Thursday, August 18, 2011

ለቤተ መጻሕፍትዎ

     ከእንጦጦ ኀሙስ ገበያ እስከ መርካቶ


አዘጋጅ:- ብርሃኑ ሰሙ
ኅትመት:- አልፋ አታሚዎች
የታተመበት ዘመን:- 2003 ዓም
የገጽ ብዛት:- 328
ዋጋ:- 50 ብር
ኢትዮጵያ ውስጥ የቅዱሳን፣ የነገሥታት፣ የጦር መሪዎች፣ የፖለቲከኞች ታሪክን መጻፍ በስፋት የተለመደ ነው፡፡ ከዚህ ወጣ ብሎ የነጋዴዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የገበሬዎች፣ የጉልበት ሠራተኞች፣ የባሮች፣ የቤት እመቤቶች፣ የቤት ሠራተኞች፣ የሊስትሮዎች፣ ወዘተን ታሪክ መጻፍ ግን እንደ ዋልያ በብርቅ የሚታይ ነው፡፡
ብርሃኑ ሰሙ ስላልተነገረላቸው የኢትዮጵያ ጀግኖች ከጻፉ የሀገራችን ታሪክ ጸሐፊዎች አንዱ ነው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ የንግድ ቦታዎች እና ነጋዴዎች ነው የጻፈው፡፡ አዲስ አበባ ስትመሠረት ከነበረው የእንጦጦ ኀሙስ ገበያ ተነሥቶ እስከ ታላቋ መርካቶ ድረስ ያለውን የንግድ እና የነጋዴ ታሪክ ያስነብበናል፡፡
እርሱ ያነሣውን ጉዳይ በደንብ የሚዘግቡ መዛግብት እንደ ልብ በማይገኙበት፣ ባለ ታሪኮችን እየዞሩ ማነጋገር የግድ በሚሆንበት፣ በየቤቱ እንደ ዋዛ የተቀመጡ ዶሴዎችን ማግኘት በሚጠይቅበት በዚህ መስክ ወጥቶ ወርዶ ድንቅ ነገር አስነብቦናል፡፡
ምኒሊክ አዲስ አበባን ሲቆረቁሩ የመጀመርያ የነበረው «ሥላሴ ገበያ» አሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በተሠራበት ቦታ ላይ እንደነበር፤ የአራዳ ጊዮርጊስን መተከል ተከትሎ ደግሞ የአራዳ ገበያ መተከሉን፤ ጣልያን ሲገባ አራዳን ፒያሳ አደረገና ገበያውን ወደ ዛሬው መርካቶ እንዳባረረው፤ በኋላ ዘመን ማርስ ሆቴል የተባለው ቦታ የጥንቶቹ የመርካቶ መሥራቾች የኪኪያኖች ቤት እንደነበር፤ የአዲስ አበባ የመጀመርያው መናኸርያ ፒያሳ አትክልት ተራ ላይ እንደ ነበር፤ በሽቶ ምርታቸው የሚታወቁት የሁነኛው መራ ታሪክ፣ የአስፋው ተክሌ ሕንፃን ገንብተው ስለተወረሰባቸው አጎናፍር ወልደየስ፣ የመርካቶውን የሀገር ውስጥ ገቢ ሕንፃ ያሠሩት የኢብራሂም መሐመድ ሸኖ ታሪክ፣
ዓለም ተስፋ ሕንፃን ያሠሩት የመኮንን መፈሪያ ታሪክ፤ የአስፋው ወሰን ሆቴልን ሕንፃ ስላስገነቡት ነጋሽ ቢርቢሶ ታሪክ፤ ዛሬም ድረስ አካባቢው በስማቸው ስለሚጠራላቸው ስለ ሞላ ማሩ ታሪክ፤ ገበርዲንን ለኢትዮጵያውያን ስላስተዋወቁት ታደሰ ደስታ (ታደሰ ገበርዲን) በላይ ተክሉ ታሪክ፣
ሴት ልጅ ከቤት በማትወጣበት ዘመን መርካቶ ገብተው ንግዱን ያስከነዱት የነበሩት የሴት ነጋዴዎች የነ ዘምዘም ገርቢ፣ ሐበሻ መሸሻ፣ ጸዳለ ደስታ፣ ገነት ወልደ ገብርኤል፣ መነን አመዴ፣ በላይነሽ ምሕረቴ፣ ዐጸደ ወልደ ጻድቅ፣ ታሪኮች ተካተተዋል፡፡
ዛሬ መርካቶ ውስጥ የምናያቸውን ሕንፃዎች የገነቧቸው እነማን እንደሆኑ ከነ ፎቶአቸው ይነግረናል፡፡ በመርካቶ የነበረውን ሕይወት፣ ስፖርት፣ ዕድር፣ በጎ አድራጎት እና ትራንስፖርትም ያስቃኘናል፡፡ የአህያን፣ የጋሪን፣ የሴንቼንቶን ታሪክ እናገኛለን፡፡ በአዲስ አበባ መጀመርያ ላይ ተቋቁመው ስለነበሩት የታክሲ ማኅበራትም ያስነብበናል፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ ኮንትራቶችን፣ ብድሮችን እና ሽልማቶችን እናያለን፡፡ ንጉሡ ሳይቀር ከመርካቶ ነጋዴዎች ገንዘብ እንዴት ይበደሩ እንደነበረ የሰነድ ማስረጃ ያቀርብልናል፡፡
በመጨረሻም በየሠፈሩ ያሉ እና የነበሩ ገበያዎችን ታሪክ በማስቃኘት ይጠናቀቃል፡፡
በሀገራችን ብዙም ያልተነገረለትን የንግድ እና የንግድ ሰዎች ታሪክ የሚያስነብብ፤ ታሪካችንም በየዘርፉ እንዲሟላ ከሚያደርጉ መጻሕፍት አንዱ ነውና ገዝታችሁ አንቡት፡፡

9 comments:

 1. if i will get the book,i will read at least through borrowing.As Birhanu Semu wrote a book about Addis's history of trade,i hope anyone may write Ethiopia's history in a near future using birhanu book's as an input.
  Wubshet Zetenta!

  ReplyDelete
 2. Thank you Dn. Daniel
  what an interesting book. I can't wait to read it . thank you. Atlanta.

  ReplyDelete
 3. writing books like this links with reading our society.

  ReplyDelete
 4. if you are like it, i will read it as soon as possible.

  Thanks Dani,

  ReplyDelete
 5. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሄር ለሠጠህና ላካፈልከን ነገር ሁሉ ከልቤ የማመሰግንህ የት ነው ስል ይህን አጋጣሚ በማግኘቴ እግዚአብሄር ይመስገን፡፡ ዛሬ ተሣክቶልኝ ብሎግህን ሳይ የስልክ ቁጥርህም ከእኔ የግል ሥልክ ጋር ያለው ልዩነት አስገረመኝ አሁን ያለው ባለቤቴ ጋር ቢሆንም 0911474508.ካሁን በፊት ከነበሩህ የመጽሃፍ ጥቆማዎች እንዴት ማግኘት እችላለሁ፡፡ እግዚአብሄር እድሜህን አብዝቶ ብዙ እንድታስተምር ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 6. it is amazing i will read it soon this is the basic one dani.

  ReplyDelete
 7. Dear Dani, thank you as usual for this information. I like who dare to write everything and appreciate Berhanu Semu for his effort for his work. Dani I like to read your lovely articles, but the article on freedom of thinking was exceptional. At this crucial time, when the talk of censorship reaches it climax you know what does it mean. However, only God know what will happen, you may understand what I am thinking hahahaha...

  ReplyDelete