Tuesday, July 26, 2011

ተመንሱስ

የሺወርቅ ወልዴ አትሮንስ በተባለ መጽሐፏ አያቷ ያጫወቷትን ተረት ነግራናለች፡፡

ሳጥናኤል አንድ ልጅ ነበረው ይባላል፡፡ ተመንሱስ የሚባል፡፡ የኔ ልጅ ከማን ያንሣል አለና ትምህርት ቤት አስገባው አሉ፡፡

ተመንሱስ ትምህርት ቤት ከገባበት ቀን ጀምሮ አርባ ስድስት ተማሪዎችን የያዘው ክፍል ቀውጢ ሆነ፡፡ የተማሪ ደብተር ይጠፋል፣ የአንዱ ደብተር ከሌላው ጋር ይቀላቀላል፤ ድንገት የአንዱ ተማሪ ወንበር ወደ ኋላ ይሄድና ተማሪው ይወድቃል፡፡ አንዱ ተማሪ ሳያስበው ሌላውን ተማሪ ይመታዋል፡፡ ጎን ለጎን በፍቅር ሲያወሩ የነበሩ ተማሪዎች ድንገት ጭንቅላቶቻቸው ይጋጫሉ፡፡

ተማሪዎችም አንተ ነህ አንተ ነህ እየተባባሉ መነታረክ፣ መቧቀስ እና መካሰስ የዘወትር ሥራቸው ሆነ፡፡ የክፍል ኃላፊ መምህሩ ያ ሰላማዊ የሆነ ክፍል ሲበጠበጥ የሚያደርጉት ነገር ይጠፋቸው ጀመር፡፡ ዛሬ የተፈታው ችግር ነገ እንደገና ያገረሻል፡፡ ቢጨንቃቸው ለዳይሬክተሩ አመለከቱ፡፡ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክ ተርም በመምከር፣ በማስታረቅ እና የተማሪዎችን ወንበር በማቀያየር ለመፍታት ሞከሩ፡፡ ግን አልተሳካም፡፡

የተማሪዎቹ ወላጆች ተጠርተው ልጆቻቸውን እንዲያርሙ፣ እንዲመክሩ እና እንዲቀጡ ተነገራቸው፡፡ ወላ ጆች ግን ስለ ልጆቻቸው የሰሙት በቤታቸው ውስጥ ከሚያዩት ጠባይ የተለየ ሆነባቸውና ግራ ገባቸው፡፡ ችግሩም እየባሰ መጣ፡፡

ተማሪዎች ለዕረፍት ወጣ ብለው ሲመጡ ክፍሉ በአንድ እግሩ ቆሞ ይጠብቃቸዋል፡፡ መምህሩ ጥቁር ሰሌ ዳው ላይ የጻፉት እየጻፉ ይጠፋባቸዋል፡፡ የክል ኃላፊው መምህር ስም እየጠሩ ድንግርግር ይላቸዋል፡፡ የተማሪዎች ደብተር ይሞጫጨራል፡፡ የክፍሉ መስኮት እና በር ወላልቆ የጣልያን ቦንብ የመታው መሰለ፡፡

የክፍሉ ተማሪዎች ፣መምህራኑ እና ወላጆች ግራ ተጋቡ፡፡

ተማሪዎቹ ሸንጎ ተቀመጡ፡፡ ስለ ችግሩ አወጡ አወረዱ፡፡ ለመሆኑ ማን ከመጣ ወዲህ ነው ክፍሉ እንዲህ ቀውጢ የሆነው? ብለው ጠየቁ፡፡ በመጨረሻም ተመንሱስ ወደ ክፍሉ ከገባ በኋላ ክፍሉ መረበሹን ደረሱበት፡፡ እርሱን ለብቻ ለይተው በጉዳዩ ላይ መከሩ፡፡ ተመንሱስ ከክፍል እንዲባረር ወሰኑ፡፡ ትምህርት ቤቱም ለአንድ ወር አገደው፡፡

በማግሥቱ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ ተመንሱስ ቀድሟቸው ሰልፍ ላይ ተገኘ፡፡ ደነገጡ፡፡ የክፍሉ ኃላፊም ከትምህርት ቤት እንዲወጣ አዘዙት፡፡ ከግቢውም ወጣ፡፡ ሰልፉ አልቆ ክፍል ሲገቡ ተመንሱስ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ተገኘ፡፡ የትምህርት ቤቱ የጥበቃ ሠራተኞች በበር እንዳልገባ አረጋገጡ፡፡ ተማሪዎችም ግራ ገባቸው፡፡ አሁንም ለውይይት ተቀመጡ፡፡ ተመንሱስ በጆንያ ተደርጎ ገደል መጣል እንዳለበት ተማሪዎቹ ተስማሙ፡፡ ወዲያው ጆንያ ተፈልጎ ተመንሱስ በግድ ተከተተ፡፡ ሁሉም ተማሪዎች እየተረዳዱ ከትምህርት ቤቱ የግማሽ ቀን መንገድ ርቀት ከሚገኝ ገደል ጥለውት መጡ፡፡ የተመንሱስ ነገር አለቀለት ብለው አጋና ተመታቱና ወደየቤታቸው ገቡ፡፡

በማግሥቱ ግን ከሁሉም ቀድሞ ተመንሱስ ሰልፍ ላይ ተገኘ፡፡እንጨት ተሰብስቦ ተማሪዎቹ ደነገጡ፡፡ መምህራኑም ግራ ገባቸው፡፡ እንደገናም ለስብሰባ ተቀመጡ፡፡ ከስብሰባ በቀር ሌላ መፍትሔ ሊታያቸው አልቻለምና፡፡ ተመንሱስን ቆራርጠው ለማቃጠል ወሰኑ፡፡ እሳት ተያይዞ ተመንሱስ ተወረወረ፡፡ ዓይናቸው እያየም ተቃጠለ፡፡ ተማሪዎችም እፎይ ብለው ወደ ቤት ተበተኑ፡፡

ሲነጋ ግን ተመንሱስ የቀደመው ተማሪ አልነበረም፡፡ አንዳንዶቹ በድንጋጤ ራሳቸውን ሳቱ፡፡ ሌሎቹ ፈርተውት በረገጉ፡፡ የቀሩትም ወደፊት እዚህ ትምህርት ቤት መማር እንደ ሌለባቸው ወሰኑ፡፡ አንዳንዶቹ ግን ለተመንሱስ እጃችንን መስጠት የለብንም አሁንም ሌላ መፍትሔ እንፈልግ ሲሉ ተነሡ፡፡

እሺ ምን ይደረግ? የሚለው የሁሉም ጥያቄ ነበር፡፡ አንድ ተማሪ ሃሳብ አቀረበ፡፡ «ተመን ሱስን ለማጥፋት ብቸኛው መፍትሔ እርሱን ተካፍሎ መብላት ነው» አለ፡፡ መጀመርያ ሁሉም ደነገጡ፡፡ እየቆየ ግን መፍትሔውን እየተቀበሉት መጡ፡፡ በመጨረሻም ቢቀፋቸውም ተስማሙ፡፡

ተመንሱስ ታደና ሁሉም ተካፍለው በሉት፡፡ ተመንሲስ ተበልቶ አለቀ፡፡ የተረፈ ነገር አልነበረውም፡፡ ተማሪዎቹም ወደየቤታቸው ተበተኑ፡፡ ሁሉም ሲነጋ የሚሆነውን ለማየት ጓጉቶ ነበር፡፡ ሲነጋ ግን ተመንሱስ ትምህርት ቤት አልተገኘም፡፡ ቢጠበቅ ቢጠበቅ አልመጣም፡፡ ተማሪዎቹ ጮቤ ረገጡ፡፡ መምህራኑ ፈነጠዙ፣ አስተዳደሩ አለቀ በቃ አለ፡፡ የጥበቃ ሠራተኞቹ ተገላገልን አሉ፡፡ ወላጆች ዜናውን ሰምተው አረፍን ሲሉ ተሰሙ፡፡

ተማሪዎቹ ተረጋግተው ትምህርታቸውን በማከናወን ላይ እያሉ የተመንሱስ አባት ልጁን ፍለጋ መጣ፡፡ ክፍል ውስጥ ገብቶ ሲያየው ሊያገኘው አልቻለም፡፡ በአካባቢው ቢጠይቅም አየነው የሚል ሰው አጣ፡፡ በመጨረሻም በክፍሉ በረንዳ ላይ ቆሞ «ተመንሲስ ተመንሲስ ልጄ፤ የት ነው ያለኸው» እያለ በልቅሶ ሲጣራ በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ተማሪዎች ሁሉ «አባዬ አባዬ አባዬ እዚህ ነኝ» እያሉ ከክፍል እየወጡ የተመንሲስን አባት ከበቡት፡፡ ትምህርት ቤቱም ቀውጢ ሆነ፡፡ ይሉናል የየሺወርቅ አያት፡፡

አንድ ተመንሲስን እናጠፋለን ብለው አርባ ስድስት ተመንሲሶችን አፈሩ፡፡ የችግሩ መፍትሔ ከችግሩ የባሰ ሆኖ ተገኘ፡፡ ለምን?

ተመንሲስ የክፍሉ ችግር ነው፡፡ ክፍሉን የበጠበጠው እና ሰላም የነሣው ተመንሲስ ነው፡፡ ተማሪዎቹ የክፍሉን ዋነኛ ችግር ለይተውታል፡፡ ችግሩ የመጣው ከመፍትሔው ላይ ነው፡፡ የተመንሲስ ችግር የተፈታው ራሱ ተመንሲስ እንኳን ሠርቶት በማያውቀው ክፋት ነው፡፡ ተመንሲስ ዕቃ ሰርቋል፤ ወንበር ስቧል፤ ሰው አደባድቧል፡፡ ወንበር ደበላ ልቋል፡፡ ተመንሲስ ሰው አልቆራረጠም፤ ሰው ግን ቆራርጦ አልበላም፡፡

የተመንሲስ ክፍል ተማሪዎች ተመንሲስ በክፍሉ ከፈጠረው ችግር በላይ ነው በተመንሲስ ላይ ያደረጉት፡፡ ከተመንሲስ ባሱ እንጂ አልተሻሉም፡፡ ተመንሲስ ያመጣውን ችግር ከተመንሲስ በላይ በሆነ ጭካኔ ነው ሊፈቱት የተነሡት፡፡

ይህ ታሪክ ብዙ ጊዜ በሰው ልጆች ታሪክ ላይ ተከስቷል፡፡ ቅኝ ገዥዎቻቸውን ከቅኝ ገዥዎች በባሰ መንገድ አስወግደው፡፡ በኋላም ከቅኝ ገዠዎች የባሱ የሆኑ የድኻ አገር መሪዎች አሉ፡፡ አምባገነኖችን ከአምባገነኖች በባሰ መንገድ አስወግደው በምትካቸው አያሌ አምባገነኖችን የፈለፈሉ ሕዝቦች አሉ፡፡ ጭቆናን ከጨቋኞች በባሰ መንገድ አስወግደው አንድን ጨቋኝ በብዙ ጨቋኞች የተኩ ሀገሮች አሉ፡፡

አንዳንዴ እንዲያውም ያስወገድናቸው፣ ያሸነፍናቸው፣ የገለበጥናቸው ወይንም ደግሞ ድል ያደረግናቸው አካላት ያላደረጉትን ጭካኔ እና ኢፍትሐዊነት ገልባጮቹ ወይንም አስወጋጆቹ ሲያደርጉት ይታዩና ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ የሚባልበት ጊዜ አለ፡፡

ችግርን መለየት፤ ማስወገድ እና ነጻ መሆንን የመሰለ ነገር የለም፡፡ እግር አስወጋጁ ግን ከችግሩ ወይንም ከችግር አምጭው የተሻ የሃሳብ እና የሞራል ልዕልና ያስፈልገዋል፡፡ ችግሩን ያመጣውን አካል ማስወገድ ቀላል ነው፡፡ ከባዱ ችግሩን ያመጣው አካል የነበረውን አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ የሞራል ድቀት፣ የኅሊና ልሽቀት እና የክፋት መንገድ ማስወገዱ ላይ ነው፡፡

ልናስወግደው ወይንም ልናጠፋው በምንፈልገው ነገር ላይ ያለን ልዕልና ምንድን ነው? የኃይል ወይንም የሥልጣን፣ የገንዘብ ወይንም የዕድል ልዕልና ብቻ ከሆነ ያስወገድነውን ነገር መልሰን በባሰ ሁኔታ መድ ገማችን እንዲያውም ካስወገድነው ነገር በላይ ሆነን መገኘታችን የማይቀር ነው፡፡ ያለን ልዕልና የሃሳብ፣ የሞራል፣ የአመለካከት እና የችግር አፈታት መንገድ ልዕልና ከሆነ ግን በርግጥም ያንን ችግር እንዳይመለስ አድርገን መፍታት ይቻለናል፡፡

ሰዎችን በጭካኔ የገደሉ ሰዎች ፍርድ ቤት ገብተው፣ ተገቢው የእሥረኛ አያያዝ ተደርጎላቸው፣ መብ ታቸው ተጠብቆ፣ በሕግ ተከራክረው፣ በሕግ ተሸንፈው፣ ሕጉ የሚፈርድባቸውን እንዲቀበሉ የሚደረገው እነዚህ ሰዎች የሠሩትን ጭካኔ በመርሳት አይደለም፡፡ እነዚህን ሰዎች በእነርሱ ወይንም ከእነርሱ በባሰ ጭካኔ ማሸነፍ ስለማይገባ ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች በኅሊና እና በሞራል ልዕልና ማሸነፍ ስለሚገባ ነው፡፡ የእነዚህን ሰዎች የጭካኔ ሃሳብ በፍትሐዊነት ማሸነፍ ስለሚገባ ነው፡፡

ችግርን ስንፈታ መፍታታችንን ብቻ ሳይሆን ችግሩን በማይደግም መንገድ መፍታታችንንም ማየት አለብን፡፡ ለጊዜው መገላገል፣ እፎይታ ማግኘት እና እንዳናየው ማድረግ ችግሩን ከሥሩ ላይፈታው ይችላል፡፡ አንድ ሆኖ እንደ ተመንሲስ የበጠበጠን ችግር ከጊዜ በኋላ አርባ ስድስት ሆኖ ሊመጣ ይችላልና፡፡

አንዳንዴ የበጠበጠን ችግር ሲጠፋ ተወግዶ ነው ብለን ብቻ አናስብ፡፡ ተበልቶም ሊሆን ይችላል፡፡ ጉቦን ሲቃወም የኖረው ሰው ለምን ዝም አለ? የጉቦ ችግር ተወግዶ ነው ወይስ እርሱ ራሱ ጉቦ በልቶ? ያለ አግባብ ሥልጣን ስለመያዝ ሲናገር የነበረው ሰው የት ሄደ? ችግሩ ተወገደ ወይስ እርሱ ራሱ ሥልጣኑን በላው? ዲቪ የሚያመጣውን ችግር በተመለከተ ሲያስተምር የነበረው ሰው የት ሄደ? የዲቪ ችግር ተወገደ ወይስ እርሱ ራሱ ዲቪ ደረሰው? ስለ ዘረኛነት ክፋት ሲነግረን የነበረው የት ገባ? ዘረኛነት ጠፋ ወይስ እርሱም ዘረኛነቱን በላው?

ስንቶቹኮ ችግር ያሉትን ራሱን በልተው፤ ከችግሩም ብሰው፣ ችግሩንም አብሰው፣ ችግሩንም አብዝተው ተገኝተዋል፡፡

ተመንሲስን ማጥፋት ቀላል ነው፡፡ ችግሩ የማጥፊያው መንገድ አርባ ስድስት ተመንሲሶችን ያመጣ ጊዜ ነው፡፡

 This article is published on Addis Guday magazine.

40 comments:

 1. Wow, that is really deep! Dani, I envy you.

  ReplyDelete
 2. eski negerochn bekena lib temelkten bekinnet hulun endenaderg yirdan. seran bekfa sera tenkoln bekefa tenkol mashenef yichalal endalew gn gudatu kefit yekefa new yemihonew yihn lelaw biker begeza betarikachin ayitenewal.

  ReplyDelete
 3. 1.ልናስወግደው ወይንም ልናጠፋው በምንፈልገው ነገር ላይ ያለን ልዕልና ምንድን ነው? የኃይል ወይንም የሥልጣን፣ የገንዘብ ወይንም የዕድል ልዕልና ብቻ ከሆነ ያስወገድነውን ነገር መልሰን በባሰ ሁኔታ መድ ገማችን እንዲያውም ካስወገድነው ነገር በላይ ሆነን መገኘታችን የማይቀር ነው፡፡ ያለን ልዕልና የሃሳብ፣ የሞራል፣ የአመለካከት እና የችግር አፈታት መንገድ ልዕልና ከሆነ ግን በርግጥም ያንን ችግር እንዳይመለስ አድርገን መፍታት ይቻለናል፡፡

  2.ስንቶቹኮ ችግር ያሉትን ራሱን በልተው፤ ከችግሩም ብሰው፣ ችግሩንም አብሰው፣ ችግሩንም አብዝተው ተገኝተዋል፡፡


  Let us pray to get rid of devil's work for today

  ReplyDelete
 4. interesting story!!! the way you see things are quite impressive! Thank you

  ReplyDelete
 5. ርብቃ ከጀርመንJuly 26, 2011 at 11:00 PM

  በመጀመሪያ እንኩዋን ለቅዱስ ገብርኤል በአል በሰላም አደረሰህ ዳኒ እንዴት ውብና አስተማሪ የሆነ ጽሁፍ እንደሆነ! አወ እንዳልከው ችግሩን የምንፈታበት ዘዴ ችግሩን ከመፍታት ባለፈመልኩ ችግሩን እያሰፋውና በባሰሁኔታ በችግር እየተዋጥን እንደመጣን በየግዜው የምናየው ነው በቤተክርስቲያናችንምሆነ ባጠቃላይ ባገራችን ጉዳይላይ የመፍትሄ አሰጣጣችን ላይ ችግርእንዳለ የሚያስገነዝበን ጽሁፍነው ከእንሰሳትና እንዲሁም ከመላእክት አስበልጦ በአርያው የፈጠረን አምላካችን በሰጠን ብሩህ አይምሮ ተጠቅመን ችግራችንን ለመፍታት የመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የመላእክት ተረዳኢነት ይርዳን ላንተም የማስታዋል ጥበቡ አብዝቶ ይስጥልን !

  ReplyDelete
 6. ዳ/ን ዳኒ ጥሩ ተመልክተሃል። ይህን ጽሁፍ ሳነብ አገር ቤት እያለሁ ሰዎች አገራቸውን ትተው እንዳይወጡ አስተምር እና እመክር ነበር አሁን ግን እኔ እራሴ ዲቪውን በላሁትና ከሃገር ወጣሁ። ቢሆ ንም ግን እምነቴን እና ሃገሬን አልረሳም።

  ReplyDelete
 7. Joro yalew yisma!

  ReplyDelete
 8. Maferia !! Who do you think will listen your Teret!! We have seen your 'netela Zema' that you realosed together with 'Begu'

  ReplyDelete
 9. GIRUM EYETA NEW!!GOD BLESS YOU!!


  Daniel form marry land

  ReplyDelete
 10. D. Daniel selam new?I mean selam?? you used write about church ,preaching holly bible..what happen now?? you start writhing someting kind of poletics?? I'm not say it's bad but,we don't know you this way. you never know TEMENSUS...OOO
  BESEMEAB!.any way..

  ReplyDelete
 11. አንዳንዴ የበጠበጠን ችግር ሲጠፋ ተወግዶ ነው ብለን ብቻ አናስብ፡፡ ተበልቶም ሊሆን ይችላል፡፡ ጉቦን ሲቃወም የኖረው ሰው ለምን ዝም አለ? የጉቦ ችግር ተወግዶ ነው ወይስ እርሱ ራሱ ጉቦ በልቶ? ያለ አግባብ ሥልጣን ስለመያዝ ሲናገር የነበረው ሰው የት ሄደ? ችግሩ ተወገደ ወይስ እርሱ ራሱ ሥልጣኑን በላው? ዲቪ የሚያመጣውን ችግር በተመለከተ ሲያስተምር የነበረው ሰው የት ሄደ? የዲቪ ችግር ተወገደ ወይስ እርሱ ራሱ ዲቪ ደረሰው? ስለ ዘረኛነት ክፋት ሲነግረን የነበረው የት ገባ? ዘረኛነት ጠፋ ወይስ እርሱም ዘረኛነቱን በላው?

  woy gud America gebetewal degemo lela zemare yezew tenestewal aluleh be bet kehenetum be bet mengestum
  ke Atlanta tazabew

  ReplyDelete
 12. Thank you D/n Dani
  It is excellent view. I like it.
  I have seen so many articles with very deep messages.I want to raise one question to all readers. Are we tying to apply at least some part of the message in to practice???????? Change start from ourselves. We have to see things from different angles. I believe the objective of this blog is to make changes in seeing issues which help us to change ourselves and then our country.

  D/n Dani is investing his time, mind and money to do his part to us and to his country.We have to repay his investment by practicing the idea he raise.

  ReplyDelete
 13. Joro yalew yismma, semitom tegbarawi biyadergew melkkam new.

  Egziabhar Ybarkih Dani,

  Temesgen, Dire Dawa.

  ReplyDelete
 14. Betam Astemary new

  ReplyDelete
 15. ሰላም ዲ/ን ዳንኤል አምላከ ቅዱሳን ሰላሙን ያብዛልህ!!!!

  አንድ ተመንሲስን እናጠፋለን ብለው አርባ ስድስት ተመንሲሶችን አፈሩ፡፡ የችግሩ መፍትሔ ከችግሩ የባሰ ሆኖ ተገኘ፡፡ ለምን?

  አሁን ያለዉ ችግር የማስወገጃ ዘዴ ይህ መሆኑ ያሳዝናል፡፡
  ምድራችን በብዙ ተመንሲሶች እየተሞላች ነዉና
  አሁን ያለዉ ችግር የማስወገጃ ዘዴ ይህ መሆኑ ያሳዝናል፡፡
  ምድራችን በብዙ ተመንሲሶች እየተሞላች ነዉና

  ReplyDelete
 16. Interesting issue, thanks,

  ReplyDelete
 17. ዳኒ የሚገርም እይታ ነው፡፡
  እኔ ያየሁትንና አሁን ያለውን እውነታ ላጫውታችሁ፡፡ በአንድ ቦታ ላይ ያሉ በእድሜም በደረጃም ትልቅ የሚባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ አንዱ አንዱን ሲጥለው ክብሩ ሞራሉ ገሎ ማንነቱ እንዲንኮታኮት እንዲሸማቀቅ አድርጎ ያባርረዋል እሱም በተራው ቦታውን ሲይዝ ያኛው ካጠፋውና ከሰራው ክፋት በላይ ከታች ያለው ሰው ላይ በማን አለብኝነት ይፈጽማል፡፡ ነገር ግን የስልጣን ጊዜውም የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው፣ አወዳደቁም ከበፊተኛው እጅግ የከፋ ነው፡፡ ሶስተኛውም ይሄን ጥሎት ሲተካ ከሁለቱ የከፋ ይሆናል፡፡ ይሄ ታዲያ ወንበሩ ነው ወይስ ተመንሲስን በልቶ እጥፍ አድርጎ መውለድ

  ማሂ

  ReplyDelete
 18. ያ ተመንሲስ እኔ እሆንን?

  ReplyDelete
 19. አንዳንዴ ቺግሮችን ነቅሶ ማውጣት መፍትሄውን ከ መጠቆም ይቀላል። አኔ በ አዛ ቦታ ላይ ብሆን ምን አወስን ነበር? አንዴት አይነት አካሂአድ ነበር የምጠቀመው? ብሎ መጠየቅ አና ስህተት ሲኖር መፍትሄው ይሄ ነበር ብሎ ማቅረብ የመሰለ ትልቅ ነገር የለም። አና ዳን መፍትሄም ይጠቆም!!!!

  ReplyDelete
 20. ዲ/ን ዳንኤል አምላከ ቅዱሳን ሰላሙን ያብዛልህ!

  ለሚማርና ለሚያስተውል ጥሩ አስተማሪ ጽሑፍ ነው::

  እግዚአብሔር ይስጥልን::

  ያለሜ

  ReplyDelete
 21. please brothers, at least let us appreciate such wonder man like dani.
  thank you dani

  ReplyDelete
 22. Dear Anonymous at 12:44,

  Would you mind if you try to have a little bit of kindness which is an exact opposite of retaliation? If you have a point to make try to make it in a more civilized and more Christian way. Otherwise, you will be one of those guys who ate temensus.

  ReplyDelete
 23. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel
  To the person who wrote at 12.44AM, I just want to mention that millions of people around the world will listen to Dn. Daniel's sibket not as you call it teret. Eventhough he tells teret, we won't be tired to listen to him because he is one of those brothers who made a big difference in our generation's christian life. That's the reason why his blog is visited by many around the world. By the way, INCLUDING YOU!!!

  ReplyDelete
 24. ኃ/ገብርኤል ከአራት ኪሎJuly 27, 2011 at 6:44 PM

  ዲ/ን ዳንኤል ሰላም ለአንተ ይሁን።
  እንደው አሁን በተለያዩ የስራ ወይም የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያለንና በእኛ አካባቢ የነበሩትን ተመንሲሶችን የበላን ሰዎች ብንቆጠር ስንት እንሆን ይሆን??? እስካሁንም ያልታወቅነው ስላልበላናቸው ሳይሆን አባቶቻቸው ፍለጋ ስላልመጡ እኮ ነው። በየእድሩ ፣እምነት ተቋማቱ፣ በየማኅበራቱ፣ በየፍርድ ቤቱ፣ በየፓርላማው፣ በተለያዩ የግል እና የመንግስት ድርጅቶች ስንት ተመንሲሶች ይሆን የተበሉትና እና በዚያው መጠን የተባዙት?

  ReplyDelete
 25. thank you D/n dani

  ReplyDelete
 26. የዚህ አባዜ ተጠቂ እኔ እራሴው ሳልሆን እቀራለሁ!! ተመንሲስን ለማጥፋት የምጠቀመው ስልት የማይረባ ነው። ስር ነቀል የሚባል ነገር የተገለጠልኝ አይመስለኝም። ለጊዜው ከለቀቀኝ በቃ ከራሴ የወረደ ይመስለኛል። ምን አልባት በዚህ ብገልጠው ይገባችሁ ይሆን። ሲያም ፔን ኪለር እንደ መውሰድ ቁጠሩት። ፔን ኪለሩ የወሰደውን ሰው ያደነዝዝና በሽታው የለቀቀው ያስመስለዋል። ግን እኮ በሽታው አለ አብሮ ለመኖር እረዳው እንጂ። የኔውም እንዲሁ ነው። እግዚአብሔር ይስጥህ---ተመንሱስን ለማስወገድ ቆም ብዬ እንዳስብ ትልቅ ትምህርት ሰጠኸኝ።

  ReplyDelete
 27. በጣም ጥሩ ምልከታ ነው ዲ/ን:: ተባረክ:: Truth always hurts ይላሉ:: ክርስትና እኮ ስለ እውነት መኖርም ነው:: ማስተማርም ነው:: እየጎመዘዘንም ቢሆን እንጋተዋለን:: ሀገርን; አለምን(our planet)ረስቶና ጥሎ መኖር አይቻልም (የመኖር ጸጋ ከተሰጣቸው ውጭ ላለነው):: ስለሰው ልጅ ሰላም ማስተማር ትልቅ ጸጋ ነው:: በርታ:: Anonymous at 12:44:የምትገርም "ክርስቲያን" ነህ:: ራስህን መርምር:: He never, ever be Maferia like you. This is not the way Tewahido is teaching. ለመነ አስለመነ..አማላጅ ላከ..አልሰማ ብለው በሚዲያ ከሂዱ መልስ መስጠት ነዉር አይደለም:: እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር ነው ክርስትና::

  ReplyDelete
 28. To Anonimous at 12:44 AM:

  Did u appear here 4 z 1st time w zis comment?, or r u regular reader?
  U r so unique.
  R u an ethiopian in ur blood?
  Hv u really grown up breast feeding of ur mam? or blood feeding?
  God c & breath in 2 ur brain!
  Beg others 2 pray 4 u not 2 die b/r u Sob of ur Dead comment!
  (AGE) z 1st time w zis comment?, or r u regular reader?
  U r so unique.
  R u an ethiopian in ur blood?
  Hv u really grown up breast feeding of ur mam? or blood feeding?
  God c & breath in 2 ur brain!
  Beg others 2 pray 4 u not 2 die b/r u Sob of ur Dead comment!
  (AGE)

  ReplyDelete
 29. I am really amazed by some people who do not be happy when someone works for other for free, but if you ask what you do they do not have any single contribution.
  May be bad thing , gossiping and sins. By the way we always be positive thinker for our life to be changed
  and also we could tell the mistake of others to keep them away from their mistake.
  We have to always know what we are doing???????, why????????, what will I get spiritually ????????
  our mind will tell the truth and listen.common sense.

  otherwise we have to concentrate on ourselves to be changed first.

  Sharing negn

  ReplyDelete
 30. ለ/@/ July 27, 2011 12:44 AM ጸሐፊ ለምን ተነካን ማለት ጥሩ ነው? እኛ ምነው ለዘመናት ሰለ ስንቱ አልን አደለ እንዴ? ከስህተቱ የማይማር ፈንጅ አምካኝ ብቻ ነው :: አሁንም ሊነገረን ይገባል ከጸሎትና ከእንባ ጋር::


  ዳኒ ይህንን ታሪክ ግቢ ገብርኤል ሰ/ት/ቤት በልጅነቴ መስማቴን አስታውሳለሁ:: ጥሩ ማስታወሻ ግሩም እይታ !

  ReplyDelete
 31. D/n Daniel:

  I am a member of MK and I believe you have recently raised on DS the issues that have been a concern to me for many years. Will you re-write them and open the ideas for discussion here? I know many people including MK members and Sira asfetsami wants not to discuss. But it is good if it is open for discussion.

  Best!

  ReplyDelete
 32. Really nice article. I was planning to solve my personal problem in wrong way. You save me on the spot. Egziabhere yistelign.

  ReplyDelete
 33. Dn.Danial qale hiwot yasemalen Egziabhar stegawen yabzalhe.

  ReplyDelete
 34. For some readers,

  As you respect Daniel's article, you have to respect other's comment too. It will be helpful for Daniel in various ways and for readers to see ideas from different perspectives. That is why we have to comment and tell our opinions; to learn from each others. Don't always expect positive comments; they will make this media one sided. Be your self and say something in your mind in an Ethiopian manner.

  Please, respect everyone's comments and try to see them in a positive way.

  By the way, I love the way Daniel present stories including this one.

  God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 35. እንዲህም አለ ለካ። ለመጀመሪያ ጊዜ ችግርን ባደባባይ ማዬት ምን ያህን እንደሚያስደነግጥ ላንባቢው ሁሉ ትቸዋለሁ። ቆዬት ብየ ሳስበው ግን ምንም ችግር የለውም። ሁሉም በፍቃደ እግዚአብሔር የሚከናወን ነው። ማህበረ ቅዱሳን የተቋቋመው በእግዚአብሔር ፍቃድ ነው። ያ ባይሆን ብዙ ጠመዝማዛ መንገዶችን አልፎ ለዚህ ባልበቃ ነበር። አሁን የሚፈራና ብዙዎች አይናቸውን የአፈጠጡበት ማህበር ነው። በተለይ ከመናፍቃኑ ጎራ ምን ያህል ጥርስውስጥ እንዳለ እነሱ እራሳቸው ያውቁታል። ማህበረ ቅዱሳን ከተመሰረተበት ጀምሮ ስላደረገው የቤተክርስቲያን አስተዋጽኦ ማንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚናገር ይመስለኛል። ለምሳሌ እኔን ከመናፍቃን ጉሮሮ ፈልቅቆ ያወጣኝ ማህበር ነው። ያኔ ገና ምኑንም ሳላውቀው በመናፍቃንን የተከበበ ዩኒቨርስቲ ስገባ ከማጡ ውስጥ ያወጣኝ ማህበረ ቅዱሳን ነው። ዛሬ በራሴ ድክመት ለማህበሩ አንዳች ነገር አላደረግሁም። ወደ ዕለት ከዕለት ኑሮዬ ዞርኩኝ። ምን አልባትም ቤተክርስቲያን አሁን ካለችበት ችግር አንጻር የሚጠበቅበትን ያህል እንዳይሰራ ካደረጉት ወንድሞች አንዱ ነኝ ብዬም አስባለሁ። እኔ እና መሰሎቼ ገብተን በሚፈልገን ነገር ብናግዝ ኑሮ ለዚህ ባልበቃ ነበር። ለእዚህ እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ። እንዲህ አይነት ስር የሰደደ ነገር ሳነብ ውስጤ አነባ። ደማሁም። ወንድሞቼና እህቶቼ ጊያዊ ማንቀላፋት ውስጥ ስለገቡ የማስተማሪያ አርጩሜ በማህበሩ ወረደበት። ሰይጣናዊ ስራቸውን ያጋለጠባቸው ግለሰቦች ይህን ማህበር አንዳች ነገር ለማድረግ ሁሌም ይደክሙና ሲሰሩ ነበር። ማህበሩ ካልጠፋ ስራቸውን መቀጠል እንደማይችሉም ባደባባይ አንብቤላቸው አውቃለሁ። እናም እነሱ አጋጣሚውን ተጠቅመው አቅጣጫ እንዳያስቀይሱ ምን ይደረግ? አሁንም እንዴት እንደሚያራግቡት የአደባባይ ሚስጢር ነው። የአመራር አባላት ያለባችሁን ችግር በወ.ዘ.ተ ሳታስቀምጡ ተነጋገሩበት፤ራሳችሁን መርምሩ፤ተወያዩ። የሐሳብ ፍጭት ወደ ተሻለ አቅጣጫ ያመራል። ስህተት የሰራ ባደባባይ ይቅርታ እየጠየቀ ወደ ስራው ይመለስ። ድርቅ ብሎ ምንም ችግር የለም የሚል ካለ ግን ሌላ ነገር አለ ማለት ነው። ሁላችንም ያሰባሰበን የቤተክርስቲያን፤የእግዚአብሔር ቤት ጉዳይ ነው። መሰባሰባችን ለሌላ ለማንም አይደለም። ለሌላ ተሰባሰቡ ከተባልን በግልጽ ይነገረን። እኔ ዲን ዳንኤል ፍጹም ነው ያኛው ደግሞ ችግር አለበት ማለቴ አይደለም። ነገር ግን ቢያንስ ያለውን ችግር በግልጽ ነግሮናል። ለምን አደባባይ ወጣ። ይህ ችግሩን የሰሙ ሰዎች በወቅቱ ምላሽ አለመስጠት ይሆናል። ምን አልባት አኮ ባደባባይ ተነግሮ ወደ ተሻለ ነገር ሊሄድም ይችላል። ማን ያውቃል? ችግሩን እንዴት እንፍታው ወደሚለው እንሂድ። ችግር የለም ብሎ ብቅ የሚል ካለ፤አደጋ አለ ማለት ነው። መሸፈን የመጨረሻው ግቡ ምን እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን።ስለዚህ መነጋገርና መወያየት ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን አንዘንጋ
  አብርሃም

  ReplyDelete
 36. It reminds me of a discipline committee at a Gov't office in Bahirdar. It's hard to sort the wolves among the sheep's as the wolves tend to wreak havoc easily. Hence, I am always yearn to know why cruelty is the default setting in most of us? Why we failed to work to injure no man, but to bless all mankind??

  Te Tena Tabia folk (Kebele 03)
  Bahirdar

  ReplyDelete
 37. ርእሱን አይቼው ሳበቃ በመጀመሪያው ቀን ላይ ለማንበብ ብዙም አልፈለግሁትም ነበር፡፡ነገር ግን በሌላ ቀን በትእግስት ሳነበው ምን ያህል ጥለቅ ቁምነገር እንዳለው ለመረዳት ቻልኩ፡፡ምን ያህል ጥልቅ ሃሳብና መልእክት ያለው እይታ እንደሆነ ለመግለፅና ለማድነቅ እፈልጋለሁ፡፡በዚህም ብቻ አላበቃም ይህ ፅኁፍ እንዳስታውስ ያደረገኝን ሁለት አንኳር ነጥቦች ለማንሳት እፈልጋለሁ፡፡አንደኛው ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላና ከዚያም ተከትሎ ካለው የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ የዓለማችን መነጋገሪያና ከፍተኛ ፈተና የሆነው ‘ሽብርተኝነት’ የተባለው ነገር ነው፡፡ሁለተኛው ደግሞ በስልጣን ላይ ከ40 ዓመታት በላይ ሊቢያን የገዙትንና አሁንም በፈታኝ ሁኔታ ወስጥ ያሉትን(ፈተናው ሊቢያንና ህዝቧን ይጨምራል) የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊን ጉዳይ ነው፡፡ሁለቱንም ከላይ ያነሳኋቸውን ነጥቦች በቀጥታ በሳጥናኤል ልጅ ተመንሱስ የመመሰሉን እጅግ በጣም አከራካሪ ነገር ለጊዜው እንተወውና(ወይንም ቢያንስ ለጊዜው ከአንባቢ ጋር ሌላ አላስፈላጊ የህሊና እሰጥ አገባ ውስጥ ላለመግባት ስል ለጊዜው በዚህ ተመንሱስ ሊመሰሉ ይገባል በሚለው ልስማማና) እነዚህን በተመንሱስ የተመሰሉ ሁለት ችግሮችን መፍትሄ ለመስጠት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃውችና አጣቃላይ አቀራረቦች ግን ከዚህ ፅኁፍ ጋር በተወሰነ ተመሳሳይ ሆነውብኛል፡፡
  አሸባሪነትን ለመዋጋት በሚል ካላፉት 10 ዓመታት በላይ ጀምሮ እየተደረገ ያለውና አሁንም እየተደረገ ያለው አጣቃላይ ፈታኝ እንቅስቃሴና እርምጃ በራሱ አሸባሪነት የሚባለው ችግር ካመጣው ችግርና ጣጣ በበለጠ ዘርፈ ብዙ በሆነ መልኩ አሸባሪ እየሆነ እየመጣ ነው፡፡Therefore, from time to time the over all war on Terrorism is endlessly becoming and escalating to be even more terrorizing than the Terrorism itself..ስለዚህም “አሸባሪነት” የሚለውና ይህንንም ተከትሎ በተቃራኒው ያለው “አሸባሪነትን መዋጋት” የሚለው ፅንሰ ሃሳብና ችግር እጅግ ውስብስብና እጅግ አሻሚ ትርጓሜ ያላቸው የአለማችን ፈታኝ ነገሮች እየሆኑ ሊመጡ ችለዋል፡፡
  ሌላው የኮሎኔል ጋዳፊ አምባገነንነትና ይህንን አምባገነንነት ለማስቆም በምእራባውያንና በኔቶ የተወሰደውና አሁንም በቀጣይነት እየተወሰደ ያለው አጠቃላይ እርምጃ ነው፡፡ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ ላለፉት 40 ዓመታት ያህል የኮሎኔል ጋዳፊ አምባገነንነት በሊቢያና በሊቢያ ህዝብ ላይ የፈጠረውን አጠቃላይ ጥቅምና ጉዳት ፍርዱን በዋናነት በመጀመሪያ ደረጃ ለራሱ ለሊቢያ ህዝብ የሚተው ነገር ነው፡፡ነገር ግን አንባቢ በግርግርና በስማ በለው ሳይሆን በሰከነ እይታና ማስተዋል በጥሞና ተከታትሎ የመሰለውን የራሱን ፍርድ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ አሁን ይህንን በተመንሱስ እየተመሰለ እየቀረበ ያለ ችግር የተባለ ነገር መፍትሄ ለመስጠት ተብሎ በሰብአዊ እርዳታ ሽፋን “No Fly Zone” ተብሎ ተጀምሮ ከዚያ በኋላ ግን መልኩን ቀይሮ በምእረባውያንና በኔቶ ቀን በቀን እየተፈፀመ ያለው ድብደባና በዚህም እየተፈፀመ ያለው አሳዛኝ የህይወትና አጠቃላይ የመሰረተ ልማት ውድመት ምን የሚሉት መፍትሄ ነው?እኔ ይህ ክስተትትምህርት ሊወሰድበት የሚገባና ከማያውቁት መንፈስ ቅዱስ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል ወይንም ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለወጥ የሚለውን የአበው አባባል የሚያስተውሰኝ ነው፡፡በእኔ እይታ ከላይ ባሉት በሁለቱም ጉዳዮች ላይ ችግር ለተባለው ነገር መፍትሄ ነው ተብሎ እየተሰጠ ያለው ነገር በራሱ ከችግሩ የከፋ ሌላ የባሰ ችግር እየሆነ ነው የመጣው፡፡ስለዚህም ዛሬ የሀገራችንና የአጠቃላዩ አለምም እጅግ ፈታኝ ነገር አንዱ ዳንኤል እጅግ በሚገርም የረቀቀ አስተዋይ አቀራረብ ያነሳው ይህ ክስተት ነው፡፡
  እናም ቆም ብለን በሰከነ መንገድ በጥሞና እናስተውል፡፡

  ከምስጋና ጋር፡፡

  ReplyDelete