁ አይናችሁን ጨፍኑና ላታላችሁ አይነት አጉል ከንቱ የሆነ የብልጣብልጥነት አካሄድ ደግሞ በሌሎች ትዝብት ውስጥ ከመግባትና ከመናቅ ባለፈ የትም አያደርሰንም፡፡ፍላጎትን ስሜትንና ሀሳብን በግልፅነትና በድፍረት ለመናገር ካለመበረታታቱ ካለመቻሉና ይህም ባህል ካለመኖሩ የተነሳ ሰዎች አንድን ግልፅ የሆንን ነገር አስታከው የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎትና አስተሳሰብ ለማስተላለፍና ለማስረፅ ዘወትር ላይ ታች ሲሉ ይታያል፡፡ልጅ ዳንኤል ልትነግረኝና ልታሳምነኝ የምትፈልገው እጅግ ትልቅ የሆነ ቁም ነገር ካለህ ፊት ለፊት ንገረኝ እኔም እንደዚሁ፡፡ሰው በግልፅ ለሚያምንበት ነገር ልቡንና ስሜቱን አይደለም ህይወቱንስ ጭምር ይሰጥ የለም እንዴ፡፡ከዚህ ውጪ ግን እንደዚህ አይነቱን ትልቅ ቁምነገር በብልጣብልጥነት ላሳምንህም ሆነ ልታሳምነኝ ከቶ ያን ያህል አይቻልም፡፡አንተም ሆንክ እኔ ሁለታችንም ክርስቲያኖች ነን፡፡ክርስቶስ በዚህ ምድር 33 ዓመት ከ3 ወር በስጋ ተመላልሶ ሲኖር ማንንም በብልጣብልጥነት አላሳመንም ተከታይም አላደረገም፡፡ማንንም በልምምጥ አላሳመንም ተከታይም አላደረገም፡፡ማንንም አስገድዶ አላሳመነም ተከታይም አላደረገም፡፡ማንንም ህይወቱን እስኪሰጥ ድረስ ያመነበትን ከማድረግ አልፈራም፡፡
  መቅረዝን በአልጋ ስር ሳይሆን በፊት ለፊት እንዲያደርጉት ሁሉ ያን ያህል ከእውነት የተሰወረ ነገርና ወደ ገሃድና ፊት ለፊት የማይወጣ ነገር የለም ነበር ያለው፡፡ሁሉን በፍቅር በእውነት በግልፅነትና በማስተዋል አደረገ፡፡መቼም እኛ እሱን መቼም ቢሆን ከቶ ለመሆን አንችልም፡፡ግን ቢያንስ እሱን እናስታውሰው፡፡
  Continues .......

  ReplyDelete
 58. UNITY Part-3
  ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ እንዲሉ የራሳችን ያልሆነውንና ብዙም የማይጠቅመንንና የማይሆነንን ነገር ለማግኘት ስንል የራሳችን የሆነውን የሚረባንንና የሚሆነንን ነገር ባለማስተዋል አሳልፈን ሰጥተናል፡፡መልካም የሆነውን መተሳሰብን ፍቅርን ቅንነትን እውነትን ታማኝነትን አንድነትን በሂደት ሳናውቀው ከውስጣችን አስወጥተን በምትኩና በተቃራኒው መጥፎ የሆነውን ራስ ወዳድነትን ጥላቻን ጠማማነትን ሸፍጠኝነትን ከሃዲነትን መለያየትን አንግሰናል፡፡ይህ መጥፎ ነገር የፈጠረው ስር የሰደደ አስተሳሰብና ስሜት በሂደት በእኛ በኢትዮጵውያን ዘንድ ትልቅ መለያየትንና የእርስ በርስ ባዳነትን ፈጥሮብናል፡፡ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ጥራው በለው የተባለው ነገር ሳይሆን ቀርቶ የማይቀየረውን እውነትን ከመጋፈጥና የሚመጣውንም የማይቀር ነገር መጥፎም ይሁን ጥሩ በፀጋ ከመቀበል ይልቅ ይህንን በከንቱ ብልጣብልጥነት በተራ ፕሮፖጋንዳና በሸፍጠኝነት ለመቀየር ነፍሳችን እስክትታክትና እስክትታወክ ድረስ ላይ ታች ስንልና ስንባክን በየቀኑ እየሞትን ያለነው እለታዊ ሞት ከመጨረሻው ከማይቀረው ሞት እጅጉን የከፋ መሆኑን የተረዳነው አይመስለኝም፡፡እስኪ ማናችን ነን ሞትን በብልጣብለጥነት ማምለጥ የምንችል?ነፍሱን ሊያድናት የሚወድ ጭራሹን እሱ ያጠፋታል አይደለምን የተባለውን፡፡ህይወትንስ ከደፋር ከየዋህ ከቀናና ከግልፅ ሰው በተሻለ እውን ፈሪዎች ስግብግቦች በልጣብልጦችና መሰሪዎች ኖረዋት ይሆንን?አንድ መሆን የምንችለው ብዙነታችን ሲከበርም ጭምር ነው፡፡አንድ መሆን የምንችለው ሁላችንም ከየተደበቅንበት ጉሬና ዋሻ ሳናፍርና ሳንሸማቀቅ በግልፅነትና በድፍረት እውነተኛውን መንገድ ተከትለን ወደ እውነተኛው የጋራ መሰብሰቢያ መድረክና አደባባይ ለመገናኘትና ለመሰብሰብ ስንችል ነው፡፡እንደ ንብ አውራ ሁሉ ገዢዎቻችንም እኛን አንድ የሚያደርጉን የእኛ አርዓያና አውራ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡እነሱ እራሳቸውን እንደ ግለሰብ የማያምኑ የሚፈሩና በውስጣቸውም ሰላምና ስምምነት የሌለ ከሆነ ይህንን ወደውም ሆነ ተገደው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሂደት ወደውጪ ወደ ዜጋቸውና ህዝባቸው ማስተላለፋቸውና ማስረፃቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡የአንድ ትልቅ ቤተሰብ እራስ አባወራና እማወራ እንደሆኑት ሁሉ የአንድ ሀገርና ህዝብም ራሶች የተለያዩ የፖለቲካ የሀይማኖትና የሌላም ዋና ዋና መሪዎችና እራሶች ናቸው፡፡እነሱም ከእኛው የወጡ በእኛም ጭምር የተቀረፁ ናቸው እኛም በእነሱ የምንመራና በእነሱ የምንቀረፅ ጭምር ነን፡፡እንደ ዶሮውና እንደ እንቁላሉ አይነት ፊትና ኋላው ብዙም የማይለይ የተሳሰረ ነገር ነው፡፡ጊዚያዊ ጥቅምና ስልጣን ፈልገን ዘላለማዊ የሀገርና የህዝብ አንድነትና(የመንፈስና የአካል) ህልውና ሸርሽረን እንዳይሆን ቆም ብለን እያንዳንዳችን እራሳችንን እንጠይቅ፡፡በዘመነ ግሎባላይዜሽን ላለፉት 20 ዓመታት በራሳችን ላይ የተከናወኑትን ጥሩም ሆነ መጥፎ የተለያዩ አበይት ክንውኖችን ቆም ብለን ገምግመን ምን እንዳጣንና ምን እንዳገኘን በጥሞናና በእውነት ተመስርተን ሂሳብ ልናወራርድ ግድ ይለናል፡፡እረሳችንን ቆም ብለን በእውነትና በድፍረት ልንገመግም ግድ ይለናል፡፡የሚያስማማንና አንድ የሚያደርገን በምክንያት ላይ የተመሰረተ እውነትን በድፍረትና በቀናነት ስንከተል ብቻ ነው፡፡ብዙዎቹ አለመግባባቶች ግጭቶችና መለያየቶች በአይዲሎጂ ወይንም በሀይማኖት ወይንም በዘርና በቋንቋ ወይንም በፆታ ወይንም በሌላ የተለመደ የሚታመን ወይንም የሚሰጥ ምክንያት ብቻ ሳይሆን እንዲያውም በዋናነት እስከ እለተ ሞታችን ድረስ ሚስጥር ከሆነብን ሰው ሆነን ከመፈጠራችን ምንነትና ትርጉም ጋር የተያያዘ ነው፡፡እኛ ፍጡር የሆንን ሰዎች የፈጠረን አምላካችን በህይወታችን ውስጥ በነፃነት የማሰብንና የመንቀሳቀስን (Will power & Freedom) ነፃ ፈቃድ ሃላፊነትን ከመውሰድ ጋር ጭምር በልግስና ሰጥቶናል፡፡ይህ የሰው ልጅ ምን ያህል ትርጉም ያለው ክቡር ፍጡር እንደሆነ የሚያስረዳ ነው፡፡ነገር ግን ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ እንዲሉ ፍጡር የሆነው ሰው በሌላው ተመሳሳይ ፍጡር የሆነ ሰው ላይ ይህንን መሰረታዊና ዘላለማዊ እውነታ እጅጉን በተፃረረ መልክ የራሱን ጠባብና ስግብግብ ፍላጎት ሃሳብና አላማ ያለርህራሄ በጭካኔና በሀይል ወይንም በብልጣብልጥነትና በመሰሪነት ለመጫን ማሰቡ መፈለጉና መንቀሳቀሱ የአለመግባባቶችና የግጭቶች ሁሉ ዋና መሰረታዊ ምንጭ ነው፡፡ግጭትና አለመግባባት ደግሞ ቅራኔንና መለያየትን ስለሚፈጥር የጋራ የሆነ የአንድነት መንፈስን ያዳክማል ወይንም ይገድላል ማለት ነው፡፡ በፖለቲካ አመለካከታችን ተመስርተን ኢህአዲግ ወይንም ወያኔ ወይንም ቅንጅት ወይንም ኦህዴድ ወይንም ኦነግ ወይንም ግንቦት ሰባት ወይንም በዘር በሃይማኖት በቋንቋ ተመስርተን ወይንም በሌላ መልክ አይደለም እውነተኛ ማንነታችንን አግኝተን እውነተኛ መስማማትንና አንድነትን ያን ያህል መመስረት የምንችለው፡፡እውነተኛ አንድነትንና መስማማትን ትርጉም ባለው መልክ ያን ያህል በዘላቂነት መመስረት የምንችለው እነዚህ የሚያቀራርቡን የተለያዩ ነገሮች እንዳሉ ሆነው በተጨማሪ በዋናነትና በመሰራታዊነት ሰው በመሆናችን ብቻ በእውነትና በምክንያዊነት ላይ የተመሰረተ የጋራ የሆነ አስተሳሰብና አመለካከት መከተል ስንችል ጭምር ነው፡፡ማንኛውም ነገር ዝም ብሎ በዘፈቀደና በልማድ ብቻ በፅናት ሊቀጥል አይችልም፡፡ኢትዮጵያዊነትም እንደዚሁ በተለያዩ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ክስተቶች የተነሳ የሚገጥሙት የተለያዩ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ፈተናዎች አሉበት፡፡ስለዚህም አሁንም ይህ ወቅትም እንደዚሁ አንዱ ትልቅ ፈተና ያለበት ወቅትና የታሪክ አጋጣሚ ነው፡፡አንድ የሚያደርገን ኢትዮጵዊነታችን ትርጉሙና ፋይዳው ግልፅ ሊሆንና ሊፀና የሚችለው የተጋረጡበትን የተለያዩ ፈተናዎች በፅናት በትጋት በእውነትና በማስተዋል ተመስርተን እኛ እንደ ዜጋና እንደ ህዝብ ለመቋቋምና ለማዝለቅ ስንችል ብቻ ነው፡፡ኢትዮጵያዊነታችን የአንድነታችን ምልክት መሰረትና ዋልታ ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው በስሜታዊነት ላይ ብቻ ተመስርቶ ሳይሆን በእውነትና በምክንያታዊነትም ላይ በማስተዋል ጭምር ሲመሰረት ነው፡፡
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

  ReplyDelete
 59. Dear Dn Daneil wheather ur saying is convincing or not i don't it is beyond my thinking but by huk or kuk we are thinking one integrated "ETHIIOPIA" and our integrity come through one and only one thing that is RED,Yellow and GREEN flag nothig else and to be with integrity let us pray to our beloved GOD that he can give us the way......

  ReplyDelete
 60. I read most of the comments and they r surprising, because i read the article with positive way, but i think there is something behind. What is all about the relation between Weyane and Dani...is he under cover?? Please don't Dani we don't need to lose u. our difference is not the things tht u mentioned in the article, there is main reason for those happenings , tht is the Tyrant Weyane ,that is all. Pleas u know it , u know why all they did this…and u know its positive result for them….pleas say it !! They did wht all they want to control their power.

  ReplyDelete
 61. and finally i found it ... "Sheger FM"

  ReplyDelete
 62. thank you dani
  that is good idea
  the rulers are very selfish and and racist
  if they think about their history what they make
  they may do better on wards
  thank u

  ReplyDelete
 63. uNITY PART 3
  THE WRITER IS HOPFULL FOR US SO PLEASE START TO WRITE SAME THING LIKE THIS YOU R GOOD WRITTER
  PLEASE COME ON
  tadeyfen@yahoo.com

  ReplyDelete
 64. @ጌታ፥ እኛም ያልነው ለምእራባውያን አሽከር ከሆነውና በዘር ከከፋፈለን ጋር አትሁን ነው። በዘር የሚከፋፍሉትና ባነዳዎችን እንደ አንድ ልዩነት ወስደን እናክብራቸው ማለትህ ያሳፍራል። ይህማ ከሆነ ቅኝ ገዥዎችን ለምን እምቢ አልን? ልዩነት ፈጣሪዎችን ከመቃወምና ከማስወገድ በቀር አንድ በሚያደርገን ጉዳይ ላይ የሚባል ማጭበርበር ቦታ የለውም። ልዩነት ማለት እንዲህ ሀገርን ህልውና ፈጽሞ እንዳልነበረና አዲስ አገር እንመሰርታለን ከሚል ጋር አይደለም። ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አንድ ጊዜ ተሰርታለች በውድም በግድም። አሜሪካንም በውድም በግድም የተሰራ ሀገር ነው። እንገነጠላለን ብለው ያወጁትን ካሮላውያን በግድ በጦርነት ነው እንዲቀላቀሉ የተደረገው።(the beginning of the civil war was denial of secession act of the Carolinas) እንደ አንድ ልዩነት ተገንጣይነትንና አስገንጣይነትን እንውሰድና በጋራ ነገሮች ላይ እንነጋገር አልተባለም። ሊባልም አይገባም። ስለዘህ ጽሑፉ በማር የተለወሰ መርዝ ነው! ከጣልያን ጋር አንድ በሚያደርጉን እንደ መንገድ ስራ ድልድይ ስራ ወዘተ መደራደር ነበረብን? መጀመሪያ አገራችንን መልቀቅ ነበረበት በውድም በግድም። አሁንም ያመው ነው።

  ReplyDelete
 65. Hy,Dani, your idea is very nice but the expression which you said supporting from heart and opposing from stomatch is not appropriate. There are many persons whom I Know supporting TPLF for stomach. the other issue is ok.

  ReplyDelete
 66. ሐዋሪያነት ከሰንደቃላማዉ ይበልጥ ክርስቶስን መስበኩ መልካም አይመስልም? ክርስቶስን ከአወቅን በአንድ መንፈስ:በአንድ ሀገርነት ባንድራዉን እናነሳለን !!!
  1 ቀድም የነበረዉ ባንድራ ምን ይመስል ነበር? ያኔ የሁሉም ብሔረሰብ አባቶች አጥንት የተከሰከሰለት ባንድራ?
  ያኔ መህመድ፣ገመቹ፣በላቸዉ፣ተክላይ፣ኡጇሉ,,,የሞቱለት?
  2 በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙት የእምነት ተቋማት በሙሉ ባንድራዉን ይቀበሉታል? ይህ በአንድ ሀገር ላይ ለሚኖር ዜጋ ወሳኝ የሆነ የሀገርነት ፍቅር/ባንድራ/ መገለጫ ይመስለኛል

  ReplyDelete
 67. We all should work in to that hardly

  ReplyDelete
 68. dani good view....keep it up. you have the right to express your view .....don't follow such pessimist peoples idea. thank's for sharing us your view.

  ReplyDelete
 69. tiliku beshita yihe new !!

  ReplyDelete
 70. DANIEL KIBRET.....Dehna neh stihfochih yamralu gin min alebet kewegenawinet stedteh lemestaf bitmokr?

  ReplyDelete
 71. "ልዩነቶቻችንን በተመለከተ አንብበን፣ ተርጉመን፣ ምሥጢር አደላድለናል..." I hate this statment. liyunetochachin andinetachin lay tesieno sayadersu sikeru new andinet linoren yemichilew.

  ReplyDelete
 72. As idea it so interesting. But our unity comes from the real aceptence of difference. The writer still hopes that unity should be miantianed with the same way of before 50 or 40 yeas back. which comes first? humanity or nationality? if nationality goes agianst my humanity I hate to be ethiopian. The pro Ethiopianism ideology lacks such understanding. If you work for "ethiopia" ignoring my humanity still I prefer to say I am east African rather that saying Ethiopian. If ethiopia is built on the expense of humanity and personality, what is nation, ethiopia and.......... do mean?

  ReplyDelete
 73. please invite me to the meeting.

  ReplyDelete