ብጹእ አቡነ ዘካርያስ በማኅበረ በዓለ ወልድ ሰባተኛ ዓመታዊ ጉባኤ ቺካጎ ላይ ተገኝተው እንዲህ አሉ፡፡
ወደ መዓርገ ጵጵስና ከመምጣቴ በፊት የሐዲሳት ትርጓሜ አስተምር ነበር፡፡ አንድ ቀን የዮሐንስ ራእይን ምእራፍ 19 ሳስተምር «በጉ እና የበጉ ሚስት» የሚለው ላይ ደረስን፡፡ የበጉ ሚስት ያልነው «መርዓተ በግዑ» የሚለውን ነው፡፡ ይህንን ለተማሪዎቹ አስተምሬያቸው ሊቀጽሉ ወደ ጫካ ገቡ፡፡ በጫካው አጠገብ መንገድ አለ፡፡ በመንገዱ አንድ ገበሬ ከሚስቱ ጋር ይሄዳሉ፡፡ የገበሬው ሚስት ቀደም ብላ ባሏም ተከትሏል፡፡
የሚቀጽሉት ተማሪዎች «በጉ እና የበጉ ሚስት» ሲሉ ሴትዮዋ ሰማችና ወደ ተማሪዎቹ ተጠጋች፡፡ «እናንተ ማንን ነው የበጉ ሚስት የምትሉት? እኔ ነኝ የበጉ ሚስት» ብላ ትውረገረጋለች፡፡ ይሄኔ ባልዋ ይደርሳል፡፡ «ምንድን ነው?» ብሎ ሲጠይቃት «የበጉ ሚስት እያሉ ይስቁብኛል» ትለዋለች፡፡ እርሱም ይባስ ብሎ «እናንተ ማንን ነው በግ የምትሉት» አለና በያዘው ሽመል ያንቆራጠጣቸው ጀመር፡፡
ልጆቹ ዱላው ሲብስባቸው «መምህራችን አስተምረውን ነው» ይሉታል፡፡ እንደ ተናደደ ሽመሉን ይዞ «እኔን በግ እያሉ የሚያስተምሯችሁ የትኛው መምህር ናቸው» እያለ መጣ፡፡ እኔም ሌላ ነገር ሳይከተል ብዬ ሸሸሁ፡፡ በኋላ የአካባቢው ሽማግሌዎች መጥተው ገላገሉን፡፡ መጽሐፍ ስመለከት ከዚህ ላይ ከደርስኩ አስታውሰዋለሁ፡፡
ችካጎ
I wish i was there, he is such a great father. He tells it like it is.
ReplyDeleteAbatachinin Yitebiklin
Girum Timihirt,
ReplyDeleteGin Esachew Begu Yalut Esu Alemehonun lemin Alasredutim kemeshesh...
Anything need clarity for any one to be understood and for any oen to understand well. Otherwise, it will be abstract picture yemilut ayinetina hulum beyersau siteregumew yinoral...
selam D/ Dan
ReplyDeleteልጆቹ ዱላው ሲብስባቸው «መምህራችን አስተምረውን ነው» ይሉታል፡፡ እንደ ተናደደ ሽመሉን ይዞ «እኔን በግ እያሉ የሚያስተምሯችሁ የትኛው መምህር ናቸው» እያለ መጣ፡፡ እኔም ሌላ ነገር ሳይከተል ብዬ ሸሸሁ፡፡ tadelewal yane maseterk yemechl shemagele neber
በኋላ የአካባቢው ሽማግሌዎች መጥተው ገላገሉን፡፡
tazabew Ke Atlanta
From this I understand that:
ReplyDeleteDon't denounce what you hear from others. Understand what is said. Just very expressive experience.
ዳኒ በጣም ደስስስስስ ይላል፡፡ በርታ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡
ReplyDeleteEWNETUN SISEMU BALNA MISTU YE TSESET DULA ANAT ANATACHEWN ENDEMILACHEW ATTERATERU.
ReplyDeleteየአባታችን ትምህርት በወቅቱ/ለእናንት/ ምሳሌ ነበረው አሁን ግን ምን ለማለት ነው? ሳይገባቸው ትምህርቱን ባልሆነ አስተምህሮ የሚረዱት እነማን ናቸው ማለት ነው? ቢብራራ ጥሩ ነው ለእኔ ቅኔ ሆኖብኛል ::
ReplyDeleteደስ የሚል አባባል አባታችንን ይጠብቅልን አሜን
ReplyDeleteከላይ ''ምስጢር ሆንብኛል----ይብራራ'' ያለው ወንድሜ በጥላቻ አና በተንኮል የተሞላ ቃላትህ ከ አፍህ ሲፈጽ አየዋለሁ። አሁን ዳንኤልን ምን አለ ልትል ፈልገህ ነው? ''ጉድጉአድ ስትቆፍር አርቀህ አትኮፍረው ማን አንደምገባበት አይታወቅም አና'' የሚለው አባባል ገና አልደረሰህም ይሆን? ምሳሌው ነገር በደንብ ሳይረዱ ወይንም ስለምን አንደተናገሩ ሳያረጋግጡ ወደ ውሳኔ ለሚደርሱ ሁሉ የተመሰለ ነው። ደግሞስ ምሳሌውን ያስተማሩ አባታችን ዳንኤል አኮ ራድዮ ነው አዚህ ጋር። አንተ ፀብህ ከ ራድዮኑ ነው ወይስ ራድዮኑ ውስጥ ከተናገሩት አባት ነው? አስኪ ለ አኔ ደሞ ይህን መልስልኝ።
ReplyDeleteጌታቸው
A big message 2 me!A big message 2 me!
ReplyDeleteእግዚአብሄር ይቅር ይበለን ያልገባኝን መጠየቄ እንደነውር ከተቆጠረብኝ እጄን እሰበስባለሁ ወንድሜን ከማሰናክል እኔው ህጢያቴን ይዤ ወደ ጥልቁ ልውረድ::
ReplyDeletePlease Ato Getachew, He just asked a question. He hasn't understood the concept behind the story. This is not a crime.
ReplyDeleteWud Getachew... Ebakih Sidbih wedegon tewow. Daniel eko minm sayil awutitotal... Every one has right what to say and Dn. has right to allow the comment visible. Ante gin gudguwad... minamin tilaleh..
ReplyDeleteLe wondime Getachew
ReplyDeleteአሁን ዳንኤልን ምን አለ ልትል ፈልገህ ነው? new yalekew? ante
endasebekew belehese?
Ebakeh Besew lay atemeka esum bezih yemiyamen meselegn! alamawum ayedelem! bemitsefew tumera legna betayen melku tergumen yemitekemenen becha weseden lelawun lerasu....... Wendeme Getachew negeren tolo alemeredate eko antsarawi new!
ዲ/ን ዳንኤል፡- ሚስጢሩ ጠለቅ ያለ ነውና ማብራርያ የሚያስፈልገው ነው፡፡ የሚቀጽሉት ተማሪዎች «በጉ እና የበጉ ሚስት» ሲሉ ሴትዮዋ ሰማችና ወደ ተማሪዎቹ ተጠጋች፡፡ «እናንተ ማንን ነው የበጉ ሚስት የምትሉት? እኔ ነኝ የበጉ ሚስት» ብላ ትውረገረጋለች፡፡ ይሄኔ ባልዋ ይደርሳል፡፡ «ምንድን ነው?» ብሎ ሲጠይቃት «የበጉ ሚስት እያሉ ይስቁብኛል» ትለዋለች፡፡ እርሱም ይባስ ብሎ «እናንተ ማንን ነው በግ የምትሉት» አለና በያዘው ሽመል ያንቆራጠጣቸው ጀመር፡፡
ReplyDeleteመምህር፣ በጉ፣ የበጉ ሚሰት፣ ተማሪዎች፣ ገበሬና ሚስቱ….
ይቅርታ! ቸኩዬ በቅን አለማየቴ ነው።ይቅርታ ወንድሜ ሁላችሁም ይቅርታ። አንዳንዴ ቅን ልቦና ማጣት አኔስ ውስጥ ይጠፋል ብላችሁ ነው?
ReplyDeleteGetachew
ዳኒ ይህን ለመረዳት ሌላ ጽሁፍ ያስፈልገኛል በአጭሩ አልተረዳሁትም ?
ReplyDeleteየገደለው ባልሽ
ReplyDeleteየሞተው ወንድምሽ
ሐዘንሽ ቅጥ አጣ
ከቤትሽ አልወጣ!!
Each of us need a revolution on ourselves -
ReplyDelete1. Lets read what we wrote
2. Lets listen what we spoke
3. Lets live a life like we are preaching
4. LETS NOT FORGET, that WE ARE NOT INFALLIBLE
The Lord,God of Abraham, be with us all.
Dani. I hope I understood what you want to say in this message. There are some people, who understands scriptures very literaly and creates problems on the intellectualls. Instead of asking more clarification they want to use there power like Peter. Dani, we are not the disciples to understand the allegorical expressions. So, when you write such kinds of exampleries, we need your detail translations.
ReplyDeleteEmen enji atefera..Bezuwoch bezuriah aluna.
Amelake kedusan segawen yabezaleh
what is wrong with people every body seems angery and frustrated,due we lost our hope,please God is with us we can pass every chalanges and the better days will come let us be strong and united
ReplyDeleteመቼም ስለ በጉ ሲነሳ አለመስማማት መነሳቱ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ዳኒም ሊደንቅህ አይገባም፡፡ነገር ግን ይህንን አለመግባባት ያመጣው ለእውነት ላለመሸነፍ የጨከነ ልብ ከያዙ ሰዎች በሚመነጩ አሳቦች የተነሳ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ይህ በሰንበት ት/ቤት ሳለን ከሰማናቸውና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መሰረታዊ ትምህርቶች መካከል አንዱ ነው (በጉ፡- ክርስቶስ፣ሚስት ወይም ሙሽራይቱ፡ - ቤ/ክ)፡፡ ስለዚህ አለማወቅ ኃጢአት ባይሆንም ለማወቅ ፈቃደኝነት አለማሳየት ግን በደል ነውና ክርክሩን ትተን ወደ በጉ እንመለስ፡፡ ዳኒ ስለ በጉ እና ሚስቱ ሰፋ ባለ መልኩ ብትነግረን መልካም ነው እላለሁ፡፡
ReplyDeleteቂቂቂ ... የአቦየን ........ የበላ ለፍልፍ ለፍልፍ ይለዋል አሉ !!!!! ትገርማላችሁ፡፡ አሁን እዚህ ምን ነገር አለ እና ነው “ጃኬቴን አቀብሉኝ ነገር ፍለጋ ልሄድ ነው፡፡” ብላችሁ እዚህ ብሎግ ላይ ዘው ያላችሁ ? ኧረ እባካችሁ ለቁምነገር ብቻ ግቡ፡፡
ReplyDeleteYou are a great person Getachew... Endih Yemil tefana eko new hulachinm yeminchachaw...
ReplyDeleteዲያቆን ዳኒኤል በመምህሩ እና በተማሪዎች ላይ የድደረሰው አጋጣሚ እጅግ በጣም ይገርማል።ዳኒ አንተ ለብዙዎቻችን መልካም መምህራችን ነህና ከልብ እንወድሃለን።
ReplyDeleteሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የተባለው ነገር በአንተ ላይ ደርሷል።የማህበሩን አመራር አካል አንተ እንዳልከው በስውር የሚመራ አካል ካለ በጣም ያሳዝናል።
The most interesting collective comments. You should do this more often.
ReplyDeleteስለበጉ እራሱን የቻለ ትምህርት ነው። ትልቁ ነገር አትቸኩል የሚለውን መልክት ነው የሚያስተላልፈው። አቶ ጌታቸው ቆጣ ቢሉም ጠበቃ እየቆሙ ነበር እኮ። እንደሴትየዋ እንዳይሆን እላለኹ እንጂ። "ንባብ ይገላል ትርጓሜ ያድናል" ይላሉ እንዲህ ነው።
ፈጣሪ አምላክ በየዘመኑ በየምክንያቱ ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑትን ሁሉ ይናገራል እና ልባችንን እልከኛ ሳናደርግ ስለእውነት ብቻ በመቆም ከሆኑ ካለፉ ነገሮች ትምህርት ትምህርቱን እየወሰድን የበለጠ ጠቃሚዎች ለመሆን ያብቃን። ውድ ወንድማችን ዲ.ዳንኤል ክብረት ከሁልጊዜ አድናቂዎችህ አንዱ ነኝ በዚህ ዘመን ለአገልግሎት ከተጠሩት አገልጋይ አባቶች ወንድም እህቶች ጋር በምታገለግሉት አገልግሎትና ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅ በምታደርጉት ትጋት በእግዚአብሔር ፈቃድና ቸርነት ይሄንን የፈተና ዘመን እያለፍን ነውና ፀጋውን እግዚአብሔር ያብዛልህ በርታ ወንድሜ። በርታ ግለጥ። "ከበቀሉ ማደግ ነው"
ReplyDelete‹‹ከበቀሉ ማደግ ነው›› አስተዳደጉ ግን ይለያያል!!!
ReplyDeleteዳንኤል ሆይ የአቡኑን የሕይወት ተሞክሮ በማቅረብህ ምስጋናዬን ከወዲሁ እያስተላለፍሁ አቡኑም በአገልግሎት ሕይወታቸው የገጠማቸውን ተግዳሮት በግልፅ በመናገቸው ሊደነቁ ይገባል እላለሁ፡፡ እንዲሁም የአቡኑ ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት እየተወያዩ መሄዳቸው ልብ ሊባል የሚገባ ዓብይ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ ከቤተክርስቲያን ስንወጣ የሰማነውን እዚየው ደጀ ሰላም ጥለን ስለሰውና ሰለሌሎች ጉዳዮች እያወራንና እያማን መሄዱ ልማድ ሆኗል ይመስለኛል፡፡ የሚመለከተን ከሆነ እንታረም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡኑንና ተማሪዎቻቸውን ያገኛቸውን የዱላ ገጠመኝ እንመልከት፡፡ ከሁሉ በፊት እኛ እንደ ምዕመናን እንዲህ አይነቱ ተግዳሮት ቢገጥመን ምን እናደርግ ነበር የሚለውን ማሰብ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ በእርግጥ ከላይ አንዱ አስተያየት ሰጭ እንደፃፉት ‹‹መምህሩ ናቸው ያስተማሩን›› ብሎ ለጊዜው ነገሩን ከራሳችን ማሳለፍ ወይ እንደ አቡኑ ‹‹ ጥሎ መሸሽ›› ምን ያህል አግባብ ነው? ዱላ ብቻ ሳይሆን እስራትና ሞት እንኳን ሳይፈሩ የወንጌሉን እውነት በተቃዋሚዎቻቸው ፊት በድፍረት ካበሰሩት ሐዋሪያትና የእምነት አባቶች ይህንን እንማራለንን፤ ክርስትና በብዙ መስዋዕትነትና ተጋድሎ እኛ ዘንድ ከደረሰ እኛስ ለዚህ ክቡር እምነት ዋጋ ለመክፈል ምን ያህል ዝግጁ ነን ? እናስብበት:: ‹‹በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ›› (2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡12) ይላልና ቅዱስ ቃሉ፡፡
ReplyDeleteሌላው የገረመኝ አቡኑንና ተማሪዎቻቸውን ከተቆጡት ባልና ሚስት ጋር ያስታረቁት የሠፈር ሽማግሌዎች ሊመሰገኑ ይገባል፤ ድሮ ድሮ አስታራቂ ሽማግሌ ቄሱ አቡኑ ነበሩ አሁን አሁን ከሕብረተሰቡ የተገኙ ሽማግሌዎች ሆነዋል ማለት ነው ! ይበል፤ ይደግ የሚያሰኝ ነው፤ ዳሩ ግን ቄሶቹ የማስታረቁ ሥራ በዋናነት የተሰጣቸው መሆኑን ተገንዝበው ወደ ኃላፊነታቸው ይመለሱ ባይ ነኝ በበኩሌ፡፡ በመጨረሻ አቡኑና ተማሪዎቻቸው የተፈተኑበትን የአዲስ ኪዳን ክፍል እንድጠቅስ ይፈቀድልኝ፡-
‹‹ ሃሌሉያ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነገሦአልና፡፡ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ›› (የዮሐንስ ራዕይ 19፡6-7)
ከላይ አንዱ አስተያየት ሰጭ በትክክል እንደአስገነዘበው በጉ ለዓለሙ ሁሉ ነፍሱን ቤዛ ያደረገው መድኃኒ ዓለም (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) ሲሆን በሚስት (ሙሽራ) የተመሰለችውም ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ቅዱሱ ቃሉ እንደሚለውም ቤተክርስቲያን ማለትም ሕንፃውና ነዋየ ቅዱሳቱ ሳይሆኑ እኛ በመልኩና ባምሳሉ የተፈጠርን በደሙም የተዋጀን የእግዚአብሔር ልጆች ሕብረት፤ አንድነት ነው፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ዛሬ እንደሚስት እንደሙሽራ ለተመሰልን ለእኛ ይህ ነው፡- ተዘጋጅተናል ወይ ? ከላይ ቃሉ እንደሚለው ሰርጉ ደርሷል፤ ለሠርጉ እንደታዳሚ ብቻ ሳይሆን እንደሙሽራ ተዘጋጅተናል (በቅድስና፤ እግዚአብሔርን በመምሰል፤ በፅድቅ ኑሮ፤ በፍቅር . . .) ?
ቸሩ አምላካችን ረድኤቱን ያብዛልን፡፡ በቸር እንሰንብት፡፡
ከሰላምታ ጋር
ልሳነ ጥዑም ዘእንጦጦ