Wednesday, July 20, 2011

የሃይማኖት ፖሊሲ፣ ሕግ እና ተቋም የሌላት ሃይማኖተኛ ሀገር


 
ኢትዮጵያ ታሪኳም ሆነ ሕዝቧ ሃይማተኛ ነው፡፡ ቅርሷ እና ባህሏ፣ ዘይቤዋ እና ሥነ ምግባርዋ ሃይማኖተኛ ነው፡፡ በቅርቡ በተደረጉት ቆጠራዎች 90 በመቶ በላይ ሕዝቧ ሃይማኖተኛ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያውያን ኑሮ ውስጥ ሃይማኖት ዋናው ነገር መሆኑን አሳይቷል፡፡ የኢኮኖሚ፣ የባህል፣ የሕግ፣ የአሠራር፣ የውጭ ግንኙነት፣ የትምህርት፣ ወዘተ ፖሊሲዎች እና ዐዋጆች ሲወጡ የሚዘነጋው ነገር ግን መዘንጋት የሌለበት ነገር ኢትዮጵያ ሃይማኖተኛ ሀገር መሆንዋ ነው፡፡
 ኢትዮጵያ ግን የሃይማኖት ፖሊሲ እና ሕግ የላትም፡፡ «መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው» ማለትኮ መንግሥት በሃይማኖት ተቋማቱ አሠራር አያገባውም ማለት አይደለም፡፡ በትምህርተ ሃይማኖታቸው፣ በሥርዓታቸው፣ በባህላቸው እና በትውፊታቸው ውስጥ ገብቶ ይህንን እመኑ ያንን አትመኑ፣ እንዲህ ጹሙ እንዲህ ጸልዩ አይበል እንጂ የዚህች ሀገር አካል እንደመሆናቸው ሁሉ ሀገራዊ ሕግ እና ፖሊሲ ያስፈልጋቸዋል፡፡
አንድን ሃይማኖት ሃይማኖት የሚያደርገው ምን ምን ሲያሟላ ነው? ወይስ ሃይማኖት ነኝ ብሎ የመጣ ሁሉ ሃይማኖት ነው? አንድ ሃይማኖት የሚመዘገበው እንዴት ነው፡፡ አንድ የሃይማኖት ተቋም ተጠያቂ የሚሆነው እንዴት ነው፡፡ በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች እንዴት ይፈቱ? የሃይማኖት ተቋማት ወሳኝ አካላት ዕውቅና የሚያገኙት እንዴት ነው፡፡ በሃይማኖት ተቋማት አመራሮች እና ምእመናን መካከል መከፋፈል ቢመጣ በምን ይፈታል? መጨረሻው መለያየት ቢሆንስ ጉዳዩ እንዴት ያልቃል?
የአንድ እምነት እሴቶች፣ ወጎች፣ ቅርሶች፣ ይትበሃሎች፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ሀብቶች፣ ታሪኮች እንዴት ይጠበቃሉ? የባለቤትነት እና የመጠቀም መብትስ እንዴት ይታያል? በእነዚህ ነገሮች የይገባኛል ጥያቄ በተለያዩ እምነቶች መካከል ቢፈጠርስ እንዴት ይፈታል?
እነዚህን እና ሌሎችንም ሀገራዊ ጥያቄዎች ሊመልስ የሚችል የሃይማኖት ፖሊሲ እና ራሱን የቻለ ሃይማኖት ሕግ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል፡፡ በእምነት ተቋማት መካከል መተዋወቅ፣ መከባበር እና መረዳዳት እንዲኖር፣ ሁሉም ሥነ ምግባር በታነፀ እና በሠለጠነ መንገድ ልዩነቶቻቸውን እንዲያስኬዱ፤ የጋራ የሆኑ እሴቶች ለሀገሪቱ ጉዞ ግብአቶች እንዲሆኑ ፖሊሲው እና ሕጉ ታላቅ አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡
የእምነት ተቋማትን የእምነት ቦታ አጠያየቅ፣ አፈቃቀድ እና ባለቤትነት፣ የሂሳብ አሠራር እና ሪፖርት፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት፣ መሥራት የሚችሉትን እና የማይችሉትን፣ የሰው ኃይል አስተዳደራቸውን፣ የስም አሰጣጣቸውን፣ የድምፅ አወጣጣቸውን፣ ምርጫ እና ሹመታቸውን፣ በአንድ እምነት ተቋም ሥር ስለሚ ቋቋሙ የሃይማኖትን ጉዳይ ስለሚያዩ ፍርድ ቤቶች ጉዳይ፣ የሚዲያ አጠቃቀማቸውን፣ ወዘተ የሚደነግግ ሕግ ያስፈልገናል፡፡
ትምህርት ቤቶቻቸው ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፤ የሃይማኖት ተቋማትን የእምነት /ቤቶች ደረጃ የሚያወጣና የሚከታተል አካል ያስፈልጋል፡፡ የሰው ኃይል አቀጣጠራቸው ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
ለምሳሌ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ሀገር ሆና ለምን በትምህርት ቤቶች የሃይማኖት ትምህርት አይሰጥም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ዋና ዋና የእምነት ዘውጎች አስተምህሮ የሚገልጥ፣ የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያሳይ፣ አንዱ ሌላውን እንዲያውቀው የሚያደርግ ዓይነት ትምህርት፡፡ በእምነት ሰዎች መካከል ግጭቶች ለምን ይነሣሉ? እንዴትስ ይፈታሉ? ማንኛውም የእምነት ሰው ሊኖረው የሚገባው ሥነ ምግባር ምንድን ነው? በሃይማኖት ስም የሚፈቀዱ እና የማይፈቀዱ ተግባራት ምን ምን ናቸው? እና ሌሎች ነገሮች በትምህርት ደረጃ መሰጠት አለባቸው፡፡ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ሀገር ናትና፡፡
አንዱ በእምነት ተቋማት እና በምእመኖቻቸው መካከል ግጭት እንዲከሰት የሚያደርገው አለመተዋወቃቸው ነው፡፡ በሃይማኖት ተቋማት እና በተከታዮቻቸው መካከል ያለው ግንኙነት በእሳት መድረክ ላይ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ በልጅነት እድሜ በተማሪነት ዘመን ውይይቶች እና የልምድ ልውውጦች ባህል መሆን አለባቸው፡፡ በዑጋንዳ ትምህርት ቤቶች አንድ ጥሩ ልምድ አይቻለሁ፡፡ የአንዱ እምነት ወገን ወደ ሌላው ሄዶ ይጠይቃል፣ ያያል፣ ስለዚያኛው ወገን ከራሱ ከባለቤቱ ይረዳል፡፡
ይህ ነገር ሁለት ጥቅሞች አሉት፡፡ አንደኛው በአሉባልታ የተነሣ ከሚፈጠሩ መጠራጠሮች እና አለመግባባቶች ያድናል፡፡ በሁለተኛ ደረጃም መከባበር እና በበጎ መተያየትን ያመጣል፡፡
ከመተዋወቅ እና ከመከባበር ባሻገር ኢትዮጵያ ውስጥ የእምነት ተቋማት ምክር ቤትም ያስፈልጋል፡፡ በእምነቶች መካከል መተዋወቅ እና መቀራረብ እንዲኖር፣ በመካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች በጋራ እንዲፈቱ የሚያደርግ፣ የጋራ እሴቶች የሀገሪቱ ባህል፣ ሥርዓት፣ ሕግ፣ አሠራር፣ ትምህርት እና ፖሊሲዎች አካል እንዲሆኑ የሚሠራ፣ በእምነት ተቋማት አሠራር ላይ የሥነ ምግባር ሕግ የሚያወጣ፣ ምክር ቤት፡፡
የጋራ የሆነ የርዳታ እና የልማት ተቋም ሊኖረን አይችልም? አሁን የእምነት ተቋማት ያላቸውን ሃብት እና ተቀባይነት መሠረት አድርገው አንድ ታላቅ የርዳታ ተቋም በጋራ ቢያቋቁሙ ድርቅ በመጣብን ቁጥር ፈረንጅ መለመናችንን ባቆምን ነበር፡፡ ያላቸው ተደራሽነት፣ ርዳታ ቢሰበስቡ የሚኖራቸው ተቀባይነት፣ እንዲሁም ታማኝነት ከፈረንጆቹ በላይ እንዲሠሩ ያደርጋቸው ነበር፡፡ ሀገሪቱም ችግር በገጠማት ቁጥር የሌሎችን እጅ ከማየት ትድን ነበር፡፡
በየራሳችን ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የመጠጥ ውኃዎችን፣ መንገዶችን እና የግብርና ሥራዎችን መሥራታችን ይቀጥል፡፡ ነገር ግን ለሀገራችን የምናበረክተው የጋራ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ የመጠጥ ውኃ፣ መንገድ፣ ድልድይ፣ የለንም እንዴ? በጋራ የምንሠራው፡፡ በሀገራችን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ የርዳታ ድርጅቶች ገንዘብ የሚያገኙት ከአውሮፓ እና አሜሪካ የእምነት ተቋማት ነው፡፡ ምናለ እኛስ ሞልቶ ከተረፈው ገንዘብ ለሀገራችን ብናውለው፡፡ የጋራው ምክር ቤት ይህንን ሁሉ መሥራት ይችል ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ብሮድካስቲንግ የለም፡፡ ምናልባት እሳት እንዳይጭር ተሠግቶ ይመስለኛል፡፡ ይህንን ግን የእምነት ተቋማቱ ተነጋግረው መፍታት አይችሉም ማለት ነው? የእምነት ተቋማቱ ምክር ቤት የጋራ የብሮድካስቲንግ የሥነ ምግባር ሕግ አውጥቶ፣ ተቆጣጣሪ ቦርድ መድቦ፣ ቅሬታ አስተናጋጅ አካል ሰይሞ፣ ግጭት ሊፈጥር በማይችል መልኩ የሃይማኖት ብሮድካስቲንግ የሚስተናገድበትን መንገድ ለምን አንተልምም፡፡
ለመሆኑ በየእምነቱ የሚገኙ የአለባበስ ሥርዓቶችን የሚመዘግብ፣ የባለቤትነት ፈቃድ የሚሰጥ፣ አንዱ በሌላው ተጠቅሞ እንዳይቀስጥ የሚከላከል፣ ሁሉም የየራሱን ተጠቅሞ የሌላውንም አክብሮ እንዲሄድ የሚያደርገው ማነው? እንደ እኔ እንደ እኔ በሕግ የተቋቋመ የሃይማኖት ተቋማት ምክር ቤት መሆን አለበት፡፡

25 comments:

 1. it the most interesting issue, which, the government should address.if there is clear cut rule with regard to religion, there would not be recurring conflicts, and other disagreements among different religion followers, and the government does not have the anxiety on this issue. countries like Ethiopia are very much sensitive in religion, hence, the attention made on religion will even induce integrity among the people and faith on the government.

  ReplyDelete
 2. it is a nice observation.but i am not sure about gov't intervention.most of our problem occurred in our church is because of political popes.this is one indicator.the other is there was a genocide or massacre in Oromiya and Harare region i am the victim of that dark event,this all happened by one gov't official stupid hatred speech.any way i can't explain all things here.
  may Lord topple this crazy gov't.i am always pray to it.
  May lord be also with you.
  Download: www.ieType.com/f.php?FAIIfQ  Download: www.ieType.com/f.php?FAIIfQ

  ReplyDelete
 3. ዳኒ፣
  ዛሬ ከመድረክህ መውረድ እስኪያቅተኝ በመልካም መጣጥፍ ታስሬ መዋሌ ነው። ለማነኛውም መላ ምትህ እጅግ የምደግፈው ነው። አየህ ሀገራችን በአጀማመር እንጂ በአጨራረሱ ደካማ ናት፤ ከሩጫው በስተቀር። በቅርብ ጊዜያት ወገኖቻችን «የሚመስሉት» እምነት ምንጩ በአብዛኛው ከድህነት ማምለጫ መሆኑን ልብ ይሏል (ኩርፊያን ሳንረሳ)። ይህ ለውጭ ድርጅቶች ትልቅና መልካም አጋጣሚ ነው- ብዙዎቹ ወደ ደሃ ሀገራት እምነት ተቋማት የሚልኩት ገንዘብ የሚቆረጠው በአባሎቻቸው ቁጥር ብዛት ነው።

  ለዚህ ነው የእምነት ተቋማት እንደ አሸን እዬፈሉ ከሞራልና ሥነምግባር ውጭ አልባሌ ሥራዎችን ሲሰሩ የሚታዩት። ሀገራችን በታምር ካልሆነ በስተቀር በውሃ ሊጠፋ የማይችል ረመጥ እያዳፈነች እንደሆነች ልንገነዘብ ይገባል። በርካታ አዳዲስ እምነቶች ከኢትዮጵያዊነት ስሜት በማሸፈት ለማናውቀው ሀገር ባህል፣ ልምድ ተገዥ እንድንሆን ሌት ተቀን እየተጉ ሲሆን እኛ ግን ዳር ቆመን ዝም ብለናል። የእምነት ነጻነት ማለት የሀገር ክህደት ማለት አይደለም! ዛሬ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ለመጥራት የሚጸየፉ ሽፍቶች ተፈልፍለዋል- አንዱና ዋነኛው ምንጩ ደግሞ ሥርዓትና መቋጫ የጠፋለት የእምነት ተቋማት እንደ አሸን መፍላት መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።

  በዚህ ላይ የሚመለከተን ወገኖች ብናስብበት መልካም ነው።

  ReplyDelete
 4. Dani, Thanks for sharing such a wonderful idea.

  It would be an important step for our government to step up and create policy, rules, and regulation regarding the country's religions. Having institution that can deal with such issues is very crucial, especially for a country like Ethiopia.

  I remember Muslims(just to provide an example, nothing personal) have built more than one hundred mosques in Addis Ababa in just one term of a certain Mayor (because he was Muslim). In addition, I have seen so many conflicts between two religion followers to build a church or a mosque next to each other. For example, ayer tena kidanemihert area, CMC area, and others.

  If we had such kind of policies to solve problems, which arise in relation to religion like those, we could have saved so many lives and resources. At the same time we wouldn't take things personally; fix complaints in a timely fashion.

  However, in my opinion the government likes to keep this idea as it was previously; no law about this issue. Because, it will give the gov't another means of separation the people so that they can stay longer in power; this kind of law will unified people. whereas, the current gov't strategy is to separate people inasmuch possibilities as there are out there to rule more.

  Most of our current leaders don't even believe in religion; they don't go to any religious institution. They think that religion makes them out of in line of leader.

  Therefore, Dani for this idea to happen in our time, the leaders, policy makers, have to receive a good moral character and get this idea from positive and constructive view.

  ReplyDelete
 5. እኛ ሀገር እኮ አብሮ መብላት እንጂ አብሮ መስራት ወንጀል ሳይሆን አልቀረም


  ገብረማርያም
  ከአአ

  ReplyDelete
 6. Thank u dn Dani. It is very interesting. Hig binor manim kehig belay ayhonim neber. Bizegeym tegbarawi bidereg yewushochu kutir yikens neber.

  ReplyDelete
 7. ኃ/ገብርኤል ከአራት ኪሎJuly 20, 2011 at 4:52 PM

  ዲ/ን ዳንኤል ሰላም ላንተ ይሁን
  ብዙ ጊዜ በሀገራችን ላይ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው የሚተገበሩት ፖሊሲዎች የሚጠኑት እና ረቂቃቸው የሚዘጋጀው በውጪ ዜጎች ነው። እነዚህ ፖሊሲ አርቃቂዎች በሀገራቸው የለመዱትን አሰራር ከእኛነታችን ጋር ሳያለማምዱት በግድ ይግቱናል። በሃገራቸው ሃይማኖተኛ ህዝብ ስለሌለ ለእኛ ሃገር ሃይማኖተኛ ህዝብ አይጠነቀቁም። እነሱስ ባለማወቃቸው ነው የሚገርመው የኛዎች የእነሱን አስተሳሰብ እንደወረደ መቀበላቸው ነው። ከውጪ የመጣው አስተሳሰብ በሃገርኛው የአኗኗር ስልት እና ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሊጣጣም በሚችል መልኩ ቢዘጋጅ እንዴት ጥሩ ነበር። በመሆኑም እኔ ያነሳኸው ችግር የውጪ ሃገሮችን ፖሊሲዎች ያለምንም ማስተካከያ እንደወረደ የመቀበሉ ነፀብራቅ ነው ባይ ነኝ።

  ReplyDelete
 8. Oh Dani! that is very nice view, every responsible guy should pay attention!

  ReplyDelete
 9. Dani ...................??????????

  ReplyDelete
 10. Betiqilu hasabu Tiru new gin bezih menged Iwenet min ayenet Temokiro ale. Chigirachinim eko Yemininagerwin yemanitegebir Hayimanotachinin mekofesha,memetsadeqiya yadereginim eko nin letifat kametebaber yiliq betenkol,bmachibereber Ye andun Eminet teketay lematifat Eminetunim lemasqeyer sinirot aleng yemilewin qirisim lemewidem sinirot eko new Yeminigennyew Ende hager habt massebe Yemibal negerima Yet tegengto? bizuwoch begilits Docterinachewin mastemar sigebachew bemamitatate,bematilalat lay anidandem Yalihonutin nen,yalawqotin aweqaleh bemalet Hilinachewina Egziabher Eyemesekerebachew sitagelu Yegengalu.... Degemom Eko Mengist malet Hulunim Yemisera bihon Yetingaw new meri ena Temeri Yemihonew. silezih Hasabun Madaber meserte meteYeq yalebet YeYeiminetu teketay new Enji endet Yewich akal Taliqa alegebam Yemil;jemari/prime mover/lihon Yichilal?

  ReplyDelete
 11. የኔ ጥያቄ አገር: ፖለቲካ እና ሃይማኖት ይለያያል? ከተለያየስ ሁለት ባህሪ የሚለዉ አስተምህሮ ተቀባይ አንሆንም? በተዋሕዶ (እነዚህ ሶስቱ አይገናኙም ከሚል) ከማያምን ፖለቲከኛ አሁን አንተ የሚታነሳቸዉን ነገሮች ማግኘት ይቻላል?

  ReplyDelete
 12. Yezih Ayinetu kumnegerima bifeter endet betadelin nebere. Gin Alemenoru Yemibejachew silalu mengist Tikuret Yemisetew ayimesilegnim. Hasabu gin dink new.

  ReplyDelete
 13. Dear Daniel,

  Well you intervention has significant, sound, and realistic ground.

  Yes indeed, Ethiopia is a country of religion and belief. However, I am wondering how can we tackle the competition between religions.

  Leave alone the competition between the different religions, the competition within the same religion is too ugly.

  The western and Eastern Orthodox Christians even defame one another.

  The council of beliefs, religion policy and regulations could bring some rapport building among others.

  ReplyDelete
 14. በትክክል በህግ አምላክ የምንልበት የሀይማኖት ህግ ያስፈልገናል፡፡ ዛሬ የሀይማኖት ህግ ቢኖር ኖሮ የቤተክርስቲያናችን ትክሻ ላይ ተንጠልጥለው በተቀደሰው ስሟ የሚነግዱ ዘማሪያን እና ሰባክያን ነን ባይ አጭበርባሪ ነጋዴዎችን በህግ ጅራፍ ገርፈን ቤተክርስቲያናችን የወንበዴዎች ዋሻ ከመሆን ትድን ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው ይኸው ማን አባራሪ ማን ተባራሪ እንደሆነ እንኳን ግራ እስኪያጋባን ድረስ ተፋጠናል፡፡


  “ ለካ….. እኔ ነኝ የምወጣ አለ አሉ ደባል”
  አንዱ ደባል የሰው ቤት ገብቶ ሲኖር ሲኖር የራሱ ቤት መስሎት ጥጋብ ጥጋብ አለው እና ውጡልኝ ብሎ አላቸው፣ ባለቤቶቹም እኛማ የቤቱ ባለቤቶች ነን አንተ ውጣ እንጅ ሲሉት “ ለካ….. እኔ ነኝ የምወጣ” ብሎ አለ፡፡


  የዛሬዎቹ የቤተክርስቲያን ደባሎች ግን ባለቤት ነን እያሉ ነው እና በህግ እንዳንዳኛቸው ህግ የለንም ያው ታናሽ ወንድሜ እንዳለው በጉልበት ………… ወይ ጣጣ ፈተና ነው እኮ!!!!!!

  ReplyDelete
 15. ዳኒ ጥሩ እይታ ነበር ግን፡-

  አሁን አስቲ ማን ይሙት የራሱን ሀይማኖት በቅጡ መቆጣጠር ያቃተው የሀይማኖት ተቋም እንዲ ተጠማምሮ ፍሬያማ የሚሆን ይመስላል፡-

  ኦርቶዶክስ ውስጧ የተሰገሰጉ ግብስብሶችን እንኳን ማውጣት አቅቷት ከፓትሪያሪክ እስከ ዳቆኑ እንደ መዥገር ተጣብቀው ደሟን መጠው ሊገሏት እየተናነቃት፣ ሙስሉሞ ክርስቲያን ገድሎ ለመጽደቅ በሚጣጣርበት ጊዜ እነዚ በጅማት ካልተሰፉ ለእግ ተገዝተው ለበጎ ምግባር አንድ ላይ የሚሰለፉ አይመስለኝም፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 16. it is the most interesting.

  ReplyDelete
 17. It's an interesting and valid theoretical assumption and hope that will be materialized in our country. BUT.....ለሃይማኖቱ ሕግና ለመንፈሳዊ አምላኩ ልዕልና ያልተገዛ ለምድራዊ ህግ በጅ ማን ይላል:: I doubt it!!!!

  ReplyDelete
 18. Tiru new. Lemisal Qidus sinodosu yewesenewin Patriarchu alasfetsim silu, hay yemil ye haimanot fird bet linor yigebal. Weyim meemenanen yemibetebitu ye bitibit hawariyatin patriarichu lishomu sitiru hay bay yasfeligal. Kelebelezia ye hageritu selam yideferisal. Ahunim gize ale yemimeleketew akal liasibibet yigebal.

  ReplyDelete
 19. Dear Dani, you have raised a very important issue. At this juncture, I don't think Ethiopia needs religious policy. Remark, I amn't asking why and what but when. During the reign of kings, Church's affiliation,which I prefer to call direct marriage, with state could have been vividly seen. Every ruler's legitimacy was given from Church. No clergy would have accepted the king's power if he isn't descendant of Solomon dynasty. The palace used to protect the Church and vice versa. The renowned book "FIKIR ESKE MEKABIR" is the best example. This used to be Ethiopia's character until 20th century. Fast forward to this decade, you will come across a society bewildered by liberalism and modernity. Even though, the constitution clearly states about the separation between state and church, I can confidently say that neither of them are separate/P.S I DON'T BELIEVE WHAT YOU PROVIDED IS THE LEGAL AND POLITICAL MEANING OF SEPARATION BETWEEN CHURCH AND STATE./ In the pretext of resolving conflicts, the governments usually interferes with the Synod's affair. Thus, I can safely conclude that Ethiopia is a religious country by default despite the supremacy of secular government.
  Now, the question I want to pose here is, would it be acceptable if we have a religious policy at this time? I answer in the negative. Because this can make our Church susceptible for government's manipulation, እንደ አሁኑ ዓይነት ሰዎች የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ላይ ተቀምጠው አንተ ባሰብከው የሃይማኖቶች ምክር ቤት ተቀምጠው ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ሥራን ይሠራሉ ብዬ አላምንም፡፡ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ‹‹የብሔር ግጭት ይነሳባታል›› ተብሎ በ‹‹ስጋት ያለች›› አገር ላይ የሃይማኖት ፖሊሲ አውጥቶ የሃይማኖቶች አስተዳደርን ለመምራት መሞከር ከድጡ ወደማጡ ሊሆን ይችላል፡፡
  አንድ ፖሊሲ ፖሊሲ ብቻ ሆኖ አይቀጥልም፡፡ ፖሊሲውን ለመተርጎም ሕግ ይወጣል፤ ሕጉን ለመተርጎም አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ የወጡትን ሕጎችም በሥራ ላይ በማዋል የሚያስፈጽም ፍ/ቤትም-የሚወስነው ቅጣት አስተዳደራዊ ሆነም አልሆነ- የግድ ይላል፡፡ አገሪቱ ያለችበትን አዘቅት እያየን እነዚህን ሁሉ ማድረግ affordable መስሎ አይታየኝም፡፡ ጊዜውም አሁን አይደለም ባይ ነኝ፡፡
  በኢትዮጵያ ውስጥ በምንም መልኩ መንግሥት ከሃይማኖት ጥገኝነት ሊላቀቅ አይችልም፡፡ ይህንን ጉዳይ እስካልተገነዘበ ድረስ ለኅልውናው ማሰብ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሊበራል አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 20. It is me Part-1

  ሀይማኖትና ፖለቲካ፡፡
  ሀይማኖትና ፖለቲካ አይገናኙም፡፡
  ይህ አባባል በግርድፉ ወይንም በጥሬው በወረቀት ላይ ብቻ ሲታይ እውነት ሊመስል ይችላል፡፡
  ነገር ግን በዚህ አለም ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በፍጥነትም ይሁን በአዝጋሚ የሂደት ለውጥ እርስ በርሱ የማይገናኝ ነገር ብዙም ያን ያህል አይገኝም፡፡ስለዚህም ሀይማኖትና ፖለቲካ አይገናኙም
  ተብሎ በወረቀት ደረጃ የሰፈረውም በእርግጥ እንዲያውም በተቃራኒው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጣም ስለሚገናኝ ነው፡፡ከእያንዳንዱ ሀይማኖት ጀርባ ፖለቲካ አለ፡፡እንደዚሁም ከእያንዳንዱ ፖለቲካ ጀርባ ሀይማኖት አለ፡፡በእርግጠኝነት የትኛው የትኛውን ይመራዋል ለሚለው እጅግ ሰፊ ነገርና ብዙ ጥናት የሚፈልግና እንደየ ሀገሩ ነበራዊ ሁኔታ የሚለያይ ነው የሚሆነው፡፡ነገር ግን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሀይማኖትና ፖለቲካ ለሚባሉት ቃላት የተለመደውን የሚያግባባንን ትርጓሜና እሳቤ ይዘን ከሄድን በእኛ ሀገር ስንመጣ ፖለቲካው ሀይማኖቱን ለመምራት የሚፈልግ ይመስላል፡፡
  በእርግጥ ፖለቲካ ለሚለው የተለመደውን የሚያግባባንን ትርጓሜና እሳቤ ይዘን ከሄድን የህይወት አንድ የተወሰነ ዘርፍ ነው፡፡ሰፋ ያለ ትርጉም ከሰጠነው ደግሞ በሰዎች መካካል ያለው አጠቃላይ መስተጋብርና አካሄድ እንዲሁም አጠቃላዩ ህይወት በራሱ ፖለቲካዊ ይዘት ግንኙነትና ትስስር አለው፡፡በሀይማኖት ስንሄድ ሰማያዊ የሆነ መለኮታዊ መንግስት እነዳለ ሁሉ በተቃራኒው ደግሞ የዚህ ሰማያዊ መለኮታዊ መንግስት ነፀብራቅ የሆኑ ብዙ ምድራዊ መንግስታት አሉ ማለት ነው፡፡በሰማያዊው መንግስት ዋናው ፈጣሪና ሌሎችም የመላእክት አለቆች እናዳሉ ሁሉ እንደዚሁም በግልፅ ህጋዊ ባይሆንም እንደዚሁ ብዙ ምድራዊ መንግስታት ባሉበትም በዚህች አለማችንም ውስጥም ሀያላን መንግስታት አሉ ፡፡አዎ ሌሎች የጠነከረ አቅም የሌላቸውን ደካማ መንግስታትን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሀይልም ይሁን በፖለቲካ አካሄድ ከላይ ሆነው የሚያዙ ሀያላን መንግስታት አሉ፡፡
  ስለዚህም ሀይማኖትና ፖለቲካ ብለን ስንከፋፍላቸው እንዲያው ያን ያህል በጣም የተለያዩ ጥቁርና ነጭ የሆኑ ወይንም እንደ ዘይትና ውሃ ፈፅሞ የማይቀላቀሉ ነገሮች አድርገን ማየት የለብንም፡፡በፖለቲካ ውስጥ ሀይማኖት አለ በሀይማኖትም ውስጥ ፖለቲካ አለ፡፡ብዙውን ጊዜ ፖለቲካ ወይንም ሀይማኖት ለሚለው ፅንሰ-ሀሳብ በቲዎሪም ይሁን በልማድ እየሰጠነው ያለው ትርጓሜና እይታ በትክክል በተግባር ከሚታየው ተጨባጩና ነባራዊው አለም አጠቃላይ መስተጋብር ጋር ያለው አንድነትና ልዩነት ያን ያህል በጠራ መልኩ ግልፅ አይደለም፡፡ለምሳሌ በወረቀት ደረጃ ሀይማኖትና ፖለቲካ አይገናኙም ተብሎ ቢፃፍም ወይንም በአደባባይ ዘወትር ቢወራም በተግባር ግን በሀገራችን የመንግስት ለውጥ ሲደረግ አብሮ ስዩመ-መንግስት አይነት ይዘት ያለው የሚመስል የሀይማኖት መሪዎች ለውጥ ተደርጎ ነበር፡፡በአርግጥ በተቃራኒው ደግሞ በጥንቱም አስተዳደር ዘመን ስዩመ እግዚአብሄር(በእግዚአብሄር ፈቃድ የተሾመ) ተብለው በሀይማኖት መሪዎች የሚባረኩትን ነገስታት ታሪክ እናገኛለን፡፡
  ከዚህ የምንረዳው ነገር እንደየወቅቱ ሁኔታ አንዱ በአንዱ ላይ የተወሰነ ሀይልና ተፅእኖ ነበረው ማለት ነው፡፡በጥንት ዘመን በእየሱስ ክርስቶስ ዘመንም ስንመጣ ደግሞ እንደዚሁ ሀይማኖትና ፖለቲካ የተወሰነ ትስስር ነበራቸው፡፡ለምሳሌ የአይሁድ መምህራን እየሱስ ክርስቶስን ለቄሳር መንግስት ግብር ስለመክፈል ተገቢነት የሚመለከት ፈታኝ ጥያቄ ጥይቀውት ነበር፡፡ነገር ግን ለዚህ ፈታኝ ጥያቄ እየሱስ ክርሰቶስ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሄርን ለእግዚአብሄር ስጡ በማለት እጅግ የሚገርም አስተዋይነት የታየበት መልስ ነበር የሰጠው፡፡በእርግጥ እሱ በወቅቱ ይህንን ቢልም በኋላ ላይ ግን የቄሳር የበታች ገዢ ለነበረው ለጲላጦስ ተቃራኒውን ለቄሳር ግብር አትክፈሉ ይላል ብለው በሀሰት ወንጅለውት ነበር እንጂ፡፡ከዚህ የምንረዳው ጥንቱንም ፖለቲካና ሀይማኖት ተለያይተው አያውቁም ነበር ማለት ነው፡፡
  ትልቁ ቁም ነገር ግን አንዱ አግባብነት በሌለው የተሳሳተ አካሄድ ሌላኛውን ልምራ ወይንም ልዳኝ እንዳይል ከመጠንቀቁ ላይ ነው፡፡አንድ የሀይማኖት መሪ እንደ ግለሰብ እንደማንኛውም ሌላ የሀገሪቱ ዜጋ የአንድን ሀገር ህግና ስርዓት የማክበር ግዴታ አለበት፡እየሱስ ክርስቶስ ለቄሳር ግብር ስለመክፈል ሲጠየቅ የቁሳርን ለቄሳር በማለት የተለመደውን ግብር ክፈሉ ማለቱ እንዱ ሌላውን ምን ያህል አክብሮ መኖር እንዳለበት የሚያስረዳ ነው፡፡
  ይቀጥላል !!!

  ReplyDelete
 21. It is me Part-2
  እንደዚሁም በአንድ ሀገር ውስጥ ያለ አንድ የፖለቲካ ስርዓት አንድ ዜጋ ወይንም ግለሰብ ትክክለኛና አግባብነት ያለውንና በብዙሀኑ ተቀባይነት የለውን የዚያን ሀገር ህግና ስርዓትን እስካከበረ ድረስ የፈለገውን ሀይማኖት የመከተል መብቱን ሊያከብርለትና ጥበቃ ሊያደርግለት ይገባል፡፡ምክንያቱም ማንም የውጪ ሀይል የአንድን ግለሰብ የውስጥ እምነት ወይንም ሀይማኖት በመግባባትና በፈቃደኝነት ካልሆነ በስተቀር በሀይል ሊቀርፅና ሊቀይር ፈፅሞ አይቻለውምና ማለት ነው፡፡እንደኔ አመለካከትና አስተሳሰብ ግን አንድ የተወሰነ ሀይማኖትም ይሁን አንድ የተወሰነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ሰብአዊነት(Humanity) ለሚባለው የመጨረሻው እጅግ ትልቅ የጋራ ወሳኝ ቁምነገር ወይንም እሴት(Value) ምን ያህል ፍቅርና ክብር አላቸው በሚለው ሊመዘኑ ይገባል፡፡ሀይማኖትና ፖለቲካ ሁለቱም ለዚህ ሰብአዊነት(Humanity) ለሚባለው እጅግ ትልቅ የጋራ ወሳኝ ቁምነገር ወይንም እሴት(Value) ተገቢውና ትክክለኛ ፍቅርና ክብር ከሌላቸው ቢገናኙም ባይገናኙም ለእኔ ብዙም ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም፡፡ነገር ግን ሀይማኖትና ፖለቲካ ሁለቱም ለዚህ ሰብአዊነት(Humanity) ለሚባለው እጅግ ትልቅ የጋራ ወሳኝ ቁምነገር ወይንም እሴት(Value) ተገቢውና ትክክለኛ ፍቅርና ክብር እስካላቸው ድረስ መቼም ቢሆን መገናኘታቸው አይቀርም፡፡እርስ በእርስ በመተማመንና በመከባባር ላይ እስከተመሰረተ ድረስ ይህ መገናኘታቸው ደግሞ የሚያስደስት ጤናማና ተገቢ የሆነ የሚደገፍ ተግባር እንጂ ያን ያህል የሚያሳፍር ወይንም የሚያሸማቅቅ ሊሆን አይገባውም፡፡
  እንደኔ አስተሳሳብ ሀይማኖት ማለት እኮ በአንድ የተወሰነ ነገር ላይ የሚኖረን የማያወላውል ጠንካራ እምነት ማለት ነው፡፡ለምሳሌ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የአቶ መለስ ወይንም የአንድ የኢህአዲግ አባል ጠንካራና የማያወላውል አስተሳሰብ ወይንም አመለካከት ከሆነ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የእነዚህ ሰዎች ሀይማኖት ነው ለማለት እንችላለን፡፡በእግር ኳሱ አለም አርሰናልና ማንቸስተር ወይንም ሌሎች ተቃራኒ ቡድኖች ሲጋጠሙ ለምን ተሸነፍኩ ብሎ እራሱን እስከማጥፋት ወይንም እስከመጋደል ከተደረሰ ለዚያ ግለሰብ ወይንም ህብረተሰብ እግር ኳስ ሀይማኖት ነው ማለት ነው፡፡በሌላው አቅጣጫ ደግሞ ስናይ በአንድ የሀይማኖት ተቋም ውስጥ የዚያ ሀይማኖት ተከታዮች ወይንም መሪዎች ለስልጣን ወይንም ለጥቅም እርስ በእርሳቸው ከተሻኮቱ በዚያ የሀይማኖት ተቋም ፖለቲካ ወይንም ፖለቲካዊ ሽኩቻ አለ ማለት ነው፡፡የመላእክት አለቃ የነበረው ሳጥናኤል እውነተኛው የሁሉ ፈጣሪና ገዢ እግዚአብሄር ለጊዜው ስለተሰወረ አጋጣሚውን ጠብቆ መላእክትን እኔ ፈጣሪያችሁ ነኝ ብሎ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሞክሮ ስላልተሳካለት ከመላእክት አለቃነት አሁን በዳለበት የእርግማን ሁኔታ ውስጥ መውደቁ በራሱ ፖለቲካ አይደለም እንዴ፡፡ቁምነገሩ ፖለቲካ ወይንም ሀይማኖት በሚለው ቃል ሽፋን ውስጥ ወይንም በስተጀርባ ከህይወትና ከሰብአዊነት አንፃር ያለው ትልቅ ምክንያታዊ እውነታ ምንድነው የሚለው ነው፡፡ከዚህ አንፃር ካልሆነ በስተቀር በተለምዶው ባለው ተግባቦት ባላ ያለ ፖለቲከኛነት ወይንም ሀይማኖተኛነት በራሱ የመጨረሻው የእውነተኛነት መመዘኛ አይደለም፡፡
  ፖለቲከኛነት ሀይማተኛነትን ወይንም በፈጣሪ ማመንን አይከለክልም፡፡እንደዚሁም ሀይማኖተኛነት ፖለቲከኛነት አይከለክልም፡፡ፖለቲካ ወይንም ፖለቲከኛነት ማለት የግድ ፓርላማ ከመግባት ወይንም ፓርቲ ከማቋቋም ወይንም ለምርጫ ከመወዳደር ወይንም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ከመሆን ጋር ብቻ ሊያያዝ አይገባውም፡፡ሰብዓዊነትና ህይወት እስካለ ድረስ ፖለቲካም ሆነ ሀይማኖት በዚያ ሁለቱም አሉ፡፡ነገር ግን ሁሉም ከተፈጥሮ ህግ ከሰው ሰራሽ ህግና ከፍቅር ውጪ ሊሆኑ አይችሉምም አይገባምም፡፡እምነት ወይንም ሀይማኖት ብለን የምንጠራው ሰማያዊው አለም የራሱ መለኮታዊ ስርዓትና ህግ አለው፡፡የመጨሻው የፍርድ ቀንስ በራሱ ፖለቲካዊ አይደለምን፡፡
  ስለዚህ ሀይማኖትም በሌላ በኩል ፖለቲካ ነው ፖለቲካም በሌላ በኩል ሀይማኖት ነው፡፡ቁምነገሩ ግን ሁለቱንም በስርዓትና በህግ በየትክክለኛው አካሄዳቸውና መስመራቸው በተገቢውና በትክክለኛው መንገድ አስማምቶና አዛምዶ የማስኬዱ ጉዳይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 22. arife asab nehu yansakew

  ReplyDelete
 23. Dani ijig betam asfelagi yehone guday new yanesahew. Yihenin yemisema mengist & yehaymanot abbatoch alun gin??????????????????????????

  ReplyDelete
 24. ዳኒ፣
  YIHEN ASTEYAYET BETAM SILEWODEDHUT DEGME LIKEWALEHU. "ዛሬ ከመድረክህ መውረድ እስኪያቅተኝ በመልካም መጣጥፍ ታስሬ መዋሌ ነው። ለማነኛውም መላ ምትህ እጅግ የምደግፈው ነው። አየህ ሀገራችን በአጀማመር እንጂ በአጨራረሱ ደካማ ናት፤ ከሩጫው በስተቀር። በቅርብ ጊዜያት ወገኖቻችን «የሚመስሉት» እምነት ምንጩ በአብዛኛው ከድህነት ማምለጫ መሆኑን ልብ ይሏል (ኩርፊያን ሳንረሳ)። ይህ ለውጭ ድርጅቶች ትልቅና መልካም አጋጣሚ ነው- ብዙዎቹ ወደ ደሃ ሀገራት እምነት ተቋማት የሚልኩት ገንዘብ የሚቆረጠው በአባሎቻቸው ቁጥር ብዛት ነው።

  ለዚህ ነው የእምነት ተቋማት እንደ አሸን እዬፈሉ ከሞራልና ሥነምግባር ውጭ አልባሌ ሥራዎችን ሲሰሩ የሚታዩት። ሀገራችን በታምር ካልሆነ በስተቀር በውሃ ሊጠፋ የማይችል ረመጥ እያዳፈነች እንደሆነች ልንገነዘብ ይገባል። በርካታ አዳዲስ እምነቶች ከኢትዮጵያዊነት ስሜት በማሸፈት ለማናውቀው ሀገር ባህል፣ ልምድ ተገዥ እንድንሆን ሌት ተቀን እየተጉ ሲሆን እኛ ግን ዳር ቆመን ዝም ብለናል። የእምነት ነጻነት ማለት የሀገር ክህደት ማለት አይደለም! ዛሬ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ለመጥራት የሚጸየፉ ሽፍቶች ተፈልፍለዋል- አንዱና ዋነኛው ምንጩ ደግሞ ሥርዓትና መቋጫ የጠፋለት የእምነት ተቋማት እንደ አሸን መፍላት መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።

  በዚህ ላይ የሚመለከተን ወገኖች ብናስብበት መልካም ነው"

  ReplyDelete
 25. Biniam
  I understand the need to create a policy to solve social, political, and economical problems of Ethiopia. However, this can't be done when the so-called GOVERNMENT doesn't represent the people. A government is the political direction and control exercised over the actions of the members, citizens, or inhabitants of communities, societies, and states. HOW CAN ETHIOPIA CREATE SUCH POLICY-THAT IS EVEN IF WE DID-WHEN THE PEOPLE HAS LOST HOPE IN THE GOVERNMENT. There is no doubt that the government should have the power to regulate and solve religion issues, but this can't happen with a totalitarian MelesZenawism so-called government. When the Government truly represent the people and works on behalf of the people, then I-just like many Ethiopians would support having a law/policy that will solve the social, political, and economical issues. And, government can't solve every issue that Ethiopia encounters, but at least, it would solve most of them... :)

  ReplyDelete