የዓለም የጦማሪዎች ቀን
ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓም [August 31, 2011]
አትላንታ የሰማሁትን አስገራሚ ነገር ልንገራችሁ፡፡ አንድ ሰው ሜዳ ላይ ሥጋ ለመጥበስ የሚያገለግለውን ዕቃ (ባርቢኪው ይሉታል) ውጭ ያሳድረዋል፡፡ ይህንን ሰሞን በፈረንጆቹ ዘንድ የሙቀት ወቅት ነውና የቻለ በራሱ ዕቃ ያልቻለ ለአካባቢው ነዋሪ በተዘጋጀው መጥበሻ ሜዳ ላይ ሥጋ የማይጠብስ የለም፡፡ ይህ ታሪኩን የምንናገርለትም ሰው ቤቱ ፊት ለፊት ያለው መስክ ላይ ሥጋ ሲጠብስ አምሽቶ ትቶት ገባ፡፡ በማግሥቱ መጥበሻው በቦታው አልነበረም፡፡ አካባቢው ደኅና ሠፈር የሚባል ነበርና የመጥበሻው መጥፋት ሰውዬውን አስገረመው፡፡ ቀናት አልፈው ሳምንት ሆነው፡፡ መጥበሻው እንደጠፋ ቀረ፡፡
አንድ ቀን ጠዋት ወደ ሥራ ሊሄድ ከቤቱ ሲወጣ መጥበሻው የጠፋበት ቦታ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ማመን አልቻለም፡፡ ከሰማይ ወረደ ወይስ ከምድር ፈለቀ አለ ለራሱ፡፡ ጠጋ ብሎ ሲያየው የራሱ መጥበሻ ነው፡፡ አመዱ እንኳን አልተነሣም፡፡ ብቻ አመዱ ላይ አንዳች ነገር ተቀምጦበታል፡፡ ፖስታ፡፡
ፖስታውን ለማንሣት ስለፈራ በእንጨት ገፋ አድርጎ መሬት ላይ ጣለው፡፡ አሁንም በእንጨቱ ፈልቅቆ ፖስታውን ከፈተው፡፡ ውስጡ ካርዶች አሉ፡፡ ካርዶቹን አወጣቸው፡፡ አራት ካርዶች ናቸው፡፡ የፊልም ቤት መግቢያ ካርዶች፡፡ ፖስታውን መልሶ ሲያየው የተለጠፈ ወረቀት አገኘ፡፡
«መጥበሻችሁን ሳናስፈቅድ በመውሰዳችን ይቅርታ፤ በሠራነው ስሕተት ተፀፅተናል፡፡ ስለ ውለታችሁ እነዚህን አራት የፊልም መግቢያ ካርዶች ለቤተሰቡ ልከናል፡፡» ይላል፡፡ ባለቤቱ አልተጻፈበትም፡፡ ወደ ቤቱ ተመልሶ ኢንተርኔት ውስጥ ገባ፡፡ ልክ ነው በዚያ ቀን እና ሰዓት፣ ካርዱም ላይ ባለው ቦታ የተጠቀሰው ፊልም ይታያል፡፡ በእጁ ያለው ካርድም በዌብ ሳይቱ ላይ የሚያየው ዓይነት ካርድ ነው፡፡ የካርዱን ቁጥሮች ሲያስገባቸውም ርግጠኞች መሆናቸውን ነገሩት፡፡
እየተገረመ ለባለቤቱ ሊነግራት ወደ ፎቅ ወጣ፡፡ መጥበሻቸው መመለሱን፣ ያገኛቸውን ካርዶች፣ ሰዎቹ የላኩትን ደብዳቤ እና እንዴት ኢንተርኔት ውስጥ ገብቶ እንዳረጋገጠ በዝርዝር ተረከላት፡፡ ልጆቹም በሆነው ነገር ከመገረማቸው በላይ በተጋበዙት ፊልም ይበልጥ ተደሰቱበት፡፡
ፊልሙ የሚታየው ዓርብ ምሽት ነበር፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ ተዘጋጅቶ በአባትዬው መኪና ወደ ፊልም ቤቱ ተጓዘ፡፡ ካርዳቸውን ሰጥተው ትኬት በመቀበል ወደ ፊልም ቤቱ ገቡ፡፡ የተጋበዙት ፊልም የአንድ ቤተሰብን ውጣ ውረድ የሚገልጥ ፊልም ነው፡፡ ቤተሰቡ ሀብቱን በሌቦች ተዘርፎ የሚገጥመውን መንከራተት፡፡
ፊልሙ የአንድ ሰዓት ተኩል ርዝመት ነበረው፡፡ ሁሉም በተመስጦ ነበር ያዩት፡፡ የጋበዟቸውን ሰዎች እያመሰገኑም እያደነቁም፡፡ ልጆቹማ ምነው ሁልጊዜም መጥበሻችን በጠፋ ብለዋል አሉ፡፡
ፊልሙን ጨርሰው ረጋ ብለው እየተጨዋወቱ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡
ወደ ቤት ደርሰው የሳሎኑን በር ሲከፍቱት ያለ ቁልፍ ወለል ብሎ ተከፈተ፡፡ ሳሎኑ ወና ሆኗል፡፡ ዕቃ የሚባል ነገር አይታይበትም፡፡ ደነገጡ፡፡ ወለሉ ላይ ብቻ አንድ ደብዳቤ ተቀምጧል፡፡ ባለቤቱ ፈጥና ከፈተችው፡፡
«ፊልሙን ስለተጋበዛችሁልን እናመሰግናለን፤ ብዙም የማትጠቀሙባቸውን ዕቃዎች ወስደናቸዋል፤ አንድ ቀን ደግሞ እነርሱን መልሰን ሌላ ፊልም እንጋብዛችሁ ይሆናል» ይላል፡፡ ከቤቱ ዕቃ የቀረ የለም፡፡ ተበርብሮ፤ ተመርጦ፣ ተጭኖ ተወስዷል፡፡ እነርሱ ፊልም ሲያዩ ሌቦቹ ዕቃ ለመጫን በቂ ጊዜ ነበራቸው፡፡ እያዝናኑ የሚሰርቁ የተማሩ ሌቦች፡፡
ማንኛውም ነገር ተመጣጣኝ አመክንዮ ከሌለው ጤነኛ አይሆንም፡፡ አንድ ሰው መጥበሻውን ሰርቆ፣ እንደገና መልሶ አምጥቶ፣ ለአራት ቤተሰቡ ፊልም የሚጋብዝበት አመክንዮ ምንድን ነው? ለመሆኑ አንድን ነገር በጎ የሚያደርገው ምንድን ነው? ተግባሩ ነው ወይስ የተግባሩ አመክንዮ? ያለ ተመጣጣኝ አመክንዮ የሚመጣ ስጦታ ፊልም ሰጥቶ ንብረት ይነጥቃል፡፡
ተመጣጣኝ አመክንዮ ምንድን ነው? ተመጣጣኝ አመክንዮ ማለት ለአንድ ለሚደረግ ነገር ለኅሊና ሊረዳው እና ሊደርስበት የሚችል ተጠየቃዊ ምክንያት ማለት ነው፡፡ ለምን? እንዴት? ማን? መቼ? ለሚሉት ጥያቄዎች ቢያንስ ኅሊናችንን እንዳይቆረቁር የሚያደርግ፣ ልቡናችንን «አላውቅም» ከሚለው ጨለማ የሚያወጣ፣ ድንገቴ እና አጋጣሚ ብቻ ከሚመስል ሂደት ምክንያታዊ እና ተጠየቃዊ ወደሚያደርግ ሂደት የሚያስገባ ነገር ነው፡፡
ያለ ተመጣጣኝ አመክንዮ የሚመጣ ደስታም ሆነ ኀዘን፣ ማግኘትም ሆነ ማጣት፣ ክብርም ሆነ ውርደት፣ ሥልጣንም ሆነ ሽረት፣ ሀብትም ሆነ ድህነት፣ ውዳሴም ሆነ ወቀሳ፣ ምስጋናም ሆነ ትችት፣ ወዳጅነትም ሆነ ጠላትነት፣ ዕድለኛነትም ሆነ ዕድለ ቢስነት ውጤታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡
አንዳንዶች ያገኙት ሥልጣን ከትምህርታቸው፣ ከአስተዳደጋቸው፣ ከልምዳቸው፣ ከሌሎች ጋር ካላቸው ብልጫ፣ ከማሸነፋቸው፣ ከጥረታቸው ጋር የማይጠማጠን መሆኑን ያውቁታል፡፡ ያንን ሥልጣን ለማግኘ ታቸው ምንም ዓይነት ተመጣጣኝ አመክንዮ የላቸውም፡፡ እንዲሁ ሲመጣ ተቀበሉት እንጂ፡፡ በዚህም የተነሣ ፊልም ተቀብለው ንብረት እንዳጡት ሰዎች ሥልጣን አግኝተው ኅሊናቸውን አጥተውታል፡፡ ያለ አመክንዮ ባገኙት ሥልጣን የተነሣ ያለ አመክንዮ ኅሊናቸውን ተሰርቀዋል፡፡
አንዳንዶችም የሚቀርብላቸውን ውዳሴ እና ክብር በአመክንዮ አይመዝኑትም፡፡ ለምን? ይገባኛል ወይ? የሚነገረው ነገር ከእኔ ጋር ይመጣጠናል ወይ? ብለው አይጠይቁም፡፡ ሰጭው ያቀረበላቸውን ውዳሴ እና ክብር ሁሉ እንዲሁ ይቀበሉታል፡፡ እንደ ፊልሙ በውዳሴ ከንቱ እያዝናና የመወሰን እና እምቢ የማለት ኃይላቸውን እየሰረቃቸው መሆኑን አይረዱትም፡፡
እልም ጭፍን ያለ፣ ሙዝዝ ፍዝዝ ያለ፤ ከፍቅር የበለጠ፣ ከአድናቆት ያየለ ፍጹማዊ ድጋፍ እንዴት ጤነኛነት ይሆናል? አንድን አካል አይሳሳትም፣ እንከን የለውም፣ አያጠፋም፣ ሁሉም ነገሩ ትክክል ብቻ ነው፣ የሚለውን ፊልም የሚጋብዙን ሰዎች እውነት ደጋፊዎቻችን ናቸው? እንዴው በየትኛው አመክንዮ ሰው መቶ በመቶ ትክክል ይሆናል? በየትኛው አመክንዮ አንድ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ተቋም፣ ቡድን፣ መቶ በመቶ ፍጹም ይሆናል? እነዚህ ሰዎች እየደገፉን ነው ወይስ ፊልም ጋብዘው ሊሰርቁን ነው?
የሃይማኖት መሪዎቻችንን ኅሊና የሰረቁት እነማን ናቸው? ርግጠኛውን ማንነታቸውን የሚነግሯቸው፣ ሰዎች መሆናቸውን የሚያሳስቧቸው ወዳጆቻቸው አይደሉምኮ፤ አማልክት ናቸው፣ እንዲያውም ከአማልክት በላይም ናቸው እያሉ በመወድስ አዝናንተው ልባቸውን የሚሰርቁባቸው ጠላቶቻቸው እንጂ፡፡
የባለሥልጣናቱን ኅሊና የሰረቁት እነማን ናቸው? እውነቱን ፊት ለፊት የሚነግሯቸው ወዳጆቻቸው አይደ ሉምኮ፤ እንደ ውሻ ተሽቆጭጥቁጠው፣ እንደ ንብ ከብበው፣ እንደ ምንጣፍ ተነጥፈው፣ እንደ ከዘራ ታጥፈው፣ እንደ ወናፍ እፍ እፍ ብለው ልባቸውን የሰረቁባቸው ጠላቶቻቸው እንጂ፡፡
ስትቆጡ የሚስቅ፣ ስትስቁ የሚያለቅስ፣ ሳይገባው አንገቱን የሚነቀንቅ፣ ሳይረዳ እጁን የሚያወጣ፣ ሳይስ ማማ የሚያጨበጭብ፣ ሳያምንበት አባል የሚሆን እንዴት ጤነኛ ይሆናል? ሰጥቶ የሚሰርቀው ነገር ከሌለው በቀር፡፡
መርካቶ ውስጥ ነው አሉ፡፡ አንዲት ፈረንጅ ቱሪስት መኪናዋን አቁማ እርሷ መስተዋቶቿን ዘጋግታ ፍሬቻ አብርታ መኪናዋ ውስጥ ቁጭ ብላለች፡፡ አካባቢዋን በአራቱም መስተዋቶቿ ትቃኛለች፡፡ ድንገት በስፖ ኪዮው ስታይ አንድ ወጣት ልጅ ወደ ኋላዋ ፍሬቻ ይጠጋል፡፡ ሊሰርቅ ነው ብላ ትኩር ብላ አየቺው፡፡ ሲጋራውን አወጣና በፍሬቻው ሊለኩስ ይታገላል፡፡ «እንዴ ፍሬቻው ቀይ ሲሆን ጊዜ እሳት መሰለው እንዴ?» ብላ ተገርማ ትርኢቱን በአድናቆት ተመስጣ ታየው ጀመር፡፡
ልጁ የተለያዩ ሲጋራዎችን እያወጣ ይሞክራል፡፡ ይታገላል፡፡ አፉ ላይ አድርጎ ለመሳብ ይፍጨረጨራል፡፡ ገርሟት ካሜራዋን አወጣችና በስፖኪዮው በኩል ትቀርፀው ጀመር፡፡ ልጁ ታግሎ ታግሎ አቃተውና አንገቱን እየነቀነቀ ሄደ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በፍሬቻ ሲጋራ ሊለኩስ የሚሞክር ሞኝ ሰው መኖሩ ገርሟት፤ የቀረፀችውንም ለወዳጆቿ ለማሳየት ጓጉታ፣ ካሜራውን ቦርሳዋ ውስጥ ልትከት ወደ ኋላዋ ዘወር ስትል ቦርሳዋ የለም፡፡ ላፕቶፕዋም የለም፤ ሹራቧም የለም፡፡ ፍጥጥ ስትል የኋላዋ በር ገርበብ ብሏል፡፡
እርሷ በሞኙ ልጅ ትርኢት ተመስጣ ስትቀርጽ የመርካቶ ጩሉሌዎች መኪናዋን እስኪበቃቸው በርብረው የሚፈልጉትን ሁሉ ወስደዋል፡፡ ያም ልጅ ሞኝ አልነበረም፣ እርሷን እያሞኛት ነበር እንጂ፡፡
መርካቶ ውስጥ፣ ያውም በአካባቢው አያሌ መኪና እየወጣ እየወረደ፣ አንድ ወጣት ፍሬቻ እና እሳት አይለይም ብሎ ለማሰብ እንዴት አይከብድም? ተመጣጣኝ አመክንዮ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው እንግዲህ፡፡
ሊቃውንቱ ሔዋን ያጣቺውን ተመጣጣኝ አመክንዮ ድንግል ማርያም አገኘቺው ይላሉ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ መጥቶ ትፀንሻለሽ ሲላት እንዲሁ አልተቀበለቺውም፡፡ «እኔ ድንግል ነኝ፣ ያለ ወንድ እንዴት እፀንሳለሁ?» ብላ ነው የጠየቀቺው፡፡ አንዲት ባል ያላገባች፣ በድንግልና የምትኖር ሴት በድንገት ትፀንሻለሽ ስትባል መጠየቅ ያለባት ተመጣጣኝ አመክንዮ ይኼ ነው፡፡ ሰይጣን ለሔዋን ውዳሴ ሰጠና ኅሊናዋን ሰረቃት፣ ክብር ሰጠና አእምሮዋን ነሣት፣ አምላክነትን የሰጠ መስሎ ሰውነትን ወሰደባት፡፡
እንዲህ ልታገኝ ነው፣ እንዲህ ልትሆን ነው፣ ወዲህ ልትወጣ ነው፣ ወዲህ ልትወርድ ነው እያሉ ብልጦች ሲያታልሏቸው የሚውሉት ወገኖቻችን ነገሮችን የሚቀበሉበት ተመጣጣኝ አመክንዮ ስለሌላቸው ነው፡፡
ሰውዬው የሰጡትን ሁሉ እንዲሁ ሳይጠይቅ የሚቀበል ነው አሉ፡፡ ታድያ አመሉን የሚያውቁ ሌቦች ያለቺውን አንዲት አህያ ሊሰርቁት ያደባሉ፡፡ እርሱ እና አህያው ምድር ቤት ነበር አሉ የሚተኙት፡፡ ከምድር ቤቱ መውጣት የሚቻለው ከውስጥ በሚከፈት በር ወይንም በላይኛው ቤት ወለል ላይ ባለ ቀዳዳ ነበር፡፡ ሌቦቹ የምድር ቤቱን በር መክፈት ሲያቅታቸው ጊዜ የላይኛውን ቤት ሰብረው መግቢያውን ቀዳዳ ከፈቱት፡፡ ከዚያም አንደኛው ሌባ ወደ ምድር ቤቱ በገመድ ወረደ፡፡ በሩን ቢፈልግ ቢፈልግ ጨለማ ስለሆነ ሊያገኘው አልቻለም፡፡ ቢጨንቀው አህያዋን በገመድ ሆድዋ ላይ አሠራት፡፡ ከዚያም እርሱ በገመዱ ተንጠላጥሎ ወጣ፡፡ ሌቦቹ ከላይ ሆነው አህያዋን በገመድ ይጎትቷት ጀመር፡፡
አህያዋ እየተሳበች ወደ ላይ ስትወጣ ገመዱ ስላጣበቃት ጮኸች፡፡ ባለቤቷም ነቃ፡፡ ቀና ሲል አህያዋ ወደ ላይ ትወጣለች፡፡ ፈጥኖ ሚስቱን ቀሰቀሰና «ይገርማል፣ አህያዬ በቅታ ወደ ላይ እያረገች ነው፤ ነይ እዪ» አላት፡፡ ሚስቱም ተነሥታ ከባልዋ ጋር በአድናቆት አህያቸውን እያዩ አስወሰዷት ይባላል፡፡
ያለ አመክንዮ መቀበልም ሆነ ያለ አመክንዮ መቃወም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ፈተና እና ፀፀት፡፡
ሀገረ አትላንታ- መንበሮሙ ለሲ ኤን ኤን ወ ኮካ
ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።
ህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።
በጣም ተመችቶኛል ዳኒ ተከታታይህ!!! ነኝ በርታ ብዙ ነገሮችን ካንተ ለመበዝበዝ አኮብኩበናል.....
ReplyDeleteመቅሱድ ከ ቴሌ ገራዥ አዲስ አበባ
በእውነቱ ከዚህ ጽሑፍ ትልቅ ነገር ተምረንበታል ብዬ አምናለሁ ፡፡ እንደ ርግብ የዋሆች እንደ እባብ ብልሆች ልንሆን እንደሚገባ በሚገባ አስገንዝቦናል ፡፡
ReplyDeleteFikremariam S
ReplyDeleteDany nice view, we are acting before we internalized the ideas,that is why we will be headed to dangerous situation.God bless us all.
I love this Dani. A strong argument, expressed in a convincing way!!!Thanks for sharing!
ReplyDeleteFrm Germany
Wonderful! How can I send it to our Prime Minister?
ReplyDeletetha very good be go over it I am your apprciater danie from woldia
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin Dn. Daniel
ReplyDeleteNow I have hope that you might be staying in Atlanta until Sunday. I can't wait to see you at the church. Also the way you finished your writing is funny so does the story. What an educated burglar. Now a days people have money problem so they will come up with creative ideas to steal. Please let's be careful. Atlanta
Dani these days your written materials are becoming-
ReplyDelete-More edited
-more matured and
-well organized
When I read the whole contents, each line has very selective, coherent and very nice flow from one paragraph to the next.
Thank you please keep it up!!!!!!!
GG
ሠላም ዲ/ን ደንኤል፣ ግሩም ጽሑፍ ነው። አዎ! የሆነ ነገር ሲሰጠን በቅድሚያ ራሳችንን፡- "ይህ ነገር ይገባኛል ወይ?" ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል። በሌላም በኩል፣ "ካበረከትኩት ሥራ፣ ከያዝኩት ሥልጣን አንፃር ይህ ክብር፣ ይህ ሞገስ፣ ይህ ውዳሴ አስፈላጊ ነው ወይ?" ብሎ ከራስ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል። ይህንን የማያሰላስል ሰው ግን በቀላሉ ይወድቃል፤ አለፍ ሲልም ይታበይና አናት ላይ ይወጣል። ስህተቱን እንኳ ብትነግረው ከተበረከተለት ከንቱ ውዳሴ አንፃር ነገሮችን ስለሚመለከታቸው አንተን ይጠላሃል፤ ከዚያም ባሻገር አንተን የሚያጠፋበትን መንገድ ሲቆፍር ይውላል። ግለሰቡ ባለሥልጣን ከሆነማ ነፍስህን ለማዳን ስትል ሳትወድ በግድህ አገርህን ጥለህ ትሰደዳለህ። ስንቶቻችን እንዲህ ባለ አጋጣሚ ከአገር ተሰደን ይሆን? ቤት ይቁጠረው!
ReplyDeleteI like it. Especially about notes St. Mary & Hewan...
ReplyDeleteIt has great massege!
NO WORD KEEP ON GOING BRO... GOD BE WITH U.
ReplyDeleteተስፋ አትቆርጥም ታድለህ የምትጽፋቸው ነገሮች ለውጥ ያመጣሉ በለህ ታምናለህ እኔ ግን በተለይ በቤተክረስቲያነ ጉዳይ እያዘንኩ ነው መቸ ይሆን ጭንቀታችን ንዴታችን ሀዘናችን ቀርቶ
ReplyDeleteስለሀጢአቱ የሚጨነቅና የሚለቅስ ምእመን መሆን የምንችለው
"አንዱ እኔ"
ReplyDeleteአንዱ እኔ ሳይገባኝ የምፍልግ ድርሻ ፣
ያለዋጋ ማግኘት ውዳሴን የምሻ።
ውስጣ ውስጤን ያጣሁ ሳይገባኝ የተቀበልኩ፣
መሰረተ በሌለው በአለም የከበርኩ።
ምንዱባን ዘ ሲያትል ነኝ
አምላከ ቅዱሳን መንገድህን ሁሉ ይጠብቅልህ ውንድሜ ዲ.ዳንኤል
Betam des yemil temhrt azer melikt new. My God bless you dani.
ReplyDeleteAdisu teketatayh shimels ke minjar arerty. God bless you dani.
Adisu teketatayh shimels ke minjar arerty.
Impressive!!!
ReplyDeleteያለ አመክንዮ መቀበልም ሆነ ያለ አመክንዮ መቃወም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ፈተና እና ፀፀት፡፡
ReplyDeleteit is beyond that!!!!!!!!!!!!!!!
batame yegaremal.10q dani
ReplyDeleteDani p/s sey something about Hanebal Gadafe & his wife
ReplyDeleteየባለሥልጣናቱን ኅሊና የሰረቁት እነማን ናቸው? እውነቱን ፊት ለፊት የሚነግሯቸው ወዳጆቻቸው አይደ ሉምኮ፤ እንደ ውሻ ተሽቆጭጥቁጠው፣ እንደ ንብ ከብበው፣ እንደ ምንጣፍ ተነጥፈው፣ እንደ ከዘራ ታጥፈው፣ እንደ ወናፍ እፍ እፍ ብለው ልባቸውን የሰረቁባቸው ጠላቶቻቸው እንጂ፡፡
ReplyDeleteThank you Danie,solomon From Wollo Kombolcha
God bless u!!!God bless u!!!
ReplyDeleteKalew Hiwot Yasemalin
ReplyDeleteAmeha Giyorgis
DC Area
Danny...Berta Berta..Betam Arif Neaw...Enem ..eyserku..lefeace book frindocha... eyakfelku.neaw..thankyou!
ReplyDelete"ያም ልጅ ሞኝ አልነበረም፣ እርሷን እያሞኛት ነበር እንጂ፡፡"ይገርማል ሞኝ ሆኖ ሰዉን ማሞኘት ሲቻል፡፡
ReplyDeleteዳኒ በርታልን
hi
ReplyDeletei love it!!!
ReplyDeleteእድሜና ጤናውን ይስጥልን፡፡ እውቀትና ጥበቡንም ይጨምርልን፡፡ ብሎግህንም ከፍተን አንጣህ
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteIt so nice article that entails the audience to think thoroughly and reasonably. Logical thinking is so necessary.
abet abet ...abet...girim naw yalegn...egzhiabeher kante gar yhiun
ReplyDeletewhat an observation.
ReplyDeleteሊቃውንቱ ሔዋን ያጣቺውን ተመጣጣኝ አመክንዮ ድንግል ማርያም አገኘቺው ይላሉ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ መጥቶ ትፀንሻለሽ ሲላት እንዲሁ አልተቀበለቺውም፡፡ «እኔ ድንግል ነኝ፣ ያለ ወንድ እንዴት እፀንሳለሁ?» ብላ ነው የጠየቀቺው፡፡ አንዲት ባል ያላገባች፣ በድንግልና የምትኖር ሴት በድንገት ትፀንሻለሽ ስትባል መጠየቅ ያለባት ተመጣጣኝ አመክንዮ ይኼ ነው፡፡ ሰይጣን ለሔዋን ውዳሴ ሰጠና ኅሊናዋን ሰረቃት፣ ክብር ሰጠና አእምሮዋን ነሣት፣ አምላክነትን የሰጠ መስሎ ሰውነትን ወሰደባት፡፡
ReplyDeletedani. tilik timihirt naw AMLAK KANTE GA YIHUN
ReplyDeleteበጣም ደስ ይላል ስንቶቻችን ይሆን አንድን ነገር ለማግኘት ብለን የሚያስፈልገንን እና የራሳችን የሆነውን ያጣነው!
ReplyDeleteDink New Dani!
ReplyDeleteBemikniyat endinwesin yastemral. abzagnochachin beyilugntana yale beki mikinyat enwesinalen.
GOD BLESS YOU!!!
constarcting ones argument based on logic always resulted in correct concluion. and that is the basies of reasionable & informed decision and that of reasionable society.
ReplyDeleteያለ አመክንዮ መቀበልም ሆነ ያለ አመክንዮ መቃወም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ፈተና እና ፀፀት፡፡kale hiwot yasemalin dn daniel.
ReplyDeletei also learn a lot from this article 10q
ReplyDeletedanny,Logic Wasege yehyewt kefel new ..amerwacheni yemyazabuin..Addiction,excess desire of things..may lead us to in proper logic to r4eason out.That dangerous...we need to pray..wyenru alemner len yehe neaw..yale logic!!!
ReplyDeleteህሊናቺን ሳይወቅሰን ለእውነት ሰአርተን፣ ተግተን፣ በታሪክ አቅጣጫ መልካም አሻራ ጥለን ለማለፍ እንጣር። ከተባረክን ፊቅርና አንድነት እርሱ ካልሆነ ደግሞ ሰላም፣ እውነትና ፍቅር አንድ ስለሚያደርጉን ስለነዚህ እንኑር። ይህ ደግሞ በአለማዊውም ሆነ በመንፈሳዊ ህይወት ዋጋ አለው። ዳኒ የተሰጠህን ስለተጠቀምክበትና አኛንም ስለጠቀምከን እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ። በሚቀጥለው ስለዚሁ ታስነብበን ይሆናል።
ReplyDelete