Wednesday, August 31, 2011

የዓለም የጦማሪዎች ቀን


 ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓም [August 31, 2011] 

የኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች ጉባኤ
የዓለም የጦማሪዎች ቀን በዚህ ዓመት ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓም [August 31, 2011] ይከበራል፡፡ በተለያዩ ድረ ገጾች እና የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እንደምናየው የየሀገሩ፣ የየከተማው እና የየክፍለ አህጉሩ ጦማሪዎች የተለያዩ ዝግጅቶችን በአንድ አካባቢ በማዘጋጀት ዕለቱን ለማክበር ተዘጋጅተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እና በኢትዮጵያውያን አካባቢ የሰማሁት ነገር የለኝም፡፡
በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በእምነት፣ በኪነ ጥበብ ወዘተ ላይ የሚያተኩሩ ጦማሪዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡
ሰዎች ሃሳባቸውን መግለጣቸው፣ መረጃ መለዋወጣቸው እና መገናኘታቸው መቼም ቢሆን በሥዕለት የሚገኝ ዕድል ነው፡፡ «አህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም» የሚለውን ብሂል «ሃሳብ ቢቧቀስ ጥርስ አይሳበርም» ወደሚለው ለመቀየር የሚቻለው የሃሳብ መግለጫ መንገዶች ሲበዙም ሲጠነክሩም ነው፡፡ ከእነዚህ መንገዶች ላይ ዘመኑ ብሎግን ጨመረልን፡፡
በሀገር ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነት ማነስ እና የጥራት ችግር እንዳለ ሆኖ ብቅ ብቅ ያሉትን ጦማሪዎችም ሆነ ሊመጡ ያሰቡትን ጦማሪዎች የሚያሳስቡ ወይንም ሊያሳስቡ የሚገቡ ነገሮች ግን አሉ፡፡
የመጀመርያው የማስተዋወቂያ መድረክ እጦት ነው፡፡ ብሎጎቹ መጀመራቸውን፣ መኖራቸውን እና የሚያ ወጧቸውን ጉዳዮች የሚያስተዋውቁ መድረኮች እምብዛም አይገኙም፡፡ እኔ ለምሳሌ አንዳንዶቹን ብሎጎች ማወቅ የቻልኩት ከተጀመሩ ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ እነዚህን የሃሳብ መንሸራሸርያ መንገዶች በአንድ ቦታ የምናገኝበት፣ ሲጀመሩም ዜናቸውን የምንሰማበት መንገድ ቢኖር እኛም ከመረጃው እና ከሃሳቡ እንጠግብ፣ አዘጋጆቹም «የደገሰውን ሲበሉለት፣ የወለደውን ሲስሙለት» በሚለው መሠረት ይደሰቱ ነበር፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የልምድ መለዋወጫ መንገድ አለመኖሩ ነው፡፡ አዳዲሶቹ ጡመራዎች የቀድሞዎቹን ስሕተት የሚደግሙት፣ በተሻለ አሠራር እና ገጽታ የማይመጡት፣ አዲስ ነገርም የማያሳዩት ምናልባት ለምድ የሚቀስሙበት መንገድ ከማጣት ይመስለኛል፡፡
ሦስተኛው የጋራ የሆነ አካል አለመኖሩ ነው፡፡ ማንኛውም ክዋኔ ደረጃ፣ የሥነ ምግባር ደንብ፣ የመረጃ ማዕከል፣ ወዘተ ያስፈልገዋል፡፡ የዚህ ዓይነቱ አካል መኖር የጡመራዎቹ የሞያ ደረጃ እንዲሻሻል፣ የልምድ መለዋወጫ መንገዶች እንዲኖሩ፣ ቅሬታዎች በመግባባት እንዲታረሙ፣ ጦማሪዎች እና ጡመራች የሚመ ሩባቸው የሥነ ምግባር ደንቦች በጋራ እንዲወጡ፣ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ዛሬ ያለው የዓለም ሥርዓት አንድን ሥራ ለመሥራት የግድ በአንድ ቦታ መገናኘትን የማይጠይቅ እየሆነ ነው፡፡ የመረጃ መረብ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙት ጦማሪዎች ከላይ የተነሡትን ነገሮች ለመተግበር የግድ መገናኘት አያስፈልጋቸውም፡፡ ያንኑ መረብ ተጠቅመው ነገሮችን መሥራት ይችላሉ፡፡
እናም «የኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች ጉባኤ» (Society of Ethiopian bloggers) ቢኖረን ምን ይመስላችኋል? እስኪ ሃሳብ ስጡበት፡፡

17 comments:

 1. Nigusie From Dz
  Thank you for your invitation. It is nice idea to upgrade the capacity and capability of the blogger and for the owner it is a good opportunity to share experience from each other. God blessing you

  ReplyDelete
 2. የኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች ጉባኤ መኖሩ ተገቢ ነው፡፡፡፡

  ReplyDelete
 3. ኢትዮጵያውያን የማኅበር ነገር የሚሳካልን አይመስለኝም፡፡ግን ብንሞክረው አይከፋም፡፡

  ReplyDelete
 4. እኔ ብቻ አውቃለው የማይባልበትና ትክክለኛ መረጃ ይዞ የሚጦምር እስከሆነ ድረስ ማእከላዊነት
  1. ለመተዋወቅ
  2. አብሮ ለመስራት
  3. ትውልዱን አንባቢ ለማድረግ
  4. አሉታዎ ተጽህኖ በትውልድ ላይ የሚያመጡትን አመለካከቶች ለመቅረፍ፥ ወዘተ....
  ይጠቅማል ባይ ነኝ።

  ReplyDelete
 5. what a nice idea
  greate idea

  ReplyDelete
 6. Just awesome! Good idea keep going on Dani

  ReplyDelete
 7. it is good idea!!!!

  ReplyDelete
 8. እኔ ብቻ አውቃለው የማይባልበት እስከሆነ ድረስ ይጠቅማል

  ReplyDelete
 9. አንድም ሃሳብን የመግለጥ፤የመወያየት እና የመነጋገር ባህላችንን በጥቂቱም ቢሆን ለማሳደግ አንድም መረጃ ለመለዋጥ እና የዘመኑን ፍጥነት ለመከተል ሁነኛ መንገድ ነው፡፡ከሁሉም ከሁሉም ይህ የጦማር ነገር እንዴት ከዛሬዋ ኢትይጵያ ጋር አብሮ ሊሄድ ይችላል የሚለውን ነገር ሰብሰብ ብሎ መነጋገር ይበጃል፡፡እግረ መንገዱን ለጦማሪዎቻችንም እውቅና ቢጤ መስጠት ይቻላል፡፡ደራሲዎቻችን፤ሃያሲዎቻችን….ይኸ ጦማር አንድ መንገድ መሆኑን ቢያውቁትም አይከፋም፡፡

  ReplyDelete
 10. በጣም ግሩም ሃሳብ ነው። ምንም እንኳ የጽሑፍ ችሎታ ባይኖረኝም በሂደት እማራለሁ ብዬ እኔም ያለኝን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ። ስለዚህ ይህ ጉባኤ መመስረቱ ለእንደኔ ላሉት ጀማሪዎች ሁነኛ ድልድይ ይሆናል። በተቻለኝ መጠን ለየት ባለ ነገር ላይ ለመጦመር መረጃዎችን እያሰባሰብሁ ነው። አንድ ሃሳብ መጦልኛል፤ ባንተ ብሎግ ላይ አድቨርታይዝመንት ከሚለው ላይ አዳዲስ ብሎጎች ሲወጡ ቢላክልህና አዬት አድርገህ-ብታስተዋውቅልን ምን ይመስልሃል?

  ReplyDelete
 11. በጣም መልካም ሃሳብ ነው ዲ.ዳንኤል መቸም ከግዜው አስክፊነት አንጻር ይህ እርምጃ በተለያዩ አካሎች በክፉ እንዳይተረጎምብህ ጥንቃቄ ቢታከልበት ጥሩ ነው። የአገሬ ሰው ከዉሃ በላይ የጠማው መቼም ካላጋነንኩ 'በነጻ እራስን መግለጽ' ሳይሆን እንደማይቀር ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። አሁን አንተና መሰሎችህ የምትወያዩበትን ርእሶች ማን ይሙት በየከፍተኛ ተቆማት እና የተለያዩ መሰብሰቢያ ቦታዎች መልካም ዜጋን ለመቅረጽ ሁነኛ መፍትሄ ነብሩ፡፡ ግና የሰው ልጅ ከተውያየና ካወቀ፤ ለምን ነገሮች እንዲህ ሆኑ፣ እንደዚያስ ቢሆኑ ማለቱ አለፎም ተርፎም ለውጥን በይበልጥ መሻቱ እና መተባበሩ እንደማይቀር ጠንቅቀው የተረዱት ሳንውድ በግድ ያስቀመጥናቸው 'መሪዎቻችን' አጉል እንዳያደርጉህ እባክህ ጠንቀቅ በል፤ አምላከ እስራኤልም ይጠብቅህ!

  ReplyDelete
 12. It is so nice idea what i sens it for our reading habit. Ase said

  ReplyDelete
 13. Oh Dani,bizu gize sasibew yenebre hasab nebre,yemegermih lik andante group benore yemeli hasab begile'a Bloge lay laweta bezigejet lay nebreku...lemanignawim melkam hassab new atikurote benisetew konjo new....

  ReplyDelete
 14. በጣም የተቀደሰ ሃሳብ ነው። ነገር ግን እኛ አብሮ መብላት እንጂ አብሮ መስራት ሆኖልን አያውቅምና በዚህ ላይ ጥርጣሬ ቢኖረኝም ጢቂቶች አብሮ መስራት ጥቅሙ የገባቸው ቢጀምሩት ሌሎችም ሊከተሉ ስለሚችሉ ይሞከር ባይ ነኝ ለተግባራዊነቱ እንበርታ። እግዚአብሔር ይጨመርበት።

  ReplyDelete
 15. Dani, what is 'TOMARIE' mean? I never hire.

  ReplyDelete