የዓለም የጦማሪዎች ቀን
ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓም [August 31, 2011]
አትላንታ የሰማሁትን አስገራሚ ነገር ልንገራችሁ፡፡ አንድ ሰው ሜዳ ላይ ሥጋ ለመጥበስ የሚያገለግለውን ዕቃ (ባርቢኪው ይሉታል) ውጭ ያሳድረዋል፡፡ ይህንን ሰሞን በፈረንጆቹ ዘንድ የሙቀት ወቅት ነውና የቻለ በራሱ ዕቃ ያልቻለ ለአካባቢው ነዋሪ በተዘጋጀው መጥበሻ ሜዳ ላይ ሥጋ የማይጠብስ የለም፡፡ ይህ ታሪኩን የምንናገርለትም ሰው ቤቱ ፊት ለፊት ያለው መስክ ላይ ሥጋ ሲጠብስ አምሽቶ ትቶት ገባ፡፡ በማግሥቱ መጥበሻው በቦታው አልነበረም፡፡ አካባቢው ደኅና ሠፈር የሚባል ነበርና የመጥበሻው መጥፋት ሰውዬውን አስገረመው፡፡ ቀናት አልፈው ሳምንት ሆነው፡፡ መጥበሻው እንደጠፋ ቀረ፡፡