አንድ ሰው ከሚያሳድዱት ሰዎች እየሸሸ ይሮጣል፡፡ ሊያመልጥ በሚችልባቸው መንገዶች ሁሉ እየተሹሎከሎከ ተጓዘ፡፡ ሰዎቹ እንዳያዩት ሊደበቅባቸው በሚችሉ አማራጮች ሁሉ ተፈተለከ፡፡ በስተ መጨረሻ እግሩ ከአንድ ግምብ አጠገብ አደረሰው፡፡ ግንቡ እጅግ ቁመታም እና ረዥም ነበር፡፡ ተንጠላጥሎ ለማለፍም ምንም ዓይነት መወጣጫ አልነበረውም፡፡ ምናልባት የሚያስገባ ቀዳዳ ባገኝ ብሎ የግንቡን ጥግ ተከትሎ ሮጠ፡፡ ነገር ግን እርሱ ደከመው እንጂ መገቢያ ሊያገኝ አለቻለም፡፡
በመጨረሻ ተስፋ ሊቆርጥ ደረሰ፡፡ ከኋላው የሚያሳደዱት ሰዎች እንደርሱው ግንቡን ሲያዩ መጀመርያ ደነገጡ፤ በኋላ ግን እርሱን ለመያዝ አመቺ መሆኑን ዐውቀው ደስ አላቸው፡፡ ሊሄድ ይችላል በሚሏቸው በሁለቱ የግንቡ አቅጣጫዎች ተከፋፍለው ሮጡ ፡፡
ልቡ እየደከመ፣ ሃሳቡ እየዛለ፣ እንጥሉ እየወረደ፣ ሐሞቱ እየፈሰሰ፣ አንጅቱ እየራቀ፣ መቅኔው እያለቀ መጣ፡፡ «ይህንን ሁሉ መንገድ ለፍቼ ለፍቼ ሊይዙኝ ነው» ብሎም ከአንድ ዛፍ ሥር ቁጭ ብሎ አለቀሰ፡፡ ዕንባውን ጠርጎ ቀና ሲል ከግንቡ ራቅ ካለ ዛፍ ላይ የተጠጋ አንድ ሐረግ አየ፡፡ የሐረጉን ሥር በዓይኑ ሲከተለው ከግንቡ በላይ ከወጣው ዛፍ ተንጠላጥሎ ሲሳብ አየው፡፡ ጥቂት ብርታት አገኘ፡፡ ተስፋ ካለ ብርታት አለና፡፡ ሰው የሚደክመው ኅሊናው ሲደክም ነው፡፡
ጠጋ ብሎ ሐረጉን ያስጠጋውን ዛፍ ተደገፈ፡፡ ጠንካራ ነው፡፡ «ምን ላድርግ?» አለና ተጨነቀ፡፡ ያለ የሌለ ዐቅሙን አሟጠጠ እና ዛፉ ላይ ወጣ፡፡ የሐረጉንም ጫፍ ሳብ ሳብ አደረገው፡፡ ጠንካራ ነው፡፡ መልሶ መላልሶ ሳበው፤ ሐረጉ ጠንካራ ነው፡፡ ይህን ጊዜ የሰው ድምጽ ሰማ፡፡ ዝቅ ብሎ ሲያይ የሚያሳድዱት ሰዎች በአካባቢው ደርሰዋል፡፡ ደግነቱ አላዩትም፡፡
ሐረጉን በመዳፉ ጠመጠመና ወደ ኋላ ተስቦ ዛፉን በኃይል ለቀቀው፡፡ ያን ጊዜ ሐረጉ እንደ ፔንዱለም ተወርውሮ ከግንቡ በላይ አንጠለጠለው፡፡ ቋ ቋ ቋ የሚል ድምጽ ሰማና ሐረጉ ተበጠሰበት፡፡ ደግነቱ የወደቀው ግንቡ ላይ ነበር፡፡ ዘወር ሲል አሳዳጆቹ አይተውታል፡፡ የተረፈችውን ሐረግ ይዞ ወደ ምድር ወረደ፡፡
ክዚያ በኋላ የሆነውን አያውቀውም፡፡ ሮጠ ሮጠ ሮጠ እናም በቃ ሮጠ፡፡ ሲበቃው ዐረፈ፡፡ ሰውነቱ እንጂ ኅሊናው አላረፈም ነበር፡፡ እስካሁን ድረስ አንዳች ማምለጫ ለምን አላገኘሁም፡፡ ይህንን ሁሉ ስደክም ያለተገለጠልኝ መንገድ እንዴት አሁን ታየኝ? ያወጣ ያወርድ ጀመር፡፡
እናም መንፈስ እንዲህ አለው፡፡ መጀመርያኮ ትሮጥ የነበረው በኅሊናህ አይደለም በእግርህ ብቻ ነው፡፡ እግርህ መሄድ ስለቻለ እና መንገዱም ሊያስኬድህ ስለቻለ ብቻ ነው የሮጥከው፡፡ ስለቻሉ መሮጥ አና እንዲችሉ ሆኖ መሮጥ ይለያያሉ፡፡ ስለሚያስኬድ መሄድ እና እንዲያስኬድ ሆኖ መሄድ ይለያያሉ፡፡» አለው፡፡ ይኼኔ ሰውዬው ደንግጦ «እንዴት?» አለ፡፡
አንዳንድ ጊዜ አጋጣሚዎች፣ ሁኔታዎች እና መንገዶች ይመቻቹልሃል፡፡ ያንተ ሃሳብ ሳይጨመርበት እንዲሁ የሚያፈራ ፍሬ፣ የሚወጣ እንጀራ፣ የሚያተርፍ ንግድ፣ የሚያበላ ሥልጣን፣ እና የሚያስደስት ትዳር ይገጥምሃል፡፡ ይኼኔ ኅሊናህ ቦዘኔ ይሆናል፡፡ መሄድህን እንጂ መድረሻህን አታውቀውም፡፡
እንዲህ የሆኑ ሰዎች እንዳንተ የተዘጋ የመሰለ ግንብ ሲገጥማቸው ይደነግጣሉ፡፡ ቦዘኔ የነበረ ኅሊናቸውን ቀስቅሰው ማሠራት ይከብዳቸዋል፡፡ ቦዘኔ ኅሊናን ከመቀስቀስ ደግሞ የሞተ የመኪና ባትሪ መቀስቀስ ይሻላል፡፡
አጋጣሚኮ መነሻ እንጂ መድረሻ መሆን የለበትም፡፡ የበረደን የመኪና ሞተር በባትሪ እንደ ሚያስነሡት የተኛን ኅሊና በአጋጣሚዎች ሊቀሰቅሱት ይቻላል፡፡ መኪናን በባትሪ ኃይል አይነዱትም፡፡ ሕይወትንም በአጋጣሚ አይመሯትም፡፡
አንድ ነጋዴኮ በአጋጣሚ ጥሩ ቦታ ላይ ስላለ፣ ዕድለኛም ስለሆነ፣ ብቸኛም ስለሆነ፣ ጊዜውም ስለረዳው፣ ሊበለጽግ ይችላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን የኅሊናን ርዳታ ሳይፈልጉ እንደ አንተ እግር የሚኳትኑ ናቸው፡፡ አንተኮ ለጊዜው አምልጠሃል፤ ሸሽተሃል፤ መፍትሔ አግኝተሃል፡፡ ነገር ግን ኅሊናን የሚጠይቅ ጊዜ ላይ ስትደርስ ነበር የተሸነፍከው፡፡ ያም ነጋዴ ኅሊናን የሚጠይቅ አንድ ቀን ያጋጥመዋል፡፡ ዕድል ተበላሽቶ፣ ዘመን ተቀይሮ፣ ባለ ሥልጣን ወርዶ፣ ኑሮ ተለውጦ፣ ቦታውንም ተቀምቶ፣ ተወዳዳሪም በዝቶ ያ እንደ ልቡ የሚሮጥበት መንገድ የተዘጋ ሊመስለው ይችላል፡፡
ታድያ ያን ጊዜ ተኝቶ የኖረን ቦዘኔ ኅሊና መቀስቀስ ከባድ ነው፡፡
በጣልያን ጊዜ ከጣልያን ጋር አብረው ሕዝባቸውን እየወጉ በዘመኑ የሚጠቀሙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ዘመኑ የሰጣቸውን ከመብላት፣ ከመጠጣት፣ ከመሾም፣ ከማጋበስ፣ ከመላላክ፣ በቀር ኅሊናቸውን ያልተጠቀሙ፡፡ ቦዘኔ ኅሊና የነበራቸው ሰዎች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚውን ዕውቀት ለመቅሰም፣ ሥልጣኔን ለመማር፣ ሞያ ለመልመድ የተጠቀሙበት ባለ ኅሊናዎችም ነበሩ፡፡ በአንድ በኩል ከጣልያን የሚያስቀሩትን እያስቀሩ በሌላ በኩል የውስጥ አርበኞች ሆነው የሠሩ ንቁ ኅሊና ያላቸው ሰዎች ነበሩ፡፡
ታድያ ሕዝቡ በእነዚያ ቦዘኔ ኅሊና ባላቸው ሰዎች በማዘኑ የተነሣ
አርኩም ይሄድና
ሶልዲውም ያልቅና
ያስተዛዝበናል ይሄ ቀን ያልፍና
ብሎ ገጠመ ይባላል፡፡ ብዙዎቹ አስበውበት አልነበረም የኖሩት፤ እንዴው ዘመን የወደደውን፣ ጊዜ የወለደውን ሲያደርጉ እንጂ፡፡ ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብለው እንጂ፡፡ ታድያ በኋላ ተቸገሩ፡፡ አርኩም ሄደና ሶልዲውም አለቀና ተቸገሩ፡፡ የቦዘነ ኅሊናቸውን ተነሥ ቢሉት እምቢ አላቸው፡፡ ትርፍራፊ እና ልቅምቃሚ ለምዶ፣ ችሮታ እና ስጦታ ለምዶ አሁን ምን ይዋጠው፡፡
አየህ ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ አሳብ አይበላም፣ አልጋ ተመቸ ተብሎ ያለ አሳብ አይተኛም፡፡ ጨዋታ ደራ ተብሎ ያለ ልክ አይወራም፤ ገንዘብ አለ ተብሎ ያለ መጠን አይወጣም፤ እግር አለ ተብሎ ያለ ምዕራፍ አይኬድም፡፡ ይህ ኅሊናን ማቦዘን ነው፡፡
ለመሆኑ ለምን ነበር ያ ሐረግ የታየህ?
አማራጭ አልነበረህም፡፡ አሁን እግር እንደወሰደ የሚኬድበት መንገድ የለም፡፡ ያለው ግንቡ ብቻ ነው፡፡ የግድ ኅሊናህ መሥራት ነበረበት፡፡ አሁን አጋጣሚዎች አያጋጥሙህም አጋጣሚ ትፈጥራለህ እንጂ፤ መንገድህ አልቋል መንገድ ታበጃለህ እንጂ፡፡ ስለዚህ ኅሊናህ በውጥረት መሥራት ጀመረ፡፡ ያን ጊዜ ሐረጉን አየኸው፡፡
ማየት አቅቶህ እንጂ እዚህ ድረስ ሳትደክም ልታመልጥባቸው የምትችል አያሌ መንገዶች ነበሩህ፡፡ አንተ ግን ኅሊናህን ስላቦዘንከው ልታያቸው አልቻልክም፡፡ እንዲሁ እግርህ እንደሄደልህ፣ መንገድ እንደወሰደህ፣ አገር እንደ ቀናህ ነበር የምትሮጠው፡፡ ታድያ እንዴት ታየው?
ዝግ ኅሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም፡፡
መንገድ የሚከፈተው ኅሊናህ ውስጥ ነው፡፡ አስቀድመው በኅሊና መንገድ ወደ ጨረቃ የሄዱ ሰዎች በኋላ በመንኮራኩር መንገድ ለመሄድ አልቸገራቸውም፡፡ የኅሊናቸው መንገድ ዝግ የሆነባቸው ግን ይኼው አሁንም «ጨረቃ ድንቡል ቦቃ ዐጤ ቤት ገባች ዐውቃ» እያሉ በመዝፈን ላይ ናቸው፡፡
ማጂላን ዓለምን ከመዞሩ በፊት ኅሊናው ዓለምን ዞሮ ነበር፤ ቫስኮ ዳጋማ ሕንድ ከመድረሱ በፊት ኅሊናው ደርሶ ነበር፡፡ ዋናው ኅሊና ነው፡፡ አስቀድሞ ኅሊናቸው የጸደቀ ሰዎች እኮ ናቸው በኋላም አካላቸው የሚጸድቀው፡፡
መኖር ማለት ማግኘት አይደለም፤ መኖር ማለት መትረፍረፍ አይደለም፤ መክበር እና መንፈላሰስ አይደለም፡፡ መኖር ማለት ማሰብ ነው፡፡ በሥጋ ሳይሆን በኅሊናህ ኑር፡፡ በኅሊናህ ከኖርክ የተዘጋ መንገድ የለም፡፡ ቢኖርም ትከፍተዋለህ፡፡
አንድ ታሪክ ልንገርህ፡
አንድ ፈላስፋ ነበር አሉ፡፡ አንድ ቀን መንገድ ሲሄድ መሸበትና ከአንድ ዛፍ ሥር ዐረፍ አለ፡፡ ጨለማው እንደ ግብጽ ጨለማ የተጠቀጠቀ ነበር፡፡ ፈላስፋው ምናልባት አንዳች ነገር በዚህ ጨለማ ውስጥ ብመለከት አለና ዓይኑን ፍጥጥ አድርጎ ማየት ጀመረ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ዓይኑን ደከመው፡፡ እየጨፈነ እና እየገለጠ ማየት ቀጠለ፡፡ ትንሽ ቆይቶ የሆነ የብርሃን ጭላንጭል ታየው፡፡ እየቆየ ሲሄድ አካባቢውን በደምሳሳው ማየት ቻለ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ከፊት ለፊቱ ያለው የበቆሎ እርሻ መሆኑን ለየ፡፡ በመጨረሻም በእርሱ እና በበቆሎ እርሻው መካከል የጥበቃ ማማ ታየው፡፡
ወዲያው አፈፍ አለና ተነሣ፡፡ ወደ ማማው ሄዶ በዚያ አደረ፡፡ በአውሬ ከመበላትም ዳነ፡፡ ይህ ፈላስፋ ታድያ ምን አለ መሰለህ «ማየት ለሚችል ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን አለ፡፡ ጨለማን ጨለማ ያደረገው የፀሐይ መጥፋት ሳይሆን የኛ አለማየት ነው» አለ፡፡
እኔስ የኅሊና እንጂ የመንገድ ዝግ የለውም ያልኩህ ይህንኑ አይደል?
ይህንን ነግሮት መንፈሱ ከእርሱ ተለየ፡፡ መንገደኛውም የመንፈሱን ትሩፋት ተቀብሎ ሄደ፡፡ ይህንን ከወሬ ወሬ የሰማ አንድ ሰውም እነሆ በብሎጉ ላይ ጻፈው፡፡
Wow wow wow, how an interesting article it is! I got a very important advice at the right time when I badly need. Thank you Dani for your generosity. It gives me an endurance to win such challenging and difficult hardships and temptations. Thank you once again.
ReplyDeletethat's true; thank u Danny.
ReplyDeleteየ አለም ታሪክ የሚያሳየን ህሊናቸው ያልሞተ ሰዎች የሰሩትን ተግባር ነው:: ህሊናው ያልሞተ ትውልድ መሆን ይገባናል::እውነት ላትደበዝዝ ህሊናችንን መግደላችን ምን ይባላል? ''እግዚአብሄር ባንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውልም'' ይላል መጽሃፈ ኢዮብ
ReplyDeletewonder ful article thank you....
ReplyDeleteዳኒ እዉነት ነው ህሊና ካላየ ሁሉ ከንቱ ነዉ።
ReplyDeleteit is nice view,
ReplyDeletebengerhi lay hule yemayigebagn neger ale may be ante litaye ena litastemirew yemichal. hule in our chirch (orthodox) kidasie kegeba behuala sewoch yiwetalu yigebalu neger gin sirat ayimeslegem so if u understand me let u observe and say some thing about it cause ur learning way is so easy and may be people read it n learn each other. thankyou
Realy interesting advice which changes once life. Thank you Thank you
ReplyDeleteWonderful article! One of your best fruits!!! Thanks Dani.
ReplyDeleteFrom Germany
that is interesting view.I got great lesson
ReplyDeletethanks dani
Thank you Dani this history is directly related with qidus Yared's history which is the indicator for the who think as things are beyond his/her capability
ReplyDeleteWHAT A VISION AND IMAGINATION
ReplyDeleteThanks Dani.
ReplyDeletevery interesting, but doesn't always work for our country...
ReplyDeleteአሁን አመጣከው ይህቺ የኔ ህይወት ናት፡፡ "ሰው የሚደክመው ህሊናው ሲደክም ነው" አመሰግናለሁ ጥሩ መክረኸኛል
ReplyDeleteማየት ለሚችል ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን አለ፡ዝግ ኅሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም፡፡
ReplyDelete10q dani there is all ways a choice be for doing some thing.
ReplyDeleteegziabher yebarkehe D.Daniel its relay a wonderfull saying.tnx 4sharing us.
ReplyDeleteDn. Daniel, It is really very impressive article. I like it very much. May GOD always be with you and bless your Spiritual and social services.
ReplyDeleteM.A
Kombolcha/Wollo
ዝግ ኅሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም፡፡
ReplyDeletereally good article. may God bless you.
ReplyDeleteአጋጣሚኮ መነሻ እንጂ መድረሻ መሆን የለበትም፡፡ ብዙ የሚባልበት፡፡
ReplyDeleteበሕይወታችን ስንት አጋጣሚዎችን ሳናያቸው አምልጠውን ይሆን፡፡ አጋጣሚ የህሊና መንገድ መክፈቻ ነው ወይስ ሕሊና የአጋጣሚዎች መመልከቻ መነጽር፡፡
ፁኁፎችህ በጣም ድንቅ ናቸው፡፡
ቦዘኔ ኅሊናን ከመቀስቀስ ደግሞ የሞተ የመኪና ባትሪ መቀስቀስ ይሻላል፡
ReplyDeleteዝግ ኅሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም፡፡
በጣም አስገራሚ ጽሑፍ ነው
ቃለ ህይወት ያሰማልን
ሰው የሚያደርገውን ሲገልጽ ደስ ይላል፡፤
zig hilina enj zig menged yelem Egziabher yistilin diacon daniel edmehn yarzimln
ReplyDeleteegziabher yistiln diacon tiru timihrt aggntenibetal mengesha wondimu HARAR
ReplyDelete«ማየት ለሚችል ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን አለ፡፡ ጨለማን ጨለማ ያደረገው የፀሐይ መጥፋት ሳይሆን የኛ አለማየት ነው»
ReplyDelete<
ዳኒ ግሩም አባባል ነው፡፡ ፍቅር ካለ፣ መነጋገር ካለ፣ ይለቁንም በጎ ኅሊና ካለ ዝግ መንገድ ድቅድቅ ጨለማ የለም፡፡ እግዚአብሄር አንተንም ልጆችህንም ይጠብቅልን፡፡
Always there is a way. tnx Dani QHY
ReplyDeleteThanks Thanks Thanks a lot Dan.
ReplyDelete(AGE)
thank u dani i had a great advice !
ReplyDeleteThank God for letting that the one who heard and write on the blog. This is gonna give resurrection of mind to many.
ReplyDeleteThat was a good one, Dani. I like the article with the fact that I have been challenged with the message behind it.
ReplyDeleteOne can't run without a systematic approach to win a competition or to escape from the chasers.
He could have taken a lot of lessons from Haile, Kenenissa, and our track and field runners or heroes. Even though they have to run 5k, 10k, or marathon, they know when to run fast, when to run slow, and what tactic they have to use. They have plans throughout the game to finish the competition first, and bring that medal/award and national pride for Ethiopian people and them selves.
I think we have to plan ahead to accomplish our dream well; what ever kind of outcome we are looking for.
I will consider the message behind it for my self. I will try to work on it as much as I can to see ahead, use my thoughts first, and run as quick as possible systematically to accomplish my goals.
Yes ! It very interesting and inspiring article . I really like it . Thank you for your effort to teach us.
ReplyDeleteVery Interesting Idea - Appreciable !
ReplyDeleteA person, enemies, a bulwark, a tree, a corp., street and an imagination! It is good view for anyone.
ReplyDeleteIf suddenly havens something you don't have time to analyze anything to use of you naiad. You just run or do something goosing to evacuate away from enemy. But if you have chance to think some idea you can move out wisely to save yourself or you can do some protection to protect yourself from attacks.
ejig betam astemary metatef naw 10 Q dan
ReplyDeleteephrata ke shiluvo chaka
እውነት ብለሀል ዳኒ! ዝግ ህሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም። ኩዋንተም ፊዚክስም ያረጋገጠው ይሄንኑ እውነት ነው ሁሉም ነገር የትየለሌ አማራጭ ውስጥ እንደሚገኝ። "ሁሉም ነገር በሙላት ይገኛል" ይባላል ግን ደግሞ እንዴት የሚል ጥያቄንም ሊያስነሳ ይችላል። ይህ ደግሞ "የሁሉም ነገር እጥረት አለ" የሚለውን አባባል የሚቃረን ነው። የጥሬ እቃዎች እጥረት አለ፣ የስራ እጥረት አለ፣ የአቅርቦት እጥረት አለ፣የምሁራን እጥረት አለ፣ የነዳጂ እጥረት አለ፣...። ይህ መሰሉ እጥረት እጥረት የሚሸት አስተሳሰብና እጥረቱን ተከትሎ የሚሰማ ውስጣዊ የጭንቀት ስሜት ላንድ ግለሰብ ወይም ማህበረሰብ ከመረበሹም በላይ መረጋጋት እንዳይችል ያደርገዋል። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ከተፈጥሮ ህግ ውጭ ነው። ምክንያቱም መላው ተፈጥሮ ስፍር ቁጥር ከሌለው ንጥረ ነገር የተገነባ ነው። ይህ መሰል የትየለሌ መስራች ግብአት ባለበት ሁኔታ ውስጥ ከእነዚህ የሚሰሩትና በዕለት ዕለት የሰው ልጆች ህይወት ግብአትነት የሚውሉ ነገሮች እጥረት ሊኖር አይችልም። በርግጥ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የሰው ልጂ የፈጠራና የማቀናጀት አስተሳሰብ ጥቅም ላይ መዋል አለበት።
ReplyDeleteበአሁኑ ወቅት የምናያቸው እጂግ በጣም ብዙና የሰውን ልጂ አኖኖር የለወጡ ልዩ ልዩ የፈጠራ ውጤቶች የተገኙት ከምድር ተቆፍረው ወይም ከሰማይ ወርደው ሳይሆን በሰው ልጂ ጭንቅላት ውስጥ ምናባዊ ምስል መፍጠር በመቻላቸው ነው። ከየትኛውም ፈጠራ በፊት ውጤቱን ያስገኘ ምናባዊ ምስል በአዕምሮችን ውስጥ ይገኛል ። ከዚያም በቀጥታ በዙሪያችን ያሉትን ልዩ ልዩ ግብአቶች በመጠቀም በአዕምሮችን ውስጥ ለመፊጠር የፈለግነውን ነገር እንድንፈጥር ያግዘናል። ምናልባት እጥርት አለ ከተባለ ሊኖር የሚችለው የፈጠራ ሀሳብ እጠረት ብቻ ነው። ለምሳሌ እስከዛሬ የምንጠቀመው የነዳጂ ሀይልን ነበር ነገር ግን አሁን እያለቀ ነው ዋጋውም በየጊዘዜው እየጨመረ ነው። ይሁን እንጂ የነዳጂ ሀይል አንዱ መንገድ እንጂ ብቸኛው አማራጭ አይደለም። ምክንያቱም 100% ሊተካው የሚችል የፀሀይ ሀይል፣ የንፋስ ሀይል፣ የውሀ ሀይል፣ ከተክሎች የሚመረት ነዳጂ ዘይት፣ የኒኩሊየር ሀይል፣ የሀይድሮጂን ጋዝ ሀይል፣...አለ። ብዙዎቻችን ከአዲስ አበባ ተነስተን ደሴ ለመድረስ የሚመጣልን ጣልያን የሰራው ስፋልት ብቻ ነው።ነገር ግን የጣርማ በር ዎሻ ቢናድና መንገዱ ቢዘጋ እጂግ መጠነ ሰፊ አማራጮች አሉ። በአስመራ በኩል ሊሆን ይችላል፣ በጂማ በኩል ሊሆን ይችላል፣ በሱዳን በኩል ሊሆን ይችላል፣ በአውሮፕላን ወይም በፓራሹት ሊሆን ይችላል፣ ከአልፋ ሴንቼሪ ኮከብ በስተጀርባ ዞሮም ደሴ መግባት ይቻላል። ይለናል ኩዋንተም ፊዚክስ። ችግሩ በህይወታችን ባስቀመጥነው ግብ ላይም እንደጋሪ ፈረስ ፊት ለፊት መመልክት ይቀናናልና ከዚህ አይነጥላ እንላቀቅ ዘንድ እንድናስብ፣ እንድንመራመር፣ እንድንናነብ፣ አንድንጠይቅና እንድናውቅ እግዚአብሄር ልቦና ይስጠን።
አጋጣሚኮ መነሻ እንጂ መድረሻ መሆን የለበትም፡፡ የበረደን የመኪና ሞተር በባትሪ እንደ ሚያስነሡት የተኛን ኅሊና በአጋጣሚዎች ሊቀሰቅሱት ይቻላል፡፡ መኪናን በባትሪ ኃይል አይነዱትም፡፡ ሕይወትንም በአጋጣሚ አይመሯትም፡፡
ReplyDeleteyou are right!!smooth seas cant make you a skillful sailor yibals yele. kale hiwot yasemah,yekidusan milija ayileyih and really happy and glad about the mis understanding between MKD resolved peacefully.
ReplyDelete"ጨለማን ጨለማ ያደረገው የፀሐይ መጥፋት ሳይሆን የኛ አለማየት ነው" አይመስለኝም
ReplyDelete"ጨለማን ጨለማ ያደረገው የብርሃን አለመኖር ነው" ቢባል የበለጠ ትርጉም ይሰጣል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ብርሃን ነው: በእርሱ የተጀመረ ... ፍጻሜው ያማረ ነው:: No dead end.
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ። በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።
ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።
በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ
በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።
የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።
የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ
F
I am speechless
ReplyDeleteልብ ካላየ የአይን ማየት ሚስጥሩ፤መንገድም ሲቀና ህሊና ነው እግሩ፤ህሊና ልብ ነው በአይን መንገድ ምግባሩ፤ባይተማመኑ ወድቀዋል ካጥሩ።
ReplyDeleteግሩም ነው ዳኒ በጥበቡ ይጎብኝ የሰራዊት አምላክ።ወድጀዋለሁ።«ልብ ካላየ የአይን ማየት ሚስጥሩ፤የመንገድም መቅናት ህሊና ነው እግሩ፤ህሊናና ልብ በአይን ሲመተሩ፤ባይተማመኑ ወድቀዋል ካጥሩ።»
ReplyDeleteI LIKE IT YOU SO WOND.......FUL.
ReplyDeletei like it
ReplyDeleteSince I couldn't read the Amharic letters in my iPhone I only read the English comments. Many people impressed by your post, and cann't stay well until I read it. I am really conscious until I read it
ReplyDeletehey, dani it is such an impressive article keep it up may GOD BLESS YOU & UR FAMILY.
ReplyDeleteBel Endih Tsafna Asdesten Enji Ledani Yemayihon nitirik wust gebteh netrakoch Adereken eko.
ReplyDeleteI don't know how much I am right, but I always refrain myself from comments.
ReplyDeleteI am happy that we got one inspirational thinker and writer that has similar value with most of us.
Please keep on writing and reflecting you ideas, surely it will have positive impact on generation.
God Bless your work
ዳኒ በብዙ መንገዶቸ እየተማርን ነው አምላክ ይጠብቅህ ዮናስ አበበ
ReplyDeleteZIG HILINA ENJE ZIG MENGED YELEM! EWNET NEW!
ReplyDelete*****************************************
ReplyDeleteአየህ ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ አሳብ አይበላም፣ አልጋ ተመቸ ተብሎ ያለ አሳብ አይተኛም፡፡ ጨዋታ ደራ ተብሎ ያለ ልክ አይወራም፤ ገንዘብ አለ ተብሎ ያለ መጠን አይወጣም፤ እግር አለ ተብሎ ያለ ምዕራፍ አይኬድም፡፡ ይህ ኅሊናን ማቦዘን ነው፡፡
************************************************
ድንቅ ፅሁፍ ነው ዳኒ
ቅዱስ መፅሀፍ፥ “ሁሉ ተፈቅዷል ሁሉ ግን ለበጎ አይሆንም ፡፡”
ግን ኢትዮጵያውያን ላለፉት 20 ዓመታት ምን እያደረግን እንደነበር ቆም ብለን እራሳችንን ማየት ችለን ነበርን፡፡ላለፉት 20 ዓመታት እኮ ብዙ የቀረቡልንና የተፈቀዱልን ነገሮች ነበሩን ነገርን ግን ስንቶቹ ለበጎ ነገር የሚጠቅሙን ሆነው ተገኝተው ይሆን እንጂ፡፡ከውጪ ስናየው የተፈቀደልን የመሰለን ነገርም እኮ እንዲያው ለጊዜው ነገሩን በጥልቀት ስላልተረዳነው መሰለንና እንደ እንቦሳ ጥጃ ጋለብን እንጂ ፈፅሞ ያልተፈቀደልን ነበር፡፡የተፈቀደልንም ነፃነት በእርግጥም የሚጠቅመንን እውነተኛውን ነፃነት አልነበረም አላወቅነውም እንጂ አንዳንዱ ጭራሽ ለጥፋታችን የሚሆነን አጉል መረንነትን ነበር እንጂ፡፡
አዎ ምግብ እንደልብ ቀረበ ተብሎ ቁንጣን እስኪይዝ ያለ ምርጫና ያለ ለከት አግበስብሶ አይበላም፡፡በዘመነ ግሎባላይዜሽን ላለፉት 20 ዓመታት ይሀች ሀገር ምን አጣች ምን አተረፈች ምዘናውንና ፍርዱን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እተወዋለሁ፡፡ልብሱም በየፋሽኑና በያይነቱ ሆኖ በየሱቁና በየአዳራሹ ለአይን እንዲስብና እንዲያማልል ሆኖ ቀረበልን፡፡ግን የቀረበልንን ሁሉ እንደሚሆነንና እንደሚስማማን ሆነን መርጠን ተጠቅመን እንደሆነ እያንዳንዳችን እናውቃለን፡፡በየዲሹም ለአይናችን የሚስብ የሚያማልል በአክሽን በሮማንስ በሌላም አይነት ሆኖ ቀረበልን እንደሚስማማንና እንደሚጠቅመን ሆነን መርጠን አይተን እንደሆነ እያንዳንዳችን እናውቃለን፡፡ኢንተርኔቱም ይኸው ከደጃችንና ከቢሯችን ቀርቦልናል ስንቶቻችን ለመልካም ተጠቀቅመንበት ይሆንን?
ፓርቲውም መዝናኛውም በገፍ ቀርቦልናል ስንቶቻችን እንደሚበጀንና እንደሚጠቅመን ሆነን ተጠቅመነበት እንደሆንን እያንዳንዳችን እናውቃለን፡፡የውጪው አለም ሌሊትን ለፓርቲ አይነት ነገር በገፍ እንደቀረበልን ሁሉ የውጪው አለም ሌሊትን ለስራ ጭምር ስንቶቻችን ተጠቅመንበት ይሆንን? በዘመነ ግሎባላይዜሽን ላለፉት 20 ዓመታት ምርጫና ዲሞክራሲ የሚባለውም ነገር እኮ በገፀ በረከትነት ከሸቀጡ ጋር አብሮ እየቀረበልን ነበር ፡፡ነገር ግን በምን አይነት መልኩ እየቀረበልንና እየተጠቀምንበት ነበር ወይንስ በምን አይነት መልኩ ደግሞ ወደፊት ይቀርብልን ይሆን?በልካችን እየተሰፋ ይሆን የሚቀርብልን ወይንስ ያለገደብ?በማስተዋል ለመልካም እንጠቀምበት ይሆን ወይነስ ባለማስተዋል ለመለያየትና ለጥፋታችን?
ጊዜና ሁኔታዎች ፈቀዱልን ብለው ህዝብንና ዜጋን ጥራት የሌለው እቃ እያቀረቡ ለመስማት የሚሰቀጥጥና ለማየት የሚቀፍ ዋጋ እያስከፈሉ በሌላው ወገናቸው ስቃይና ድህነት ሀብት ያከማቹ መቼ በሰላምና በጤና ይበሉት ይሆንን?በዚህስ መልኩ በዘረፉት ገንዘብ ሁሉ ተፈቅዶልናል ብለው የቱን የቱን ሀጢያትና ግፍ ሰርተውበት ይሆንን ወይነስ መልካም ነገርን አድርገውበት ይሆንን?
ሀይልና ስልጣኑ አለን ብለው የስልጣናቸውን የመጨረሻ ድንበርና ወሰን ለመፈተን እየፈለጉ ያሉ Adventurers የገዛ ራሳቸው የስልጣን አባዜ ከፊታቸው የጋረጠባቸውን ፈተና ያለፉት ይሆንን?
ነው ወይነስ “እስኪ የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ይህንን ድንጋይ ዳቦ አድርግ” ተብሎ በሰይጣን እንደተፈተነው እየሱስ ክርስቶስ “ሰው በእህልና በውሃ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሄርም በሚወጣው ቃል ጭምር እንጂ ብለው”እነሱም ፈተናውን በተመሳሳይ መለኩ በማስተዋል ያልፉት ይሆንን?
በስተመጨረሻ እንድ ታሪክ ላንሳና ነገሬን ልቋጭ፡፡አንድ ወቅት “God መust be Crazy” የሚል አፍሪካ ውስጥ የጥንታዊ ጋርዮሽ የሚመስል አይነት ህይወት በሚኖሩ ኋላቀር አፍሪካውያን ቡሽ ሜኖች ላይ የተሰራ የድሮ ፊልም ላይ አይቼ ነበር፡፡በእርግጥ በፊልሙ ላይ ነጮችም ይሰራሉ፡፡እንዲያውም God የሚለውና እና “God Must be Crazy” የሚለው ስያሜ በጥቁሮቹ ለነጮቹ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ታዲያ አንዷ ነጭ አንዱን ጥቁር ቡሽ ሜን እንደመፍለጫ ወይንም እንደመገልገያ መሳሪያ የሚጠቀምበትን ድንጋይ ወይንም ሱፋጭ የሚመስል ምሳር ነገር ለማየት ትቀበለዋለች፡፡ልብ ብላ ስታየው ለካ ብርቅዬና ውድ ማእድን ወይንም ጠንካራ ዲያመንድ ነው ለካ፡፡በዚህ ጊዜ ነገሩ ስላላማረው ያ ቡሽ ሜን ወንድ መልሳ እንድተስጠው እጁን ይዘረጋላታል፡፡ምክንያቱም ከእጁ የማይለየው የእለት ጉርሱን ወይንም ሆዱን የሚሞላበትና የተለያየ ስራ የሚሰራበት የቀኝ እጁ የሆነ መገልገያ መሳሪያው ነውና፡፡ከዚያም ለማዘናጋት ብላ ደንገት ከቦርሳዋ ትዝ ያላትን አንድ ትንሽ የፊት መስታወት ታወጣና ፊቱን እንዲያይበት ትሰጠዋለች፡፡እሱም ለጊዜው ከዚህ በፊት አይቶት በማያውቀው መስታወት የራሱን ምስል ድንገት ሲያየው በመገረም ከራሱ ምስል ጋር ለትንሽ ጊዜ መጫወት ጀመረ፡፡በዚህ መሀል ይህች ብልጣብልጥ ሴት ይህንን ውድ የዲያመንድ ማእድን አዘናግታ ልትወስድበት አስባ ነበር፡፡በእርግጥ እሱ መገልገያ መሳሪያነቱን እንጂ ውድ የዲያመንድ ማእድን መሆኑን ፈፅሞ ሊያውቅ አይደለም እንኳን አልጠረጠረም፡፡መጨረሻ ላይ ይህችው ብልጣብልጥ ነጭ ሴት አዘናግታ በፊት መስታወት አታላ በልዋጭ ልትወስድበት ስትል ይህ አንኳን አይሆም የኔ እመቤት ያለዚህ መገልገያ መሳሪያዬ መኖር አልችልም ብሎ መስታወትሽን እንቺ ውሰጂልኝ ብሎ መልሶ ይቀበላታል፡፡አዎ በስተመጨረሻ መስታወቱ አይቶት የማያውቀው አዲስ ነገር ሆኖበት ለጊዜው ተገርሞ እየተዝናና ቢያየውም ነገር ግን ያለ መገልገያ መሳሪያው ደግሞ ህይወቱና ህልውናው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ በኋላ ላይ ከእንቅልፉ ባኖና ነቅቶ ነበርና መልሶ ውድ ንብረቱን እጁ ማድረግ ቻለ፡፡ሰዶ ማሳደድ ካመረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ ነው ያለው ያገራችን ሰው፡፡
እኔም በዚህ ይብቃኝ ለዛሬ፡፡
ከምስጋና ጋር
it factual, truthful mentality opens any enclosure.
ReplyDeleteBetam tekami Tsehufe new, Thanks Dani,tedegagmo tenebo aymero weste bekemt tiru new memeria endehune huwoten lale machelem yeredale berhane yehounale,adis mengede lemekeyes yanesasal, takalehu tsehufochene manbebe betame new yemewedewe Berta eshe, Leuel Egzabehar kante ena kebetseboche gare yehune.
ReplyDeleteመንገድ የሚከፈተው ኅሊና ውስጥ ነው፡፡
ReplyDeletedany, Egziabher yistilin
መኖር ማለት ማግኘት አይደለም፤ መኖር ማለት መትረፍረፍ አይደለም፤ መክበር እና መንፈላሰስ አይደለም፡፡ መኖር ማለት ማሰብ ነው፡፡ በሥጋ ሳይሆን በኅሊናህ ኑር፡፡ በኅሊናህ ከኖርክ የተዘጋ መንገድ የለም፡፡ ቢኖርም ትከፍተዋለህ፡፡
ReplyDeleteየሚገርም ነው ዳኒ በታም እናመሰግናለን፡፡ ብርህ ህሊና ይስጠን
ReplyDeleteIMPRESSIVE.
ReplyDeletegreat and insightful!
ReplyDeleteዳኔ በጣም ጥሩ ጱሀፍ ነው እናመስግናለን
ReplyDeleteከዚህ በፊት ከሰማሁት፣
ReplyDeleteአንድ ሰው ለወዳጁ ያጋጠመውን እንዲ ብሎ ይነግረዋል፣
‹‹ለጥ ባለ አውላላ የሳር ሜዳ ላይ እያቋረጥሁ ወደ መንደሬ እየሄድሁ ሳለ እንበሳ መጣብንኝ፡፡ ዙሩያዬን ብመለከት አንድም ተንጠላጥዬ ላመልጥበት የሚያስችል ዛፍ አጣሁ፡፡ ቦታው ሳር ብቻ ነበር ያለው፡፡›› ብሎ ሲነግረው ፤ ወዳጁ መልሶ ‹‹ ታዲያ እንዴት አመለጥክለ?›› ቢለው
‹‹ዛፍማ መኖር አለበት፡፡›› አለው ይባላል፡፡
መኪናን በባትሪ ኃይል አይነዱትም
ReplyDeleteDear Deacon Daniel,
ReplyDeleteMany thanks in deed for your deep and philosophic perspective. May God bless you so that we exploit you more.
A person, enemies, a bulwark, a tree, a corp., street and an imagination! It is good view for anyone. If suddenly happens something, you don't have time to analyze anything to use of you mind. You just run or do something to evacuate away from enemy. But, if you have chance to think some idea during the time, you can move out wisely to save yourself or you can do some protection to protect from attacks.
ReplyDeleteThank you Dani
ReplyDeleteit is one of your best articles
my mind is totally changed!!!
thank you again
I just remember a Book saying about the concept of Double Creation.Mental and Physical Creation.If someone is unable to visualize what to happen he will never see what he needed.Brother Daniel has elaborated this in a way I can visualize it....such that I can live it.
ReplyDeleteThank you Dear for sharing such wonderful idea!!!
ReplyDeleteBenegerachin lay semonun yemitawotachew tsihufoch rasihin ketifat lemeshef stil new really!!! surprising i don't accept it for me!!!
ReplyDeleteደስ የሚል ምክር ነው
ReplyDeleteDani Thank you.It is very interesting message.please keep it up.God bless you&your family
ReplyDeletewow very nice .
ReplyDeleteሰው የሰራው ስለሆነ ግንቡም ይፈርሳል አሳዳጆቹም ያስተውላሉ ተሳዳጁም ይጽናናል ዛፉ ግን እስከአለም ዳርቻ ድረስ ተንሰራፍቶ ይኖራል በመከራ ስጋ በህሊና ሰቆቃ የተንገላቱ ሁሉ ያርፉበታል በዚያም ከችግር ከመከራ ይጽናናሉ ስለዚህ ዋናው ዛፉን መጠበቅ ነው ከምስጥ ከፍልፈል ዛፉ ግን የግዴታ መኖር አለበት ያለዚያ የቁም ጽልምት ይመጣልና
ReplyDeleteበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ReplyDeleteየተከበርክ መምህር እንደምን ሰንብተሃል ሱባዔ እንዴት ነው?
የዛሬው ጽሁፍህ ትንሽ ረቀቅ ያለ ነው ሙሉ በሙሉ የተረዳውህ አይመስለኝም የገባኝን ያህል እንድል ፍቀድልኝ
ተስፋ መቁረጥ እንደማይገባ በማናቸውም አስቸጋሪ ሁኔታዎች በቀቢጸ ተስፋ ከመዋጥና ከመቆዘም ይልቅ ተረጋግቶ በእምነትና በእውቀት መፍትሄን ማፈላለግ እንዲገባ ለማስረዳት የፈለግህ ይመስለኛል።
እውነት ነው ዛሬ ለብዙዎቻችን ያልተረዳን ነገር ይህ ነው ሐዋርያትን ብንመለከት የድንግልን ማረግ ወንድማቸው ካስረዳቸው እንዴት እኛስ ሳናይ ብሎ መቆጨት የሚጠበቅ ነገር ነው እኛም የርሱን ደስታ ማየት አለብን ብሎ ሱባዔ መግባት ግን እንዴት ያለ እምነት ነው? እኛ ዛሬ በሕይወታችን በቤተክርስትያናችን በሃገራችን እንዲመጡ የምንሻቸው መፍትሄዎች የዚህን ያህል የራቁ ናቸውን?አይደሉም ግን እኛ ችግሮቻችን አንድም በጋዜጣና በመጽሄት ስናየው ወይ ነዶ እያልን የወሬያችን ማጣፈጫ ብቻ ነው የምናደርጋቸው ወይም ከዚህ በከፋ መልኩ ማን ይህን አለው ከየትኛው ወገን ነው ብለን የኛ ያልነው ወገን ተናግሮት ከሆን ምን ይበል ምን የተናገረውን ፍሬ ነገር እንኳ ሳንመረምር ድንገት መርምረንዉ ቢጎረብጠን እንኳ እንዲህስ ባላለ ከማለት እንዴት እንዲህ አለ ብሎ ከመመርመር ፋንታ ጭፍን ተሟጋቾች/ደጋፊዎች መሆን ይቀናናል በተቃራኒ ወገን የተሰለፈ ያልነው ከሆነ ደግም ለማጥላላት ተቀባይነትን ለማሳጣት የማናቀርበው መረጃ የማንጠቅሰው ጥቅስ የለም ታድያ መግባባት/መፍትሄ/ ከየት ትማጣለች አንዳንዶች ደግሞ በጸሎታችን ብናነሳውም በፍጹም እምነት አንቀርብም ስለዚህም ምንም አናገኝም።
በጽሁፍህ እንዳተትከው ከእምነት ጋር የሚያስፈልገው ሌላው እውቀት /ሕሊና/ ነው ዲሜጥሮስ ልጆቹን የተረዳበትን የተንከባከበበትን እውቀትና ፍቅር እነ ሀቢብ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያናቸውን የታደጉበትን ቆራጥነትና ስልት ሌሎችንም በአባቶች በምእመናን አርቆ አሳቢነት የመጡ ለውጦችን ስናይ እውቀት በህሊና መመራት ከቤታችን ምን ያህል እንደጠፋ ያስረዳናል።
“እናም መንፈስ እንዲህ አለው፡፡ መጀመርያኮ ትሮጥ የነበረው በኅሊናህ አይደለም በእግርህ ብቻ ነው፡፡ እግርህ መሄድ ስለቻለ እና መንገዱም ሊያስኬድህ ስለቻለ ብቻ ነው የሮጥከው፡፡ ስለቻሉ መሮጥ አና እንዲችሉ ሆኖ መሮጥ ይለያያሉ፡፡ ስለሚያስኬድ መሄድ እና እንዲያስኬድ ሆኖ መሄድ ይለያያሉ”፡፡የሚለው የጽሁፍህ ክፍል ለኔ አልተዋጠልኝም ወይም አልተረዳሁህም በመንገድ ላይ ሮጦ ሮጦ ከግንብ ጋር መጋፈጥኮ በራሱ ስህተት ወይም ወደህ የምታመጣው ላይሆን ይችላል እርግጥ በጥበብ መሄድ ሊያሳልፍህ ይችላል። አንዳንዴ ግን ጥበብህ ግንቡን እንድታሳልፍህ እውነትን እንድትገፋት እንድትረግጣት ታስገድድህ ይሆናል ።እናም ገና ግድግዳ አለ ተብሎ መንገድ መቀየር የለበትም፤ ግድግዳውን እንዳታገኘው የሚያደርግህ መንገድ ሁሉ ምን የወደድከው ቦታ የሚያደርስህ ቢመስልህም ከእውነት ጋር ካጋጨችህ ከህሊና ብትወጣም ብልጠት ነች። እናም እርሷን ከመከተል እውነትን ይዞ ግድግዳውን መግፋት የሚበልጥበት ጊዜ አለ። መንገድን ስለሚያስኬድ መከተል እውነት ነው እግር እንጂ ኅሊና የማይጠይቅ ተራ ነገር ነው እንዲያስኬድ ያልነው መንገድ ከእውነት ጋር ያለውን ዝምድና መርምሮ መሄድ ግን ከባለአእምሮነት በላይ መንፈሳዊነት ነው። እናም መንገዳችን ከዚህም አንግል መመርመር ይገባዋል እላለሁ ።
ሌላው የውስጥ አርበኝነትም ከባንዳነት ይሻላል እንጅ ቆርጦ የወጣን አርበኛ አያክልም። የውስጥ አርበኞቹ ቆርጠው የወጡት አርበኞች ባይኖሩ ብቻቸውን ጣልያንን ማባረር ሊችሉ ቀርቶ ስንት ነገር በሆነ ነበር እነ አቡነ ጴጥሮስ ከኢትዮጵያ አልፎ በአለም ሰማእትነታቸው ሊመሰከርላችው እንደዛሬው ትውልዱን ሊሞግቱ ቀርቶ ደመ ከልብ/በሰው ዘንድ/ ሆነው በቀሩ እኛም ሌላ ታሪክ በተማርን ነበር አርበኝነት /ፊትለፊት መናገር ፊትለፊት መጋፈጥ/ መኖር አለበት በተለይ ዛሬ ቤተክርስትያንን እርቃኗን ሊያስቀሩ የሚፋተጠኑ ሃሳውያን መምህራን በፈሉበት፧ በሚሾሙበት፧ አድራጊ ፈጣሪ በሚሆኑበት ጊዜ አጎንብሶ እልፍኝ ዘግቶ የሚያልጎመጉም ሳይሆን ባደባባይ ቀና ብሎ የሚመሰክር የሚሞግት ከህዝቡ ቀቢጸ ተስፋን የሚያርቅ ለቤተክርስትያንና ለቤተክርስትያን ክብር ብቻ ራሱን አሳልፎ የሰጠ ለግል ጥቅሙ ክብሩ የማይባዝን ጀግኖ የሚያጀግን አርበኛ ያስፈልገናል እላለሁ። አምላክ እርሱን ያስነሳልን አንገት መድፋትን መቆዘምን የምናርቅበትን የኅሊናን መንገድ የሚያሳይ የውስጣችንን ጨለማ የሚያርቅ መሪን ይስጠን ድንግል በምልጃዋ ትርዳን።
እግዚአብሔር ይባርክህ ታይቶ ከመጥፋት መስሎ ከመቅረት ይጠብቅህ
thank you, long live
ReplyDeleteእኔ እንደተረዳሁት
ReplyDeleteእግር፤ህሊና፤ግንብ፤ዛፍ፤ሐረግ ከ እዉቀት እንዲሁም ከ እዉነት ጋር ያላቸዉ ዝምድና እንዴት ነዉ፡፡ግንቡማ መልኩን ይቀያይራል እንጂ ሊጠፋ አይችልም፡፡ዛፉም ሁሌ ግንቡን ለማሳለፍ ዝግጁ ነዉ፡፡አሁን ምርጫዉ ግንቡን ላለማግኜት መንገድ መቀየር ነዉ፡፡ይህ ደግሞ መጨረሻዉ ከግንብ የባሰ አዘቅት ነዉ፡፡አሳዳጆችም ይኖራሉ፡፡ተሳዳጆችም መንገዳቸዉን መቀየር የለባቸዉም፡፡ህሊናን መጠቀም ጥሩ ነዉ፡፡ትኩረቱ ግን ሁልጊዜ ዛፉን እያሰቡ መሆን አለበት፡፡የበለጠም መሆን አለበት፡፡ይህ ዛፍ የሚሳነዉ ነገር የለምና፡፡ግንብን አይደለም፣ባህርን ይከፍላል፡፡እዉነት የሆነዉን ዛፍ ግን በእግርም በህሊናም ልንተካዉ አንቺልም፡፡
ልጀ፡ ግሩም ትጽፉለህ ግን ጊታ ለኛ የሚሰማ ጆሮ ይስጠን። አሜን
ReplyDeleteWow dani, it's very interesting. God gives, long live with good health 4 u & ur family! ong live with good health 4 u & ur family!
ReplyDeleteLong live to Dani and his blog!!!!
ReplyDeleteኅሊና እና መንገድ እኔ እንደገባኝ!
ReplyDelete1.አሳዳጅ /ጠላት/ የተባለው ዲያቢሎስ ሲሆን ተሳዳጁ የሰው ልጅ ነው፡
አሳዳጆች ሰዎችን ሊያሸንፉ የሚችሉበትን አመቺ ጊዜ ጠብቀው እንዲሳደዱ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡም እንደሚደሰቱ /ግንቡ ትልቅና መውጫ እንደሌለው ለመያዝም አመቺ መሆኑን አስበው እንደተደሰቱት/ ሰዎች በሥጋ ዝሙት ወይም በነፍስ ዝሙት (በምንፍቅና) እንዳይወድቁ ሲጠነቀቁ በትዕቢት (እኔ ያልኩት ካልሆነ በማለት) ወይም በውዳሴ ከንቱ (እንደ እኔ ያለ ማን አለ? ማንም እኔ የማስበውን ማሰብ እና እኔ የምሰራውን (የኔን ይህን) መስራት አይችልም ብሎ በማሰብ እና ሌሎችን በመናቅ) እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል፡፡
ዲያቢሎስ የረዥም ዓመት ልምድ ያለው በመሆኑ ሰዎች በምን ሊወድቁ እንደሚችሉ በማሰብ ባልጠበቁት መንገድ ይፈትናቸዋል ይላሉ የግብፁ ፓትሪያርክ አቡነ ሺኖዳ 3ኛው ስንቶቻችን ነን ባልጠበቅነው መንገድ ተፈትነን ያልወደቅነው?
2.ያ ሰው መጀመሪያ በእግር የሮጠው ሩጫ ለመንፈሳዊ ፈተናዎች ሥጋዊ መፍትሔ መሻትን ነው፡
ለመንፈሳዊ ፈተና ሥጋዊ መፍትሔ /ብልሐት፣እቅድ፣ቀመር፣ስልት…../ መፍትሔ አያመጣም፡፡ ይልቁንም በኅሊና መሮጥ (መንፈሳዊ መፍትሔን መሻት) ያስፈልጋል፡፡
ያ ሰው በመጀመሪያ በእግሩ ብዙ ሩጦ ሲደክመው ተስፋ ሊቆርጥ እንደደረሰ ሰዎች ለሚመጣባቸው ፈተና የሥጋዊ መፍትሔን በመፈለግ መፍትሔ እንዳልሆነ ሲረዱ ተስፋ እንደሚቆርጡ ያሳየናል፡፡ በዘመድ፣ በዘር፣በስልጣን፣በዕውቀት፣በገንዘብ እና በመሳሰሉ ነገሮች በሚመካ ሰው እነዚህ ሁሉ ላጋጠመው ችግር መፍትሔ እንደማይሆኑ ሲረዳ ያዝናል ይተክዛል ተስፋ ለመቁረጥም ይደርሳል፡፡ ብርቱ ከሆነ ወደ እውነተኛው መፍትሔ ይመለሳል፡፡ አቡነ ሺኖዳ አንደሚሉት ተስፋ ከቆረጠ ግን ሁሉም ነገር አለቀ ማለት ነው፡፡
3.በኅሊና የተደረገው ሩጫ መንፈሳዊ መፍትሔ መሻትን ነው፡
ሰዎች የእግር ሩጫቸውን ጨርሳው ወደ ኅሊና ሩጫ ሲመለሱ ለችግርቻቸው መፍትሔ የሚሆን ነገርን እንደሚያገኙ ሁሉ የሥጋዊ መፍትሔ እውነተኛ መፍትሔ አልሆን ሲላቸው መንፈሳዊ መፍትሔን መፈለግ ሲጀምሩ መንገዱ ይታያቸዋል፡፡
በእስራኤላውያን እምነት ባለበት ጩኸት የኢያሪኮ ግንብ እንደፈረሰ፣ በእምነት ባህረ ኤርትራ ለእስራኤላውያን ብቻ መንገድ ሆኖ እንደተከፈተ 'ሩጫችን መንፈሳዊ ሲሆን በዚህ በረዥሙ ግንብ ውስጥ ያለውን መውጫ ቀዳዳ ለማየትና ዛፍ በተባለው እግዚአብሔር ሐረግና ቅርንጫፍ በሆኑት በእመቤታችንና በቅዱሳን ተራዳኢነት እንዴት መሻገር እንደሚቻል መንገዱ ይታየናል፡፡ ይቆየን…..
አምላክ ሁላችንንም በኅሊናና በመንፈስ እንድንጓዝ ይርዳን!
ከወልደሚካኤል ዘሜክሲኮ
Exciting!!!
ReplyDeleteተሳዳጅ = አንተ
ReplyDelete“አሳዳጅ”= _ _ _ _
ግድግዳ = ፈተና
ዛፍ = ቤተ ክርስትያን
ዛፍ ላይ የተጠጋ አንድ ሐረግ= - - - -
ከግድግዳው ጀርባ ያለ ህይወት = I don’t know may be self actualization(non sense)
ከልብ የሞላው በአፍ ይወጣል ሃረጉን እንደ ፔንዱለም ማወዛወዝ፤ መበጠስ ለምን አስፈለገህ ነው ሃረጉን የማይበጥስ ተረት አይመችህም ? መስሎህ እንጂ ሃረጉ ባንተ ተረት እንጂ በእውነቱስ አልተበጠሰም እንዳንተ ሳይሆን ወደ በለጠው ጸጋ ገና አእላፍ ይሸጋገሩበታል
ቂቂቂቂ....... አይይይይ የእኛ ሰም እና ወርቅ አዋቂዎች ..... ምናለ መጀመሪያ በጐ ህሊና ቢኖራችሁ? ማን ተርጉሙልን አላችሁ? ይህን የክፋት ትርጉማችሁን እዛው የክፋት ልባችሁ ውስጥ አስቀምጡት፡፡
ReplyDeleteTo anonymous August 14,2011 9:56
ReplyDeleteBefore writing ,especially critics, better to think ten times. Your start is accompanied by good analysis, but you finish it with feeling. To my knowledge perception and feelings should not go further beyond reinforcement for writing. What I see on your comment is that you finished with perception expressed by feeling /words of feeling/.
This will kill the value of your comment.
When I see your conclsion from the main article point of view it seems for me wrong. The article didn't say he/the writer/ is the only person
እኔ ብዙ ትምህርት አግኝቼበታለሁ እግዚአብሔር ይባርክህ
ReplyDelete"አየህ ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ አሳብ አይበላም፣ አልጋ ተመቸ ተብሎ ያለ አሳብ አይተኛም፡፡ ጨዋታ ደራ ተብሎ ያለ ልክ አይወራም፤ ገንዘብ አለ ተብሎ ያለ መጠን አይወጣም፤ እግር አለ ተብሎ ያለ ምዕራፍ አይኬድም፡፡ ይህ ኅሊናን ማቦዘን ነው፡፡" በጣም ደስ የሚል አገላለፅ ይህ የአብዛኞቻችን ችግር ነው ዳኒ እግዜር ይባርክህ
ReplyDeletewonderful idea thanks.
ReplyDeleteasteyaetochu berasachew 1 bilog nachew, kale hiwot yasemalin
ReplyDeleteDinik tsihuf new
ReplyDelete