Saturday, August 20, 2011

ታሪክ ላይ መተኛት (ክፍል አንድ)እዚህ አሜሪካ ስመጣ ሁልጊዜም የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፡፡ በኢትዮጵያ አዲሱ ትውልድ ዘንድ የተዘነጉ አካላት እዚህ እንደ ትኩስ ወጣት ሲራወጡ አያለሁ፡፡
ከዛሬ አርባ እና ሃምሳ ዓመታት በፊት ወጣቱን፣ ገበሬውን፣ ወዛደሩን፣ ሴት እና ወንዱን ከጎናቸውም ሆነ ከኋላቸው ያሰለፉ፤ በሕፃን በዐዋቂው አንደበት እንደ ውዳሴ ማርያም በየሰዓቱ ስማቸው ሲነሣ የነበሩ፤ ልጅ ሆነን እንኳን በስማቸው እንጫወት የነበሩ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች መኖራቸው ትዝ የሚለኝ እዚህ አሜሪካ ስገባ ነው፡፡
ጋዜጦቹ፣ ሬዲዮዎቹ፣ ዌብ ሳይቶቹ እና የስብሰባ መጥሪያ ወረቀቶቹ እነዚያን አዛውንት ፓርቲዎች እና ድርጅቶች ስም ያነሣሉ፡፡ ከዚያም አልፎ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ከእነዚሁ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች በተያያዘ ስማቸው ሲነሣ ይሰማል፡፡
አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በንቁ ተሳትፎ ያለው ትውልድ ከሰባዎቹ አጋማሽ በኋላ የመጣው ነው፡፡ ኢሕአፓ፣ ኢዲዩ፣ መኢሶን፣ ኢጭአት፣ የዘውድ ምክር ቤት የሚባሉትን ድርጅቶች ከሰማበት ይልቅ መጀመርያ ስለ ደርግ እና ኢሠፓ፣ በኋላም ስለ ኢሕአዴግ፣ መዐሕድ፣ ኦነግ፣ ቅንጅት፣ ኅብረት፣ ኦብኮ፣ ወዘተ የሰማበት ዘመኑ ይበልጣል፡፡ የግራ እና የቀኝ፣ የፊት እና የኋላ ፓርቲ ታሪክ እምብዛም ቁቡ አይደለም፡፡
አንድ ወዳጄ እንዲያውም «ስለ ኢዲዩ ታውቃለህ ብዬ ስጠይቀው «ይኼ ስድስት ኪሎ ያለው ምግብ ቤት ነው ብሎኛል፡፡ ስድስት ኪሎ ኢዲዩ ቤት የሚባል ምግብ ቤት አለ፡፡ እርሱ የሚያውቀው ኢዲዩ ያንን ነው፡፡
የቀድሞ ታሪካችንን የምናይበት ሙዝየም እንደ ልብ በሌለበት፣ ስለ ቅርቡ ታሪካችን የሚተርኩ መጻሕፍት በብዛት ባልታተሙበት፣ ቢኖሩም የማንበብ ልምዳችን ጨቅላ በሆነበት፣ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ተዋናይ እና ሙዚቀኛ የነገሡባቸው ኤፍ ኤሞች በሞሉበት ማኅበረሰብ ውስጥ፣ የዛሬ አርባ ዓመት የነበሩ ድርጅቶችን ማስታወስ፣ አስታውሶም ከእነርሱ ጋር መሥራት የማይሞከር ነው፡፡
ያውም ብዙዎቹ መሠረታቸው አሜሪካ፣ መናገርያቸው የአካባቢ ሬዲዮ፣ መጻፊያቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በጭንቅ የሚገኝ ዌብ ሳይት፣ የሚሰበሰቡት ቨርጂንያ፣ ቦስተን፣ አትላንታ እና ዲሲ በሆነበት ሁኔታ የዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ትውልድ መኖራቸውን በምን ያውቃቸዋል? የሀገሬ ነዳይ እናንተ የምታዩኝ እኔ የማላያችሁ ይላል፡፡ እነዚሀን ደግሞ እናንተ የማታዩኝ እኔም የማላያችሁ ሳይል አይቀርም፡፡
አንዳንድ ጊዜ በሬዲዮአቸው ኢትዮጵያን እንዲህ እናደርጋለን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲያ ለመሥራት እያሰብን ነው እያሉ ሲናገሩ ስሰማ እነዚህ ሰዎች ታሪክ ላይ ተኝተዋል እላለሁ፡፡ አሁንኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢሕአፓ የፓርቲ ስም ይሁን የቦታ ስም፣ ኢዲዩ የምግብ ቤት ስም ይሁን የትምህርት ቤት፣ መኢሶን የወጣት ማኅበር ይሁን የሴት ሰምቶ የማያወቅ ትውልድ እየተነሣ ነው፡፡ አንደኛ ነገር በዘመናቸው አልነበረም፣ ሁለተኛ ስለ እነርሱ በትምህርት ቤት፣ በሙዝየም፣ በጋዜጣ፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቭዥን አይማርም፣ አያይም፣ አይሰማም፡፡ ታድያ እንዴት ነው ሊያውቃቸው የሚችለው?
አንዳንዶቹ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ሬዲዮ አለን ይላሉ? ከዚህ ይላክ ይሆናል፣ ከዚያ ግን መሰማቱን እጠራጠራለሁ፡፡ እነርሱን የሚወደው የሚያደንቀው፣ በልቡ ጽላት ስማቸውን የጻፈው፣ ስማቸው ሲጠራ ደሙ የሚሞቀው ትውልድኮ ወይ ተሰዷል፣ ወይ አልፏል፣ ወይ ቀዝቅዟል፣ ወይም ደግሞ ዘንግቷቸዋል፡፡
አንዳንዶቹ እንዲያውም ትክክለኛው የዚህ እና የዚያ ፓርቲ ወራሽ እኔ ነኝ እኔ ነኝ እያሉ ሲከራከሩ ስሰማ፣ ግራ እጃቸውን አውጥተውም «እገሌ ያቸንፋል/ያሸንፋል» ብለው ሲፈክሩ ሳይ የት ቦታ ሆነው ነው የሚያሸንፉት እያልኩ እገረማለሁ፡፡
አብዛኞቹ ይህንን መሰል ድርጅቶች ላለፉት አርባ ዓመታት በተመሳሳይ ሰዎች የተመሩ ናቸው፡፡ ስለ በለሳ፣ አሲምባ፣ ደደቢት፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ የትግራይ እና ኤርትራ በረሃዎች፣ የሱዳን ስደት፣ ስለ ማርክሲዝም እና ሌኒኒዝም፣ ስለ አድኃሪ፣ አቆርቋዥ፣ አናርኪስት፣ ትሮትስካይ፣ ማኦይስት፣ መሐል ሠፋሪ፣ አጎብዳጅ፣ የሚያወሩ ናቸው፡፡
ለእነርሱ አሁንም ዲሞክራሲያ የምትባል መጽሔት አለች፡፡ ይህ ትውልድ ግን ከመስከረም መጽሔት ተነሥቶ በየካቲት በኩል፣ ጎሕ፣ ጦቢያ፣ ሠይፈ ነበልባል፣ አስኳል፣ ሩሕ፣ ላይ አርፎ፣ በዚያም ተሸጋግሮ እነ ላይፍ፣ ፋሽን፣ ጽጌረዳን አንብቦ ዕንቁ፣ ቁም ነገር፣ አዲስ ጉዳይ እና ዘመን የሚባሉ መጽሔቶች ላይ ደርሷል፡፡
«ይድረስ ለሰፊው ሕዝብ» እያሉ የሚያወጡትን መግለጫ እንዴት ለሰፊው ሕዝብ እንደሚያደርሱት እንጃ፡፡ ወይንም ይህ ሰፊው ሕዝብ የሚባለው የኢንተርኔት ቅርበት ያለው ሊሆንም ይችላል፡፡ እንዲያውም በአንዱ የድርጅት ዌብ ሳይት ላይ ድርጅት በመከፋፈሉ «መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንገቱን ደፍቷል» የሚል በቀይ የተሠመረ ሐረግ አንብቤያለሁ፡፡ ይኼ «መላው» የሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ በአገር ቤት ያለነው ሰማንያ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የለንበትም እንዴ!
እነርሱ አሲምባ ላይ እገሌ ከዳ፣ ሱዳን ላይ እገሌ ምሥጢር አወጣ፣ መርሐቤቴ ላይ እገሌ ድርጅት ከፈለ፣ ጠገዴ ላይ እነ እገሌ እጅ ሰጡ፣ እያሉ የሚንገበገቡበትን ነገር ይህ ትውልድ ከልቡ ጠብ አያደርገውም፡፡ ይህ ትውልድ የኢሕአዴግ እና የቅንጅት ትውልድ ነው፡፡ የተሳተፈውም፣ የሞተውም፣ የተሰለፈውም፣ የሰማውም ስለ እነርሱ ነው፡፡
ሰዎቹ አሜሪካ ይሁኑ እንጂ አሁንም ዌብ ሳይቶቻቸው ከበረሃ አልወጡም፡፡ የሚያወጧቸውም መጻሕፍት የማሳረጊያ ቃላቸው «እንግዲህ ትውልድ ፍረደን» የሚሉ ናቸው፡፡ የማያውቃቸው ትውልድ እንዴት ይፈርዳቸዋል?
በታሪክ ላይ መተኛት ትልቅ በሽታ ነው፡፡ ትናንት በነበረው ነገር ተቆጭቶም ይሁን ኮርቶ ከትናንቱ አዙሪት አለመውጣት፣ የማሰቢያ መሣርያውንም «ትናንት» ማድረግ፣  ፍርድ እና ውሳኔንም በትናንት ላይ ብቻ ተመሥርቶ መስጠት ነው ታሪክ ላይ መተኛት፡፡
አንዳንድ ጊዜ በአንዳንድ ምግብ ቤቶች፣ ግብዣዎች፣ መርሐ ግብሮች እና እንዴው በእግረ መንገድም አንዳንድ ሰዎችን «ይኼን ሰውዬ ታውቀዋለህ» ሲሉኝ እንዳጋጣሚ ሆኖ ብዙዎቹን አላውቃቸውም፡፡ «ይህኮ የዚህ ፓርቲ ሊቀመንበር ነው፣ መሥራች ነው፣ የታወቀ ነው፣ በሬዲዮ ስሙን ሰምተህ አታውቅም፣ እንትን የተባለ ፓርቲን እየመራ ከጎንደር፣ ከትግራይ፣ ከወለጋ፣ ከጎጃም፣ ሱዳን የገባኮ ነው፤ ኃይለኛ ሰው ነው» ይሉኛል፡፡
አስበዋለሁ፡፡ ስሙን ስሰማ ያነበብኳቸውን መጻሕፍት እና ዌብ ሳይቶች አስባለሁ፡፡ ታድያ በኋላ አገሬ ገብቼ ከጓደኞቼ ጋር ስናወራ መከራዬን አያለሁ፡፡ እነርሱ እንዲያ የሚባል ጦር መኖሩን፣ ተመርቶ ሱዳን መገባቱን፣ ጭራሽም እንዲያ የሚባል ድርጅት መኖሩን አልሰሙም፡፡ ምን ላድርጋቸው?
አንዳንዶቹ አሁንም ስለ «ጠቅላይ ግዛት» የሚያወሩ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ግዛት አልፎ መጀመርያ ክፍለ ሀገር፣ ከዚያ አስተዳደራዊ ክልል፣ ከዚያ ዞን፣ ከዚያ ክልል መምጣቱን እንኳን የሰሙ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዶቹ በአሁኑ ዘመን ብሔረሰቦች የሚጠሩበትን ስም አልሰሙም፡፡ ሌሎቹም ያሸንፋል እና ያቸንፋል በዚህ ዘመን ትርጉማቸው አንድ መሆኑን አላወቁም፡፡ የወዝ ሊግ አልፎ የወጣት ሊግ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መምጣቱን ማን በነገራቸው? የውይይት ክበብ ተረስቶ ሽሽ ክበብ የሚባል ምግብ መምጣቱን ማን ባቀመሳቸው? የሴል ታሪክ ተረስቶ የሴልፎን ታሪክ መምጣቱን ማን በተረከላቸው?
እነዚህ ድርጅቶች አማራጫቸው ሁለት ይመስለኛል፡፡ አንደኛው ራሳቸውን መፈተሽ እና አርባውን ዓመት ተሻግረው ወደ 2003 መምጣት ነው፡፡ የውጩን ትተው በውስጣቸው አብዮት ማካሄድ አለባቸው፡፡ የትናንቱ ታሪክ መነሻ እንጂ መተኛ ሊሆን አይችልም፡፡ አንድ ድርጅት ትናንት ትክክል እና ጠንካራ ተወዳጅም ስለሆነ ብቻ በጥንቱ ቦሎ መንዳት አይችልም፡፡ በየዘመኑ ከሚገኝ ትውልድ ቦሎውን ማሳደስ አለበት፡፡ ለዘመኑ የሚሆን ሥራም መሥራት አለበት፡፡
የትናንት ጥያቄ እና የዛሬ ጥያቄ ይለያያል፤ የትናንት ኢትዮጵያ እና የዛሬ ኢትዮጰያ ትለያያለች፤ የእነርሱ ትውልድ እና የኛ ትውልድ ተለያይቷል፡፡ በተለይ ደግሞ፣ አብዛኞቹ የሚኖሩት በውጭ፣ አዲሱ ትውልድ ደግሞ እየተፈጠረ ያለው በሀገር ውስጥ እንደመሆኑ ርቀታቸውን የአብርሃም እና የነዌ ያደርገዋል፡፡
እስክንድር ባለሟሉን የጠየቀው ጥያቄ እዚህ ላይ ቢነሣ መልካም ነው፡፡
«ለመሆኑ በእስያ የእኔን ታሪክ የሚያውቅ አለ?» አለው፡፡
«በሚገባ» ሲል መለሰለት፡፡
«በአፍሪካስ አለው
«አለ» አለው
«በምሥራቅስ
«በመጠኑ» አለ
«በፋርስስ?»
«ያጠራጥራል»
«በቻይናስ?»
«እነርሱስ መስማት የሚፈልጉም አይመስለኝም» አለው ይባላል፡፡
ቦታ እና ዘመን እየራቀ ሲመጣ የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን ማወቅ የሚፈልግም እየጠፋ እንደሚመጣ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ሁለተኛው እና ከዘመኑ ጋር መራመድ ትውልዱንም ማሰለፍ ካልተቻለ ታሪክን ደምድሞ፣ ዶክመንት እና ቅርስን ወደ ሙዝየም ልኮ፣ ከተቻለም መጽሐፍ ጽፎና ፊልም ሠርቶ፣ መሰናበት ነው፡፡ ከነ ክብር መሞት፡፡ ያለበለዚያ ግን ታሪክ ላይ ተኝቶ የማይሆን ሕልም ማየት ለተመልካቹም ለተርጓሚውም አይጠቅምም፡፡
ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ቨርጂንያ፣ ዱክ መንገድ አጠገብ

29 comments:

 1. ወይ ዳኒ ታድለህ የማታመጣው ነገር የለህ መቼስ፣ እግዚአብሄር አምላክ ረጅም እድሜና ጤናውን ይስጥህ ፣ክፉ አይንካህ፣

  ReplyDelete
 2. Dani Thanks ene hule beweswte yalewen new ahun ante betiru huneta yetsafekew ene ezeh America kemetahu gena 3 amete new gin ezeh kalu politica enawekalen kemelu semoch ga megebabat alchalekum neber ahun yanten tsuf copy eyadereku elekelachewalehu kezemenu ga aberew endehedu wayenem tureta edewetu hulum malet yechalal yemenorut be hilm alem new.Ebakih hulem ke enga teweledem endante yalu awakewoch edalu asayelegn Egezeabher edemehin yarezemelen.
  MELAW

  ReplyDelete
 3. Betam yasikal, yastemiral, yanadidal, ya.....

  ReplyDelete
 4. Dear Daniel,

  I faced the same challenges here in the US. I couldn't agree with the people, who live here. I couldn't find anyone who has a strong idea and the way forward. Everybody talks good for nothing. I don't think people have understanding the actual situation in Ethiopia. One can not tailored the hallucinated idea to his/her own country. What I actually perceived, people classified themselves even which is not realistic in Ethiopia. Oh, God, Let the almighty God Blessed Ethiopia.

  ReplyDelete
 5. "endeh lek lekachinin nigeruna" alu Janhoy. Really timely and great observation. Thanks a lot man

  ReplyDelete
 6. ሰዎቹ አሜሪካ ይሁኑ እንጂ አሁንም ዌብ ሳይቶቻቸው ከበረሃ አልወጡም፡፡ የሚያወጧቸውም መጻሕፍት የማሳረጊያ ቃላቸው «እንግዲህ ትውልድ ፍረደን» የሚሉ ናቸው፡፡ የማያውቃቸው ትውልድ እንዴት ይፈርዳቸዋል? Whst a joke !! lol I like your post Daniel

  ReplyDelete
 7. ያኔ ያኔ የቅንጂት ትኩሳት በኢሕአዴግ ስምንት መግለጫዎች እንኩዋን በረድ በማይልበት ወቅት እዚህ ፈረንጂ አገር ያለ አሲምባዊ ፖለቲከኛ ወዳጄን « ልምድህ እኮ ይጠቅም ነበር ለምን የቻልከውን አታግዝም?» ብዬ ስጠይቀው « ምን ቦታው ሁሉ እኮ ተይዟል ! ምን አደርጋለሁ ብለህ ነው?» ብሎኝ አረፈው። የዚያ ትውልድ ታላላቆች ትልቁ በሽታቸው መምራት እንጂ መመራትን አለመውደዳችው ይመስለኛል። ይህችን መራራ ሃቅ በክትፎና በስምንት ውስኪ አወራርደው መዋጥ ቢችሉ ሌላው ሁሉ ቀስ እያለ ስክት ስክት ይልላቸው ነበር። ምን ዋጋ ዓለው ዐለማቸው እና ዐለማችን በተለያዬ ፕላኔት ላይ ሆነች እንጂ!

  ReplyDelete
 8. Hello The 70th YISEMAL! Let U review, evaluate and update yourself. WIN 98 is archaic be either WIN 7 or Mac version.

  ReplyDelete
 9. በረግጥ እንዳልከው ወያኔ ያሁኑን ትውልድ ምንም ግንዛቤ እንዳይኖረው የትምህርቱን ፖሊሲ በማበላሸት አንብቦ ሬዲዮ ሰምቶ እውቀቱን እንዳያዳብርና ስለ ሀገሩም ሆነ ስለ አለም ሁኔታ ጠቅላላ እውቀት እንዳያገኝ ፕሬሶችን በማፈን ወያኔ እሱንና የርሱን አራጋቢዎች ብቻ ሊኖሩባት የምትችል ሀገር ከመሰረተ 20 አመታት ሞልቶታል በጣም የሚያሳዝነው በዚህ ሂደት ብዙ ልደቱ አያሌዎች መፈጠራቸው ሲሆን ያንተ ደገሞ 11ኛው ሰአት ላይ መሆኑ የባሱን ያስለቅሳል ::
  ጔደኞችህ እነመስፍን እውነትን ስለሚፅፉ ተሰደዱ ብእራቸው ግን ሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው አለም ይነበባል::
  ወንድምየ እንድታውቀው ያህል ኢትዮጵያ ሀይማኖተኛ ነኝ እኔን ብቻ ስሙኝ የማይሉ ስለ እውነት የሚሞቱ ብዙ እስክንድር ነጋዎች አሏት ::

  ReplyDelete
 10. ዳኒ ምልከታህን በጣም አድንቄዋለሁ። "በድሮ በሬ ያረሠ የለም" አይደል የሚለው ብሂሉ

  ReplyDelete
 11. i do not have a word to express my feeling
  thank you

  ReplyDelete
 12. ይድረስ ለሰፊው ሕዝብ» እያሉ የሚያወጡትን መግለጫ እንዴት ለሰፊው ሕዝብ እንደሚያደርሱት እንጃ፡፡ ወይንም ይህ ሰፊው ሕዝብ የሚባለው የኢንተርኔት ቅርበት ያለው ሊሆንም ይችላል፡፡ እንዲያውም በአንዱ የድርጅት ዌብ ሳይት ላይ ያ ድርጅት በመከፋፈሉ «መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንገቱን ደፍቷል» የሚል በቀይ የተሠመረ ሐረግ አንብቤያለሁ፡፡ ይኼ «መላው» የሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ በአገር ቤት ያለነው ሰማንያ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የለንበትም እንዴ
  i love this,,,,,

  ReplyDelete
 13. ትክክል ነህ ዳኒ ግን እንደ ነፃ ተመልካች ኢህአዴግም ህዝቡ መረጃ እንዳይደርሰው የሚያደርገውን አፈናም መጠቆም ይገባህ ነበር:: የተቃዋሚ ዊብ ሳይቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚታፈን እያወክ ፖርቲዎቹን ብቻ መውቀስ በአንድ መልኩ የአንተን ፍርሃት ያሳያል:: በል በነካህ እጀህ እስቲ መንግስት ተች:: ያኔ ለእውነት እንደቆምክ እና የሰላም ሰው መሆንህን እንረዳለን

  ReplyDelete
 14. This is wonderful!

  ReplyDelete
 15. D Daneil selam le ante yihun yekirb wedaji neg yihinn anebebikut betsam des yilal tigermegalehi ahunis anten sayihon fetsarhin amesegenkut sanebew bedesta bizat eyesaku new yalekew tebarek negeru hulu giltsi hak new

  ReplyDelete
 16. ሀገር መምራትና ሀገር መግዛት የተለያዩ ናቸው:: አንተ የጠቀስካቸው ትውልዶች የሐገር “ግዛት” ትውልዶች ናቸው:: ርስት እዚያ አለኝ፤ አንድ ቀላድ ከዚያ ወንዝ ማዶ: ሁለት ቀላድ ከዚህኛው ማዶ በሚባልበት ዘመን ተወልደው ውጋ! ንቀል! ወድር! በሚባልበት ዘመን ደግሞ ለአቅመ አዳም ደረሱና የዕድገት በኅብረት: የመሠረተ ትምህርትና: የመንደር ምሥረታ ዘማቾች ሆኑ:: እናም ዛሬ የሚጽፉልን የውጋ-ንቀሉን ታሪክ ብቻ ሆነብን ወዳጄ::

  እርሱም በሥርዓት ተጽፎ በመጣና ባለማንበባችን በተወቀስን ደስ ባለኝ ነበር:: የአንዱ ዘር ዕንቁ መሆን የአንደኛው ዝቅተኛ መሆን በየዌብ ሳይታቸው አያስፍሩ እንጂ ከልባቸው ሊነቀል አልቻለም:: ያው አይደል “ቤተክርስቲያን”ን ለብቻ እንደ እድር ድንኳን የመትከል አባዜ ያሳደረባቸው? ኢህአዴግም ብሔር ብሔረሰብ በሚል ሽፋን የ“ቴዎሪ” እኩልነት ሲያራግብ እነዚህኞቹ “ለሰፊዉ ህዝብ” የሚጽፉቱ ደግሞ ተቀብለው በየራሳቸው ጓዳ በተግባር መፈጸም ጀመሩ:: እናም “ይሄ ትውልድ” ብሎ ማስተጋባት:: የቱ ነው ይሄ ትውልድ፡ ምንስ በደለው ይሄ ትውልድ:: በራሳቸው ለፈጠሩት አጋንንት ይህንን ትውልድ እሪያ አድርገው መፈረጅ ታሪክ ላይ መተኛት ብቻ ሳይሆን ታሪክን አለማወቃቸውን ከእነርሱ አሻግረን እንድንመለከት እያደረገን ነው:: እነርሱ ያላሳዩንን የትውልድ ፋይዳ ባናይም የጦረኝነት አባዜ አልተጠናወተንም:: ክፉ አመራር ሲመጣብን ችለን ታግሰን ማለፋችን ሊያስመሰግነን እንጂ እንደ አርዮስ ሊያስወግዘን አይገባም:: የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮቻችን ምን ጻፉልን? የትኛውን መጽሐፍ አስቀመጡልን? ያለፉበትን ሥርዓት ጥሩና መጥፎ ጎን መቼ አሳዩን? ዛሬም ቢሆን ስለ ኦክስፎርድ: ስለ ሀርቫርድ... ከሚተርኩ መጻህፍት ባሻገር የትኛውን አስተላልፈውልን ነው ለወቀሳ የተዳፈሩት?! ሀዲስ አለማየሁ በሕይወት ኖረው ቢወቅሱን ደስ ባለን፤ የወቅቱን አምባ ገነንነት በፊታውራሪ መሸሻ አሳይተውናል: ዘመናዊውን ትውልድ በጉዱ ካሳ አድርገው አስተምረውናል፡ የፍቅርን ኃያልነት በሰብለ ወንጌል በኩል አድርሰውናል: የመማርን ጥቅም በበዛብህ በኩል ፍንጭ አሳይተውናል:: በሌው አቅጣጫም ቢሆን ከቅርቡ ብናነሳ ከዘመናዊዉ ትምህርት ደግሞ እነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም የጂኦግራፊን መጽሐፍ ሀገሪቷን በእግራቸው ዞረው መጻፋቸው: ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ የስነ ፍጥረት ሳይንስን (በዮሎጂ) መጽሐፍ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚመጥን መልኩ መጻፋቸው አዎ በድካማችን ውስጥ ድፍረው እንዲወቅሱን ያስችላቸዋል::

  ከዚህ ባለፈ አዎ ይሄ ትውልድ አባይ ላይ ገና ለሚገነባው ግድብ ዋሽንግቶን ዲስ ላይ የማፍረሻ አታሞ ከእነርሱ ጋር ሊመታ አይችልም:: አዎ ይሄ ትውልድ ዘርህን አውቅልሀለሁ የሚለውን ያረጀ ያፈጀ አስተሳሰብ እሺ እወቅልኝ ብሎ ሊቀበል አይችልም:: እዚህም ቢሆን ካልደገፍከኝ ሥራ አታገኝም እየተባለ ማደጉን አይረሳውም: የኔን ቋንቋ ካልተናገርክ “የኔ” ቀዬ ውስጥ መወለድህ እንደ ኃጢያት ይቆጠርብሀል እየተባለ ውስጡ እንክርዳድ እየተዘራ እያደገ መሆኑን አይዘነጋውም:: መቼም ቢሆን መቼ ግን ይህንን ዕይታ ለቀጣይ ትውልድ እንዳሁኖቹ አድርጎ የማያስተላልፍ መሆኑን ሊነገራቸው ይገባል “ለሰፊው ህዝብ ጸሐፊዎች”:: ሀገሪቷ የቆረቆዘች ብትሆን ኖሮ ዛሬ እዚሁ በተማሩት ትምህርት በሃያሏ ሀገር ሄደው ሥራ ባላገኙባት ነበረ:: ኢንተርኔት አገኙ እንጂ አጠቃቀሙን አላወቁበትም:: ደመኞች ሆነው ጎራ ይዛችሁ ደም መልሱልን ሲሉ አሻፈረኝ እምቢ በማለታችን “ይህ ትውልድ” በሚል ምጸት አዘል ንግግር ሊዘልፉን አይገባም:: ይቅር ባይነትን ሳያስተምሩን ይቅር ብለን ችለን መኖራችን: ወርቅ ቤት ደጃፍ እያደረ ጎዳና ላይ እየለመነ የሚኖርን ትውልድ “ይህ ትውልድ” ብሎ ማሽሟጠጥ የራሳቸው ድክመት እና ሰብዓዊ አመለካከት ጉድለት ነው:: ባይሆን ነገሩ ከወዲህ ነው:: አሁን አሁን መቃወሚያ መንገዶች እየጠፉ ናቸው:: የጥገኝነት መጠየቂያ ነጥቦች እየመነመኑ መጥተዋል:: ስለዚህ ፍላጎታቸው ይህንን ትውልድ መክሰስ ብቻ ነው:: ይህ ትውልድ ግን ምንም አንቀጽ የለውም:: በፖለቲካ: በዘር: በብሔር ... ወዘተ የተመዘገበ አይደለም:: የሀገሩን ንጹህ አየር በሀገሩ ሆኖ የሚተነፍስ ችግሩንም መከራውንም አብሮ የሚጋራ ትውልድ ነው:: ስለዚህ ወገን ይህን ትውልድ ከመውቀሳችን በፊት ትውልዱ ውስጥ የዘራነውን ወይም ለመዝራት ያዘጋጀነውን እንክርዳድ እንንቀል::
  የትውልዱ ልጅ::

  ReplyDelete
 17. ወንድም ዳንኤል ሁልጊዜ አንተን የምገልጽህ ጎበዝና ትጉህ ሰባኪ ብልጣብልጥ ጋዜጠኛ አድርጌ ነው፡፡ ምን አለ የፖለቲካ ምልከታህን ለእነ እስክንድር ነጋ ብትተወው፡፡ አሁን በውኑ እነዚህ የምትወቅሳቸው ፖለቲከኞች ሁልጊዜ አሜሪካ ስትመጣ የምትሰማቸው ሃገር ቤት የማትሰማቸው ለምን እንደሆነ ጠፍቶህ ነው? ለዚህ ነው የፖለቲካ ምልከታህን ሁልጊዜ ድፍረት የተሞላበት ሳይሆን ብልጠት ያለበት ሁኖ የማገኘው፡፡ አንተም ቢሆን የአሁኑ ትውልድ ብለህ ስትናገር የአንተንና የምታውቃቸውን ሰዎች ብቻ ሁኔታ እንዳትገልጽ ጥንቃቄ ማድረግ አለብህ፡፡ አንተ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ስትወስድ እኔ 8ኛ ክፍል ነበርኩ አንዳንድ የወቀስካቸውን ፓርቲዎች ለምሳሌ የሬዲዮ ፕሮግራሞቻቸውን በመከታተል ያኔ ጀምሮ አውቃቸዋለሁ፡፡ አንተን የሚመስሉ እንዳሉ ሁሉ እኔን የሚመስሉ ደግሞ አሉ ያለጥናት በ100% በጀምላ መናገር መልካም አይደለም፡፡ በርግጥ ያ ትውልድ እኮ የሚል የትውልድ ውድድር ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ መንፈሳዊያን ገጥመውኝ ያውቃሉ፡፡ በእኔ አመለካከት ግን ለዚያ ትውልድ የእናንተን ያህል ቃለ እግዚአብሔር እድል ገጥሞት ቢሆን ኖሮ ለምድራዊው ነገር እንዲያ የሞቱ ለሰማያዊው ነገር እንዴት በደከሙ ነበር፡፡ ይልቁንስ ሳትከፍሉ ለዚህ ያበቃችሁን አምላክ አመስግኑ፡፡ ለጎበዝና ብልህ የእግዚአብሔር ሰው ከወዳጆቹና ተከታዮቹ ድምጽ ይልቅ የሚወቅሱትንና የሚሰድቡትን ስድብ መስማት እንዴት ታላቅ ነው፡፡ በእግዚአብሔር እርዳታ የምትናገሩት ቃል አልቆ ነገራችሁ ስጋና ደም ከሚገልጽላችሁ እውቀት የሚመነጭበት ዘመን እንዳይመጣባችሁ የቅዱሳን ጸሎት አይለያችሁ፡፡
  መልካም የእመቤታችን ትንሳኤ በአል፡፡

  ReplyDelete
 18. Chigiru eneziay sewoch bezuwochu intrnate metekem ayawekum.
  Selezih Yihe tsehuf beye Ethiopian restaurantoch be frame bisekel tiru new.

  Thank You

  ReplyDelete
 19. ምድረ ዲያስፖራ ለካ እንዲህ ናችሁ!!! በሉ ራሳችሁን ከዘመኑ ጋር አገናኙት፡፡ በድሮ በሬ ያረሰ የለም፡፡

  ReplyDelete
 20. Why are you posting only the positive comment???? like Dejeselam!!!!!!!

  ReplyDelete
 21. I agree with your point partly. Most of the political parties outside do not know the real situation here; they are running for their benefit, they are extremists and simple theoreticians. These are some of their defect. But here our gov't is also dictator, wants only to impose their idea and hate other ideas like a sword. the major reason why this generation do not now external parties is not these parties it is the government who closed all the possible medias, who weakens the education policy and produce a generation with no identity who craves for external issues (like EPL). it is the government who makes the generation to forget his history and to concentrate on silly issues...

  ReplyDelete
 22. ጥያቄ አለኝ፡፡ እኛ ሁሉን ነገር በጎሪጥ የማየት፣ የተለየ ሃሳብ ያለውን የማውገዝ፣ የመናናቅ፣ በብሔር በጎጥ በቡድን የመከፋፈልና ተከፋፍሎ የመናቆር ችግሮች እያመሱንና ወደሁዋላ እየጎተቱን ይገኛሉ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ያደጉና የበለጸጉ ሀገሮች አሁን ላሉበት ደረጃ የደረሱት ይህን ሁሉ ችግር አልፈው ነው ወይስ ይህ እኛን ብቻ መርጦ የተጠናወተን አባዜ ነው

  ReplyDelete
 23. የሴል ታሪክ ተረስቶ የሴልፎን ታሪክ መምጣቱን ማን በተረከላቸው?

  ጽሁፍህ ተስማምቶኛል ላይ ጠቅሼ ባስቀመጥኩት ንግግርህ ግን አልስማማም ዳንኤል! የሴል ታሪክ መቼ ተረሳ በየዩኒቨርስቲው ብትመጣ ተማሪው ሁሉ “በፈቃዱ” በሴልና በህዋስ ተከፋፍሎ ‘ሌላ ሀሳብ’ ሊያስቡ የሚችሉ ‘ጸረ ሰላም ሀይሎችን’ ለመዋጋት ‘ቆርጠው ተነስተዋል’ ሲጠራሩም ጓድ እየተባባሉ ነው ‘ሂስ መዋጥ’: ጠርናፊ ምናምን የሚባሉ ቋንቋዎችም አሁንም አሉ…የሀገራችን ትምህርት ሚኒስቴርም በዌብሳይቱ ላይ ለዩኒቨርስቲ መምህርነት የተመረጡ ተማሪወች የተመረጡበትን standard ሲናገር በስነ ምግባር C እና ከዚያ በላይ ያላቸው ይላል …ስነምግባርን የሚመዝን ተቋም በየዩኒቨርስቲዎቻችን ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ? የመሪ ድርጅታችን ቋሚ ተቀጣሪዎች ናቸው…

  ታድያስ ታሪክ ላይ የተኙት እነ ኢህአፓ ብቻ ናቸው እንዴ…?

  This is from one of Ethiopia's politically affiliated Universities...oh..I forget one thing every university is made politically affiliated.

  ReplyDelete
 24. ዲያቆን ዳንዔል ምስጋንዬን ተቀበለኝ። ከዚህ
  ጽሁፍህ እነኢህአፓ ጥሩ ትምህርት እንደሚያገኙ አልጠራጠርም፣ አርባ ዓመት አስቆጠርን እያሉ እነቅንጅትን ዘርጥጠው ለመጣል ከወያኔ ቀድመው የሮጡ እነሱ ነበሩ፣ እነሱ ያልሰሩት ወት አይጣፍትም የሚል የስብቴ ዘመን መፈክራቸውን ይዘው እንደተራበ ውሻ ዛሬም ባውሮፓና ባሜሪካን ያላዝናሉ፣ እስቲ እንዲህ ልክ ልካቸውን ንገርልን
  ስብሃት ለእግዚአብሄር

  ReplyDelete
 25. as writer you have good point, but D.Danie, you know the weyane poltics better than anyone, there is no free press like tv, radio, and freedom of speach. so how do you expect people can learn the past or the present event? there is a good example for you as suggestion from me , if you read the new article from adebaba " about anger management " how people learn the past and the present". i gree with you with some parts about the diasporas poltics .

  ReplyDelete
 26. it is really nice article u said all, it was what i thought for years there is big generation gap very big gap....the problem is such kind of people are every were in politics in church's in sport events ....

  ReplyDelete
 27. Let every one carry his owen cross!

  ReplyDelete
 28. ከእንዳንተ ዓይነቱ ተላላኪ ቡችላ ምን ይጠበቃል፡ ይልቅዬ አንተ ነህ ህሊናህ ላይ ተኝተህ ዛሬም የምታንኮራፋው። ሞያ በሊብ እንዲሉ የአንተን ወይም የአባትህን ክስ ለማስረሳት ትሞነጫጭራለህ የፍርድ ቀን ሲመጣ እየተለቀምክ ለፍርድ ትቀርባለህ፡ እስቲ ደግሞ የምን አትርሱኝ ነው ኋላ ከማዘን ፎቀቅ ብሎ መቅዘን ይመረጣል።

  ReplyDelete