Tuesday, August 23, 2011

ታሪክ ላይ መተኛት (ክፍል ሁለት)


አንድ ሰው ተዋወቅኩላችሁ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ፡፡ «ኢትዮጰያ ውስጥ ታዋቂ ጋዜጠኛ ነበረ» አለኝ ሰውዬውን ያስተዋወቀኝ ሰው፡፡ ቀጠል አድርጎም እኔም «ጋዜጠኛ» መሆኔን ገለጠለት፡፡ ሰውዬውም «ምን ጋዜጣ በኛ ጊዜ ቀረ፤ ሠራነው በጊዜው» አለ አውራ እና መሐል ጣቱን አጋጭቶ እያጮኸ፡፡ ስሙን ለመስማት ጓጓሁ፡፡
«መቼም በዝና ሳታውቀኝ አትቀርም፣ እንትና እባላለሁ» ብሎ ስሙን ሲነግረኝ ልቤ ቀጥ ልትል፡፡ ሰው ፊት የሚሳቅ ቢሆን ኖሮ በዚህ ቀን ስቄ አላባራም ነበር፡፡ ዐወቅኩት፡፡ ጋዜጣውም ትዝ አለኝ፡፡ ያንን ጋዜጣ ለርእሰ አንቀጹ እና በውስጡ ይጽፉ ለነበሩ ሁለት ጎበዝ ሰዎች ስል እገዛው ነበር፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት ኅትመት አቁሟል፡፡
ይህ አሁን ከፊቴ የቆመው «ታዋቂ ጋዜጠኛ» በጋዜጣው ላይ በአንድ ጥግ ይጽፍ ነበር፡፡ ይቅር ይበለኝና የርሱን ጽሑፍ ከሁለት ዐርፍተ ነገሮች በላይ ለማነበብ ይከብደኛል፡፡ እንዴውም በዚያ ጋዜጣ ላይ የርሱ ጽሑፍ መውጣቱ ምንጊዜም እንዳበሳጨኝ ነበር፡፡ የጋዜጣ ጽሑፍ እንዴት እንደማይጻፍ ማስተማርያ ከተፈለገ የርሱ ጽሑፍ አለ፡፡ ነጠላ ሠረዝ፣ ድርብ ሠረዝ እና አራት ነጥብ ድርሽ እንዳትሉ ተብለው የተሰደዱበት ጽሑፍ ቢኖር የርሱ ነው፡፡
አይ አሜሪካ፤ ስደት ለወሬ ያመቻል፤ እዚህ መጥቶ «ታዋቂ ጋዜጠኛ» ተብሎ ሬዲዮ ከፍቷል አሉ፡፡ በየስብሰባው እየተነሡ «እገሌ እባላለሁ ታዋቂ ጋዜጠኛ ነበርኩ» እያሉ ታሪክ ላይ ተኝተው ዲስኩር ቢጤ ሲያሰሙ ታድያ ሰውም ታሪክ ላይ አብሯቸው ተኝቶ ያዳምጣቸዋል፡፡
እኔ የምለው ግን የንጉሡ አንጋቾች፣ አልባሾች፣ ልብስ ሰፊዎች፣ ወጥ ሠሪዎች፣ ሽንኩርት ከታፊዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ዘምዛሚዎች፣ አንጣፊዎች፣ አጃቢዎች፣ ዳዊት ደጋሚዎች፣ ገንዘብ ቤቶች፣ ጠጅ ጣዮች፣ ጠላ ጠማቂዎች፣ ድቁስ ደቋሾች፣ ፎቶ አንሺዎች ሁሉ አሜሪካ እንዴት ሊመጡ ቻሉ?
በሄድኩበት ቦታ ሁሉ የንጉሡ እንትን ነኝ የማይል የለምኮ፡፡ ቆይ ግን ደርግ ባላባቶችን፣ መሳፍንቶችን እና ልዑላኑን ሲገድል ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን አሜሪካ ነው እንዴ ያመጣቸው፡፡ እኔ ደርግ የወታደሮችን ልጆች ኩባ መውሰዱን እንጂ የባላባቶችን ልጆች አሜሪካ መላኩን ሰምቼ አላውቅም ነበር፡፡
የልጅ መስፍን ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ የልጅ ኢያሱ የልጅ ልጅ፣ ልጅ፣ ልጅ፤ የራስ ስለሺ ልጅ፣ የራስ ሚካኤል የልጅ ልጅ፣ የልዑል እንትና የልጃቸው የእኅት ባል፣ የደጃዝማች እንቶኔ የሚስታቸው የእኅት ልጅ፤ የቀኛማች እንትና  የልጃቸው ሚስት ነኝ የማይል ማነው?
ታሪክ ላይ እየተኛንኮ መከራ አየን፡፡ እዚህ ሀገር መጥቶ በተማረው፣ በሠራው እና በሆነው ነገር የሚጠራ አበሻ ጥቂት ነው፡፡ አብዛኛው ለራሱ ማንነት የታሪክ ትራስ ሰጥቶ ይንፈላሰሳል፡፡
ከቻሉ የታዋቂ ሰው ልጅ፣ እናት፣ እኅት፣ ሚስት፣ ባል፣ ዘመድ መሆን ነው፡፡ ካልቻሉ ደግሞ ጎረቤት፣ አብሮ አደግ፣ አብሮ ተማር፣ አብሮ ስዱድ መሆን ከተገኘም አይከፋም፡፡ ያም ካልተቻለ ደግሞ የዚያ የታዋቂ ሰው ሠፈርተኛ መሆን አይጠላም፡፡ ይህ ሁሉ የማይገኝ ከሆነም የርሱን ስልክ ቁጥር ማወቅም ቢሆን አሜሪካ ውስጥ ቅጽል ያስገኛል፡፡ «እገሌን ተዋወቃት የዚያ የታዋቂው የእገሌ ስልክ ቁጥር አላት» ሊያስብል ይችላል፡፡
እዚህ ከተማ አንድ ሰው አሉ «ታዋቂ ተዋናይ»፡፡ «ከሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን ጋር አብረው ስንት እና ስንት ቴአትር ሠርተዋል» ትባላላችሁ ስትተዋወቋቸው፡፡ እርሳቸውም «ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት» የሚለውን ቲያትር ለማሳየት እያዘጋጁ መሆናቸውን በኩራት ይነግሯችኋል፡፡ እኔ ድራማው እየተዘጋጀ ነው ተብሎ ሲሰነብትብኝ አገር ቤት ብሔራዊ ቴአትር የሚሠሩ ወዳጆቼን ጠየቅኳቸው፡፡
እውነት ነው ሰውዬውን ያውቋቸዋል፡፡ ግን ተዋናይ አልነበሩም፡፡ ተዋንያኑ የሚለብሱትን ልብስ ይይዙ የነበሩ ንብረት ክፍል ነበሩ፡፡ አሜሪካ ገብተው «ታዋቂ ተዋናይ» ተብለዋል፡፡ እርግጠኛ ነኝ እርሳቸው የአቡነ ጴጥሮስን ድራማ አዘጋጅተው ሳይጨርሱ ምጽአት ደርሶ ራሳቸው አቡነ ጴጥሮስ ይነሣሉ፡፡
በመንደሩ ሜዳ ለተጫዋቾች ኳስ ሲያቀብል የኖረው ሁሉ «ታዋቂ ተጨዋች» ሆኗል፡፡ በየስቴቱ የጤና ቡድን አሰልጣኙ እርሱ ነው፡፡ 
ወጣቶቹ እንኳን በሽታው ተጋብቶባቸው የዚህ ማኅበር አባል ነበርኩ፣ እዚህ ሰንበት /ቤት ያደግኩ ነኝ፣ ባሕታዊ እገሌን አውቃለሁ፣ የአቡነ እገሌ አብሮ አደግ ነኝ፣ ይህንን እና ያንን ገዳም ተሳላሚ ነበርኩ፣ ለዚህ ክለብ በቡድን ተጫውቻለሁ፣ ሚኒ ሚዲያ አቅራቢ ነበርኩ የማይል አታገኙም፡፡
ጥቂትም ቢሆን የሚያወራው ታሪክ ያጣው የኔ ቢጤ ደግሞ ስለ ወንዙ፣ መንደሩ እና ጎሳው ይተርካል፡፡ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የትግራይ፣ የወለጋ፣ የሐረር፣ የአርባ ምንጭ ልጅ ነኝ የሚሉ አያሌ ካናቴራዎች አሜሪካ ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ካናቴራዎች በየአበሻው ደረት ላይ ታዩዋቸዋላችሁ፡፡ የአዲስ አበበ ልጆች ታድያ የሰሜን የደቡብ ብለው የሚከፋፈሉበት ቢያጡ «የፒያሳ፣ የአራት ኪሎ፣ የሽሮ ሜዳ፣ የላፍቶ፣ የኮተቤ ልጅ» የሚል ካናቴራ አሳትመዋል፤ ማን ከማን ያንሳል፡፡
ወደው እንዳይመስላችሁ፤ ሠርታችሁ ከምታሳዩ ይልቅ ታሪክ ስትተርኩ እና መደገፊያ ሲኖራችሁ ቦታ ስለምታገኙ ነው፡፡
አንዳንዶቹ ዘመዶቻችን አሜሪካ መጥተው ያሰቡት አልሳካ፣ እንዳለሙትም አልሆን ይላቸዋል፡፡
አሜሪካ ላይ ወድቄ ብነሣ
መላው አካላቴ ወርቅ ይዞ ተነሣ
የሚል ዘፈን ሰምተው ተመስጠው የሞቀ ሥራ፣ የደመቀ ቤት፣ የጦፈ ንግድ፣ የተንደላቀቀ ኑሮ ጥለው ይመጡና «ያሰብኩት ተሳካ፣ ያለምኩት ሆነልኝ» የሚለው ዘፈን እዚህ ሲደርሱ እንደ ሰማይ ይርቅባቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ታድያ ከሥነ ልቡና ኪሳራ እንደ መውጫ የሚያገለግላቸው ታሪክ ላይ መተኛት ነው፡፡
አገር ቤት ጥለውት ስለመጡት ምርጥ ቤት፣ ስለነበራቸው የኮራ ሥራ፣ ያገኙ ስለነበሩት ጫን ያለ ደመወዝ፣ ስለ ስለ ነበራቸው ላቅ ያለ ሥልጣን፣ ስለ ተማሩት ትምህርት ማውራት ይጀምራሉ፡፡ ሰውም ስለ እነርሱ ሲነግራችሁ አሁን የሆኑትን አያነሣላችሁም፡፡ «አገር ቤት ምን የመሰለ ሥራ ነበረው፤ ኤን ጂኦ ነበር የሚሠራው፤ ሃያ ብር የሚከራይ ቤት አለው፤ የዚህ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ነበርኮ» ይላችኋል፡፡ ታሪክ፡፡
በነገራችን ላይ የአሜሪካ ኢኮኖሚ ያጋጠመው ድቀት ኢትዮጵያውያንን በሁለት መልኩ ጎድቷቸዋል ይባላል፡፡ የመጀመርያው እንደማንኛውም የሀገሩ ነዋሪ የአንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችን መቋረጥ፣ ከሥራ መፈናቀል፣ ተጨማሪ ሥራ ለማግኘት አለመቻል እና የዋጋ መናር አጋጥሟቸዋል፡፡
የኢኮኖሚ ድቀቱ ያመጣው ሌላም ችግር አለ፡፡ ሁለት ሥራ ይሠሩ የነበሩት አንደኛውን በማጣታቸው፣ አንድ ሥራ የነበራቸውም ከሥራ በመሰናበታቸው ለወሬ የሚሆን ሰፊ ጊዜ ተገኝቷል፡፡ እናም አሜሪካ ውስጥ በአበሾች ዘንድ ወሬ ጨምሯል፡፡ ወሬ ሲጨምር ደግሞ ታሪክ ላይ የሚያስተኙ ወሬዎችም ይጨምራሉ፡፡  

43 comments:

 1. Good points Dani. But take care of keeping the standard of your articles. To be honest, I did not found this one as appealing as others, not due to the substance but your expressions. Pleae, focus on the quality of your articles. Thanks.

  ReplyDelete
 2. Hello Dani....I like it. Habeshan Liklikun yeminegir ewunetegna signe des yilal. Berta.

  ReplyDelete
 3. flipos embete esdrossAugust 23, 2011 at 8:59 AM

  አሜሪካ ላይ ወድቄ ብነሣ
  መላው አካላቴ ወርቅ ይዞ ተነሣ good saying

  ReplyDelete
 4. ቸ ጤና ይስጥልኝ ዳኒ ይሄ ታሪክ ላይ መተኛት ኢትዬዽያዊ ባለበት ያለ ችግር ይመስለኛል።ምክንያቱም እኔ በምኖርበት እስራኤልም እኔ ታዋቂ እንትን ነበርኩ፤ከእገሌ ጋ ሰርቻለሁ ወይም ሰርቻለሁ የሚሉ፣ከእነሱ ወዲያ የሚያውቅ ያለ የማይመስላቸዉ፣በአጠቃላይ እነሱን ያላማከለ ስራ እርባና ቢስ እንደሆነ የሚያስቡ አሉ።የሚገርመዉ ሠዉ እራሱ የሚሰጣቸዉ ቦታ ነዉ።ምክንያቱም እሱ እኮ ታዋቂ እንትን ነዉ ስለሚባል ነዋ ኪ ኪ ኪ ታዲያ የኔ ቢጤዉ ምን ይዋጠዉ ለሁሉላችንም ልቦና ይስጠን ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 5. gerume eyeta. kale hywot yasemalen Dany

  ReplyDelete
 6. Nigusie from Dz
  Dn.Dani thank you! this is really which is written on bible before for a gays say we are from Abrham relatives but they didn't found with a single act as Our Father Abrham God blessing

  ReplyDelete
 7. WOW! WHERE YOU GET IT?

  ReplyDelete
 8. We all love u Dani!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 9. ደሳለኝ ወንድሙAugust 23, 2011 at 10:18 AM

  ዳኒዬ ይኼኛው ጽሁፍህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ እኔ ከጻፍክላቸው ሰዎች አንጻር ወጣት ስለሆንኩ ታሪካቸውን አላውቅም፡፡ አንተም እንደጠቀስከው ስለነሱ በጽሁፍም አላውቅም፡፡ ባንተ ብቻ ትንሽ ተገነዘብኩ፡፡ ሆኖም በዚህ ጽኁፍኅ የትችት ዘየቤህ ከቁምነገሩ ይልቅ ሹፈቱ በዛ ያለ መሰልኝ፤ ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ገና ብዙ የምትጽፈው ቁምነግር ስላለህ በነዚህ አይነት ሰዎች እንድትጠቆር አልፈልግም፤ ማለቴ ሳታብጠለጥላቸው ጽፈኸው ቢሆን ኖሮ እንዲህ አልልህም ነበር፤ እውነትን እስከጻፍክ ድረስ በርታ ብቻ ነው የምልህ፡፡ አጻጻፍኅን ብቻ ትንሽ ለዘብ አድርገው ለማለት ነው እንጅ … ጻፍ፡፡ በዚኅኛው ጽኁፍኅ ብቻ ነው እችን የግል አስተያየቴን ለመስጠት የደፈርኩት … ሆኖም አንተ ትክክል ልትሆን ስለምትችል አስተያየቴን ችላ ልትለው ተችላለህ፤ የጉዳዩን በህሪይ ካንተ ከጻፍከው በላይ አንባቢው እኔ ልረዳው ስለማልችል፡፡ ብቻ ለራሴም ላንተም ስል ስለማስብልህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይጠብቅልን ከሁሉ ቤተሰብህ ጋር፡፡

  ReplyDelete
 10. Great article, Be tarik lay metegnat yet yihon yemikerew???!!!!

  የአዲስ አበበ ልጆች ታድያ የሰሜን የደቡብ ብለው የሚከፋፈሉበት ቢያጡ «የፒያሳ፣ የአራት ኪሎ፣ የሽሮ ሜዳ፣ የላፍቶ፣ የኮተቤ ልጅ» የሚል ካናቴራ አሳትመዋል፤ ማን ከማን ያንሳል፡፡

  ReplyDelete
 11. ደሳለኝ ወንድሙAugust 23, 2011 at 10:39 AM

  ዳኒዬ ይኼኛው ጽሁፍህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ እኔ ከጻፍክላቸው ሰዎች አንጻር ወጣት ስለሆንኩ ታሪካቸውን አላውቅም፡፡ አንተም እንደጠቀስከው ስለነሱ በጽሁፍም አላውቅም፡፡ ባንተ ብቻ ትንሽ ተገነዘብኩ፡፡ ሆኖም በዚህ ጽኁፍኅ የትችት ዘየቤህ ከቁምነገሩ ይልቅ ሹፈቱ በዛ ያለ መሰልኝ፤ ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ገና ብዙ የምትጽፈው ቁምነግር ስላለህ በነዚህ አይነት ሰዎች እንድትጠቆር አልፈልግም፤ ማለቴ ሳታብጠለጥላቸው ጽፈኸው ቢሆን ኖሮ እንዲህ አልልህም ነበር፤ እውነትን እስከጻፍክ ድረስ በርታ ብቻ ነው የምልህ፡፡ አጻጻፍኅን ብቻ ትንሽ ለዘብ አድርገው ለማለት ነው እንጅ … ጻፍ፡፡ በዚኅኛው ጽኁፍኅ ብቻ ነው እችን የግል አስተያየቴን ለመስጠት የደፈርኩት … ሆኖም አንተ ትክክል ልትሆን ስለምትችል አስተያየቴን ችላ ልትለው ተችላለህ፤ የጉዳዩን በህሪይ ካንተ ከጻፍከው በላይ አንባቢው እኔ ልረዳው ስለማልችል፡፡ ብቻ ለራሴም ላንተም ስል ስለማስብልህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይጠብቅልን ከሁሉ ቤተሰብህ ጋር፡፡

  ReplyDelete
 12. u right Dani. u really explained the real personality of Ethiopians.

  ReplyDelete
 13. dani endet ayehelegne benateh
  hulgeze yemegermegnen neger newu yehe neger SEDET LEWORENA LEPHOTO yemechal
  semachenen senekolrl lelawu negerachen tenedo aleke
  eski amelake beka yebelen
  SOFINIYAS.A

  ReplyDelete
 14. Dn. Danny, its really a nice article for those who have mind.....enamsegenalen for sharing eshi?

  Thanks

  ReplyDelete
 15. Dany what a nice view, u know what surprised me, the Addis Ababa divission there, what is going on there? God bless Ethiopians in USA. Fikremariam s

  ReplyDelete
 16. ተው አንተ ሰው ከዲያስፖራው አታቀያይመን፡፡ በሰው አገር ሲኖሩና በራስ አገር ሲኖሩኮ የአስተሰሳሰብ ጣቢያው ይለያያል፡፡ በሰው አትፍረድ፡፡ አንተም ተመላላሽ ሆነህ ነው እንጂ ቋሚ ተቀማጭ ስትሆን ሳትቀላቀል አትቀርም፡፡ ጽሑፉ ለኔ እንደ እብድ ለብቻዮ ፍርስ አድርጎ አስቆኛል፡፡ በከፊልም ቢሆን እውነታውን ስለማውቀው፡፡ ሌሎችን ግን እንዳያስኮርፍብህ ስጋት አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 17. I was impressed with the first part of this series and was looking forward to the second one. But it did not come close to the first one. Compared with the first one, this has less educational value. Indeed it is more fluff than substance.

  Besides the substance, I have come to expect a certain style/quality of writing from you that even when I disagree with your points, I enjoy the writing. This one does not have neither substance nor the quality that I have come to expect.

  You have proved yourself to be one of the influential short story writers of our generation(IMO) and I am sure you will continue to produce more quality articles in the future.

  BTW, congratulations on on being awarded the Ambassador of Peace award.

  ReplyDelete
 18. Nice view... Always we get something from your article. Keep on writing Dani!

  ReplyDelete
 19. Dani Gudih

  Ke America Ye Ariticle tekus tetekuso Gadfin enaymet.... Tsaf gn be akbrot... endatasdeb eshi....

  ReplyDelete
 20. ማንነትህን በዚህ መልኩ ማሳወቅህ ምን ይሉታል?
  ለየልህ ልበል?

  ReplyDelete
 21. Thank you Dn. Dani
  I really like it. I am recent immigrant to USA and unable to listen the talks of many people. To your surprise there are people who do not know the fall of Derg. I had met a person who talked about the situation during the Derg era.
  The problem is also in Church as well in USA. Some people consider themselves as the key to the survival of the church.
  One thing I can say to all Ethiopians who lives in USA is that:- ... live in a very developed and civilized nation, lets wake up and go with the current situation.Our fathers and mothers did lot of history for us, We have to have our own history for the next generation as well. Talking about history will take us nowhere. Let us keep our fathers history and add our own.

  Wake up Wake up Wake up!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 22. hahahahaha Yaseqeh!Erasean Ande Tege Laye Betetsafe Manenet Agegnehut! Endih Lek Lekachen Yemineger Neqwri Ayasatan!

  ReplyDelete
 23. ጥሩ እይታ ነው እንደተለመደው ዳኒ:: በርታ አምላክ ያበርታህ:: ጽና:: ማስኮረፍ ምናምን አያሳስብህ:: እኛ ሁልጊዚ እውነትን መሸሽ እንወዳለን:: ካኮረፉ እራሳቸውን እየዋሹ እንደሆን ህሊናቸው ይነግራቸዋል ከሱ ማምለጥ አይቻልምና::ከታቻለ እኒም የደረጀ ሃይሊን ዳያስፓራው ቀልድ ልጋብዛቸው: http://www.youtube.com/watch?v=GWtWHZnDYRg በተረፈ ግን ጽሁፎችህ ትውልድ የሚቀይሩ ናቸው:: የምንማረው እየተማርን ነው:: GOD BLESS YOU!!!

  ReplyDelete
 24. no word...............

  ReplyDelete
 25. Dear Daniel,

  Everybody has a wierd history. I am really faded up to listen unrecorded histories of idividuals. To my observation almost most of the people couldn't compete in Ethiopia. Everybody is leaving with defence mechanism. Shame for them.

  ReplyDelete
 26. I agree with some of the comments given above that your article started with a good substance in part one and failed to address some thing important in the second one. It is just "gossips" that the day to day diaspora talks about. It does not criticize the main cause of the behavior you are describing!

  ReplyDelete
 27. Dani Again yeleben new yetsafekew. Ezeh yalu kelay yetsafekachew Wegenocha tiliku chegerachew Americawew erasun bedenb megeletsena sele manenetu mawerat selemewed enesu minim selerasachew yemeyawerut selelele washetew yalehonuten honew tilik meselew lemetayet yemeyaderegut teret new. seretew terew gerew ye Americanen dream yemebalewen amaletew selerasachew edemawerat hule be tizeta gezeyachewen yegelalu.
  Dani yehenen ewenet bemetsafeh bezu wegezet edemederesebeh awekalehu Egezeabher kekifu neger yesewereh.
  MELAW

  ReplyDelete
 28. ጥሩ ምልከታ ነው በርታ።

  ReplyDelete
 29. ሠላም ላንተ ይሁን ዲ/ን ዳንኤል! ተወደደም ተጠላም፣ ተቀበልነውም አልተቀበልነውም ዲሲ እና አካባቢው ያለው አንዳንዱ ሰው (አብዛኛው ለማለት ቢከብደኝም) ራሱን ሆኖ ሳይሆን፣ አንተ በትክክል ባስቀመጥከው መልኩ ራሱን እየካበ፣ ሌላውን እያኮሰሰ የሚኖር ነው። "አልሰሜን ግባ በለው" አሉ። ከሁሉም በላይ የሚያሰለቸው ግን "ከንጉሣውያን ዘር ነን" የሚሉቱ ናቸው። ጎበዝ! ይህ አሉባልታ አይደለም፤ አገር ቤት ሄደው DNA ያስመረመሩ ሰዎች (እኔም በግል ከማውቃቸው ውስጥ) እንዳሉም ደርሼበታለሁ። ነገሩ ግራ ስላጋባኝ መነሻቸው (ምክንያታቸው) ምን ሊሆን እንደሚችል ለመመራመር ሙከራ አድርጊያለሁ። የደረስኩበት ነገር አንድም አሳዛኝ ነው አልያም የሚያሳፍር ነው። ችግሩ ጎልቶ የሚታየው ደግሞ ወላጆቻቸው ቤተ መንግሥት ሲሠሩ ወይም ወጣ ገባ ማለት ያዘወትሩ የነበሩቱ ላይ ነው። ትንሽ 37 ዓመት ወደኋላ ልመልሳችሁና (የንጉሡን ዘመን ለማስታወስ ነው) ጃንሆይ ዕቁባት በማብዛት የታወቁ ነበሩ። እንደ ንጉሥ ዳዊት፣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን። መንገድ ላይ እንኳ ቆንጆ ልጅ ሲያዩ መኪና አስቁመው ያስጠሩ እንደነበረ በወቅቱ ከነበሩ ሰዎች ሰምቻለሁ። በወቅቱ በዕድሜ ልጅ የነበርኩ ቢሆንም "እገሊት የጃንሆይ ቅምጥ ናት" እየተባለ ሲነገር፤ ቆንጆ መኪና እና ቤት ይሰጣቸው እንደነበረም አስታውሳለሁ። በመሆኑም፣ የጃንሆይን “አይምሬነት” የሚያውቁ አንዳንድ ልጆች (የአሁኖቹ ጎልማሶች) እናቶቻቸው ሳይንበረከኩላቸው እንደማይቀር "በመገንዘብ" ራሳቸውን ከንጉሣውያን ቤተሰብ ደምረው ያቀርባሉ። በዚህም ምክንያት አንዳንድ ባለጌዎች ለእናቶቻቸው እንደዚህ ዓይነት አሳፋሪ ጥያቄ በማቅረብ "ዓይንህ ለአፈር" ተባብለው የተለያዩ እንዳሉም ደርሼበታለሁ። አሳዛኝም፣ አሳፋሪም ነው። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ግን ሰው ያላወቀላቸው የአዕምሮ በሽተኞች ናቸው።
  ከዚህ ውጪ፣ ራሳቸውን በሌላቸው እና ባልሆኑት ነገር መካቡ እንዳለ ሆኖ፣ አንድ የሚያውቁትን ሰው (ያ ሰው በመልካም ምግባሩ/ተግባሩ በሚሠራበት አካባቢ ሊታወቅ ቢችልም በሕዝብ ዘንድ ታዋቂም ላይሆን ይችላል) ስም በመጥቀስ ከሱ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው፣ አብሯቸው “እንደሚሠራ” (በተለይ ፖለቲከኞቹ አካባቢ)፣ በዚህም ሳቢያ ብዙ ኢንፎርሜሽን እንደሚያገኙ የሚለፈልፉ በርካታዎች ናቸው። የሚገርመው ነገር ግን፣ ያ ስሙ የሚነሳው ሰው ስለ ሁኔታው ምንም የሚያውቀው ነገር አለመኖሩ ነው። ባላወቀው ነገር አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በጠላትነት ሲፈርጁት “ምንድን ነው ነገሩ?” ብሎ ሲመራመር ነገሩ ይገለጽለታል። ያልጠበቀው አደጋም ሊያጋጥመው ይችላል።
  በተረፈ፣ አብዛኞቹ ኑሮዋቸውን ለማሸነፍ ስለሚሯሯጡ አልባሌ ነገር (ቦታ) ላይ አይታዩም። ሁላችንም ልንገነዘበው የሚገባው ነገር የተሻለ ሕይወት ለማግኘት ከድሀ አገር መምጣታችንን፣ አውርተን ሳይሆን ሠርተን የራሳችንን እና የቤተሰቦቻችንን (የወገኖቻችንን) ሕይወት መቀየር እንዳለብን፣ አገር ቤት የነበረንን ማንኛውንም ነገር (ዕውቀታችንን፣ ኪሳችንን፣ ምግባራችንን፣ አዕምሮአችንን… ወዘተ) አሳድገን ካለፈው ተሽለን መገኘት እንደሚገባን፣ ያለፈው ማንነታችን አሜሪካን አገር ስም እንጂ ዳቦ እንደማይሆነን ማወቅ ነው። መከበር በአገር ቀረ። ሌላው ቁም ነገር፣ ራሳችንን ከጊዜው ጋር ሳናራምድ የቀረን እንደሆነ፣ ዘመኑ አንድ ሁለት እያለ ወደ ፊት በሄደ ቁጥር አስተሳሰባችን አገር ቤት ካለው ወገን ጋር ሲነጻፀር አንድ ሁለት እያለ ወደ ኋላ መሄዱ ነው። በመሆኑም፣ እስከጠቀመን ድረስ አንዳንድ ትችቶችን በጸጋ እንቀበል። ባይዋጥልንም እውነታውን መቀበል ግን ግድ ይላል። ያለበለዚያ ከአገር መሰደዳችን ምንም ፋይዳ አይኖረውም። እግዚአብሔር ይርዳን! ለሁላችንም ፍቅር ይስጠን!

  ReplyDelete
 30. Part 2 is way below standard as compared to both part 1 and all your previous posts. Teraa Hamet Naw Yemimeslew

  ReplyDelete
 31. Now a days ethiopians are running for money and dignity rather than thinking about their country.

  ReplyDelete
 32. grume new dani,enem yedejazmach haylu kibret yehtachew yelije lije negne....

  ReplyDelete
 33. kib
  ...ስለ ወንዙ፣መንደሩ እና ጎሳው ይተርካል፡፡ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የትግራይ፣ የወለጋ፣ የሐረር፣ የአርባ ምንጭ ልጅ ነኝ የሚሉ አያሌ ካናቴራዎች አሜሪካ ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ካናቴራዎች በየአበሻው ደረት ላይ ታዩዋቸዋላችሁ፡፡ የአዲስ አበበ ልጆች ታድያ የሰሜን የደቡብ ብለው የሚከፋፈሉበት ቢያጡ «የፒያሳ፣ የአራት ኪሎ፣ የሽሮ ሜዳ፣ የላፍቶ፣ የኮተቤ ልጅ» የሚል ካናቴራ አሳትመዋል፤ ማን ከማን ያንሳል...

  ReplyDelete
 34. Dn Daniel , ekuan adereseh
  anjeten araskew !! betam eko aschegari new sew ene endih negn kalalkew degmo yemidersibih tata ayital new.tarik feteari yemihonutim wedew ayidelem. beqa yewere timat wuuuuuuu
  thanks

  ReplyDelete
 35. ageligilotih yibarikilih wud dn daniel.tiru hasab new yesetehegn gin and tiyaqe liteyikh felegikugn ene mesrat balchilim hagere endih nat bilo's tarik lay metegnat yichalal? eski kechalik(if u have time)silezih guday asnebiben
  GOD BLESS YOU AND YOUR FAMILY

  ReplyDelete
 36. Alex Lexington, USAAugust 26, 2011 at 2:07 PM

  Hi Dani it is a very good comment but I suggest you present the other part of the diaspora in your next comment. I believe there are hard working and successful diasporas from whom we can learn a lot.

  ReplyDelete
 37. it is known that to day we ethioopians have been fragmented on many aspects. the root cause of the problem is the ethno-centric political program of this regime. yesterday, we ethiopians were united with the same and harmoniosu relationship and view. but to day, that is not the case. may God bring good days to ethiopia!

  ReplyDelete
 38. ይገርማል! መድሃኒት የሆነ ፅሁፍ! ከተኛንበት የታሪክ ፍራሽ ላይ እንድንነሳ እንዲህ ያለ ብዕር ያስፈልገናል፡፡
  ስመኝ

  ReplyDelete
 39. Here we go...the known spiritual person and preacher whom some ppl call him ' Talaq wendim, Yelibim sew' engulfed in gossips and rumors ...what is next ? May be as a 'political party leader'....shame....

  ReplyDelete
 40. በፅሁፍህ ውስጥ“ወደው እንዳይመስላችሁ፤ ሠርታችሁ ከምታሳዩ ይልቅ ታሪክ ስትተርኩ እናመደገፊያ ሲኖራችሁ ቦታ ስለምታገኙ ነው፡፡” ያልከው ምንም አስተያየት ከመስጠት እንድቆጠብ አድርጎኛል፡፡ ምክንያቱም በደንብ ይገልፃቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 41. Hey bro,Where U going?I read most of your articles,i have not seen one like this.Appreciation may sometimes make people to be lost.Take Care

  ReplyDelete
 42. በለው በለው፤መልዕክትህ እንደውሀ የሚጠርግ ቢሆን ኖሮ ጠራርጎ ወደ አትላንቲክ በጨመረን ነበር፤ መማር ካለብን የምንማርበት ጊዜ
  አልፎ በባከነ ጊዜ ደውል እየመታህ ነውና በርታ፤ዳ.ዳናኤል ግና “በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዳይሆን..”በፅሁፍህ መስታወት እኔነትን እንመልከት።
  ምኞቴ ብዙነህ @ከፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete