Monday, August 22, 2011

አይ ጋዳፊ i


ይህን ጽሑፍ ቨርጂንያ አሌክሳንድርያ ዱክ መንገድ አጠገብ ከሚገኘው የወዳጄ የአካሉ ዮሴፍ ቤት ሆኜ ስጽፍ የኮሎኔል ጋዳፊ የሥልጣን ፀሐይ ለመጨረሻ ጊዜ በማቆልቆል ላይ ነበረች፡፡

ዐማጽያኑ ወደ ዋና ከተማዋ ወደ ትሪፖሊ ገብተው ከተማዋን በመቆጣጠር ላይ ናቸው፡፡ ሁለት የደቡብ አፍሪካ አውሮፕላኖች በዋና ከተማዋ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ እንደቆሙ አሉ፡፡ ሁለቱ ጋዳፊ  ልጆች ተይዘዋል፡፡ የቤንጋዜ ሕዝብም ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ታሪክ በማየት ላይ ነበር፡፡
ዓለማችን ከፈርዖን በፊትም ሆነ በኋላ አያሌ አምባገነኖችን አስተናግዳለች፡፡ በተለያየ መንገድ የሚገዙ፣ የተለያዩ ጠባያት ያሏቸው አምባገነኖች፡፡ ሁሉንም ግን አንድ ነገር አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ አምባገነኖች ከእነርሱ በፊት ከነበሩት አምባገነኖች ውድቀት አለመማራቸው፡፡
ጋዳፊ እንኳን በቅርቡ ከቱኒዝያው እና ከግብጹ አምባገነኖች መማር ይችሉ ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው አምባገነኖች ያማርራሉ እንጂ አይማሩም፡፡
እኤአ 1969 የጀመረው የጋዳፊ የአምባገነንነት ዘመን ሰዓታት ቀርተውታል፡፡ ጋዳፊ ለሊቢያ ልቧም፣ ሳንባዋም፣ ጭንቅላቷም፣ ጉበቷም፣ ጥርሷም ምላሷም ሆኖ ከአርባ ሁለት ዓመት ኖረ፡፡ ያለ እኔ ሊቢያ ልትኖር አትችልም ብሎ የፈጣሪ ያህል ታበየ፡፡ እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ገል ቀጥቅጦ ገዛ፡፡
እነሆ ግን ዘመኑ በማለቅ ላይ ነው፡፡ ለሌች እሱን መሰል አምባገነኖችን «በሉ ደኅና ሁኑ፣ ከኔም ተማሩ» እያለ በመሰናበት ላይ ነው፡፡ ችግሩ አምባገነኖች ከመሰሎቻቸው ውድቀት አይማሩም እንጂ፡፡
ለረዥም ዘመን መቆየት፣ ጠንካራ ወታደራዊ ተቋም መመሥረት፣ በገንዘብ መናጠጥ ለአምባገነኖች ዋስትና እንደማይሆናቸው ነው አሁን ሁሉም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እያሳዩ ያሉት፡፡ ሊቢያውያን የምግብ ረሃብ አልነበራቸውም፣ በሀገራቸውም የውጭም የርስ በርስም ጦርነት የለም፡፡ ሕዝባቸው በዝቶ ቦታ አልጠበባቸውም፡፡ ቢበዛ ስድስት ሚሊዮን ናቸው፡፡
እነርሱን የራባቸው ነጻነት ነው፡፡ ኅሊናዊ ነጻነት፡፡ ሰው እንስሳ አይደለም፡፡ እንስሳ ከበላ ከጠጣ እና ከተመቼው በቃው፡፡ ሰው ግን በመብላት እና በመጠጣት ብቻ የሚረካ አይደለም፡፡ ሰው ዐዋቂት፣ ተናጋሪ፣ እና ሕያው ነፍስ አለቺው፡ ዐዋቂ ናትና መመራመር፣ ማሰብ ትሻለች፡፡ ነባቢት ናትና መናገር፣ ሃሳቧን በነጻነት መግለጥ ያምራታል፤ ሕያዊት ናትና የመኖር ዋስትናዋ እንዲጠበቅ ትፈልጋለች፡፡
ለዚህ ነው ሊቢያውያን ከአምስት ወራት በፊት በነፍስ ወከፍ መሣርያ የታጠቀውን የጋዳፊ ቅልብ በጦር የገጠሙት፡፡
ብልህ ከሌላው ይማራል፤ ሞኝ እና አምባገነን ግን ከራሱ ውድቀትም አይማርም፡፡
@ 2.04 Libyan time

26 comments:

 1. ሠላም ዲ/ን ዳንኤል! ግምገማህ ግሩም ነው፤ የኛዎቹ ከዚህ ቢማሩ መልካም ነበር። ከላይ አንድ ቦታ ላይ ስትገልጽ "ሁለቱ የሳዳም ሁሴን ልጆች ተይዘዋል፡፡" ብለሃል። በእርግጥ የሳዳም ናቸው ወይስ የጋዳፊ? ሳዳም ሁሴን እዛ ልጆች እንዳሉት ስላላወኩ ነው። በተረፈ፣ ዲሲ አካባቢ ስላለሁ ፈቃደኛ ከሆንክ መገናኘት እንችላለን። መልካም የፍልሰታ በዓል ይሁንልህ!
  ይህንን መልዕክት ፖስት አታድርገው!

  ReplyDelete
 2. Nice story, Dani. You just made it clear that in every little detail, there is something we learn...

  BTW, You said the two Sons of Sadam. I guess you meant Gadafi's Sons?

  ReplyDelete
 3. Hi, dani that's a nice aricle,,,,,,,,,keep it up
  MAY GOD BLESS U to live many many years,,,,,,,
  gebregzabher, Atlanta, GA

  ReplyDelete
 4. Dear Daniel,

  I recall your mindful interview to Ghadaffi article. Let him rest in peace.

  ReplyDelete
 5. diaqon daniel i admire you a lot. what you write in many issues gives me knowledge and more ever your preaches too.i personally believe that in Africa, leaders does not want to learn from others. it is enough to see our country. i say eprdf build dam on abay so that they should build date for their worthless regime.i don't want eth. be Libya. let our God protect, teaches and gives you long life.

  ReplyDelete
 6. Dear decon Daniel,

  i really appreciate your thoughts, article& writings always may GOD gives to u & your family joy, happiness,& peace always.
  wishing u all the best............

  ReplyDelete
 7. Nigusie Dz
  Hi Dn.Dani it is anice article and evaluation keep it! Happy Filseta

  ReplyDelete
 8. ውይ ዳኒ
  ለካ ሕዝቡ ሥራ ነጻነት አጥቶ ነው እንዲህ ሕይወቱን ጭምር የሰጠው ወይኔ እኔ መች አወቅሁልህ! የግሪክ አማልክት ከወደቁበት ተነሥተው ይፍረዱብኝ! በዚህ ዓይነት ጋዳፊ ብቻ ሳይሆን ቤንዓሊም፣ ሙባረክም የተባረሩት ሕዝባቸውን ነጻነት አሳጥተው በማፈናቸው ነበር ለካ፡፡ ወይኔ! አላወቅሁም ነበር፡፡ ሕዳሴን ስልህ!
  እኔ የምከታተለው የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚነግረኝ ሕዝቡ ሥራ በማጣቱ የተነሣ ተስፋው እንደጨለመ፣ አምባገነኖቹም ሀገሪቱን እንደ ግል ርስታቸው እንዳሻቸው ሲበዘብዟት በመኖራቸውና የሕዝቡን ኑሮ በሕዳሴያዊ ስትራቴጂ ማለምለም ባለመቻላቸው እንደተንኮታኮቱ ነው፡፡ ዴሞክራሲ ጠየቁ፤ የኅሊና ነጻነት አማራቸው… ምናምን የሚል ነገር እኔ የምከታተለው የቴሌቪዥን ጣቢያ አያወራም፡፡ እኔ ከእማዬ ሬድዮ የተነገረኝ ሰዉ በሥራ አጥነት ስለተሰቃየ እንዳመጸ ነው፡፡ ከምር!
  ለካ ጉዳዩ እንደሰው መቆጠር፣ እንደ ሰው በኅሊና ነጻነት አሸብርቆ መኖር፣ “እንዲህ ብለህ የተናገርኸው እንዲህ ስላሰብህ ነው፡፡” እያሉ ሐሳቡን በሐሳባቸው እየተነተኑ ከሚነተርኩት ሰዎች መገላገል ኖሯል፡፡ ወይ ጉድ! ያ በየጣራው ላይ የሚሰቀል የወሬ ድስት ያላቸው ሰዎች እንዴት ብጹዓን ናቸው ጃል!
  በነገራችን ላይ አምባገነኖች ከሚጋሯቸው ጠባያት አንዱ ራሳቸውን የሀገሪቱ ምሶሶና ማገር፣ ጣራና ግድግዳ አድርገው ማሰባቸው ይመስለኛል፡፡ በእነርሱ አእምሮ ውስጥ እነርሱ ወይም የእነርሱ ፈላጭ ቆራጭ ቡድኖች ከሌሉ ሀገሪቱ “ያልቅላታል”፡፡ ሀገሪቱ ከእነርሱ በፊት “እንዳልነበረች” ሁሉ ከእነርሱ በኋላም መኖር “ያቅታታል”፡፡ ምክንያቱም ሀገሪቱን ጠፍጥፈው የፈጠሯት እነርሱ ናቸዋi በዙሪያቸው የሚሰበስቧቸው እበላ ባይ አቆላማጮቻቸውም ይህንን የእነርሱን ፉከራ “አሜን! አሜን! አሜን!” እያሉ ስለሚያዳምቁላቸው የራሳቸው አስተያየት እውነት መስሎ ይሰማቸዋል- “ሕዝቡ” ተቀብሎታላi “ሕዝቡ” “አሜን!” ካለ ወዲያ ም የሚጠራጥር ነገር ይኖራልi
  አምባገነኖቹን እንደተሳሳቱ የሚነግራቸው ወይም ሊነግራቸው የሚሞክር ሰው የመጀመሪያው ዱላ የሚሰነዘርበት ከአቆላማጮቹ ነው- ጥቅማቸው ይነካልና፡፡ ሥልጣናቸው፣ በሙስና የተገነቡት ፎቆቻቸው፣ የሚንደላቀቁበት ኑሮ በሙሉ እነርሱ ከአምባገነኖቹ ጋር ተጠግተው “የድርሻቸውን በመውሰዳቸው” እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ስለዚህም ይህንን ጥቅማቸውን ለመከላከል የማያደርጉት ነገር የማይፈነቅሉት ደንጊያ አይኖርም፡፡ የሞራል ብቃት፣ ሰብአዊነት፣ ኅሊና፣ ወዘተ. በእነርሱ ዘንድ ቦታ የላቸውም፡፡ በእነርሱ ዘንድ እጅግ አስፈላጊው ነገር ጥቅም ነው፡፡ በየትኛውም መስክ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ- ሌሎችን በመረጋገጥም ቢሆን! ሀገሪቱን የሚጠቅም ነገር ማለት እነርሱ ቤት የሚገባ ጥቅም የሚስገኝ ነገር ማለት ነው፡፡ በቃ! ከዚያ በኋላ ለአለቆቻቸው ሪፖርት ማዘጋጀት ነው፡፡ አለቆቻቸው እንደሆነ ከዓይናቸው ይልቅ “ሕዝባቸውን” እንደሚያምኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ ሕዝቡ የተቸገረው ዘይት ተወድዶበት ብቻ ነው፡፡ ስኳር አልቆበት ብቻ ነው፡፡ ሥራ አጥቶ ብቻ ነው፡፡ ነጻነቱንማ ከተቀዳጀ እነሆ ዓመታት ተቆጠሩ!

  ለሁለተኛ ጊዜ በነገራችን ላይ ልበልና፣ አምባገነኖችን የሥነ ልቡና ባለሙያዎች ቢያጠኗቸው ምን የሚያገኙባቸው (ላቸው/ ልን) ይመስላችኋል?

  ReplyDelete
 9. Propaganda & Truth !!!
  ልጅ ዳንኤል ማንም ሰው አምባገነንነትን አይፈለግም ከራሳቸው ከአምባገነኖቹ በስተቀር ፡፡በፅሁፍህም ላይ የፃፍካቸው በግርድፉ ሲታዩ እውነትና ትክክል ይመስላሉ፡፡ነገር ግን አለም ከምንጊዜውም በላይ በተራ ፕሮፖጋንዳ የተወናበደበትና እውነት የሚመስል ውሸት የነገሰበት የታሪክ አጋጣሚ አሁን ይመስለኛል፡፡እውነትና ሀሰት ተደበላልቀው ሰምና ወርቅ ሆነዋል፡፡በእርግጥ እውነትና ንጋት እያደር እንዲሉ ሁሉንም ነገር ወደፊት ጊዜ እየመነጠረ ገሀድ ያወጣዋል፡፡ሰዎችም ልብ ያለንና ከታሪክ የምንማር ከሆነ እንማራለን፡፡እኔ በመሰረቱ ጋዳፊንም ሆነ አንባገነንነትን አልደግፍም፡፡የሊቢያ ጉዳይ ግን አንተ እንዲህ አቃለህ አምባገነን ወዘተ በሚሉ በተከሸኑ የተለመዱ ቃላት ልታቀርበው እንደፈለከው ባለ ተራ ጉዳይና የቀለለ እይታ ያለው አይደለም፡፡ምናልባት ሰዎች ነገሮችን የምንተረጉምበትና የምንረዳበት እይታ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡አንተ ስለሊቢያና ስለጋዳፊ ንቃተ-ህሊናህ የፈቀደልህን ያህል ይህን ብለሃል፡፡
  ነገሮችን በተለየ መልኩ የሚያዩና የሚተረጉሙ ጥቂቶች ሌሎች ሰዎች ግን ምን እንደሚሉ አንተም ሆንክ ሌሎች ብዙሀኑ እንዲሰሙና እንዲረዱ ድፍረቱ ቀናነቱና እውነተኛነቱ ካለህ ግን የሚከተለውን የመረጃ ምንጭ በቀናነት በጥሞና እንዲነበብ እጠቁማለሁኝ፡፡
  http://www.globalresearch.ca/index.php?context=va&aid=25637
  http://www.globalresearch.ca/index.php?context=va&aid=24471
  http://www.globalresearch.ca/index.php?context=va&aid=24527

  ReplyDelete
 10. "ሁለቱ የጋዳፊ ልጆች ተይዘዋል፡፡ የቤንጋዜ ሕዝብም ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ታሪክ በማየት ላይ ነበር፡፡"

  ሳዳም የሚል አላገኘሁም። ከየት አነበባችሁ?

  ReplyDelete
 11. እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል!!!!!!!!!!!
  GB

  ReplyDelete
 12. እሳቱም ይኸው ውሃውም ይኸው እጅህን የፈለግህበት ክተት ነው ያለው ቅዱስ መፅሀፍ፡፡
  የሊቢያ ህዝብ ምርጫ ቀርቦለታል እጁን የፈለገው ቦታ እንዲከት ማለት ነው፡፡
  ሌላውስ 3ኛው ዓለም ከዚህ ምን ይማራል?ልብ ያለው ልብ ብሎ ያስተውላል፡፡
  ነገር ግን በህይወት ውስጥ ዝም ብሎ ምርጫ ብቻ የሚባል ነገር የለም፡፡
  ማለትም በምናደረግው ማንኛውም ምርጫ ለሚከተለው ማንኛውም ነገር ሁሉ ሃላፊነት መውሰድም ጭምር ግድ እንደሚል ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ከታሪክ እንደምንማረው ህዝብ የሚባለው ነገር ብዙውን ጊዜ በብልጣብልጦችና አፈ ጮሌዎች ያማሩ አማላይ ቃላቶች ዘወትር ሲታለል እንደኖረ ነው የምንማረው፡፡አንድ ወቅት በታላቋ ሶቭየት ህብረት መፈረካከስ መውደቅና ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ በዘመነ ሶሻሊዝም የነበረውን በማስታወስ የራሺያ ህዝብ እንዲህ አለ ሲባል ሰምቼ ነበር፡፡
  በዘመነ ሶሻሊዝም አፋችንን እንደፈለግን መክፈት(መለፍለፍ)አንችልም ነበር ነገር ግን ወደ አፋችን የምንከተው(የምንበላው) ብዙ ነገር ነበረን፡፡አሁን በዘመነ ዲሞክራሲ ግን አፋችንን እንደፈለግን መክፈት እንችላለን ወደ አፋችን የምንከተው(የምንበላው)ነገር ግን ምንም የለንም፡፡ይህ እንቆቅልሽ ምንድን ነው?
  እንደኔ አስተሳሰብና ፍላጎት ግን ከሁለተኛው የበፊቱን እመርጣለሁኝ፡፡ሌላ ብልጥ የሆነ ሰው ደግሞ የለም ሁለቱንም አንድ ላይ ማግኘት እፈልጋለሁኝ ሊል ይችላል፡፡ቢሆንማ እኔስ መች እጠላለሁኝ፡፡ነገር ግን ሁለቱንም ማድረግ ግን የተጨባጩ አለም የሚፈቅደው ትክክለኛ እውነታ ነዎይ ግለሰቡ ምርምሮ ይድረስበት፡፡ጊዜና እድሜ እስከሰጠን ድረስ የሊቢያንም ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡አሁን ከወሰደው ምርጫና እርምጃ አንፃር ወደፊት ምን ይላል ወደፊት በጊዜ መነፅር የሚታይ ይሆናል፡፡ይህ ዲሞክራሲ የሚባለው ነገርና የተጨባጩ አለም የሚፈቅደው ትክክለኛ እውነታ ምንድን ነው?ይህ የዘመኑ ትውልድ የተጋረጠበትና ወቅቱ ያቀረበለት ሊያልፈው የማይችለውና መልስ ሊሰጠው የሚገባው ከባዱ ወሳኝ ጥያቄና እንቆቅልሽ ነው፡፡አዙሮ ማየቱና ማስተዋሉ ከጠፋማ በዲሞክራሲያዊ መንገድም እኮ የራስን ጥፋትና ውድቀት ማፋጠን ይቻላል፡፡ዲሞክራሲ ግን እንደ ምግብ ቤት ሜኑ ወይንም እንደ ሱቅ እቃ ወይንም ሸቀጥ በምርጫዎት “ምን ይምጣልዎት የኔ ጌታ” ወይንም “ምን ይምጣልዎት” የኔ እመቤት ተብለው ለማንኛውም ሰው እንደፈገው በምርጫዎ የሚቀርብልዎት ነገር ነው እንዴ?በሜኑ ላይ ያለውን ምግቡን ወይንም የሱቁን ሸቀጥ እኮ ማማረጥ የሚያስፈልግህና የምትችለውም እኮ በኪስህ ገንዘብ እስካለህና መግዛት እስከቻልክ ድረስ ብቻ ነው፡፡የሚገርመው እኮ የምትበላው ምግብና የምትገዛው እቃም አኮ ደረጃውና ጥራቱ እንደየቦታው እንደ ኪስህ አቅም ይለያያል፡፡በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ አሉ አበው፡፡ይህ ህዝብ ግን ዲሞክራሲ በሚባለው ከወደ ምእራብ የመጣ መጤ ጅኒ መቼና እንዴት እንደተለከፈ ከቶ ላውቀው አልቻልኩኝም፡፡ግን ከዚህ ጅኒስ የሚያላቅቀውና ፈውስ የሚሰጠው መድሀኒት ወይንም ፀበል ያገኝ ይሆንን? ይቺ ናት ዲሞክራሲ ቂቂቂቂቂቂቂቂ

  ReplyDelete
 13. እሳቱም ይኸው ውሃውም ይኸው እጅህን የፈለግህበት ክተት ነው ያለው ቅዱስ መፅሀፍ፡፡
  የሊቢያ ህዝብ ምርጫ ቀርቦለታል እጁን የፈለገው ቦታ እንዲከት ማለት ነው፡፡
  ሌላውስ 3ኛው ዓለም ከዚህ ምን ይማራል?ልብ ያለው ልብ ብሎ ያስተውላል፡፡
  ነገር ግን በህይወት ውስጥ ዝም ብሎ ምርጫ ብቻ የሚባል ነገር የለም፡፡
  ማለትም በምናደረግው ማንኛውም ምርጫ ለሚከተለው ማንኛውም ነገር ሁሉ ሃላፊነት መውሰድም ጭምር ግድ እንደሚል ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ከታሪክ እንደምንማረው ህዝብ የሚባለው ነገር ብዙውን ጊዜ በብልጣብልጦችና አፈ ጮሌዎች ያማሩ አማላይ ቃላቶች ዘወትር ሲታለል እንደኖረ ነው የምንማረው፡፡አንድ ወቅት በታላቋ ሶቭየት ህብረት መፈረካከስ መውደቅና ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ በዘመነ ሶሻሊዝም የነበረውን በማስታወስ የራሺያ ህዝብ እንዲህ አለ ሲባል ሰምቼ ነበር፡፡
  በዘመነ ሶሻሊዝም አፋችንን እንደፈለግን መክፈት(መለፍለፍ)አንችልም ነበር ነገር ግን ወደ አፋችን የምንከተው(የምንበላው) ብዙ ነገር ነበረን፡፡አሁን በዘመነ ዲሞክራሲ ግን አፋችንን እንደፈለግን መክፈት እንችላለን ወደ አፋችን የምንከተው(የምንበላው)ነገር ግን ምንም የለንም፡፡ይህ እንቆቅልሽ ምንድን ነው?
  እንደኔ አስተሳሰብና ፍላጎት ግን ከሁለተኛው የበፊቱን እመርጣለሁኝ፡፡ሌላ ብልጥ የሆነ ሰው ደግሞ የለም ሁለቱንም አንድ ላይ ማግኘት እፈልጋለሁኝ ሊል ይችላል፡፡ቢሆንማ እኔስ መች እጠላለሁኝ፡፡ነገር ግን ሁለቱንም ማድረግ ግን የተጨባጩ አለም የሚፈቅደው ትክክለኛ እውነታ ነዎይ ግለሰቡ ምርምሮ ይድረስበት፡፡ጊዜና እድሜ እስከሰጠን ድረስ የሊቢያንም ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡አሁን ከወሰደው ምርጫና እርምጃ አንፃር ወደፊት ምን ይላል ወደፊት በጊዜ መነፅር የሚታይ ይሆናል፡፡ይህ ዲሞክራሲ የሚባለው ነገርና የተጨባጩ አለም የሚፈቅደው ትክክለኛ እውነታ ምንድን ነው?ይህ የዘመኑ ትውልድ የተጋረጠበትና ወቅቱ ያቀረበለት ሊያልፈው የማይችለውና መልስ ሊሰጠው የሚገባው ከባዱ ወሳኝ ጥያቄና እንቆቅልሽ ነው፡፡አዙሮ ማየቱና ማስተዋሉ ከጠፋማ በዲሞክራሲያዊ መንገድም እኮ የራስን ጥፋትና ውድቀት ማፋጠን ይቻላል፡፡ዲሞክራሲ ግን እንደ ምግብ ቤት ሜኑ ወይንም እንደ ሱቅ እቃ ወይንም ሸቀጥ በምርጫዎት “ምን ይምጣልዎት የኔ ጌታ” ወይንም “ምን ይምጣልዎት” የኔ እመቤት ተብለው ለማንኛውም ሰው እንደፈገው በምርጫዎ የሚቀርብልዎት ነገር ነው እንዴ?በሜኑ ላይ ያለውን ምግቡን ወይንም የሱቁን ሸቀጥ እኮ ማማረጥ የሚያስፈልግህና የምትችለውም እኮ በኪስህ ገንዘብ እስካለህና መግዛት እስከቻልክ ድረስ ብቻ ነው፡፡የሚገርመው እኮ የምትበላው ምግብና የምትገዛው እቃም አኮ ደረጃውና ጥራቱ እንደየቦታው እንደ ኪስህ አቅም ይለያያል፡፡በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ አሉ አበው፡፡ይህ ህዝብ ግን ዲሞክራሲ በሚባለው ከወደ ምእራብ የመጣ መጤ ጅኒ መቼና እንዴት እንደተለከፈ ከቶ ላውቀው አልቻልኩኝም፡፡ግን ከዚህ ጅኒስ የሚያላቅቀውና ፈውስ የሚሰጠው መድሀኒት ወይንም ፀበል ያገኝ ይሆንን? ይቺ ናት ዲሞክራሲ ቂቂቂቂቂቂቂቂ

  ReplyDelete
 14. Dear deacon Daniel,

  Somewhere in all of us at one time or another as a fellow human being on this earth there is a desire to help and do something that we think will help make society better. Beyond all desires of man, there is a profound call of certain men to preach the gospel of Jesus Christ for the saving of the soul of man. This duty requires passionate dedication in its occupations. Therefore, it leaves no room for any other concern. It is clear that as men of God, the man of God cannot assume the office of the politician for reasons of his dedication to his call. Furthermore, there are a few rational explanations of why he cannot hold such office. The most noticeable explanation is the origin of the rise to the positions of the preacher and the politician. Both positions are with the people. The politicians are sent and speak for the people while the man of God is sent by Christ and speaks to the people. The politician is forbidden to speak freely for God, and speaks only in behalf of the people he represents. The man of God, on the other hand, is required to speak only of the things of God to the people the Lord has sent to him.

  The politician carries the desires and the concerns of his constituents while the preacher carries the word and commands of the Lord. In both positions there is no room for personal opinions. The politician must speak the interest of his constituents. The man of God is required by the Holy Ghost to speak the interest and desires of no one but the one that sent him; no not even his own interests and opinions. "Jesus said to them, my meat is to do the will of him that sent me, and to finish his work." St. John 4:34; 5:30; 6:38; not the will of the people. The man of God must keep himself in position with the Lord to save the people and to prepare them for his soon coming.

  Tazabiw from VA,

  ReplyDelete
 15. it is really nice

  '....እነርሱን የራባቸው ነጻነት ነው፡፡ ኅሊናዊ ነጻነት፡፡ ሰው እንስሳ አይደለም፡፡ እንስሳ ከበላ ከጠጣ እና ከተመቼው በቃው፡፡ ሰው ግን በመብላት እና በመጠጣት ብቻ የሚረካ አይደለም፡፡ ሰው ዐዋቂት፣ ተናጋሪ፣ እና ሕያው ነፍስ አለቺው፡ ዐዋቂ ናትና መመራመር፣ ማሰብ ትሻለች፡፡ ነባቢት ናትና መናገር፣ ሃሳቧን በነጻነት መግለጥ ያምራታል፤ ሕያዊት ናትና የመኖር ዋስትናዋ እንዲጠበቅ ትፈልጋለች....' this paragraph should be read by all afican leaders cause it may click their mind from...

  ReplyDelete
 16. yalafoten ambaganen manegeste tareke ayanabome beanaboma enkone baseletane lamakoyate kareto seletanen yetalote nabare

  ReplyDelete
 17. እንደኔ አስተሳብና እንደተሞክሮየ በአብዛኛው 5 ዓይነት አገዛዞች አሉ፡፡እነሱም በተወሰነ መልክ በአጭር በአጭሩ እንደሚከተለው ናቸው፡፡

  የመጀመሪያዎቹ ጭልጥ ያሉ አምባገነኖችና አረመኔ ጨካኞች ኛቸው፡፡እነዚህ እንደወረደ የሚባሉትና በዘመነ ባርባሪዝም ያሉ አይነት ይመስላሉ፡፡እነዚህኛዎቹ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ምንም አይነት ፍቅርና አክብሮት የላቸውም፡፡ህዝባቸውን ያደኸያሉ ይጨቁናሉ ያሰቃያሉ ይዘርፋሉ ወዘተ ወዘተ.ህዝባቸውም እንደዚሁ ለነሱ ከፍርሃት ውጪ ምንም አይነት ፍቅርና አክብሮት የለውም፡፡

  ሁለተኛዎቹ መካከለኛ አምባገነኖች ናቸው፡፡እነዚህኛዎቹ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ፍቅርና አክብሮት አላቸው፡፡ህዝባቸውና ሀገራቸው እንዲበለፅጉና በነፃነት ተከብረው እንዲኖሩ ይፈልጋሉ፡፡የሀገራቸውንና የህዝባቸውን ብሄራዊ ጥቅምና ነፃነት ለሌላ አሳልፈው መስጠት ፈፅሞ አይፈልጉም፡፡ስለዚህም በቀናነት ለራሳቸው ያመኑበትን ነገር ከማስፈፀም ወደኋላ አይሉም፡፡ያልሆኑትን ሆነው ለመታየት አይፈልጉም ወይንም ዲሞክራሲ ገለመሌ እያሉ በከንቱ አይቀባጥሩም አይወሻክቱም፡፡እነዚህኛዎቹ አምባገነኖች ትንሽ ቢዘርፉም እንኳን እራሳቸውን በሚጠቅም መልኩ እንጂ ከዚያ አልፎ ተርፎ ያን ያህል ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ክፉኛ በሚጎዳ መልኩ አይደለም፡፡ስለዚህም እነዚህን አምባገነኖች ህዝባቸውም እንደዚሁ ይወዳቸዋል ያከብራቸዋል፡፡ቢያንስ አይዋሹምና እንዲሁም ለቃላቸው ታማኝ ናቸውና፡፡

  ሶስተኛዎቹ አምባገነኖች እጅግ በጣም መሰሪና ውሸታም ናቸው፡፡እነዚህኛዎቹም እንደ መጀመሪያዎቹ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ምንም አይነት ፍቅርና አክብሮት የላቸውም፡፡ህዝባቸውን ያደኸያሉ ይጨቁናሉ ያሰቃያሉ ይዘርፋሉ ወዘተ ወዘተ፡፡ህዝባቸውም እንደዚሁ ለነሱ ከፍርሃት ውጪ ምንም አይነት ፍቅርና አክብሮት የለውም፡፡ከመጀመሪያዎቹ ልዩነታቸው ዘመናዊ በሆነ መልኩ እጅግ በጣም ሸፍጠኛ ውሸታምና መሰሪ መሆናቸው ነው፡፡ያልሆኑትን ሆነው ለመታየት የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ህዝባቸውንና ሌላውን አለም ለማታለል ዲሞክራሲ ምርጫ ወዘተ እያሉ ለማደናገር ይፈልጋሉ፡፡ግን ምርጫቸውም ሆነ ዲሞክራሲያቸው ስልጣናቸውን በየተወሰነ አመት የሚያሳድሱበትና ህጋዊ የሚያደርጉበት እጅግ ሲበዛ የውሸት ድራማ ነው፡፡

  አራተኛዎቹ ደግሞ በተወሰነ መልኩ ለህዝባቸውና ለሀገራቸው ፍቅርና አክብሮት ያላቸው ናቸው፡፡
  ህዝባቸውና ሀገራቸው እንዲበለፅጉና በነፃነት ተከብረው እንዲኖሩ ይፈልጋሉ፡፡አሁን በዘመኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ነው ተብሎ በብዙሀኑ የሚታሰበውንና የሚታመነውን የተለመደውን ምርጫና ዲሞክራሲን ለህዝባቸው ያቀርባሉ፡፡ማለፍ የማይገባቸውን ቀይ አደገኛ መስመር እስካላለፉና ትልቅ አደጋና ስጋት መፍጠር እስካልቻሉ ድረስ ተራ ዜጎቻቸው እንደፈለጉ እንዲናገሩ እንዲለፈልፉና ስሜታቸውን እንዲገልፁ እድሎችን በተለያዩ መልኮች ያመቻቻሉ፡፡ በየተወሰነ ጊዜም የስልጣን ባለቤትነት በምርጫ ይቀያየራል፡፡ነገር ግን እነዚህ አገዘዞች ህዝባቸውን በረቀቀ መንገድ በማታለል ደረጃ እጅግ ሲበዛ ብልጦችና መሰሪዎች ናቸው፡፡ለስሙ ለይምሰል ምርጫ እያካሄዱ ስልጣንን ቢያቀያይሩም ኖሮ ዞሮ ዞሮ ግን ሁልጊዜ በፖሊሲዎቻቸውና በመመሪያዎቻቸው በረቀቀ መንገድ ከበስተጀርባ የሚያስፈፅሙት በምርጫ ሰሞን ቃል የገቡለትን የብዙሀኑን ህዝባቸውን ፍላጎትና ጥቅም ሳይሆን በዋነኝነትና በቀዳሚነት የጥቂት ሀብታሞችን(Establishment Elite) ፍላጎትና ጥቅም ነው፡፡ስለዚህም ብዙሀኑን ዜጎቻቸውን ባማሩና አማላይ ቃላትና ተስፋ ብቻ እየሸነገሉ ድህነትና ችግር ውስጥ ሊከቱ ይችላሉ፡፡

  አምስተኛዎቹ ደግሞ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ከፍተኛ ፍቅርና አክብሮት አላቸው፡፡ህዝባቸውና ሀገራቸው እንዲበለፅጉና በነፃነት ተከብረው እንዲኖሩ ይፈልጋሉ፡፡ትክክለኛ ፍትህን ነፃነትን ዲሞክራሲንና ምርጫን ያለመሸራረፍ ለህዝባቸው ያሰፍናሉ፡፡የሀገራቸውንና የህዝባቸውን ብሄራዊ ጥቅምና ነፃነት ለሌላ አሳልፈው መስጠት ፈፅሞ አይፈልጉም፡፡በዚህ የተነሳም ህዝባቸው ለእነዚህ መሪዎች እንደዚሁ ከፍተኛ ፍቅር እምነትና አክብሮት አለው፡፡በላባቸው ደክመው ከፈጠሩት የራሳቸው ሀብት ውጪ በሙስናም ሆነ በሌላ መለኩ የህዝብና የሀገር ሀብት አምስት ሳንቲም መንካት አይፈልጉም፡፡የእነዚህ መሪዎች የመጨረሻ እርካታ የራሳቸው የዜጋቸው የህዝባቸው የሀገራቸው ደህንነትና ሰላም ተጠብቆ በነፃነት በሰላም በፍቅር በብልፅግና በአንድነት ተስማምቶ መኖር ነው፡፡


  ከላይ ከተራ ቁጥር አንድ እስከ አራት ያሉትን ሁሉ እስከዛሬ አለማችን አስተናግዳለች አሁንም እያስተናገደች ነው፡፡ነገር ግን በተራ ቁጥር አምስት ያለውን ግን ገና አላስተናገደችም፡፡ወደፊትም እስከምፅአት የምታስተናግድ አይመስለኝም፡፡አምስተኛው አይነት አገዛዝ የዚህ አለም ብዙሀን የዋሆች በምናባችን የሳልነውና ውስጣችን የተጠማው አይነት ነው፡፡አንዳንዶችም ይህንን እናመጣለን እያሉ ያለውን ለመጣል ላይ ታች እያሉ ነው፡፡አንዳንዶች በዚህ የቅዠት አለም(Fantasy or Illusion) ውስጥ ያሉና ሌላውንም በተመሳሳይ መልክ ለመክተት የሚፈልጉ አሉ፡፡

  ReplyDelete
 18. anjete kibe teta....ufeeeeeeyeeee....illlelleleel

  ReplyDelete
 19. እነርሱን የራባቸው ነጻነት ነው፡፡ ኅሊናዊ ነጻነት፡፡ ሰው እንስሳ አይደለም፡፡ እንስሳ ከበላ ከጠጣ እና ከተመቼው በቃው፡፡ ሰው ግን በመብላት እና በመጠጣት ብቻ የሚረካ አይደለም፡፡ ሰው ዐዋቂት፣ ተናጋሪ፣ እና ሕያው ነፍስ አለቺው፡ ዐዋቂ ናትና መመራመር፣ ማሰብ ትሻለች፡፡ ነባቢት ናትና መናገር፣ ሃሳቧን በነጻነት መግለጥ ያምራታል፤ ሕያዊት ናትና የመኖር ዋስትናዋ እንዲጠበቅ ትፈልጋለች

  ReplyDelete
 20. @Amha
  Not Sadam's, They are son's of Gadafi. Dani write's correctly

  ReplyDelete
 21. እኔ ግን ስለ ሊቢያ ይህንን ሁለት ነገር ብቻ እላለሁኝ፡፡

  ይህ የቅዱስ መፅሀፍ ቃል አንድ ወቅት በዚሁ በአንተ ዌብ ሳይት ላይ በአንድ የአስተያየት ታዳሚ የተሰጠ ነው፡፡እየሱስ ክርስቶስ ወደ እየሩሳሌም ሲቃረብ (እራሱን በቃል ኪዳኑ መሰረት በፈቃዱ መስዋእት ሊያደረግ ማለት ነው) ከአፋፍ ላይ ሆኖ አይቷት በማዘን አለቀሰላት ለራሷም እንዲህ ነበር ያላት፡፡“እየሩሳሌም ሆይ ምነው ለሰላምሽ የሚበጅሽን ዛሬ አውቀሽ የተረዳሽ ቢሆን ኖሮ፡፡ነገር ግን አሁን ይህ ነገር ከአይንሽ ተሰውሮብሻል፡፡ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሰርተው በየአቅጣጫውም ከበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፡፡አንቺንና በቅጥርሽም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ከአፈር ይደባልቃሉ፡፡ድንጋይም በድንጋይ ላይ አይተውም የመጎብኘትሽን ዘመን ከቶ አላወቅሽምና፡፡”

  ሌላው በዴርቶጋዳ መፅኀፍ ላይ “ማሄር ሻላል ሀሽ ባዝ” ማለትም “ብዝበዛ ንጥቂያ ዝርፊያ ነገሰ” የሚለው የምስማኩ አባባል ትዝ አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 22. "ብልህ ከሌላው ይማራል፤ ሞኝ እና አምባገነን ግን ከራሱ ውድቀትም አይማርም፡፡
  "
  Thanks Dani

  ReplyDelete
 23. ብልህ ከሌላው ይማራል፤ ሞኝ እና አምባገነን ግን ከራሱ ውድቀትም አይማርም፡፡
  ሁለቱ የጋዳፊ ልጆች ተይዘዋል?

  ReplyDelete
 24. DearDaniel I like the way u look at it!but there is a lot of things You don't know it about Gadafi!
  the only thing the western they don't care about Gadafi Existance in power they dont even care Libyan people any way they concer about OIL!!OIL!!

  ReplyDelete
 25. ብልህ ከሌላው ይማራል፤ ሞኝ እና አምባገነን ግን ከራሱ ውድቀትም አይማርም፡፡

  ReplyDelete
 26. dear daniel,i cant find what u wrote about MK. SO COULD U PLZ TELL ME WR IT IS FOUND? AND ALSO IF IT has a title i would appreciate if i know it.Thanks

  ReplyDelete