Friday, July 22, 2011

ረጅም ዕድሜ ለማንዴላ! ረጅም ዕድሜ ለሰው ልጆች መብትና ነፃነት ለሚታገሉ ሁሉ!!!


በፍቅር ለይኩን -ከደቡብ አፍሪካ
የ93 ዓመቱ አዛውንትና የነፃነት ታጋይ የኔልሰን ማንዴላ የልደት በዓል ሰኞ ሐምሌ 18 2011 እ.ኤ.አ በዚህ በደቡብ አፍሪካ በታላቅ ስሜት ነው የተከበረው፡፡ በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ የዜና አውታሮች እና ዓለም አቀፍ የመገኛኛ ብዙሃን ለእኚህ ታላቅ አባት የእንኳን አደረሰዎ መልእክትና የመልካም ልደት ምኞት መግለጫ ተጨናንቆ ነበር የዋለው፡፡
መሰረቱን በዚህ በደቡብ አፍሪካ ያደረገው DSTVም በዕለቱ የማ ንዴላንና የትግል አጋሮቻቸውን የነፃነት ተጋድሎ የሚያዘከሩ ሁለት ጥናታዊ ፊልሞች አቅርቦ ነበር፡፡ በሀገሪቱ ከሚታተሙና በርካታ አንባቢ ካላቸው ጋዜጦች መካከል ታይምስ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው በመላው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ታዳጊ ህፃናት ለኔልሰን ማንዴላ ሰኞ እለት በትምህርት ቤታቸው 93ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው እንኳን አደረስዎ የዘመሩት መዝሙር ከህጻናቱ ፎቶግራፍ ጋር አውጥቶት ነበር፡፡ የመዝሙሩ መልእክት የህፃናቱን ከልብ የሆን ፍቅራቸውን የሚያነጸባርቅና በእጅጉ ልብን የሚነካ ነው፡፡
 በዛ የሰው ልጅ በቆዳው ቀለም በሚፈረጅበትና የአፓርታይድ ዘረኛ መንግስት መብታችን ይከበር ብለው በወጡ የስዌቶ ጨቅላ ህፃናት ተማሪዎች በነጭ ፖሊሶች ጥይት ደማቸው የውሻ ደም በሆነበት ሀገራቸው፣ ዛሬ በአዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያለምንም የዘር ልዩነት ለነፃነትና ለዚህ እኩልነት ያበቋቸውን ኔልሰን ማንዴላን መልካም ልደት በሚል ጥኡም ዜማ እንዲህ ዘመሩላቸው፡-
Madiba, Halala
Happy birthday to you!
Happy birthday to you!
Happy birthday dear Tata![1]
We love you Tata
                                                   We love you Tata
Nelson Mandela. Ha hona
Ya tshwanang le wena (there is no like you)
Yeep yeep!
Hooray!
በኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን አስተባባሪነት በዚህ በደቡብ አፍሪካ ማንዴላ ልደት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ነበር የዋለው፣ በኢንግላንድ፣ በአቡዳቢና በሌሎች ሀገሮችም ጭምር የልደት ቀናቸው የተከበረው በበጎ ፈቃደኝነት ወላጅ አልባ ህፃናትን በመጎብኘት፣ የህክምና እርዳታ በመስጠት፣ አረጋውያንን በመጎብኘትና በመሳሰሉት በጎ ተግባራት ነው፡፡ በኢስተርን ኬፕ የትውልድ ቀዬቸው በሆነችው በቁኑ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የቀድሞ ባለቤታቸውና የትግል አጋራቸው ዊኒ ማንዴላ እነዲሁም የANC ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በድምቀት ነበር የማዲባ 93ኛ የልደት በዓል የተከበረው፡፡
በኒዮርክ የሚገኘው የመንግስታቱ ድርጅትም በጽ/ቤቱ በእለቱ የማንዴላን ፖለቲካዊ ሰብእናና የነፃነት ትግል የሚዘክር አውደ ርዕይ አዝጋጅቶ ነበር፡፡  ጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫም፡- The exhibition is a special dedication to Mr. Mandela in part as a commemoration of his ninety-third birthday on July 18 and most importantly, for his selfless devotion of his life “to the service of humanity - as a human rights lawyer, a prisoner of conscience, and an international peacemaker.”

ከተለያዩ የዓለማችን መሪዎችና ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የእንኳን አደረስዎ መልእክት ተቀብለዋል፡፡ በእለቱ ደቡብ አፍሪካን ሲጎበኙ የነበሩት የብሪትሹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ባሰተላለፉት የእንኳን አደረስዎ መልእክታቸው፡-
"President Mandela is an inspiration to the world, and as we celebrate his birthday and look back at just how far South Africa has come, so I believe we can look forward with confidence to an even better future for South Africa and her people,"

 የዩናይትድ ስቴትሱ ባራክ ኦባማም በራሳቸውና በአሜሪካ ህዝብ ስም ባስተላለፉት የመልካም ልደት ምኞት መግለጫቸው፡-
“Mandela is a beacon for the global community and for all who work for democracy, justice and reconciliation. His legacy exemplifies wisdom, strength and grace, and on the anniversary of his birth we salute the example of his life"
ማንዴላ ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ እኩልነትና ነፃነት የታገሉ የፍቅርና የይቅርታ ሰው መሆናቸውን በዚህ በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ ፍሪ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሬክተር የሆኑ ፕሮፌሰር ጃነሰን በጆሐንስበርግ ለሚታተመው ታይምስ ለተባለው ጋዜጣ በላኩት ጹሑፍ፡-
“…affectionately known to all South African by his clan name, Madiba, and Tata (isi Xhosa for Father), Mandela represents many things: the importance of standing by your own beliefs, dignity, equality, humility, strength, determination, selflessness and above all, forgiveness…
የተባበሩት መንግስታት በ2009 በዓለም አቀፍ ደረጃ የማንዴላ ቀን እንዲከበር ወስኗል፣ በዚህም ቀን መሪዎች ለዜጎቻቸው እኩልነትና ነፃነት የማንዴላን የሰላም፣ የአንድነትና ይቅር ባይነትን መርህ በመከተል ዓለማችን የሰው ልጆች ፍትህ በማጣት የሚሰቃዩባት፣ በአምባገነኖች የአገዛዝ ቀንበር ፍዳቸውን የሚቆጥሩበት የሰቆቃ ዘመን ሚያበቃበት እንዲሆን ነበር የእኚህ የሰው ልጆች መብት ታጋይ፣ የሰላምና የፍቅር-የይቅርታ ተምሳሌት የሆኑት የኔልሰን ማንዴላ ቀን እንዲከበር የወሰነው::
አሰገራሚው እውነታ ግን በጣት ከሚቆጠሩ የአፍሪካ መሪዎች በስተቀር ሀገራችንን ጨምሮ  የእኚህን የነፃነት ታጋይ ከማሞካሸት በስተቀረ ህዝባቸው የነፃነት አየር ይተነፍስ ዘንድ ፍትህና ዲሞክራሲ ይሰፍን ዘንድ ፍቃደኞች አለመሆናቸውንና እነዲሁም ላለፉት የትውልዱ የታሪክ ስህተቶች ለአንድነትና ለሰላም ሲባል ስህተቶችን በይቅርታ ለመዝጋት የሚችል የመንፈስ ልእልና ላይ ገና ያልደረሱ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ታዝበናል፡፡
ለ27 ዓመታት በዘረኛው የአፓርታይድ መንግስት ቀዝቃዛውን የአትላንቲክ ውቅያኖስ ተጎራብቶ በተገነባው በሮቢን ደሴት ላይ በግዞት የታሰሩት ማንዴላ ከእስር በተፈቱ ማግስት ያደረጉት ነገር ቢኖር ህዝባቸውን ለበርካታ ዓመታት ለሞት፣ ለውርደትና ለሰቆቃ ከዳረገው የአፓርታይድ ዘረና መንግስት መስራችና አቀንቃኝ ወደነበሩት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ሟች ፕሬዝዳንት ሚስት ዘንድ በመሄድ በቀድሞ የአፓርታይድ ዘመን አሁን በሕይወት የሌሉት ባለቤታቸው በሳቸውና በህዝባቸው ላይ ስላደረሱባቸው ታሪክ ለማይረሳው ግፍ ከልብ የሆነ ይቅርታ ማድረጋቸውን በአካል በሟች ፕሬዝዳነቱ ቤት ተገኝተው በሕይወት ለነበሩት ለባለቤታቸው፣ ለህዝባቸውና ለዓለም በማወጅ ለሀገራቸው አዲስ ታሪክ ምእራፍን ከፈቱ፡፡ ዛሬይቱ ደቡብ አፍሪካ ሰላምና ብልጽግና ማንዴላና የሳቸውን መርህ የተከተሉ በሳል የፖለቲካ አመራሮች የወሰዱት ለሰው ልጆች መብት መከበርና ፍትህ መስፈን በጽናት መቆም ነው፡፡
ዛሬ በሀገራችን ትውልድ እርስ በርሱ የሚወቃቀስበት፣ ዘርና ጎሳ ለይተን እርስ በራሳችን ለበቀል የምንፈላለግ ወደ መሆን ዘግናኝ የታሪክ ምዕራፍ የተሻገርነው በከፊል በሀገራችን ታሪክ ለዘመናት የነበሩ ነገሥታትና መንግስታት ልዩነቶቻቸውን ይፈቱ የነበሩት ደም በማፍሰስ ብቻ ስለነበር ነው፡፡ በደልን በይቅርታ ሽሮ ለሀገርና ለህዝብ ሰላምና አንድነት ሲሉ ይቅር መባባል በእኛ ታሪክ ውስጥ ውርደት ከውርደትም በላይ የሞት ሞት ነው፣ በፍቅር መሸነፍ በእኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ፈጽሞ የለም፣ ሰለዚህም የመበላላትና የመጠፋፋት ታሪካችን ዛሬም ቀጥሏል፡፡ ገና ያላወራረድነው የደም ካሳ በብዙዎቻችን ልቡ ውስጥ እያቃጨለ ነው፡፡
ማዲባ በፍቅር በመሸነፋቸው ሀገራቸውን ካነዣበበባት የእርስ በርስ እልቂት ለመታደግ ችለዋል፣ ምንም እንኳ የዘረኝነቱ አበሳ አሁንም ድረስ ፈጽሞ ያልጠፋ ቢሆንም፣ ጥቁሩ ድቡብ አፍሪካዊም ከነጮቹ አነፃር ሲታይ በኢኮኖሚ ቀውስ፣ በድህነት የሚቆራፈድ፣ በስራ እጦት የሚስቃይና ችግሮቹ ሙሉበሙሉ የተቀረፉ ባይሆንም የትናትነዋ ድቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ የዘረኝነትና የመለያየት ግንብ ፈርሶ ያለምንም የቆዳ ቀለም ልዩነት ሰዎች ሁሉ በነፃነት እና በእኩልነት መኖር ይችሉ ዘንድ ማንዴላ ለዲሞክራሲያዊ ሥረዓት፣ ለፍትህና ለነፃነት የከፈሉት መስዋዕትነት ማንዴላን በብዙዎች ልብ እንዲታሰቡና ከልብ በመነጨ ፍቅር ባወጁት የይቅርታ መንፈስም የደቡብ አፍሪካውያንና የዓለምን ህዝብ ወዳጅነትና ፍቅር ማግኘት ችለዋል፣ ከቂም በቀል ምን ትርፍ አለ- እርስ በርስ ከመጠፋፋትና ከመበላላት በስተቀር፡፡
በዚህ የማንዴላ የ93 ዓመት የልደት በዓል በተከበረበት ቀን ከኔልሰን ማንዴላ ጸረ አፓርታይድና ከመላው ጥቁር ህዝብ የነፃነት መራር ተጋድሎ ጋር የጠበቀ ታሪካዊ ትስስር ያላት ሀገራችን ኢትዮጵያን ዛሬ ያለችበትን ፖለቲካዊ፣ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥንቅጥ ሳስብ መቼ ይሆን በሀገራችን ለህዝብ መብት መከበር የሚሟገት፣ ለፍትህና ለነፃነት የሚቆም እንደ ማንዴላ የይቅርታና የፍቅር ልብ ያለው በሳል የፖለቲካ መሪን የምንታደለው በማለት ራሴን ጠየቅሁት፡፡ ይሄ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አንገብጋቢ የወቅቱ ጥያቄ እንደሆነ እገመታለሁ፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ጥናት ኮንፈረስ በተካሄደበት የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በዋናው ግቢ የኔልሰን ማንዴላ መንገድ መሰየሙን አሰታወሳለሁ ይሄ ይበል የሚያሰኝ ነው፣ ግና በዛ አንጋፋ የትምህርት ተቋም እንኳ፤ የማንዴላ መርህ የሆኑት ነፃነት፣ ፍትህ፣ መብትና እኩልነት ገና በሰማይ ላይ የተንጠለጠሉ የተሰፋ ዳቦዎች ናቸው፡፡ የሚበዙት ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞቻችን በዘረኝነት የሚማቅቁ፣ ተማሪዎቻቸውም እርስ በርሳቸው በብሔርና በዘር ተከፋፍለው በጎሪጥ የሚተያዩበት የጥላቻና የመለያየት ነጋሪት የሚጎሰምባቸው ተቋማት ወደመሆን ከተሸጋገሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
ገና ከጠዋቱ በህዝቦች የፍትህና የዲሞክራሲ ጥያቄ የተነሳ የብዙ ወጣት ምሁራን ደም እንደ ውኃ የጎረፈበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለሰው ልጆች መብት መከበር፣ ለፍትህና ለሰላም መራር ትግል ባደረጉት በኔልሰን ማንዴላ ስም መንገድ ከመሰየም ባሻገር ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥረዓት ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት የሚቆሙ ቆራጦች የሚወጡበት ይሆን ዘንድ ያሰፈልገዋል፡፡ ሀገራችን ወደተሻለ እድገትና ብልጽግና እንድትመጣ፣ ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት ግንባር ቀደሙን ሚና መጫወት ያለባቸው የሀገራችን የትምህርት ተቋማት ከዘረኝነትና ከጎሳ ድንበር አልፈው የሚያስቡ የለውጥ ሐዋርያት የሆኑ ወጣት ሙሁራን ይወጡበት ዘንድ ነፃነት ሊታወጅላቸው ስፈልጋቸዋል፡፡   
ረጅም እድሜ ለሰው ልጆች መብት መከበር፣ ለፍትህና እኩልነት ለሚታገሉ ሁሉ!
እግዝአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!          


[1] Tata is ‘Father’ in Xhosa Language.

20 comments:

 1. ረጅም እድሜ ለሰው ልጆች መብት መከበር፣ ለፍትህና እኩልነት ለሚታገሉ ሁሉ!Yes! Yes!Yes!
  ሀገራችን ኢትዮጵያን ዛሬ ያለችበትን ፖለቲካዊ፣ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥንቅጥ ሳስብ መቼ ይሆን በሀገራችን ለህዝብ መብት መከበር የሚሟገት፣ ለፍትህና ለነፃነት የሚቆም እንደ ማንዴላ የይቅርታና የፍቅር ልብ ያለው በሳል የፖለቲካ መሪን የምንታደለው በማለት ራሴን ጠየቅሁት፡፡
  One day! coming soon.

  ReplyDelete
 2. Hello! You have an interesting website. It is nice to visit here.

  ReplyDelete
 3. እንደ ማንዴላ ያሉ እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች(በራሳቸው ምንም ስህተት የሌለባቸው ፍፁም ናቸው ባንልም እንኳን) ዘወትር ሊከበሩና ሊወደሱና ሊዘከሩ የሚገባቸው የአለም እንቁ ናቸው፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች እራሳቸውን መጀመሪያ ከህሊናና ከመንፈስ ባርነት ነፃ ያወጡና ለአጠቃላዩ የሰው ልጅ ጥልቅ ፍቅርና ክብር ያላቸው ናቸው፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አይነት እኛ ከሌለን እናነተ ልትኖሩ አትችሉም አይሉም፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች የመጨረሻ ግባቸው ስልጣንና ቁሳዊ ጥቅም ሳይሆን በራሳቸውና በሌሎች የነፃነት አየር መተንፈስ የሚገኝ የህሊናና የመንፈስ እርካታ ነው፡፡
  ስለዚህም የሌሎች የነፃነት አየር መተንፈስ እነሱን ከማስደሰት ውጪ ያን ያህል አያስጨንቃቸውም ወይንም አይረብሻቸውም፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች እኛ በከፈልነው መስዋእትነት ነው እናንተ የነፃነት አየር እየተነፈሳችሁ ያለችሁት የሚል የዘወትር አሰልቺ መዝሙር እየዘመሩ በአጉል ግብዝነትና ትምክህት እየተመፃደቁ ህዝባቸውን መልሰው የራሳቸው ባርያና የህሊና ግዞተኛ አያደርጉም፡፡
  ስለዚህም እናንተ ከእኛ አኩል ለመኖርም ሆነ እንደኛ ለመናገር ወይንም እንደኛ የነፃነት አየር ለመተንፈስ እኛ የከፈልነውን አይነት መስዋእትነት ወይንም እኛ የሄድንበትን አይነት ውጣውረድና መንገድ መሄድ አለባችሁ ብለው ሌሎችን አያሸማቅቁም ወይንም አንደዚያ አያስቡም፡፡
  ወይንም እኛ የምናስበውን ካላሰባችሁ እኛ የምንናገረውን ካልተናገራችሁ እኛ የምንወደውን ካልወደዳችሁ እኛ የምንጠላውን ካልጠላችሁ ወዘተ በማለት ሌሎች በነሱ ሳንባ ልብና አእምሮ እንዲመሩና እንዲኖሩ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጭፍን ጫናና ተፅእኖ ለማሳደር አይፈልጉም፡፡
  ስለዚህም እራሳቸውን ከሌሎች የበላይና የተሻሉ አድርገው ለመታየት ያን ያህልም አይጥሩም ወይንም አይፈልጉም፡፡
  እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች የወጡበትን የገዛ ወገናቸውንና ህዝባቸውን ከእነ ስህተቱና እንከኑም ቢሆን ያከብራሉ ያፈቅራሉ ያምናሉ፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች ስልጣን ወንበር ላይ ቢወጡም ሆነ ቢወርዱም ምንጊዜም በህዝባቸው ህሊናና መነፈስ ውስጥ ዘወትር ሲታሰቡ ሰከበሩና ሲዘከሩ ይኖራሉ፡፡ስለዚህም ምንጊዜም ስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች ባላነሰ ወይንም በበለጠ ይከበራሉ ይወደዳሉ፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች ትግላቸውና ፀባቸው ከሰዎች መጥፎ አስተሳሰብና ድርጊት ጋር እንጂ ከራሱ ከሰዎች ስብእና ጋር አይደለም፡፡ስለዚህም ዘወትር እውነተኛና ተገቢ የሆነ ሰላምና እርቅ ማውረድን ይፈልጋሉ ይመርጣሉ፡፡እንደዚሁም ሰዎችን መቅጣት የሚፈልጉት ፍትሃዊ ፍርድ ለመስጠትና ለማስተማር እንደዚሁም ወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ለመከላከል እንጂ በጥላቻና በብቀላ ስሜትና አስተሳሰብ በመመራት አይደለም፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች በስልጣናቸውና በሀይላቸው አይመኩም አይመፃደቁም፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች ሰላሳ ሺህ የህግ ድሪቶ በመደራረብ የህዝባቸውን እውነተኛ ነፃነት በሂደት መልሰው በረቀቀ መንገድ ለመስረቅና ለማፈን አይጥሩም፡፡እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አይነት እኛ ከሌለን ሌሎች እኛን ፈፅሞ ሊተኩ አይችሉም የሚል አጉል ቅዠትና ክፋት ውስጥ ፈፅሞ አይገቡም፡፡ስለዚህም እነሱን የሚተካ ሰው ለማዘጋጀትና ለማግኘት 20 እና 30 ዓመታትን እነሱ በስልጣን ላይ ሆነው እንዲያሳልፉ አያደርጉም፡፡
  እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች ከህዝባቸው ጋር በፍቅር በእምነት በአክብሮትና በነፃነት አድሎና ልዩነት ሳያደርጉ ከሁሉም ዜጋቸው ጋር ብዙም ሳይጨነቁ በተለያዩ አጋጣሚዎች ይቀራረባሉ፡፡የታመሙትን የታሰሩትን የተጨነቁትን የተጎዱትን እንደ ቤተሰብ ሆነው ይጠይቃሉ ይጎበኛሉ፡፡ስለዚህም እራሳቸውን ጥይት በማይበሳው የመስታወት ሽፋን ውስጥ ሆነው ለህዝባቸው በአደባባይ አይቀርቡም፡፡
  ኔልሰን ማንዴላም እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች ከሚባሉት ሊመደቡ የሚገባቸው የአለም ህዝቦች ሁሉ የነፃነት አባት ናቸው፡፡ስለዚህም እራሳቸው በቅጡ ነፃ ሳይወጡ በሌሎች ስም የነፃ-አውጪነት ካባ ወይንም ጭንብል የለበሱ ሀይሎችና ግለሰቦች ሁሉ ከእኚህ እንቁ የአለም አባት ትልቅ ትምህርት ሊወስዱ ይገባል እላለሁኝ፡፡
  መልካም ልደት በማለት ረዥም እድሜና ጤንነት እመኝላቸዋለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Right*Right*Right*Right*Right*Right*Right* up to infinity

   Delete
 4. በእርግጥም ኔልሰን ማንዴላ እውነተኛ የነፃነት ታጋይና ለአጠቃላዩ የሰው ልጅ ትልቅ ፍቅርና አክብሮት ያላቸው ብርቅዬ የአለም ህዝቦች ሁሉ አባት ናቸው፡፡እሳቸውን ልዩ የሚያደርጋቸው ደግሞ ለ27 ዓመታት በእስር ያማቀቃቸውን የአፓርታይድ ስርዓት አራማጅ ነጮች ይቅር ማለታቸውና በሀገሪቱም ቀጣይነት ያለው ሰላምና ልማት እንዲኖር ማድረጋቸው ነው፡፡ይህ ይቅርታ በእርግጥ ለተቀማጭ ቀላል ቢመስልም እጅግ ፈጣንና አስቸጋሪ ነው፡፡ነገር ግን እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ነገር ይህ እርቅና ሰላም ለነጮቹ የኢኮኖሚ ጥቅም ደህንነትንና ሰላምን የሚያረጋግጥ ሲሆን ለብዙሀኑ ጥቁሮች ደግሞ የፖለቲካ ነፃነትን የሚያጎናፅፍ ነው፡፡ጥቁሮቹ ባላቸው የቁጥር ብዛት የተነሳ የፖለቲካ ስልጣንን በምርጫ ለመቆናጠጥ አስችሏቸዋል፡፡ከዚህ ውጪ ግን አሁንም ብዙሀኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊ በድህነት በመሃይምነትና በስራ አጥነት እየማቀቀ ነው ያለው፡፡አሁንም የኢኮኖሚ የበላይነቱን ተቆጣጥረው እስካሉ ድረስ ነጮቹ በተቀራኒው የፖለቲካ ስልጣኑን በድርድር በማስረከባቸው ያን ያህል የተጎዱት ነገር ያለ አይመስልም፡፡ብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከዛሬ 60 ዓመት በፊት ነፃነትን ከቅኝ ግዛት አፈና ፈልቅቀው ሲጎናፀፉ ያገኙት ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት እንጂ የኢኮኖሚ ነፃነት አልነበረም፡፡
  ስለዚህም አሁንም ብዙሀኑ ታዳጊ ሀገራትና አፍሪካም ጭምር ማለት ነው እውነተኛ ነፃነትን አልተጎናፀፍንም፡፡ማለትም እውነተኛ ነፃነት=የፖለቲካ ነፃነት+የኢኮኖሚ ነፃነት ::
  አሁንም ባለው ተጫበጭ ሁኔታ መላው ታዳጊ ሀገርና አፍሪካም ጭምር በተዘዋዋሪ የእጅ አዙር የቅኝ ግዛት ውስጥ ነው ያለነው፡፡ብዙዎቻችን የነፃነትን ፋይዳና ትርጉም በአደባባይ ከመለፍለፍና ወይንም አደባባይ ወጥቶ የምርጫ ካርድ ኮሮጆ ውስጥ በመክተት አበበን አውርዶ በቀለን ከማውጣት በዘለለ ካለ አስተሳሳብ ለማየትና ለመመዘን አልቻልንም፡፡አሁን ባለው ተቸባጭ አለም እየተፈጠረ ያለው ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምቅልቅልም አንዱ ብዙዎቻችን ከዚህ የተሳሳተ ግልብና ጥራዝ ነጠቅ አስተሳሳብ ልንላቀቅ ስላልቻልን ነው፡፡ያለ እውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነት ሊኖር አይችልም፡፡እንደዚሁም ያለ እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነት እውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት ሊኖር አይችልም፡፡ስለዚህም አንዱ ያለ አንዱ በራሱ ያን ያህል በነፃነት ለዘለቄታው በአስተማማኝ ፀንቶ ሊኖር አይችልም፡፡ለዚህም ነው ብዙው የአለም ህዝብ በውሸት ዲሞክራሲ ሽፋን የተነሳ በቀጣይነት በድህነትና በሰቆቃ ዘመናዊ ባርነት ውስጥ እየገባ ያለው፡፡ለዚህም ነው ዛሬም ድረስ በአፍሪካና በመላው አለም ጦርነትና አለመረጋጋት እየቀጠለ ያለው፡፡
  ስለዚህም የነፃነትን ትክክለኛ ትርጉምና ፋይዳ በጥልቀት እንመርምር እንረዳ፡፡የሀገራችንንም ውስብስብ ሁኔታ ከዚህ አንፃር በቅጡ ልንመረምረውና ልንረዳው ግድ ይለናል፡፡
  መልካም ልደት ረጅም እድሜና ጤና ለውዱ ኔልሰን ማንዴላ፡፡

  ReplyDelete
 5. Ya Dani it is true. Eruk sanihad est mejemeria kirbachin yalewn sew yiker enibelew yemigermign neger zewiter beselotachin bedelachininim yeker belin eignam ende yiker endeminlin. eyalin yeminlimnewn betegbar enawilem.sew yiker enibelew yemigermign neger zewiter beselotachin bedelachininim yeker belin eignam ende yiker endeminlin. eyalin yeminlimnewn betegbar enawilem.

  ReplyDelete
 6. ጦማሮችህነ የምወዳቸዉን ያህል የፖለቲካዊ ንዝረታቸዉ የጎላ ሲመስለኝ የሆነ ቀን የሆኑ ሰዎች ተከፍተዉ የብእርህን ቀለም ከማለቁ በፊት እዳያደርቁት መስጋቴን ከተራ ስጋት እንደማያልፍ ማን ሊያሳምነኝ ይችል እንደሆን አላዉቅም ባለብዙ ፋይዳዎችነታቸዉ የሚሰሙኝ ፅሁፎችህን ግን ገና ገና ብዙ ልማርና ልመከር እንዲገባኝ ሳስብ ዘመናትን በመደማማትና ጠልፎበመጣል የተገነባዉን ፖለቲካችንን (ፖለቲካቸዉን)በጥልቀት ባትነካካባቸዉና ከፈጠጠዉ እዉነት ባታላትማቸዉ በመልሱም እነሱ መጦመሪያህን እንዳይቀዳድዱትና አደራ አደራ...............
  አግኝቶ ከማጣት ................................. ይሰዉረን አሜን

  ReplyDelete
 7. ሃሌ ሉያ!!!

  ReplyDelete
 8. SELAM D Daniel I think you going to far..pls
  come back .. I know this is not you'rs view..but you need to pay attension for this kind of view.some peopls are trying to add you to poletics ..in my opinion you are born for spritual activites !NOT FOR POLETICS! God bless u!!
  D EPHREM KE USA

  ReplyDelete
 9. Dear Befiker,

  Thanks for your intervention. I can say Nelson Mandela is an African icon. Besides his devotion and sincere commitment to equality and justice, he is the man who introduce truth and reconciliation to the world. His move was an exemplary, which most people couldn't do it.

  ReplyDelete
 10. Hello,Our Leaders,
  Hello Opposition Leaders,
  Hello Spiritual Fathers,
  Hello Honors,
  Hello the hope of Tomorrow's Ethiopia
  Hello there in Ethiopia,

  DO YOU HEAR THE VOICE OF LONG-LASTING PEACE AND UNITY.

  Please hear the voice of reconciliation, peace, unity, being Ethiopianess.

  Long live Madiba, Long Live AFrica, Long Live South Africa and last but not least LONG LIVE ETHIOPIAAAAAAAAAA.

  ReplyDelete
 11. መቼ ይሆን ኢትዮጵያ ለዚህ የምትታደለው? አምላክ ሆይ ኢትዮጵያን አስባት፡፡

  AA from Addis Ababa

  ReplyDelete
 12. It is given from God. long live Mandela.

  ReplyDelete
 13. ዳኒ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ደብቃ ከጭልፊት እንደምትከላከለው አንተንም በዚህ መልኩ በክፋ ከሚያዩህ ማዳን ቢቻለን ጥሩ ነበር፡፡ ሁሌም ስለአንተ እፈራለሁ፡፡ እስኪ እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡ የእርሱ ጥበቃ ይበልጣል እና፡፡

  ReplyDelete
 14. ስለ ማንዴላ ትናንት የተጻፈውን ግጥሜንና ቀደም ብሎ የፃፍኩትን "ፀሎተ-ዘወትር" የተሰኙትን ግጥሞች ላስቀምጥ
  1. ኦ ማንዴላ!
  ኦ ማንዴላ
  የማትሰክር በጠላ
  በአረቄ የማትጠነብዝ
  በወይን የማትደነዝዝ
  ያን ሁሉ ስቃይ ተግተህ
  ያን ሁሉ ግፍ ጠጥተህ
  ሰክረህ ያልተንገዳገድከው
  ይኸ ድንቅ አምላካችን
  ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??
  ኦ ማንዴላ
  የማትሰክር በጠላ
  በአረቄ የማትጠነብዝ
  በወይን የማትደነዝዝ
  ያን ሁሉ ዝና ጨልጠህ
  ያን ሁሉ ክብር አንዶቅዱቀህ
  በስልጣን አረቄዋ
  በናላ አዟሪዋ እጅ ወድቀህ
  ሰካራም ሆነህ ያልቀረኸው
  ይኸ ግሩም ጌታችን
  ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??
  //-///
  ሐምሌ 17 2003 ወደ ምሽት( ነገ የ ማንዴላ 93ኛ ዓመት የልደት በዓል ይከበራል)
  ፒያሳ: ኪይብ ካፌ
  ከወዳጄ በረከት ጋር ስለ ማንዴላ አውርተን ውስጤ ቢነሳሳ ጊዜ ጻፍኩት
  ለማንዴሎች ሁሉ ጌታ ለጌታ ኢየሱስ!!

  2.ፀሎተ ዘወትር

  ስንት መንግስት ሰማን ስንት መንግስት አዬን
  ስንት መንግስት አጠገበን ስንት መንግስት አሰቃዬን::
  እባክህ
  "መንግስተ-ምድር" ይወረድ "መንግስተ ምድር ይውጣ"
  ፍቃድህ በምድር ትሁን መንግስትህ በምድር ትምጣ::


  20-10-2003 ዓ.ም
  አ.አ ቤላ ::ከጣልያን ኤምበሲ አጥር ስር
  ጠዋት 2:30

  ያልታተሙ::ተጨማሪ ግጥሞቼን http://tsegaye-poems.blogspot.com/ ላይ ያንበቡ

  ReplyDelete
 15. Comment
  Dear Fikir: Qale Hiwot yasemalin.
  And thank you Dn Daniel for sharing this article...

  I think it is a great article that asks one of the most, most ... important questions for our Ethiopia. Of course some ppl above are commenting that you should not be involving urself with or writing about such stuff - political views, urging you to stick to the Church stuff only, I disagree, ... but these ppl should remember there is Church politics too, and we can't ignore it forever. Unless, we (as Christians) are advocating for blind violence and chaos... there is nothing wrong with standing up for the basic human rights, the Holy Bible never teaches us to bury our heads in the sand when it comes to the main issues facing our country... remember the Church (EOTC) fighting the Mussolinis with the other brave sons and daughters of Ethiopia. And this was just one instance in our history when ppl had to rise up to never lose their freedom.

  People have to be able to enjoy freedom to the fullest to actually appreciate it. B/c when you know freedom, you don't want to lose it again, to any tyrant, no matter what. I think we Ethiopians (of the recent generations) never had the chance to fully enjoy what freedom is actually like. That is why the different ethnic groups have come to the top (ruled) and gone away thru out our history with out making any significant contribution to the taste of freedom. Even though some groups had more freedom, but others have been suppressed or persecuted by the same ruling class; as we see it today. And these conditions will go on forever unless ppl rise to change them for the better. And that is why most of us will never do anything beyond talk ... It is said, "Freedom is never free." So that is why we all have to appreciate the ppl who stood up for freedom and one day, may be before we die, we might take up the struggle ourselves and ensure freedom for all. Believe me, there is never more noble a cause ...

  May God protect Ethiopia, EOTC and its true followers,

  God bless,
  YeAwarew

  ReplyDelete
 16. ዳኒ በጣም ትልቅ ስህተት ሰራህ፡፡ ግን ለምን? እባክህን ዳንኤል አንተ እንኳን ትረፍልን፡፡ አንተ ደግሞ ለምን ታሳዝነናለህ? እየው እስኪ የስህተትህን ውጤት http://waywisdom383.blogspot.com/2011/07/blog-post_3760.html?spref=fb
  ይህን አልነበረም ከአንተ የምጠብቀው፡፡

  ReplyDelete
 17. Dani kemesimer yewetah meselegn eziga bikom yishalal

  ReplyDelete
 18. Dear D/n Daniel tinish yetedaferk ena mesmer yezelelik meselegn ena endezi aynetun batawetaw yishalihal

  ReplyDelete
 19. thank you dy daniel

  ReplyDelete