Saturday, July 30, 2011

ፖሊስ ሆኖ ቀረ


አንዲት እናት ቤት ሄጄ ነበር ይህንን የሰማሁት፡፡ ልጆቻቸውን አስተምረው ለወግ ለመዓርግ ያደረሱ እናት ናቸው፡፡ እነዚህን ልጆች እዚህ ቦታ ለማድረስ እርሳቸው ከቅጠል ሻጭነት እስከ አስመጭ እና ላኪነት ተጉዘዋል፡፡
ቤታቸው ተጋብዘን ሄድንና ልጆቻቸውን ያስተዋውቁን ጀመር፡፡ «ይሄ ሐኪም ሆኗል፡፡ ይሄም መምህር ነው፡፡ ይህችም ነርስ ናት፡፡ ይህችኛዋ ደግሞ አካውናታንት ሆናለች፡፡ ያቺ ደግሞ ጋዜጠኛ ናት፡፡ እርሱ እሳት የላሰ ነጋዴ ሆኗል» አሉና አበቁ፡፡ እሴይ ሳሙኤል በጠየቀው ጊዜ ዳዊትን እንደዘነጋው ሁሉ አንደኛውን ልጃቸውን ዘነጉት፡፡ ደግነቱ እርሱም እንደ ዳዊት ቤት ውስጥ አልነበረም፡፡
ከመካከላችን አንዱ በቀልድ መልክ አደረገና «ምነው እንትናን ዘነጉት» አላቸው፡፡ እርሱማ ፖሊስ ሆኖ ቀረ ሲሉ ክው አልኩ፡፡ ብቻዬን በሆዴ «ፖሊስ ሆኖ ቀረ፣ ፖሊስ ሆኖ ቀረ» እል ጀመር፡፡ ማሞ ውድነህ የተረጎሙት «ካርቱም ሄዶ ቀረ» የሚለው መጽሐፍ ትዝ አለኝ፡፡
ፖሊስነት ምንድን ነው? አልኩኝ ለራሴ፡፡ የሚኮንበት ነው ወይስ የሚቀርበት፡፡ እኒህ እናትስ ለምንድን ነው ፖሊስ ሆኖ ቀረ ያሉት፡፡ በዚያ የዓመት በዓል ቀን ፖሊሱ ልጃቸው የለም፡፡ የሌለው በዓል ማክበር ጠልቶ አይደለም፡፡ ነገር ግን እርሱ ቤት ውስጥ ካለ እነርሱ በዓል ማክበር ስለማይችሉ ነው፡፡ እርሱ ከተማዋን እየዞረ ጸጥታ እየስከበረ ነው፡፡
እርሱ ፖሊስ ባይሆን ኖሮ እነርሱ የከተማ ነዋሪ ይሆኑ ነበር? ብዬም አሰብኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነው፤ እርሷ ነርስ ናት፣ እርሷም አካውነታንት ናት፤ እርሱም ጋዜጠኛ ነው፡፡ እርሱም ነጋዴ ነው፡፡ ለምን? እርሱ ፖሊስ ስለሆነ ነዋ፡፡
አንድ ጊዜ ሰውዬው ለመታወቂያ ፎቶ ሊነሣ ሲሄድ ማጅራቱ እየዞረ አስቸገረው ይባላል፡፡ ፎቶ ግራፍ አንሺው ዙር ይላል፡፡ ማጅራት ይመልሳል፡፡ አንሺው ያዞራል፤ ማጅራት ይመልሳል፡፡ በመጨረሻ ፊቱ ማጅራቱን ተናገረው አሉ፡፡ «ለምን ፎቶዬን ታበላሻለህ አለው፡፡
«አንተ ብቻ ለምን ፎቶ ላይ ትወጣለህ ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
«ፎቶ ከፊት እንጅ ድሮስ ከኋላ ይነሣል ወይ ሌላ ጥያቄ ከፊት በኩል መጣ፡፡
«እርሱ ስሕተት ነው፡፡ ከፊት ብቻ ለምን እኛ የኋላ ደጀኖቹ ከሌለን ፊት ብቻውን ምንድን ነው? ለምንድን ነው የውበት ውድድር ሲደረግ ከፊት ብቻ የሚታየው? የኋላውስ ማጅራቱስ፣ አከርካሪውስ፣ ሕብለ ሠረሠሩስ? ለመሆኑ እነዚህ ከሌሉ ፊት ብቻውን ይኖር ዘንድ ይችላልን» ማጅራት ጠየቀው፡፡
እስኪ ዘፋኙን ስማ ዓይንሽ፣ ጥርስሽ፣ ከንፈርሽ፣ ፀጉርሽ፣ ጉንጭሽ እንጂ ማጅራትሽ፣ አከርካሪሽ፣ የጀርባ አጥነትሽ እያለ ሲዘፍን ሰምተህ ታውቃለህ? ለመሆኑ የጀርባ አጥንትን የሳለ ሰዓሊ አለ? በየቤቱ የተሰቀለው ፎቶ የእናንተ ብቻ ነውኮ፤ እናንተ እንድትዋቡ ያደረግነው እኛ ነን፡፡ ግን ተረሳንና መመስገን፣ መከበር ሲገባን «ማጅራታም» እየተባለ መሰደቢያ ሆንን፡፡ ለዚህ ነው እኔም ፎቶ መነሣት አለብኝ ያልኩህ» አለው ይባላል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ እንድንኖር የሚሞቱ፣ እንድናርፍ የሚደክሙ፣ እንድንቀመጥ የሚቆሙ፣ ሰላም እንድናገኝ ሲሉ ሰላም የሚያጡ፣ እንድንተኛ የሚነቁ፣ ባለሞያዎች ሞልተዋል፡፡ ጠረፍ ላይ ወታደር ባይኖር መውሊድ እና ፋሲካን እንደ ባህላችን መች እናከብራቸው ነበር፡፡ በየጣቢያው ያሉ የመብራት ኃይል ባለሞያዎች ዓመት በዓሉን ትተው እዚያው ባይውሉ ፋሲካ ፋሲካ መሆኑ ቀርቶ መከራ ይሆን አልነበረም? ተረኛ ሐኪሚች በየሆስፒታሉ ቤታቸውን ትተው ባይውሉ ኖሮ የዓመት በዓል አደጋ የለቅሶ በዓል ያስመስልብን አልነበረም?
እነዚያ በአየር ላይ ናቸው፤ እነዚህ መርከብ ላይ ይጓዛሉ፡፡ እነርሱ የከተማዋን ጸጥታ ፍለጋ ይዞራሉ፤ እነዚህ የቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ናቸው፡፡ እነዚያ ደግሞ እኛን ለማጓጓዝ አውቶቡስ ውስጥ ገብተዋል፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች ሕዝብ ይዝናናል ብለው የቤታቸውን መዝናኛ ትተው ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ጣቢያ ገብተዋል፡፡ እኛ ግን ይኼው በዓመት በዓልን ተሰባስበን እያከበርን ነው፡፡
ልጅ ሆነን ስናጠፋ «ፖሊሱ መጣብህ» እየተባለን አደግን፡፡ እኛም በተራችን ልጆቻችን ሲረብሹ «ፖሊስ እጠራብሃለሁ» እያልን አሳደግናቸው፡፡ ፖሊሶቹም በተራቸው ዱላቸውን እያወዛወዙ በሠፈራችን አለፉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ባደግንበት ማስፈራርያ ላይ «አንተ ተነሣ፣ ጥፋ፣ ሂድ፣ » የሚሉ ኃያል ቃላትን ጨመሩባቸው፡፡ አልፎ አልፎም ጥፊ የሚያልሱ፣ ካልቾ የሚያቀምሱ ፖሊሶች ታዩ፡፡ ይኼው በዚህ ምክንያት እኒህ እናት ልጃቸውን «ፖሊስ ሆኖ ቀረ» ብለው እስከማዘን ደረሱ፡፡
ሳስበው ይህንን ሥዕል የፈጠርነው ሁላችንም ተባብረን ነው፡፡ አሁን አሁን እየተሻሻሉ መጡ እንጂ ፖሊስ ጣቢያዎቻችንን የቆርቆሮ አጥር ያላቸው፤ ግድግዳቸው የፈረሰ፤ የወየበ ቀለም የተቀቡ፤ ሰበርበር ያለ ጠረጲዛ እና ወንበር ያላቸው፤ ክላሴር የሞላባቸው፤ በአንዲት ክፍል ብዙ ሰዎች የታጨቁባቸው፤ እንዲሆኑ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ እኛ ልጅ ሆነን መሥሪያ ቤት ሲባል የምናውቀው የሞቀ፣ የደመቀ፣ ወንበሩ የሚሽከረከር፣ መብራቱ የሚያምር፤ ግቢው አበባ ያነቆጠቆጠውን ቢሮ ነው፡፡ ፖሊስ ጣቢያዎቻችን ደግሞ እንዲህ አልነበረም፡፡ አንዳንዶቹም እንዲህ አይደሉም፡፡ ታድያ እንዴት መሥሪያ ቤት እንበላቸው?
ሕዝቡ ደግሞ ፖሊስን ከመማታት፣ ከማሠር፣ ከመፍታት፣ ከኃይል፣ ከቁጣ ጋር ብቻ ያስበዋል፡፡ ያለፍንባቸው አሠራሮች የፈጠሯቸው የፖሊስ መመዘኛዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ አሁንም አሉ፡፡ ፖሊስን ይማታል የሚል እንጂ ያቅፋል የሚል የለም፤ ያሥራል የሚል እንጂ ያስፈታል የሚል የለም፤ ይቆጣል የሚል እንጂ በትኅትና ይናገራል የሚል የለም፤ ይጨክናል የሚል እንጂ ያዝናል የሚል የለም፤ ያስለቅሳል የሚል እንጂ ያለቅሳል የሚል የለም፡፡ እናም አንድ የሚማታ፣ ኃይለኛ፣ ትከሻው ደንዳና፣ ቁጣቀጣ የሚለው ሰው ሲታይ «ይሄን ፖሊስ ማድረግ ነበር» ይላል፡፡
ፖሊሱም እዚህ ላይ ጨምሮበታል፡፡ ማኅበረሰቡ ሰው መሆኑን፣ እንደሰው የሚያዝን፣ የሚያለቅስ፣ የሚራራ፣ ችግሩን ለመፍታት የሚፈልግ፣ የሚሰማው፣ ልቡ የሚሰበር፣ ሊሳሳትም የሚችል፤ የማኅበረሰቡ ችግር ችግሩ፤ ደስታውም ደስታው የሆነ መሆኑን ማሳየት አልቻለበትም፡፡
እንደ ፖሊስ ማኅበረሰብን የማገልገል እና ሕግ የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት እንዲመሩባቸው የተነገሩ ሦስት ቃላት አሉ፡፡ «መረዳት፣ መርዳት እና ማርዳት»፡፡ «መረዳት» ማለት መጀመርያ ችግሩን ለመረዳት፣ ለመገንዘብ መጣር ማለት ነው፡፡ ከመወሰን፣ ርምጃ ከመውሰድ እና ከተግባር በፊት ምን ለምን፣ በማን፣ እንዴት፣ መቼ ተፈጠረ? ብሎ መረዳት ማለት ነው፡ ያን ጊዜ ኅብረተሰቡ ይረዳኛል፤ ብነግረው ይሰማኛል፤ ባቀርብለት ያይልኛል ብሎ በዚያ አካል ላይ ይተማመናል፡፡
ሁለተኛው «መርዳት» ነው፡፡ ችግር የደረሰበትንም ሆነ ችግር ያደረሰውን አካል በአካል፣ በቁሳቁስ፣ በመንፈስም ሆነ በሥነ ልቡና መርዳት ነው፡፡ በተለይም የተጠቃውን አካል ሰብአዊነት ባልተለየው ስሜት መርዳት፡፡ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ አጋዥ፣ ረዳት፣ ወገን፣ የቅርብ ደራሽ ሆኖ መገኘት፡፡
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘውን አካል ደግሞ ቅጣቱን «ማርዳት» ነው፡፡ መቅጣት ከሁለቱ ነገሮች በኋላ መምጣት አለበት፡፡ ያን ጊዜ ተቀጭውም ቢሆን ስሕተቱን ለማመን፤ ራሱን ለማረም እና የተጣለበትን ቅጣት ተገቢ ነው ብሎ ለመቀበል ይችላል፡፡ ለፍትሕ ሥራውም ተባባሪ ይሆናል፡፡
እነዚህ ነገሮች በሥራው የተሰማሩትንም ሆነ የሥራው ተጠቃሚ የሆኑትን አካላት የሚያግዙ ናቸው፡፡ እኛም ብንሆንኮ መጀመርያ የፖሊሱን ተግባር፣ ዓላማ፣ አሠራር፣ ችግር፣ እጥረት፣ መረዳት አለብን፡፡ ከተረዳነው መርዳት ወደተባለው መጓዝ ቀላል ነው፡፡ እያንዳንዱ መንደር የአካባቢውን ፖሊስ ጣቢያ አሳምሮ መሥራት ያቅተዋል? ከረዳን በኋላ የማይታረሙ ችግሮች ካሉ ደግሞ በተገቢው አሠራር ተጉዞ «ማርዳት» ነው፡፡ ችግሩን በግልጽ መንገር፣ ማኄስ፣ ማረም እና ማስተካከል ነው፡፡
እንዲህ ከሆንን «ፖሊስ ሆኖ ቀረ» ያሉትን እናት «ጎሽ እንኳን ፖሊስ ሆነ» እንዲሉ እናደርጋቸዋለን፡፡

23 comments:

 1. እግዚአብሔር ይስጥልኝ ዲ/ን ዳንኤል! በጣም ጠቃሚ እና አስተማሪ ትምህርት ነው፡፡ ቃለ- ሕይወት ያሰማልን!!! ዛሬም ቢሆን ፖሊስ ማስፈራርያ ሆኖ እያየን ነው፡፡ ይህ ሁሉ አብቅቶ ሁሉም የስራ መስክ ለሰው ልጆች መብት፣ ፍላጎት፣ ነጻነት ወዘተ መጠበቅ በእኩል ዓይን ቢታዩ መልካም ነው፡፡ ፖሊስም ፖሊሳዊ ሳይንሱን በተግባር ላይ ቢያውለው ከመፈራት ወደ መወደድ ይመጣል የሚል ዕምነት አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 2. Interesting view! Ayi Asitedadeg yemayametawu neger aleh bilachihu new!

  ReplyDelete
 3. In my view I don't think this is the reason. The mother forgot him because in our country policeman is the one, who is paid very little.

  ReplyDelete
 4. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel
  I just loughed so hard after finishing reading. The reason? i pictured the policemen in our country. Their uniform, the way they walk, and their short stick. Atlanta

  ReplyDelete
 5. S.G (itala)

  በጣም አመሰግናለሁ ውድ ዳኒ

  በውጪው ዓለም ማንኛውንም የፖሊስ (የህግ አመራር) ሰራተኞች እንደማንኛውም ሰው በስልጣኑና በማህረጉ ከህብረተሰቡ እራሱን አልቆ አይቆጥረውምም አይክበውምም::

  እዚህ ሃገራች ፖሊስ (የህግ አመራር) እራሱን አልቆ እራሱን አክቦ በስልጣኑና በማህረጉ ተመክቶ እራሱን የሚክብ አንድና ሁለት ብቻ አይደሉም ቤት ይቁጠራቸው::

  ስልጣናቸውን ህዝብን ከማገለገል ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም ይጠቀሙበታል እቁብና እድር ለመክፈያ ገንዘብ ማፈላለጊያ ያደርጉታል ታዲያ እኒያ እናት ወደው አይደለም ፖሊስ ሆኖ ቀረ ያሉት::

  እናም ህዝቡ በእየ ቢሮ እና በእየ ጉዳዩ ሲሄድ የሰለቸው ነገር አለ:: ታዲያ ህዝቡ እንዴት ነው ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚለው::

  ReplyDelete
 6. nice view ,,khy !

  ReplyDelete
 7. It is good!It is good!

  ReplyDelete
 8. Dear Daniel,

  I used to a Police man, even I had the senior position. I were one of an instructor in Ethiopian Police College too. Fortunately, I had an opportunity to be trained in Germany, England, US, Turkey, India and other places. One thing what I saw in these countries Police as a profession is respected by others. In some developed nations you could be a police officer if you have a family within the police service. Our problem is the perception which is based on our culture. To my observation, there must be a platform that make the people and the community to be engaged more. Policing all over the world has been passed four eras (1) Political ... serving state officials (2) Law enforcement ... detection and investigation of crime (3) Service oriented ... delivering service to the public (4) Community policing ... building partnership with the community. The last era is the good platform to bring both the police and the public together. Police must be the public and the public must be the police.


  This is easy to say but very hard to do, particularly in a country with a history of authoritarianism and little, if any, meaningful participation of citizens in the way they are governed. Over the past fifty years, Ethiopia has gone from one extreme to the other – from feudalism to socialism before settling in the 1990s for a significantly more open political system. This blends federalism and decentralization with strong state structures that are required to serve what national leaders call ‘the developmental State.’

  The police have not been exempt from the political winds that have blown in different directions in Ethiopia. The force as a modern institution was established in 1942. As a law enforcement body, it has continued its tradition of serving the government of the day, yet the political changes have had an impact. For one, when the country adopted the federal system, the structure of the police force changed substantially. Each regional state got a police force of its own, answerable to elected regional bodies, while the Federal Government gained the services of the Federal Police.

  Structural change is one thing. What is critical is effecting change in the way normal business is done at every level. Although decentralizing the police structure could be seen as a step in the right direction towards good governance, the question is whether the police are relating better to the public and if the change of structure has brought about a change of behavior?

  The impartial enforcement of laws requires the operation of fair legal frameworks that are enforced impartially, as well as the existence of an independent judiciary. It also requires the full protection of human rights, particularly those of minorities and an impartial and incorruptible police force.

  There are signs that the police forces in Ethiopia are trying to deal with the requirements of good governance. One example is the effort to introduce and implement community policing. From the way in which the police manage to get information from communities, it would seem that the launch of the practice of community policing has strengthened the effectiveness of the police through the improvement of relations between the force and the community at large building and enhancing partnership among them selves.

  There is also growing coordination within the justice system as the police, prosecutors, courts and other related institutions interact more purposefully while maintaining their independent mandates. It is hoped that this beginning will speed up the delivery of justice, for long a worrying feature in the Ethiopian judicial landscape.

  The very fact that the police consider their work as ‘service delivery’ is in itself a departure from the past. The force has pledged to upgrade its education and training system, as well as its administration, and plans to revamp its crime prevention and investigation work.

  To sum up Police service is required by all and the profession it self is highly respected.

  ReplyDelete
 9. Nice view lets say KALEHIWOT YASEMALIN only for spirtual messages

  ReplyDelete
 10. ለመሆኑ በእኛ ሀገር ሁኔታ ፖሊስ ሁኖ ቀረ ቢባል ይበዛበታል እንጅ መች ያንስበታል፡፡ እነርሱ ብዙውን ጊዜ የቆሙት ለአንድ ነገር ነው እርሱም ባለ “ወንበሮችን” መጠበቅ፡፡ ይህን ስል ግን የተወሰኑ ለሙያቸው እና ለስራቸው ታማኝ የሆኑ ፖሊሶች መኖራቸውን ዘንግቸው አይደለም፡፡

  AA from Addis Ababa

  ReplyDelete
 11. ዳኒ በእውነት ኮራሁብህ፡፡ እንዲህ ነው የተግባር ሰው መሆን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 12. ስለ ፖሊስ ሳስብ ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ግዜ አንድ መምሀሬ የነገረኝ ነገር ሁሌም ትዝ ይለኛል በውጪው ዓለም በተለይም በበለፀጉት አገሮች አንድ ሰው ፖሊስ ሲያይ ወይም ስለ ፖሊስ ሲያስብ እየተጠበቀ እንደሆነ ያስባል/ ይሰማዋል እኔ ግን አለ መምህሬ እዚህ አገር ፖሊስ ሳይ የሚሰማኝ ፍርሐት ነው ምክንያቱ ደግሞ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ብጥብጥ ይነሳና በኡራል መዓት ፖሊስ መጥቶ ምንም ሳያጣሩ እየደበደቡ ያገኙንን ሁሉ ሰብስበው ይዘውን ሄዱ ከዚያ በኋላ በቃ ፖሊስ ሳይ ችግር ፈጣሪ እንጂ ችግር ፈቺ ናቸው ብዬ አላስብም አለኝ፡፡ እኔም ይኸው የሱ ታሪክ በራሴ ስለ ደረሰ በሐሳቡ እስማማለሁ፡፡ እስኪ ማናችን ነን ወይ ስንደባደብ ወይ ስንገላግል የፖሊስ ጥፊ ያልቀመስን? ወይ ቲያትር ቤት ወይ ስቴዲየም ለመግባት ሰልፍ ይዘን የፖሊስ ዱላ ያልቀመስንስ ስንቶች ነን?

  ሌላው ከፖሊስ ጋር ተያይዞ ትዝ የሚለኝ የአስራ አራት ዓመት ልጅ በነበርኩበት ወቅት ለአዲስ ዓመት የሚያስፈልገንን የትምህርት ቁሳቁስና ልብስ ለመግዛት ከሰፈር ልጆች ጋር አራዳ ጊዮርጊስ በኃውልቱ በኩል ባለው በር ግንቡ ላይ ሊስትሮ እንሠራ (ጫማ እንጠርግ) ነበር፡፡ እዚህ ቦታ ላይ አሁንም ድረስ ብዙ ሊስትሮዎች ይገኛሉ፡፡ በዚህ ቦታ ላይ በቋሚነት የሚሰሩት ከቤተ ክርስቲያኑ ፊት ለፊት (ለጥምቀት ታቦቱ የሚቆምበት ቦታ) ከተለያዩ የጉራጌ ክፍለ ሐገር የሚመጡ፤ ከበሩ በስተቀኝ ከከንባታ እና ሐዲያ የሚመጡ፤ ከበሩ በስተ ግራ በኩል ደግሞ የአዲስ አበባ ልጆች ነን፡፡ ታዲያ እዚህ ቦታ ላይ በሰላም ስንሰራ ቆይተን በኋላ ላይ የገበያ ሽሚያ እየተፈጠረ በተለይ እኛ የአዲስ አበባ ልጆች በሁለት ወር ክረምት ብዙ ደምበኛ ስናፈራና አንዳንዶች የጉራጌ እና የሌሎች ደንበኞችን ወደ ራሳችን መሳብ ስንጀምር ግጭት ተፈጠረ፡፡ ታዲያ አንድ ወቅት እኛ በቁጥር አነስ ብለን የነበር ዕለት ተሰብስበው ደበደቡን ሊስትሮአችንንም ሰበሩብን የእኔ ወንድም ተፈነከተ አንዳንዶቻችንም መጠነኛ ጉዳት ደረሰብን፡፡ በኋላ ይህን ጉዳይ ሌሎች ጓደኞቻችን ሲሰሙ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው መጥተው ደበደቧቸው፡፡ እነሱም ብልጥ ነበሩና ቶሎ ሸሽተው ወደ ማዘጋጃ ቤት ይሄዳሉ በዚያ ለጥበቃ ለተመደቡ ፖሊሶች ጉዳዩን አስተዛዝነው ይነግራሉ፡፡ ከዛ ምን ልበላችሁ እኛ መቆሚያ መቀመቻ አጣን አንዳችን ስንሰራ አንዳንችን ስንጠብቅ ፖሊስ መጣ ስንባል ስንሸሽ ሳይዙን ብዙ ጊዜ ቆየን፡፡ አንድ ቀን ሁላችንም ጉዳዩን ረስተን ተሰብስበን ወሬያችንን ስንቀድ ለምን ከበው አይይዙንም፡፡ ከዚያም ሁላችንንም ሰብስበው ማዘጋጃ ቤት የሚጠብቁባት አንድ ግማሽ መስታወት የሆነች ቤት ውስጥ አስገብተው ጥያቄ የለ ምን የለ ከግራ ከቀኝ በጥፊ በርግጫ ያጣድፉን ጀመር፡፡ እንጮኻለን ቤቷ ደግሞ ምንም ድምፅ ወደ ውጪ አታስወጣ ገላጋይ እንኳን ሊመጣ አልቻለም፡፡ በኋላ አንዱ ሲሰነዝር የተፈነከተውን ወንድሜን ቁስሉን ይመታዋል፤ ወንድሜ ጩኸቱን ይለቀዋል በዚህ ጊዜ ይደናገጡና ምን ሆነህ ነው? ብለው ጥያቄ ያቀርባሉ ከዛማ መጀመሪያ የተደበደብነው እኛ እንደሆንን ይረዱና ከዚህ በኋላ እንዳንጣላ አስጠንቅቀውን ይለቁናል፡፡ እንግዲህ ከመረዳትም፣ ከመረዳትም፣ ከማርዳትም ውጪ የሆኑ እንዲህ ዓይነት ፖሊሶችም አሉ፡፡ የሚዛን ስዕል መለዮአቸው ላይ አለ እንጂ ምንም ሚዛናዊነት የማያውቁ ነገሮችን ለመረዳት የማይጥሩ፡፡

  ከአዲስ አበባ
  ስለ ፖሊስ ሳስብ ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ግዜ አንድ መምሀሬ የነገረኝ ነገር ሁሌም ትዝ ይለኛል በውጪው ዓለም በተለይም በበለፀጉት አገሮች አንድ ሰው ፖሊስ ሲያይ ወይም ስለ ፖሊስ ሲያስብ እየተጠበቀ እንደሆነ ያስባል/ ይሰማዋል እኔ ግን አለ መምህሬ እዚህ አገር ፖሊስ ሳይ የሚሰማኝ ፍርሐት ነው ምክንያቱ ደግሞ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ብጥብጥ ይነሳና በኡራል መዓት ፖሊስ መጥቶ ምንም ሳያጣሩ እየደበደቡ ያገኙንን ሁሉ ሰብስበው ይዘውን ሄዱ ከዚያ በኋላ በቃ ፖሊስ ሳይ ችግር ፈጣሪ እንጂ ችግር ፈቺ ናቸው ብዬ አላስብም አለኝ፡፡ እኔም ይኸው የሱ ታሪክ በራሴ ስለ ደረሰ በሐሳቡ እስማማለሁ፡፡ እስኪ ማናችን ነን ወይ ስንደባደብ ወይ ስንገላግል የፖሊስ ጥፊ ያልቀመስን? ወይ ቲያትር ቤት ወይ ስቴዲየም ለመግባት ሰልፍ ይዘን የፖሊስ ዱላ ያልቀመስንስ ስንቶች ነን?

  ሌላው ከፖሊስ ጋር ተያይዞ ትዝ የሚለኝ የአስራ አራት ዓመት ልጅ በነበርኩበት ወቅት ለአዲስ ዓመት የሚያስፈልገንን የትምህርት ቁሳቁስና ልብስ ለመግዛት ከሰፈር ልጆች ጋር አራዳ ጊዮርጊስ በኃውልቱ በኩል ባለው በር ግንቡ ላይ ሊስትሮ እንሠራ (ጫማ እንጠርግ) ነበር፡፡ እዚህ ቦታ ላይ አሁንም ድረስ ብዙ ሊስትሮዎች ይገኛሉ፡፡ በዚህ ቦታ ላይ በቋሚነት የሚሰሩት ከቤተ ክርስቲያኑ ፊት ለፊት (ለጥምቀት ታቦቱ የሚቆምበት ቦታ) ከተለያዩ የጉራጌ ክፍለ ሐገር የሚመጡ፤ ከበሩ በስተቀኝ ከከንባታ እና ሐዲያ የሚመጡ፤ ከበሩ በስተ ግራ በኩል ደግሞ የአዲስ አበባ ልጆች ነን፡፡ ታዲያ እዚህ ቦታ ላይ በሰላም ስንሰራ ቆይተን በኋላ ላይ የገበያ ሽሚያ እየተፈጠረ በተለይ እኛ የአዲስ አበባ ልጆች በሁለት ወር ክረምት ብዙ ደምበኛ ስናፈራና አንዳንዶች የጉራጌ እና የሌሎች ደንበኞችን ወደ ራሳችን መሳብ ስንጀምር ግጭት ተፈጠረ፡፡ ታዲያ አንድ ወቅት እኛ በቁጥር አነስ ብለን የነበር ዕለት ተሰብስበው ደበደቡን ሊስትሮአችንንም ሰበሩብን የእኔ ወንድም ተፈነከተ አንዳንዶቻችንም መጠነኛ ጉዳት ደረሰብን፡፡ በኋላ ይህን ጉዳይ ሌሎች ጓደኞቻችን ሲሰሙ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው መጥተው ደበደቧቸው፡፡ እነሱም ብልጥ ነበሩና ቶሎ ሸሽተው ወደ ማዘጋጃ ቤት ይሄዳሉ በዚያ ለጥበቃ ለተመደቡ ፖሊሶች ጉዳዩን አስተዛዝነው ይነግራሉ፡፡ ከዛ ምን ልበላችሁ እኛ መቆሚያ መቀመቻ አጣን አንዳችን ስንሰራ አንዳንችን ስንጠብቅ ፖሊስ መጣ ስንባል ስንሸሽ ሳይዙን ብዙ ጊዜ ቆየን፡፡ አንድ ቀን ሁላችንም ጉዳዩን ረስተን ተሰብስበን ወሬያችንን ስንቀድ ለምን ከበው አይይዙንም፡፡ ከዚያም ሁላችንንም ሰብስበው ማዘጋጃ ቤት የሚጠብቁባት አንድ ግማሽ መስታወት የሆነች ቤት ውስጥ አስገብተው ጥያቄ የለ ምን የለ ከግራ ከቀኝ በጥፊ በርግጫ ያጣድፉን ጀመር፡፡ እንጮኻለን ቤቷ ደግሞ ምንም ድምፅ ወደ ውጪ አታስወጣ ገላጋይ እንኳን ሊመጣ አልቻለም፡፡ በኋላ አንዱ ሲሰነዝር የተፈነከተውን ወንድሜን ቁስሉን ይመታዋል፤ ወንድሜ ጩኸቱን ይለቀዋል በዚህ ጊዜ ይደናገጡና ምን ሆነህ ነው? ብለው ጥያቄ ያቀርባሉ ከዛማ መጀመሪያ የተደበደብነው እኛ እንደሆንን ይረዱና ከዚህ በኋላ እንዳንጣላ አስጠንቅቀውን ይለቁናል፡፡ እንግዲህ ከመረዳትም፣ ከመረዳትም፣ ከማርዳትም ውጪ የሆኑ እንዲህ ዓይነት ፖሊሶችም አሉ፡፡ የሚዛን ስዕል መለዮአቸው ላይ አለ እንጂ ምንም ሚዛናዊነት የማያውቁ ነገሮችን ለመረዳት የማይጥሩ፡፡

  ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 13. እግዚአብሔር ቃለ-ሕይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል፡፡ May GOD help us to practice «መረዳት፣ መርዳት እና ማርዳት» in our day to day life. AMEN
  Dejen from Mekelle

  ReplyDelete
 14. ብዙዎቹ የፖሊስ ጽ/ቤቶች በጣም ጥራት ጎደላቸው ቢሆኑም የፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት ግን በተለየ መልኩ ኩሁሉም ሚኒስቴር መ/ቤቶች የበለጠ የሚያምር ነው፡፡አሁን ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ የፖሊስ ዋና ተቀዳሚ ስራ ወይንም ሀላፊነት ስልጣን ላይ ለውን አገዛዝ ህልውናና ደህንነት መንከባከብና ማስጠበቅ ነው፡፡ሁለተኛው ስራ ስልጣን ላይ ለውን አገዛዝ ህልውናና ደህንነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሰላማዊ መንገድም ይሁን በሀይል ሊፈታተን የሚፈልግን ማንኛውንም ግለሰብ ወይንም ሀይል ማስፈራራት ማሸማቀቅ መቅጣትና ማሰቃየት ነው፡፡በሶስተኛ ደረጃ ላይ የህግ የበላይነትንና የሀገሪቱን ዜጎች ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡ከምንጊዜውም በላይ በአሁኑ ወቅት እንዲያውም የህግ የበላይነት ስላምና ደህንነት በዋናነት ፋይዳቸው ከዜጎች ደህንነት አንፃር ሳይሆን በዋናነት ስልጣን ላይ ለውን አገዛዝ ወንበር ከመጠበቅና ከመንከባከም አንፃር ነው፡፡
  ከምርጫ 97 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሀገሪቱ በተለይም ዋና መዲናዋ አዲስ አበባ መሳረያ ባነገቱ የፖሊስና የወታደር ሀይል እየተጠበቀች ነው፡፡አሁንማ ጭራሽ ብሶበት ዱላ በያዙ ሌሎች ዩኒፎርም ባጠለቁ ፖሊስ መሳይ ሰዎች በየአካባቢውና በየስርቻው ሳይቀር እንደ አሸን እየተርመሰመሱ ነው፡፡
  እና ይህ በእውነት በዋነኝነት ለተራው ዜጎች ደህንነትና ሰላም ተብሎ ነውን?ፈፅሞ አይደለም፡፡
  በተለይም በአሁኑ ወቅት ከምነጊዜውም በላይ በህብረተባችን ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም አይነት ግጭትና አለመግባባት ስልጣን ላይ ያለውን ሀይል ህልውና የሚፈታተን እስካልሆነ ድረስ ይህ ነው የሚባል ተገቢው ክትትልና መፍትሄ ሊሰጠው አይፈለግም፡፡
  እናም በአሁኑ ወቅት የፖሊስ ዋና ስራውና ፋይዳው የህግ የበላይነት የሚለውን መፈክር የስልጣን የበላይነት በሚል የተካ ይመስላል፡፡በአሁኑ ወቅት በተለይ ዜጎች ፖሊስን ሲያዩ ባብዛኛው ትዝ የሚላቸው ደህንነት ሳይሆን ፍርሃትና መሸማቀቅ ነው፡፡ምክንያቱም የፖሊሱ እዚያ መኖር ውስጣቸውን ደመነፍሳቸውን የሚነግራቸው እነሱን ለመጠበቅ ሳይሆን በዋናነት ምኒልክ ቤተመንግስት ያለውን ስልጣን እንደሆነ ነው፡፡
  ፖሊስ በህብረተቡ ዘንድ የተወደደና የተከበረ ስራ ሆኖ ሊታይ የሚችለው ይህ አይነቱ ነገር ሲቀርና ፖሊስም በዋናነት ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ አገልጋይ መሆኑ ቀርቶ በተቃራኒው በዋነኛነት የህግና የህዝብ አገልጋይ መሆን ሲችል ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 15. አልቀበለውም ይህንን ሀሳብ:: ለምን በለኝ? እንደው እውነት እንነጋገር ከተባለ ፖሊስ በሀገራችን ለድህንነት ቆሟል ነው የምትለኝ??? አንድ አጭር ምሳሌ ልስጥህ አንድ ቀን ለይኩን ምግብ ቤት (ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት)ወንድሜን ሌቦች ለአራት ሆነው ይዘርፉታል ለብ በል ሰዓቱ ከአመሻሹ 12:00 ሰዓት ነው:: እንደው ሁሉ ነገር በገሃድ የሚታይ ነው:: መሳሪያ የታጠቅ ፖሊስ ከመንገዱ ባሻገር ሆኖ ሁሉንም እንደ ድራማ ይመለከታል:: ወንድሜ አልሞት ባይ ተጋዳይ የሚሉት ዓይነት ሆኖ መጀመሪያ የመታውን ጠፍንጎ ይዞ አልለቀውም ይላል:: ፖሊስ እያለ ይጮሃል ጀርባውን ወደዛ አዙሮ ነው የሚሄደው:: በዚህ ሁሉ ትንቅንቅ ውስጥ ሆኖ ይደውውልልኛል ወንድሜ "ድረስልኝ" የሚል የሲቃ ጥሪ ነው የሰማሁት:: ከጦር ኃይሎች መኪናዬን አስነስቼ ማንኛውንም የትራፊክ ህግ እየጣስኩ ነው የደረስኩኝ:: አስበው እኔ ከጦር ኃይሎች ተነስቼ ንግድ ሥራ ኮሌጅ እስክደርስ ፖሊስ ፊቱን አዙሮ ማየት አልቻለም:: ልክ ስደርስ የእኔ ሥራ የነበረው ሌባውን መምታት ብቻ ነበረ:: ያኔ ፖሊሱ መጣ ከዛ የተፈጠረው እጅግ ከማሳዘንም አልፎ ሀገር ወገን የሚባለውን የሚያስጠላ ነገር ነው:: ቅድም ወንድሜን ሲደበድቡት ምንም ያልተናገሩት የሩቅ ተመልካቾች አሁን ቀርብ አሉና "ሚስኪን ዘመድ የሌለው ሊገድሉት ነው" የአዛኝ ቅቤ አንጓች የሚባለው ዓይነት ምስክርነት ጀመሩ:: ብቻ ጣጣው ብዙ ሄደ፤

  ሁለተኛ ልጨምርልህ፤ ትዝብት ነው:᎗
  ቦሌ ጋ አንድ መኪና ቆማለች እና ሶስት ትናንሽ ልጆች ዙሪያዋን ቆመዋል::
  ሹፌሯ ሴት ናት፤ ሁሉንም መስኮት ዘግታ በጣም ፍራቻ ይነበብታል ከፊቷ:: ልጆቹ "የጎዳና ተዳዳሪዎች ናቸው" ዕድሜያቸው ከ10-13 ይሆናል:: እያለፍን እያለን ሁኔታዋን ስናስተውል ምን ሆነሽ ነው ብለን ጠየቅናት "ብር ካልሰጠሽን እንገድልሻለን አሉኝ እሄዳለሁ ብትይ መስተዋቱን እንሰብረዋለን አሉኝ" አለች"" ከዛ ኑ ብለን ፖሊስ ጋር እንወስዳችኋለን ስንላቸው "ውሰዱን እዛ ይሻለናል" አሉን::

  ReplyDelete
 16. As a matter of fact POLICE is an acronym for: Protection of Life in Civil Establishment (POLICE). However, in a rather bizarre twist, POLICE in Ethiopia have had a different meaning and it's scary as hell. So, as the author argues, We all are responsible to create a more benign image of POLICE. Above all, the incumbent is more responsible and should mould a better and yet responsive POLICE officer!!!

  Ye Tena Tabia Folk (Kebele 03)
  Bahirdar

  ReplyDelete
 17. አይ ፖሊስ....
  ኧኒ በበኩሊ ፖሊስ ማስፈራሪያ መሆኑን ልጅ ሆኚ ብቻ ሳይሆን አድጊ፡ ዩኒቨርሲቲ ገብቺም ጭምር ያየሁት ጉዳይ ነው። ለምን መስላችሁ...
  ግዚው 1993 ዓ.ም አ.አ.ዩ ግርግር ተነሳና መጠጊያ ስናጣ ሁላችንም(አስላም፡ ክርስቲያን፡ ፐሮቲስታንት) ተነስተን ወደ ቢ/ክ(ቅ.ማርያም)ገባን። አዛው ባለንበት "ፖሊስ" መጥቶ ይዞን ወደ ስንዳፍ... አይ አዛ የነበረ መከራ! መቺም በዛን ግዚ የነበሩ አንባብያን የጻፍኩትን ሳይሆን በህሳቢ ያለውንም ጭምር አንደሚረዱኝ ጥርጥር የልኝም። ታድያ ይሂንን አያየን አንዲት ነው "ፖሊስ"ን የምንወደው? ለዚያውም ያገር ልጅ ወገን.... በሩቁ ነው አንጂ...ይበልጡን የሚያናድደኝ በታስርንበት ክፍል ውስጥ ስለ ፓሊስ የተጻፉት ጥቅሶች... ብቻ ምናለፋችሁ ለኛ ህገር "ፖሊሶች" ሊላ ስም ብናወጣላቸ ኧስማማለሁ። ማንያውቃል አኚሀም አናት የኒ ኧጣ አልደረሰባቸው ይሆን?! የገጠመኝን ነው የጻፍኩት ካጠፋሁ ይቅርታ!

  ReplyDelete
 18. አስተማሪ ጽሑፍ ነው ዳኒ በርታ ወንድማችን!! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን!!

  ReplyDelete
 19. *****************************************
  አልቀበለውም ይህንን ሀሳብ:: ለምን በለኝ? እንደው እውነት እንነጋገር ከተባለ ፖሊስ በሀገራችን ለድህንነት ቆሟል ነው የምትለኝ??? አንድ አጭር ምሳሌ ልስጥህ አንድ ቀን ለይኩን ምግብ ቤት (ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት)ወንድሜን ሌቦች ለአራት ሆነው ይዘርፉታል ለብ በል ሰዓቱ ከአመሻሹ 12:00 ሰዓት ነው::
  ***********************************************
  ይህንን ከላይ ያለውን ሀሳብ ያቀርበከው ውድ ወንድሜ ሃሳባችን የተለያየ መስሎህ እንጂ ብዙም የሚለያይ አይደለም፡፡ምክንያቱም የፖሊስን ፋይዳና ስራ በቅደም ተከተል እንደደረጃው ያስረዳሁኝ መሰለኝ፡፡
  የብዙሀኑ ህዝብና የሀገር ደህንነትና ሰላም እንዲጠበቅ የሚፈለገው በዋናነት አገዛዝ ላይ ያለውን ስልጣን ድህንነትና ሰላም ለመጠበቅ ተብሎ ነው አልኩህ እኮ፡፡በትክክለኛ አካሄድ ግን መሆን ያለበት አገዛዝ ላይ ያለውን ስልጣን ድህንነትና ሰላም መጠበቅ የሚያስፈልገው በዋናነት የብዙሀኑን ህዝብና የሀገርን ደህንነትና ሰላም እንዲጠበቅ ለማድረግ ተብሎ መሆን ነበረበት፡፡እዚህ ላይ ቅደም ተከተሉ ከፈረሱ ጋሪው አይነት ሆኖ ተምታታ እንጂ አገዛዝ ላይ ላለው ስልጣን ሰላምና ደህንነት ሲባል የፖሊስ ጥበቃ አያስፈልገውም እያልኩኝ አይደለም፡፡ምክንያቱም ስልጣን ወይንም መንግስት የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ዝም ብሎ የምናመልከው መንፈስ ብቻም ሳይሆን ስጋ የለበሱ ግለሰቦች ስብስስብ ጭምር ስለሆነ እነሱም እንደ ዜጋ ካለባቸው ሀላፊነት አንፃር እንዲያውም ከተራው ዜጋ በበለጠ ሰላማቸውና ደህንነታቸው ሊጠበቅ ያስልጋቸዋል፡፡ነገር ግን የብዙሀኑ ህዝብና የሀገር ደህንነትና ሰላም ሲጠበቅ አገዛዝ ላይ ያለው ስልጣን ሰላምና ደህንነትም ጭምር አብሮ እግረ መንገዱን ይጠበቃል ለማለት ነው፡፡በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ግለሰቦች ደህንነትና ሰላም ከአጠቃላዩ ሀገርና ህዝብ ደህንነትና ሰላም የበለጠ ከበሬታና እንክብካቤ ሊሰጠው ግን አይገባም፡፡ፖሊሶች ማንኛውም ግርግር ወይንም ወከባ ወይንም ወንጀል ሲፈጠር የፖለቲካ ትርጉም ብቻ እየሰጡት ሊያስተናግዱት የሚፈልጉ ከሆነ ይህ የህግ የበላይነት ሳይሆን የስልጣን የበላይነት መፈክር ያነገበ ያስመስለዋል ማለት ነው፡፡እዚህ ላይ እየተናገርኩ ያለሁት ጤናማ ስለሆነ አስተሳሰብና አካሄድ ባለው እይታ ነው፡፡ከዚያ ውጪ ወንድሜ ያልከው ችግር ስለመኖሩማ ፈፅሞ አልክድም እንዲያውም የእኔውን ፅኁፍ መንፈሱን በደንብ ከተረዳኸው ይህንኑ አስረግጦ የሚያምን ነው፡፡
  ይህንን ከላይ ያለውን ሀሳብ ያቀርበከው ውድ ወንድሜ ሃሳባችን የተለያየ መስሎህ እንጂ ብዙም የሚለያይ አይደለም፡፡ምክንያቱም የፖሊስን ፋይዳና ስራ በቅደም ተከተል እንደደረጃው ያስረዳሁኝ መሰለኝ፡፡
  የብዙሀኑ ህዝብና የሀገር ደህንነትና ሰላም እንዲጠበቅ የሚፈለገው በዋናነት አገዛዝ ላይ ያለውን ስልጣን ድህንነትና ሰላም ለመጠበቅ ተብሎ ነው አልኩህ እኮ፡፡በትክክለኛ አካሄድ ግን መሆን ያለበት አገዛዝ ላይ ያለውን ስልጣን ድህንነትና ሰላም መጠበቅ የሚያስፈልገው በዋናነት የብዙሀኑን ህዝብና የሀገርን ደህንነትና ሰላም እንዲጠበቅ ለማድረግ ተብሎ መሆን ነበረበት፡፡እዚህ ላይ ቅደም ተከተሉ ከፈረሱ ጋሪው አይነት ሆኖ ተምታታ እንጂ አገዛዝ ላይ ላለው ስልጣን ሰላምና ደህንነት ሲባል የፖሊስ ጥበቃ አያስፈልገውም እያልኩኝ አይደለም፡፡ምክንያቱም ስልጣን ወይንም መንግስት የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ዝም ብሎ የምናመልከው መንፈስ ብቻም ሳይሆን ስጋ የለበሱ ግለሰቦች ስብስስብ ጭምር ስለሆነ እነሱም እንደ ዜጋ ካለባቸው ሀላፊነት አንፃር እንዲያውም ከተራው ዜጋ በበለጠ ሰላማቸውና ደህንነታቸው ሊጠበቅ ያስልጋቸዋል፡፡ነገር ግን የብዙሀኑ ህዝብና የሀገር ደህንነትና ሰላም ሲጠበቅ አገዛዝ ላይ ያለው ስልጣን ሰላምና ደህንነትም ጭምር አብሮ እግረ መንገዱን ይጠበቃል ለማለት ነው፡፡በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ግለሰቦች ደህንነትና ሰላም ከአጠቃላዩ ሀገርና ህዝብ ደህንነትና ሰላም የበለጠ ከበሬታና እንክብካቤ ሊሰጠው ግን አይገባም፡፡ፖሊሶች ማንኛውም ግርግር ወይንም ወከባ ወይንም ወንጀል ሲፈጠር የፖለቲካ ትርጉም ብቻ እየሰጡት ሊያስተናግዱት የሚፈልጉ ከሆነ ይህ የህግ የበላይነት ሳይሆን የስልጣን የበላይነት መፈክር ያነገበ ያስመስለዋል ማለት ነው፡፡እዚህ ላይ እየተናገርኩ ያለሁት ጤናማ ስለሆነ አስተሳሰብና አካሄድ ባለው እይታ ነው፡፡ከዚያ ውጪ ወንድሜ ያልከው ችግር ስለመኖሩማ ፈፅሞ አልክድም እንዲያውም የእኔውን ፅኁፍ መንፈሱን በደንብ ከተረዳኸው ይህንኑ አስረግጦ የሚያምን ነው፡፡

  ReplyDelete
 20. min alefah police le ne meleyo lebash hulet eger yalew tenqesaqash yetor mesaria azilo ethiopia lay siltan yemiyizu fituranin ye miyagib fitur new,yihe tshuf 1997n yastawisegnal,12th class,minim kemetekos wichi maseb be mayichilu godolo sewoch yayehut beki new. bicha ...

  ReplyDelete