Thursday, August 4, 2011

የአንድ ዕብድ ትንቢት


አንድ ዕብድ አራት ኪሎ ላይ ጆሊ ባር ፊት ለፊት ቆሞ «ወደፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ በስድስት ይከፈላል፣ በስድስት ይከፈላል» እያለ ቡትቶውን እየጎተተ ይጮኻል፡፡ አጠገቡ የነበሩ ጋዜጣ ሻጮች «ዝም በል፣ ዕብድ፣ ተነሣብህ ደግሞ፤ ማን ይከፍለዋል ደግሞ፤ መዓት አውሪ» አሉና ሊያባርሩት እጃቸውን ወነጨፉ፡፡ እርሱም በተራው ከት ብሎ ሳቀና «የዕውቀት ማነስ ችግር አለባችሁ፡፡ ኩላሊታችሁ ችግር አለበት፡፡ የኛ ሰው መከፋፈል ልማዱኮ ነው፡፡ በዝባዥ እና ተበዝባዥ፤ አድኃሪ እና ተራማጅ፤ ፊውዳል እና ፀረ ፊውዳል፤ ኢምፔሪያሊስት እና ፀረ ኢምፔሪያሊስት፤ አብዮተኛ እና ፀረ አብዮተኛ፤ ሕዝባዊ እና ፀረ ሕዝብ፤ ልማታዊ እና ፀረ ልማት፤ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ኪራይ ሰብሳቢ» መልሶ ከት ብሎ ሳቀ፡፡
ቀጠለ «ወደፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ በስድስት ይከፈላል» አለና የቀኝ እጁን መዳፍ ጠቅልሎ እንደ ጡሩንባ ነፋው፡፡
«ምን ተብሎ ነው የሚከፈለው» አሉት አንድ ጋዜጣ የሚያነበቡ አዛውንት፡፡
«ጥሩ ጥያቄ ነው» አለና ጉሮሮውን በስላቅ እንደመጠራረግ ብሎ «የሚበላ፣ የሚበላ /ይጠብቃል/ የማይበላ፣ የሚያባላ፣ የሚያስበላ፣ የሚያብላላ ተብሎ ይከፈላል» ይህንን ሲናገር በአካባቢው የሚያልፉትን የብዙዎችን ጆሮ ለመሳብ ችሎ ነበር፡፡ አንዳንዶቹም መንገዳቸውን ገታ አድርገው ያዳምጡት ጀምረዋል፡፡
«እስኪ ተንትነው» አሉት እኒያ አዛውንት ጋዜጣቸውን አጠፍ አድርገው
«'የሚበላ' ማለት ጤፍ መቶም መቶ ሺም፣ መቶ ሚሊዮንም ቢገባ መገዛቱን እንጂ የተገዛበትን የማያውቅ፤ በጋዜጣ ካልተጻፈ፣ በሬዲዮ ካልተነገረ በቀር የኑሮ ውድነቱ የማይነካው፤ የውጭ ምንዛሪ ቢጠፋም ባይጠፋም ዶላር የማያጣ፣ ወረፋ ቢኖርም ባይኖርም ባንክ እምቢ የማይለው፣ ጨረታውን ሁሉ ለማሸነፍ የሚያስችል ድግምት ያለው፤ ተራራ ቁልቁለት መውጣትና መውረድ ሳያስፈልገው ቤቱ ቁጭ ብሎ ሚሊየኖችን የሚያፍስ፤ ሰው ሁሉ በእጁ የጠቀለለው በእርሱ ጉሮሮ የሚያልፍለት፤ ሰው ሁሉ የጎረሰው በእርሱ ሆድ የሚቀመጥለት፣ ሰው ሁሉ ሮጦ እርሱ ሜዳልያ የሚሸለም፣ ለመብላት እንጂ ለመሥራት ያልተፈጠረ ማለት ነው፡፡ 
 «'የሚበላ' ማለት ደግሞ ጉቦ ለመስጠት፣ ኪራይ ለመክፈል፣ ግብር ለመክፈል የተፈጠረ፡፡ ምንም ሕግ አክብሮ ቢሠራ አንዳች ጉርሻ ካላጎረሰ ሥራው የማያልቅለት፤ ለመጋገር እንጂ ለመብላት ያልታደለ ማለት ነው፡፡ 'ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት' ሲባል አልሰማችሁም፡፡ የርሱም ነገር እንደዚህ ነው፡፡ ለመበላት የተፈጠረ ነውና ሕገ ወጦቹ ተቀምጠው እርሱ በሕጋዊ መንገድ እየሠራ እና እየኖረ እርሱ ነው የሚከሰሰው፤ እርሱ ነው የሚጉላላው፡፡ እዚህ አንዳንድ ሠፈር ያሉ ቀበጥ ወላጆች ለልጆቻቸው ሁለት ሁለት ሞግዚት ነው አሉ የሚቀጥሩት፡፡ አንዷ አሳዳጊ ናት፡፡ አንዷ ደግሞ ልጁ ሲያጠፋ የምትመታ ናት፡፡ ልጃቸው እንዳያመው እርሱ ባጠፋ ቁጥር እርሷ ትመታለች፣ እርሷ ታለቅሳለች፡፡ እነዚህም እንደ እርሷ ናቸው፡፡
«'የማይበላ' የሚባለው ለቁጥር የሚኖረው ነው» አለና ወደ ሕዝቡ ዘወር ብሎ «አሁን ለምሳሌ እኔ እና እናንተ ጥቅማችን ለቁጥር ነው» ሲል ብዙዎች በፈገግታ አዩት፡፡ «አዎ እኛኮ ቁጥሮች ነን፡፡ ቁጥር ደግሞ ምዝገባ እንጂ ምግብ አያስፈልገውም፡፡ የኛ ሥራ መመዝገብ ነው፤ መብላት አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲቆጠር እንካተታለን፤ ሲበላ ግን አንካተትም፤ ርዳታ ለማግኘት እናስፈልጋለን፤ እርዳታውን ለመቀበል ግን አናስፈልግም፡፡ ስለዚህ ቁጥር ነን ማለት ነው፡፡ ወደፊት እንጀራን በቴሌቭዥን ዳቦንም በፊልም ነው የምናየው፡፡ ወደፊት ምግብ ቤቶች ሁለት ዓይነት ክፍያ ያዘጋጃሉ፡፡ አንዱ ለሚበላ፣ አንዱ የሚበላውን ለሚያይ፡፡ እኔ እና እናንተ ገባ ብለን ምግብ እና አመጋገብ አይተን እንወጣለን፡፡
እንጀራ በሰማይ እኔ በእግሬ ሆኜ
አልደርስበት አልኩኝ ባክኜ ባክኜ 
የተባለው 'ፍካሬ ሕዝብ መጽሐፍ' ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸማል፡፡
«'የሚያባላ' የሚባለው ደግሞ ከሚበላው ተጠግቶ ለበይዎች እንደ 'ሀፒታይዘር' የሚያገለግል ነው፡፡ አያችሁ የሚበሉት መንቀሳቀስ አይወዱም፣ ውቃቢያቸው ይጣላቸዋል፤ ስለዚህም የሚያባላቸው ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ የሚቀበሉ፣ የሚያቀባብሉ፣ የሚያስተላልፉ ናቸው፡፡ እንደነዚያ ጠግበው ባይበሉም ትርፍራፊ ግን አያጡም፡፡ እነዚያ ግንድ እነዚህ ሥር ናቸው፡፡ እነዚያ ሆድ እነዚህ ግን እጅ ናቸው፡፡ የነዚህ ጥቅማቸው ከምርቱ ሳይሆን ከቃርሚያው ነው፡፡ በሞያቸው፣ በልምዳቸው፣ በአፍ ቅልጥፍናቸው፣ በመመቻመች ችሎታቸው ከሚበሉት ይጠጉና 'እባክህ ጌታዬ እንዲበላ ብቻ ሳይሆን በልቶ እንዲያተርፍም አድርገው' እያሉ እየጸለዩ ይኖራሉ፡፡ እነዚያ የሚበሉት ምግብ ሲዘጋቸው የሚያባሉትን ይሰበስቡና ይጋብዟቸዋል፡፡ ታድያ እነዚህ መታ መታ እያደረጉ ሲበሉ የነዚያም የምግብ ፍላጎታቸው ይከፈትላቸዋል፡፡ ምናልባትም የሚበሉት ካልተስማማቸው  የሚያባሉት ይታመሙላቸዋል፡፡
«አንድ ጊዜ አንድ ገበየሁ የሚባል ሰው በምኒሊክ ጊዜ ነበር አሉ»
«..............» የሚል የቀልድ ምላሽ ከከበበው ሰው አገኘ፡፡
«እና ገበየሁ በወቅቱ ለነበሩት አቡን አገልጋይ ሆነና የተጣላውን ሰው ሁሉ እያስገዘተ እጅ እግሩን አሣሠረው፡፡ ይህንን ያዩ ያገሩ ሰዎች
                                      ገብሽ መች ቀሰሰ ከየትስ አምጥቶ
                     ይወጋናል እንጂ ካቡን ተጠግቶ
ብለው ገጠሙለት አሉ፡፡
«'የሚያስበላ' የሚባለው ደግሞ የተሰጠውን ሥልጣን፣ ዕውቀት እና ኃላፊነት ተጠቅሞ የሚበሉትም እንዳይራቡ የማይበሉትም እንዲጠግቡ ማድረግ ሲገባው 'ላለው ይጨመርለታል' እያለ መሬቱን ሲቸበችብ፣ ግብር ሲቀንስ፣ ያልተፈቀደ ዕቃ ሲያስገባ፣ ሕገወጥ የሆነ መመርያ ሲያስተላልፍ፣ የሚውል ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሀገር የሚያስበሉ ናቸው፡፡ ስሕተቱን፣ ጥፋቱን፣ ሕገ ወጥነቱን፣ ጉዳቱን፣ በኋላ ዘመን የሚያመጣውን መዘዝ እያወቁ እኔን ምን ቸገረኝ ብለው ለበይዎች የሚስማማውን ብቻ የሚሠሩ ናቸው፡፡ እነርሱም አይጠቀሙም፤ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሀገራቸው ማረሚያ ቤት ነው፤ እነሆ ነገ ግዳጃቸውን ሲፈጽሙ እንደ ሸንኮራ ተመጥጠው፣ እንደ ሙዝ ልጣጭ ተልጠው ይወድቃሉ፡፡»
'የሚያብላላ' ይህ ደግሞ ለመብላት የሚያመች ሕግ ፣መመርያ፣ አሠራር እንዲዘረጋ የሚያደርግ፣ የሚበሉት አጋጣሚዎችን ሁሉ እንዲጠቀሙ መንገድ የሚያመቻች፤ ከበሉም በኋላ በተቻለ መጠን የበሉትም፣ አበላላቸውም ሕጋዊ መልክ እንዲኖረው የሚያመቻች ነው፡፡ መንግሥት ለበጎ ብሎ የዘረጋውን አሠራር፣ ያወጣውን መመርያ እና ያዋቀረውን መዋቅር እርሱ እንዴት ለበይዎች እንደሚስማማ ያጠናል፣ ያመቻቻል፣ ያስፈጽማል፡፡ ከመመርያው እና ከአሠራሩ ጋር የሚሄድ ደረሰኝ፤ ዶክመንት፣ ማስረጃ፣ ያዘጋጃል፤ አበላሉን ያሳልጠዋል፡፡ እነዚህ የጨጓራ አሲድ ናቸው፡፡ የጨጓራ አሲድ የበላነውን እንዲዋሐደን አድርጎ ይፈጨዋል፣ያስማማዋል፡፡ እነዚህም እንደ ጨጓራ አሲድ ይፈጩታል ያስማሙታል፡፡
«አንተ ይህንን ትንቢት ከየት አመጣኸው» አሉት አንዲት እናት ገርሟቸው፡፡
«በዕብድነቴ ነዋ እናቴ፤ አዩ እዚህ ሀገር ካላበዱ በቀር ብዙ ነገር አይገለጥልዎትም፡፡ እንዲገለጥልዎት ከፈለጉ እንደ እኔ ማበድ አለብዎ፡፡ ለነገሩ እዚህ ሀገር ዕብዱ ብዙ ነው ግን ዓይነቱ ልዩ ልዩ ነው» አላቸው፡፡ «ደግሞ የዕብድ ምን ዓይነት አለው፤ ሁሉም ያው ነው» አሉት እኒያው እናት የነጠላቸውን ጫፍ ወደ ትከሻቸው እየመለሱ፡፡
«ተሳስተዋል፤ አዩ ይህም ቢሆን ካላበዱ በቀር አይታይዎትም፡፡ ብዙ ዓይነት ነው ዕብዱ፡፡ የመጀመርያው ያበደና ማበዱን እንደኔ የተረዳ ነው፡፡ ሁለተኛው አብዶ ማበዱን እያወቀ ግን ማመን የማይፈልግ ነው፣ እንደ ብዙዎቻችሁ፤ ሌላው አብዶ ግን ማበዱን ባለማወቁ የተምታታበት ነው፡፡»
«ቆይ አንተ ችግሩ ብቻ ነው የተገለጠልህ፤ መፍትሔውን አልገለጠልህም፤ ማበድህ ካልቀረ ለምን ከነ መፍትሔው አታብድም ነበር» አሉት እኒያ አረጋዊ፡፡

78 comments:

 1. dani I like the way how to erite .wonderful God bless you and your family

  ReplyDelete
 2. I wish if "Those got mad" could read this article...well done dani!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. We all are reading bro! Please re-read our category around the last paragraph of this blog!

   Tks Dani! U 'r really gifted! Let God bless all ur time!

   Delete
 3. Danie Amlak yitebeke agelgeloteken yibarkele

  ReplyDelete
 4. nigusie from dz
  Dn. Dani thank you for you post! you are right there is many 'ibdi' but not identify themselves as 'ibdi' these guys are found around the church and also other public and non-public office.It is amazing that they assume themselves as a normal man but their act / work are just work of evil these is the cause even for the absence of unity in diversity.God blessing you

  ReplyDelete
 5. Wechew gud gene kesbekes hulachinm enabdalen malet new? Kezihis yisewren!!

  ReplyDelete
 6. ድንቅ ተሰጦ ነው፡፡ እውቀት ማለት ያወቁትን ማሳወቅ ነው፡፡ የመጨረሻው የጹሁፉ ሐረግ በጣም ይመቻል፡፡ ‹‹ማበድህ ካልቀረ ለምን ከነመፍትሄው አታብድም ነበር››
  በጣም ይገርማል ሴትየዋ ያበደው ሰውዬ የተናገረው ሁሉ የመፍትሄው አካል መሆኑን አልተገነዘቡም ወደሚል ድምዳሜ አደረሰኝ፡፡ ለካስ ጆሮም ካበደ በትክክል አይሰማም፡፡ የስሜት ህዋሶቻችን ለየብቻቸው ተነጣጥለው ሲብዱ እንዴት ይታረቁ ይሆን፡፡

  ReplyDelete
 7. ዳኒ ይሄ ምንም እብድ ነው አውቆ አበድ እንጂ እንዴት ታይቶታል?

  ReplyDelete
 8. አይ ዳኒኤል እብዱንም አዳመጥህ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ካነበብኩ በኋላ አፌን ነው ዬዘኩት!


  እንጀራ በሰማይ እኔ በእግሬ ሆኜ
  አልደርስበት አልኩኝ ባክኜ ባክኜ
  ገብሽ መች ቀሰሰ ከየትስ አምጥቶ
  ይወጋናል እንጂ ካቡን ተጠግቶ

  ReplyDelete
 9. አይ ዳኒኤል እብዱንም አዳመጥህ! እጅግ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ካነበብኩ በኋላ አፌን ነው የያዝኩት!አይ ዳኒኤል እብዱንም አዳመጥህ! እጅግ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ካነበብኩ በኋላ አፌን ነው የያዝኩት!
  እንጀራ በሰማይ እኔ በእግሬ ሆኜ
  አልደርስበት አልኩኝ ባክኜ ባክኜ
  ገብሽ መች ቀሰሰ ከየትስ አምጥቶ
  ይወጋናል እንጂ ካቡን ተጠግቶ

  ReplyDelete
 10. Thanks so much...dani ejege btame teru eyeta nwe....eneme edakeme lmfetehewe abedalhu mabdeneme amegne ekblalhueme lmfetehewe abedalhu mabdeneme amegne ekblalhu

  ReplyDelete
 11. ayi Dani influencial view!May the Holly God be with You!!!

  ReplyDelete
 12. Dn. Dani it is verry interesting message God bless you bright views keep it up!!!

  ReplyDelete
 13. ገብሽ መች ቀሰሰ ከየትስ አምጥቶ
  ይወጋናል እንጂ ካቡን ተጠግቶ

  ReplyDelete
 14. Nice One! Articles with tremendous lessons like this deserve to be reposted. Thanks!

  ነገርን ነገር ያነሳዋል አሉ ...

  ይኼው 4 ኪሎ ጆሊ ባር አካባቢ የታየው ዕብድ ነው ፤ ባለፈው መገናኛ ድልድይ ሥር ፤ ሰው ፈጣሪውን 'ሰላም አውለኝ' ብሎ ወደየጉዳዩ ለመሄድ ሲጣደፍ ... " አለም ዘጠኝ ነው! ... ዘ . ጠ .ኝ ነው! ... ሐበሽም ዘጠኝ አይነት ነው! " እያለ ሲጮህ ነበር። ወቸ ጉድ አሁንማ አንድኛውን ለይቶለታል ማለት ነው ... መገናኛ እኮ ጨርቁንም አልጣለም ነበር ... ደግሞም " ትንቢት " አልነበረም የሚለው ... " ዛሬ! ... አ . ሁ . ን! " ነበር የሚለው። ... ታዲያ የዛን ዕለት ... ለወትሮው ፡ ካሰበበት በጊዜ ለመድረስ ቀንዶ / Higer Bus / ላይ ለመፈናጠጥ ፣ ባስና ሚኒባስ ለማግኘት ሲሯሯጥ ፣ ሲገፋፋና ሲጎሻሸም የሚያረፍደውን የመገናኛ ሰው ቀልብ ገዝቶ እና ባንድ አገር ሰው ተከቦ ... በማበዴ አገኘሁት በሚለው ነጻነት በመጠቀም ... አሁንም አሁንም " አለም ዘጠኝ ነው! ... ዘ . ጠ .ኝ ነው! ... ሐበሽም ዘጠኝ አይነት ነው! " እያለ ነበር ፤ ለነገሩ ሥርዓት አስከባሪዎችም ጭምር " ደግሞ ዛሬ ምን ይለፈልፍ ይሆን? " በማለት ከሰዉ ጋር አብረው ከበው ማርፈዳቸው ይህንኑ ነጻነቱን ቢያጸድቁለት አይደል?

  መገናኛ ባሰማው ዲስኩር ፡ 4 ኪሎ መጥቶ ከዘረዘራቸው ከስድስቱ ፦ የሚበላ፣ የሚበላ /'በ' ይጠብቃል/፣ የማይበላ፣ የሚያባላ፣ የሚያስበላ፣ የሚያብላላ ፤ ሌላ የሚብላላ ፣ የሚባላ/'ባ' ይጠብቃል/ እና የማያስበላ የሚሉ መደቦችን ጨምሮ " ሐበሽ ዘጠኝ አይነት ነው! " እያለ ሲጮህ ነበር፡፡ ... መቸም ተናግሮ አናጋሪ አይጠፋምና ... ከበው ከቆሙት መሃል ፤ አንድ በትከሻው ቀበቶዎችን ፤ በእጆቹ ደግሞ የጫማ ገበሮችን የተሸከመ ወጣት ግማሽ አስተውሎቱን ድንገት ለሚመጣ ገበያተኛ ሰጥቶና አንገቱን አስግጎ ፤ በተሰላቸ ድምጽ " አንተ መዓት ጠሪ ፣ ለፍላፊ ዕብድ ፤ ደሞ ዛሬ ምን መዓት ይዘህ መጣህ? " በማለት ጠየቀው ... ዕብዱም የሳቁን ምክንያት እርሱ ራሱ በሚያውቀው ፤ ከት ብሎ ስቆ ... አገሬውን ሁሉ በዘጠኝ መደብ የመደበበትን ዝርዝር መተንተኑን ቀጠለ ... እዚህም እዚያም እየረገጠ ፣ አሁንም አሁንም " ብታምኑም ባታምኑም አለም ዘጠኝ ነው! ... ዘ . ጠ . ኝ ነው! ... ሐበሽም ዘጠኝ አይነት ነው! " እያለ ፣ ደግሞ ደጋግሞ እየሳቀ የዘጠኙንም አይነት ዝርዝር በአንድ ጊዜ ወጣው ፤ ... የስድስቱ አይነት ዝርዝር 4 ኪሎ ላይ እንደዘረዘረው ነበር ... ስለቀሩት ሦስቱ የተናገረው ደግሞ የሚከተለውን ነበር ...

  የሚብላላ ፦ እዚህ ላይ ሲደርስ ቀበቶ ተሸክሞ ወደቆመው ወጣት ዞሮ ፤ ጠበቅ ያለ እውቂያ ያላቸው በሚመስል አኳኋን " ሰማህ? ... የሚብላላው እንደ ጓደኛህ አይነቱ ዕድለ ቢስ ነው ፤ እሱነቱ ከዚህም ከዚያም በሚነፍሱ ነገሮች የተመሰረተ ነው ፤ ሲፈጥረው ለምን? እንዴት? የሚባል ነገር የማያውቅ ፤ በድንግዝግዝ የሚጓዝ አይነት ነው ... ድንገት አንዱ ተነስቶ ' እነ እንቶኔ የደከምህበትን እየበሉት ነው ... ያስበሉት ደግሞ እነ እገሌ ናቸው ' ፤ ያለው እንደሆነ ማስረጃና መረጃ ፤ ግራና ቀኝ ሳይል ሲብላላ ፣ ሲተራመስ ፣ ሲራገም ፣ ሲወቅስ ይቆይና ፤ ሌላው ተነስቶ ደግሞ ' አይ እነ እገሌማ አይደሉም ፤ እነ እንቶኔ እንጅ ' ያለው እንደሆነ ያለ አመክንዮ ሲወቅሰው የነበረውን እገሌን በቅጡ ይቅርታ ሳይጠይቅ እንቶኔን ሊያጠፋ ሲብላላ የሚኖር ነው። ... ነገሮችን የመፈተሽ ልምድ ስለሌለው ብልጣብልጦች ይጠቀሙበታል ፤ የሚበሉትን ለማግኘት ኃይል እንዲሆናቸው ሲያብላሉት ሲያብላሉት ይከርሙና ፤ መሻታቸው ሲፈፀም አናውቅህም የሚሉት ነው።

  ይህን ብሎ አይኑን ከወጣቱ ላይ መልሶ ትንፋሽ ሲወስድ ... የዕብዱ ጓደኛውን ጠቅሶ መናገር ያላስደሰተው ባለቀበቶው ወጣት ፤ የሚቀጥለውን ዝርዝር ለመስማት መጓጓቱን ለመደበቅ እየተጠነቀቀ " የሚባላውስ? " አለው? ... ዕብዱ ቀጠለ ...

  " የሚባላው? ... የሚባላው? ... የሚባላውማ ፦ ዕድል ያልቀናው ነዋ ፤ ምስኪኑን ገፍቶና ደሃዋን አስለቅሶ ያላቸውን እንዳይቀማ ጊዜና ቦታ ስላልፈቀደለት ፤ ከበላተኛውም አፍ እንዳይመነትፍ ወኔና ብርታት ስለሌለው ፤ በይውንም ፣ ተበይውንም በአንድ ጨፍልቆ በነገር ጅራፍ የሚገርፍ ነው። ... ለእርሱ የተበዮች እሮሮና ለቅሶ እኩል ከበይዎች ተድላና ደስታ ያስጠላዋል። እርሱን አስፈቅደው እንደሚበሉ በላተኞችን ሲተች እንኳ ' መብላቱንስ ብሉ እሺ ፤ ግን እንዲህ አድርጋችሁ ባትበሉ ፣ እንዲህ አድርጋችሁ ደግሞ ብትበሉ ፣ ይህንን ደግሞ ባትበሉ ' እያለ ለሚሰማው ... ሁልጊዜ እርሱ በላተኛ የሚሆንበትን ዘመን በመናፈቅ እንደሚኖር ያሳብቅበታል። ይህን ጊዜ ከበውት የቆሙ ሁሉ አንድ ላይ አውካኩ ፤ እርሱ ግን ንግግሩን በመቀጠል ... " እጣ ፈንታውንም የሚባላ ያደረጉት እነርሱ ይመስል ፤ በተበዮች ብሶት ላይ ነዳጅ መጨመር የሚያስደስተው ነው። " በማለት የዚህኛውን መደብ ብይኑን ፈፀመ።

  ከዚህም በኋላ በድጋሚ ትንፋሽ ወስዶ " በመጨረሻ ... " ሲልና በንግግሩ እጅጉን የተገረሙ አንዲት እናት " ወቸ ጉድ! የዕብድ ቀን አያልቅም አሉ ... የማያስበላውስ? " ሲሉ አንድ ሆነ። ... አየት አድርጓቸው ፈገገ አለና ...

  " በመጨረሻ እውነተኛ የሐበሽ ሰው አለ " በድጋሚ ረገጥ አድርጎ " እውነተኛ! " በማለት ቀጠለ ... " የማያስበላው ፦ ይኼኛው ባንዱ ላብ ሌላው ለምን ይበላል? ፤ ባንዱ ድካም ሌላው ለምን እረፍት ያደርጋል? ፤ ... የሚል ነው። " አለና " ግን ... ግን ይቅርባችሁ እንዲህ አይነቱ ጥቂት ሰው ነው ፤ ብዙ ሰው አይወደውም ፤ ይጠላዋል ... እናንተም ትጠሉታላችሁ ... እናንተም ትጠሉታላችሁ " ብሎ እንደማቀርቀር አለ ፤ ባቀረቀረበትም በለሆሳስ " እናንተም ትጠሉታላችሁ " የሚለውን ደግሞ ዝም አለ ... ዝምታውን ላዬ ፤ ከደቂቃዎች በፊተ ሲጮህና ሲወራጭ የነበረ አይመስልም ነበር። ... ከብቦት የነበረውም ሰው ለአፍታ ባለበት ከእርሱ ጋር አርምሞ የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ሁለት ሶስት ሆኖ የመጣው ፤ በነገሩ እየተወያየ ፤ ለብቻውም የመጣ አንገቱን እየወዘወዘና ከንፈሩን እየመጠጠ ወደየጉዳዩ ተበተነ። ... እርሱም ...

  ReplyDelete
 15. This division of Ethiopian people in six repeated again. As Alberto Sebachi wrote in 1985, Italians in 1935 have a plan to divide Ethiopia into six.
  Again, Daniel told us this ibid has a classification of Ethiopian people into six.

  Awey memesasel

  ReplyDelete
 16. Gudu Kasa be FIKIR ESKE MEKABIR Metshaf lay ''GODU'' yetebalew ye zemenu sew kemyiasbew kedmo slemyiasb neber.

  ReplyDelete
 17. And there are those,7th or whatever, who would just stop by the side of the road and listen to an insane, mad man talking non sense!

  ReplyDelete
 18. Hi Dani,
  The article was clear and have message to wake up to all and to level one of the three categories! we need people like u in hard period of time to show things boldly.Everyone is matto/mad when he is alone.
  nesa zega

  ReplyDelete
 19. Dani it's interesting thanks a lot.

  ReplyDelete
 20. አሁን እኔ በዚይ አካባቢ ብኖር ኖሮ የሰውየውን ማንንነት ልመረምር እውዳለው። ይህ ሰው እውቀት ያለው ሰብአዊ አመለካከቱ ጠለቅ ያለም ይመስላል። ይህ ሰው እንዴት አበደ? መድኃኒት አጠጥጠውት ይሆን? ድግምት አድርገውበት ይሆን? ቀንተውበት ይሆን? ደብረሊባኖስ ቢወሰድ እኮ ለኢትዮጵያ አንድ ሰው ማትረፍ ይቻል ነበር። ይህን ሰው መርዳት ክርስትና አይደለም ትላላችኹ። በአካባቢይ ይላችሁ እና የምታቁት ካላችሁ እርዱት። ይህ ሰው እኮ በውስጠታዋቂ ለእርዳታ እየጮኸ ነው። ይህ ሰው ቤተሰቦች አሉት ይሆን? (እነዚ ሁሉ ጥያቄዎች በህሊናዮ መጥተውብኝ ነው)

  ReplyDelete
 21. Dear Daniel,

  Interesting intervention.

  ReplyDelete
 22. ha ha ---
  betam ymiral agelaletsu

  yes there are many people in Addis Abeba who are crazy due to Nuro wudinet , bizu sewu bichawun sihed eyawora newu yemihedewu

  i do not know why the rulers do not think and help at least once to help the citizen
  i think they did not need to help the people purpose fully

  thank you brother and let GOD give more men like you

  ReplyDelete
 23. you have excellent eagles eye! say thanks to your lord!

  ReplyDelete
 24. ደቂቀ ፀሃፍት ዘሳንሆዜAugust 5, 2011 at 12:51 PM

  እብደቱን የሚያውቅ እብድ ምን ትለዋለህ? እብደት ሲጀምር ለእብዱ ይታወቀው ይሆን? እንደኔ እብደት የሽንፈት የመጨረሻው ውጤት ነው። ብዙ ጊዜ የእብደት መድሃኒት ያበዱበት ነገር መሆኑ አይገርምም? የእብድት መስራች ማን ነው? አሳባጅ ወይስ አባጅ? የእብደትስ ጥቅሙ ምንድን ነው? የእብድ ሃኪምስ ማን ነው እብድ ወይስ ጤነኛ ሀኪም?

  ReplyDelete
 25. በደንብ አይተሀል፡፡ መፍትሔውን ማን ያሳየን?

  ReplyDelete
 26. ቆይ አንተ ችግሩ ብቻ ነው የተገለጠልህ፤ መፍትሔውን አልገለጠልህም፤ ማበድህ ካልቀረ ለምን ከነ መፍትሔው አታብድም ነበር» አሉት እኒያ አረጋዊ፡፡

  ReplyDelete
 27. very nice perspective ...just the right touch of sarcasm! anyone with tiniest brain can understand what's really messing up our country...it doesn't take a genius to figure that out. Anyways, the problem with our country is that the Crazy ones end up getting the key positions and they in turn drive everyone crazy..its a crazy country with all z crazies in the world! May God lead us to a greener field!

  ReplyDelete
 28. "ወደፊት እንጀራን በቴሌቭዥን ዳቦንም በፊልም ነው የምናየው፡፡ ወደፊት ምግብ ቤቶች ሁለት ዓይነት ክፍያ ያዘጋጃሉ፡፡ አንዱ ለሚበላ፣ አንዱ የሚበላውን ለሚያይ፡፡ እኔ እና እናንተ ገባ ብለን ምግብ እና አመጋገብ አይተን እንወጣለን፡፡"
  ብዙ ወደፊት የሚባል አይመስለኝም አሁንም አየተደረገ ነው። አስኪ ስንቶቻችን(የመንግሰት ስራተኞች፤ ደሞዝ ተከፋዮች) ጠግብን የምንበላ? ምግብ ቢት ሂደን አዘን ተጠቅመን የምንወጣ ምናልባት ባምት አንዲ 'ኧንደ መስቀል ወፍ' ለዛውም አስር ግዚ ሚኑ(Menu) አገላብጠን። ደግ ግዚ ፈጣሪ ያምጣልን።

  ReplyDelete
 29. Don't you have post this before? Wednesday, October 6, 2010. OR is there some thing

  ReplyDelete
 30. is ithis from crazy person's tought ,or just a bad sprits and superstition.

  ReplyDelete
 31. ዲ ዳንኤል
  ግማሽ ዕድሜህን ስታገለግልበት ከነበረው MK. (ድርጅት) በድንገትም ይሁን በቆየ ምክንያት ቁርሾ ከፈጠርህ ወዲህ የድርጅቱ አባላትም ሆኑ ደጋፊዎቹ ፡ አንተንም ሆነ መጣጥፎችህን በጥርጣሬ ዓይን እንደሚያዩህና ቀስ በቀስም እያገለሉህ እንደሚመጡ ፤ ከአሁን በሗላ በምታቀርባቸው መጣጥፎች የአንባቢዎች ምላሽ ለመረዳት ራስህን አዘጋጅ ።

  ማህበሩን የሚጠሉትም ሆነ በጥርጣሬ ዓይን የሚያዩት ሰዎችም ቢሆኑ የድሮ የአንተን ማንነት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አምነውህ ሊደግፉህም ሆነ ምንም ዓይነት አስተያየት ሊሰጡህ አይችሉም ።

  የወደፊት ሕይወትህን እንዴት ልትመራው እንዳሰብህ የምታውቀው አንተው ራስህ ብትሆንም ፡ ከድርጅቱ ጋር ያለህን ቅራኔ ካልፈታህ : ወይም ራስህን ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ካላገለልህ በቀር ፤ ትንሽ የሚከብድብህ ይመስላል ።

  ለማንኛውም ቅንነትህን እና ቀጥተኛ የሆነ ሃይማኖታዊ ዝንባሌህን አይቶ ፈጣሪ እንዲረዳህና ቀጣይ ሕይወትህን የተረጋጋ እንዲያደርግልህ ምኞቴ ነው ።

  ከአድናቂዎችህ አንዱ/ዷ

  ReplyDelete
 32. ዘቢለን ጊዮርጊስAugust 5, 2011 at 9:24 PM

  ትክክለኛውን ጽሁፍ በትክክለኛ ጊዜ

  ReplyDelete
 33. lol this is funny. awesome insight. Dani, you the man!

  ReplyDelete
 34. Wendata EKo NEH DANI,TEBAREK YEHAgere Lej.

  ReplyDelete
 35. ቆይ አንተ ችግሩ ብቻ ነው የተገለጠልህ፤ መፍትሔውን አልገለጠልህም፤ ማበድህ ካልቀረ ለምን ከነ መፍትሔው አታብድም ነበር

  ReplyDelete
 36. In my area, if the crazy person stayes as crasy for seven years, the peolpe considers his words as a prophecy. They consider him as an enlightend one. Because he is far away from sin or he doesn't do sin consciouslly. We, all are mad. When we see somebody works good we want to fight with him/her. When someone works great job, which is not our par we want to acuse him. That is our way for a long time and we don't bring any Change. Know it is a time to see ourselves, starting from our personal life, our family. our organization and then our country. We cann't bring change unless we change ourselves. The crazy guy says you cann't understand the things unless you are not one of a crazy one.
  For me, a crazy one is a person we thinks like you, which is different from your sect/group. Bebedoch mekakel ytegegn tenegha erasu ebde new.

  Keep your critical writing. God bless you.

  ReplyDelete
 37. Ejege betame ymigereme Tsehufe new lasetewalew.

  ReplyDelete
 38. The way you see things/ideas and trying to write such an article is cleverly done. I really admire the writing and critical thinking skill of Daniel's.

  It is a sarcastic way of insulting the current government and our church administrators. However, all those classifications, discussed above, between people are present everywhere in the planet of earth; in all countries. It is also a situation which was with us, the people in the world, since mankind was created, you know stories in the bible. In addition, it will not be avoided or eliminated in the future too; the gap might be narrowed though.

  You are trying to make a point that this kind of situations seem like our problem only, which I don't agree with.

  ReplyDelete
 39. It has nothing relevant dear.

  ReplyDelete
 40. Dear Dn Daniel Have hard time reading your blog. It was my breakfast lunch & dinner before.Please try to solve with them.Make your self hummble.

  ReplyDelete
 41. egnam sew men yelal belen new enji abdenal...or we are burning inside...tnx for telling our pain to us and to those who can read and understand

  ReplyDelete
 42. KEEP IT UP BROTHER!

  ReplyDelete
 43. የአንድ ዓይን ነገር ሆኖብን ነው እንጂ፤ መወቃቀሱ እኮ አዲስ ነገር አልነበረም።
  አየህ የኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን ሕይወት መርሮታል፤ ምድራዊው ኑሮ እንዴት እንደከፋበት ታውቃለህ፤ ነገሮች ይሻሻላሉ የሚል ተስፋ የለውም፤ ታዲይ መጽናኛውን ቤተክርስትያን አድርጎ ሲኖርም፤ የቤተክርስቲያን ነገር ዕለት ዕለት የእግር እሳት ሆኖበታል፤ በዚህ መሀል አንድ የቀሩት እሴቶቹ ማህበረ ቅዱሳን እና እንዳንተ ያሉ አገልጋይ ወንድሞች/እህቶች ብቻ ናቸው።
  እንግዲህ አንድ ዓይን ያለው ሰው፤ በዚያች ሲመጡበት እጅግ ይቆጣል፤ይረበሻል፤ ተስፋ ይቆርጣል። የአንተ ጽሑፍ መውጣቱን ተከትሎ የተከሰተውም የዚሁ አምሳያ እንጂ ጉዳዩ ያን ያህል ከብዶ አልነበረም። ሰው የተረበሽ ሕይወት ውስጥ እያለ፤ ጭራሽ አንድ ዓይኑን አንተን እና አንድ ዓይኑን ማኅበረቅዱሳንን በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሲያገኝ፤ከንግዲህስ ምን ቀረኝ እያለ የሚያደርገው ቢያጣ ይታዘንለታል እንጂ በእናንተ ጨክኗል አያስብልም፤ ሰው እጅግ አምርሮ ቢናገርም እጅግ ስለሚወድህ እንጂ፤ ቢጠላህ ኖሮ ትዝም አትለውም። እባካችሁ ተስፋችንን መልሱትና ፋሲካን እናድርግ።ዳኒ በናትህ ያለእናንተ የእኛ ህይወት እኮ ባዶ ነው። በዚህ ክፉ ዘመን መልካምን ነገር የምሰማው እኮ ከእናንተ ብቻ ስለሆነ ነው አሁን በተከሰተው ተስፋ የቆረጥነው።
  በርቱ ሰላሙን ሁሉ ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 44. ጥሩ እብድ ነው: እብድና ባለጊዚ ያሰበውን ይናገራል ይበሃል የለ:: አልታወቀንም እንጂ እኮ ሁላችንም በውስጣችን እየነደድን ነው:: ይችን ሃገር የሚታደጋትን የህዝቦችዋ አምላክ ይፍለግ እኛስ የባቢሎንን ሰዎች ሆነናል::

  ReplyDelete
 45. dani betam inwedihalen abetu amilakachin hoy wedimachinin tebikilin tibebuna mastewalun adililin telat yafir zend

  ReplyDelete
 46. I think it's already happening, the gap b/n Z rich n z poor is getting wider n wider every day, this is what WE ALL CAN observe but u expressed it in an interesting way. MAY GOD THE ALMIGHTY SAVE ETHIOPIA FROM SUCH A SYSTEM. ETHIOPIA EJOCHUAN WEDE EG/R TIZEREGALECH... AMEN!!!

  ReplyDelete
 47. እኔ በዚህ ሰዓት ዲያቆን ዳኒ ከማህበረ ቅዱሳን አመራር ጋር እርቅ ማውረዱን አንብቤ ለመግለፅ ከምችለው በላይ በሆነ ደስታ ውስጥ ሆኜ ነው ይህን ፅሁፍ ያነበብኩት:: ዳኒ ትልቅ ሰው ነህ ! ቃላቶች የሉኝም መቼም ቢሆን አንተን ከ MK ተነጥለህ ማየት አልመኝም ነበር ተነጋግራችሁ ችግራችሁን ስለፈታችሁ በጣም ደስ ብሎኛል እድሜህን ያርዝምልን!
  ይሔን መጣጥፍ ግን ከዚህ በፊት አንብቤዋለሁ ልበል አንተው ሳይት ላይ ? ግን እጅግ አሪፍ ስለሆነ በመደገሙ ደስ አለኝ ለዚህ ሰአትም ያስፈልጋልና እንኳን አስታወስከን! በርታልን እናከብርሃለን!!!
  አስካለ ማርያም ከቅዱስ ዮሴፍ

  ReplyDelete
 48. Insanity Vs Ignorance ? Part-1
  **************************************************************************************
  «አንተ ይህንን ትንቢት ከየት አመጣኸው» አሉት አንዲት እናት ገርሟቸው፡፡
  «በዕብድነቴ ነዋ እናቴ፤ አዩ እዚህ ሀገር ካላበዱ በቀር ብዙ ነገር አይገለጥልዎትም፡፡ እንዲገለጥልዎት ከፈለጉ እንደ እኔ ማበድ አለብዎ፡፡ ለነገሩ እዚህ ሀገር ዕብዱ ብዙ ነው ግን ዓይነቱ ልዩ ልዩ ነው» አላቸው፡፡ «ደግሞ የዕብድ ምን ዓይነት አለው፤ ሁሉም ያው ነው» አሉት እኒያው እናት የነጠላቸውን ጫፍ ወደ ትከሻቸው እየመለሱ፡፡
  «ተሳስተዋል፤ አዩ ይህም ቢሆን ካላበዱ በቀር አይታይዎትም፡፡ ብዙ ዓይነት ነው ዕብዱ፡፡ የመጀመርያው ያበደና ማበዱን እንደኔ የተረዳ ነው፡፡ ሁለተኛው አብዶ ማበዱን እያወቀ ግን ማመን የማይፈልግ ነው፣ እንደ ብዙዎቻችሁ፤ ሌላው አብዶ ግን ማበዱን ባለማወቁ የተምታታበት ነው፡፡»
  «ቆይ አንተ ችግሩ ብቻ ነው የተገለጠልህ፤ መፍትሔውን አልገለጠልህም፤ ማበድህ ካልቀረ ለምን ከነ መፍትሔው አታብድም ነበር» አሉት እኒያ አረጋዊ፡፡

  ይህ ፅኁፍ እኮ እጅግ ድንቅ የሆነ ፅኁፍ ነው፡፡
  ታላቁና ቅዱሱ ሀዋርያው ፓውሎስ እለት እለት የሚያሳስበው የአብያተ ቤተክርስትያናት ነገር እንደሆነና ስለዚህም ነገር አጥብቆ ሲያስብና ሲናገር እንደ እብድ ያናግረኛል ነበር ያለው፡፡
  በመሰረቱ እብደት ማለት እንፃራዊ ነገር ነው፡፡በአንድ ነገር ላይ ከሚፈለገውና ከተለመደው በላይ ስሜትን አእምሮን ሁለመናን ሙሉ በሙሉ ሰጥቶ በዚያ ነገር ላይ ከመጠን ያለፈ ትኩረት ከምጠትም ይመነጫል፡፡በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ሁሉ በውስጣችን ስላለው ነገርና ሀሳብ ፈፅሞ የማይረዱን ሲሆንና በሀሳብ መጣጣም ፈፅሞ ሲጠፋ እብደት ይከተላል፡፡አንድ ሰው ከህብረተሰቡ በአስተሳሰብና በአመለካከት እጅግ የላቀ ሲሆንና ይህም የአስተሳሰብና የአመለካከት ልዩነት እጀግ የጎላ ሲሆን ወደ እብደት ሊያመራ ይችላል፡፡የስነ ህዋ ተመራማሪ የነበረው ኮፐርኒከስ በጥንት ዘመን ብዙሀኑ ፀሀይ መሬትን እንደምትዞር በሚያስብበትና በሚያምንበት የተሳሳተ አመለካከት ውስጥ እሱ ተቃራኒውን መሬት ፀሀይን እንደመትዞር በመናገሩና በማስተማሩ እንደ ወፈፌ ወይንም አሳሳች ተቆጥሮ የሞት ፍረድ ተፈርዶበት ነበር፡፡ታላቁ የፊዞክስ ሊቅ ጋሊልዎም ተመሳሳይ ችግር ውስጥ ገብቶ እንደነበር ከታሪክ እንማራለን፡፡
  ጤነኛና እብድ በሚለው መካካል ያለው መሰረታዊ ልዩነት ጥቁርና ነጭ እንደምንለው ያለ ጥርት ያለ የመስመር ልዩን ያለው ነገር አይደለም፡፡እንዳንድ ጊዜ ጤነኞች ነን ብለን የምናስብ ሰዎች የጤነኝነታችን ዋናው ምንጭ ምንም ነገር ያለማወቃችን(Ignorance is a bliss እንደሚባለው ማለት ነው) ነገር ሊሆን ይችላል፡፡አንድ ሰው ስለምንም ነገር ካለወቀ ወይንም ለማወቅ ካልፈለገ ስለዚያ ነገር የሚያስጨንቀውና የሚያብሰለስለው ነገር የለም ማለት ነው፡፡ስለዚህም በስሜቱም ሆነ በአእምሮው ጤነኛ ነው ማለት ነው፡፡አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በዚህ የአለማወቅና ለማወቅም ያለመፈለግ የምቾት ፍራሽ ውስጥ የሞቀ ብርድ ልብስ ተከናንበው ድብን ያለ እንቅልፍ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ስለዚህም ሌሎች ከዚህ የሚመች እንቅልፍ ውስጥ እንዲነቁ የሚቀሰቅሳቸውን ነገር ሁሉ በጠላትነት ወይንም በእብድነት ሊፈርጁ ወይንም በዘመኑ ቋንቋ አካባጅ የሚል ታፔላ ሊለጥፉ ይፈልጋሉ፡፡
  በእርግጥ ጤነኝነት ዋነኛውና አንዱ በመጀመሪያ ከራስ ውስጣዊ ማንነት ጋር ተስማምቶ መኖር ነው፡፡ቀጥሎ ደግሞ ከራስ ውጪ ካለው ከባቢ ነገር ጋር ማለትም ህይወት ካለውም ሆነ ህይወት ከሌለው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ስራ ጋር ሁሉ ማለት ነው፡፡በእርግጥ ያለመስማማትም ጉዳይ ስለሚኖር የተቃርኖንና የልዩነትንም መኖር በራሱ እንደ እብደት ይቆጠራል ማለቴ አይደለም፡፡
  በእርግጥ የሰው ልጅ ከተፈጥሮና ከፈጣሪ ህግ ውጪ መሆን ሲጀምር ነው ያን ጊዜ ትልቁ ፀብና እብደት፡፡ይህ እስካልሆነ ድረስ በህብረተሰባችን ዘንድ ባለው አስተሳብና አመለካከት ከሄድን እብድ የሚባለው በትክክል ከተጠናና ከተመረመረ ጤነኛ ሊሆን ይችላል በተቃራኒው ጤነኛ የሚባለውም በትክክል ከተጠናና ከተመረመረ እብድ ሊሆን ይችላል፡፡ከላይ እንዳልኩት ብዙሀኑ ባለማወቅና ለማወቅም ፈፅሞ ባለመፈለግ የምቾት ፍራሽ ውስጥ የሞቀ ብርድ ልብስ ተከናንበው ድብን ያለ እንቅልፍ ውስጥ እየኖሩ ሳለ ከዚህ እንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸውንና የሚረብሻቸውን አንዳንድ ግለሰብ እብድ ብለው ሊጠሩት ይችላሉ፡፡ህዝብ እኮ ያብዳል፡፡አንዲያውም ህዝብ ሲያብድና ሲሳሳት እንዲህ በቀላሉ በቶሎ አይደለም ነገር ግን ካበደና ከተሳሳተ ደግሞም ከያዘው ጅኒና አባዘዜ መቼ እንዲ በቀላሉና በቶሎ ይላቀቃል መሰላችሁ፡፡
  To be continued .....

  ReplyDelete
 49. Insanity Vs Ignorance Part-2

  የፈጣሪን ፍቃድ ለፈጣሪ ትተነው በሰወኛ አስተሳሰብ ስናስብ ለምሳሌ አይሁድ በገዢው በጲላጦስ ከበርባንና ከእየሱስ ክርስቶስ የቱን በምህረት ልፍታላችሁ ተብለው ሲጠየቁ በምህረት እንዲፈታ የመረጡት ወንበዴውን በርባንን ነበር፡፡ከዚህ የበለጠ እብደት ታዲያ ወዴት አለን?
  የቁጥር ብዛት እኮ በራሱ የትክክለኛነት መመዘኛ ሊሆን አይችልም፡፡ህዝብ በቁጥር ስለበዛ ብቻ ትክክል ወይንም ጤነኛ ተብሎ ሊቆጠር ጥቂቶች ደግሞ በቁጥር ስላነሱ ብቻ እብድና ስህተተኛ ተብለው ሊቆጠሩ ወይንም ሊወገዙ አይገባም፡፡ከቅዱስ መፅሀፍ ታሪክ እንደምንማረው ጥቂት የሆኑ ነብያትና ሀዋርያቶች የመለኮታዊውን አለም እውቀትና ስራ በመንፈሳዊ እይታ ተመርተው ስላስተማሩና ስለገለፁ እብዶች ተብለው ጤናኛ ነን ብለው በሚያስቡ በብዙሀኖች ተሰውተው መስዋእት ሆነዋል፡፡
  ነገር ግን ጉዳዩ በተቃራኒው ሆኖ እብድ የተባሉት ጤነኛ ነበሩ ጤነኛ ነን የሚሉትም በተቃራኒው እብዶች ነበሩ፡፡የዚህ አለም ዋነኛ የግጭት መንስኤ የሀይማኖት ወይንም የአይዲኦሎጂ ወይንም የፖለቲካ ወይንም የዘርና የቋንቋ ልዩነት አይደለም፡፡ዋናው መንስኤ የአለመግባባት(understanding) ቀጥሎ ደግሞ ገደብ ከሌለው ስግብግብነት የመነጨ የራስ ወዳድነት (unbridled greed and Selfishness).Lack of understanding or Deep-rooted misunderstanding in a certain society is the very cause of insanity for human beings.
  ትልቁ ችግር ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን እብደት ለሚባለውም ነገር ሆነ እብዶች ለምንላቸው ያለን ግንዛቤና አመለካከት እጅጉን የተንሸዋረረና የተሳሳተ መሆኑ ነው፡፡ብዙዎቻችን ከእኛ አስተሳሰብ ፍላጎትና ስሜት ያፈነገጠ ነገርን ሁሉ የመጋፈጥ የመረዳትና ተቀብሎ የማስተናገድ ባህል የለንም፡፡
  የዘመኑ ብሄርተኝነትም ባብዛኛው ከመግባባትና ከመቀራረብ በመነጨ ባለ አካሄድ ያለ ሳይሆን ባብዛኛው እራሳችንን የምንደብቅበት የዳካማ ማንነታችን መሸሸጊያ ጭንብል ነው፡፡ሌሎችንም ባብዛኛው የምንደግፈውና የምናቀርበው ወይንም የምንወዳቸው ለስሜታችንና ለአስተሳሰባችን ስለተመቹን ብቻ እንጂ በእውነትና በምክንያታዊነት አስተሳሰብ ላይ ጭምርም ተመስርተን አይደለም፡፡ለምሳሌ ዳኒ ባለፈው ያቀርበከው በአንድ መ/ቤት ስላሉ ሁለት ሰራተኞች ምዘናና ሽልማት የሚያሳየው እንደ ህብረተሰብ የአስተሳሰብ ደረጃችን ምን ላይ እንዳለ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡
  በአለም ላይ አሁን የምናያቸውና እየተጠቀምናባቸው ያሉ ድንቅ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤቶች እኮ ጥቂት ግለሰቦች ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን መስዋእት እድረገው ከልክ በላይ አእምሯቸውን አስጨንቀውና ሌት ተቀን ፈግተው እንደመገኘታቸው መጠን በራሳቸው እኮ የእብደት ውጤቶች ናቸው፡
  ቶማስ ኤዲሰን እኮ ኤሌክትሪክን ሲፈጥር ላቦራቶሪው ውስጥ ከድካም ስሜት እዚያው ያንቀላፋ ነበር፡፡
  እስቲ ይታይህ ሩቅ ሳትሄድ ይህ የኢንተረኔት ቴክኖሎጂና አገልግሎት እኮ በራሱ የሚገርም የእብደት ውጤት ነው፡፡
  ሌላው ከልክ ያለፈ ስልጣንና ጥቅምም እኮ ወደ እብደት ውስጥ ይከታል፡፡ሰዎች ገደብ የሌው ስልጣንና ጥቅም ሲያሰክራቸውና ሲያደነዝዛቸው እንኳን ሌላውን ተራውን የሚያስተዳድሩትን ዜጋና ህብረተሰብ አይደለም ለቅርብ የእናታቸው ልጅ ለሆነው ለመንድማቸውና ለልጃቸውም ቢሆን ርህራሄ አይነኖራቸውም፡፡ማለትም “Absolute power corrupts absolutely.” እንደሚባለው ማለት ነው፡፡


  የእብዱን በፅኁፉ የተጠቀሰውን የህበረተሰባችንን አበዳደብ(የሚበላ የሚያስበላ …. ወዘተ) እንኳን መንስኤውን ምን እንደሆነ ማውራቱ በራሱ እኔንም ትንሽ ሊያሳብደኝ ይችላልና ለጊዜው የሚከተለውን ብዬ አጭሩ ልተወው፡፡
  እየሱስ ክርስቶስ ወደ እየሩሳሌም ሲቃረብ (እራሱን በቃል ኪዳኑ መሰረት በፈቃዱ መስዋእት ሊያደረግ ማለት ነው) ከአፋፍ ላይ ሆኖ አይቷት በማዘን አለቀሰላት ለራሷም እንዲህ ነበር ያላት፡፡
  “እየሩሳሌም ሆይ ምነው ለሰላምሽ የሚበጅሽን ዛሬ አውቀሽ የተረዳሽ ቢሆን ኖሮ፡፡ነገር ግን አሁን ይህ ነገር ከአይንሽ ተሰውሮብሻል፡፡ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሰርተው በየአቅጣጫውም ከበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፡፡አንቺንና በቅጥርሽም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ከአፈር ይደባልቃሉ፡፡ድንጋይም በድንጋይ ላይ አይተውም የመጎብኘትሽን ዘመን ከቶ አላወቅሽምና፡፡”
  አዎ በቅዱስ መጽኀፍ ህዘቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፋ እንዲሁም ደግሞ የማያስተውል ትውልድ ይገለበጣል አይደል የተበላው፡፡አዎ ዛሬ በግድየለሽነትና ባለማስተዋል ባለ የምቾት እንቅልፍ ውስጥ በሀይለኛው ተደብተን ያለነው ብዙሀኖች የህብረተሰብ ክፍሎች እራሳችንን ጤነኛ ነን ብለን አጉል ተኮፍሰን ነገር ግን ከዚህ ጥልቅ የሆነ የምቾት እንቅልፍ ውስጥ እንድንነቃ የሚቀሰቅሱንን አንዳንድ አንቂ ደውል የሚደውሉ አስተዋይ ግለሰቦችን እብድ የሚል ታፔላ እየለጠፍንላቸው ነው፡፡
  ግን በእውነት የእበደት አይነት ይለያይ ካለሆነ በስተቀር ብዙሀኑስ የራሱን አይነት እብደት በራሱ መንገድ ላለማበዱ ምን ማረጋገጫ አለን፡፡
  ለማንኛውም ፈጣሪ እራሳቸው እንደ ሻማ ቀልጠው ለሌላው ለብዙሀኑ ብርሀን የሚሆኑና ሌላውም የራሱን እብደት ወደ ውስጥ እንዲያይ የሚያደርጉ እንደዚህ አይነት አስተዋይ ነቢያት እብዶችን አያሳጣን፡፡
  ከሰላምታ ጋር፡፡

  ReplyDelete
 50. it is a wonderful message for those who found in 4 kilo minielik palace.

  ReplyDelete
 51. dani be Minilik becha ayedelem ... begnam gize eytekesete new ...

  ገብሽ መች ቀሰሰ ከየትስ አምጥቶ
  ይወጋናል እንጂ ካቡን ተጠግቶ

  ReplyDelete
 52. በመካከለኛው ምስራቅ በምድረ ፍልስጤም በምትገኝ በኢየሩሳሌም በ63 ዓ.ም እንዲህ ሆነ ኢያሱ የተባለ ሰው ተነስቶ ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! እያለ ይጮኽ ጀመረ፡፡ ሕዝቡ ግን ይህ ዕብድ ምን ይለፈልፋል እያለ ነገሩን ከቁብም አልቆጠረው፡፡ ኢያሱ ግን የታየው ታቶታልና 7 ዓመት ሙሉ ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! እያለ ጩኸቱን አጠንክሮ ቀጠለ፡፡ ልትጠፋ ያለች ከተማ ነጋሪት ቢጎስሙባትም አትሰማም እንዲሉ ሰሚ ጠፋ፡፡ እነሆ 70 ዓ.ም ገባ ጌታ በዕለተ ሆሳዕና ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ከተማይቱን አይቶ እጅግ አዘነ ብታውቂ ሰላምሽ ወደ አንቺ መጥቶ ነበር ሰላምሽን አላወቅሽም ብሎ ለከተማይቱ (በማኅደሩ አዳሪውን፤ በአዳሪው ማኅደሩን መጥራት የመጽሐፍ ልማድ ነውና ጌታ የሚመጣውን ጥፋት አስቦ ለሕዝቡ አዘነላቸው ሲል ነው) አለቀሰላት ዳግመኛም ያን ከባድ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ እየወደቀ እየተነሳ ሲወጣ የኢየሩሳሌም ሴቶች አለቀሱለት እናንት የኢየሩሳሌም ሴቶች ለእኔ አታልቅሱ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ ብሏቸዋል፡፡ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ሳይፈጸም አይቀርምና ጥጦስ በ70 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን እንዳልነበረች አድርጎ አጠፋት ይኸው በድጋሚ በ1948 ዓ.ም ዳግም እስራኤል እስክትቋቋም የአይሁድ ዘር እንደ ጨው በዓለም ተበትኖ ኖረ፡፡

  ዝም ብዬ ሳስበው አይሁድ ምነው ያ እንደ ዕብድ የቆጠርነው ኢየሱ እንዲያ ሲለፈልፍ በሰማነው ኖሮ! ማቅ ለብሰን አመድ ነስንሰን አምላካችንን በለመንነው ብለው ሳይጸጸቱ ይቀራል ብላችሁ ነው? መቼም እስራኤል ለመንፈሳዊው ነገር ልበ ደንዳኖች ናቸውና ይህን እንኳን ባይሆን ሁላችን በየራሳችን ኢየሩሳሌምን ነጻ ለማውጣት (በሮማውያን አገዛዝ ሥር ነበረችና) የምናደርገውን ጥረት አቀናጅተን ራሳችንን አደራጅተን ጠንካራ የጦር ኃይል አቋቁመን የጥጦስን ጥፋት በተከላከልን ነበር ሳይሉ ይቀራሉን?

  እኛስ እንዲህ ያለ ዕብድ ስንሰማ እንደ ባሮክና እንደ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን (ኢትዮጵያን፤ የቤተ ክርስቲያን) ጥፋት አታሳየን ብለን ሁሉን ወደ ሚችል አምላክ ልንጮኽ ይገባን ነበር፡፡ ሙሾ አወርድንላችሁ አላለቀሳችሁም፤ ሰፈንንላችሁ አልመለሳችሁም የተባለው ለኛ ሳይሆን ይቀራል ብላችሁ ነው?!

  ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!!!

  ከአዲስ አበባ
  በመካከለኛው ምስራቅ በምድረ ፍልስጤም በምትገኝ በኢየሩሳሌም በ63 ዓ.ም እንዲህ ሆነ ኢያሱ የተባለ ሰው ተነስቶ ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! እያለ ይጮኽ ጀመረ፡፡ ሕዝቡ ግን ይህ ዕብድ ምን ይለፈልፋል እያለ ነገሩን ከቁብም አልቆጠረው፡፡ ኢያሱ ግን የታየው ታቶታልና 7 ዓመት ሙሉ ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! ወዮ! ለኢየሩሳሌም! እያለ ጩኸቱን አጠንክሮ ቀጠለ፡፡ ልትጠፋ ያለች ከተማ ነጋሪት ቢጎስሙባትም አትሰማም እንዲሉ ሰሚ ጠፋ፡፡ እነሆ 70 ዓ.ም ገባ ጌታ በዕለተ ሆሳዕና ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ከተማይቱን አይቶ እጅግ አዘነ ብታውቂ ሰላምሽ ወደ አንቺ መጥቶ ነበር ሰላምሽን አላወቅሽም ብሎ ለከተማይቱ (በማኅደሩ አዳሪውን፤ በአዳሪው ማኅደሩን መጥራት የመጽሐፍ ልማድ ነውና ጌታ የሚመጣውን ጥፋት አስቦ ለሕዝቡ አዘነላቸው ሲል ነው) አለቀሰላት ዳግመኛም ያን ከባድ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ እየወደቀ እየተነሳ ሲወጣ የኢየሩሳሌም ሴቶች አለቀሱለት እናንት የኢየሩሳሌም ሴቶች ለእኔ አታልቅሱ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ ብሏቸዋል፡፡ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ሳይፈጸም አይቀርምና ጥጦስ በ70 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን እንዳልነበረች አድርጎ አጠፋት ይኸው በድጋሚ በ1948 ዓ.ም ዳግም እስራኤል እስክትቋቋም የአይሁድ ዘር እንደ ጨው በዓለም ተበትኖ ኖረ፡፡

  ዝም ብዬ ሳስበው አይሁድ ምነው ያ እንደ ዕብድ የቆጠርነው ኢየሱ እንዲያ ሲለፈልፍ በሰማነው ኖሮ! ማቅ ለብሰን አመድ ነስንሰን አምላካችንን በለመንነው ብለው ሳይጸጸቱ ይቀራል ብላችሁ ነው? መቼም እስራኤል ለመንፈሳዊው ነገር ልበ ደንዳኖች ናቸውና ይህን እንኳን ባይሆን ሁላችን በየራሳችን ኢየሩሳሌምን ነጻ ለማውጣት (በሮማውያን አገዛዝ ሥር ነበረችና) የምናደርገውን ጥረት አቀናጅተን ራሳችንን አደራጅተን ጠንካራ የጦር ኃይል አቋቁመን የጥጦስን ጥፋት በተከላከልን ነበር ሳይሉ ይቀራሉን?

  እኛስ እንዲህ ያለ ዕብድ ስንሰማ እንደ ባሮክና እንደ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን (ኢትዮጵያን፤ የቤተ ክርስቲያን) ጥፋት አታሳየን ብለን ሁሉን ወደ ሚችል አምላክ ልንጮኽ ይገባን ነበር፡፡ ሙሾ አወርድንላችሁ አላለቀሳችሁም፤ ሰፈንንላችሁ አልመለሳችሁም የተባለው ለኛ ሳይሆን ይቀራል ብላችሁ ነው?!

  ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!!!

  ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 53. ደቂቀ ጸሃፍት ዘሳንሆዜAugust 10, 2011 at 8:50 PM

  ጤና ይስጥልኝ ዲ/ን ዳንኤል ከዚህ ጽሁፍ በፊት ስለ እብዱ ትንቢት የጻፍከውን አንብቤ እኔም በእብደት የጻፍኩልህ አስተያየት ነበር። ዛሬ ደግሞ በነቃ ህሊና ይህን ጻፍኩ። ለማንኛውም ህሊና በትምህርት፤ ጥበብና የመሳሰሉት ብቻ አይደለም የሚነቃው።ህሊና በፈጣሪ መፈጠርን ብቻ ሳይሆን መመራትንም ትፈልጋለች። የህሊና ፈጣሪዋ እግዚአብሄር ነውና በፈጠራት አምላክ መንፈስ የምትመራ ህሊና አትደነብርም። በችግርም ጊዜ በራሷ ዘዴ ከመፍታት ይልቅ መጸለይና የመንፈስ ቅዱስን መሪነት መጠበቅን ትመርጣለች። የእግዚአብሄር መንፈስ ምሪት ዋስትና አለው። የ አባቶቻችን ህሊና ከእኛ የሚለየው በዚህ ነው። እነርሱ በጸሎታቸው በዘንዶ መሰላልነት ተራራ ሲወጡ በ እሳት ሰረገላ ሲያርጉ አይተናል። ሀይማኖት ለሌለው ህሊና ይህ ተረት እየመሰለው በመንኮራኩርና አውሮፕላን በረራ ግን ሲደነቅ ይስተዋላል። ህሊናችን ስርአተ አእምሮ/አንጎል/ ብቻ አይደለም መንፈስም ነው። አለበለዚያማ ሲፈርስ ሁሉ ይፈርሳል። የክርስትያን ህሊና ግን ፈርሶ የሚቀር ሳይሆን ዘላለማዊ ነውና እባካችሁ ህሊናችን ከእግዚአብሄር ጋር ይሁን። ስጋዊ ህሊና በሌላ ፕላኔት መኖር ሲናፍቅ መንፈሳዊ ህሊና ግን መንግስተ ሰማያትን ይናፍቃል።

  ReplyDelete
 54. kene mefithew biyabid zemenunin yewaje ebid. . . yewaje ebid. . .

  ReplyDelete
 55. Geberemeskel-ke-BahidarAugust 11, 2011 at 1:14 PM

  hi dani betam des yemelina astemari tsihuf new kezih befit gin bemahiberu yeneberwin chigir bewuyiyit bemefitatachihu betam tedesiten dejeselam lay endanebebin keguadegnayegar tekakifen alekisenal fetari betekiristiyanachinina hagerachinin yitebikilin amen

  ReplyDelete
 56. i was excpecting u to preach about God but u playin politics game am sory this not expected from u coz there are a lot of resposible body for that u should talk about bible unless u also one of the crazy u wrote here

  ReplyDelete
 57. ማሞ ሌላ መታወቂያ ሌላ አሉ ይቅርታ የማያውቅ ክርሲቲያን ምንፈለጋችሁ ንሰሐ ግቡ ያስፈልጋችኋል አትደባልቁ ምን አገናኘው አሁን እናንተም አብዳችኋል ማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
 58. It is nice to see your trial but i wonder that you lost your track to identify why we become such kind of people? Identifying problem is easy, may be everybody knows it and what makes you different is you can present it in a nice way, but finding the real cause and predicting what will happen in future based on scientific analysis is difficult and that is what i expect from you. Please keep moving, i just wrote the above to encourage you to hit the point rather than rounding about.

  ReplyDelete
 59. It is a great lesson for all of us see who we are and who will be from now on. I personaly appreciated ur viewse who we are and who will be from now on. I personaly appreciated ur views

  ReplyDelete
 60. በጣም ደስ ብሎኛል እድሜህን ያርዝምልን
  Aynalem

  ReplyDelete
 61. the guy categorize it well .out of which the "yemiyablala" type is the chronic problem to the society. there unique identity is playing with false numeric game , false statistic , and they can say a lot but literally nothing valuable came out of there mind at the end endihu endablalu tebeltew yalkalu .erasen endemehone men teru neger ale !.

  ReplyDelete
 62. this is the graet history that i saw he was not amaddd he is mor than heman being ...................ayalkebet foloe me on my fac book

  ReplyDelete
 63. D.Dani betam enmesgnalen yebdu ababal gen btegbar eyayenew slhone bergete slot yasfelgnal God yerdan ande yadergen.

  ReplyDelete
 64. Dani tebark God Ethiopian Yetebk Amen!

  ReplyDelete
 65. Dani God yebarkhi Ethiopian ytebekat Amen! yebdu ababel betgbar eyayenew newe

  ReplyDelete
 66. ግሩም በጣም ግሩም… ግን ምን ያደርጋል፤ ስንቱ ሀገር ቤት ያለው ወገናችን ነው ይኼን ለማንበብ የሚችለው?

  ReplyDelete
 67. Wow, Wonderful insight from the so called 'mad' or 'insane' individual. I think this man is not mad but he has a wonderful insight to observe and understand the ongoing severe problem of the society. Bless u!

  ReplyDelete
 68. Wow, it is shown as a wonderful insight from the so called 'mad' or 'insane' individual. I think this man is not mad but he has a wonderful insight to observe and understand the ongoing severe problem of the society. It is definitely true and exactly practicable but not simply a futuristic prophecy. "Ebidina sekaram ye libun yinageral' ayidel ..ayidel yemibalew!

  ReplyDelete
 69. ዳኒ በጣም የሚገርመው ይሄ ነገር ልብ ላለው አሪፍ መልእክት ነው ለገዢውም ለተገዢውም ለእምነት አባቶችም …..

  ReplyDelete
 70. XGዚxBሔር የአገልግሎት ዕድሜህን ያርዝምልህ::
  አሜን!
  ሃብተጊዮርጊስ (ከመቀሌ)

  ReplyDelete
 71. Wow Dani, i really love it the way u write. God Bless Ethiopia!

  ReplyDelete
 72. when I always read ur books"tomars".I am hop full by God b/c he always give us great fothers,brothers---like u!!!
  Egziabehere tsegawun yabizalih

  ReplyDelete
 73. * የወደፊት ሕይወትህን እንዴት ልትመራው እንዳሰብህ የምታውቀው አንተው ራስህ ብትሆንም ፡ ከድርጅቱ ጋር ያለህን ቅራኔ ካልፈታህ : ወይም ራስህን ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ካላገለልህ በቀር ፤ ትንሽ የሚከብድብህ ይመስላል ።* በማለት የጻፍከው ግለሰብ ሆይ ማንነትህ ስለተነቃብህ ሰይጣን ሆይ ከኛ ዘንድ ዞር በል ብለንኃል፡፡

  ReplyDelete